✍«የምኒሊክ ጎዳና በእንግሊዝ»
💚💛❤️
✦የእምየ ምኒሊክ መንገድ የሚገኝው በእንግሊዝ ዋና ከተማ ለንደን ውስጥ ሲሆን ከለንደን 5.7 ማይል በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ ገባ ብሎ እንዲሁም ከቅዱስ አልባን ካቴድራል 14.72 ማይሎች ራቅ ብሎ ይገኛል። ምኒልክ መንገድ ከዌስትበር ጎዳና ተነስቶ እስከ ሚኒስተር ሮድ ይደርሳል። እንግሊዛዊዊ ተመራማሪ ፓውል ኮተን እንደ አውሮፖውያን አቆጣጥር በ1900 በእምየ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት ጊዜ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ28 በላይ የአፍሪካ ሀገራትን የጎበኝ ሲሆን ኢትዮጵያ እያለም አፂ ምኒሊክን አግኝቷቸው ነበር።
✦ፓውል ኮተን ሲጎበኝ ያስደሰቱትን ሁነቶች በእንግሊዝ መንገዶች እንዲሰየሙለት አድርጓል ። በአፍሪካ የሚገኙ ቦታዎች በእንግሊዝ መንገዶች ላይ ሊሰየሙ ችለዋል ከነዚህም መካከል:-Gondar Gardens (ጎንደር ) በ1892, Skardu Road (1897), Rondu Road (1900), Somali Road (1904) and Menelik Road (ምኒሊክ ሮድ) 1904 ....ተብለው ተሰይመው ይገኛሉ...ጎንደር ጋርደን እና ምኒሊክ መንገድ የሚሉት ስያሜዎች ከቅድስት ኢትዮጵያ የወሰዶቸው ስያሜዎች ናቸው። በጣም ሚገርመው ሁሉችም የቦታ ስም ሲሆኑ የምኒሊክ መንገድ ግን በእሩህ ሩሁ ንጉስ እምየ ምኒሊክ ስም መሰየሙ ለየት ያደርገዋል ።
✦ እስቲ አሁን በምኒልክ አደባባይ እንጂ በፑሽኪን አደባባይ ማን ይከራከራል ? በበላይ ዘለቀ መንገድ እንጂ በቼርችል ጎዳና ማን ይከራከራል ? ይሔው እኛ ፒሽኪን ቸርችል እያልን አደባባዮቻችንን ሁሉ በነሱ ሰይመን ለእምየ ምኒሊክ ሚሆን ቦታ አጣን.....እኛ የናቅነውን ይሄው ፈረንጅ አንስቶ ከፍ ከፍ አደረገው አክብሮ መንገድ ሰየመለት ደግሞ በዚህም እኮ ሚናደዱ አይጠፋም......!
✦ ለአንዲት ሀገራቸው ብለው የሞቱ ጀግኖቻችንን ሀገራዊ ራዕይ በቀበሌና በጎጥ ልንገድበው እንፈልጋለን። የአድዋን ድል ከምናከብር ይልቅ የጥቁር አሜሪካውያንን የነፃነት ቀን የምናከብር፣ እነ እምዬ ምኒሊክን እቴጌ ጣይቱ የልደት በዓላቸውን ከምንዘክር ይልቅ የማርቲን ሉተር ኪንግን መታሰቢያ ለማክበር የምንመኝ ራሳችንን በወረዳ ጎጥ ከፍለን ከዘራችን ውጭ ማሰብ የማንችል ከንቱዎች ሆነናል።አዎ አሁንም ጊዜው አረፈደም ፊታችንን ወደ ምስራቅ እንመልከት እጆቻችንን ለጸሎት እናንሳ ተሰጦም እንቀበል!......ንጉሴ መልካም ልደት ! [የልደት ቀናቸውን ምክንያት በማድረግ በድጋሚ የተለጠፈ]
🕹ለተጨማሪ መረጃ ቦታውን በ Google Gps መመልከት ይቻላል "Menelik Road in Londone"
✍ኢትኤል ነኝ
ጣና ዳር : ባሕር ዳር🌴
.
《....#ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች!....》
♡┈••✦ #ሼር_share_ሼር ✦••┈ ♡
💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️
⤵️〰⤵️〰⤵️

👍3❤1
✍«ስውሩ ድንጋይ»
« ኡይ - ኤውታ»
💚💛❤️
✦ ኡይ - ኤውታ የተሰኜው የከበረ ማዕድን ስውርና የማይታይ ድንጋይ ነው ። ነገር ግን ወፍ በበላዮ ጎጆ ሰርታ እንቁላል ትጥልበታለች በዚህን ጊዜ ወፍዋ ስትበር ይታያል።ስታርፍበት ደግሞ መልሶ ይሰወራል።
✦ ይህ ማዕድን አብዛኛውን ጊዜ የሚገኝበት ስፍራ ከዋሻና ከአለታማ ድንጋይ ላይ እንደ ሙጫ ተለጥፉ ይገኛል።መልኩም የጠራ ኩል ውሃ ይመስላል።ከአለቱ ላይ ቀርፋውን ስናነሳ ተጠንቅቀን መሆን አለበት አንዴ ከእጃችን ካመለጠን አይታየንምና ።ይህን የከበረ ማዕድን እንደ አክሊል ከወርቅ ጋር አሰርተን በአራቱም አቅጣጫ ለብጠን ከራሳችን ላይ ብናደርገው የተሰውረን ነገር በዓይነ ልቦና ለመመልከት ያስችላል።
✦ ሥጋዊ ዐይን ያላየውን እንደ ውኃ ሙላት ፣ ንፋስን ፣ በሰውነት ላይ ያለን ደዌ ፣ የማይታዮ ህዋሳትን ፣ ጥቃቅን ፍጥረታትን (micro organism) ጥርት አድርጎ መመልከት ያስችላል ነገር ግን ይህን አክሊል ሁልጊዜ ማድረግ አይመከርም ምክንያቱ እኛን ጨምሮ ሊሰውረን ስለሚችል።
.
✍ኢትኤል ነኝ
ጣና ዳር :ባሕር ዳር 🌴
📜ምንጭ:- ፩) 'ጥበበ ዕንቆ አእባን ከዜና' ፧ አበውና ከኁልቆ አእባን ፡ በመሪራስ አማን በላይ
《.... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !....》
📌ማሳሰቢያ:- [ከዚህ በታች በምስሉ ላይ የምታዮት ማዕድን ከላይ የገለፅሁት(ኡይ - ኤውታ) እንዳልሆነ ለማሳወቅ እወዳለሁ!]
♡┈••✦ #share_ሼር_Shere ✦••┈♡

👍2
✍በየኔታ ማዕበል ፈጠነ
💚💛❤️
ይህ ትውልድ የዕለቱንም ሆነ የዓመቱን ክስተት የሚመረምርበት ጥበብ አልባ ስለሆነ አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር ፍሥሓ ይተናነቀዋል። መጪው ዘመን ምን ምን በረከት ምን መርገም እንዳለው ግን መመርመር ሞቱ ነው። ለማንኛውም "መጪው ዘመን ከአለፈው ቢከፋ እንጂ አይሻልም። ዛሬ በዓለም ያለው ወረርሽ ቢያክትምም ቅሉ ሁለት ፈተናዎች ይኖራሉ። እነሱም ጦርነትና ረሐብ ናቸው። በማቴዎስ ዘመን ግን ከረሐቡ ይልቅ ጦርነት ያስፈራል ይላሉ ዓመታትን በሠንጠረዥ የለኳት ጠቢባን። ያንን እንደጉም ይገፍልን ዘንድ እግዚአብሔርን በጸሎት ቀድመን እንለምነው። የዓመት በዓሉ ሽርሽር ቀስ በቀስ ይደርሳል። የሆነው ሆኖ እንኳን ለአዲስ ዓመት አደረሳችሁ ብያለሁ። የመጣው ቢመጣ ነገም የእኔው ነው ብሎ በሚያምን ሰው ልብ ውስጥ ተስፋ አትሞትም። በማትሞት ተስፋ ተሰውሮ አዲስ ዓመትን የሚቀበል እሱ ደግሞ ብፁዕ ነው።

✍መልካም ዜና ፥ ለሁሉም የሚድያ አካላት
💚💛❤️
📌ጉዳዮ:- የእንቦጭ አረም ማጥፊያ መድኃኒት በምናስተዋውቅበት ፕሮግራም የሚድያ ሽፋን እንድትሰጡን መጠየቅን ይመለከታል።
ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደ ሞከርነው የእንቦጭ አረም በሀገራችን ትልቁን የጣና ሐይቅ ጨምሮ በርካታ ሀይቆቻችንን በመውረር በሀይቁ ላይ የከፋ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ይታወቃል።የእንቦጭ አረም በተለያዮ ሀይቆች ላይ እየተንሰራፋ በመሆኑ ከተሰማ ጀምሮ አረሙን ለማጥፋት የተለያዮ ሙከራዎች ቢደረጉም ውጤታማነታቸው በሚፈለገው ልክ መሆን አልቻለም ።
አረሙ ኢትዮጵያ ያሏትን የውሃ ሀብቶች እያጠፋ መሆኑ ያሳሰበው የኢትዮጵያ ሊቃውንትና ምሁራን ማህበር አረሙን ለማጥፋት የሚያስችል ሀገራዊ ፕሮጀክት ቀርፆ ታዋቂ ባለሙያዎችን በማሳተፍ የምርምር ስራዎችን ሲያካሂድ ቆይቶ አረሙን ለማጥፋት የሚያስችል መድኃኒት ለማግኝት በቅቷል ።
የማህበሩ መስራችና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት እና የባህል መድኃኒቶች ላይ በመመራመር ስኬታማ ግኝቶችን በማበርከት የሚታወቁት መርጌታ በላይ አዳሙ ማህበሩ በቀረፀው የእንቦጭ አረም ግኝት ፕሮጀክት ሙያዊ አቅማቸውን አሟጠው አረሙን ለማጥፋት የሚያስችል መድኃኒት አግኝተዋል።
መርጌታ በላይ አዳሙ ያገኙት መድኃኒት በባሕር ዳር ዮኒቨርስቲ ፣ በአማራ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዮት እውቅና የተሰጠው ሲሆን ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት የባለቤትነት የምስክር ወረቀት ተሰጧቸዋል።የኢትዮጵያ ሊቃውንትና ምሁራን ማህበርም መርጌታ በላይ አዳሙ ያገኙትን የእንቦጭ አረም ማጥፊያ መድኃኒት ለህዝብ በይፋ ለማሳወቅ ለማክሰኞ መስከረም 12/1/2013 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል ።
በመሆኑም ጋዜጣዊ መግለጫው በሚሰጥበት ኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል ከጥኋቱ 2:30 ባለሙያ መድበው የሚድያ ሽፋን እንዲሰጡን በአክብሮት እንጠይቃለን።
🕹አዲስ አበባ : ኢትዮጵያ
《..#ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !..》
♡┈••✦ ሼር✦••┈♡

« ቻይና ልትጸድቅበት አይደለም! »
✍በማዕበል ፈጠነ
💚💛❤️
✦ከዐራት ዓመት በኋላ የቻይና ደራሲያን በአማርኛ ቋንቋ ረጅም ልበ ወልድ: ወግና የጉዞ ማስታዎሻ ምናምን ጽፈው ቋንቋውን ይራቀቁበታል። ከዚህ ቀጥሎ ጀርመኖች በግእዝ ቋንቋ መወድስ ይዘርፋሉ። የግእዝ ክሕሎታቸው እየዳበረ ሲሄድ በብራናው የተከተቡ ምሥጢራትን መመርመር ይጀምራሉ። ከዚያስ? በእኔ ግምት "ኁልቆ አእጋሪሃ ለፀሐይ እስራ ወክልኤቱ ምእት" ከሚለው ውስብስብ የፀሐይ አውታር ውስጥ ዘው ብለው ጥልቅ ይላሉ።
✦ ይህን በአኀዝ የተጠቀለለ ፍልስፍና ዐርባ ዓመትም ቢሆን ዘግተው ማፍታታት ይጀምራሉ። ሲደርሱበት ዛሬ በነዳጅ የሚሠሩ የዓለም ቁሳቁሶችን ከሀ እስከ ፈ በፀሐይ ብርሃን ብቻ እንዲሠሩ ያደርጓቸዋል። ያም ማለት በፀሐይ ብርሃን ብቻ የሚበር አይሮፕላን ያመርታሉ። እየቆዩ በአየር ያሉ ደቃይቅ ብርሃናትን ብቻ እየለኩ ከቀዝቃዛ አየር ጋር አስማምተው ፈጣን ፈጣን በሰማይ በራሪ መርከቦችን ያመርታሉ።
✦ ክንፋቸው ከነፋስ አውታር ፍጥነታቸው ከብርሃንና ከነፋስ ሲዳቀል መንኮራኩራቸው ነፋስ መሥመራቸው የፀሐይ አውታር ይሆናል። እኒህ የፀሐይ እግሮች(አውታር) ቀላል ቀላል ነገሮችን መሸከም የሚችሉ ሲሆኑ በአውታራቸው ልክ ቅለትና ክብደት ያለው ቁስ ይሸከማሉ። ያንንም እንደ ካስማ ወጥረው በአውታራቸው ይሸክሙታል።
✦ ካስማ ድንኳኖኝችን ወጥሮ እንዲሸከም አውታሩም በልኩ የተሠሩ ማናቸውንም ቁሳቁስ ይሸከማቸዋል። ይህ ሁሉ የሚመጣው ግን ቋንቋ ከማወቅ ነው። ቻይና አማርኛ ቋንቋን መማር ማስተማር መጀመሯ ልትጸድበት ሳይሆን በኢትዮጵያ ሊቃውንት የተከተቡ ስውራንን ወደ ሥጋዊ ዓለም ለመሳብ ነው። ግን ግእዝ ቋንቋ ማስተማር ብትጀምር ይበልጣት ነበር።
.
《... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !..》
♡┈••✦ #ሼር ✦••┈♡

« የምስራች!»
✍የግዕዝ ትንሳኤ
💚💛❤️
✦በትግራይ ክልል ከ2 ሽህ በላይ ለሚሆኑ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የግዕዝ ቋንቋን በመደበኛ ትምህርት መርሃ ግብር ከዘንድሮው አመት ጀምሮ ለመስጠት እንደ ተዘጋጀ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አብስሯል! ትግራይ አሐዱ ብሎ ስለ ጀመረው ከልብ እያመሰገነ ነገር ግን በመላው ኢትዮጵያ ስርዓተ ትምህርቱ ውስጥ ሊካተት ይገባል።
✍ግዕዝ
■ሔኖክ ስነ ህዋ የተመራመረበት
■ተዋናይ በቅኔ ሰረገላ የመጠቀበት
■ሊቁ ክፍለ ዮሐንስ የተቀኝበት
■በምስጢር የተሞሉ የብራና መፃሕፍት የተከተቡበት.....