ኢትኤል
2.28K subscribers
97 photos
11 files
8 links
ስለ ጥንታዊው የኢትኤል ስልጣኔ እናወራለን! እንዘምራለን!
Download Telegram
Forwarded from #LWEQESH-Ethiopia
ኢትዮጵያዊው የህንድ ንጉሥ
በአለማችን ውስጥ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት እና በወታደራዊ ስነስርዓት በቀዳሚነት ከምትጠራው ሀገር አንዷ ህንድ ናት። በስልጣኔ ዘመንም ቢሆንም ህንድ ጥንታዊ ከሚባሉት ሀገሮች ውስጥ ትመደባለች። በዚህም የስልጣን ዘመን የተለያዩ ነገስታት የነገሱባት ሲሆን ለረጅም ጊዜ ከነገሱት ንጉሶች አንዱ ኢትዮጵያዊው ማሊክ አምባር ይገኝበታል። ማሊክ አምባር ትውልዱ በኢትዮጵያ ሐረር ውስጥ የነበረ ሲሆን ገና በልጅነት ዕድሜው በባርነት ለተለያዩ ሀገራት የተሸጠ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት እና ህንድ ይገኝበታል። ህንድ ከገባ በኃላ በአስተሳሰብ እንዲሁም በጦር አመራር ስልት እጅግ በሳል እና ጀግና በመሆኑ የጦር አዛዥ ሆኖ በተለያዩ የቅጥር ጦርነቶች ላይ ተሳትፏል።በመቀጠል ህንድን ከ 1549 - 1626 (፲፭፻፵፱-፲፮፻፳፮) ዓ.ም ማለትም ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ በመምራት ኢትዮጵያዊ የህንድ ንጉስ በመሆን አልፏል።ጀግንነት የአፈራችን ማንነት የራሳችን.... ልወቅሽ ኢትዮጵያ💚💛❤️
👍2
ይህ የጨለማ ጊዜ ያልፋል
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት'ም ያሸንፋል!!!


《. #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !.》

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️
👍4
መጻሕፈ ፈውስ ብራና.pdf
32 MB
ጥንታዊ የህክምና ጥበቦችን የያዘ ብራና መጻሕፍ

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️
ደግነትን ላስተማራችሁን።
በአድዋ ኪዳን ላስተሳሰራችሁን።
ባርነትን ሳይሆን ነፃነትን ላወረሳችሁን።
አንገታችንን ቀና አድርገን እንድሄድ ላስቻላችሁን።
የአሸናፊነት ስነ - ልቦና እንዲነግስብን ላደረጋችሁ።
ለጥቁር የሰው ዘር ነጭን ማሸነፍ እንደሚቻል በቃል'ም በተግባር'ም ላሳያችሁ ለእናንተ ውለታችሁን መክፈል ባንችል'ም ሁሌ በልባችን ዝንት ዓለም ነግሳችሁ ትኖራላችሁ!!! የዛሬዋ ቀን እምዬ ምኒልክ ፣ እቴጌ ጣይቱ ፣ ፊት አውራሪ ገበየሁ ለእኛ ገፀ በረከት ይሆኑ ዘንድ በኢትዮጵያ ምድር የተወለዱባት ልዮ ቀን ናት።

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️
🥰2
የምኒልክ መዝሙረ ዳዊት

ተሰርቆ ወደ ውጭ ሂዶ የነበረው ጥንታዊ የአፄ ምኒልክ መዝሙረ ዳዊት ይህን ይመስላል። መዝሙረ ዳዊቱ የዳግማዊ አጼ ምኒልክ እንደነበረ ያረጋገጡትና ወደ እናት ሃገሩ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ጥረት ካደረጉት ተመራማሪዎች መካከል በፎቶው ላይ የሚታዮት ፕሮፌሰር ስቲቭ ዴላማርተር አንዱ ናቸው።

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️
1
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!!!

ጥንታዊ የኢትዮጵያ መስቀሎች

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️
🥰1
የምስራች!

ለመጀመሪያ ጊዜ በግዕዝ ቋንቋ ከአንደኛ እስከ አሥረኛ ክፍል የማስተማሪያ መጻሕፍት እየተመረቀ ይገኛል ! በሀገርም በቤተ ክርስቲያንም ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በግዕዝ ቋንቋ ከአንደኛ እስከ አሥረኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የሚውል 10 የማስተማሪያ መጻሕፍት ታትሞ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 20 ቀን 2015 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ እየተመረቀ ይገኛል።

የመጽሐፍቱ ዝግጅት 15 ዓመታት እንደፈጀ የመጻሕፍቱ አዘጋጅ የሆነችው መምህርት ኑኃሚን ዋቅጅራ ለተ.ሚ.ማ በሰጠችው ቃለመጠይቅ ገልጻለች።እስከ 12ተኛው ዘመነ መንግስት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ የነበረው የግዕዝ ቋንቋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአደራ እናት ሆና ጠብቃ አቅፋ የያዘችው እና እየተገለገለችበትም ነው ያለችው መምህርቷ የግዕዝ ቋንቋ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ብቻ እና የአንድ ማኅበረሰብ ብቻ ተደርጎ የሚታሰበው ልክ አለመሆኑን ገልጻ ዛሬ ላይ ያጣነውን ማንነት ለማግኘት ወደ ትላንት መመለስ አለብን ስለዚህም ሁሉም ሰው እና ታዳጊ ህፃናት የግዕዝ ቋንቋን እንዲማሩ ታስቦ መጻሕፍቱ ታትመው መመረቃቸውን መምህርቷ ገልጻለች።

መምህርት ኑኃሚን አክላም "ሁሉም ሰው በመጻሕፍቱ እንዲማር እና የግዕዝ ቋንቋን እንዲያውቅ መልዕክት አስተላልፋለች።በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ጨምሮ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፤ መምህራነ ወንጌል እንዲሁም ዘማርያን ፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።

መምህርት ኑኃሚን ዋቅጅራ በስፔሻል ኒድ የመጀመሪያ ዲግሪ ከዲላ ዩኒቨርስቲ ፣ በነገረ መለኮት የመጀመሪያ ዲግሪ ከቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በግዕዝ ሥነ ድርሳን በማስተርስ ዲግሪ ተመርቃለች።


@ethale