ሰበር ዜና ET🇪🇹
24.6K subscribers
9.15K photos
352 videos
11 files
2.31K links
መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ

ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

@Akiyas21bot


የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇
Download Telegram
የትንሳኤ ሎተሪ ወጣ።

የ2017 ዕጣ ዛሬ በኢትዮጵያ ሎተሪ  አገልግሎት በዕድል አዳራሽ መውጣቱን የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አሳውቋል።

በዚህም ፦

1ኛ ዕጣ ቁጥር 0312160 ➡️ 10,000,000 ብር (አስር ሚሊዮን ብር)

2ኛ ዕጣ ቁጥር 0302606 ➡️ 5,000,000 ብር (አምስት ሚሊዮን ብር)

3ኛ ዕጣ ቁጥር 0269838 ➡️ 2,500,000 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር)

4ኛ ዕጣ ቁጥር 1301182 ➡️ 1,500,000 ብር (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር)

(ሙሉ የዕጣ ማውጫ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል)

ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
ወልቃይት‼️
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ለህወሓት መግለጫ ምላሽ ሰጠ‼️
ትላንትም፣ ዛሬም፣ ነገም አጀንዳችን ሰላም ነው!
ሕወሓት ሚያዚያ 10/2017 ዓ.ም የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞንን የተመለከተ መግለጫ ማውጣቱን ለመረዳት ችለናል፡፡

ቡድኑ በመግለጫው እንደተለመደው ራሱን የሰላም ዘብ አደርጎ በማቅረብ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የሚያደርገውን የሰላምና የልማት እንቅስቃሴ በጸብ-አጫሪነት ወንጅሏል፡፡

ከሕወሓት ጥንተ-ተፈጥሮ አንጻር የወጣው መግለጫና የመግለጫው ይዘት የሚያስገርም ባይሆንም፣ አንዱ ወገን የፈለገውን ተናግሮ ሌላው ጉዳዩን በዝምታ ማለፉ የዚያኛውን ወገን መሠረተ-ቢስ ውንጀላ የእውነተኛነት ገጽታ ስለሚያላብሰው፣ ይህን አጭር ማስታወሻ ለማቅረብ ተገደናል፡፡

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሕዝብ የትላንትም፣ የዛሬም፣ የነገም መሪ አጀንዳ ሰላምና ሰላም ብቻ ነው፡፡

በሕወሓት የግፍ አገዛዝ ለ27 ዓመታት ሲማቅቅ፣ ሲገደልና ሲፈናቀል ለኖረው ሕዝባችን ሰላም ልዩ ትርጉም ያለው ነው፡፡ ስለሆነም ሰላሙን ለማረጋገጥ ያለ እንቅልፍ ይሠራል፣ ይተጋል፣ ያተጋል፣ ለአማራዊ ማንቱ ዘብ ሁኖ ይቆማል፡፡

መላው የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሕዝብ ራሱን በሰላም አስከባሪነት በማዘጋጀት የራሱንና የአካባቢውን ውስጣዊ ሰላም ከሰርጎ ገቦች፣ ከወያኔ መንገድ ጠራጊ ኃይሎች፣ ከባንዳዎች ሲጠብቅ ቆይቷል፡፡ ወደፊትም ይቀጥላል፡፡ የተከዜ ዘብ፣ የሰላም ዘብ ሲሆን በዞኑ ሕዝብ የተዋቀረ የዞኑ ሰላም አስከባሪ እንጂ የማንንም አልፎ የማይጠይቅ፣ የራሱን ማንነት አሳልፎ የማይሰጥ እና የጠባ-ጫሪነት አጀንዳ የሌለው ኃይላችን ነው ፡፡

ሕወሓት ከወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን እንዲወጣለት የጠየቀው የዞኑን ሕዝብ ነው፡፡ በርግጥ ከፍ ብሎ እንደተገለጸው፣ ለእኛ ሕወሓት ይህን ማለቱ ፈፅሞ አያስገርመንም፡፡

ሕወሓት ከጥንት እስከ ዛሬ የማያከብረውን ሕገ መንግሥትና ፌዴሬሽን ደግሞ ደጋግሞ የሚጠቅስ፤ የማያምንበትንና የማያከብረውን የፕሪቶሪያ ስምምነት ደግሞ ደጋግሞ የሚያወሳ ቡድን እንደሆነ አሳምረን እናውቃለንና፡፡

ስለሆነም ሕወሓት የሚፈልገው የወልቃይት ጠገዴን ሕዝብ እንደለመደው ከርስቱ አፈናቅሎና ጨፍጭፎ የአማራ ርስት የሆነውን የወልቃይት ጠገዴን ለም መሬት መጠቅለል እንደሆነ ግልጽ ነው።

ቡድኑ አካባቢውን በጉልበት በወረረበት ዘመን ያደረሳቸው ግፎችና በደሎችም ሆነ በጎረቤት አገር ያሉ ተዋጊዎቹ በወልቃይት ጠገዴ አማራዎች ላይ እያደረሱት ያለው  ማሳደድና መጨፍጨፍ የቡድኑን ፍላጎትና ቋሚ ዓላማ በማያሻማ መልኩ ፍንትው አድርገው የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡

በመሆኑም ከመግለጫው ለመረዳት እንደሚቻለው ወያኔ አጭበርባሪና ቁማርተኛ ቡድን መሆኑን ፀሐይ የሞቀው፣ ሕዝብ ያወቀው ነውና አዲሳችን አይደለም!

የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ዛሬም እንደ ትላንቱ ሕግንና ሕገ መንግሥትን መሠረት አድርጎ ሰላሙንና ነፃነቱን አስጠብቆ ለመኖር ይሰራል፣ ለሀገር ዳር ደንበር በጎ ጠረፍ ጠባቂ ሁኖ ይቀጥላል፡፡

የፕሪቶሪው ስምምነት በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን ያለንን ቁርጠኝነትም ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ ስንገልጽ ቆይተናል፡፡ የስምምነቱ በተሟላ ሁኔታ ተፈጻሚ መሆን፣ ለዞናችን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያዊያን ዘላቂ ሰላም በጣም አስፈላጊ መሆኑን እንገነዘባለንና!

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን
ሁመራ ከተማ
@ET_SEBER_ZENA
ድንገተኛ ሞት‼️
ሁሉም ዜሮ ዜሮ በሚለው ዘፈኑ የሚታወቀው አርቲስት ሰለሞን በዛሬው እለት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል። ኑሮውን በሃገረ አሜሪካ  በአትላንታ ከተማ አድርጐ የነበረው ሰለሞን የፋሲካ በዓልን ከቤተሰቦቹ ጋር ካሳለፈ በኋላ አመሻሽ ላይ ትንሸ ህመም ተሰማችኝ ብሎ ወደ ሆስፒታል እንደሄደና በዛው ህይወቱ እንዳለፈ ተገልጿል።
Via:- መዝናኛ ሚዲያ
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
በሞያሌ ድንበር የንግድ ልውውጥን በ1 ሺህ ዶላር ጣሪያ ሊጀመር ነው‼️
ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለሁለት ዓመታት በዘለቀ ድርድር በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ማዕቀፍ የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥን ለማቀላጠፍ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

በዚህም መሰረት በሞያሌ ድንበር ላይ ለሚደረጉ የሸቀጦች ንግድ የመጀመሪያ ጣሪያ 1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንዲሆን ተወስኗል።

በሞምባሳ የተጠናቀቀው ይህ ስምምነት የንግድ ሂደቶችን በማቅለል የድንበር ማህበረሰቦችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማሳደግ ያለመ ነው ተብሏል።
===================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
አዲሱ ህግ ፀደቀ‼️
ተራ አስከባሪ ግብር እንዲከፍሉ ተወሰነ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የታክሲ ተራ አስከባሪ ማኅበራት ከገቢያቸው 20 በመቶውን ለመንግሥት እንዲሰጡ የሚያስገድድ ደንብ አጽድቋል።

ደንቡ ማኅበራቱ “ዝግ እና መደበኛ የባንክ አካውንት" እንዲከፍቱና ከሁለት ዓመት በኋላ “ወደ ሌላ የሥራ ዘርፍ እንዲሸጋገሩ” ግዴታ ይጥላል።

“የተርሚናል አገልግሎት አሠራርና ቁጥጥር” የተሰኘው ደንብ፣ ኢንተርፕራይዝ በማለት የሠየማቸው ማኅበራት የሚደራጁት በከተማዋ የሥራና ክህሎት ቢሮ መስፈርት መኾኑን ታውቋል።

ኢንተርፕራይዞቹ 30 በመቶ “የግዴታ ቁጠባ” መቆጠብ፣ 50 በመቶውን በተንቀሳቃሽ የባንክ ሒሳብ ማስቀመጥና ያንድ ዓመት ውል መፈረም እንዳለባቸውም ይደነግጋል።
===================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
ከሸፈ‼️
በ#ቡርኪናፋሶ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ ላይ ያነጣጠር ግድያ/Assassination/ ከሸፈ‼️
የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው በርካታ ወታደራዊ አባላትን ያሳተፈ እንደነበር የሀገሪቱ የደህንነት ሚኒስትር ማሃማዱ ሳና አስታውቀዋል።

የሀገሪቱ የደህንነት አገልግሎት ተቋማት የሴራው አካል በሆኑ የቡርኪናቢ ወታደሮች እና የታጣቂ ቡድን መሪዎች መካከል የነበረውን ግንኙነት በመጥለፍ የሚገኙበትን ቦታ እና የወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ዝርዝር ሁኔታ እንዳገኙ ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ላይ የተሴረው መፈንቅለ መንግሥት በመጀመሪያ ሚያዝያ 8 ቀን ለማካሄድ ታቅዶ እንደነበር ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የውጪ ዜጎችን ጨምሮ ዘጠዥ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ከዚህ ጀርባ የፈረንሳይ እጅ እንዳለበት ተዘግቧል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
ሞቃዲሾ‼️
ወደ ሞቓዲሾ እየገሰገሰ የነበረውን የአልሸባብ እንቅስቃሴ ለመግታት የቱርክ መከላከያ ሰራዊትን የያዙ 2 የጦር አውሮፕላኖች ሶማሊያ ሞቃዲሾ አርፈዋል።
በዚህም በመጀመሪያ 500 የቱርክ ኮማንዶ ከስፍራው ደርሰዋል።
ባለፉት ቀናት ውስጥ አልሸባብ በሶማሊያ ጦር ላይ ከፍተኛ የማጥቃት ዘመቻ መጀመሩን ተከትሎ የሶማሊያ ጦር የመፈራረሰ አደጋ ውስጥ መግባቱን የተመለከተችው ቱርክ በሁለት አንቶኖቭ አውሮፕላን 500 ሰራዊት ከበቂ መሳሪያ ጋር ወደ ሞቃዲሾ ልካለች።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
የመውጫ ፈተና‼️
በሰኔ 2017 የሚሰጠውን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ዳግም ለመፈተን እየተጠባበቃችሁ ያላችሁ አመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ሚያዝያ 14 /2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 05/2017 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የመመዝገቢያ ቅፅ https://exam.ethernet.edu.et ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ፈተናው የሚሰጥበት ቀን ወደፊት ይገለፃል ተብሏል፡፡

ፈተናውን ለመውሰድ የብሔራዊ (ፋይዳ) መታወቂያ መያዝ ግዴታ ሲሆን፤ የአገልግሎት ክፍያ (500 ብር) በቴሌብር በኩል ብቻ የሚፈፀም መሆኑ ተገልጿል፡፡
===================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
በኢትዮጵያ "ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለረሃብ" መጋለጣቸውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።

በኢትዮጵያ "ከአስር ሚሊዮን በላይ" ሰዎች በሀገሪቱ "እየጨመረ ላለው ረሃብ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት" መጋለጣቸውን የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።

ድርጅቱ በዛሬው ዕለተ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ፕሮግራሙ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚያከናውነው ሥራ የሚውል ተጨማሪ ገንዘብ በአስቸኳይ የማያገኝ ከሆነ "ለ3.6 ሚሊዮን" ሰዎች የሚያቀርበው "የነፍስ አድን ምግብ" ድጋፍ "በመጪዎቹ ሳምንታት" እንደሚያቋረጥ አስጠንቅቋል።

ተቋሙ ኢትዮጵያ ውስጥ የረሃብ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እየጨመረ የመጣው ሀገሪቱ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ችግሮች ምክንያት እንደሆነ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል።ግጭት፣ ቀጣናዊ አለመረጋጋት እና መፈናቀል ተቋሙ ከጠቀሳቸው ምክንያቶች መካከል ናቸው።

በሀገሪቱ ውስጥ ያለው "ኢኮኖሚያዊ ቀውስ" እና ድርቅ እየጨመረ ለመጣው ረሃብ እና ተመጣጠነ ምግብ እጥረት በምክንያትነት ተጠቅሰዋል። እነዚህ ችግሮች "ሚሊዮኖችን ያለ በቂ የተመጣጠ ምግብ እንዳስቀሩ" የዓለም የምግብ ፕሮግራም ገልጿል።

የተቋሙ መግለጫ፤ "በመላው ኢትዮጵያ ከአስር ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለረሃብ እና ምግብ እጥረት ተጋልጠዋል" ብሏል። ከእነዚህ ሰዎች መካከል "ሦስት ሚሊዮን ያህሉ በግጭት እና በአስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ" እንደሆኑም ጠቅሷል።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያለበትን ደረጃ "አሳሳቢ" ሲል ጠርቶታል። የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያጋጠማቸው "4.4 ሚሊዮን ነፍሰ ጡር እና አጥቢ እናቶች እንዲሁም ህጻናት ህክምና እንደሚያስፈልጋቸው" አስታውቋል።

በ2025 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከሦስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች የምግብ እርዳታ ማቅረቡን የገለጸው የዓለም የምግብ ፕሮግራም፤ ከእነዚህ ውስጥ 80 በመቶው ድጋፍ የቀረበው "ለተፈናቀሉ እና የከፋ የምግብ ዋስትና" ችግር ላጋጠማቸው ኢትዮጵያውያን መሆኑን አስታውቋል።

የዓለም የምግብ ድርጅት በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ ለሚገኙ አንድ ሚሊዮን ገደማ ስደተኞች 60 በመቶ የምግብ ድጋፍ እንዳቀረበ አስታውሷል።
ቢቢሲ
===================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
እሳት‼️
በእስራኤል ከተሞች በከባድ ሙቀት ምክንያት ከፍተኛ የሰደድ እሳት መነሳቱ ተነግሯል‼️
የሰደድ እሳቱ የተነሳው በእየሩሳሌም እና በዋና ከተማዋ ቴልአቪቭ አቅራቢያ ሲሆን እሳቱን ለመቆጣጠር የእስራኤል ባለስልጣናት ኤሊኮፍተሮችን እና የእሳት አደጋ መኪኖችን ወደ ስፍራው በመላክ እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ እያደረጉ እንደሚገኙ ተገልጿል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢኒያሚን ኔታንያሁ በሀገሪቱ የተነሳውን እሳት ለመቆጣጠር ከባድ መሆኑን ገልጸው የሰደድ እሳቱ የሚባባስ ከሆነ እስራኤል ለአጋር ሀገራት እርዳታን ትጠይቃለች ሲሉ ገልጸዋል።
===================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
#Factcheck‼️
ይሄ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ ተመልክተናል።
ይሄ መንገድ የተቆፈረው በአማራ ክልል ውስጥ ሳይሆን Umzinyathi በሚባል በደቡብ አፍሪካ አንዲት ከተማ ውስጥ ሲሆን እነዚህ ሰዎች መንገድ ለመቆፈር የተገደዱት ውሃ እና መብራት አልገባልንም በሚል ነበር።
ምስሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተነሳነው ከአምስት አመት በፊት November 24 2020 ላይ ነው።
የአማራ ክልል በመንገድ እጦት የሚሰቃይ ክልል እንደሆነ ይታወቃል። መንገድ የደም ስር እንደመሆኑ መጠን ያለውን መንገድ መጠበቅ እና ተጨማሪ መንገዶችን መስራት ለዚህም ተባባሪ መሆን ለአማራ ህዝብ ከሚቆረቆር ግለሰብም ይሁን ቡድን የሚጠበቅ ነው።
በዚሁ አጋጣሚ አጠራጣሪ ምስሎችን ሲያገኙ Tineye የሚባል ድረገፅ ላይ በማስገባት ምስሉ መቼ እና የት እንደተሳ ማረጋገጥ ትችላላችሁ።
===================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
ልጅ የሚወልዱ 5000 ዶላር‼️
ፕሬዝዳንት ትራምፕ አዲስ ለሚወለዱ ህጻናት 5,000 ዶላር እንደሚሰጡ ቃል ገቡ‼️
ትራምፕ የእናቶችን የወሊድ መጠን ለማበረታታት አዋጭ ያሏቸውን እርምጃዎች እየወሰዱ ነው ተብሏል፡፡

ውሳኔው፣ "አሜሪካን እንደገና ጤናማ ማድረግ" ከሚለው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔድ እቅድ አካል መሆኑ ተገልጿል።

የወቅቱ የአሜሪካ መንግስት አሜሪካውያን እንዲያገቡና ብዙ ልጆች እንዲወልዱ እያበረታታ እንደሚገኝ FOX ዘግቧል፡፡
===================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA