ኢትኤል
2.28K subscribers
97 photos
11 files
8 links
ስለ ጥንታዊው የኢትኤል ስልጣኔ እናወራለን! እንዘምራለን!
Download Telegram
የሐበሻ የጦርነት ጥበብ

THE ART OF WAR የተሰኘው እድሜ ጠገብ መፅሀፉ ከክርስቶስ ልደት በፊት ተፅፎ ከክርስቶስ ልደት በኋላም ላሉ ጦርነቶች መራሄ ሆኗል። በርግጥ መፅሀፉ ከጦርነት አልፎ ለበርካታ የቴክኖሎጂ
ካምፓኒዎችም መነሳትና መመንደግ አገልግሏል።

'ሳን ዙ በመፅሀፉ ያነሳቸው በርካታ ምክሮች የድል መንገድ ናቸው' እያሉ መመሪያውን የተጠቀሙ የጦር አበጋዞችም ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። ለብዙዎቹ የጦር አዛዦች መፅሀፉ ከሼልፋቸው ይልቅ
ለጠረንጴዛቸው ቅርብ ነው።

እኔ ግን እላችኋለሁ በእኛ በሀበሾች ሽለላ፣ ቀረርቶና ፉከራ (war song) ውስጥ ያሉ መልእክቶች ሳን ዙ ከፃፋቸው ሀሳቦች ጋር
አቻ ይሆናሉ።ስነቃሎቻችንን ስላልተረዳናቸ፤ ተረድተንም ስላልተነተናቸው ተንትነንም የሼልፍ ሸክም ከማድረግ ስላላሳለፍናቸው እንጂ ሀገር በቀል የጦርነት ጥበብ በነበረን፤ ለዚህኛው ትውልድም የነአድዋ
ድል ምክንያት ጭላንጭል በተገለጠልን ነበር።

ለአብነቱ ያህል ጥቂት የሳንዙን የጦርነት መርሆችን ከኛ ቃል ግጥሞች ጋር እያነፃፀርን እንይ፦

"ደረሰባቸው ሳይታጠቁ
እንደዝንጀሮ ፀሀይ ሲሞቁ፤"

ጠላት በተዘናጋበትና ባላሰበበት ቅፅበት ደርሶ የጠላትን ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ማድረግ የወገንን ጦር ኪሳራ ይቀንሳል። ድልንም አፍጥኖ ያስሞግሳል። በዚች የቃል ግጥም ውስጥ ጠላትህ እንደማትደርስበት አስቦ አንዴ ደረቱን አንዴ መቀመጫውን
እያገላበጠ ለፀሀይ በሰጠበት ጊዜ ደርሰህ አበራየው የሚል ምክርም አለ።

ሳን ዙም በምክሩ እንዲህ ይላል "...ጠላትህ ባልተዘጋጀበት ጊዜ
ውጋው..." (በርግጥአንድን ጠላት ታጥቂያለሁ ታጠቅ ሳይሉ መውጋት
በሀበሻ ልማድ ነውር ነው። ግን ታጥቂያለሁ ታጠቅ ከተባለ በኋላና ጦር ከተሳለ ጋሻ ከተራገፈ በኋላ እንዲያ ብሎ ነገር የለም)
ሳን ዙ በሌላ ምክሩ "...እሩቅ ሆነህ ሳለ ቅርብ፤ ቅርብ ሆነህ ሳለ እሩቅ ምሰል..." ይላል። የኛዎቹ ጦረኞችም ደጋ ሲባሉ ቆላ ቆላ ሲባሉ ደጋ ይገኙና ነው ድል የሚቀዳጁት።ለዚህ አይነቱ ሰው ደግም የመወድስ ፉከራ አለው።

"ቆላ ነው ሲሉት ደጋ እሚገለጥ፤
ጥላው ለጠላት የማይጨበጥ።"
የጦር ጠበብቱ ሳን ዙ ".... ስታጠቃ እንደመብረቅ ፍጠን..."

ይላል። ግሩም ምክር ናት። እሱም እንደሚለው በተለይ የጠላት ሀይል ብዙ ያንተ ደግም ትንሽ ከሆነ በብዙ አቅጣጫ በፍጥነት ማጥቃት ይመከራል። ይቺን ሀሳብ ሀበሻው በሁለት መስመር ግጥም እንዲህ ይገልፃታል።

"እነሱ ብዙ ማለት ምንድነው
ፈጥነን እንሂድ ድሉ የኛ ነው፤"
ሀበሻ ሲፈልገው ይቺንው ግጥም ቤት መድፊያ ስንኟን ብቻ"...እንግጠማቸው ድሉ የግዜር ነው..." ብሎ ይቀይርና በፈጣሪ መተማመኑንም ይነግርሀል።(ተለዋዋጭነት የስነቃል አንዱ ባህሪ መሆኑን ልብ ይሏል) በዚህ ብቻ አይበቃውም ሀበሻው

"የሌሊት አውሬ የቀን ጃውሳ
ጠዋት የሚያደርስ ያሞራ ምሳ"
ይልና ምሳን በቁርስ ሰአት የሚያደርስ ፈጣን ሁን ይልሀል።በዚችው ግጥሙ ቀንና ማታ የተለያየ አይነት ባህሪ ይኑርህ ብሎ "..በጦርነት ውስጥ አንድ አይነት አፈፃፀም የለም፤ እንደ ሁኔታው ይለዋወጣል።" የሚለውን የሳን ዙን የጦር መርህም ደርቦ
ይገልጣል።

"...ዛሬ ነገ እያልክ እድልህን አታባክን ..." ይላል ጠቢቡ ሰውዬ።እርግጥ ነው ዛሬ ነገ ማለት ውስጥ ላጥቃ አላጥቃ የሚል መወላወል አለና በዛ መሀል የልብ መፍረክረክ ይመጣል። ያ ብቻም ሳይሆን ጠላትም ጊዜ እንዲሸምትና እንዲደራጅ ወይም እንዲሸሽ ይረዳዋል። ለዛ ነው ሳን ዛሬ ነገ አትበል የማለው። ዛሬ ነገ ሲል ጠላቱ ያመለጠው ሀበሻስ ቁጭቱን እየገለጠ በተራዛማውም ሌላውን ሲመክር እንዲህ አይደል የሸለለው

"ያረባ ወንድ ልጅ እየወላወለ
ሰደደው ጠላቱን ዛሬ ነገ እያለ"
ጠቢቡ "ጠንካራ ሆነህ ሳለ ደካማ፤ ደካማ ሆነህ ሳለ ጠንካራ ምሰል" እያለ ይመክራል። ደካማ በሆንክበት ጊዜ ጠንካራ መስለህ ካልታየኸው በቀላሉ ትጠቃለህ። ጠንካራ በሆንክ ጊዜ ደግም ደካማ መስለሀው የመጣ ጠላትን በውስጡ ያሳደረው ንቀት አግዞህ ብዙ መሰዋት ሳትከፍል ካፈር ትቀላቅለዋለህ።
ይቺንው ሀሳብ ሀበሻ በቀረርቶው እንዲህ ብሎ የገልጣታል።

"አጭር ናቸው ብለው በኛ ላይ መጡብን
ቀጭን ናቸው ብለው በኛ ላይ መጡብን
መች አወቁንና አመል እንዳለብን"
"ጠላትህ ንዴት ካለበት ተንኩሰው፤ ከተረጋጋም እረፍት አትስጠው"
ይላል ሳን።

"ነካካየው ነካካቸው አትስጣቸው ጤና
ምንጊዜም ደህና ሰው አልተባልክምና"
ይላል ደግሞ ያገራችን ሸላይ።



@ethale
👍137🤔2
አዕዋፋት እና ካፈቾዎች።

(ክፍል - ፩)

--------
<<ገመና ከታቹ የሳር ቤት ያማረሽ
ምሥጢረ መለኮት ማነው ያስተማረሽ
የሳር ኪዳን ጎጆ መሬቱን ፈልፍሎ ከሰማይ ቤት ዕጣሽ ማን በሰጠኝ ከፍሎ>>

-------
ከፋ(ካፋ፥ካፈቾ) ከጥንታውያን የጎንጋ ቤተሰብ (Gonga Families) ከሚባሉት ሕዝቦች(ከፋ፣ሸካ-እናርያ ፣ሽናሻና ጃንጀሮ)
መካከል አንዱ ነው። ጎንጋ ባሁኑ ጊዜ በአገራችን የተለያዩ ክፍሎችና አቅጣጫዎች ተበታትኖ ይገኛል። ከፋና ሸካ ባገራችን ደቡብ ምዕራብ ይገኛሉ። ዛሬ ስለ ከፋዎች ነው ልነግራችሁ ያሰብኩት።

ስለ ከፋዎች እና ስለ አዕዋፎቻቸው።
ከፋዎች እና ተፈጥሮ ያንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ከዛፉ ከወፉ ፣ ከወንዙ ፣ ከላሙ ከበሬው ይግባባሉ። ቋንቋ አላቸው።
በሬዎቻቸውና ላሞቻቸው ስም አላቸው። ስም አወጣጡም ብዙውን ጊዜ የከብቱ የቆዳ ቀለም ላይ በመመስረት (ቦቃ፣መጋላ..ወዘተ አይነት) ነው።

በስም ጠርተው <<ሃእ፥ሃእ - እንካ፥እንካ/እንች፥እንች>> ብለው
መዳፍ ሲዘረጉ ስሙ የተጠራው ከብት ሰተት ብሎ ሲመጣ ማየት
አጀብ ያሰኛል። አንዳዴ ከብቱ ጌታውን ሲያይ ብቻ ስሙ ሳይጠራ ይመጣል። የመጣውን ከብት(ላም/በሬ) አሞሌ ያስልሱታል።አሞሌ ቢያጡ ግራዋ ቀጥፈው ያበሏቸዋል(ግራዋ ከብቶችን የማይማረረው ለምንድነው? ምሬቱን ይሆን ሚወዱት? ተፈጥሮወጥተው የሆነ ምላስ የላትም? ይኸው ይመስለኛል የስሙርነቷና
የመቀጠሏ ምስጢር።) ግራዋም ከታጣ ከብቱ ትናንት የበላበት እጅ ነውና ባዶ መዳፍ ይልሳል።

ባለቤትየው ቁጭ ያለ እንደሆነም
የጌታውን ራስ ይልሳል(በላብ መልክ የወጣውን ጨውይሆናልን ..?)። አለ ጌታው የማይጠመድ በሬ ፥ የማይለጎም ፈረስ
፤ አለእመቤቷ የማትታለብ ላም አሉ።
ከፋ ተወልደው ያደጉ በሬዎች(በሬም እንደሰው ተወልዶ ያድጋልን? - አዎን!) ቋንቋ ያውቃሉ። <<ዬኻኻ..አማህን ታዶኖ -
ቁምማ ጌታው፥አትሂድ ጎበዜ..>> ሲሏቸው ቀጥ ይላሉ።

በሬው እያረሰ ያዳለጠው፥የወደቀ እንደሆነ ገበሬው እንደሰው <<ታድህቦን ታዶኖ - እኔ ልውደቅ ጌታው>> ይለዋል ። በሬውም
ይሰማል ይኼን። ያውቃል ይኼን።
ከተራራው፥ከጋራው - ከወጠጤው ከአውራው ፤ ከዛፉና ከሐረጉ -
ከጎባጣው ከዝርጉ ፤ ከ አድባርና ከደብሩ - ከአዝመራው ከመኸሩ ከክረምትና ከበጋው..ከዝናብና ፀሐዩ ፣ ከበልግና ከጸደዩ፥ከሰኔና ከነሐሴ ከመስከረምና አደዩ... ወዘተረፈ ያላቸውን ቁርኝትና ቋንቋ
ካነሳሁ ''...ብዙ ቢያወጉ ይዘነጉ '' እንዳያስብልብኝ ቶሎ ወደ ተነሳሁበት ልመለስ። ከፋና አዕዋፍ።

፩. ካፌ/ካፎ - ወፊት/ወፍ - ዖፍ*
<<ኧህህህ ወፊቱ..ኧህህህ ወፍዬ
ኧህህህ ወፊቱ..ኧህህህ ወፍዬ>>
በዘልማድም ይሁን ልብ ብለነው የ ወፎችን ዝማሬ እንሰማለን።ያዳመጥን ግን ያለጥርጥር ጥቂቶች ነን። በተለይ በሥነጥበብ ስራዎች ላይ ጎልቶ ሲነገር ስለሰማን ብቻ የወፎችን ዝማሬ ነገር
የምናውቅ ይመስለናል። ያብዛኞቻችን እውቀትና አድናቆት ግን የ 'ስማበለው'ና ለራሳችንም ሳይታወቀን (Unconsciously) ነው።

ይሄን ለመታዘብ እንዲሁ አበባን ፣ ጨረቃን ፣ የፀሐይ ጮራን...ወዘተ "እወዳለሁ" እያለ ፣ አስቁመህ ለነዚህ ነገሮች ያለው ፍቅር ከምን የመነጨና እንዴት ያለ እንደሆነ ፣ መደመሙስየትምህርት ድረስ እንደሆነ ሲጠየቅ ግራ የሚገባውን ሕብዝ** መመልከት ነው። ታዲያልህ ከፋዎችና ፣ የወፍና ፥ የወፍ ዝማሬ ነገር ያላቸው
ግኑኝነት የ 'ስማበለው'ና የዋዛ ባይሆን ነው ልነግርህ መነሳቴ።ከፋዎች ወፊት ከፋ እንደሆነች ያምናሉ። በፍጹም ያምናሉ።
በአፈታሪኮቻቸውም ሆነ ዛሬ ባሉት ከፋዎች ዘንድም ወፊት ቋንቋዋ ከፍኛ እንደሆነ ያምናሉ። ቢያንስ ከፋ ውስጥ ያለች ወፊት ከፋ ናት።በወፍ ያስተነብያሉ። ያስተነትናሉ። ይተነትናሉ ። ወፊትን ያምናሉ።መንገድ ሲወጡ ፣ ከዳኛ ዘንድ ነገር ሲኖራቸው ፤ የያዙትን እኩይ መክያ(በትር፣ጦር አንካሴ) ክረምት እንደሆን መሬቱ እንዳያዳልጣቸው እየተመረኮዙ ፤ በጋ እንደሆን እትከሻቸው
አጋድመው በሃሳብ ተውጠው ጭልጥ ብለው ዱሩን እየጣሱ ድንገት የዱር ወፍ ከሃሳባቸው ታናጥባቸዋለች...

ከሁለት አንድ ነው፦
✤"ዴ'ተ ገት ፥ ወድተ ገት ፤ ሻታህን! -በጀልኝ በል ፥ አማረ በል፥ ሰመረ በል -አትፍራ!"
ይኸንን ያለችው እንደሆነ ጮቤ ይረግጣል። ወፊት ከፈጣሪ ዘንድ የተላከች መላክተኛ እንደሆነች ያምናል። ወፊትን ሰምቶ ዝም
አይልም። የሱ መልስ አለ ፦
"ነ ኩቾ ጠባያ፤
ነ ቡሾ ቅታያ፤
ሻትያነ ዬርን ግበነሆ -
ጎጆ ይስፋሽ
ጫጩት አይሙትብሽ
አዎን አልፈራም እግዚአብሔርን እታመናለሁ " ይላታል ።

✤ "ሻት፥ሻት፥ሻት፥ሻት - ፍራ፥ፍራ፥ፍራ፥ፍራ"
ይኸን ያለችው እንደሆነ ከወጣበት መንገድ ይመለሳል። ይፈራል።ያሰበው እንደማይሳካ እንደማይቀና ያምናል። ወፊት ይኽን
ያለችው እሱ ምንም ሳያስብ ከሆነም ምን ሊመጣብኝ ይሆን እያለ ይሰጋል።
ከላይ ያልነውን ብስራትም ሆነ መርዶ ወፏ እየደጋገመች፤ ሰውዬው እየተራመደ ከሆነም እየተከተለች የምትለው ከሆነ
ሰውዬው ነገሩ/መልዕክቱ/ትንቢቱ ለርሱ መሆኑንና ቁርጥ ፥ ዕሙን መሆኑን ያምናል።

ክፍል - ፪ ይቀጥላል......
__
* ካፎ - ወፍ = ባለ ብዙ ሕብረ ቀለምና ስብጥር ዝርያ(በዛውም ስብጥር ዝማሬ) ያላቸውን ትንንሽ ወፎችን ለመወከል የተነገረ
ነው።


**ሕብዝ = ልባዌ (Consciousness) ለሌለው ሕዝብ የሚቀጸል ለበጣ ።


@ethale
@ethale
@ethale
8👍8
2
አዕዋፋት እና ካፈቾዎች።
(ክፍል - ፪)

--------
፪. መቸኮ።
በከፍኛ 'መቸኮ' የሚባለውን ወፍ ድምፅ እንጂ መልኩን አይቼ ስለማላውቅ የወፉን መልክና ስም ለይቼ አልነግራችሁም።
እንድትገምቱት ግን ድምጹና ዝማሬውን በአማርኛ ሲያደምጡት "መሸኮ" የሚል ቃናና ድምጸት አለው።

ስለዚህ ወፍ የሚነገር የከፋዎች አፈታሪክ አለ። ፈጣሪ ለሁሉም ፍጡራን ሚስት ያድል ነበር አሉ።(በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ትውፊት
ውስጥ ሔዋን ገና ሳትፈጠር አዕዋፍ ለእያንዳንዳቸው ከተሰጧቸው ከእንስታቸው ጋር ሲጫወቱ አዳም አይቶ እንደቀና
የሚነገረውን ልብ ይሏል።) እና ለሁሉም ተባዕት ሚስት ስትታደል መቸኮ ለሚባለው ወፍ የደረሰችው ሚስት ፉንጋ ነበረች ይላል
የካፈቾ ሚት። መቸኮ ተበሳጨ። 'እምቢ አልፈልጋትም' አለ።"ተወዋ!" አለና እግዜር ሚስቱን ንስት ክልክል! ይኸው እስከዛሬ 'መቸኔ፥መቸኮ - አወየው ሚስቴ-ሚስትዋ..' እያለ እየጮኸ እየተጸጸተ ይኖራል ይላሉ።

ከእግዚአብሔርና ከተፈጥሮ የሆነ ሥጦታ ልክ ነው፤ ፍጹም(Absolute) ተረክ ነው። ተረትም እውነትም። በቅንፍ፦
(ያው ተረት አናቆርፍድ ብለን እንጂ ሚስት ከሌለችው ማንን ተኝቶ ከማን ወልዶ ዘሩን ተክቶ ኖረ ብለን እንጠይቃለን። በዛውም ላይ መቸኮ በሚለው ቃል ውስጥ መቸ(ቼ) ማለት ሚስት ቢሆንም ኮ (ኮ - koo) የሚለው የኔነት(Possession) አመልካች ተቀጥላ ጥቅም ላይ የሚውለው በኦሮሚኛ እንጂ ከፍኛ ውስጥ መኖሩንአላውቅም።)

፫. ኡጌ - እርግብ - ርግብ!
ከአዕዋፋት ገራገርና የዋህ ብንባል እርግብን ቀድሞ የሚመጣልን
ያለ አይመስለኝም። በወንጌልም "እንደ እርግብ የዋሖች ሁኑ ፤ እንደ እባብ ልባሞች ሁኑ" ተብሏል። እባብ ብል ትዝ ያለኝን 'የከፋ- የእባብና - የወፍ' ነገር ነግሬአችሁ ወዳነሳነው የ 'እርግብና ከፋ' ወግ እንመለሳለን። እንደ እርግብ ገራገርና የዋሕ የሆኑ ከፋዎች እንዴት እንደ እባብ ልባሞች እንደሆኑ እዩ።ተመልከቱ።ወፍ ጎጆ ትቀልሳለች።ጠላቷ እባብ ነው።ስለዚህም ከጥቃት ራሷንና እንቁላሏን ለመከላከል ስትል ዘዴ ትዘይዳለች። ይኸውም ማሳሳቻ ሐሳዊ ጎጆ (pseudo nest) መቀለስና እንቁላሏን ግን በድብቁና እውነተኛው ጎጆ ውስጥ መጣል ነው። በዚህም ከጠላት
(በተለይ እባብ) ታመልጣለች። ከፋዎች በርሷና በእባብ መካከል ያለውን ጥላቻ ስለሚያውቁ አረንጓዴነቱ ያልጠፋ ልጥ በብዙ መንገድ ከገላው አንስቶ እስከሌላው ነገር እባብ እንዲመስል አድርገው የወፏን ጎጆ ይጠመጥማሉ።

ወፏ ወደ ጎጆዋ ስትመጣ እባብ(ልጥ ወይም ሌላ ከእባብ የተገናኘ ምልክት ዳና..) ስታይ ዕጽ እየበጠሰች ታመጣለች(ይኽን የሚያደርግ የወፍ ዝርያ
ውስን/አንድ ብቻ ሊሆን ይችላል)። እሱን ዕጽ(ለምሳሌ ዕጸ ዜዌ ቢሆን..) ዘሩን ዓይነቱን ለይተው መርምረው ያጠኑታል። ታዲያስ እንዲህ አይደል እንደ እባብ ልባም መሆን!

ንግባዕኬ ሀበ ጥንተ ነገር.. ወደ እርግብ እንመለስ። እርግብ በከፍኛ ኡጌ(Ugge) ይሏታል። ይህች ገራገር ወፍ የምትዘምረው
ዝማሬ(የሌሎች ወፎች ዝማሬ እንደ ክራር - የእርግብ ዝማሬ እንደ በገና ነው) በከፋዎች ዘንድ ተቀድቶ ተተርጉሞ ግጥም
ተገጥሞ ይዜማል።

ይዘመራል።'እቴሜቴ..የሎሚ ሽታ' ስትሉ ኢትዮጵያውያን ሕጻናት ባንድነት እንደሚቀበሏችሁ ሁሉ የከፋ ገጠሮች ኼዳችሁ "ጉድች እንዴ ታንዴ.." ብትሏቸው በፍጹም ሃሴት ሆነው "ቡሼ ከኖ ዋቴ...ገሜ እከ ሸቄን ኡሽ ገደ ባጤ.." እያሉ ይቀበሏችኋል።ዜማው የሚወርደው እርግቧ ራሷ በምታዜምበት ስልት ነው።ራሱን። ግጥሙ ደሞ እሷ በድፍን ያለችው ተፈትቶ ተገስሶ ፤እሷን አብነት አድርጎ በሰው አፍ ተገጥሞ ነው።

የከፋ እርግብ የሕጻናት ዝማሬና ዜማ ናት። አሳድጊያቸው ነች።የመንፈስ ሞግዚት። በተቀዳ ሲዲ ሳይሆን በተፈጥሮ አፍ..
በርግብ እምምታ ነው የከፋ ማቲዎች የሚያደጉት።የዶሮና የከፋዎችን ነገር እናውጋና በቃን።

፬. ባኮ - ዶሮ - ዶርሖ
አዕዋፍ ሁለት ምድብ ናቸው። አዕዋፍ ዘቤት(የቤት ወፎች ፣ እነዚህም ዶሮዎች ናቸው) እና አዕዋፍ ዘአፍዓ(የውጭ ፥ የዱር
ወፎች ፣ እነዚህም ከሚበሉት ወገን ቆቅና ጂግራ.. እና ሌሎች እማይበሉ አሉበት..) ተብለው ይከፈላሉ በግዕዙ ሥነፍጥረት
ትምህርት።

፬.፩ ቆቅ

"ኧህህ.. ፈጣሪዋን አምና ኧህህ.. ያፏን ጥሬ ዘርታ፣ለጭሮ አዳር ውሎን በዝማሬ ወጥታ፣አዳኝ እንዴት ያጥቃት ፍርድና ዳኛ አጥታ..? " የከፋ ኮበሌዎች ጀብድ(adventure) የሚጀምሩት ቆቅ
በማጥመድ ነው። ከዚያም በላይ ቆቅን ከማደሪያዋ አስነስቶ ስትበር እየተከተሉ አዳክሞ መያዝ ደሞ የጀብዶች ጀብድ ተደርጎ ይቆጠራል። ይኬ ግን ቆቋ በበረራ አጥማጅ በሩጫ ስለሆነ ፉክክሩ ቆቅ ይቀናታል። በባሕርይዋ አየር ላይ እየበረረች መቆየት አትችልምና ሲደክማት እምናምኑ ገብታ ኮሽ ሳትል ትደበቃለች።ይኼ ነው እንግዲህ ቆቅ ማጥመድን ብርቅና አስደሳች የሚያደርገው። አደይ ግውው ብሎ ሲያብብ ያን ጊዜ ቆቅ ትፎክራለች። ታሽካካለች። ታዜማለች።

የከፋ ገጠር ጠዋት፥ጠዋት ከሚጤሰው የደመና ተራራ ፣ካበበው አበባ ከቡና ወቀጣ ድምጽ ጋር..የቆቅ ማሽካካት ሲጨመርበት
እግዚኦ ማሕሌት!!! ለአቅመ ማጥመድ ያልበቁቱ የቆቅ እንቁላል ፍለጋ ጧቱን
ይሰማራሉ። ዕድለኛው ማቲ(አዋቂም ቢሆን) ደስታው የቆቅ ግማሽ ያህላል።

፬.፪ ለማዳዋ ቆቅ - ነገረ ዶሮ።
በከፋዎች የኖረ ስርዓት ሴቶች ዶሮ አይበሉም ነበር። (ዛሬም ቢሆን በዕድሜያቸው ያለፈው ትውልድ አካል የሆኑትና በወግ አጥባቂው የከፋ ገጠራማ ክፍል ያሉ ሴቶች የዶሮ ስጋ አይበሉም። በቁጥር ግን ጥቂት ቀርተዋል።)

ታዲያላችሁ.. በኋላ ሴቶቹ ዶሮ መብላት ጀመሩ። ወንዶቹ በዘፈናቸው፣በዝርውና በግጥማቸው ሴቶችን ሸነቆጡ - ተቆጡ።
አወሩ። አሸሞሩ።ወንዶቹ ዘፈን መሃል እንዲህ ብለው ከሰሱ፦
(በተቀራራቢ አማርኛ ስመልስላችሁ..)

"ኧረ ሴቶች ተበላሹ
ወይዛዝርት ተበላሹ
ዶሮ በሉ ቅቤ እያሹ።"
ወግ ጥሰው ዶሮ መብላት ያመጡት አፈንጋጭ ሴቶችም እንዲህ
መለሱላቸው፦
"ማን አባክ ሽንኩርት ልጦ?
ማን አባክ ቅቤ አቅልጦ?
እኛ እንጂ ብልት የበለትን-
እኛ እንጂ ላባ የነጬን
እኛ እንጂ ቆላነው ፈጬን፥
አዝሙድ አብሹን ቅመሙን
'በሉብን' ብላችሁ ታሙን?
እኛን እንጅ እሳት የፈጀን
እሰየው እንኳን አበጀን
እሰይ እንኳን ተበላሸን
ዶሮ በላን ቅቤ እያሸን"
የሴቶቹ አብዮት ጸንቶ የዛሬዎቹ የከፋ ሴቶች(ከላይ ካልናቸው
ጥቂቶች በቀር) ብልት ተቀራማች ሆነዋል።

እውነትም እሰይ
አበጁ!
በዚህ ይብቃን።
በአያ ሙሌ የነፍስ አድርስ ብዕርና በአበበ ተካ ጉሮሮ ልሰናበታችሁ

"....ኧህህ..ምነው ባደረገኝ ኧህህ.. የሷ ጋሻ ጃግሬ እንደምንም ብዬን እኔም ጥሬ ግሬ
ያገዳ ጎጆዬን ባቆምኳት ማግሬ...፤
ገመና ከታቹ የሳር ቤት ያማረሽ ምሥጢረ መለኮት ማነው ያስተማረሽ የሳር ኪዳን ጎጆ መሬቱን ፈልፍሎ ከሰማይ ቤት ዕጣሽ ማን በሰጠኝ ከፍሎ...ኧህህ.. ፈጣሪዋን አምና ኧህህ.. ያፏን ጥሬ ዘርታ፣ለጭሮ አዳር ውሎን በዝማሬ ወጥታ፣አዳኝ እንዴት ያጥቃት ፍርድና ዳኛ አጥታ..ታማ ትንፋሽ አጥታ ደክማ ስታጣጥር ማን ያቃናት ይሆን ውለታ ሳይቆጥር..!?
ኧህህህ ወፊቱ..ኧህህህ ወፍዬ
ኧህህህ ወፊቱ..ኧህህህ ወፍዬ"
ድጎ ቱነባ - ኬር ይሁን!!
----------

@ethale
10👍9
ጥንታውያን የኢትዮጵያ ሊቃውንት ከሽህ ዘመናት በፊት ብራና አውጥተው ፣ ብዕር ቀርፀው ፣ ቀለም በጥብጠው ያዘጋጇቸው የብራና መጻሕፍት ኢትዮጵያ ለዓለም ካበረከተቻቸው የስነ ጹሑፍ ሀብቶች መካከል ግንባር ቀደም ናቸው።ለብራና መጻሕፍት ለመጻፊያነት ከሚጠቀሙባቸው ነገሮች መካከል አንዱ ቀለም ነው።የቀለማቱ ዓይነት የተለያየ ኀብረ መልክ ነበረው።

በመካከለኛው ዘመን የነበሩ ቀደምት የቁም ጸሐፊዎች የብራና መጻሕፍትን ለመጻፍ ጥቁርና ቀይ ቀለማትን ከእጽዋት በማዘጋጀት የዘወትር መገልገያዎቻቸው አድርገዋቸው እንደነበር መዛግብት ያስረዳሉ።

ጸሐፊዎቹ ቢጫ(የወይን ጠጅ) ቀለም ፣ አረንጓዴ ቀለም ፣ ውሃ ሰማያዊና ነጭ ቀለማትን ከየመልካቸው ጋር የሚቀርቡትን ድንጋዮችና የአፈር አይነቶችን አሰባስበው በመፍጨት በጣም ሲልም እየቀቀሉና እያነጠሩ ለማያያዣ ሙጫ ጨምረው ወደ ቀለምነት በመለወጥ ይጠቀሙ እንደነበር ይነገራል።እነዚያም ቀለማት ሰባቱ ቀለማት የሚል መጠሪያ ስም ማግኘታቸው ይታወቃል።

ጸሐፊዎቹ ቀለማቱን የሚጠቀሙባቸው ለቤተ ክርስቲያን ሥዕል በሚስሉበትና የብራና መጻሕፍትን ጽፈው ለመጻሕፍቱ ውበት ሐረግ በሚጥሉበት ጊዜ ፣ ድርሰቱን የጻፈውን ሐዋሪያ ወይም መጻሕፍቱ የተጻፈለትን ባለ ታሪክ (በገድል) በሥዕል ለማስተዋወቅ የሚያደርጉት መግለጫ እንደ ነበር በየዘመናቱ የተጻፉት መጻሕፍት በዋቢነት ይጠቀሳሉ።

ይቀጥላል!
.
@ethale
👍148
ንጉስ ባልታዛር የኢትዮጵያ የገና አባቷ ነው።

የኢትዮጵያ ገና በዓል በደረሰ ሰሞን በመብራት ያሸረቀ ጽድ ፤ የፈረንጆችን የገና አባት ሳንታ ክላውስንን በቴሌቭዥን ማየት የተለመደ ሁኗል።የራሷ የዘመን ስሌት ያላት ሀገር የራሷ የገና አባት ስለሌላት ነው?! አይደለም! ራሳችንን ማክበር ስላለመድነ እንጅ

ከሳንታ ሽህ ዘመናት የቀደመ ፤ ስሙ በመጻሕፍ ቅዱስ የተጠቀሰ ፤ ሰማይና ምድርን የፈጠረ አምላክ በተወለደ ጊዜ የወርቅ ስጦታ ለአምላክ ያቀረበ ፤ ኮከብ እየመራው ቤተልሔም የደረሰ ፤ የአክሱሙ ንጉስ ባዜን (balthasar) የኢትዮጵያ የገና አባቷ ነው።

መዝሙረኛው ዳዊት  መዝ 71 ፥ 9 ላይ " በፊቱም ኢትዮጵያያን ይሰግዳሉ ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ።የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ።የዓረብና የሳባ ነገስታት  እጅ መንሻ ያቀርባሉ ነገስታትም ሁሉ ይሰግዱለታል።" የሚለውን ትንቢት እውን ሊያደርግ ከሶስቱ ሰብዓ ሰገድ አንዱ የሆነው ንጉስ ባዜን ከኢትዮጵያ ተነስቶ ወደ ቤተልሄም የተጓዘ መስጠትን በተግባር ያሳየ ሰው ነው።

የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን እንዲሁም ፋሲል ግንብ ጣሪያ ላይ'ም እነ ንጉስ ባዜንን የመራቸው ኮከብ ተስሎ ይገኛል።

መካነ መቃብሩም በአክሱም ሐውልት አቅራቢያ ከአለት ላይ ተፈልፍሎ እንደተሰራ ዮኒስኮ በቦታው ባስቀመጠው መሰረተ ድንጋይ ላይ ተጽፏ ይገኛል።(ፎቶውን መመልከት ይቻላል።)

በብዙ መጻሕፍት ላይ ስሙ ተደጋግሞ ይነሳል።ታዲያ ኢትዮጵያ ንጉስ ባዜንን የመሰለ legendary ሰው እያላት ሳንታ ክላውስን መገለጫ ማድረጋችን አያሳፍርም?! ይህ ከቀኝ ግዛት አይተናነስም አድዋ ያ ሁሉ መስዋዕትነት የተከፈለው ስለ መሬቱን ብቻ ሳይሆን ባህል ፣ ማንነት ፣ ሐይማኖትን ላለማስደፈር የተደረገ ተጋድሎ ነው።

"የግመሎች ብዛት የምድያምና የጌፌር ግመሎች ይሸፍኑሻል።ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ ወርቅ እና እጣን ያመጣሉ የእግዚያብሔርንም ምስጋና ያወራሉ" እንዲል ትንቢተ ኢሳያስ 60 ፡ 6።

ንጉስ ባዜን የኢትዮጵያ የገና አባት  መገለጫ እንዲሆን የሁል ጊዜ ምኞቴ ነው።
ከወዲሁ መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ።

@ethale
14👍1🔥1
Forwarded from ዓለም ማያ (ኒያስ)
ሸዋረገድ ገድሌ በፋሺስት ጣሊያን ወረራ ጊዜ አስደናቂ ጀብድ ከፈጸሙ ሴት አርበኞች መካከል ግንባር ናት።ቀይ መስቀል ሲመሰረት ሙሉ ሀብቷን በመሸጥ ድጋፍ አድርጋለች።

ለአርበኞች ስንቅ በማቀበል ፤ መድኃኒት በመስጠት እንዲሁም መረጃ በማሰባሰብ ትታወቃለች።

ሸዋረገድ አንድ ዕለት ጫካ ውስጥ ስትዋጋ ጣሊያኖች አገኟት።ሴት በመሆኗ በንቀት ዐይን እያዮዋት

" ቆይ አንች ሴት ነሽ ጫካ ውስጥ ምን ትሰሪያለሽ? " በማለት ጣሊያናዊው ወታደር ጠየቃት።

"ምክንያቱም የአንበሶች መኖሪያ ጫካ ስለሆነ! " በማለት ነበር ምላሽ የሰጠችው።

እንኳን ለ84ተኛው የኢትዮጵያ አርበኞች በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

📍share & join⚡️
@alememaya
@alememaya
20👍7👏4🥰3
አሜሪካዊው ሳይንቲስት መህሙድ ጃዋይድ አረጋገጠ!

🔴➨የኤዶም ገነት የምትገኝው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።

#DAILY_MAIL ሳይንቲስቱ አለምን ጉድ ያሰኘው አዲስ ዜና ይዞ ብቅ ብሏል!

በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት የሚገኙ የተመራማሪ ቡድኖች የመፅሐፍ ቅዱስን ኤደን ገነት ትክክለኛ መገኛ ስፍራ በአፍሪካ ውስጥ ኢትዮጵያ እንደሚገኝ አረጋገጡ።

ትርጉሙን እንደሚከተለው አቅርበነዋል!

በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የኤደን ገነት እግዚአብሔር አዳምና ሔዋንን ያስቀመጠበት ስፍራ ነበረ::

በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱት ታላላቅ ወንዞች ማለትም ግዮን፣ ኤፍራጥስ፣ ጤግሮስና ፒሶን ሲሆኑ ብዙ ምሁራን ጤግሮስ እና ኤፍራጥስ በዘመናዊቷ ኢራቅ ውስጥ ስለሚጓዙ ኤደን በዚያ አካባቢ መሆን አለበት ብለው ሲገምቱ ከርመዋል ነገር ግን የቴክሳስ ምርምር መሪው #ማህሙድ ጃዋይድ የኬሚካል መሐንዲስ ሲሆን በምርምር ውጤቱ መሰረት የኤደን ገነት በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ለም በሆነው ባህር ዳር፣ ብሉ አባይ በሚጀምርበት የጣና ሀይቅ ደቡባዊ ጫፍ አቅራቢያ እንደሆነ መረጋገጡን ይናገራል።

ማህሙድ የሚመራው ቡድን ጥናቱን የተመሰረተው መጽሐፍ ቅዱስን እና ቁርኣንን በጥንቃቄ በማንበብ ስለ አዳምና ሔዋን፣ ስለ ወንዞችና ስለ አትክልት ስፍራው የሚገልጹትን መግለጫዎች በመተንተን ነው።

እ.ኤ.አ. በ2025 የተደረገው ጥናት በአቻ-ያልተገመገመ፣ የብሉ ናይል ወንዝ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው ግዮን ጋር ሊመጣጠን እንደሚችል እና የጣና ሀይቅ ፈሳሾች ወደ ብዙ የውሃ መስመሮች ተከፍለው በዘፍጥረት የተገለጹትን አራቱን ወንዞች ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

ቀደምት የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ እንዲሁ በዚህ ፅንሰ-ሀሳብ ውስጥ ሚና ተጫውቷል፣ አዳም የሰው ልጅ መገኛ ነው ተብሎ በሚታሰበው በምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ ከሆሞ ሃቢሊስ ወይም ከኦስትራሎፒቴከስ ዘግይቶ ከተገኘ የአውስትራሊያ ስምጥ ሸለቆ ሊሆን እንደሚችል ሀሳብ አቅርቧል።

ከዚያ ተነስተው አዳምና ሔዋን በቁራአን 'ሀባታ' ብሎ የገለፀውን በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ሰፍረው ከመውረዳቸው በፊት በከፍታ ቦታ ላይ በምትገኘው በባህር ዳር ደጋማ ቦታዎች 'ሊቀመጡ' ይችሉ ነበር።

ምክንያቱም ክልሉ ከባህር ጠለል በላይ 6,000 ጫማ ከፍታ ላይ ስለሚገኝ፣ ለምለም እፅዋት፣ የተትረፈረፈ የዱር አራዊት እና ብሉ ናይል የሚጎርፈው፣ ከሁለቱም መጽሐፍ ቅዱሳዊው የኤደን ወንዞች መግለጫ እና የቁርአን ፅንሰ-ሀሳብ ጋር የሚጣጣሙ ባህሪያት ናቸው።

መህሙድ ጃዋይድ ከዚህ በፊት ከ11 በላይ የእስልምና የጥናት መፅሃፍቶችን በማሳተም የሚታወቅ ሲሆን በዚህ አዲስ ጥናት መሰረት ኤደን ገነትን በተመለከተ ሁሉም ፍንጮች የሚያመለክተው ባህር ዳር ጣና ሃይቅ እንደሆነና ይፕጣና ሀይቅ የኤደንን መግለጫ በትክክል ይስማማል' ሲል ሲጽፍ የእሳተ ገሞራ ሸንተረሮች በዙሪያው ያሉትን ደጋማ ቦታዎች እንደሚሸፍኑ እና የበርካታ ወንዞችን ስርዓቶች እንደሚመገቡም ጠቁመዋል።

በመልሶ ግንባታው የጣና ሐይቅ ራሱ ኤደንን የሚወክል ሲሆን የኤደን ገነት ወዲያውኑ ወደ ደቡብ፣ ባህር ዳር ዙሪያ፣ ‘ከኤደን ምስራቃዊ’ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አገላለጽ ወንዙ ከሐይቁ የሚወጣበት ነው።

የኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ አዳምና ሔዋን ከተባረሩ በኋላ ሰዎች ወደ ሕይወት ዛፍ እንዳይገቡ አምላክ በገነት መግቢያ ላይ ያስቀመጠውን ‘የሚንበለበል ሰይፍ’ ይናገራል የሕይወት ዛፍ የዘላለም ሕይወት የሚሰጥ ፍሬ ያለው እውነተኛ ዛፍ ነበር። አዳምና ሔዋን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ በልተው ኃጢአት ከሠሩ በኋላ የሕይወትን ዛፍ እንዳይበሉና በወደቁበት ሁኔታ ለዘላለም እንዳይኖሩ ከኤደን ተባረሩ።

የጃዋይድ ጥናት ‘የሚያብረቀርቅ ሰይፍ’ በኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች በጣና ሀይቅ ዙሪያ በሚገኙት የእሳተ ገሞራ ሸንተረሮች ሊወክል እንደሚችል ጠቁሟል።

ሸለቆው በታሪካዊ ንቁ እሳተ ገሞራዎች የተከበበ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ንቁ የሆኑት እሳተ ገሞራዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰውን የእሳት ሰይፍ መሥራታቸው ይቻላል' ሲል ተናግሯል።

ጥናቱ በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በቁርኣን ላይ ያተኮረ ሲሆን እያንዳንዱም በምድር ላይ ያለን የአትክልት ስፍራ ለጻድቃን ከተዘጋጀው ዘላለማዊ ገነት የተለየ መሆኑን በመጥቀስ የክልሉ የአየር ጠባይ፣ ለም አፈር እና የተትረፈረፈ የውሃ አቅርቦት ከረሃብ፣ ከጥማት እና ከአስጨናቂ ሙቀት የጸዳ ቦታን በቅዱሳት መጻህፍት እንደሚያንጸባርቅ አመልክቷል።

መሃሙድ በቅርቡ ክልሉን የዳሰሰችው እና 'ጓሮዎች በቀለማት ያሸበረቁ bougainvillea፣ ትልቅ ሂቢስከስ እና ጥሩ መዓዛ ባላቸው የፍራንጊፓኒ ቁጥቋጦዎች የተሞሉ ናቸው' የሚለውን የቨርጂኒያ ሞሬል ስራዎችን ጎላ አድርጎ ገልጿል።

ወፎቹ በብዛት ይገኛሉ፣ ‘ዘማሪ ወፎች፣ ሸንኮራ አድራጊዎች፣ ጎሽ ሸማኔዎች፣ ሮዝ ፊንቾች፣ ከአበባ ወደ አበባ የሚበሩ ናቸው። ሞሬል እንዳለው ጥቅጥቅ ያሉ የፓፒረስ ቁመቶች በጣና ሀይቅ የባህር ዳርቻ ላይ ይበቅላሉ።

‹ባህር ዳር በደረቀ አየሯ እና በአበቦች እና በአእዋፍ ችሮታ ፣ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ገነት የመድረስ ያህል ቅርብ ነች።

የአእዋፍ ዝማሬ እና ነፋሱ በጃስሚን፣ ዝንጅብል እና ሃኒሱክል መዓዛ ያለው ንፋስ አካባቢውን በጣም ከፍ ያደርገዋል። የበለስ እና የማንጎ ዛፎች፣ ግራር እና የውጭ ባህር ዛፍ በአካባቢው ባለው የጥቁር አባይ ሳር ዳር ላይ ጥሩ ጥላ ይሰጣሉ።'

እነዚህ ዝርዝሮች፣ መሃሙድ ጃዋይድ እንዳለው፣ ክልሉ በምድር ላይ ለገነት በጣም ቅርብ ቦታ እንደሚሆን ጠቁመዋል።

በቁርአን መሰረት አደምና ሀዋ (ሄዋን) ከፀሀይ እና ከሙቀት የተጠበቁ ስለነበሩ የተለያዩ አይነት ፍራፍሬዎች የሚበሉበት፣ ወፏ የሚዘምርበት እና ጥሩ መዓዛ ያለው ንፋስ የሚሸቱበት ባህር ዳር ጥሩ ቦታ መሆን አለበት' ሲል ጥናቱ አስነብቧል።

ምንጮ:-

1ኛ:- Daily Mail

https://www.dailymail.co.uk/sciencetech/article-15166613/Garden-Eden-expert-claims-Biblical-paradise-sits-shores-mysterious-blue-lake.html

2ኛ:- GBI

https://www.gbnews.com/science/garden-of-eden-found-ethiopia

3ኛ:- Daily Express USA

https://www.google.com/amp/s/www.the-express.com/news/world-news/186241/engineer-claim-garden-eden-map-location/amp

4ኛ:- Acadamia.edu

https://www.academia.edu/129924395/The_Location_of_the_Garden_of_Eden

5ኛ:- UNILAD

https://www.unilad.com/news/world-news/george-kourounis-door-to-hell-reveals-what-he-found-545414-20231213

6ኛ:- Amazon.com

https://www.amazon.com/-/es/Mahmood-Jawaid/dp/1598729624
15🔥3👍2
15👍3👏2
ማቲሴን የሚያስከነዱት የኢትዮጵያ ጠቢባን አባቶች!

ከዚህ በታች የሚገኘው የብራና ገጽ 600 ዓመታትን ያስቆጠረ ድንቅ ጥበብ ነው። ዛሬ "ዘመናዊ" የምንላቸው የጥበብ ፍልስፍናዎች ገና ሳይወለዱ፣ አባቶቻችን በብራና ላይ ጥበብን አፍስሰውታል።

📜 ከጥፋት የተረፈው ድንቅ ቅርስ

ይህ ገድል በንጉሥ ዳዊት ዘመን በሊቃውንት አባቶቻችን የተሳለና የተፃፈ ነው። ግራኝ አህመድ የቤተክርስትያን ድርሳናትን ያወድም ነበረ በሚባልበት ክፍለታሪክ ወቅት፣ ካህናቱ ለሕይወታቸው ሳይሳሱ ረዥም መንገድ ተጉዘው ይህን ድርሳን ከሰው እይታ ሰውረውታል።

ጉዞው፦ ከቆመበት ስፍራ 500 ኪሎሜትሮችን ተጉዞ ዛሬ በዝዋይ ሐይቅ ደብረ ፅዮን ገዳም ተጠልሎ ይገኛል።

💡 ከሄንሪ ማቲሴ በ 500 ዓመት ቀድመን!

የዓለም የጥበብ ታሪክ መጽሐፍት (በተለይ በ 2023 የታተሙት) በዚህ ሥዕል ተገርመዋል። ምክንያቱም፦

ፈረንሳዊው ሰዓሊ ሄንሪ ማቲሴ (Henri Matisse) በ 20ኛው ክፍለ ዘመን ያስተዋወቀውን የ "Collage" እና የዝርዝር መደፍጠጥ (flat design) ስልት፣ የእኛ አባቶች ከ 500 ዓመት በፊት ተጠቅመውበታል።

አውሮፓውያኑ በ "Renaissance" ዘመን ገና የባለ ሶስት ገፅታ (3D) አሳሳልን ሲለማመዱ፣ የእኛ አባቶች ረቂቅ (Abstract) ጥበብ ላይ ደርሰዋል።

"የአውሮፓ አብስትራክት አርቲስቶች እንደ አክሱም ያሉ በረቂቅ ዲዛይን የተቀመሩ ስራዎችን ቢያዩ ምን ይሰማቸው ይሆን? በሺህ ዓመታት ቀድመናቸዋል!"

⚠️ የኋሊት ጉዟችንና የራሳችንን መናቅ

የሚያሳዝነው ግን፣ ይህን የመሰለ የላቀ የፅሕፈት አርት (Calligraphy) እና ስልጣኔ የነበረው ሕዝብ፣ በዛሬው ዘመን በምን ተዓምር አብዛኛው መሐይም (መፃፍ ማንበብ የማይችል) ሆኖ ወደ "መሰረተ ትምህርት" ተመለሰ? የሚለውን ስናስብ ነው።

ስህተታችን ፦ ዘመናዊነትን ከውጭ ፍርፋሪ ፍለጋ ጋር አቀላቀልነው።

ውጤቱ፦ የራሳችንን የከበረ ጥበብ አርክሰን፣ የሰው ተውሶ የምንኖር "ተንሳፋፊ" ትውልድ ሆንን።

🛡️ ታሪካችንን እንጠብቅ!

አንዳንድ ጸሐፍት "ኢትዮጵያውያን ይህን ሊሰሩት አይችሉም፣ የውጭ አገር ሰዓሊዎች ተቀጥረው ነው" ይላሉ። እውነታው ግን ላሊበላም ሆነ እነዚህ የብራና ስዕሎች የአባቶቻችን የላብና የጥበብ ውጤቶች ናቸው።

እኛ ለዓለም ያስተማርን፣ ዓለምን የቀደምን ነበርን! ዛሬ ቁልቁል ብንወርድም፣ የዓለም ጉዞ ገና አላበቃም። ልጆቻችን ከዚህ የታሪክ ቁጭት ወጥተው፣ የራሳቸውን መነሻ አውቀው ለክብር እንደሚበቁ ተስፋ እናደርጋለን።

© አሳፍ ኃይሉ

@ethale
9🔥6
🔥133🥰3
የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የሀገረ አሜሪካ ህዝብ በዋናው አውራ ጎዳና ላይ በሰልፍ በመውጣት ንጉሡ ነገሥቱ እንኳን ደህና መጡ በማለት የክብር አቀባበል ሲያደርግላቸው የተነሱ ፎቶዎች ነው።

ግርማዊ ጃንሆይ እና የአሜሪካ ፕሬዝዳት ጆን ኤፍ ኬኔዲ (በሊንከን ሜሪኩሪ ኮንቲኔንታል ፕሬዚዳንታዊ ሊሙዚን) ሞዴል መኪና ላይ ሆነው ከኒውዮርክ ጎዳና ወደ ፔንስልቬንያ ጎዳና ላይ እየተጓዙ ለህዝቡ ሰላምታ ሲሰጡ ይታያል።

ህዳር 12 ቀን 1956 ዓ.ም
ዋሽንግተን ዲሲ

@ethale
🥰53👍1🔥1🎉1