ኢትኤል
2.28K subscribers
97 photos
11 files
8 links
ስለ ጥንታዊው የኢትኤል ስልጣኔ እናወራለን! እንዘምራለን!
Download Telegram
« ቻይና ልትጸድቅበት አይደለም! »

በማዕበል ፈጠነ

💚💛❤️

✦ከዐራት ዓመት በኋላ የቻይና ደራሲያን በአማርኛ ቋንቋ ረጅም ልበ ወልድ: ወግና የጉዞ ማስታዎሻ ምናምን ጽፈው ቋንቋውን ይራቀቁበታል። ከዚህ ቀጥሎ ጀርመኖች በግእዝ ቋንቋ መወድስ ይዘርፋሉ። የግእዝ ክሕሎታቸው እየዳበረ ሲሄድ በብራናው የተከተቡ ምሥጢራትን መመርመር ይጀምራሉ። ከዚያስ? በእኔ ግምት "ኁልቆ አእጋሪሃ ለፀሐይ እስራ ወክልኤቱ ምእት" ከሚለው ውስብስብ የፀሐይ አውታር ውስጥ ዘው ብለው ጥልቅ ይላሉ።

✦ ይህን በአኀዝ የተጠቀለለ ፍልስፍና ዐርባ ዓመትም ቢሆን ዘግተው ማፍታታት ይጀምራሉ። ሲደርሱበት ዛሬ በነዳጅ የሚሠሩ የዓለም ቁሳቁሶችን ከሀ እስከ ፈ በፀሐይ ብርሃን ብቻ እንዲሠሩ ያደርጓቸዋል። ያም ማለት በፀሐይ ብርሃን ብቻ የሚበር አይሮፕላን ያመርታሉ። እየቆዩ በአየር ያሉ ደቃይቅ ብርሃናትን ብቻ እየለኩ ከቀዝቃዛ አየር ጋር አስማምተው ፈጣን ፈጣን በሰማይ በራሪ መርከቦችን ያመርታሉ።



✦ ክንፋቸው ከነፋስ አውታር ፍጥነታቸው ከብርሃንና ከነፋስ ሲዳቀል መንኮራኩራቸው ነፋስ መሥመራቸው የፀሐይ አውታር ይሆናል። እኒህ የፀሐይ እግሮች(አውታር) ቀላል ቀላል ነገሮችን መሸከም የሚችሉ ሲሆኑ በአውታራቸው ልክ ቅለትና ክብደት ያለው ቁስ ይሸከማሉ። ያንንም እንደ ካስማ ወጥረው በአውታራቸው ይሸክሙታል።


✦ ካስማ ድንኳኖኝችን ወጥሮ እንዲሸከም አውታሩም በልኩ የተሠሩ ማናቸውንም ቁሳቁስ ይሸከማቸዋል። ይህ ሁሉ የሚመጣው ግን ቋንቋ ከማወቅ ነው። ቻይና አማርኛ ቋንቋን መማር ማስተማር መጀመሯ ልትጸድበት ሳይሆን በኢትዮጵያ ሊቃውንት የተከተቡ ስውራንን ወደ ሥጋዊ ዓለም ለመሳብ ነው። ግን ግእዝ ቋንቋ ማስተማር ብትጀምር ይበልጣት ነበር።
.

《... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !..》

♡┈••✦ #ሼር ✦••┈♡

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
« የምስራች!»

የግዕዝ ትንሳኤ

💚💛❤️

✦በትግራይ ክልል ከ2 ሽህ በላይ ለሚሆኑ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የግዕዝ ቋንቋን በመደበኛ ትምህርት መርሃ ግብር ከዘንድሮው አመት ጀምሮ ለመስጠት እንደ ተዘጋጀ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አብስሯል! ትግራይ አሐዱ ብሎ ስለ ጀመረው ከልብ እያመሰገነ ነገር ግን በመላው ኢትዮጵያ ስርዓተ ትምህርቱ ውስጥ ሊካተት ይገባል።


ግዕዝ
■ሔኖክ ስነ ህዋ የተመራመረበት
■ተዋናይ በቅኔ ሰረገላ የመጠቀበት
■ሊቁ ክፍለ ዮሐንስ የተቀኝበት
■በምስጢር የተሞሉ የብራና መፃሕፍት የተከተቡበት.....
.

《... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !..》
♡┈••✦ #ሼር ✦••┈♡

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
👍2
«ደብረድማህ(ዲማ ጊዮርጊስ)»

💚💛❤️

በዜማ ምሰሶ ÷ በትርጉም ተማግራ፤
ገድ አፋፍ ላይ ቁማ ÷ ቅኔ ምታበራ።
የሊቆች መጠጊያ ÷ እልፍኝ የነበረች፤
"አስኳላ" ገፍትሯት ÷ ጋጥ ሁና ከረመች።

በፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ
.

《... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !..》
♡┈••✦ #ሼር ✦••┈♡

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!
" የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፤የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።"
(ትንቢተ ዕንባቆም 3፥7)


《... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !..》

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
👍1
«አሐሜኔስ ኢትዮጵያዊ»

💚💛❤️

♡┈••✦#share_ሼር_Shere ✦••┈♡


✦ በ1900 ከክርስቶስ ልደት በፊት አሐሜኔስ የተባለ ኢትዮጵያዊ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕላኔቶች እንዳሉ የተናገረ ሰው ነው። ይህ አሐሜኔስ የተባለው ኢትዮጵያዊ 16 ፕላኔቶች እንዳሉ የተናገረ ሲሆን፤ ፀሀይን ለመዞር ስንት ግዜ እንደሚፈጅባቸው፤ በስንት ምህዋር እንደሚዞሩና በውስጣቸው ያሉትን ፍጥረታትን ጽፍል።


#NASA እንኳን አስካሁን እርገጠኛ የሆነው ዘጠኝ ፕላኔቶች እንዳሉ ነው ነገር ግን ገና 7 ፕላኔቶች ይቀራሉ።


✦ አሐሜኔስ መዝገበ ሰማያትና አውደ ከዋክብት የተባለው መፀሀፈ በታወቀው ቦታ ዋልድባ እሚገኝ ሲሆን ይህው መፀሀፍ ደግሞ ጀርመን፣ እንግሊዝ፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ እና አሜሪካ ውስጥ በስርቆት ተወስዶ በሚስጥር ተቀመጦ ይገኛል።


✦ እነዚህም ባለ ሥስት ማዕዘን ድንጋይ ያለስሚንቶና ያለጭቃ ሰው ሊሸከመው በማይችል በትልልቅ ድንጋይ ተነባብሮና ተደራርቦ በሚያስደነቅ ሁኔታ ታንጿል።የጥንት ስሟም ምሥር የተባለችውም ግብጽ ኢትዮጵያኖች ለመጀመሪያ ጊዜ ምሥርን ስላበቀሉባት ምሥር እየተባለች ትጠራ ነበር።


✦ ኢትዮጽያ ውስጥም እንደ ምሥር/ግብጽ/ሀውልቶች/ ከብዙ ድንጋዮች ሳይሆን ከአንድ ወጥ ድንጋይ የተሰሩ 700 ፒራሚዶች 600 የአክሱም አይነት ሀውልቶች ከነ ቤተመንግስታቸው እና በዙ የላሊበላ አይነት ሀውልቶች ይገኛሉ። ይህም አንድ ግዙፍ ከተማ ማለት ነው።


✦ ነገር ግን እነዚህን ሀውልቶች ኢትዮጵያኖች አስቀብረዋቸዋል። እነዚህም ከተማዎች የጥንቷን ኢትዮጵያ ጥበብ ሸክፈው ይዘዋል። እነዚህን ሀውልቶች የት እንደሚገኙና በስንት ሜተር እርቀት ቆፍሮ ማውጣት እንደማቻል ዋልድባ ባለው መዝገብ ላይ እሚገኝ ሲሆን፤ ገር ግን ጊዜው እስኪደርስ በሚስጥር ተይዟል።


✦ ለምሳሌ ያህል ደግሞ በቅርቡ በቁፍሮ የወጣውን የዳግማዊ ላልበላን ሀውልት ማየት ይቻላል። ዮሐንስ በራዕዩ ሲከፈት ያየው ቤተ-መቅደስ እነዚሁ የላልበላን ሀውልቶች እንደሆኑ አባ ተስፍ ስላሴ ሞገስ ያስረዳሉ።


✦ እንደ ምንጭነት የተጠቀሰውም የምሥጢሮች ሁሉ ቁልፍ የሆነው መፀሀፈ ምሥጢር ዘአዶናይ ራፍኤል ሲሆን ይህም መፀሀፈ እጅግ በጣም ብዙ ምሥጢሮችን የያዘ ሲሆን መፀሀፍ ሙሉ በሙሉ ቢተረጎም እጅግ በጣም የሚያሥፈራና አስደንጋጭ ታይቶና ተስምቶ የማይታወቅ ከሰው ልጆች በላይ የሆነ ምሥጢር አለው፤ ሁሉም ነገር እንደ ፈጣሪ ፋቃድ በጊዜው ይሆናል።የተለየ መንፈሳዊ አይን ያለው ሰው ግን አሁንም እነዚህን የፒራሚድ ከተሞች መመልከት ይቻላል።
[በድጋሜ የተለጠፈ]

📚 ምንጭ፦ የሊቁ አባ ተስፍ ስላሴ ሞገስ መፃሕፍት
.

《... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !..》

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
👍2
«የቃል ኪዳን ምድር»


💚💛❤️


✦ << እነርሱም፡ ከተስፋቸው ከኢትዮጵያ፡ ከትምክሕታቸውም፡ ከግብጽ የተነሣ ይፈራሉ ያፍሩማል" (ኢሳ. ፳፥ ፭)s።


#ቶማስ ሙር እኮ ዮቶጵያ ያላት እንዲሁም ፕሌቶ አትላንቲስ ያላት የቃል-ኪዳን ምድር ኢትዮጵያ ናት። #ፍራርሲክ ቤከን እኮ "ዘ ኒው አትላንቲክ" ያላት በኋላም ፕሮክለስ የተባለ 415-482 ዓ.ም የነበረ እንዲሁም የፕሌቶን አስተሳስብ የቀረፀ ሰው እንዲህ ይለናል "ፕሌቶ አትላንቲስ ፍፁማዊ አገር የሰላም አገር የፍቅር አገር :የበረከት አገር ያላት ፊክሽናል አለም ሳትሆን #የኢትዩጵያ_ግዛት ነው" ብሎ ያኔ ፅፋታል።>>



✦ ኢትዮጵያ የቃል ኪዳን ሀገር ስለሆነች፣ የሚገነቧት ይገነባሉ፣ ሊያፈርሷት የሚሞክሩ ደግሞ ይፈርሳሉ" ይለናን ቀሲስ ዶ/ር ዘበነ ለማ ሰሞኑን ሰይፉ ጋ ባደረገው ቆይታ እጅግ ደስ የሚል ቆይታ ቢሆንም አንዳንዶች ግን ኢትዮጵያ የቃልኪዳን ሀገር አይደለችም ይላሉ እውነት ግን አይደለችምን እስቲ ከዚህ በታች ያሉ የተለያዩ ማስረጃዎችን እንመልከት:-



✦ በጥንት ልደተ ክርስቶስ የፐርሻዎ ንግስት እኮ ኢትዩጵያን ለመውጋት ዘምታ ጦሯን አስጨርሳ ተመለሰች ይላል ።ታላቁ እስክንድር 127 ሀገራትን ሲገዛ ኢትዩጵያን አልገዛም።ንግስት ማክዳ እኮ ጠቢቡ ሰለሞንን የጠየቀች ጠቢብ ነች።



✦ ኢትዮጵያ በግብፅ 18 የነገስታትን አንግሳለች። ሜምኖን የተባለዉ ኢትዮጵያዊ የግብፅ ንጉስ ከ1320 አ.አ እስከ ሴፕዩምስኬኩረስ 170 አ.ም የቆመ ሀዉልት እንደነበረዉና ሀዉልቱም ጠዋት ጠዋት ፀሀይ ሲያርፍበት የክራር ድምፅ ያሰማ እንደነበር ሄሮዱተስ በፓፒረስ ወረቀት ላይ አስፍሮት ይገኛል።



✦ ከማንም አገር ያልተዳቀለ የራሳችን የሆነ ይህም ብቻ ሳይሆን ለዓለም ፊደላት መሰረት የሆነ ፊደል፣ አሀዝ፣ የቀን መቁጠርያ ለአለም የሠጠች።ከአለም መጀመሪያ እግዚያብሔርን ስታመልክ የኖረች እስከ አለም መጨረሻ የምትኖር እና የምታሳምን ኢትዮጵያ ናት ምክንያተም የቃል-ኪዳን ምድር ናት።



✦ ከአራራት ተራራ ግርጌ ከግዮን መፍለቂያ ጀምረው ሜዴትራንያንን ተሻግረው እስከ የመን ድረስ ሰፊ ግዛት የነበራቸው የዛሬዎቹን የአትላንቲክና የሕንድ ውቅያኖሶችን ጨምሮ መላው አፍሪቃን በስማቸው የሰየሙ።ውቅያኖስን አቋርጠው በዛሬዎቹ አማሪካና አውሮፓ : ኢስያን ቀድመው የሰፈሩ።



✦በጥንት ስሟም ምሥር የተባለች የምትጠራዋን ግብጽን ኢትዮጵያኖች ለመጀመሪያ ጊዜ ምሥርን ስላበቀሉባት ምሥር እየተባለች እንጥትጠራ ያደረጉ። #ኢትዮጵያ ከሌሎች የዓለም ሀገራት በተለየ የምስጢራት እና የጥበባት መገኛ ነች ፡፡ ለዚህም ዋንኛው መንስኤ በምድራዊ ሰማያትና በሰማያተ ሰማያት በሚገኙት መላእክት ቅዱሳን አባቶች ብሎም የአዳም ልጆች መካከል ግንኙነት ከሚፈጠርባቸው በምድር ላይ ከሚገኙት ሰባቱ የክብር ቦታዎች መካከል አራቱን ይዛ መገኘቷ ነው፡፡



✦ሀገራችን ኢትዩጵያ ብዙ የመከራ ጊዚያት እንደምታሳልፍና ንጋት እንደሚመጣ አስቀድመው በማየት ለብዙዎቻችን ተናግረዋል፣ ጽፈዋል፣ በየበረሀውም ጩኸዋል። ብዙ ቅዱሳንም ከፍ ከፍ ያሉት እንደሚወርዱ፣ ዝቅ ዝቅ ያሉትም ከፍ እንደሚሉ፣ የወጡት እንደሚገቡና የገቡትም እንደሚወጡ በምልክት አይተው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አምላክ አገራችንን አይጥላትም ።


✦ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃ የኖረችው ረጅም ወንዝ ስላለን ነው? ተራሮች ስላሉን ነው? አይደለም። በአፍሪካ ከሌሶቶ በላይ ተራራ ላይ የተመሰረተ አገር የለም፣ ከኪሊማንጃሮ የሚበልጥ ተራራም የለም፤ ነገርግን ከቅኝ ግዛት አላመለጡም።


✦ኢትዮጵያ ለማጥፋት የሳጥናኤል ልጆች ለ700 አመታት ስትፈተን የነበር እንዲሁም በአድዋ ጊዜ ከሰራዊቱ ጋር ሆኖ የተዋጋ የረዳት እኮ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው።ለምን ካልኸኝ የቃል ኪዳን ምድር ስለሆነች እናቶቻችን “የኢትዮጵያ አምላክ” የሚሉት ጠንካራ አምላክ ስላለን እንጅ በኛ ሀይል አይደለም።


✦ኢትዮጵያ የዓለም መነሻ ነበረች፤አሁንም የዓለም መጨረሻና መደምደሚያ የቃል ኪዳን አገር መሆኗ ገሀድ እየሆነ ነው፡፡ይህንን እኛ ኢትዮጵያውያውያን አናምንም፤አንቀበልም፡፡ሌላው ዓለም ግን አምኗል ተቀብሏል፡፡ "ኢትዮጵያ የቃል ኪዳን ሀገር ስለሆነች፣ የሚገነቧት ይገነባሉ፣ ሊያፈርሷት የሚሞክሩ ደግሞ ይፈርሳሉ" ።


[በምክንያት በድጋሜ የተለጠፈ]

《... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !..》

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
👍21🥰1
💚💛❤️

« ስለ ኢትዮጵያ ሳስብ አልደነግጥም መቼም አልደነግጥም የቆምኩበትን የአባቶቼን መሠረት አውቀዋለሁ። ኢትዮጵያ ባንተ አልተጀመረችም ባንተም አትፈርስም!!! »


ፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ ከ2 ዓመት በፊት የተናገሩት ዘመን ተሻጋሪ ንግግር!


《... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !..》

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
👍2
3ቱ ኢትዮጵያን ሰብአ ሰገድ

💚💛❤️

«ሰብአ ሰገል» ማለት በግእዙ «የጥበብ ሰዎች» ማለት ሲሆን በእንግሊዝኛው ሐዲስ ኪዳን magi ይላቸዋል፡፡በትንቢተ አሞጽ 9:7 "የእስራኤል ልጆች ሆይ! እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን?" ሲል የተናገረው ከጥንት ጀምሮ ኢትዮጵያን እግዚያብሔርን የሚያከብሩ መሆኑን በመረዳት ነው።


በኋላም ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወለድ መዝ 72:9 <<በፊቱም ኢትዮጵያን ይሰግዳሉ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ : የተርሴስና የደሴቶች ነገስታት ስጦታ ያመጣሉ ......................>> የሚለው ትንቢት ይፈፀም ዘንድ ነገስታት ከኢትዮጵያ ተነስተው ሂደዋል።


ታላቁ የታሪክ ምሑር መራሪስ አማን በላይ እንዲህ በማለት ያስረዳሉ <<ከኪቴም ዳርቻ መርከቦች ይመጣሉ፤ ያስጨነቅህን አሦርንም ያስጨንቃሉ፤ ነገር ግን እርሱም ደግሞ ይጠፋል፡፡› ብሎ የተናገረውን ልጁ ደሸት ትንቢቱን ሲከታተል በቀትር ጊዜ ከምንጩ ዳር ተቀምጦ ፍልስፍናውን በአዝዋሪት ውሃ ሲያናና ሲፈለስፍ ለብልአም የታየው ኮከብ እንደገና ለደሸት ታየው የአዝዋሪቱን አረፋ ኮከብ እየተከታተለ ሲጽፍ ድንግል ሴት ያለ ዘር የተወለደ ልጅ ታቅፋ አያት፤ ወዲያውኑ ያየውንና ወደ ድንግሊቱ የመራውን ኮከብ ሥዕል በናስ ሰሌዳ ሥሎና ቀርጾና ድንግሊቱን፣ ልጅዋን እንደታቀፈች በወርቅ ሰሌዳ ሥዕሉን ቀርጾ ለልጆቹ አስቀመጠው


ሊሞት ሲል ‹ይህ ኮከብ የሚመስል በምሥራቅ በኩል ሲወጣ ዐይታችሁ፤ ጨረሩን ወደሚያመለክታቸሁ ምድር ተጉዛችሁ፣ ከምድራችሁ ከምታገኙት ከምታገኙት የምድር አበል ወርቅ፣ እጣን፣ ከርቤ፣ ልብስ ይዛችሁ ይህን አምላካችን ለአባታችን ለአዳም ለሔዋን እዲሰጣት የሰጠውን፣ አብርሃም ለአባታችን ለመልከጼዴቅ አሥራት ብሎ የሰጠውን እንአርያ በክብር ይዛችሁ፣ የኮከብ ብርሃን ለስግደት ሰግዳችሁ ስጡት፤ ሉልና ዮጴ የወርቅ ሃመልመላል ለእናቱ ስጡለት፤ ይህ እስከሚሆን ድረስ እንቆ አርያውን ተመልከቱት፤ እርሃብ ዘመን ሊሆን ሲል መልኩ ይጠቁራል፤ የጥጋብ ዘመን ሊሆን ሲል መልኩ ያበራል፤ ቅባቱ ይጭረቀረቃል ሲል እናተም ማርና ወተት ወደሚስባት ምድር ሔዳችሁ ትኖራላችሁ›


በዚያን ግዜ በደሸት ከተማ በንጅ ጎጃም የሚቀመጠው በተስፋ ሲጠባበቅ የነበረው አጎጃ ጃቦን ዬጵ የሚባለውን የግዮን ቢጫ ወርቅ እንቁዮጳዝን እንቁዮጳ ግዮን የሚባለው ሉል ድንጋይ የወርቅ ሐመልማል ማለት ወርቁን እንደ ሰፌድ ሆኖ የተሰራውን ይዞ በስሩ ሶስት ንጉሶች አስከትሎ ከጣና ደሴት ተነስቶ ኮከቡ ወደ ሚያመለክትበት ምድር ከንጉስ ሙርኖ ጋር እንዲሁም የገዲዳ ልጅ ዲዳ ሰፍ ከዝዋይ ከተማ በተርሴስ ደሴት በዛሬው አፋር የሚቀመጠው የአዜባውያን አዛል የአፍርሴካውያን ንጉስ አጋቦን ; ሜሌኩ እና ከሳባ ከተማ የሚቀመጠው አርስጣ ጋር ሆነው ሆኖ ከወርቅ ሐመልማል የተሰራ መጎናጸፊያ እጀ ጠባብ የሰንደል እንጨት እንዲሁም ንጉሦች በየግመሎቻቸውና በፈረሶቻቸው ከምድራቸው የእህል የወርቅ የከርቤ እና የእጣን ዓይነቶች ልዩ ልዩ የልብሶች ገፀ በረከቶች ይዘው የንጋቱ ኮከብ ብርሀኑን ለሚያመለክታቸው ለሰላም ንጉስ ገፀ በረከት ይዘው ኮከብ ወደ ሚያመለክተው ሀገር ወደ ኢየሩሳሌም በጥንቱ ናግራ ኤደን በዛሬው የመን አድርገው ጉዞቸውን ቀጠሉ።


እነዚህ ንጉሦች ሁሉም ዘውድ የደፉ ናቸው። ለእነዚህ ለአስራ ሁለቱ ንጉሦች የበላያቸው በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አክሱም የሚቀመጠው ንጉሥ ነገስት አፄ ባዜን ነው>>ሲሉ ጽፈዋል።በርካታ የምዕራብያውያን እና የኢትዮጵያን ሊቃውንትም ይህንን ታሪክ ይደግፋታል ለምሳሌ ታላቁ የቤተ ክርስትያን ሊቀ ሊቃውንት አያሌው ታምሩ ይህንን ሀሳብ “የኢትዮጵያ እምነት በሶስቱ ህግጋት” በተባለው መጽሀፋቸው የነዚህ ጠቢባን ስም ሚሊቹር ፣ ማንቲሶራ ፣ በዲዳስፋር እንደሆነ ሲገልጹ የምእራብያውያን የታሪክና የሃይማኖት ሊቃውንት ደግሞ Melichior ,Balthasar and Caspar ይሏቸዋል::( http://ww2.netnitco.net/ ~legend01/wisemen.htm ) ስማቸው ላይ የድምጽ ቅላፅ(pronunciation) ልዩነት ነው እንጅ አንድ ነው።



በርካታ የምዕራብያውያን ሊቃውንትም ያለቃ አያሌውን እንዲሁም የሊቁ መራራ አማን አስተምህሮ ይደግፋሉ:: ለምሳሌ William Leo Hansbery and E Harper Johnson Africa’s Golden Past Historical facts challenging notion that Christianity isn’t religion of West በሚለው ጽሁፋቸው ላይ እንዲህ ሲሉ ያትታሉ...


" it is in general agreed that the reverent visitors were members’ of the order of the Magi and they are usually identified as Caspar king of Ethiopia; Melchior king of Nubia; and Balthazar king of Saba which was for a thousand years the capital city of the African Kingdom… and here too it may be of interest to note the gold, frankincense and myrrh… are all natural product of , and very abundant in, the African regions embraced by Nubia, Ethiopia and Sudan ”


ሰብዓ ሰገል ከአገራቸው ሲነሡ 12 የነበሩ ሲሆን እያንዳንዳቸውም ብዙ ሺህ ሠራዊቶች አስከትለው ነበር ነገር ግን በጉዞ ላይ ሳሉ ድንገት ጦርነት ተነሥቶ አብዛኞቹ ሲያልቁ ገሚሶቹ ደግሞ ወደ የመጡበት ተመልሰዋል፡፡በመጨረሻም 3ቱ ነገስታት ቤተልሔም ደርሰዋል።



📚ዋቢ መፃሕፍት

፩) መራሪስ አማን በላይ ‹የጥንቷ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ታሪክ›መጽሀፋቸው
፪)አለቃ አያሌው ታምሩ“የኢትዮጵያ እምነት በሶስቱ ህግጋት”" " "
፫) https://addisabram.wordpress.com/the-three-wise-men-were-ethiopians/

© ተፃፈ በአስቻለ ካሳሁን
ጣና ዳር ፥ ባሕር ዳር
2011 ዓ.ም

[ከሁለት ዓመት በፊት የተፃፈ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በድጋሜ የተለጠፈ]


《... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !..》

♡┈••✦share_ሼር_share✦••┈♡
💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
👍41