ኢትኤል
2.28K subscribers
97 photos
11 files
8 links
ስለ ጥንታዊው የኢትኤል ስልጣኔ እናወራለን! እንዘምራለን!
Download Telegram
#ኮከቡ?.....ደሸት

💚💛❤️

✔️ ኦሪት ዘኁልቁ 24÷21 እንዲህ የሚል ትንቢት እናገኛለን "በማደሪያህ የፀና ነው፤ ጎጆህም በአምባ ላይ ተሠርቷል፤ ነገር ግን አሶር እስኪማርክህ ድረስ ቄናዊ አንተ ለጥፋት ባርነት ትሆናለህ፤ አምላክህ ይህን ሲያደርግ አወደ፤ በሕይወት ማን ይኖራል፤ ከኪቴም ዳርቻ መርከቦች ይመጣሉ፤ ያስጨነቅህን አሦርንም ያስጨንቃሉ፤ ነገር ግን እርሱም ደግሞ ይጠፋል፡፡›


✔️ ተብሎ የተነገረውን ትንቢት ኢትዮጵያዊው ስነ ከዋክብት ተመራማሪ ደሸት በቀትር ጊዜ ከምንጩ ዳር (ጣና ሀይቅ ) ተቀምጦ ሲከታተል ፍልስፍናውን በአዝዋሪት ውሃ ሲያይ እና ሲፈለስፍ ለብልአም የታየው ኮከብ እንደገና ለደሸት ታየው የአዝዋሪቱን አረፋ ኮከብ እየተከታተለ ሲጽፍ


✔️ ድንግል ሴት (እመቤታችን) ያለ ዘር የተወለደ ልጅ ታቅፋ አያት፤ ወዲያውኑ ያየውንና ወደ ድንግሊቱ የመራውን ኮከብ ሥዕል በናስ ሰሌዳ ሥሎና ቀርጾና ድንግሊቱን፣ ልጅዋን እንደታቀፈች በወርቅ ሰሌዳ ሥዕሉን ቀርጾ ለልጆቹ አስቀመጠው


✔️ ሊሞት ሲል ‹ይህ ኮከብ የሚመስል በምሥራቅ በኩል ሲወጣ ዐይታችሁ፤ ጨረሩን ወደ ሚያመለክታቸሁ ምድር ተጉዛችሁ፣ ከምድራችሁ ከምታገኙት ከምታገኙት የምድር አበል ወርቅ፣ እጣን፣ ከርቤ፣ ልብስ ይዛችሁ ይህን አምላካችን ለአባታችን ለአዳም ለሔዋን እዲሰጣት የሰጠውን


✔️ አብርሃም ለአባታችን.ለመልከጼዴቅ አሥራት ብሎ የሰጠውን እንአርያ በክብር ይዛችሁ፣ የኮከብ ብርሃን ለስግደት ሰግዳችሁ ስጡት፤ ሉልና ዮጴ የወርቅ ሃመልመላል ለስጡለት፤ ይህ.እስከሚሆን ድረስ እንቆ አርያውን ተመልከቱት


✔️ እርሃብ ዘመን ሊሆን ሲል መልኩ ይጠቁራል፤ የጥጋብ ዘመን ሊሆን ሲል መልኩ ያበራል፤ ቅባቱ ይጭረቀረቃል ሲል እናተም ማርና ወተት ወደሚስባት ምድር ሔዳችሁ ትኖራላችሁ› ብሎ ለልጆቹ በተለመደ በአሥራ አንድ ሱባኤ ሞቷል፡፡ ይህም ዘመን በእሥራኤል ንጉሥ አልነበረም፡፡


✔️ በተለያየ ጊዜ አፄ ኃይለ ስላሴ ይህን ኮከብ ቅርፅ በእጃቸው ሰርተው የምንመለከታቸው ምክንያትም አንድም በንግስት ሳባ በኩል የንጉስ ሰለሞንን ስርዑ መንግስት ተቀብያለሁ ወይም የሰለሞን የዘር ሀረግ አለኝ ለማለት ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ ይህ ኮከብ


✔️ በኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ደሸት አማካይነት ደግሞ መሲሁ መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን በተዋህዶ ከብሮ እንደ ሚወለድ እና ሰብዐ ሰገድ ከኢትዮጵያ በኮከቡ መሪነት ተነስተው አምኃ(ስጦታ) እንዳቀረቡለት የሚገልፅ ነው።


✔️ ይህ ኮከብ በቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያን እና ጎንደር አፄ ፋሲል ግንብ ላይ ተጠልስመው ይገኛሉ ። ብዙ ሰው ኮከቡ የኢሉምናንት አድርጎ ነው የሚቆጥረው ይህ ግን የተሳሳተ አመለካክት ነው። የኢሉምናንት ኮከብ በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ላይ የምንመለከተው ባለ አምስት ጎን(pentagonal) ቅርፅ ያለው ሲሆን ከላይ ያየነው የሰለሞን ወይም የጃን ሆይ ምልክት ግን ባለ ስድስት ጎን (hexagonal) ምስል ነው ለዚህም የእስራኤል ሰንደቅ አላማ
ጥሩ ምሳሌ ነው ።


✔️ በእሥራኤል ላይ የነገሠው ንጉሥ ዳዊትም በመንፈስ የታየውን ትንቢት እንዲህ ሲል ተናጋገረ ‹በፊቱ ኢትዮጵያውያን ይሰግዳሉ ጠላቶቹም አፈር ይለብሳሉ፤ የተርሲስና የደሴቶች ነገሥታት ሥጦታን ያመጣሉ፤ የአረብና የሳባ ነገሥታ እጅ መንሻን ያቀርባሉ፡፡ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል፤ አህዛብ ሁሉ ይገዙለታል፡፡› ሲል ከደሸት በኋላ ተናግል፤ ይህም ትንቢት ለመሲህ እንጅ ለሰለሞን አይደለም፡፡ ነገር ግን ከወርቅ በፊት ሰም ስለሚቀርብ ሰም የሰለሞን ወርቅ የመሲህ ትንቢቱ ተፈጽሟል፡፡ ካነበባችሁ ሌሎችም እንዲያውቁ ሼር share ማድረግ እንዳትረሱ !!!

ስለ ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ ስልጣኔ እውቀት እና መፃሕፍትን ለማግኘት ከፈለጉ የፊስ ቡክ እንዲሁም ቴሌ ግራም ፔጃችንን ይጎብኙ!

.
《.. #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !!!! .》
⤵️⤵️⤵️
3👍3
♡┈••✦ #ፈራሁ! ✦••┈♡

❀︵ #በቴዲ_አፍሮ ︵❀

❀︵♡┈┈••✦✿✦••┈┈♡︵❀

ደመናት በሰማይ ቅርጽ እየተፈጠሩ አይስሉም ትተዋል፣
የጓሮ ሰበዞች አበቦች እረግፈዋል፡፡
:
ወፎችም ጠፍተዋል እንደ ድሮ አይመጡም፣
ሽማግሌዎች ዛፍ ስር ሸንጎ አይቀመጡም፣
:
ያልጠኑ #ጥጃዎች እየፈነጠዙ መስክ ላይ አይሮጡም፣
ልጆች ሲቆጧቸው ቶሎ አይደነግጡም፣
:
ህጻናት አውቀዋል እንደልጅ አይፈሩም፣
በእሳት ዙሪያ ከበው #ተረት_አያወሩም ፡፡
:
ከዕለታት አንድ ቀን አይባልም ቀረ፣
ያልኖረውን እድሜ ልጅም እየኖረ፡፡
:
ወንዞችም ደርቀዋል እያሉ አይፈሱም፣
ወጣቶች ደክመዋል ለሽበት አይደርሱም፣
:
ክረምትና በጋም ተናፍቀው አይመጡም፣
ቀኖቹ እሮጠዋል ምንም ጊዜ አይሰጡም፣
:
እየገሰገሰ እንዲህ እየጋለበ ጊዜ በቀን ፈረስ ዘመን ቢያስስም፣
በዓመት በዓል ቀን እንኳን ዓመት በዓል አይደርስም፣
:
አሁን እንደድሮ አሁን ያለ አይመስልም፣
ቀብር ይፋጠናል ለቅሶ አይደረስም፡፡
:
#መርዶ አይተረክክም ሞትም አይፈራ፣
በሠርግ ቤት እንኳን አይሞቅም ጭፈራ፡፡
:
ለአደራ የሚበቃ ሰው አንሷል በአገሩ፣
ጎረቤት አይመጣም ጠንክሯል አጥሩ፡፡
:
እናቶች በፍቅር ቡና #አይተጣጡም
ምን አገባኝ እያሉ የሰው ልጅ አይቀጡም፣
:
ሁሉም ነገር ቢኖር በቃ! ምንም የለም፣
ጥም አይቆርጥም ውሃ አይማርክም ቀለም፣
:
ገበታ ላይ ያለም እህል ቆርሶ ይዞ መተከዝ አያጣም፣
ይሰከራል ቶሎ #በወግ አይጠጣም፣
:
በቃ!! በቃ!! ደስታ የለም፣
በቃ!! ምንም የለም፡፡
:
ምኞትም ተመኘ የድሮውን ነገር፣
ጠቅሎ ሄደና ሀገር ከራሱ ሀገር፡፡
:
አብሮ መብላት ቀርቶ ፍቅር የጠፋ ዕለት፣
ደስታም ይጨክናል ተስፋም ይጨፍናል፣
:
የፊቱ አይታይም አሁን ይደፈናል፣
መልኩ አይናገርም ተፈጥሮም # ዝም ይላል፣
:
ሙሉ ሕይወት የለም ሁሉም # ባዶ ባዶ፣ ባዶ ባዶ ይላል፣
አሁን የኛም ነገር ይህንን ይመስላል፣
:
ግን ተስፋ አለ ሁሉም ነገር ጥሩ ይሆናል፡፡
ህዳር 2001 ተፃፈ!!

●~~~~ መፃሕፍትን ለማግኘት ከፈለጉ የቴሌ ግራም ወይም የፊስ ቡክ ፔጃችን ይቀላቀሉ
.
«~~~ #ፔጁን (ኢትኤል) ከወደዱት ሌሎች አስደናቂ የኢትዮጵያ ስልጣኔ እውቀት እንዲደርሰዎ ሼር በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ!
.
《.. #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !!!! .》
♡┈┈┈••✦ #share_ሼር_share✦••┈┈┈♡
⤵️⤵️⤵️⤵️
👍2
♡┈••✦ # አለምን_ጉድ_ያሰኝ_ማዕድን ✦••┈♡
ኢትዮጵያ ተገኝ"በረቅ"
♡┈••✦ # ሼር_share_ሼር ✦••┈♡

.በመምህር ሮዳስ ታደሰ

✦በባሕር ማዶ በነበርኩ ጊዜ በአንድ ታላቅ ሚዚየም ውስጥ ከአንድ የውጪ ተመራማሪ ጋር በድንገት ተገናኘን፤ ይኽ የባሕር ማዶ ሰው ግእዝን በሚገባ
የሚችል በመኾኑ እጅግ ተደንቄ ጨዋታችንን በዚኽ በግእዝ ቋንቋ አደረግነው፤ የጻፍኳቸውን ከግእዝ ቋንቋም የተረጐምኳቸውን ወደ 19 የሚጠጉ
መጻሕፍቶቼ ስነግረው ብዙ የግእዝ ብራና መጻሕፍት በእጁ እንዳሉ ነግሮች ጥቂቶቹን ሊያሳየኝ ግን ሊሰጠኝ እንደማይችል ነግሮኝ በሌላ ቀን ቀጥሮ
አሳየኝ፡፡
:
✦ በእጁ ከያዛቸው በርካቶች ጥንታውያት የኢትዮጵያ መጻሕፍት ውስጥ ጥናት የሚያደርግበትን ደማቅና ውብ የኾነችውን መጽሐፍ አውጥቶ አሳየኝ፤
ይኽችም መጽሐፍ የቀደምት ኢትዮጵያውያንን የማዕድን ዕውቀት የሕንፃ አሠራር ጥበባቸውን የያዘች ነበረች፡፡ እነዚኽ ድብቅ የኢትዮጵያ ማዕድናት በእጁ
ከገባ ዓለምን በእጅጉ ሊያስደምሙ ጉድ ሊያሰኙ የሚችሉ ሕንፃዎችን ሊያስገነባ እንደሚችልና ለዚኽም ፍለጋ በሳተላይት ምስል የታገዘ ቊፋሮ ማድረግ
እርሱና የጥናት ቡድኑ እንደሚፈልግ ነግሮኝ ተለያየን፡፡
:
✦ ይኽንን ከተመለከትኩ በኋላ ከሺሕ ዓመት በፊት የተሠሩ የቀደምት ኢትዮጵያውያን የሕንፃ ጥበብ በአግራሞት ማሰብ ጀመርኩ፡፡ እጅግ የተራቀቁ የሕንፃ
ግንባታ መሣሪያዎች ከመሠራታቸው አስቀድመው ደንጊያ ፈልፍለው ሕንፃዎችን የሚገነቡ ነበሩ፤ በኢትዮጵያውያን ጠበብት የታነጹ ዓለምን ያስደነቁ
በአክሱም የተሠሩ ሐውልቶች፤ ከአንድ ወጥ ዐለት በላሊበላ የተሠሩ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፤ በጐንደር ያለው የፋሲልና የነገሥታቱ አብያተ መንግሥትና
እና ሌሎችም ከመሬት ተቆፍረው ያልወጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ከተሞች ይገኙበታል፡፡
:
✦ ኢትዮጵያ በማዕድናት የከበረች ሀገር ስለመኾኗ ኢዮብ ከ4000 ዓመት በፊት “ስለ ዛጐልና ስለ አልማዝ አይነገርም የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቍ ይልቅ
ይበልጣል የኢትዮጵያ ቶጳዝዮን አይተካከላትም በጥሩም ወርቅ አትገመትም” (ኢዮ 28:18-19) ይላል፡፡
:
✦ ስለኢትዮጵያ ንግሥት ስለ ማክዳም ስጦታ “ለንጉሡም መቶ ሀያ መክሊት ወርቅ እጅግም ብዙ ሽቱ የከበረም ዕንቍ ሰጠችው የሳባ ንግሥት ለንጉሡ
ለሰሎሞን እንደ ሰጠችው ያለ የሽቱ ብዛት ከዚያ ወዲያ አልመጣም ነበር” ይላል (1ኛ ነገ 10፡10) በዚኽ ላይ ጥልቅ ጥናት ካጠኑት ተመራማሪዎች
ውስጥ ሄሬንና ማውሪሴ ይገኙበታል፡፡
:
✦ ሄሬን፡- “that the ancestors of these Ethiopians had long lived in cities and had erected magnificent temples and
edifices” (የእነዚኽ የኢትዮጵያውያን ትውልዶች ዘሮች ከተማን ከትመው ይኖሩ የነበሩና ዕጹብ ድንቅ አስገራሚ መቅደሶችንና ሕንፃዎችን የገነቡ ናቸው)
ይላል፡፡ ተመራማሪው ማውሪሴና ዶክተር ዱራሱላም በምርምራቸው፡- ‘The ancient Ethiopians were the architectural giants of the past…
:
✦ (ቀደምት ኢትዮጵያውን ጥንቱኑ በሕንፃ ጥበብ ታላቅ ዝና የነበራቸው ነበሩ … ድንቅ ሕንፃ ከዐለት የሚያቆሙ፤ ተራራ በስተው መተላለፊያ የሚሠሩ፤ ሰው
ሠራሽ ሐይቅ ያዘጋጁ የነበሩና ዐልፎ ተርፎ ግብጽ ድረስ ኼደው ፒራሚዶችን የገነቡ ሕዝቦች እንደነበሩ በስፋት ጽፈዋል፡፡ ካስነበበኝ ውስጥ በእጅጉ
የገረመኝ አንድ የኢትዮጵያ መዓድን በግእዝ “በረቅ” ይባላል፤ በዕብራይስጥ ቋንቋ ባራቅ፤ በሱርስት ደግሞ ብራቅ ይባላል፤
:
✦ የቀጥታ ትርጕሙ የመብረቅ ብልጭታ፤ መፍለቅ፤ ማንጸብረቅ ማለት ሲኾን፡፡ ይኽ ማዕድን እንደ መብረቅ ብልጭታ የመሰለ ብጫ ቀለም ያለው ነበር፤
ይኽን ማዕድን መብረቅ ከመታው በኋላ ከፍሎት የሣጥን ቅርጽ ይሰጠዋል ይላል፡፡
:
✦ ቀደምት ኢትዮጵያውን መብራት ባልተሠራበት ዘመን ይኽን ማዕድን ተጠቅመው የሠሯቸው ድንቅ ሕንፃዎች በሌሊት እንዲያበራ በቀን እንዲያንጸባርቅ
ያደርጉበት ነበር ይላል፡፡ ሙሴ (thunder bird?) የተባለች አሞራ በዚኽ ማዕድን ላይ ዕንቊላሉን ሲጥል ዕንቊላሉ ጭምር ያበራል፤ ኾዷም እንደ
ዲኮሬሽን ላይት ብልጭ ድርግም ይላል፡፡
:
✦ ይኽነን ማዕድን ቀደምት ኢትዮጵያውያን አድቅቀው ኬምስትሪውን ሠርተው የሠሩት ሕንጻ በሌሊትም በመዓልትም ያበራ ነበር፤ በዚኽም ጥበባቸው በሌላው ዓለም ያሉ ነገሥታት ኹሉ ይኽን የኢትዮጵያውያንን ጥበብ ለማወቅ ይፈልጉ ነበር ይላል፡፡ ⤵️⤵️⤵️
👍31
••✦ « የቀደምት ኢትዮጵያያን ✦••
••✦ በራሪ ፈረስ (ፔጋሰስ) » ✦••
«Pegasi Aithiopes»
♡┈••✦ # ሼር_share_ሼር ✦••┈♡
✦ የተፈጥሮን ኡደት ጠብቆ መኖር ሰዋዊ ነው ፤ ተፈጥሮን ማዘዝ መቻል ግን ልእለ ሰብዕና ነው ። ከዚህ ቀደም ስለ አፄ ሰንደቅ አለማ ገድል ስናነሳ
አንዱን እፅዋት ወደ ሌላው እፅ የአንዱን አውሬ ዘር ወደ ሌላው እንዲዳቀል በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ በቅሎን ከአህያንና ፈረስን ጋር በማዳቀል ያስገኝ
ኢትዮጵያዊ ጀነቲክስ ኢንጅነሪግ አባት እንደ ነበር አይተናል።
:
✦ ዛሬ ደግሞ ወደ ባህር ማዶ እናቅናና የጥንት ኢትዮጵያያን 'በራሪ ፈረስ' ይጠቀሙ እንደ ነበር ከኔዘርላንድስ ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት የተገኙ
ማስረጃዎችን እንዲሁም የውጭ ፀሐፊያን በዚህ ጉዳይ ምን እንዳሉ እናያለን ። የጥንት ኢትዮጵያያን በዓለም ላይ ስልጣኔን ሲዘሩ የሚያገኟቸውን
አህጉሮችን እና ውቅያኖሶችን በስማቸው እየሰየሙ.....ሲሻቸውም በሰማይ ላይ ግዛታቸው ሲያስፋፉ....በስነ - ተፈጥሮ ላይ ሲመራመሩ የኖሩ ድንቅ
ህዝቦች ናቸው።
:
✦ ታዋቂዋ አሜሪካዊት የታሪክ ተመራማሪ ድሩሲላ ዱንጅ «Wonderful Ethiopians of the Ancient cushite Empire» በሚለው መጻፏ ላይ ገፅ
5 እንዲህ ሚል እናገኛለን ".....የጥንትቶች ድንቅ ኢትዮጵያያን እንደ ብዙ ሳይንቲስቶች አባባል ዛሬ ለጠፋው በርካታ የስነ ጥበብ ውጤቶች ባለቤቶች ነበሩ
፣ በዘመናቸው የኤሌክትሪክ ባህሪያትን በማወቃቸው ከሜታል(ብረት) # ሮቦቶችን የሰሩ ፣ # Pegasus (በራሪ ፈረሶች) የፈበረኩ ጥበበኞች ..." ነበሩ ስትል
ትመሰክራለች።
:
✦ ፕሊኒ Natural History በተሰኝ መጻሕፉ ላይ በራሪ ፈረሶች በመካከለኛው ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ተዳቀሉ እና አካላዊ ገፅታቸውም ባለ ሁለት
ቀንድ እና ክንፍ እንደ ነበራቸው።የተወለዱትም ከኢትዮጵያ የባህር ዳርቻ በቀይ ባህር ደሴቶች ላይ እንደ ነበር ይገልፃል ".....Ethiopian Pegasus is an
animal from Medieval bestiaries . According to Pliny the Elder,they were a breed of two-horned, winged horses from
Ethiopia . It was born on an island in the Red Sea off the coast of Ethiopia.
:
✦ ሌላውና ዋነኛው ማስረጃ በ1350 እ.ኤ.አ እንደ ተፃፈ የሚነገርለት ከታች የምታዮት ኢትዮጵያያን በራሪ ፈረስ ያዳቅሉ እንደ ነበር የሚያሳይ የብራና ስዕል
እና ፅሑፍ ከኔዘርላንድስ ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ መገኝቱ ካላየሁ አላምንም ለሚለው ለእኔ ትውልድ ጥሩ ማስረጃ ነው። ስያሜውም በግሪክኛ
Πηγασος Αιθιοπικος (Ethiopian Pegasus) የሚል ስም ሰጠውት እናገኛለን በኛ የኢትዮጵያ በራሪ ፈረስ እንደ ማለት ነው። Pegasus was a
breed of winged, horned horse native to Aithiopia (Ethiopia) in sub-Saharan Africa. https://www.theoi.com/Thaumasios/
PegasoiAithiopikoi.html
:
✦ በዚህ ዙሪያ ብዙ ጥናትና ምርምር ሊደረግበት ይገባል።የውጭ ጸሐፍያን ስለኛ ይህን ያህል ካሉ እኛስ ስለ ራሳችን ጥበብ እና ስልጣኔ ምን አልነ ?
ተመራምሮ መድረስ የሁላችን ሀላፊነት ነው ።እኛ ያወቅነውን እውነት ሌሎች እንዲያውቁ # share እናድርግ! አስተያይታችሁን ፃፏልኝ።ኢትኤል ነኝ ጣና
ዳር÷ባህር ዳር
# ዋቢ_መፃሕፍት
1)Wonderful Ethiopians of the Ancient cushite Empire by DRUSILLA DUNJEE
2) Natural History by Pliny the Elder
# ገፆች
3) https://www.theoi.com/Thaumasios/PegasoiAithiopikoi.html የብራናው ስዕል እዚህ ይገኛል።
4) https://en.m.wikipedia.org/wiki/Ethiopian_pegasus
5) Ethiopia. https://itsmth.fandom.com/wiki/Ethiopian_Pegasus
●~~~~ወደ ቴሌ ግራም ፔጃችን ይቀላቀሉ-» https://t.me/ethale
.
«~~~ # ፔጁን(ኢትኤል) ከወደዱት ሌሎች አስደናቂ መረጃዎች እንዲደርሰዎ ሼር ፣ ላይክ እንዲሁም ጓደኛዎን በመጋበዝ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ!
.
《.. # ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !!!! .》
♡┈┈┈••✦share_ሼር_share✦••┈┈┈♡
⤵️⤵️⤵️
1
2
ብዙዎቻችሁ ስትጠይቁኝ የነበረው መፅሐፍ ~ፀሎተ ንድራ ~
⤵️⤵️⤵️
1🔥1
👍1
┈••✦ የቀደምት ኢትዮጵያያን ጥበብ ✦••

┈••✦ ለኮሮና መድኃኒት ከማዕድናት !!! ✦••

♡┈••✦ # ሼር_share_ሼር ✦••┈♡

✦ የጥንት ኢትዮጵያያን አያቶቻችን የተለያዮ አይነት በሽታዎች ፣ ወረርሽኝ ፣ ቸነፈር ሲያጋጥማቸው ይጠቀሟቸው ከነበሩ ፍቱን መድኃኒቶች መካከል አንደኛው ለተላላፊ በሽታዎች መከላከያነት የተዘጋጁ የፀሎት መፃሕፍትን መፀለይ ፤ ሁለተኛ ከልዮ ልዮ እፅዋቶች መድኃኒቶችን መቀመም ፤ ሌላው ሰሞኑን በዓለም መነጋገሪያ ለሆነው ለኮሮና ቫይረስ ጨምሮ ለሌሎችም ተዋስያንን ለማጥፋት(ለመግደል) አባቶቻችን ይጠቀሟቸው ከነበሩ ጥበቦች ውስጥ አንዱ የከበሩ መዓድናትን በዋነኝነት መዳብን(copper) በጌጣኔጥ መልክ #አምባር አድርገው በመስራት እጅ ፣ አንገት እንዲሁም እግር ላይ በማሰር ማነኛውም አይነት ቫይረስ ፣ ቫክቴሪያ ፣ ኢንፍሎይንዛ በሽታዎችን እንዳይዛቸው ይጠቀሙበት የነበረ እውነተኛ ፍቱን መድኃኒት ነው ።
:

✦ አዎ አባቶቻችን ድንቆች ነበሩ በሽታው ከመፈጠሩ አስቀድሞ መድኃኒት የቀመሙ...."አምባር እጃችሁ ላይ እሰሩ በሽታን ለመከላከል ያገለግላል" እያሉ ሲነግሩህ ተረት ተረት ብለህ አሽቀንጥረህ ጥለኸው እንዳልነበር አሁን ግን እመነኝ በግድ ሳይሆን በውድ ታነሳዋለሁ አባቶችህንም ታመሰግናለህ ምክንያቱም አንተ ምታመልካቸው ፈረንጆች ኢትዮጵያያን ይጠቀሙት የነበረው copper(መዳብ) ኮሮና ቫይረስ ሙሉ ለሙሉ በሰዓታት ውስጥ የመግደል አቅም አለው !!! የሚል ምርምር በሳይንሳዊ መንገድ ስላረጋገጡልህ!!!
:

✦ በሳውዝሃምተን ዩኒቨርስቲ የአካባቢ ጤና ጥበቃ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ቢል ኪቪል እንዲህ ይላሉ " ከ5000 ዓመታት በፊት የነበሩ ስልጣኔዎች እንደ ሚያሳዮት መዳብን ጤናቸውን ለመጠበቅ ይጠቀሙባቸው ከነበሩ ቁሳቁሶች ውስጥ አንዱ ነው።ኢንፍሎየንዛ ፣ ቫክቴሪያ ፣ ኮሮና ቫይረስ የመሳሰሉ በሽታዎች መሬት ላይ ወይም እቃ ላይ እስከ አምስት ቀን ሳይሞቱ መቆየት ይችላሉ ። ነገር ግን መዳብ(copper) ላይ መቆየት አይችሉም! እነዚህ ህዋስያን መዳብ ላይ ካረፉበት በደቂቃዎች ውስጥ ይገላቸዋል!!! ከሰዓታት በኋላም ደብዛቸው ይጠፋል።"
:

✦..civilizations were referring to copper, a material that cultures across the globe have recognized as vital to our health for more than 5,o00 years.When influenzas, bacteria , superbugs like MRSA, or even # coronaviruses land on most hard surfaces, they can live for up to four to five days. But when they land on copper, and copper alloys like brass, they begin to die within minutes and are undetectable within hours."
:

✦ ሲቀጥልም እንዲህ ይላል " ቫይረሱን ሲበታትን በአይኔ ዐይቻለሁ። መዳብ ተፈጥሮአዊ ፣ ፀረ-ተህዋሲያን፣ እንዲሁም ምንም ኤሌክትሪክ ወይም ፈሳሽ ሳሙና ሳያስፈልገው በራሱ በራሱ self-sterilize ሚያደርግ አስገራሚ መዓድን ነው። ጥንታዊ የውሀ ኮዳዎችና ጽዋዎች ለዚህ ነው ከመዳብ ሚሰሩት ። " እዚህ ላይ ልብ ይበሉ የእኛ የድሮ መመገቢያና መጠጫ እቃዎች ከምን ይሰሩ እንደ ነበር ።
:

✦ ሰሞኑን The New England Journal of Medicine እንደ ዘገበው "የጥንት ግብፃውያን ወታደሮች ለጦርነት ሲሄዱ ጎራዴ(ሰይፋቸውን) ከመዳብ (copper) የሚሰሩት በሚቆስሉበት ወቅት ህመማቸውን ለማስታገስና የተለያዮ በሽታዎችን ለመከላከል ይጠቀሙበት ነበር ። አሁን ያሉ ሳይንቲስቶች ይህን እውቀት ከጥንት ከግብፃው እንዳገኙት ይመሰክራሉ።" ሲል ያትታል።እዚህ ጋ ማስተዋል ያለብን የጥንት ግብፃውያን ተብለው የተገለፁት #ኢትዮጵያያንን ነው።የእኛ ነገስታት አብዛኛው ጊዜ አልባሳቶቻቸው ፣ ጥላዎች ፣ ሰይፏች ለምን ይመስልሀል ከነሀስ እና ብር የሚሰሩ ? ይኸን ጥበብ ስለሚያውቁ ነው።

:
✦ ማስረጃ ከፈለጋችሁ የድሩስሊን <Wonderful Ethiopia of the Ancient cushite Empire > ከተሰኝው መፃፏ ላይ የጥንት ግብፃውያን ከኢትዮጵያ ወርቅ ፣ብር ፣ መዳብ ፣ ኤርመራድ የመሰሉ የከበሩ ማዕድናት እና ጥበባቸውን ጭምር ከእኛ እንደ ወሰዷቸው ትመሰክራለች።".....ግዛቶቻቸው በከበሩ መአድናት የተትረፈረፈ ከመሆናቸው የተነሳ የልዑላኖቻቸው ልብስ ሳይቀር በከበሩ ማዕድናት ያጌጡና የሸክላ ሥራዎቻቸው በጌጥ የተሸለሙ ነበሩ። ኢትዮጵያያን በተለይ ለድግስና ለበዓላት አጊጠው ነው ሚወጡ.....ይህም ከሺህ አመታት በፊት ከአያቶቻቸው የወረሱት ነው ።"


:
✦ የእኛ ጥለን ሌሎችን ስንከተል ይኸ አለም የእኛን ወስዶ ከመዳብ ለኮሮና መድሀኒት አኙለት።ሁሉን እያልሁ ግን አይደለም ለምሳሌ ሀመሮች ያየን እንደ ሆን እስካሁን ድረስ እጃቸው ላይ አምባር ያስራሉ። ሀመሮች ይህ ማህበረሰባዊ ፍልስፍና ስለሚጠቀሙ ነው ጤናቸው ተጠብቆ ሚኖር ነው እንጅ እኛማ በየትኛው የጤና ፖሊሲያች ነው። አሁንም ብዙ ምርምር ይጠይቃል! ለተጨማሪ መረጃ አምባር ማድረግ(መዳብ) መጠቀም እንዴት ኮሮናን ቫይረስ እንደ ሚገድል ሰሞኑን የወጡ ብዙ ምርምሮችን እዚህ በታች ባሉ ድረ ገፁች መመልከት ትችላላችሁ። እኔ ለመፃፍ ያልደከመኝን መችም እናንተ share ሼር ለማድረግ አይከብዳችሁም ። ሼር አድርጎ። Copper_kills_coronavirus .

ኢትኤል ነኝ
ጣና ዳር

●ማጣቀሻ መፅሐፍት እና ድህረ ገፅ
፩) Wonderful Ethiopia of the Ancient cushite Empire by Druselin
፪) https://www.insider.com/does-copper-kill-germs-and-viruses
፫) https://www.thesun.co.uk/news/11262568/copper-kills-coronavirus-survives-4-hours/
፬) https://www.fastcompany.com/90476550/copper-kills-coronavirus-why-arent-our-surfaces-covered-in-it


●~~~~ወደ ቴሌ ግራም ፔጃችን ይቀላቀሉ-» https://t.me
«~~~ የፊስቡክ ገፃችንን ይጎብኙ!

.
《.. #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !!!! .》

@ethale

⤵️⤵️⤵️
👍1
😢1
በፎቶው ላይ የምትመለከቱት በአዲስ አበባ ከተማ በከፍተኛ ገንዘብ እየተገነባ ያለ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ነው ። ይገርማል ጣና የተፈጥሮ ሀይቃችንን አይናችን እያየ እያደረቅነ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ለመስራት እንሮጣለን!!! ቆየ እኔ ምለው ፈረንጆች ወደ ሀገራችን ሚመጡት ሰው ሰራሽ ሀይቅና ኩሬ ለመጎብኝት ነው እንዴ ? እንደ ዛ ቢሆንማ ኑሮ ፓሪስና ዱባይ ከእኛ በስንት እጅ በላቁ ነበር። አባይን ወዶ ስለ ጣና አለማሰብ ማለት ውሀን ወዶ ምንጭን እንደ መጥላት ይቆጠራል። አባይን ያለጣና ማሰብ አይቻልም!!!

🔀share_ሼር_share በማድረግ ድምፃችንን እናሰማ!

📌ትኩረት ለጣና
📌ጣናን እንታደግ

@ethale

.⤵️⤵️⤵️