Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS
6.66K subscribers
4.86K photos
26 videos
3 files
154 links
Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service , EPSS, is legal entity established under the law of Federal Democratic Republic of Ethiopia Government to overcome the problems and assure uninterrupted supply of pharmaceuticals to the public.
Download Telegram
የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከለል ተገቢውን መረጃ በማሰራጨት ላበረከተው ገንቢ አስተዋፅኦ
ከጤና ሚኒስቴር የምስጋና እና የእውቅና የምስክር ወረቀት ለኤጀንሲው ተሰጠው፡፡

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ በህዝብ ግኑኝነትና የኮሙዩኒኬሽን ስራዎችን በአመርቂ ሁኔታ በመስራት ለተጫወተው ከፍተኛ ሚና ከጤና ሚኒስቴር የምስጋና እና የእውቅና የምስክር ወረቀት ነሀሴ 25 ቀን 2013 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ የጤና ሚንስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ኔትወርክ የውይይት መድረክ ላይ ተበርክቶለታል፡፡

የኤጀንሲው የህዝብ ግንኘነት እና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶት የ2013 በጀት አመት እቅድ ክንውን እና የ2014 የመነሻ እቅድ ለውይይት ቀርቧል።

የኮረና መከላከያ ግብአቶች ስርጭት፣የመከለል መንገዶችን እንዲሁም የኮረና ክትባቶችን ክምችት ስርጭት በተመለከተ ትኩረት አድርጎ ወቅታዊ መረጃወችን በማሰራጨት ዘገባ ሲሰራ እንደነበር ተገልጿል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር በደሴ ከተማ በመገኘት የቅርንጫፉን አፈጻጸም በመጎብኘት ላይ ናቸው፡፡

የመድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ በተገኙበት የደሴ ቅርንጫፍን አፈጻጸምና የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ በውይይቱ የቅርንጫፉ የማናጅመንት አባላት የቅርንጫፉን የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ገንቢ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በውይይቱ የቅርንጫፉ አጠቃላይ የግብዓት አቅርቦት ዙሪያ አሁን ካለው ወቅታዊ የስራ ጫና አንፃር የተቀናጀ ስራ እየተሰራ መሆኑ ግንዛቤ ተወስዶበታል።

በሌላ በኩል ከጤና ተቋማት ጋር ያለው ቅንጅታዊ ስራ ከምንጊዜውም በላይ የተሻሻለ ቢሆንም ከቅርንጫፉ የሚጠበቁ በርካታ ስራዎች እንደሚጠበቁም ተጠቁሟል።

በተጨማሪም የአቅርቦት ክፍተቱን ለመሙላትና በቀጣይ ስለሚከናወኑ የጋራ ስራዎች ከቦሩ ሜዳ ሆስፒታል እና ደሴ ኮምኘርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር ጥሩ መግባባት የተደረሰበት ውይይትና የጉብኝት ተግባራትን አከናውነዋል፡፡
አለማቀፍ የመድኃኒት አቅራቢዎች ኮንፈረስ/INVITATION TO EPSA INTERNATIONAL SUPPLIERS CONFERENCE/
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለቱን ለማሻሻል ከአቅራቢዎች ጋር ለመወያያየት ነሐሴ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ዓለማቀፍ ኮንፍረንስ ለማካሄድ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ሲሆን የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያላችሁ አቅራቢዎችና የባለድርሻ አካላት ተሳታፊ እንድትሆኑ ጥሪ እያቀረበ ከዚህ በታች በተገለጸው LINK እንዲሁም በኤጀንሲው ድረ ገጽ(WEBSITE) በመግባት ሊንኩን በመጠቀም ተሳታዊ እንድትሆኑ በአክብሮት ተጋብዛችኋል፡፡

INVITATION TO EPSA INTERNATIONAL SUPPLIERS CONFERENCE
Event Date - Sunday, September 5th 2021
Time - 8:30 AM - 1:30 PM East-African time

Ethiopian Pharmaceuticals Supply Agency (EPSA) is a government institution under Ministry of Health established by proclamation no. 553/2007 with a mission to ensure the continuous supply of pharmaceuticals and medical supplies to public health facilities at affordable prices and strengthening pharmaceuticals and medical supplies distribution outlets in the country.

In line with the Agencys strategic initiatives, EPSA has organized an international suppliers conference that will help to enhance and improve the supply chain operations and supplier relationship management.

The conference will focus mainly on supply chain operational issues and EPSA’s strategic directions going forward.

The agenda for the meeting will be circulated in due course to all suppliers who have registered for the conference through the specific agency corporate email: epsa.suppliersconference@epsa.gov.et

If you would like to join the conference virtually, please use the below link which is active and available at EPSA official website.

To join the video meeting, click this link: https://meet.google.com/uhw-wtoa-hmg Otherwise, to join by phone, dial +27 10 823 1085 and enter this PIN: 686 770 643# To view more phone numbers, click this link: https://tel.meet/uhw-wtoa-hmg?hs=5
Vaccines 💉 give us a high level of protection from serious illness & death from #COVID19 variants, including Delta.

The more people are vaccinated, the less opportunity the virus has to spread & develop new variants.

Get vaccinated as soon as it is your turn.