ኢትኤል
2.28K subscribers
97 photos
11 files
8 links
ስለ ጥንታዊው የኢትኤል ስልጣኔ እናወራለን! እንዘምራለን!
Download Telegram
😢1
በፎቶው ላይ የምትመለከቱት በአዲስ አበባ ከተማ በከፍተኛ ገንዘብ እየተገነባ ያለ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ነው ። ይገርማል ጣና የተፈጥሮ ሀይቃችንን አይናችን እያየ እያደረቅነ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ለመስራት እንሮጣለን!!! ቆየ እኔ ምለው ፈረንጆች ወደ ሀገራችን ሚመጡት ሰው ሰራሽ ሀይቅና ኩሬ ለመጎብኝት ነው እንዴ ? እንደ ዛ ቢሆንማ ኑሮ ፓሪስና ዱባይ ከእኛ በስንት እጅ በላቁ ነበር። አባይን ወዶ ስለ ጣና አለማሰብ ማለት ውሀን ወዶ ምንጭን እንደ መጥላት ይቆጠራል። አባይን ያለጣና ማሰብ አይቻልም!!!

🔀share_ሼር_share በማድረግ ድምፃችንን እናሰማ!

📌ትኩረት ለጣና
📌ጣናን እንታደግ

@ethale

.⤵️⤵️⤵️
ታላቁ አጼ ሰንደቅ አልማ

💚💛❤️

✔️ በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ ሰንደቅ አላማን የፈለሰፈ

✔️ለመጀመሪያ ጊዜ በቅሎን አዳቅሎ ያስገኝ

✔️የጀነቲክስ አባት

✔️በስሙ እጼያ/እስያ/ አሀጉር የሰየመ

✔️ 33 አንበሶችን የገደለ ላዕለ ሰብ(super man)

✔️የሰውና የአራዊት ንጉሥ

✔️ታላቅ ፈላስፋ
....

✦ዘመን ከተቆጠረ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አንድ አመት ዓለም ላይ ሱባ ሱባያ በሚባል ከተማ ላይ ግዬን በሚፈስበት ምድር የአምለክ አገልጋይ ካህን የነበረ የንጉሥች ንጉሥ ስመ መንግስቱ እንደ አባቱ መጠሪያ ስም ኢትዮጲስ የተባለ ኤልካኖ የሚባል ነበር።ከሰባቱም ወንዶች ታለቁ ንጉሥ ነገሥትና የኤል (የእግዝአብሔር) አገልጋይ እሴ ወይም አጼ ሰንደቅ አልማ ወለደ።


✦አጼ ከልጅነቱ ጀምሮ አስተዋይና ተመራማሪ ስለነበር ከእለታት አንድ ቀን ዱር ለዱር እየተዘዋወረ የወፍ ጎጆ አሰራሩን ከተመለከተ በኃላ የወፍ ጎጆ አስመስሎ ጠልፎ ቤቱን በዋሻና በዛፍ ላይ መስራት ጀመረ። እንደዚህ ያለ ከሰማይ ወፍና ከምድር አራዊት ጥበብን ሲማር የንብ ማር ቆርጦ ሲበላ ቆይቶ የማሩን ሰፈፍ አሰራር ሲያስተወል ለንቡ አውራ የተሠራውን የሰፈፉን ሁኔታ ወሰዶ ለአባቱ ያሳየው ነበር። አጼም ከምስጥ ተዋጊነትን፤ ከጉንዳን ፈጣንነትን ከእንስሳትና ከዱር አራዊትና ከሰማይ ወፍ ያለወን ሥረዓትና ጥበብን አየተማረ ከአራዊት ጋር አደገ።


✦አንዱን እፅዋት ወደ ሌላው እፅ የአንዱን አውሬ ዘር ወደ ሌላው እንዲዳቀል አድርጓል። ከነዚህም ውስጥ በቅሎ ከአህያና ከፈረስ እንድትወለድ #ለመጀመሪያ ጊዜ የአደረገ አጼ ነው።ብዙ ሺህ የሚሆኑተን እፅዋት አዳቅሏል።ስለቤት ምግብ፣ ስለወጥና ስለወይን ጭማቂ አንዱን ከአንዱ በማዋሐድ፣ በመቀመም ለወገኖቹ ጽፎ አስተምሯል።


✦የሰው ልጆች ከሌላው ፍጥረት የማድረግ የመስራትም እድል ስላላቸው ማንኛውንም ነገር አስተውለው ከአጠኑትና ከአወቁት ተመራምረው ከተረዱት የማይሆን ነገር እንደሌለ ጽፎአል። ብዙ ዘመን፣ ብዙ ዓመታት ከሌሎች ፍጥረት በይበልጥ እንደሚኖሩ ኅልቆ አእባን በሚባለው የድንጋይ ጥበብ መጸሐፍ ጽፎአል።


✦የሰው ልጅ ብዙ አመታትን ለመኖረ ከፈለገ ይላል ሥራቸው በማይነግል እፅዋቶችና ጥራት ካለው ድንጋይ ውስጥ የሚወጣን ውኃ በየጊዜው መጠጣት ያስፈልጋል ብሎ ተናግሯል። አጼም አቻ የሌለው ታላቅ ፈላስፍ ነበር።ለሰራዊቱ ሁሉ የጦርነት ስልትና ዘዴ ያስተምራቸውም ነበር።


✦አጼ ሰንደቅ አላማ ለልጅ ልጆቹ በየአስር አመቱ የንጉሥ ልጅ ሁሉ ሊነግሥ የፈለገ ከንጉሥ ጋር መግጠም አለበት ብሎ ከእንስሳት የተማረውን ህግ ስለመሰረተ በገዛ በአስረኛ ዘመኑ የሚገጥመው ስለጠፍ ከአንበሳ በረት ውስጥ ያሉትን አንበሶች ሁሉ ገጥሞና ጥሉ በቡጢ እየመታ 33 አንበሶችን ገደለ። አጼም የሰውና የአራዊት ንጉሥ እኔ ነኝ ብሎ ለልጁ ለታምሪያ የሳበን መንግሥት ሰጠው።የሚመስለው ጀግና ስለጠፍ ላዕለ ሰብ(super man) ተባለ።


✦ከፍብፅ እስከ ሞአብ ያሉትን ሃገሮች ወረረ። አማሌቅንና ፍልስጤምን አስገበረ። ስለዚህ ያስገበረውን ሃገር በስሙ እጼያ/እስያ/ አለው።ትርጓሜውም ታላቋ ሃገር ማለት ነው። እንደሱባውያን #እጼያ ሲሆን እንደ እብራውያን #እስያ ይባላል።


✦በዚህ ጊዜ በሼንና በምፅጳ በሚገኙ ሸለቆች ውስጥ ድንኳኑን አስተክሎ ሳለ የመልከጼዴቅና የኢትኤል አምላክ በራዕይ ተገለጸለት "አባቶችህ ያላዩትን ታያለህ፤ እድሜም በብዙ ትጠግባለህ፤ መንግሥትህም ታስረዝማለህ፤ እጅ መንሻ ጋዳ በዘርህ እና በቃል ኪዳኑ ቀን እንጅ ዛሬ አይሁን፤ ለማየት የወደድከውን ለማድረግ ተፈቅዶልሀል" አለውና በተራራዎች መካከል ሲያልፍ አየ። በዚያም አጼ/እሴ/ ነቢዩን ሳሙኤልን የአምላክ መላዕክ ነግሮት ነበርና ከአጼ ጋር ተገናኘና እጁን ሳመው። ሁለቱም እንደሚተዋወቁ ሰዎች ሆነው በአንድ ላይ አምላካቸውን አመሰገኑ።


✦በነገሠ በ14ኛው ዘመኑ ከኪትም እስከ ሙት ባህር ከትልቁ ባህር እስከ ሬሴን ያሉ ጎሣዎችና የጎሳዎች አለቃ ሁሉ በንጉሡ ጥሪ መሰረት ተሰበሰቡ ሥርዓቱም በግዬን መገናኛ ኢትዮጵ ኢትኤል በስሙ ምድሩን ኢትዮጵያ፤ ወንዙን ጵንኤል ብሎ ስም አውጥቶ የከበረ ድንጋይ በአስቀመጡበት ምድር ላይ ሌትና ቀን የተለያዩ የራስ ጌጦች፤ ስማቸው ጌራ የሚባሉ ልዩ ልዩ ክቡር በርኔጣዎች፤ የእጅ ቀለበቶች፤ ከእንቁዩጳና ከአልማዝ ድንጋይ ሺህ ጊዜ መቶ ሺህ የሚሆኑ የወርቅና የብር መክሊቶች ተዘጋጁ። ንኤል ማለት የአምላክ ፍንጣሪ፤ ግዩን ማለት ፈሳሽ ማለት ነው።


✦አጼ ሰንደቅ አልማ አንድ መቶ ሺህ ሰረገሎች በአሥር ሺህ ሰረገሎች በአሥር ሺህ አንድ መቶ አምሳ ፈረሰኞች በሰባት ሺህ ልዩ ልዩ ፈጣን ግመሎች በወርቅ እና በብር ጌጥ በተሸለሙ እግረኛ ሰራዊት ሁሉ ታጅቦ ወደ ግዮን ዳርቻ ወረደ።


✦በዚያም አንድ በመንፈስ የሚመራ ታላቅ ነቢይ እና ካህን ነበረ እርሱም ቅባአ መንግስቱን አዘጋጅቶ ጠበቀው ነብዩy ከቀባው በኋላ እንዲህ አለው " ሺህ አመት ንገስ አንተን የሚመስል የሚስተካከል ንጉስ ፈጽሞ አይመጣም። ስምህም ለዘላለም በዘርህ ዘንድ # አጼ እንጂ እጼ ወይንም እሴ አትባልም። የመንግስትህም ስም ያየሁት #ሰንደቅ_አልማ ሲባልና በተለያዩ # ቀለሞች_በአለም ላይ ሲውለበለብ አይቻለሁ። " ብሎ ታላቁ ካህን እና ነቢይ ራኤል ትንቢት ተናገረ። የኢትዩጵያ ሰንደቅ አላማ ከዚህ የመጣ ነው።

ኢትኤል ነኝ
ጣና ዳር
┈┈┈••✦~~~~~~~

ምንጭ 📚:- ፩)የጥንቷ ኢትዮጵያ ትንሳኤ ታሪክ መፃህፍ በመሪ ራስ አማን በላይ

.~~~~~¦~~~~~

«.....#ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !!!.....»

♡┈••✦share_ሼር_share✦••┈♡

💚@ethale💚
💛@ethale💛
❤️@ethale❤️

⤵️⤵️⤵️
2
💚💛❤️ኢትኤል💚💛❤️

በክርስቲያን ታደለ

ጥቁር ነኝ የተዋብሁ እንደቄዳር ድንኳን፣
በእንቁ ያጌጥሁ መቅደስ የከበበኝ ጊዮን፡፡

ዓይኖቼ የእርግቦች ጉንጮቼ የዋኖስ፣
ጠረኔ የከርቤ ትንፋሼ የናርዶስ፣

ስሜም እንደሽቱ በዓለሙ የሚፈስ፡፡

ደናግላን ሁሉ የዓለም ቆነጃጅት፣
በፍቅሬ ተነድፈው ስሜን ይነቀሱት፡፡

መጠሪያቸው ልሁን በስሜ ይማሉ፣
ፍቅሬን የተጠሙ የተራቡ ሁሉ፡፡

የተኛውን ፍቅሬን ቀስቅሱት ይነሳ፣
ዓለሙን ያስደምም ጥቁረቴ ድል ይንሳ፡፡

የክብር ዘውድ ነኝ ዙፋን መናገሻ፣
መልኬ ኢትዮጵያዊ መጠሪያዬ አበሻ፡፡

ስሜን ያትምና ሁሉም በከንፈሩ፣
ይመለስ ዳግመኛ የቀደመ ክብሩ፡፡

ኢትኤል 'ሚለው ስሜ በክብር ይታተም፡፡

የዓለም ቆነጃጅት ደናግላን ሁሉ
ጥቁሩ ኢትዮጵያዊ ግዮን ኢትኤል በሉ፡፡

ይሁን መታወቂያ በስሜ ተጠሩ፣
ግዮን እያላችሁ ፍጡራን ዘምሩ፡

የክብር ዘውድ ነኝ ዙፋን መናገሻ፣
መልኬ ኢትዮጵያዊ መጠሪያዬ አበሻ፡፡

የተኛውን ፍቅሬን ቀስቅሱት ይነሳ፣
ዓለም ትስገድልኝ ጥቁረቴ ድል ይንሳ፡፡

ኢትኤል እያላችሁ ቀሳውስት ቀድሱ
ሙታን ሕያው ሆነው በስሜ ይነሱ፡፡

በዙፋን ላይ ስሜን አርማ እያስከተቡ፣
በፍቅሬ ተባርከው ነገስታት ይቀቡ፡፡

በየቤተ-እምነቱ ይጸለይ በስሜ፣
ለሐበሻነቴ ለጥቁሩ ቀለሜ፡፡

የዓለም ነዳዓያን የትም የወደቁ፣
ስለኢትኤል ብለው ምጽዋት ይጠይቁ፡፡

የምድር ነገሥታት ጎበዛዝት ሁሉ፣
በስሜ ሲታረቅ የተጣላ ሁሉ፡፡

አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቁን ሰቅሎ፣
ዓለሙ ይዘምር ኢትኤል ኢትኤል ብሎ!!

«...ኢትዮጵያ በዳግም ትንሳኤ ትነሳለች!....»

ኑ ስለ ኢትኤል በህብረት እዘምር!
💚@ethale💚
💛@ethale💛
❤️@ethale❤️

⤵️⤵️⤵️
👍1
2👍1
አክሲማሮስ.pdf
1.3 MB
የሥነ ፍጥረት ሐተታ የያዘው የቅዱስ ኤጲፋንዮስ መጽሐፍ "መጽሐፈ አክሲማሮስ"
💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️
እጅግ አስደናቂ የጥንት ኢትዮጵያያን ጥበብ

💚💛❤️

🕹የጥንት ኢትዮጵያያ x-ray ህክምና

💡በጨለማ የሚያበሩ ኪነ - ህንፃ ግንባታ

🦆 ስለ ምታበራዋ ሙሴ ወፍ

💎ስለ ብርቁ የከበረ መዓድን መድኃኒትነት


✦የጥንት ኢትዮጵያያን አምፖል(ዲም ላይት) መብራት ከመሰራቱ አስቀድሞ አብያተ ክርስቲያናን እንዲሁም ቤተ መንግስት ሲገነቡ ብርቁ ወይም ብርቅርቅ የሚባል የብርሀን ሀይል ማመንጨት ድንጋይ ይጠቀሙ ነበር።ይህ የከበረ መዓድን ሌሊት አአንዳንድ ግዜ የሚያበራ ደግሞም የሚጠፋ ድንጋይ ነው።ከዋሻ ውስጥ ወይም ከባሐር ዳር ላይ ይገኛል።እሱ በአለበት ዋሻ ውስጥ እንደ እሳት ላንቃ የመሰለ ብርሀን ይታያል።መልኩም በመዓልት ቢጫ አረንጓዴ ነው።ተወቅሮ ኪነ - ህንፃ ከተሰራበት ደግሞ ሌሊት ላይ ህንፃው ያበራል።



✦ መብረቅ ብዙ ጊዜ ይመታዋል ፣ ይሰነጥቀዋል ፣ ጭራ የመሰለ ይታይበታል።ብርቅ የምትባል አውሬ ተጠግታ ልጅ ትወልድበታለች።ማነኛውም አውሬ መጥቶ ልጅዋን አይበላውም : ልጁም እስኪያድግ ከድንጋዮ ስር አይጠፋም።አንዳንድ ጊዜም ውስጡ የተከፈተ ይገኛል።አንድ ሰው በውስጡ ገብቶ ቢተኛበት መብራቱ ሲበራ ማነኛውም የውስጥ የሰውነት ክፍሎችን(የሆድ እቃ) በሙሉ ማየት ያስችላል።ልክ በመስታውት ፊት ቁመን ከራስ ፀጉራችን እስከ እግር ጥፍራችን እንደምናየው ሁሉን አጥርቶ ያሳያል።ከደዌ ከህመምም ይፈውሳል።አራዊትም ሲታመሙ ከስሩ ሂደው ይተኛሉ ፣ ይድናሉ።በአሁን ጊዜ X- ray ብለን የምንጠቀመው ቴክኖሎጅ የጥንት አባቶቻችን በዚህ መንገድ ይገለገሉበት ነበር።


✦ እንደ ሰጎን ቁመታም የሆነች ሙሴ (thunderbird) የምትባል ወፍ አንዳንድ ጊዜ እንቁላል ትጥልበታለች።ድንጋዮን እየወቀረች በእንቁላሉ ላይ ትረጭበታለች : የታቀፈችበት እግሩዋ ፍህም ይመስላል: ከእርሱ ስር የተፈለፈለ ጫጩት ሆዱ እግሩ ያበራል።"በሊሃልም በናትሲ ሱሲ ተቀናሂም ሮሜማላ ቦሃቢ ባህፍዊ በሐተዊ መብራቂል መብረቅ ዝውእቱ ማህረጽየ ወመሐሯልየ " ብለህ እየፀለይህ የመታኸው እንደሆነ ይሰበራል፣ ይደቃልም።



✦ እኒህን እና ስለ ሌሎች የከበሩ መዓድናት የሚያብራሩ 'ኁልቆ አእባን፣መጽሐፈ አዕባን ፣ ምስጢረ አዕባን...' የተሰኙ የብራና መፃሕፍ በማህፀነ ለምለሟ የኢትዮጵያ ገዳማት ውስጥ ይገኛሉ።ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ እፁብ ድንቅ የከበሩ መዓድናት ባህሪያቸውን ፣ መገኛ ቦታቸውን ፣ እንዲሁም ጠቀሜታቸውን የሚያስረዳ መፃሕፍ መሪ ራስ አማን በላይ <ጥበበ ዕንቆ አእባን> በሚል ርዕስ 'ዜና አበውና ኁልቆ አእባን' ተርጉመውታል።ከውጭ ተመራማሪዎች መካከል እንግሊዛዊው ቶማስ ኬን 'መጽሐፈ አዕባን' አጥንቶታል።
.
ኢትኤል ነኝ
ጣና ዳር :ባሕር ዳር


📚ምንጭ:- ፩) 'ጥበበ ዕንቆ አእባን ከዜና' ፧ አበውና ከኁልቆ አእባን ፡ በመሪራስ አማን በላይ
፪) ነቅዐ መጻሕፍት : ቀሲስ ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ
፫) Thomas L.Kane (tr.) , "The Mastira a'ban - an Amharic Lapidary treatise"
.

《.... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !....》

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
👍21🎉1
የጠፋው ጥንታዊ መጻሕፍ ተገኝ!

💚💛❤️

✔️በደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ ከደብረ ሰላም ወርቻሜ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በ1962 ዓ.ም ጠፍቶ የነበረው የስንክሳር መጽሐፍ ተገኘ! በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ፀሐይ ጸዳሉ ነጋሽ እንዳሉት ከጠፋ ከ50 ዓመታት በኋላ የተገኘው ስንክሳር ከመጋቢት እስከ ነሐሴ የሚነበበውን የመንፈቅ ምንባብ የያዘ ነው፡፡


✔️ ስንክሳሩ ከ20 ኪሎ ግራም በላይ ክብደት ያለው፡፡ ስንክሳር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም የቅዱሳንን እና የጻድቃንን ታሪክ የያዘ ትልቅ ዓመቱን መገልገያ ነው፡፡ በኢትዮጵያ አሉ ከሚባሉ የሚዳሰሱ ቅርሶች መካከልም ትልቅ ሀገራዊ ገጽታ እና ሃይማኖታዊ ግልጋሎት ያለው ነው፡፡


✔️ቅርሱ ከጠፋ ጊዜ ጀምሮ የማፈላለግ ሥራ ሲከናወን ቆይቶ ሐምሌ 4 በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ደብረ-ገነት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በማዳበሪያ ተጠቅልሎ ጸሎት በሚያደርጉ እናቶች ተገኝቷል፡፡ ሕጋዊ ሂደቱን ተከትሎ ወደ ቦታው መመለሱንም ዋና ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

Via AMMA

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️
⤵️⤵️⤵️
"ደሜን ጠጡትና ስጋዬንም እንኩ
አጥንቴን ከስክሱት አያልፍም ከልኩ
ነገር ግን ሀገሬን ድንበሯን አትንኩ!"

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
👍1🥰1