ኢትኤል
2.28K subscribers
97 photos
11 files
8 links
ስለ ጥንታዊው የኢትኤል ስልጣኔ እናወራለን! እንዘምራለን!
Download Telegram
♡┈┈••✿ #በላይ_ዘለቀ ✿••┈┈┈♡
❀︵ #የደግነት_ጥግ ︵❀
♡┈••✦ #share_ሼር_Shere ✦••┈♡
✦ በላይ ዘለቀ ደጃዝማች ተብሎ ካዲስ አበባ ወደ ደብረ ማርቆስ እንደተመለሰ ከባለስልጣኖች ጋር ለመገናኘት ወደ "ጠቅላይ ግዛቱ " ጽህፈት ቤት ሄደ::ዘበኞቹም አጋፋሪውም ሲያዩት ጊዜ ሸሹ ::ከጽህፈት ቤቱ ወጥቶ ወደ ሚያርፍበት ቤት ሲገባ ወሬው ከተማውን ከመቼው እንዳደረሰው አይታወቅም ::
:
✦ ማርቆስ ያለ ሰው ሁሉ እንጀራውን ፣ወጡን ጠላውን ፣ጠጁን አረቄውን እየያዘ መጣ :: በላይ ዘለቀን ህዝቡ ሲወደው ያን ያህል ነበር ::ምግብና መጠጡ ከመብዛቱ የተነሳ ሰዎች ወደውጭ ተላኩና አላፊ አግዳሚውን "የራበኽ ስንቅ የለለኽ ና ብላ !በበላይ አምላክ ና ግባ "እያሉ ጋበዙት ::
:
✦ በበላይ ዘለቀ ሰራዊት ውስጥ መሪና ተከታይ አለቃና ጭፍራ ያለው በውጊያ ሰአት ነው እንጂ በምግብ ሰአት ሁሉም እኩል ነው :: ለሰራዊቱ የሚበቃ ምግብ ከሌለ ያለው ተቆራርሶ ለሁሉም እኩል ይደርሰዋል :: በላይ ዘለቀ መሶብ ሲቀርብለት "ሁሉም በልቷል " ይላል ::
:
✦ "አይ ዛሬ እጥረት አለ "ካሉት "እንግዲህ መልሱ ::እኔ አልበላም "ይልና ጦሙን ያድራል :: "አንድ ጊዜ ሁለት ቀን ጦም አድረው በላይ ዘለቀ ዛሬ ሶስት ድርብ (ሁለት ቁና ) ሽምብራ ላመጣልኝ ጠመንጃ እሰጠዋለሁ አለ:: አንድ ገበሬ ሽምብራውን አመጣ ጠመንጃውን ወሰደ ::
:
✦ በላይ ዘለቀ የገንዘብ ፍቅር የለበትም ::እንዲያውም ብር በእጁ አያድርም :: "ራስጌዬ አታርጉብኝ ...ይቀጥቀኛል "ይላል :: ያቃዠኛል ማለቱ ነው በጎጃምኛ። ንጉሱ ደብረማርቆስ የመጡ ጊዜ አስራ ሁለት ሺህ ብር ሰጥተውት ሄዱ።
:
✦ በላይ ዘለቀ ከማርቆስ ወደ ቢቸና ሲጓዝ አንዱ መጥቶ "ቤቴ ተቃጠለ "ገንዘብሲሰጠው ፤ ሌላው መጥቶ "ከብቴ ተዘረፈ " ሲል ገንዘብ ሲሰጠው እንዲህ ሲል ገና ቢቸና ሳይገባ አስራ ሁለት ሺ ብሩ አለቀ። "ጊዮርጊስ ያውቃል "ይላል በላይ ዘለቀ። በጊዮርጊስ በጣም ያምናል።
:
✦ ፍልሰታ ሲሆን ሁል ጊዜ ሱባኤ ይገባል። "እኔ የዘለቀ ልጅ !"ይላል ሲቆጣ። በላይ የወንዶች ቁና "ይላል ሲፎክር። ተመስገን ፈንታ የበላይ ዘለቀ የቅርብ ጓደኛው ነበር።
:
✦ አንድ ቀን ከጠላት በፊት ተመስገን ፈንታ በላይ ዘለቀን "ሸዋ ሄደን ለትልቅ ሰው እንደር። እንሾማለን ;እንሸለማለን "አለው። "እኔ ሰው ሆኜ ለሰው አላድርም "አለ በላይ ዘለቀ። "ባንተ ተኩስ ባንተ ወኔ፤ ባንዳፍታ ትሾማለኽ። "ጀግንነት ደጃችን ድረስ ይመጣ እንደሆነ ማን ያውቃል?" አለው በላይ ዘለቀ። አመታት አለፉ።
:
✦ከዛም አንድ ቀን ሞረድ እጀ ጠባብ አፈ ሾሌ ሱሪና ተመሳሳይ ኮት ጥንግ ድርብ ጥበብ ኩታ በቅሎ እንደተጫነች ጠመንጃ ከነሙሉ ዝናር ጥይት ...በላይ ዘለቀ ይህንን ሁሉ አዘጋጀና ተመስገን ፈንታን ጠርቶ፥ "ያ የጌታ አዳር ሄደን እንሸለማለን ያልከው ይኸውና "ብሎ ሸለመው።
:
✦ከዚህ በኋላ በአርበኝነት ዘመን ጓደኛሞቹ አልተለያዩም። በላይ ዘለቀ መጀመርያ "ራስ " ብሎ የሾመው ተመስገን ፈንታን ነበር። "እኔንስ ራስ አልከኝ። አንተ ማን ልትባል ነው?" አለው ተመስገን ፈንታ። "እኔንማ እናቴ አንድ ጊዜ በላይ ብላኛለች " አለ በላይ ዘለቀ ::
.
{ #ምንጭ፡- biography of Ethiopian patriot.}
.
«~~~ #ፔጁን (ኢትኤል) ከወደዱት ሌሎች አስደናቂ መረጃዎች እንዲደርሰዎ ሼር ፣፣፣፣፣ላይክ እንዲሁም ጓደኛዎን invit በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ!
.
《...... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !!!! ......》
⤵️⤵️⤵️
👍3
የታላቁ ሊቅ አባ ተስፋ ስላሴ ሞገስ " ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው የተዋህዶ አንበሳ እየሱስ ክርስቶስ ነው" የተሰኝውን የምስጢር መፃሕፍ እነሆ ጋበዝኋችሁ🙏
⤵️⤵️⤵️
ሰላም ውድ የኢትኤል ቤተሰቦች ፔጃችን ለሁሉም ተደራሽ ይሆን ዘንድ ከዚህ በታች የምትመለከቱትን ሊንክ ለወዳጆቻችሁ አጋሩ...⤵️⤵️⤵️
❀︵♡ #ጥንታዊ_ብራና_በነፃ ♡︵❀
<< መጻሕፈ ኩፋሌ>>
♡┈┈••✦ #ሼር_share_ሼር ✦••┈┈♡
✦ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ብራና መፃሕፍት በመላው አለም ተበትነው የሚገኙ ሲሆን ለምዕራቡ አለም የስልጣኔ መሰረቶች ናቸው ። ከእነዚህ ውስጥ በጣም ብዙዎች ብራና መፃሕፍት በማይክሮ ፊልም ተነስተዋል ለአብነት ያህል በፈረንሣይ ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ በርካታ የኢትዮጵያ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት፣ ደብዳቤዎች እና ታሪካዊ ሰነዶች ይገኛሉ። እነዚህ ስብስቦች መጻሕፍቱን ወደ ፈረንሣይ አገር በወሰዳቸው ሰው ስም ዝርዝር ካታሎግ ተዘጋችጅቶላቸው በጥንቃቄ ተቀምጠዋል።
:
✦ ለምሳሌ ፣ የአንቷን ዳባዲ ስብስብ ፣የማሪዮስ ሼን ስብስብ፣ የካሲሚር ሞንዶን ቪዳዬ ስብስብ  ፣ የማርሴል ግሪዮ ስብስብ፣ ...... መጥቀስ ይቻላል። ጋሊጋሊካ ቢሊያሊያቴ ፈረንሳይ (ቢኤንኤ) የተሰኝው ዲጂታል ቤተ-መጽሐፍት ደግሞ ከላይ ያየናቸውን የብራና ስብስቦች ማይክሮ ፊልም በማንሳት ጠቀም ባለ ገንዘብ ለመላው አለም ይሸጣል ። ከእነዚህ የብራና መፃሕፍት ግብይት ላይ የኢትዮጵያ ባለ ሀብቶች ቢሳተፋ እና ቅርሶቻችንን ብናስመልስ መልካም ነው ።
:
✦ ለዛሬ በፈረንሳይ ቤተ -መፃሕፍት ውስጥ ከሚገኙት የአንቷን ዳባዲ ስብስብ መካከል <<Ethiopien d'Abbadie 154 >> የተሰኝውን እጅግ ጥንታዊ እና ኦሪጅናል <<የመፃሕፈ ኩፋሌ ትርጓሜ>> 222 የብራና ገፅች ያሉት ጥንታዊ መፃሕፍ ጋበዝኋችሁ።ይህ መፃሕፍ online ግብይት ላይ በብዙ ዶላር ነው የሚሸጠው እኛ ደግሞ በነፃ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሼር በማድረግ እናጋራ ።

✦✦መፃሕፋን በቴሌ ግራም ፔጃችን ያገኙታል!!!

●~~~~ወደ ቴሌ ግራም ፔጃችን ይቀላቀሉ-» https://t.me/ethale
.
«~~~ # ፔጁን(ኢትኤል) ከወደዱት ሌሎች አስደናቂ መረጃዎች እንዲደርሰዎ ሼር ፣፣፣፣፣ላይክ እንዲሁም ጓደኛዎን invit በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ!
.
《.. # ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !!!! .》
♡┈┈┈••✦share_ሼር_share✦••┈┈┈♡
⤵️⤵️⤵️
👍2
#ኮከቡ?.....ደሸት

💚💛❤️

✔️ ኦሪት ዘኁልቁ 24÷21 እንዲህ የሚል ትንቢት እናገኛለን "በማደሪያህ የፀና ነው፤ ጎጆህም በአምባ ላይ ተሠርቷል፤ ነገር ግን አሶር እስኪማርክህ ድረስ ቄናዊ አንተ ለጥፋት ባርነት ትሆናለህ፤ አምላክህ ይህን ሲያደርግ አወደ፤ በሕይወት ማን ይኖራል፤ ከኪቴም ዳርቻ መርከቦች ይመጣሉ፤ ያስጨነቅህን አሦርንም ያስጨንቃሉ፤ ነገር ግን እርሱም ደግሞ ይጠፋል፡፡›


✔️ ተብሎ የተነገረውን ትንቢት ኢትዮጵያዊው ስነ ከዋክብት ተመራማሪ ደሸት በቀትር ጊዜ ከምንጩ ዳር (ጣና ሀይቅ ) ተቀምጦ ሲከታተል ፍልስፍናውን በአዝዋሪት ውሃ ሲያይ እና ሲፈለስፍ ለብልአም የታየው ኮከብ እንደገና ለደሸት ታየው የአዝዋሪቱን አረፋ ኮከብ እየተከታተለ ሲጽፍ


✔️ ድንግል ሴት (እመቤታችን) ያለ ዘር የተወለደ ልጅ ታቅፋ አያት፤ ወዲያውኑ ያየውንና ወደ ድንግሊቱ የመራውን ኮከብ ሥዕል በናስ ሰሌዳ ሥሎና ቀርጾና ድንግሊቱን፣ ልጅዋን እንደታቀፈች በወርቅ ሰሌዳ ሥዕሉን ቀርጾ ለልጆቹ አስቀመጠው


✔️ ሊሞት ሲል ‹ይህ ኮከብ የሚመስል በምሥራቅ በኩል ሲወጣ ዐይታችሁ፤ ጨረሩን ወደ ሚያመለክታቸሁ ምድር ተጉዛችሁ፣ ከምድራችሁ ከምታገኙት ከምታገኙት የምድር አበል ወርቅ፣ እጣን፣ ከርቤ፣ ልብስ ይዛችሁ ይህን አምላካችን ለአባታችን ለአዳም ለሔዋን እዲሰጣት የሰጠውን


✔️ አብርሃም ለአባታችን.ለመልከጼዴቅ አሥራት ብሎ የሰጠውን እንአርያ በክብር ይዛችሁ፣ የኮከብ ብርሃን ለስግደት ሰግዳችሁ ስጡት፤ ሉልና ዮጴ የወርቅ ሃመልመላል ለስጡለት፤ ይህ.እስከሚሆን ድረስ እንቆ አርያውን ተመልከቱት


✔️ እርሃብ ዘመን ሊሆን ሲል መልኩ ይጠቁራል፤ የጥጋብ ዘመን ሊሆን ሲል መልኩ ያበራል፤ ቅባቱ ይጭረቀረቃል ሲል እናተም ማርና ወተት ወደሚስባት ምድር ሔዳችሁ ትኖራላችሁ› ብሎ ለልጆቹ በተለመደ በአሥራ አንድ ሱባኤ ሞቷል፡፡ ይህም ዘመን በእሥራኤል ንጉሥ አልነበረም፡፡


✔️ በተለያየ ጊዜ አፄ ኃይለ ስላሴ ይህን ኮከብ ቅርፅ በእጃቸው ሰርተው የምንመለከታቸው ምክንያትም አንድም በንግስት ሳባ በኩል የንጉስ ሰለሞንን ስርዑ መንግስት ተቀብያለሁ ወይም የሰለሞን የዘር ሀረግ አለኝ ለማለት ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ ይህ ኮከብ


✔️ በኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ደሸት አማካይነት ደግሞ መሲሁ መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን በተዋህዶ ከብሮ እንደ ሚወለድ እና ሰብዐ ሰገድ ከኢትዮጵያ በኮከቡ መሪነት ተነስተው አምኃ(ስጦታ) እንዳቀረቡለት የሚገልፅ ነው።


✔️ ይህ ኮከብ በቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያን እና ጎንደር አፄ ፋሲል ግንብ ላይ ተጠልስመው ይገኛሉ ። ብዙ ሰው ኮከቡ የኢሉምናንት አድርጎ ነው የሚቆጥረው ይህ ግን የተሳሳተ አመለካክት ነው። የኢሉምናንት ኮከብ በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ላይ የምንመለከተው ባለ አምስት ጎን(pentagonal) ቅርፅ ያለው ሲሆን ከላይ ያየነው የሰለሞን ወይም የጃን ሆይ ምልክት ግን ባለ ስድስት ጎን (hexagonal) ምስል ነው ለዚህም የእስራኤል ሰንደቅ አላማ
ጥሩ ምሳሌ ነው ።


✔️ በእሥራኤል ላይ የነገሠው ንጉሥ ዳዊትም በመንፈስ የታየውን ትንቢት እንዲህ ሲል ተናጋገረ ‹በፊቱ ኢትዮጵያውያን ይሰግዳሉ ጠላቶቹም አፈር ይለብሳሉ፤ የተርሲስና የደሴቶች ነገሥታት ሥጦታን ያመጣሉ፤ የአረብና የሳባ ነገሥታ እጅ መንሻን ያቀርባሉ፡፡ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል፤ አህዛብ ሁሉ ይገዙለታል፡፡› ሲል ከደሸት በኋላ ተናግል፤ ይህም ትንቢት ለመሲህ እንጅ ለሰለሞን አይደለም፡፡ ነገር ግን ከወርቅ በፊት ሰም ስለሚቀርብ ሰም የሰለሞን ወርቅ የመሲህ ትንቢቱ ተፈጽሟል፡፡ ካነበባችሁ ሌሎችም እንዲያውቁ ሼር share ማድረግ እንዳትረሱ !!!

ስለ ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ ስልጣኔ እውቀት እና መፃሕፍትን ለማግኘት ከፈለጉ የፊስ ቡክ እንዲሁም ቴሌ ግራም ፔጃችንን ይጎብኙ!

.
《.. #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !!!! .》
⤵️⤵️⤵️
3👍3
♡┈••✦ #ፈራሁ! ✦••┈♡

❀︵ #በቴዲ_አፍሮ ︵❀

❀︵♡┈┈••✦✿✦••┈┈♡︵❀

ደመናት በሰማይ ቅርጽ እየተፈጠሩ አይስሉም ትተዋል፣
የጓሮ ሰበዞች አበቦች እረግፈዋል፡፡
:
ወፎችም ጠፍተዋል እንደ ድሮ አይመጡም፣
ሽማግሌዎች ዛፍ ስር ሸንጎ አይቀመጡም፣
:
ያልጠኑ #ጥጃዎች እየፈነጠዙ መስክ ላይ አይሮጡም፣
ልጆች ሲቆጧቸው ቶሎ አይደነግጡም፣
:
ህጻናት አውቀዋል እንደልጅ አይፈሩም፣
በእሳት ዙሪያ ከበው #ተረት_አያወሩም ፡፡
:
ከዕለታት አንድ ቀን አይባልም ቀረ፣
ያልኖረውን እድሜ ልጅም እየኖረ፡፡
:
ወንዞችም ደርቀዋል እያሉ አይፈሱም፣
ወጣቶች ደክመዋል ለሽበት አይደርሱም፣
:
ክረምትና በጋም ተናፍቀው አይመጡም፣
ቀኖቹ እሮጠዋል ምንም ጊዜ አይሰጡም፣
:
እየገሰገሰ እንዲህ እየጋለበ ጊዜ በቀን ፈረስ ዘመን ቢያስስም፣
በዓመት በዓል ቀን እንኳን ዓመት በዓል አይደርስም፣
:
አሁን እንደድሮ አሁን ያለ አይመስልም፣
ቀብር ይፋጠናል ለቅሶ አይደረስም፡፡
:
#መርዶ አይተረክክም ሞትም አይፈራ፣
በሠርግ ቤት እንኳን አይሞቅም ጭፈራ፡፡
:
ለአደራ የሚበቃ ሰው አንሷል በአገሩ፣
ጎረቤት አይመጣም ጠንክሯል አጥሩ፡፡
:
እናቶች በፍቅር ቡና #አይተጣጡም
ምን አገባኝ እያሉ የሰው ልጅ አይቀጡም፣
:
ሁሉም ነገር ቢኖር በቃ! ምንም የለም፣
ጥም አይቆርጥም ውሃ አይማርክም ቀለም፣
:
ገበታ ላይ ያለም እህል ቆርሶ ይዞ መተከዝ አያጣም፣
ይሰከራል ቶሎ #በወግ አይጠጣም፣
:
በቃ!! በቃ!! ደስታ የለም፣
በቃ!! ምንም የለም፡፡
:
ምኞትም ተመኘ የድሮውን ነገር፣
ጠቅሎ ሄደና ሀገር ከራሱ ሀገር፡፡
:
አብሮ መብላት ቀርቶ ፍቅር የጠፋ ዕለት፣
ደስታም ይጨክናል ተስፋም ይጨፍናል፣
:
የፊቱ አይታይም አሁን ይደፈናል፣
መልኩ አይናገርም ተፈጥሮም # ዝም ይላል፣
:
ሙሉ ሕይወት የለም ሁሉም # ባዶ ባዶ፣ ባዶ ባዶ ይላል፣
አሁን የኛም ነገር ይህንን ይመስላል፣
:
ግን ተስፋ አለ ሁሉም ነገር ጥሩ ይሆናል፡፡
ህዳር 2001 ተፃፈ!!

●~~~~ መፃሕፍትን ለማግኘት ከፈለጉ የቴሌ ግራም ወይም የፊስ ቡክ ፔጃችን ይቀላቀሉ
.
«~~~ #ፔጁን (ኢትኤል) ከወደዱት ሌሎች አስደናቂ የኢትዮጵያ ስልጣኔ እውቀት እንዲደርሰዎ ሼር በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ!
.
《.. #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !!!! .》
♡┈┈┈••✦ #share_ሼር_share✦••┈┈┈♡
⤵️⤵️⤵️⤵️
👍2
♡┈••✦ # አለምን_ጉድ_ያሰኝ_ማዕድን ✦••┈♡
ኢትዮጵያ ተገኝ"በረቅ"
♡┈••✦ # ሼር_share_ሼር ✦••┈♡

.በመምህር ሮዳስ ታደሰ

✦በባሕር ማዶ በነበርኩ ጊዜ በአንድ ታላቅ ሚዚየም ውስጥ ከአንድ የውጪ ተመራማሪ ጋር በድንገት ተገናኘን፤ ይኽ የባሕር ማዶ ሰው ግእዝን በሚገባ
የሚችል በመኾኑ እጅግ ተደንቄ ጨዋታችንን በዚኽ በግእዝ ቋንቋ አደረግነው፤ የጻፍኳቸውን ከግእዝ ቋንቋም የተረጐምኳቸውን ወደ 19 የሚጠጉ
መጻሕፍቶቼ ስነግረው ብዙ የግእዝ ብራና መጻሕፍት በእጁ እንዳሉ ነግሮች ጥቂቶቹን ሊያሳየኝ ግን ሊሰጠኝ እንደማይችል ነግሮኝ በሌላ ቀን ቀጥሮ
አሳየኝ፡፡
:
✦ በእጁ ከያዛቸው በርካቶች ጥንታውያት የኢትዮጵያ መጻሕፍት ውስጥ ጥናት የሚያደርግበትን ደማቅና ውብ የኾነችውን መጽሐፍ አውጥቶ አሳየኝ፤
ይኽችም መጽሐፍ የቀደምት ኢትዮጵያውያንን የማዕድን ዕውቀት የሕንፃ አሠራር ጥበባቸውን የያዘች ነበረች፡፡ እነዚኽ ድብቅ የኢትዮጵያ ማዕድናት በእጁ
ከገባ ዓለምን በእጅጉ ሊያስደምሙ ጉድ ሊያሰኙ የሚችሉ ሕንፃዎችን ሊያስገነባ እንደሚችልና ለዚኽም ፍለጋ በሳተላይት ምስል የታገዘ ቊፋሮ ማድረግ
እርሱና የጥናት ቡድኑ እንደሚፈልግ ነግሮኝ ተለያየን፡፡
:
✦ ይኽንን ከተመለከትኩ በኋላ ከሺሕ ዓመት በፊት የተሠሩ የቀደምት ኢትዮጵያውያን የሕንፃ ጥበብ በአግራሞት ማሰብ ጀመርኩ፡፡ እጅግ የተራቀቁ የሕንፃ
ግንባታ መሣሪያዎች ከመሠራታቸው አስቀድመው ደንጊያ ፈልፍለው ሕንፃዎችን የሚገነቡ ነበሩ፤ በኢትዮጵያውያን ጠበብት የታነጹ ዓለምን ያስደነቁ
በአክሱም የተሠሩ ሐውልቶች፤ ከአንድ ወጥ ዐለት በላሊበላ የተሠሩ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፤ በጐንደር ያለው የፋሲልና የነገሥታቱ አብያተ መንግሥትና
እና ሌሎችም ከመሬት ተቆፍረው ያልወጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ከተሞች ይገኙበታል፡፡
:
✦ ኢትዮጵያ በማዕድናት የከበረች ሀገር ስለመኾኗ ኢዮብ ከ4000 ዓመት በፊት “ስለ ዛጐልና ስለ አልማዝ አይነገርም የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቍ ይልቅ
ይበልጣል የኢትዮጵያ ቶጳዝዮን አይተካከላትም በጥሩም ወርቅ አትገመትም” (ኢዮ 28:18-19) ይላል፡፡
:
✦ ስለኢትዮጵያ ንግሥት ስለ ማክዳም ስጦታ “ለንጉሡም መቶ ሀያ መክሊት ወርቅ እጅግም ብዙ ሽቱ የከበረም ዕንቍ ሰጠችው የሳባ ንግሥት ለንጉሡ
ለሰሎሞን እንደ ሰጠችው ያለ የሽቱ ብዛት ከዚያ ወዲያ አልመጣም ነበር” ይላል (1ኛ ነገ 10፡10) በዚኽ ላይ ጥልቅ ጥናት ካጠኑት ተመራማሪዎች
ውስጥ ሄሬንና ማውሪሴ ይገኙበታል፡፡
:
✦ ሄሬን፡- “that the ancestors of these Ethiopians had long lived in cities and had erected magnificent temples and
edifices” (የእነዚኽ የኢትዮጵያውያን ትውልዶች ዘሮች ከተማን ከትመው ይኖሩ የነበሩና ዕጹብ ድንቅ አስገራሚ መቅደሶችንና ሕንፃዎችን የገነቡ ናቸው)
ይላል፡፡ ተመራማሪው ማውሪሴና ዶክተር ዱራሱላም በምርምራቸው፡- ‘The ancient Ethiopians were the architectural giants of the past…
:
✦ (ቀደምት ኢትዮጵያውን ጥንቱኑ በሕንፃ ጥበብ ታላቅ ዝና የነበራቸው ነበሩ … ድንቅ ሕንፃ ከዐለት የሚያቆሙ፤ ተራራ በስተው መተላለፊያ የሚሠሩ፤ ሰው
ሠራሽ ሐይቅ ያዘጋጁ የነበሩና ዐልፎ ተርፎ ግብጽ ድረስ ኼደው ፒራሚዶችን የገነቡ ሕዝቦች እንደነበሩ በስፋት ጽፈዋል፡፡ ካስነበበኝ ውስጥ በእጅጉ
የገረመኝ አንድ የኢትዮጵያ መዓድን በግእዝ “በረቅ” ይባላል፤ በዕብራይስጥ ቋንቋ ባራቅ፤ በሱርስት ደግሞ ብራቅ ይባላል፤
:
✦ የቀጥታ ትርጕሙ የመብረቅ ብልጭታ፤ መፍለቅ፤ ማንጸብረቅ ማለት ሲኾን፡፡ ይኽ ማዕድን እንደ መብረቅ ብልጭታ የመሰለ ብጫ ቀለም ያለው ነበር፤
ይኽን ማዕድን መብረቅ ከመታው በኋላ ከፍሎት የሣጥን ቅርጽ ይሰጠዋል ይላል፡፡
:
✦ ቀደምት ኢትዮጵያውን መብራት ባልተሠራበት ዘመን ይኽን ማዕድን ተጠቅመው የሠሯቸው ድንቅ ሕንፃዎች በሌሊት እንዲያበራ በቀን እንዲያንጸባርቅ
ያደርጉበት ነበር ይላል፡፡ ሙሴ (thunder bird?) የተባለች አሞራ በዚኽ ማዕድን ላይ ዕንቊላሉን ሲጥል ዕንቊላሉ ጭምር ያበራል፤ ኾዷም እንደ
ዲኮሬሽን ላይት ብልጭ ድርግም ይላል፡፡
:
✦ ይኽነን ማዕድን ቀደምት ኢትዮጵያውያን አድቅቀው ኬምስትሪውን ሠርተው የሠሩት ሕንጻ በሌሊትም በመዓልትም ያበራ ነበር፤ በዚኽም ጥበባቸው በሌላው ዓለም ያሉ ነገሥታት ኹሉ ይኽን የኢትዮጵያውያንን ጥበብ ለማወቅ ይፈልጉ ነበር ይላል፡፡ ⤵️⤵️⤵️
👍31
••✦ « የቀደምት ኢትዮጵያያን ✦••
••✦ በራሪ ፈረስ (ፔጋሰስ) » ✦••
«Pegasi Aithiopes»
♡┈••✦ # ሼር_share_ሼር ✦••┈♡
✦ የተፈጥሮን ኡደት ጠብቆ መኖር ሰዋዊ ነው ፤ ተፈጥሮን ማዘዝ መቻል ግን ልእለ ሰብዕና ነው ። ከዚህ ቀደም ስለ አፄ ሰንደቅ አለማ ገድል ስናነሳ
አንዱን እፅዋት ወደ ሌላው እፅ የአንዱን አውሬ ዘር ወደ ሌላው እንዲዳቀል በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ በቅሎን ከአህያንና ፈረስን ጋር በማዳቀል ያስገኝ
ኢትዮጵያዊ ጀነቲክስ ኢንጅነሪግ አባት እንደ ነበር አይተናል።
:
✦ ዛሬ ደግሞ ወደ ባህር ማዶ እናቅናና የጥንት ኢትዮጵያያን 'በራሪ ፈረስ' ይጠቀሙ እንደ ነበር ከኔዘርላንድስ ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት የተገኙ
ማስረጃዎችን እንዲሁም የውጭ ፀሐፊያን በዚህ ጉዳይ ምን እንዳሉ እናያለን ። የጥንት ኢትዮጵያያን በዓለም ላይ ስልጣኔን ሲዘሩ የሚያገኟቸውን
አህጉሮችን እና ውቅያኖሶችን በስማቸው እየሰየሙ.....ሲሻቸውም በሰማይ ላይ ግዛታቸው ሲያስፋፉ....በስነ - ተፈጥሮ ላይ ሲመራመሩ የኖሩ ድንቅ
ህዝቦች ናቸው።
:
✦ ታዋቂዋ አሜሪካዊት የታሪክ ተመራማሪ ድሩሲላ ዱንጅ «Wonderful Ethiopians of the Ancient cushite Empire» በሚለው መጻፏ ላይ ገፅ
5 እንዲህ ሚል እናገኛለን ".....የጥንትቶች ድንቅ ኢትዮጵያያን እንደ ብዙ ሳይንቲስቶች አባባል ዛሬ ለጠፋው በርካታ የስነ ጥበብ ውጤቶች ባለቤቶች ነበሩ
፣ በዘመናቸው የኤሌክትሪክ ባህሪያትን በማወቃቸው ከሜታል(ብረት) # ሮቦቶችን የሰሩ ፣ # Pegasus (በራሪ ፈረሶች) የፈበረኩ ጥበበኞች ..." ነበሩ ስትል
ትመሰክራለች።
:
✦ ፕሊኒ Natural History በተሰኝ መጻሕፉ ላይ በራሪ ፈረሶች በመካከለኛው ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ተዳቀሉ እና አካላዊ ገፅታቸውም ባለ ሁለት
ቀንድ እና ክንፍ እንደ ነበራቸው።የተወለዱትም ከኢትዮጵያ የባህር ዳርቻ በቀይ ባህር ደሴቶች ላይ እንደ ነበር ይገልፃል ".....Ethiopian Pegasus is an
animal from Medieval bestiaries . According to Pliny the Elder,they were a breed of two-horned, winged horses from
Ethiopia . It was born on an island in the Red Sea off the coast of Ethiopia.
:
✦ ሌላውና ዋነኛው ማስረጃ በ1350 እ.ኤ.አ እንደ ተፃፈ የሚነገርለት ከታች የምታዮት ኢትዮጵያያን በራሪ ፈረስ ያዳቅሉ እንደ ነበር የሚያሳይ የብራና ስዕል
እና ፅሑፍ ከኔዘርላንድስ ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ መገኝቱ ካላየሁ አላምንም ለሚለው ለእኔ ትውልድ ጥሩ ማስረጃ ነው። ስያሜውም በግሪክኛ
Πηγασος Αιθιοπικος (Ethiopian Pegasus) የሚል ስም ሰጠውት እናገኛለን በኛ የኢትዮጵያ በራሪ ፈረስ እንደ ማለት ነው። Pegasus was a
breed of winged, horned horse native to Aithiopia (Ethiopia) in sub-Saharan Africa. https://www.theoi.com/Thaumasios/
PegasoiAithiopikoi.html
:
✦ በዚህ ዙሪያ ብዙ ጥናትና ምርምር ሊደረግበት ይገባል።የውጭ ጸሐፍያን ስለኛ ይህን ያህል ካሉ እኛስ ስለ ራሳችን ጥበብ እና ስልጣኔ ምን አልነ ?
ተመራምሮ መድረስ የሁላችን ሀላፊነት ነው ።እኛ ያወቅነውን እውነት ሌሎች እንዲያውቁ # share እናድርግ! አስተያይታችሁን ፃፏልኝ።ኢትኤል ነኝ ጣና
ዳር÷ባህር ዳር
# ዋቢ_መፃሕፍት
1)Wonderful Ethiopians of the Ancient cushite Empire by DRUSILLA DUNJEE
2) Natural History by Pliny the Elder
# ገፆች
3) https://www.theoi.com/Thaumasios/PegasoiAithiopikoi.html የብራናው ስዕል እዚህ ይገኛል።
4) https://en.m.wikipedia.org/wiki/Ethiopian_pegasus
5) Ethiopia. https://itsmth.fandom.com/wiki/Ethiopian_Pegasus
●~~~~ወደ ቴሌ ግራም ፔጃችን ይቀላቀሉ-» https://t.me/ethale
.
«~~~ # ፔጁን(ኢትኤል) ከወደዱት ሌሎች አስደናቂ መረጃዎች እንዲደርሰዎ ሼር ፣ ላይክ እንዲሁም ጓደኛዎን በመጋበዝ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ!
.
《.. # ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !!!! .》
♡┈┈┈••✦share_ሼር_share✦••┈┈┈♡
⤵️⤵️⤵️
1