የእርቅ-ይሁን ማዕድ® 💌
303 subscribers
1 photo
2 links
◈ አንዳች ወሰንና ገደብም ከሌለው...ካላንዳች መድሎ እኩል ከሚለግሰው ሰላምን ከፍቅርን...አንድነትን አበርክቶ መለያየትን ጠልቶ...አይቻልም መንፈስን ከይቻላል የሚያቆራኝ...አብሮነት ከሚሻው እርቅ-ይሁን ሲል ዘወትር ይቅርታን ከሚሰብከው ከእርቅ ማዕድ እንቋደስ...!
:
:
:
#Join And #Share
..... @Erk_yehun
@Erk_yehun
For any comment... @Erk1236
Download Telegram
በመንገድህ ሁሉ ለለመነህ የምትሰጠው ነገር አታጣም፤ ቸር ለመሆን ሃብት እስክታገኝ አትጠብቅ።
💊አንዳንዶች ካንተ የሚፈልጉት ፈገግታህን ነው፤
💊 አንዳንዶች ሰላምታህን፤
💊 አንዳንዶች ጊዜህን፤
💊 አንዳንዶች ሃሳብህን፤
💊 አንዳንዶች ድጋፍህን፤
💊 አንዳንዶች ጓደኝነትህን።
ሁላችንም ለሌላው የምናካፍለው ብዙ ነገሮች አሉን፤ ያለተጠቀምንባቸው ሰስተን ሳይሆን አለን ብለን ስላላመንን ይሆናል። ሌላው ይቅር ፈገግታ እና ደስታችን፤ እንኳን የምናውቀውን ሰው ይቅርና የመንገደኛውን ሰው ቀን ብሩህ የማድረግ ሃይል አላቸው።
<የሚለኩሳቸው ያጡ ብዙ ሻማዎች አሉ፤
ለኳሾቹም ሻማዎቹም ግን እኛ ነን፤ ክብሪቱ ደግሞ ፍቅር።>
#4
አስታራቂ
"ለምን ተጣላችሁ? እኔንጃ ምንስ አድርጎሽ ነው?እኔንጃ ለምንስ እራስሽ ይቅርታ አልጠየቅሽውም? ኧረ እኔንጃ ለነዚህ መልስ የለኝም"

✍🏽ፀሐፊ፡ ፊሊሞን የማርያም ልጅ
🎙አንባቢ፡ ፊያሜታ


🖤 @Erk_yehun 🖤
🥀 @Erk_yehun 🥀
😍 የህልም እናት 😍

"ህይወቴ አደራ የምወዳቸውን ነገሮችህን ከገባሁበት አፈር አታስገባቸው...አደራ አለሜ አደራ ገር ልብህን ከኔ ጋር አትቅበር"

ፀሀፊ~ Kiza Kiza
🎙 አንባቢ~ ፊያሜታ

♥️ @Erk_yehun ♥️

♥️ @Erk_yehun ♥️
ሐምሌ 13 2014 ዓ.ም

#እንኳንም_ተወለድኩ የሚያስብሉኝ እልፍ መልካም ቀኖች ለሠጠህኝ፣ በነፃ የምተነፍሰው ንፁሕ አየር የሠጠህኝ ፣ ገልጬ ስለማልጨርሰው ፍቅርህ፣ከአመት አመት በጤና ለምታደርሠኝ የማትተኛው አምላኬ የድንግል ማርያም ልጅ ክብር ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን፡፡ #መልካም_ልደት_ለእኔ እና በዚህ ቀን ለተወለዳችሁ!❤️

🎂እርቅ-ይሁን🎂
July 20 2022
በህይወት እስካለህ ልትሳሳት፣ ልትወድቅ ትችላለህ፣ ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ፣ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ፣ በእጅህ ላይ ያለው ሙሉበሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ፣ ሰዎች ሊጠሉህ፣ ሊያሙህ፣ ወይም ስም ሊያወጡልህ፣ አልያም ሊስቁብህ ይችላሉ።

በህይወትህ ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሁኖ ለመታየት መሞከር ነው።

መልካም ብትሆን ክፋወች ይጠሉሀል። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል።

ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደደም፣ ልትጠላም አትችልም። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አቀያይር።


ከምንም በላይ ፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!!

አንድ ነገር ልንገራችሁ
በህይወታችሁ ማንንም አትውቀሱ
ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጧችኋል!!
መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኑዋችኋል!!
ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆኑዋችኋል!!
ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኑዋችኋል!!

👤 ስብሀት ገ/እግዚአብሔር

መልካም ቀን ተመኘሁ 🙏😊
#ስለኤሊያስ

ነገሩን የሰማሁበት ቅፅበት ሞቼም 'ምረሳው አይመስለኝም። በተደጋጋሚ ይታወሰኛል..አብሶ አንዳንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሳይ ቀጥታ ፊቴ ላይ ይቸነከራል።
......
አስታውሳለው...ለረጅም ደቂቃ ከናቴ ጋር በስልክ ከተነጋገርን በኋላ እናቴ ንግግሯን ስታገባድድ..
" ..ለማንኛውም የደወልኩልህ ጓደኛህ...ያ...ማነው የሆነ ሰሞን ወታደር ሆነ ያልኩህ... ?" አለችኝ።
" የትኘው..?" አልኳት... ውትድርናን የተቀላቀሉ አብሮአደጎቼን እያሰብኩ..
" የ'ትዬ አይናለም ልጅ..."
"ማ.... ኤሊ.. ኤሊያስ?"
"አዎ ኤሊያስ.. ኤሊያስ አርፏል..! ዛሬ ጥዋት ነው ለቤተሰቡ የተነገረው..."
በረዶ የሆንኩ ያህል ይሰማኛል! እኔ ትንሽ ልብ እንዳለኝ አውቃለሁ። አይደለም አንድ ለይ ብይ ተጫውተን ኳስ ተራግጠን ያደግን እንደወንድሜ የማየው ጓደኛዬ መሞቱን ሰምቼ ይቅርና እንዲቹ ድንጉጥ ነኝ። እግሮቼ ወላ ሊከዱኝ ይሻሉ።
"ቆይ...'ንዴት...? መቼ ..ማን...ምን?" ከመደንገጤ የተነሳ ምን እንደጠየኳት ራሱ አላውቅም።
" ከሞተ አንድ አመት ሆኖታል ... እዛው ትግራይ ነው የተሰዋው!... ለማንኛውም ልንገርህ በሚል ነው የደወልኩልህ"

****
ኤሊያስን ምንም እንኳ ከልጅነቴ ጀምሮ ባውቀውም ሁሌም ቢሆን ቪዥነሪ መሆኑ ይታወሰኛል። እንደ ኤሊ.. ተሰፈኛ ሰው አይቼ ኣላውቅም። ልጅ እያለን ኤለመንተሪ ስንማር ከኔ ይልቅ የሱ የነገ ህልሞቹ ነው ትዝ የሚሉኝ።
"አንተ ስታድግ ... ምን መሆን ነው ምትፈልገው?" ይለኛል ወደ ትምርት ቤት እየሄድን።
" ማ እኔ... እኔማ ኳስ ተጫዋች ነው መሆን ምፈልገው ልክ እንደ ሮላንዶ" ልጅ እያለነው ሮናልዶ እና ሮላንዶ ይምታቱብኝ ነበር።
" እኔ ግን ...." ይላል ኤሊ ሳልጠይቀው።
"ጠበቃ ነው ምሆነው...! ጠበቃ ነው መሆን የምፈልገው! ወይም ዳኛ!"
እኔም የጋሽ ዘነበ ቤትን የሚጠብቁን ዘበኛ/ጥበቃ አስብና
"አሪፍ ነው አሪፍ ነው "እለዋለው።
"ጠበቃ ሆን እና ጋሽ ዘነበ ከናቴ ለይ አጭበርብረው የወሰዱትን ንብረት በሙሉ አስመልሳለው...!"
ጋሽ ዘነበ ገዴቦ (ስማቸውን ለዚህ ፅሁፍ ሲባል የተቀየረ) ያላቸውን ንብረት አግባብ በሌለው ሁኔታ እንደሰበሰቡ ይታማሉ።
ኤሊ ህልም ብቻ አይደለም... እስከ 12ኛ የማትሪክ ፈተና ድረስ ነገ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ከልጅነቱ ጀምሮ የሚያልመውን የህግ ትምርት ጆይን በማድረግ ተምሮ ተልኮውን ለመፈፀም በርትቶ የሚያጠና ተማሪ ነበር። ዳሩ ግን ውጤት ቀረበት።😭 ሊያልፍ አልቻለም። ለዛም ነው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን የተቀላቀለው።

ዛሬ ለይ ዩኒቨርስቲ ውስጥ... ከሱስ ውጪ ሌላ ተግባር የሌላቸው .. ትምርታቸውን የማይከታተሉ..
የነገ ህልም የሌላቸው...ወዴት እየሄዱ እንደሆነ የማይረዱ ተማሪዎችን ሳይ እነሱ ናቸው የ ኤሊን ህልም ያጨለሙት እላለው።
በመዲናዋም ሆነ በክፍለሀገር... ተምሬ ነገ የራሴንም ሆነ የቤተሰቤን ድህነት ታሪክ አደርጋለው ብለው የሚያስቡ... አያሌ ተማሪዎች በነዚህ ህይወት ጨዋታ በሚመስላቸው... በኩረጃም ሆነ በምንም አልፈው ዩኒቨርስቲ በገቡ ተማሪዎች ህልማቸው ይጨልማል።

#የግርጌ_ማስታወሻ!
#ለ12ኛ_ክፍል_ተማሪዎች
ነገ ዩኒቨርሲቲ ገብታችሁ በሱስ.. በአደንዛዥ እፅ እና በመሳሰሉት ነገሮች ማሳለፍ የምትፈልጉ ከሆነ ስንት ነፍ ትልቅ አቅም ያለው የደሀ ልጅ አለ እና ... በመንገዱ ለይ አትቁሙበት...! ባጭሩ አትፈተኑ!
#ሺ_አመት_አይኖር!

ውጥረትን በመፍጠር ረገድ ቀዳሚውን ድርሻ የሚወስደው የአእምሮ መመሰቃቀል እንደሆነ ይታመናል። ባተሌው አእምሮ ሁሌም ውጥረት ይሰማዋል። የተመሰቃቀለ አእምሮ ማለት ግራ መጋባት የሰፈነበት እንዲሁም ውጥረት የነገሰበት ነው። እንዲህ ዓይነቱ አእምሮ በጭራሽ በማይወስናቸው ችግሮች ላይ በቀላሉ ያርፋል።

ከአንዱ ችግር ወደ ሌላው ችግር በጭንቀት ይዘላል እንጂ የተረጋጋ ድምዳሜ ላይ አይደርስም፤ እንዲያውም ከጉዳዩ ጋር በቁም ነገር አይታገልም። በመሆኑም እልባት ያልተሰጠባቸው እና በእንጥልጥል ያሉ ጉዳዮች ይከማቹበታል። በውጤቱም፣ አእምሮ ትልቅ ጭንቀት ውስጥ ይገባል፤ ተስፋ ወደ መቁረጥም ያመራል።

አእምሮህ ተስፋ ቆረጠ ማለት… አንተም ተስፋ ቆረጥክ ማለት ነው፡፡ እስቲ አእምሮህ ካለበት መመሰቃቀል እንዲወጣ ባለህበት አይኖችህን ጨፍንና ጥልቅ አየር ማግ በማድረግ ለአምስት ሰከንዶች ያህል ይዘህ አቆይተህ ውስጥህ ያለውን ምስቅልቅል ነገር በትንፋሽህ አውጣ፡፡

ተንፍስ… ተረጋጋ፡፡

ሺ አመት አይኖርም… አሁን በዚህች ቅጽበት ዘና በል፡፡ የሕይወት ሁሉ መፍትሄ ያለው ዘና ባለ አእምሮ ውስጥ ነውና አእምሮህን ዘና አድርገው፡፡

#በራስ_መተማመን_መጽሐፍ 5ተኛው ዕትም በገበያ ላይ ውሏል።
📗📒📕
#በአእምሮህ_መታደስ_ተለወጥ!

ከመጽሐፍት ሁሉ እጅግ ትልቁ የሚባለው መጽሐፍ፤ “ሰው በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና” ይላል፡፡

አሁን የምናስበው፣ ለረጅም ጊዜ እያሰብን የነበረው፣ ወደፊት የምናስበው ነገር ምን እንደምንሆን እና የምንኖርበትን አለም በትክክል ይወስናል።

ሁልጊዜም የምንሆነውን የሚወስነው የምናስበው ነገር ነው።

አስተሳሰባችንን ስንቀይር፣ ዓለማችንን እንለውጣለን። አስተሳሰባችንን በትክክል ስንለውጥ፣ ሁሉም ነገር ወደ ውስጣዊ ሰላም፣ ደስታና ግላዊ ኃይል ይለወጣል፡፡

ታላቁ መጽሐፍ፣ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ። (ሮሜ 12÷2) ይላል፡፡ ከዚህ የበለጠ ጥበብ ያለበት ነገር ፈጽሞ አልተነገረም።

ይህ ማለት በአስተሳሰባችን መንፈሳዊ እድሳት ራሳችንን፣ የምንኖርበትን አለም፣ የቤታችንንና የንግዳችንን ሁኔታ እንዲሁም መላ ህይወታችንን መለወጥ እንችላለን ማለት ነው።

#በራስ_መተማመን_መጽሐፍ በገበያ ላይ
📗📒📕
#በየቀኑ_የምትሰማቸው_5_ውሸቶች

#1_ሕልምህን_አሁን_ተወው_ወደፊት_አንድ_ቀን_ታልመዋለህ። አንድ ቀን? አንድ ቀን መቼ ነው? በእርግጠኝነት ያለህ ብቸኛ ቀን ዛሬ ነው፡፡ በሕይወትህ ውስጥ ለውጥ ማምጣት የምትችልበት ብቸኛው ቀን ዛሬ ነው፡፡ ዛሬን፣ የተቀረው አዲስ ሕይወትህ የመጀመሪያ ቀን አድርጋት፡፡

#2_ካልተሳካልህ_አለቀልህ። ስህተት! ይሄ ፍጹም ውሸት የሆነ ረብ የለሽ አባባል ነው፡፡ የመውደቅ አጠገቡም ሆነ ሕይወትህ የመመሰቃቀል ጫፍ እንኳ አልተቃረበም፡፡ በእርግጥ የከፋ ነገር ቢገጥምህ እንኳ አለቀልህ ማለት አይደለም።

#3_ሕልም_የምትለውን_ትተህ_አርፈህ_ስራህን_ስራ። መኝታ ክፍልህ ውስጥ ራስህ ላይ ቆልፈህ ሁለተኛ ፈጽሞ ከክፍልህ አለመውጣት፡፡ ልክ እንደዚህ አድርገህ መላው ሕይወትህን እና ሕልምህን ሽንት ቤት ውስጥ ጥለህ፣ በላዩ ላይ በውኃ ማውረድ፡፡ ይህን ነው እየመከሩህ ያሉት። አትስማቸው

#4_እሱማ_ሊሆን_አይችልም። አንዳንድ ነገሮች የማይቻሉ የሚመስሉበት ምክንያት ማንም ሰው ገና ስላላሳካቸው ነው፡፡ ይህ ማለት ግን በአንተ እርዳታ እነዚህ ነገሮች ወደፊት አይሳኩም ወይም አይቻሉም ማለት አይደለም፡፡ ለመጨረሻው ውጤት እራስህን የእውነት እስከሰጠህ ድረስ ማንኛውም ነገር የመሆን እድል አለው፡፡ ከአንተ የሚጠበቀው ከልብህ መፈለግ ብቻ ነው፡፡

#5_እድለኛ_ከሆንክ_ብቻ_ነው_የሚሳካልህ። እነዚህ እድለኞች እንዳንተ ያሉትን አሉታዊ ሰዎች አያዳምጡም፡፡ አንድ ነገር ለማሳካት ቆራጥነት፣ ፍቃደኛነት እና ጠንክሮ መስራት እንደሚያስፈልግ ያውቃሉ፡፡ ቀላልና ፈጣን እንደማይሆንም ያውቃሉ፡፡ ስኬታቸው የሚወሰነው በእነርሱ ብቻ መሆኑንም የሚያውቁ ናቸው፡፡ ከእነሱ መሀል አንዱ መሆን ትችላለህ፡፡

#ልብ_በል እነዚህን ሁሌም የሚደሰኮሩ ሀሳቦች አትቀበላቸው፤ አትመናቸው፤ ፈጽሞ እድል ፈንታ አትስጣቸው፡፡ ወዳጄ- ለማሸነፍ ተፈጥረሀል!!

#በራስ_መተማመን_መጽሐፍ 5ተኛው ዕትም በቡክላንድ አሳታሚ ታትሞ በገበያ ላይ ውሏል።

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡
📗📒📕
#ዕለት....ዕለት
ልባዊ ምስጋና ማቆረብ...!

1ኛ . ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነሳ ፈጣሪህን አመስግን

ለሊቱን በዙሪያ ባደሩ መናፍስት በሞት ልትወሰድ ስለነበር

2ኛ ሙሉ አካል ስላለህ

አካልህ ሙሉ ባይሆን እንኳን በጤና አልያም በህይወት ያቆየህ ፈጣሪ ምክንያት ስላለው ነው ለዚህም አመስግነው

3ኛ ቢያንስ በቀን አንዴ እንኳን አፍህን ትሽራለህ ቢኖር መርጠህ በልተህ ባይኖርህ ውሀ እንኳን ጠጥተህ ትውላለህ ለዚህ የፍጥረታት ጌታን አመስግን

4 . በመንገድህ ሁሉ ስትሄድ ሠላምታ እና ትህትና ከአንደበትህ አይራቅ

5. ለሚገጥምህ መጥፎ ነገር ሁሉ ምላሽህ ደግ እና መልካም ነገር ይሁን
ክፉ ተነጋግረህ ክፉ ሰርተህ ከሰውም ከእንስሳውም ከሁሉ ፍጥረት ከምትጣላ ይልቅ ሁሉን እንዳመጣጡ በፍቅር ሸኘው

6. ባረፍክበት ሁሉ እርዳታህን ለሚሻ ሁሉ ደግ ልቦናህን እና ቀኝ እጅህን አትከልክል የዛሬ ቸርነትህ የነገ እረፍትህን ያበጃጃል እና

7. ከማንም ጋር በማይረባ ጊዜያዊ ጥቅም አትጣላ አትጋጭ ችኩል አትሁን ለሚያልፍ ቀን ብለህ ፍፁም አትማረር ይልቅ ይቅር ማለትን ቅድሚ መስጠትን ለልብህ አስተምር ላንተ ያለው እንጀራ ሳይሻግት ሳይደርቅ በለምለምነቱ በጊዜው ከነሌማቱ ቤትህ ይገባልና

8. ህፃናትን ሁሉ በአንድ ልብ ውደድ ሠው ማፍቀርን ሀቀኝነትን እና ደግነትን አስተምራቸው ነገ በድካምህ ጊዜ ሮጠው የሚደርሱልህ እነሱ ስለሆኑ
ወጣት እኩዮችህን አትናቅ አንተ የደረስክበት እንዲደርሱ እርዳቸው ከአንተ የበለጡም ስለሚኖሩ ራስህን ለማሻሻልም የሚረዳህ ቸር ማድረግ ነውና ከፍ ለማለት የሌሎችን ጫንቃ አትስበር እንዲያው እጅ ለእጅ ተያይዞ መለወጥን አስብ
አዛውንቶችን አተጨቁን ምርቃታቸው ርግማናቸውም ከአፋቸው ጠብ አይለምና ከፈጣሪ እንዳትጣላ

''የሚያድግ ህፃን አይጥላህ
የሚሞት ሽማግሌ አይርገምህ''

9. ስላለህም ስላጣኸውም ሁሉ አመስግን ስላሣለፍከው መከራም ስላየኸውም ተድላ በምክንያተ አመስግን የሚሆነው ሁሉ በምክንያት ባንተ ላይ ስለተከናወነ አመስግን ማማረር ከቶ ስለማይበጅ

10. ስላሣለፍከው ቀን ሁሉ ምሽት በቤትህ ለፈጠረህ አምላክ ምስጋናን አቅርብ ብዙዎች አንተ ያየኸውን ቀን ሳያዮ ብዙ እየተመኙ በህይወት ወደማይቀረው አለም አልፈዋልና

።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ክፉ እንድናስብ እንድንፈፅም ከዚያም በራሳችን እንድናዝን እንድንፀፀት የሚያረገን የክፋት አባት እሱ ሠይጣን ነውና እሱን በቸርነት በመልካም ስራና በየእምነታችን በፈጣሪ ምስጋና እንበቀለው እንጉዳው

ከዚህ በላይ ጉዳትና በቀል የለም
ሰው ሳይሆን ሠይጣን ነውና ጠላታችን
በሱ ላይ ነው በቀለኝነታችን

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ወዳጄ....
ደስተኛ መሆን ትፈልጋለህን ? በርግጥ ቀንን እንዴት ማሳለፍ እንደሚገባህ ማወቅ ትሽለህን? አንድ መንፈሳዊ መጠጥ እሰጥህለሁ ። ይህ መጠጥ ሰካራም ሰዎች እንደሚጠጡት ንግግርን የሚያጠፋው ዓይነት መጠጥ አይደለም ። ይህ መጠጥ አንደበታችነ እንዲኮላተፍ የሚያደረግ አይደለም ። ይህ መጠጥ ዓይናችን በአግባቡ ማየት እንዲሳነው የሚያደርግ አይደለም ። መዝሙር መዘመር ተማር ! ያን ጊዜ ደስታን በእርግጥ ታየዋለህ ።

#ቅዱስ ዩሐንስ አፈወርቅ
#ሕይወት_እንደ_ነጭ_ወረቀት!

ዛሬ የማጋራችሁን ሃሳብና የማቀርብላችሁን Challenge በቁም ነገር በመውሰድ ወረቀትና እስኪሪፕቶ በመያዝና በመጻፍ (ወይም በስልካችሁ ላይ Note በመያዝ) ራሳችሁን ለለውጥ እንድታቀርቡ ላነሳሳችሁ፡፡

Challenge #1

እስከዛሬ የኖራችሁትን የሕይወት ልምምድ፣ እውቀት፣ ጥበብ፣ ከስህተታችሁ የመማር ሁኔታና የመሳሰሉትን ነገሮች እንደያዛችሁና ሳይወሰዱባችሁ ዛሬ የሕይወታችሁ የመጀመሪያ ቀን ቢሆን ምን አይነት የወደፊታችሁን በምን መልኩ ታዩት ነበር? ምን አይነት የሕይወት እቅድ ታወጡ ነበር? ምንስ አዲስ ነገር ትጀምሩ ነበር?

ከላይ ለጠየኳችሁ ጥያቄ መልስ ካሰባችሁና መልስን ከሰጣች በኋላ የሚቀጥለውን ጥያቄዬን አንብቡና ለራሳችሁ መልስ ስጡ፡፡

Challenge #2

እስከዛሬ የነበራችሁን ስኬትም ሆነ ስህተት የማሰብና ግምገማ የማድረግ ጊዜ ቢሰጣችሁና ዛሬ የሕይወታችሁ የመጨረሻ ቀን ነች ብትባሉ “ምነው አቁሜው በነበረ የምትሉት አጉል ተግባርና ልማድ … ምነው ተለይቼው በነበረ የምትሉት አስቸጋሪ ሰው …” እና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው?

አሁን ለመጀመሪያው ጥያቄ (Challenge #1) የሰጣችሁትን መልስ ተመልከቱት፡፡ በሉ ዛሬውኑ እቅዱን አውጡት፣ በትንሹም ቢሆን ውጡና ጀምሩት፡፡ ሕይወታቸውን ለተሸለ ነገር የለወጡ ሰዎች ያንን ያደረጉት በዚህ መልኩ ነው፡፡

በመቀጠል ለሁለተኛው ጥያቄ (Challenge #2) የሰጣችሁትን መልስ ተመልከቱት፡፡ በሉ ዛሬውኑ ማቆም የሚገባችሁን አጉል ልምምድ አቁም፣ መለየት የሚገባችሁን አደገኛ የሰው-ለሰው ግንኙነት አቁሙ፡፡ ሕይወታቸውን ከጤና ቢስ ልምምድና ግንኙነት ያዳኑ ሰዎች ያንን ያደረጉት በዚህ መልኩ ነው፡፡

ሕይወት ማለት እንደ ነጭ ወረቀት ንጹህ ሆና የተጀመረችና በጉዞው ሂደት ግን በብዙ ልምምዶች የቆሸሸች የፈጣሪ ስጦታችን ነች፡፡ እንደ አዲስ መጀመር የማይቻል ነገር የለም፡፡ የማይታረም ነገር ግን የለም፡፡ የማይለወጥም ነገር የለም፡፡ የለውጡ ቀን ግን ዛሬ ነው፡፡ ይህ የለውጥ እድል ነገ የመኖሩን ጉዳይ ማንም ቃል አልገባለንም፡፡

መጀመር ያለበት ዛሬ ይጀመር!!! መቆም ያለበት ዛሬ ይቁም!!!

በ......ዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ሰው ሁን....!

ሰው ነኝ ባዮች ሰው ያልሆኑ ስንቶች የተከበረውን የእርሱን ስራ ተሸክመው እየተዘዋወሩ በህይወት እንዲያ እየተመላለሱ....ኸረ ስንቶች አሉ የሰውነት ትርጉሙ ቅሉ ላፍታ ያላወቀላቸው...።
ሰውነት ትርጉሙ እና ዋጋው እጅጉን ረቂቅ ነው።ግና ላላወቀው በስሜት ፈረስ ለሚጋልብ...በሰሞነኛ ሰረገላ እራሱን አንግሶ ለሚጓዝ....ማስተዋል ለራቀው ፤ሰክኖ ማሰብ ለተሳነው፤የሰሜት ፈረስ ለሆነ አላፊዎች ለሚጋልቡት፤ወረተኛ ለሆነ፤የይቅርታን ዋጋ ሲሶዋን ላልተረዳ፤ዝምታዎች ፍራቻ፤እንክረም ሞኝነት ለመሰለው፤እውነትን አርክሶ ሀሰትን አንግሶ ለሚጓዝ፤ከመናገር በቀር መኖርን ለማይችል፤በቃላት ስንጠቃ የማወቅን ጥግ የተረዳ የሚመስለው፤ሳይጀምረው የጨረሰ ለሚመስለው፤ማወቅን በቅጡ ያልተረዳ በእውቀት በቃሁኝ ለሚል.....እስኪ ወዳጄ ለዚህ አይነቱ ፍጡር ምኑጋነው ሰው???

ሰው ነኝ ብለን ካልን እስኪ ድርጊቶቻችንን ቆም ብለን እናስተውል? ምኑጋነኝ እንበል...በፈጠረን ፊት ለአፍታ ብንቀርብ ምን ምላሽ ይኖረን ይሆን ብለን ትዕዛዛቱን ከተግባራችን እናመሳክር...!!!

ሰውነት መሆን የራቀህ ወዳጄ እስኪ ሰው ሁን!
ለራስህም የማታፍርበትን ተግባር ተግብር....ይመስለናል ግን ከሰውነት የራቅን ብዙዎች ነን ይባስ ብሎ የተሳሳተው ጉዟችን እያወቅነው ሳለ ትክክል እንደሆን እንኩራራበታለን....ይህ ግን እስከመች?
ሰው እንሁን....ወዳጄ እስኪ የተከበረውን አታርክሰው በድርጊትህ ሲጠሉህ በድርጊትህ ሲዘልፉና ሲያንቋሽሹህ የፈጣሪን ስራ እያስወቀስክ እንደሆነ አድርገህ ተረዳው....ከዛም ማስተዋልን ተላበሰው መንገድህን ምረጥ አመሻሽ ላይ መግቢያህን ሊያሳምርልህ የሚችለውን ንፁሑን እና ምቹውን ምረጥ...ጊዜያዊነት ጊዜያዊ ነው፤በሀሰት የተገነባ ይፈርሳል ውሸት ምንም ለጊዜው ያማረች ቢመስልም የቆይታ እድሜዋ አጭር ነው ማብቂያዋ ገደብ የተበጀለት...የሚሻልህን ታውቃለህ ብቻ ግን ሰው ሁን....!

:በ እርቅ-ይሁን🔔 @Erk1236
ትንሽ ፈገግታ !

መልካም ስትሆን ለሰዎች ምን እየሰጠኃቸው አንዳለህ አታውቅም ፈገግ ብለህ በማየትህ ብቻ ትልቅ ተስፋ የሰጠኃቸው ብዙዎች አንዳሉ ገምተህስ ታውቃለህ? ስለዚህ ወዳጄ ምንም ማድረግ ባትችል እንኳን ከልብህ ፈገግ ብለህ ለሰዎች ሰው እንዳላቸው እንዲሰማቸው አድርግ ውጤቱ ብዙ ነዉ!

ደስ የሚል ሰኞ ተመኘን 🙏
@manyazewaleshetu 😊
የጊዜ ጉዳይ ነው!

አንተ ነገህን መወሰን አትችልም፤ አንተ የምትችለው ደጋግመህ የምታደርገውን ልማድ መወሰን ነው፤ ከዛ ያ ልማድህ ግን ነገህን መወሰን ይችላል! የጊዜ ጉዳይ ነው ምርጥ ልማድ ካለህ ምርጥ ቦታ ያደርስሀል!

ውብ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@manyazewaleshetu!
Keep your thought positive
Because your thoughts becomes
YOUR WORDS

Keep your words positive
Your words become
YOUR BEHAVIOUR

Keep your behavior positive
Your behavior becomes
YOUR HABIT

Keep your habit positive
Your habit becomes
YOUR VALUES

Keep your values positive
Your values becomes
YOUR DESTINY

#At_any_means, #anytime, #any_where, #to_anyone stay positive

መልካም ቀን
🦻ሦስቱ መስማት የተሳናቸው

ሦስት መስማት የተሳናቸው በአንድ ሰፈር ይኖሩ ነበር እና አንድ ቀን አንዱ መስማት የተሳነው ፍየል ትጠፋበታለች እና ፍየሉን ሲፈልግ አንዲት መስማት የተሳናት ሴት ልጅ አዝላ አረም ስታርም ያገኛታል "ፍየሌን አየሽ ወይ?" ብሎ ጠየቃት እሱዋም መስማት አትችልምና " አረም እንዴት ነው?" ብሎ ይሆናል የጠየቀኝ ብላ በእጇቿ ያረመችውን እያሳየችው " ይህን ያክል አርሜያለሁ" ትለዋለች ፤ ጠያቂውም መስማት ስለማይችል " ፍየሏ በዚያ በኩል ነው የሔደችው" ያለችው መስሎት በጠቆመችው ቦታ ሲሔድ ፍየሉን ተሰብራ ያገኛታል ፤ከዛ የተሰበረች ፍየሉን ይዞ ወደ ምታርመዋ ሴት ሔዶ " በጠቆምሽኝ ጥቆማ መሰረት ፍየሏን አግንቻታለሁ ፤ ስለዚህ ለኔ ብዙ ፍየሎች ስላሉኝ ይቺን የተሰበረችዋን ፍየል ያገኘዋት በአንቺ ጥቆማ ነውና ለአንቺ ሸልሜሻለሁ" ይላታል

ከዚያ እርሷ አንቺ አሽ የሰብርሻት እያላት መስሏት " እኔ አልሰበርኩም " እያለች ስትመልስለት ይቆያሉ ሁለቱ ማለትም ፍየል የጠፋበትና ልጅ አዝላ አረም ምታርመው ሴት ብዙ እየተከራከሩ ሳለ ሌላ ሶስተኛ መስማት የተሳነው ሰው ይመጣና የተጣሉት ባዘለችው ልጅ ምክንያት መስሎት ፍየል ለጠፋበት ልጅ " አንተ ልጅ አትከራከር ይህ ያዘለችው ልጅ መልኩ ቁርጥ አንተን ይመስላል የአንተ ልጅ ነው እመን" አለው ይባላል።

🇪🇹ሀገሬን የገጠማት እንዲህ ያለ ችግር ይመስለኛል ፣ መሬት ላይ ካለው እውነታ ይልቅ በየራሳችን የፈጠርነው ነገር ውስጣችንን ያቆሸሸው ዘረኝነት፣ ፖለቲካው በሀገራችንም ብሎም በእምነታችን መጥፎ ድሩን ጥሎብን ተብትቦ ያስቀመጠን
መደማመጥ እየቻልን ማንደማመጥ እኛ ከየትኞቹ እንሁን?