ኢትኤል
2.28K subscribers
97 photos
11 files
8 links
ስለ ጥንታዊው የኢትኤል ስልጣኔ እናወራለን! እንዘምራለን!
Download Telegram
እጅግ አስደናቂ የጥንት ኢትዮጵያያን ጥበብ

💚💛❤️

🕹የጥንት ኢትዮጵያያ x-ray ህክምና

💡በጨለማ የሚያበሩ ኪነ - ህንፃ ግንባታ

🦆 ስለ ምታበራዋ ሙሴ ወፍ

💎ስለ ብርቁ የከበረ መዓድን መድኃኒትነት


✦የጥንት ኢትዮጵያያን አምፖል(ዲም ላይት) መብራት ከመሰራቱ አስቀድሞ አብያተ ክርስቲያናን እንዲሁም ቤተ መንግስት ሲገነቡ ብርቁ ወይም ብርቅርቅ የሚባል የብርሀን ሀይል ማመንጨት ድንጋይ ይጠቀሙ ነበር።ይህ የከበረ መዓድን ሌሊት አአንዳንድ ግዜ የሚያበራ ደግሞም የሚጠፋ ድንጋይ ነው።ከዋሻ ውስጥ ወይም ከባሐር ዳር ላይ ይገኛል።እሱ በአለበት ዋሻ ውስጥ እንደ እሳት ላንቃ የመሰለ ብርሀን ይታያል።መልኩም በመዓልት ቢጫ አረንጓዴ ነው።ተወቅሮ ኪነ - ህንፃ ከተሰራበት ደግሞ ሌሊት ላይ ህንፃው ያበራል።



✦ መብረቅ ብዙ ጊዜ ይመታዋል ፣ ይሰነጥቀዋል ፣ ጭራ የመሰለ ይታይበታል።ብርቅ የምትባል አውሬ ተጠግታ ልጅ ትወልድበታለች።ማነኛውም አውሬ መጥቶ ልጅዋን አይበላውም : ልጁም እስኪያድግ ከድንጋዮ ስር አይጠፋም።አንዳንድ ጊዜም ውስጡ የተከፈተ ይገኛል።አንድ ሰው በውስጡ ገብቶ ቢተኛበት መብራቱ ሲበራ ማነኛውም የውስጥ የሰውነት ክፍሎችን(የሆድ እቃ) በሙሉ ማየት ያስችላል።ልክ በመስታውት ፊት ቁመን ከራስ ፀጉራችን እስከ እግር ጥፍራችን እንደምናየው ሁሉን አጥርቶ ያሳያል።ከደዌ ከህመምም ይፈውሳል።አራዊትም ሲታመሙ ከስሩ ሂደው ይተኛሉ ፣ ይድናሉ።በአሁን ጊዜ X- ray ብለን የምንጠቀመው ቴክኖሎጅ የጥንት አባቶቻችን በዚህ መንገድ ይገለገሉበት ነበር።


✦ እንደ ሰጎን ቁመታም የሆነች ሙሴ (thunderbird) የምትባል ወፍ አንዳንድ ጊዜ እንቁላል ትጥልበታለች።ድንጋዮን እየወቀረች በእንቁላሉ ላይ ትረጭበታለች : የታቀፈችበት እግሩዋ ፍህም ይመስላል: ከእርሱ ስር የተፈለፈለ ጫጩት ሆዱ እግሩ ያበራል።"በሊሃልም በናትሲ ሱሲ ተቀናሂም ሮሜማላ ቦሃቢ ባህፍዊ በሐተዊ መብራቂል መብረቅ ዝውእቱ ማህረጽየ ወመሐሯልየ " ብለህ እየፀለይህ የመታኸው እንደሆነ ይሰበራል፣ ይደቃልም።



✦ እኒህን እና ስለ ሌሎች የከበሩ መዓድናት የሚያብራሩ 'ኁልቆ አእባን፣መጽሐፈ አዕባን ፣ ምስጢረ አዕባን...' የተሰኙ የብራና መፃሕፍ በማህፀነ ለምለሟ የኢትዮጵያ ገዳማት ውስጥ ይገኛሉ።ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ እፁብ ድንቅ የከበሩ መዓድናት ባህሪያቸውን ፣ መገኛ ቦታቸውን ፣ እንዲሁም ጠቀሜታቸውን የሚያስረዳ መፃሕፍ መሪ ራስ አማን በላይ <ጥበበ ዕንቆ አእባን> በሚል ርዕስ 'ዜና አበውና ኁልቆ አእባን' ተርጉመውታል።ከውጭ ተመራማሪዎች መካከል እንግሊዛዊው ቶማስ ኬን 'መጽሐፈ አዕባን' አጥንቶታል።
.
ኢትኤል ነኝ
ጣና ዳር :ባሕር ዳር


📚ምንጭ:- ፩) 'ጥበበ ዕንቆ አእባን ከዜና' ፧ አበውና ከኁልቆ አእባን ፡ በመሪራስ አማን በላይ
፪) ነቅዐ መጻሕፍት : ቀሲስ ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ
፫) Thomas L.Kane (tr.) , "The Mastira a'ban - an Amharic Lapidary treatise"
.

《.... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !....》

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
👍21🎉1
የጠፋው ጥንታዊ መጻሕፍ ተገኝ!

💚💛❤️

✔️በደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ ከደብረ ሰላም ወርቻሜ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በ1962 ዓ.ም ጠፍቶ የነበረው የስንክሳር መጽሐፍ ተገኘ! በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ፀሐይ ጸዳሉ ነጋሽ እንዳሉት ከጠፋ ከ50 ዓመታት በኋላ የተገኘው ስንክሳር ከመጋቢት እስከ ነሐሴ የሚነበበውን የመንፈቅ ምንባብ የያዘ ነው፡፡


✔️ ስንክሳሩ ከ20 ኪሎ ግራም በላይ ክብደት ያለው፡፡ ስንክሳር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም የቅዱሳንን እና የጻድቃንን ታሪክ የያዘ ትልቅ ዓመቱን መገልገያ ነው፡፡ በኢትዮጵያ አሉ ከሚባሉ የሚዳሰሱ ቅርሶች መካከልም ትልቅ ሀገራዊ ገጽታ እና ሃይማኖታዊ ግልጋሎት ያለው ነው፡፡


✔️ቅርሱ ከጠፋ ጊዜ ጀምሮ የማፈላለግ ሥራ ሲከናወን ቆይቶ ሐምሌ 4 በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ደብረ-ገነት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በማዳበሪያ ተጠቅልሎ ጸሎት በሚያደርጉ እናቶች ተገኝቷል፡፡ ሕጋዊ ሂደቱን ተከትሎ ወደ ቦታው መመለሱንም ዋና ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

Via AMMA

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️
⤵️⤵️⤵️
"ደሜን ጠጡትና ስጋዬንም እንኩ
አጥንቴን ከስክሱት አያልፍም ከልኩ
ነገር ግን ሀገሬን ድንበሯን አትንኩ!"

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
👍1🥰1
« ባህር ተሻጋሪው »
« የጥንት ኢትዮጵያያን ኪነ ህንፃ»

💚💛❤️

✦ ታዋቂው የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሂረን ስለ ጥንት ኢትዮጵያንን ኪነ ህንፃ ሲገልፅ... "ኢትዮጵያያን ቅድመ አያቶች በከተሞች ይኖሩ የነበሩና ታላላቅ ድንቅ ቤተ መቅደሶችንና ህንፃዎችን የገነቡ ነበሩ።ህግና መንግስት የነበራቸው እውቀታቸውንና ስነ ጥበባቸውን ለጥንቱ ዓለም በሰፊው ያሰራጩ ህዝቦች ነበሩ።" ሲል በምርምር ያረጋግጣል።



✦ ሌላው Ancient history of Hindustan የተሰኝው መፃሕፍ ፀሀፊ ቶማስ ማውሪዎስ እንዲህ ሲል ምስክርነቱን ይሰጣል... "የጥንት ኢትዮጵያን ድንቅ የፈጠራ ችሎታ እጅግ ከፍተኛ ዝና አግኝቶ በነበረበት በዛ ዘመን ፤ኢትዮጵያያን በዓለም ታላላቅ ህንፃዎች ሰርተዋል፣ከምድር በታች ዋሻዎችን ቆፍረዋል ፣ መተላለፊያዎችን ሰርተዋል ፣ ግዙፍ ግድቦችን በመገደብ ሐይቆችን ፈጥረዋል ፣የውሃ ማስተላለፊያ መስመሮችን ዘርግተዋል ፣ድልድዮችን ገንብተዋል የባሌስና የቤሉስን ታላላቅ ማማዎችንና የግብፅ ፒራሚዶችን ገንብተዋል። "



✦ "የሳልሴትንና የኤሌፋንታይን ዋሻዎች ቆፍረዋል፣በሜካኒካል ኃይል አጠቃቅማቸውና ክህሎቶቻቸው ለማመን የሚያስቸግሩ ድንቅ ስራዎች አከናውነዋል ።በቤልቤክና በቴባይ ፈርሰው ከሚታዮ ቤተ መቅደሶች መካከል ከ፩ እስከ ፳ ሜትር ከፍታ ያላቸውን ውፍረታቸው ከ፫ እስከ ፮ ሜትር የሚደርስ ሀውልቶችን ቀርፀው እንዴት እንዳቆሟቸው ዛሬም ለማመን አዳጋች የሆነ ጉዳይ ነው።" አባቶቻችን ባህር ተሻግረው ስልጣኔን ዘርተዋል የምንለው በምክንያት ነው።


📚ማጣቀሻ መፃሕፍት
፩) Ancient history of Hindustan book :by Thomas Maurice
፪) Wonderful Ethiopians of the Ancient Cushite Empire book : by Drusilla Dunjee

.

《.... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !....》
♡┈••✦ ሼር✦••┈♡

📓መፃሕፉን ለማግኝት

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
👍21
Wonderful Ethiopians Ancient Cushite Empire.pdf
746.2 KB
ጥንታዊው የኢትዮጵያ ስልጣኔ!

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
1
«የምኒሊክ ጎዳና በእንግሊዝ»

💚💛❤️


✦የእምየ ምኒሊክ መንገድ የሚገኝው በእንግሊዝ ዋና ከተማ ለንደን ውስጥ ሲሆን ከለንደን 5.7 ማይል በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ ገባ ብሎ እንዲሁም ከቅዱስ አልባን ካቴድራል 14.72 ማይሎች ራቅ ብሎ ይገኛል። ምኒልክ መንገድ ከዌስትበር ጎዳና ተነስቶ እስከ ሚኒስተር ሮድ ይደርሳል። እንግሊዛዊዊ ተመራማሪ ፓውል ኮተን እንደ አውሮፖውያን አቆጣጥር በ1900 በእምየ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት ጊዜ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ28 በላይ የአፍሪካ ሀገራትን የጎበኝ ሲሆን ኢትዮጵያ እያለም አፂ ምኒሊክን አግኝቷቸው ነበር።



✦ፓውል ኮተን ሲጎበኝ ያስደሰቱትን ሁነቶች በእንግሊዝ መንገዶች እንዲሰየሙለት አድርጓል ። በአፍሪካ የሚገኙ ቦታዎች በእንግሊዝ መንገዶች ላይ ሊሰየሙ ችለዋል ከነዚህም መካከል:-Gondar Gardens (ጎንደር ) በ1892, Skardu Road (1897), Rondu Road (1900), Somali Road (1904) and Menelik Road (ምኒሊክ ሮድ) 1904 ....ተብለው ተሰይመው ይገኛሉ...ጎንደር ጋርደን እና ምኒሊክ መንገድ የሚሉት ስያሜዎች ከቅድስት ኢትዮጵያ የወሰዶቸው ስያሜዎች ናቸው። በጣም ሚገርመው ሁሉችም የቦታ ስም ሲሆኑ የምኒሊክ መንገድ ግን በእሩህ ሩሁ ንጉስ እምየ ምኒሊክ ስም መሰየሙ ለየት ያደርገዋል ።



✦ እስቲ አሁን በምኒልክ አደባባይ እንጂ በፑሽኪን አደባባይ ማን ይከራከራል ? በበላይ ዘለቀ መንገድ እንጂ በቼርችል ጎዳና ማን ይከራከራል ? ይሔው እኛ ፒሽኪን ቸርችል እያልን አደባባዮቻችንን ሁሉ በነሱ ሰይመን ለእምየ ምኒሊክ ሚሆን ቦታ አጣን.....እኛ የናቅነውን ይሄው ፈረንጅ አንስቶ ከፍ ከፍ አደረገው አክብሮ መንገድ ሰየመለት ደግሞ በዚህም እኮ ሚናደዱ አይጠፋም......!



✦ ለአንዲት ሀገራቸው ብለው የሞቱ ጀግኖቻችንን ሀገራዊ ራዕይ በቀበሌና በጎጥ ልንገድበው እንፈልጋለን። የአድዋን ድል ከምናከብር ይልቅ የጥቁር አሜሪካውያንን የነፃነት ቀን የምናከብር፣ እነ እምዬ ምኒሊክን እቴጌ ጣይቱ የልደት በዓላቸውን ከምንዘክር ይልቅ የማርቲን ሉተር ኪንግን መታሰቢያ ለማክበር የምንመኝ ራሳችንን በወረዳ ጎጥ ከፍለን ከዘራችን ውጭ ማሰብ የማንችል ከንቱዎች ሆነናል።አዎ አሁንም ጊዜው አረፈደም ፊታችንን ወደ ምስራቅ እንመልከት እጆቻችንን ለጸሎት እናንሳ ተሰጦም እንቀበል!......ንጉሴ መልካም ልደት ! [የልደት ቀናቸውን ምክንያት በማድረግ በድጋሚ የተለጠፈ]

🕹ለተጨማሪ መረጃ ቦታውን በ Google Gps መመልከት ይቻላል "Menelik Road in Londone"


ኢትኤል ነኝ
ጣና ዳር : ባሕር ዳር🌴
.

《....#ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች!....》
♡┈••✦ #ሼር_share_ሼር ✦••┈ ♡

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
👍31
«ስውሩ ድንጋይ»

« ኡይ - ኤውታ»

💚💛❤️

✦ ኡይ - ኤውታ የተሰኜው የከበረ ማዕድን ስውርና የማይታይ ድንጋይ ነው ። ነገር ግን ወፍ በበላዮ ጎጆ ሰርታ እንቁላል ትጥልበታለች በዚህን ጊዜ ወፍዋ ስትበር ይታያል።ስታርፍበት ደግሞ መልሶ ይሰወራል።


✦ ይህ ማዕድን አብዛኛውን ጊዜ የሚገኝበት ስፍራ ከዋሻና ከአለታማ ድንጋይ ላይ እንደ ሙጫ ተለጥፉ ይገኛል።መልኩም የጠራ ኩል ውሃ ይመስላል።ከአለቱ ላይ ቀርፋውን ስናነሳ ተጠንቅቀን መሆን አለበት አንዴ ከእጃችን ካመለጠን አይታየንምና ።ይህን የከበረ ማዕድን እንደ አክሊል ከወርቅ ጋር አሰርተን በአራቱም አቅጣጫ ለብጠን ከራሳችን ላይ ብናደርገው የተሰውረን ነገር በዓይነ ልቦና ለመመልከት ያስችላል።



✦ ሥጋዊ ዐይን ያላየውን እንደ ውኃ ሙላት ፣ ንፋስን ፣ በሰውነት ላይ ያለን ደዌ ፣ የማይታዮ ህዋሳትን ፣ ጥቃቅን ፍጥረታትን (micro organism) ጥርት አድርጎ መመልከት ያስችላል ነገር ግን ይህን አክሊል ሁልጊዜ ማድረግ አይመከርም ምክንያቱ እኛን ጨምሮ ሊሰውረን ስለሚችል።

.
ኢትኤል ነኝ
ጣና ዳር :ባሕር ዳር 🌴


📜ምንጭ:- ፩) 'ጥበበ ዕንቆ አእባን ከዜና' ፧ አበውና ከኁልቆ አእባን ፡ በመሪራስ አማን በላይ

《.... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !....》


📌ማሳሰቢያ:- [ከዚህ በታች በምስሉ ላይ የምታዮት ማዕድን ከላይ የገለፅሁት(ኡይ - ኤውታ) እንዳልሆነ ለማሳወቅ እወዳለሁ!]

♡┈••✦ #share_ሼር_Shere ✦••┈♡

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
👍2