ኢትኤል
2.28K subscribers
97 photos
11 files
8 links
ስለ ጥንታዊው የኢትኤል ስልጣኔ እናወራለን! እንዘምራለን!
Download Telegram
Channel created
Channel photo updated
💚💛❤️ምርጥ መፃሕፍ ነው !
👇👇👇👇👇👇
♡┈┈••✿ #ስውር_ቀለም ✿••┈┈┈♡
❀︵ #ስውር_ብራና_ጽሑፍ ︵❀
♡┈••✦ #share_ሼር_Shere ✦••┈♡
✦ በአገራችን ስውር ቀለም ወይም የምስጢር መጻፊያ የሚባል አለ ። በቀደሙት ጊዜ ሁለት ምስጢረኞች ኃሳባቸውን ሌላ ሰው ሳያውቀው የሚጠቀሙት
ዘዴ ሲሆን አጻጻፋም ጥበብን የተሞላ ነው። ተራውን ነገር በአንድ ገጽ በቀለም በመጻፍ በስተጀርባው ደግሞ የሎሚውን ውሃ በንጹሕ ዕቃ ላይ ጨምቀው
እንደ ቀለም በመጠቀም የራሳቸውን ልዩ ምስጢር ይጽፋበታል
:
✦ ምናልባት አንዱ በኃይል ተጋፍቶ ከተላኪው ሰው ጽሑፋን በመንጠቅ ቢያነበውም ተራ ነገር መስሎ ስለሚታየው መልሶ ይሰጠዋል ። የላከለት መምህር
ግን ምስጢሩን ስለሚያውቅ የጽሑፋን ብራና ጀርባ ጢስ ጋርዶ ሲያስመታው የተደበቀው ጽሑፍ ስለሚወጣ የመጣለትን ኃሳብ ያገኛል ።መልሱንም
በተመሳሳይ ዘዴ አዘጋጅቶ ይመልስለታል ።
:
✦ ሁኖም የምሥጢሩን ጽሑፍ ዘዴ ያጠና ሌላ ሦስተኛ ሰው ሥውርን ጽሑፍ የሚያነበው በተመሳሳይ ስልት ስለሆነ ቀለሙም በጢስ ከጎላ በኃላ ተመልሶ
ስለማይጠፋ ተቀባዮ ምስጢራቸው መባከኑን በቀላሉ ሊረዳው ይችላል። አባቶቻችን ምስጢራ እና ጥበባትን የያዙ ብራናዎችን ከጠላት ወራሪ ኃይል
ለመከላከል ይህን ዓይነት ዘዴ በሰፊው ይጠቀሙበት ነበር ። ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ሼር share ሳያረግ እንዳያልፍ !
.
«~~~ #ፔጁን(ኢትኤል) ከወደዱት ሌሎች አስደናቂ መረጃዎች እንዲደርሰዎ ሼር ላይክ ፣፣፣፣፣ እንዲሁም ጓደኛዎን invit በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ!
.
#ኢትዮጵያ በዳግም ትንሳኤ ትነሳለች !!!!
♡┈┈┈••✦share_ሼር_share✦••┈┈┈♡
👍21
♡┈••✿ #ዓለም_ክብ_ናት ✿••┈┈♡

#በጥንታዊ ኢትዮጵያን እይታ ❀

♡┈••✦ #share_ሼር_Shere ✦••┈♡

✦ መላው አውሮፖ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ "ዓለም ጠፍጣፋ ቅርፅ አላት" ብለው ያምኑ ነበር ።ቀደምት ኢትዮጵያን ግን ይህ ሀሳብ የተሳሳተ እንደ ነበር በተለያዮ ግኝታቸው አሳይተዋል።ለምሳሌ በ13 መ/ክ/ዘ እንደ ተፃፈ የሚነገረው እና በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም የሚገኝው መጽሐፈ ማስያስ "ምድር ጋንን ትመስላለች" ይላል።
:
✦ ይህ የሚያሳየን አሁን ሳይንሱ ዓለም ክብ(spherical) ቅርፅ አላት ለሚለው ግኝት ፈር ቀዳጅ ነው።ሌላው ማስረጃ የኢትዮጵያን ስዕላት አሳሳል ዘይቤ ደግሞ የቅድስት ሥላሴ ሥዕል ሲስሉ ሥላሴ ዓለማትን በእጃቸው እንደ ያዙ ለማመላከት ይጠቀሙበት የነበሩ ዓለምን ክብ(spherical) አድርገው ሥለው በስላሴ እጅ በማስያዝ ነው።
:
✦ ጥንታውያኑ ሊቃውንት ሰባቱ ሰማያትን እና ሌሉች ዓለማትን ሲስሉ እንኳን በሰባት ክበቦች እያደረጉ ነበር። የሚያመለክቱት።ምን ይህ ብቻ ነገሥታቱ ራሳቸውን የዓለም ገዥዎች አድርገው በሚቆጥሩበት ዘመን ከነገስታቱ ቀለበት ላይ ለገዥነታቸው ምልክት የምትቀመጠው #ሉል እንኳን ክብ ነበረች።
:
✦ እንዲሁም አበው ፊደላትን ሲቀምሩ <<ዓለም>> ሚለውን ቃል ሲፅፋ እንኳን<<አለም>>ሳይሆን የመጀመሪያዋ ፊደል ዐይኑ ዐ ዘር የሆነችውን"ዓ" ነው ሚጠቀሙት።ምክንያቱም "ዓለም" ብለው ሲጽፋ ምድር ክብ(spherical) መሆኑዋን እየነገሩን ነውና።
●~~~~ወደ ቴሌ ግራም እና ፊስ ቡክ ፔጃችን ይቀላቀሉ ።
.
«~~~ #ፔጁን (ኢትኤል) ከወደዱት ሌሎች አስደናቂ መረጃዎች እንዲደርሰዎ ሼር ፣፣፣፣፣ላይክ እንዲሁም ጓደኛዎን invit በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ!
.
《.. #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !!!! .》
♡┈┈┈••✦share_ሼር_share✦••┈┈┈♡
1
👍2
♡┈┈••✿ #በላይ_ዘለቀ ✿••┈┈┈♡
❀︵ #የደግነት_ጥግ ︵❀
♡┈••✦ #share_ሼር_Shere ✦••┈♡
✦ በላይ ዘለቀ ደጃዝማች ተብሎ ካዲስ አበባ ወደ ደብረ ማርቆስ እንደተመለሰ ከባለስልጣኖች ጋር ለመገናኘት ወደ "ጠቅላይ ግዛቱ " ጽህፈት ቤት ሄደ::ዘበኞቹም አጋፋሪውም ሲያዩት ጊዜ ሸሹ ::ከጽህፈት ቤቱ ወጥቶ ወደ ሚያርፍበት ቤት ሲገባ ወሬው ከተማውን ከመቼው እንዳደረሰው አይታወቅም ::
:
✦ ማርቆስ ያለ ሰው ሁሉ እንጀራውን ፣ወጡን ጠላውን ፣ጠጁን አረቄውን እየያዘ መጣ :: በላይ ዘለቀን ህዝቡ ሲወደው ያን ያህል ነበር ::ምግብና መጠጡ ከመብዛቱ የተነሳ ሰዎች ወደውጭ ተላኩና አላፊ አግዳሚውን "የራበኽ ስንቅ የለለኽ ና ብላ !በበላይ አምላክ ና ግባ "እያሉ ጋበዙት ::
:
✦ በበላይ ዘለቀ ሰራዊት ውስጥ መሪና ተከታይ አለቃና ጭፍራ ያለው በውጊያ ሰአት ነው እንጂ በምግብ ሰአት ሁሉም እኩል ነው :: ለሰራዊቱ የሚበቃ ምግብ ከሌለ ያለው ተቆራርሶ ለሁሉም እኩል ይደርሰዋል :: በላይ ዘለቀ መሶብ ሲቀርብለት "ሁሉም በልቷል " ይላል ::
:
✦ "አይ ዛሬ እጥረት አለ "ካሉት "እንግዲህ መልሱ ::እኔ አልበላም "ይልና ጦሙን ያድራል :: "አንድ ጊዜ ሁለት ቀን ጦም አድረው በላይ ዘለቀ ዛሬ ሶስት ድርብ (ሁለት ቁና ) ሽምብራ ላመጣልኝ ጠመንጃ እሰጠዋለሁ አለ:: አንድ ገበሬ ሽምብራውን አመጣ ጠመንጃውን ወሰደ ::
:
✦ በላይ ዘለቀ የገንዘብ ፍቅር የለበትም ::እንዲያውም ብር በእጁ አያድርም :: "ራስጌዬ አታርጉብኝ ...ይቀጥቀኛል "ይላል :: ያቃዠኛል ማለቱ ነው በጎጃምኛ። ንጉሱ ደብረማርቆስ የመጡ ጊዜ አስራ ሁለት ሺህ ብር ሰጥተውት ሄዱ።
:
✦ በላይ ዘለቀ ከማርቆስ ወደ ቢቸና ሲጓዝ አንዱ መጥቶ "ቤቴ ተቃጠለ "ገንዘብሲሰጠው ፤ ሌላው መጥቶ "ከብቴ ተዘረፈ " ሲል ገንዘብ ሲሰጠው እንዲህ ሲል ገና ቢቸና ሳይገባ አስራ ሁለት ሺ ብሩ አለቀ። "ጊዮርጊስ ያውቃል "ይላል በላይ ዘለቀ። በጊዮርጊስ በጣም ያምናል።
:
✦ ፍልሰታ ሲሆን ሁል ጊዜ ሱባኤ ይገባል። "እኔ የዘለቀ ልጅ !"ይላል ሲቆጣ። በላይ የወንዶች ቁና "ይላል ሲፎክር። ተመስገን ፈንታ የበላይ ዘለቀ የቅርብ ጓደኛው ነበር።
:
✦ አንድ ቀን ከጠላት በፊት ተመስገን ፈንታ በላይ ዘለቀን "ሸዋ ሄደን ለትልቅ ሰው እንደር። እንሾማለን ;እንሸለማለን "አለው። "እኔ ሰው ሆኜ ለሰው አላድርም "አለ በላይ ዘለቀ። "ባንተ ተኩስ ባንተ ወኔ፤ ባንዳፍታ ትሾማለኽ። "ጀግንነት ደጃችን ድረስ ይመጣ እንደሆነ ማን ያውቃል?" አለው በላይ ዘለቀ። አመታት አለፉ።
:
✦ከዛም አንድ ቀን ሞረድ እጀ ጠባብ አፈ ሾሌ ሱሪና ተመሳሳይ ኮት ጥንግ ድርብ ጥበብ ኩታ በቅሎ እንደተጫነች ጠመንጃ ከነሙሉ ዝናር ጥይት ...በላይ ዘለቀ ይህንን ሁሉ አዘጋጀና ተመስገን ፈንታን ጠርቶ፥ "ያ የጌታ አዳር ሄደን እንሸለማለን ያልከው ይኸውና "ብሎ ሸለመው።
:
✦ከዚህ በኋላ በአርበኝነት ዘመን ጓደኛሞቹ አልተለያዩም። በላይ ዘለቀ መጀመርያ "ራስ " ብሎ የሾመው ተመስገን ፈንታን ነበር። "እኔንስ ራስ አልከኝ። አንተ ማን ልትባል ነው?" አለው ተመስገን ፈንታ። "እኔንማ እናቴ አንድ ጊዜ በላይ ብላኛለች " አለ በላይ ዘለቀ ::
.
{ #ምንጭ፡- biography of Ethiopian patriot.}
.
«~~~ #ፔጁን (ኢትኤል) ከወደዱት ሌሎች አስደናቂ መረጃዎች እንዲደርሰዎ ሼር ፣፣፣፣፣ላይክ እንዲሁም ጓደኛዎን invit በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ!
.
《...... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !!!! ......》
⤵️⤵️⤵️
👍3
የታላቁ ሊቅ አባ ተስፋ ስላሴ ሞገስ " ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው የተዋህዶ አንበሳ እየሱስ ክርስቶስ ነው" የተሰኝውን የምስጢር መፃሕፍ እነሆ ጋበዝኋችሁ🙏
⤵️⤵️⤵️
ሰላም ውድ የኢትኤል ቤተሰቦች ፔጃችን ለሁሉም ተደራሽ ይሆን ዘንድ ከዚህ በታች የምትመለከቱትን ሊንክ ለወዳጆቻችሁ አጋሩ...⤵️⤵️⤵️