ኢትኤል
2.28K subscribers
97 photos
11 files
8 links
ስለ ጥንታዊው የኢትኤል ስልጣኔ እናወራለን! እንዘምራለን!
Download Telegram
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!!!

ጥንታዊ የኢትዮጵያ መስቀሎች

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️
🥰1
የምስራች!

ለመጀመሪያ ጊዜ በግዕዝ ቋንቋ ከአንደኛ እስከ አሥረኛ ክፍል የማስተማሪያ መጻሕፍት እየተመረቀ ይገኛል ! በሀገርም በቤተ ክርስቲያንም ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በግዕዝ ቋንቋ ከአንደኛ እስከ አሥረኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የሚውል 10 የማስተማሪያ መጻሕፍት ታትሞ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 20 ቀን 2015 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ እየተመረቀ ይገኛል።

የመጽሐፍቱ ዝግጅት 15 ዓመታት እንደፈጀ የመጻሕፍቱ አዘጋጅ የሆነችው መምህርት ኑኃሚን ዋቅጅራ ለተ.ሚ.ማ በሰጠችው ቃለመጠይቅ ገልጻለች።እስከ 12ተኛው ዘመነ መንግስት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ የነበረው የግዕዝ ቋንቋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአደራ እናት ሆና ጠብቃ አቅፋ የያዘችው እና እየተገለገለችበትም ነው ያለችው መምህርቷ የግዕዝ ቋንቋ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ብቻ እና የአንድ ማኅበረሰብ ብቻ ተደርጎ የሚታሰበው ልክ አለመሆኑን ገልጻ ዛሬ ላይ ያጣነውን ማንነት ለማግኘት ወደ ትላንት መመለስ አለብን ስለዚህም ሁሉም ሰው እና ታዳጊ ህፃናት የግዕዝ ቋንቋን እንዲማሩ ታስቦ መጻሕፍቱ ታትመው መመረቃቸውን መምህርቷ ገልጻለች።

መምህርት ኑኃሚን አክላም "ሁሉም ሰው በመጻሕፍቱ እንዲማር እና የግዕዝ ቋንቋን እንዲያውቅ መልዕክት አስተላልፋለች።በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ጨምሮ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፤ መምህራነ ወንጌል እንዲሁም ዘማርያን ፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።

መምህርት ኑኃሚን ዋቅጅራ በስፔሻል ኒድ የመጀመሪያ ዲግሪ ከዲላ ዩኒቨርስቲ ፣ በነገረ መለኮት የመጀመሪያ ዲግሪ ከቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በግዕዝ ሥነ ድርሳን በማስተርስ ዲግሪ ተመርቃለች።


@ethale
አጼ ዘረ ያዕቆብ በወርቅ ቀለም ያስጻፏት የብራና መጻሕፍ።በጥንታዊት ኢትዮጵያ በወርቅ እንደ ምድር አሽዋ የነበረበት ደግ ዘመን።ስለ ግሸኗ ተዓምረ ማርያም ያልተነገሩ ምስጢሮች ....በእንባ መጻሕፍ ያስጻፉት ንጉስ...በወርቅ ቀለም የተሰሩ አብያተ ክክርቲተያኖችናሌሎች ያልተሰሙ ታሪኮች አዲስ በከፈትነው የዩቲዮብ ቻናል ይዘንላችሁ መጠናል ሀሳብ አስተያይታችሁን አጋሩን ።ሌሎች ዝግጅቶች እንዲደርስዎ subscribe ያድርጉ።


https://youtu.be/H8HPn8gIuSs
👍2
Channel photo updated
ቤተ ክርስቲያኔን ሳያት ኢትዮጵያን ዐያታለሁ!

ኢትዮጵያን ኦርቶዶክሳውያን የበለጠ የሚወድዷት በነገረ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአግባቡ ስለምትጠቀስ ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያኔን ሳያት ኢትዮጵያን ዐያታለሁ፡፡ እንኳን እና ኦርቶዶክሳውያን ቀርቶ ሌሎች መጽሐፍ
ቅዱስን የሚመለከቱ ሁሉ ኢትዮጵያን ያዩአት ዘንድ ይገደዳሉ፡፡

ኢትዮጵያ ጉልኅ ናት፣ ኢትዮጵያም ምስጢር ናት፡፡ ኢትዮጵያን አጉልታ የምታሳየኝ ቤተ ክርስቲያኔ እንደኾነች ሁሉ ምስጢርነቷንም የምትተረጉምልኝ ቤተ ክርስቲያኔ ናት፡፡ ኢትዮጵያዊነትን ኹለት ጊዜ ተቀብያለሁ፡፡ አንድ ጊዜ ከአባቴ አብራክ ከእናቴ ማኅፀን ስከፈል ሌላ ጊዜ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጥምቀት ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ስወለድ፡፡ እናም የሀገሬን ነገር ከቤተ ክርስቲያኔ ልነጥለው አልችልም፡፡ ታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ ከብሉይ እስከ ሐዲስ ሳይታክት የሚያነሣሣትን የቅድስት ሀገር ነገር ትቼ መኖር አልፈልግም አልችልምም፡፡


የመጀመሪያው መጽሐፍ የመጽሐፈ ሔኖክ ሀልዎት ያለ ኢትዮጵያ ምሉዕ አይደለም፡፡ የአበ ብዙኀን አብርሃም ታሪክ ያለ ኢትዮጵያ ከዳር አይደርስም፡፡ የሊቀ ነቢያት መጻሕፍተ ኦሪት ዘፍጥረት፣ ዘጸአት እና ዘኁልቊ ያለ ኢትዮጵያ ይጎድላሉ፡፡ የቃል ኪዳኑ ታቦት ታሪክ ኢትዮጵያ ካልገባችበት ዝርው ይኾናል፡፡ የሊቀ ነቢያት ሙሴ ሕይወት ከኢትዮጵያ ጋር ካልተቆራኘ ይጎድላል፡፡ ገና እንደተወለደ እናቱ በሣጥን አድርጋ የዓባይ ወንዝ ላይ ስትጥለው የሚጀምረው ታሪኩ ኢትዮጵያዊቷን ሲጳራ የትዳር አጋሩ እስከማድረግ ይቀጥላል፡፡ በኢትዮጵያዊው ካህን ምርጥ ትምህርት አስተዳደሩን እንዳቀና ካላወቅን እንዴት የመጽሐፍ ቅዱስ ወዳጆች እንባል ዘንድ እንችላለን?

ቅዱስ ዳዊት በምጡቅ መዝሙሩ፣ ቅኔው እና ትንቢቱ ኢትዮጵያን ከፍ አድርጎ ይሞሽራታል፡፡ መጻሕፍተ ነገሥት ኢትዮጵያን ከፍ አድርገው ካላሳዩ አይኾንላቸውም፡፡ የጠቢቡ ሰሎሞን ዜና መዋዕል ኢትዮጵያን ካላነሣ ያነክሳል፡፡ ከዐበይት እስከ ደቂቀ ነቢያት ኢትዮጵያ የትንቢታቸው ማዕከል ናት፡፡ ነቢየ ልዑል ኢሳይያስን ጠይቁት ነቢዩ ሶፎንያስን ወይም ነቢዩ ዕንባቆምን፡፡ ነቢዩ ኤርሚያስ ከኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ ታሪክ አንፃር ኢትዮጵያን እንዴት ቀሽሮ እንደገለጣት እንጠይቀው፡፡ ትንቢተ ኤርሚያስ ያለ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ አድራሻውን ያጣል፡፡ ወንጌለ ክርስቶስ ልደተ ክርስቶስን ሲያመጣው እዚያ
ውስጥ ኢትዮጵያ በደርዝ ገብታለች፡፡

ከሰብአ ሰገል አንዱ ኢትዮጵያዊ ነውና! ጌታም በንግሥተ አዜብ ወይም በንግሥተ ሳባ እርሷም ንግሥት ማክዳ በተባለችው አድርጎ የምድር ዳርቻ ሲል ይጠቅሳታል፡፡ ቅዱስ ሉቃስም ግብረ ሐዋርያትን ሲጽፍ የኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ እምነት ከኦሪት እስከ ሐዲስ ተንትኖልናል፡፡ እምነቱም በቅዱስ ጴጥሮስ እምነት መጠን እንደኾነ እጥር ምጥን አድርጎ ጽፏል፡፡ የዓለም ድኅነት ሕገ ልቡና፣ ሕገ ኦሪት፣ ሕገ ወንጌል ያለ ኢትዮጵያ መልክ ያጣል፡፡ እኛም እግዚአብሔር አድሎን አዚህች ሀገር ተወልደናል፡፡


ሀገረ እስራኤል ያልተመቻት ታቦተ ጽዮን መሥዋዕቷ ወደ ሰመረላት ኢትዮጵያ መጥታ ማረፊያ አግኝታለች፡፡ ለአማናዊቷ ጽዮን ድንግል ማርያምም የስደቷ ማረፊያ የኾነችው ይህችው ቅድስት ሀገር ናት እኮ፡፡ ጣና ከእነ ስሙ ጣና ቂርቆስ ገዳሙ ይናገረዋል ይህንን፡፡ በእስራኤል ከኖረችው ይልቅ በኢትዮጵያ የኖረችበት ዘመን ይልቃል፡፡ ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ጠቢቡ ሰሎሞን ለ፮፻ ዓመታት ብቻ የቆየች ሲኾን ይኸው ለ፪ሺህ ፱፻ ዓመታት በኢትዮጵያ ናት፡፡ አምስት እጥፍ ያኸል ጊዜ በኢትዮጵያ ኖራለች፡፡ ዓለም አድራሻው የጠፋበት የመስቀለ ክርስቶስ ግማዱ የት ነው? ከተባለ ኢትዮጵያ ነው ሀገሩ፡፡ ሌሎቹ ወይ ታሪኩ ጠፍቶባቸዋል ወይ ተሰውሯቸዋል፡፡ ዓለም ስለመስቀሉ ዝምተኛ ሲኾን ተናጋሪ መልእክተኛ ኾና የተሰየመችው ኢትዮጵያ ብቻ ናት፡፡ እናም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኢትዮጵያን በፍለጋ ሳይኾን በስፋት በደመቀ ታሪክ በጎላ ዕውቀት እናገኛታለን፡፡

ከቤተ ክርስቲያን ከቅጽሯ ስትደርስ ብቻ ሳይኾን ከሩቅ ጉልላቷን ስታይ ደወሏን ስትሰማ ኢትዮጵያዊነት ከላይ እስከ ታች እንደ ጠበል ይፈስስብሃል፡፡ አምስቱ ፊደላት እንደ አምስቱ አዕማደ ምስጢራት የሚተረጎምልህ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው፡፡ የሰንደቅ ዓላማዋ ትርጉም የሚገባህ ቤተ ክርስቲያን ስትኖር ነው፡፡

ኢትዮጵያ ያልተፈተተች ሥረ ወጥ፣ አመንዝራነትን የተጸየፈች ግን በሕግ እየኖረች ወላድ ደግሞ ተፈትሖ ማኅፀን የሌለባት ድንግል፣ መከፈት መዘጋት ሳይኖርባት የምታስገባ የምታስወጣ፣ ምስጢረ መለኮትን በልቧ የምትጠብቅ ምስጢረኛ፣ የእግዚአብሔር ሦስት አዝማናት ብቸኛ ምሥክር መኾኗን የነገረችኝ ቤተ ክርስቲያኔ ናት።ኢትዮጵያ ብዬ የምጽፍበትንም ፊደል የሰጠችኝ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡አባይ ነህ

አንድ ሲኖዶስ ~ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስያን ቅዱስ ሲኖዶስ

• አንድ መንበር ~ መንበረ ተክለ ሃይማኖት

• አንድ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ

• አንዲት ሃገር… ኢትዮጵያ 💚💛❤️

"…ሐዋርያት በሰበሰቡአት በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን" ጸሎተ ሃይማኖት

⚫️ @ethale ⚫️
4👍4👏1
መፅሐፈ ፍልስፍና ሥጋዊ ወመንፈሳዊ.pdf
17.3 MB
ከመቶ ሀምሳ ዓመት በፊት የአጼ ቴዎድሮስ ጸሐፌ ትዕዛዝ የነበሩት አለቃ ዘነብ ኢትዮጵያዊ አማካኝነት የተጻፈ ድንቅ የፍልስፍና መጻሕፍ ነው።

@ethale
@ethale
@ethale
8👍3
ፍኖተ ጥበብ.pdf
3.5 MB
በየኔታ አስረስ የኔሰው የተጻፈ ስለ ግዕዝ ፊደላት እና ስለ ዘመን አቆጣጠራችን ልጆቻችን ሊያውቋቸው የሚገቡ አጠር ያሉ ማብራሪያዎችን የያዘች መጽሐፍ ናት።

@ethale
@ethale
@ethale
👍2
ኢትዮጵያን አፋልጉኝ
💚💛❤️

ሠላም ለኪ ፅዮን ሆይ
እባክሽ የዛሬን ታደጊኝ
ኢትዮጵያን አፋልጊኝ
ያቺ የፍቅር ዋዕይ
ያቺ የምህረት ራዕይ
ያቺ የፃድቃን ደብር
ያቺ የትንሣኤ ግብር
ያቺ የዘመን ኪዳን
ያቺ የታሪክ አስኳል
ያቺ ዘንፋላ እመቤት
የልቧ የአንጀት ጎረቤት
ያቺ የአምባ ላይ ዋርካ
ያቺ የጎራው ሰገን
ያቺ የሞፈር ወገን
ያቺ የቡራኬ ማዕድ
ያቺ የፅናት አዕማድ
ያቺ ሦስትጉልቻ
ያቺ የጥርስ እንጎቻ
ያቺ የትንቢት መድብል
ፀዳለ ሰማይ ዐይን እንክብል
ያቺ የብቃት ደውል
ያቺ የእምነት ፅናፅል
“ ሀ “ ብላ በ ሀ ግዕዝ “ ፐ “ ድረስ
እምታስቀጽል
ምን አገኛት ኢትዮጵያዬን ?
አልታይህ አለኝ ፊቷ
አልገለፅልህ አለኝ ትውፊቷ
አልለይህ አለኝ ወንፊቷ
አላደርስህ አለኝ ግፊቷ
ፅዮን ሆይ አደራሽን የሷን ነገር
ብቻዬን ምንም ነኝ ምንም
እንኳን ልናገር የማልጋገር
የአባይ ና ጣና ቋጠሮ
የግማደ መስቀሉ ቀጠሮ
የቤተ - ዛጉዬ አለት እንድምታ
የፀጥታውስጥ ቅኝት - የዋይታ ማህል
ዝምታ
የፊደል የቀለም ቅይጥ
የውህደት ማህቶት ነፀብራቅ
በሞት ውስጥ ያለች መወለድ -
በምዕራብ ሙክራብ ውስጥ ያለች
ምስራቅ
የእረኛው ዋሽንት የሩቅ ጥሪ
የአዳኝ ክራር ስግትሪ
ሲማር - እንደ አሮን - እምቢ ሲል በሙሴ
በትር
የአዕዋፍ የአራዊት ሠራዊት
በአንድ ደግሞ እንደ ዳዊት
አንድ አዝምሞ እንደ ሸዊት
ላይጥለው ላይጎነጥለው
ያገር ያለህ ሲል - ሲያስመነጥለው
አቆልቋዮን በሠዓቱ
የአስራት ስፍሩን በበዓቱ
ያራስ ጥሪው ማህበር ጥዋው
ጠግቦ ሲያድር ሠማይ ህዋው
እኛን ዛዲያ ምን ይበጀን
መጀን ያልነው እያስፈጀን
የታመንለት ካልዋጀን
ምን ይበጀን ?
እናቴ ፅዮን
አንችና እሷ መሀል ያለው ሠነድ
በሲዖል እቶንም አይነድ
የፋኖ ዝናር ስናድር
የፈሪ ቤዛ ግድር
ኢትዮዽያን አንዳች ነገር
ውል ያልለየለት ተጠናውቷት
ጀንበር ነጎደ ትቷት
ቋሚው አጥንት ማገሩ ጎድን- አንድ ላይ
ታስሮ
ጅብ ሊጋልበው እርጥብ ጋን ሠብሮ
ቀን እያቦካ - ሌት እየከካ ቢገረድፈው
እንኳን ለቋቱ ለመጅ ተረፈው !
ወ - ስብሃት ለእግዚአብሔር

ባለቅኔው ሙሉጌታ ተስፋዬ


@ethale
@ethale
@ethale
👍133
👍7
Channel photo updated
የሐበሻ የጦርነት ጥበብ

THE ART OF WAR የተሰኘው እድሜ ጠገብ መፅሀፉ ከክርስቶስ ልደት በፊት ተፅፎ ከክርስቶስ ልደት በኋላም ላሉ ጦርነቶች መራሄ ሆኗል። በርግጥ መፅሀፉ ከጦርነት አልፎ ለበርካታ የቴክኖሎጂ
ካምፓኒዎችም መነሳትና መመንደግ አገልግሏል።

'ሳን ዙ በመፅሀፉ ያነሳቸው በርካታ ምክሮች የድል መንገድ ናቸው' እያሉ መመሪያውን የተጠቀሙ የጦር አበጋዞችም ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። ለብዙዎቹ የጦር አዛዦች መፅሀፉ ከሼልፋቸው ይልቅ
ለጠረንጴዛቸው ቅርብ ነው።

እኔ ግን እላችኋለሁ በእኛ በሀበሾች ሽለላ፣ ቀረርቶና ፉከራ (war song) ውስጥ ያሉ መልእክቶች ሳን ዙ ከፃፋቸው ሀሳቦች ጋር
አቻ ይሆናሉ።ስነቃሎቻችንን ስላልተረዳናቸ፤ ተረድተንም ስላልተነተናቸው ተንትነንም የሼልፍ ሸክም ከማድረግ ስላላሳለፍናቸው እንጂ ሀገር በቀል የጦርነት ጥበብ በነበረን፤ ለዚህኛው ትውልድም የነአድዋ
ድል ምክንያት ጭላንጭል በተገለጠልን ነበር።

ለአብነቱ ያህል ጥቂት የሳንዙን የጦርነት መርሆችን ከኛ ቃል ግጥሞች ጋር እያነፃፀርን እንይ፦

"ደረሰባቸው ሳይታጠቁ
እንደዝንጀሮ ፀሀይ ሲሞቁ፤"

ጠላት በተዘናጋበትና ባላሰበበት ቅፅበት ደርሶ የጠላትን ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ማድረግ የወገንን ጦር ኪሳራ ይቀንሳል። ድልንም አፍጥኖ ያስሞግሳል። በዚች የቃል ግጥም ውስጥ ጠላትህ እንደማትደርስበት አስቦ አንዴ ደረቱን አንዴ መቀመጫውን
እያገላበጠ ለፀሀይ በሰጠበት ጊዜ ደርሰህ አበራየው የሚል ምክርም አለ።

ሳን ዙም በምክሩ እንዲህ ይላል "...ጠላትህ ባልተዘጋጀበት ጊዜ
ውጋው..." (በርግጥአንድን ጠላት ታጥቂያለሁ ታጠቅ ሳይሉ መውጋት
በሀበሻ ልማድ ነውር ነው። ግን ታጥቂያለሁ ታጠቅ ከተባለ በኋላና ጦር ከተሳለ ጋሻ ከተራገፈ በኋላ እንዲያ ብሎ ነገር የለም)
ሳን ዙ በሌላ ምክሩ "...እሩቅ ሆነህ ሳለ ቅርብ፤ ቅርብ ሆነህ ሳለ እሩቅ ምሰል..." ይላል። የኛዎቹ ጦረኞችም ደጋ ሲባሉ ቆላ ቆላ ሲባሉ ደጋ ይገኙና ነው ድል የሚቀዳጁት።ለዚህ አይነቱ ሰው ደግም የመወድስ ፉከራ አለው።

"ቆላ ነው ሲሉት ደጋ እሚገለጥ፤
ጥላው ለጠላት የማይጨበጥ።"
የጦር ጠበብቱ ሳን ዙ ".... ስታጠቃ እንደመብረቅ ፍጠን..."

ይላል። ግሩም ምክር ናት። እሱም እንደሚለው በተለይ የጠላት ሀይል ብዙ ያንተ ደግም ትንሽ ከሆነ በብዙ አቅጣጫ በፍጥነት ማጥቃት ይመከራል። ይቺን ሀሳብ ሀበሻው በሁለት መስመር ግጥም እንዲህ ይገልፃታል።

"እነሱ ብዙ ማለት ምንድነው
ፈጥነን እንሂድ ድሉ የኛ ነው፤"
ሀበሻ ሲፈልገው ይቺንው ግጥም ቤት መድፊያ ስንኟን ብቻ"...እንግጠማቸው ድሉ የግዜር ነው..." ብሎ ይቀይርና በፈጣሪ መተማመኑንም ይነግርሀል።(ተለዋዋጭነት የስነቃል አንዱ ባህሪ መሆኑን ልብ ይሏል) በዚህ ብቻ አይበቃውም ሀበሻው

"የሌሊት አውሬ የቀን ጃውሳ
ጠዋት የሚያደርስ ያሞራ ምሳ"
ይልና ምሳን በቁርስ ሰአት የሚያደርስ ፈጣን ሁን ይልሀል።በዚችው ግጥሙ ቀንና ማታ የተለያየ አይነት ባህሪ ይኑርህ ብሎ "..በጦርነት ውስጥ አንድ አይነት አፈፃፀም የለም፤ እንደ ሁኔታው ይለዋወጣል።" የሚለውን የሳን ዙን የጦር መርህም ደርቦ
ይገልጣል።

"...ዛሬ ነገ እያልክ እድልህን አታባክን ..." ይላል ጠቢቡ ሰውዬ።እርግጥ ነው ዛሬ ነገ ማለት ውስጥ ላጥቃ አላጥቃ የሚል መወላወል አለና በዛ መሀል የልብ መፍረክረክ ይመጣል። ያ ብቻም ሳይሆን ጠላትም ጊዜ እንዲሸምትና እንዲደራጅ ወይም እንዲሸሽ ይረዳዋል። ለዛ ነው ሳን ዛሬ ነገ አትበል የማለው። ዛሬ ነገ ሲል ጠላቱ ያመለጠው ሀበሻስ ቁጭቱን እየገለጠ በተራዛማውም ሌላውን ሲመክር እንዲህ አይደል የሸለለው

"ያረባ ወንድ ልጅ እየወላወለ
ሰደደው ጠላቱን ዛሬ ነገ እያለ"
ጠቢቡ "ጠንካራ ሆነህ ሳለ ደካማ፤ ደካማ ሆነህ ሳለ ጠንካራ ምሰል" እያለ ይመክራል። ደካማ በሆንክበት ጊዜ ጠንካራ መስለህ ካልታየኸው በቀላሉ ትጠቃለህ። ጠንካራ በሆንክ ጊዜ ደግም ደካማ መስለሀው የመጣ ጠላትን በውስጡ ያሳደረው ንቀት አግዞህ ብዙ መሰዋት ሳትከፍል ካፈር ትቀላቅለዋለህ።
ይቺንው ሀሳብ ሀበሻ በቀረርቶው እንዲህ ብሎ የገልጣታል።

"አጭር ናቸው ብለው በኛ ላይ መጡብን
ቀጭን ናቸው ብለው በኛ ላይ መጡብን
መች አወቁንና አመል እንዳለብን"
"ጠላትህ ንዴት ካለበት ተንኩሰው፤ ከተረጋጋም እረፍት አትስጠው"
ይላል ሳን።

"ነካካየው ነካካቸው አትስጣቸው ጤና
ምንጊዜም ደህና ሰው አልተባልክምና"
ይላል ደግሞ ያገራችን ሸላይ።



@ethale
👍137🤔2