ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
8.49K subscribers
504 photos
4 videos
7 files
617 links
መንፈሳዊ ቻናል እንጋብዛቹ
@EOTCY
ምን አይነት ነገሮችን ነው የሚፈልጉት?
➢ የተለያዩ ትምህርቶችን
➢ መጣጥፎችን
➢ መንፈሳዊ ግጥሞችን
➢ ተከታታይ ትምህርቶችን
➢ ብሒለ አበው
➢ ወይስ ዜና ቤተክርስቲያን

አሁኑኑ ይቀላቀሉን የኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቀጥተኛ አስተምህሮ ያገኙበታል👇👇👇
@EOTCY
Download Telegram
የተከበራቹ የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰቦቻችን ለ2 ዓመታት የኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች በሚል ቻናል የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አስተምሮ የሆኑትን ነገሮች እያቀረብንላቹ ቆይተናል፤ ነገር ግን በታቀደለት ልክ እያደገ አይደለም ፤ የኦርቶዶክስ አስተምሮቶች ለሁሉም ይስፋፋ ዘንድ ቻናላችንን ይጋብዙልን ።
ሀሳብ አስተያታችሁ ይጠቅመናልና https://t.me/eotcy_comment ላይ ይቀላቀላሉ

ቻናሉ https://t.me/eotcy
https://t.me/eotcy
https://t.me/eotcy

ሼር ሼር ሼር

ለወዳጆ ያጋሩልን ዘንድ በአምላከ ቅዱስን ስም እንጠይቃለን🙏🙏🙏

.......እነሆ የተወደደችው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው
1ኛ ቆሮ6÷2
*********************

🔴 #የወር_አበባ በድጋሚ የተለቀቀ

በውስጥ መስመር በተደጋጋሚ የመጡ ጥያቄዎች
ለህቶቻቻችን ይዳረስ ዘንድ ያጋሩልን
#በወር_አበባ_ጊዜ_መስቀል_መሳለም_መጽሐ_ቅዱስ_እና_ሌሎች_ጸሎት_መጽሀፍትን_ማንበብ_ይቻላል

🟢 እንዲሁም ወደ ቤተክርስትያን መሄድ ይቻላል
የወር አበባ በሴቶች ላይ በየወሩ የሚታይ የደም መፍሰስ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን
አስተምህሮ “ደመ ጽጌ፣ አበባ ደም” በመባል ይጠራል፡፡አሰያየሙም የወንድ ዘር
ካላገኘ ከማህጸን ግድግዳ ፍራሽ ጋር በደም መልክ ስለሚፈስና የኋለኛው
ማንነቱ ደምነት ስለሆነ ነው፡፡ ይህም ማለት አገልግሎቱን የጨረሰ፣ ያረጀ፣ ቆሻሻ
ማለት ነው፡፡ ይህ በየወሩ ዑደትን ተከትሎ የሚሄደው የዘር ፍሳሽ በስነ ህይወት
ትምህርት ኦቫሪ (ከዘር ከረጢት) የሚለቀቅ የወንድ ዘር ካላገኘ ኦቫ (ሴቴ ዘር)
ጋር እየተቀላቀለ የሚወርድ ነው፡፡

👉🏾 የወር አበባ #በቤተክርስቲያን አስተምህሮ በሁለት ከፍለን ነው መመልከት ያለብን፤ በዘመነ ኦሪትና ዘመነ ሐዲስ ኪዳን በማለት፡፡
በርግጥ በዘመነ ኦሪት የወር አበባ የርኩሰትና የመርገም ምልክት ነበር፡፡ ለዚህም
ማስረጃነት በመጽሃፍ ቅዱስ ዘሌ 18÷19፣ 20÷18 ያሉ ጥቅሶች “በመርገምዋ
ርኩሰት ሳለች” እና “#ባለ_መርገም_ሴት” በማለት ሲገልጸው፤ ባንጻሩ ደግሞ
ከወር አበባዋ ነጻ የሆነችውን ሴት “#ከርኩሰትዋ_ነጽታ” በማለት የወር አበባ
የርኩሰትና የመርገም ምልክት መሆኑን ይጠቁማል፡፡
በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የወር አበባ የርኩሰትና የመርገም ምልክት መሆኑ ቀርቷል፡፡
ርኩሰት አይደለም፤ ርኩስም አያሰኝም፡፡ በብሉይ ኪዳን አዳምና ሄዋን በገነት
በነበሩ ጊዜ ዕጸ በለስን በልተው #እግዚአብሔርን በደሉ፤ እግዚአብሔርም ሄዋንን
ደመ ዕጸ በለስን አፍስሰሻልና “ወበከመ አድመውኪያ ለእንትኩ ዕጽ ከማሁ
ድምዊ ለለወርኁ፡፡” በማለት ደሟ በየወሩ እንዲፈስ ፈጣሪ ፈረደባት፡፡ ስለዚህ
የሄዋን ደም መፍሰስ መነሻው መርገም ነው፡፡ በሐዲስ ኪዳን #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በፈጸመው #ቤዛነት መርገምነቱና ርኩስነቱ
ተወግዷል፡፡
የወር አበባ በዚህ ዘመን ርኩሰት ወይም መርገም ባይሆንም እድፍ (ቆሻሻ) ነው፡፡

እድፍና ርኩሰት ልዩነት አላቸው፡፡
ርኩሰት ውስጣዊ ነው፤ በንስሃ እንጂ በውሃ አይጠራም፡፡ እድፍ ደግሞ ግዘፍ
አካል ያለው፣ የሚታይና ውሃ የሚያነጻው ነው፡፡ የወር አበባ በሴቶች ባህሪ ሳለ
እንደ ቆሻሻ አይቆጠርም፣ ከሰውነት ሲወገድ ግን ይቆጠራል፡፡ ይህንን
ለማስረዳት ምሳሌ መሆን ከሚችሉት ውስጥ ዛህል (ንፍጥ)፣ ሽንት፣ ምራቅ፣
ዓይነምድርና ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል፡፡

🛑 #ያስተውሉ

ወር አበባ ርኩሰት ባለመሆኑ መስቀል ከመሳም፣ ቤተክርስቲያን ከመሔድ፣ ከመጸለይ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን
ከማንበብና ከመድገም አያግድም፡፡
ነገር ግን ከሩካቤ፣ ከመጠመቅ፣ ከመቁረብና ቤተ መቅደስ ከመግባት ይከለክላል፡፡

#ከሩካቤ :-

ሩካቤ በወር አበባ ጊዜ ከሚከለከሉ ነገሮች አንዱ ነው፡፡ በወር አበባ ጊዜ
የሚደረግ ግንኙነት የህክምና ባለሙያዎች ሳይቀር ለአባላዘር፣ ለልዩ ልዩ
በሽታዎችና ለኢንፌክሽን ሊያጋልጥ እንደሚችል በመናገር እንዳይፈጸም
ይመክራሉ፡፡
👉🏽 በመንፈሳዊው አስተምህሮ ስንመለከተው ደግሞ የሰው ልጅ ዘር #ቅዱስ በሆነው #በእግዚአብሔር አምሳል በመፈጠሩ፣ ይህንን የተከበረ ዘር፣ እዳሪ
ወይም ቆሻሻ ከሆነ ደም ጋር ማዋሃድ ኃጢያት እንደሆነ ይቆጠራል፡፡
#በመጽሐፍ_ቅዱስ ሴት ልጅ በወር አበባዋ ጊዜ እንዳለች የሚፈጸምን ሩካቤ

እርሷም በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች ኃፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ ወደ እርሷ
አትቅረብ” ዘሌ 18÷19፣ ዘሌ 20÷18።

በዚህም ምክንያት በወር አበባ ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ በኦሪትም ይሁን በአዲስ
ኪዳን ክልክል ነው፡፡

👉🏽 #ከመጠመቅ:-

#ሐዋርያው_ቅዱስ_ጴጥሮስይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌ ሆኖ
አሁን ያድነናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፡፡ ለእግዚአብሔር በጎ
ህሊና ልመና ነው እንጂ” 1ኛ ጴጥ 3÷21
በማለት ተናግሯል፡፡ ስለዚህ ጥምቀት
ሥጋዊ እድፍን ማስወገጃ ስላልሆነ፣ ከመጠመቅ በፊት ተጣጥበው እንጂ ከእድፍ
ጋር ለመጠመቅ መቅረብ ተገቢ አይደለም፡፡ የወር አበባም ከላይ
እንደተመለከተው ከሰውነት ሲወጣ እድፍ (ቆሻሻ) በመሆኑ፣ ከዚህ #የቤተክርስቲያን ስርዓት ውጪ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

#ቤተመቅደስ_መግባት ፡-

ሴት በወር አበባዋ ጊዜ የምትከለከለው ነገር #ቤተመቅደስ መግባትን ነው፡፡ይህም
የሆነው በርኩሰት ምክንያት ወይም በኦሪት ሕግ ምክንያት ሳይሆን #በቤተመቅደስ_መፍሰስ ያለበት_ደም_አማናዊ_የሆነውየክርስቶስ_ደም_ብቻ_በመሆኑነው
ይህ ስርዓት #ለሴቶች #ብቻ ሳይሆን #ለወንዶችም ነው፡፡
#አንድ_ወንድ_እየነሰረው_ወይም_የሆነ_ነገር_አካሉን_ቆርጦት_ደም_እየፈሰሰው_ከሆነ_ወደ_ቤተ_መቅደስ_መግባት_የለበትም
👉🏽 ዝንየት (ህልመ ለሊት) ቢያጋጥመው ከ፩ቀን ከቤተ መቅደስ መራቅ
👉🏾 #ምክንያቱም በቤተ መቅደስ ከ #ክርስቶስ ደም ውጪ ሌላ ነገር መፍሰስ ስለሌለበት ነው፡፡

🛑አስተውሉ
**በወር አበባ ላይ ሳለች ሴት #ወደ_ቤተመቅደስ_አትግባ_ማለትቤተ_ክርስቲያን_አትሂድ_ማለት_ሳይሆን_ወደ_ቤተክርስቲያን_ሄዳ_የመጀመሪያውን_ቅጽር ( #አጥር ) #ከገባች_በኋላ_በመጠለያ_ውስጥ_በመሆን_ትጸልይ_ትማር ወይም ማንኛውንም
አይነት መንፈሳዊ ስራዎችን ሰርታ ትመለስ ማለት ነው፡፡
#ከመቁረብ፡-
ሴቶች ከወር አበባ ሳይነጹ #ሥጋ_ወደሙ መቀበል አይችሉም፡፡ ይህንን ስርዓት ተላልፈው ወደ ሥጋ ወደሙ እንዲቀርቡ ያደረገ ዲያቆንም ይሁን ቄስ ከክህነቱ
እንዲሻር #ፍትሕ_ነገስት ይደነግጋል፡፡ “ከግዳጅዋ ያልነጻችውን ሴት በደሟ ወራት
#ከቤተ_ክርስቲያን_አግብቶ_ሥጋውን_ደሙን_ያቀበለ_ከክህነቱይሻር፡፡” ፍትነገ 6፣
ዘሌ 7፡19
#ይህ_ሥርዓት_በሴቶች_ላይ_ብቻ_ሳይሆን_ወንዶችም_ህልመ_ለሊት
በሚያጋጥማቸው ሰዓት እንዳይገቡ ይከለከላል፡፡


ቤተ ክርስቲያን የገነት ምሳሌ ናት፡፡ ሔዋን ከአዳም ጋር በገነት ለሰባት ዓመታት
ስትኖር የወር አበባ አታይም ነበር፡፡ ቤተ መቅደስ የገነት ምሳሌ መሆኗ የተሟላ
እንዲሆን የወር አበባ የምታይ ሴት ወደ ቤተ መቅደስ አትገባም፡፡

........የተወደደችው ሰዓት አሁን ነው ፤ የሐዳን ቀን አሁን ነው
1ኛ ቆሮ 6÷2

ይህን የእናት ቤተክርስቲያን ትምህርት ለሌሎቹም እህቶቻችን ሼር በማድረግ
እናካፍላቸው፡፡
💚 @eotcy 💚
💛 @eotcy 💛
@eotcy
እባካችሁ የተሳሳተ voice ነው ሼር በማድረግ አትተባበሩ ሙሉውን ከታች ይነበብ👇👇👇
Https://t.me/eotcy
ወንድሞቼ አና እህቶቼ የማክበር ሰላምታዬን እያቀረብኩ መልእክቴን አደርሳለሁ ይህንን መልእክት ለውድ ኦርቶዳክሳውያን ሼር በማድረግ ተባበሩን። በመጀመሪያ ከላይ የላኩትን የሀሰት ድምጽ ይስሙት👆👆
@eotcy
የውሸት አስተምሮ ነው አትመኑ እየተበተነ ነው ይህም አስተምሮ አጠር አርጌ እገልጽላቾኋለሁ
@eotcy

📌 ውሸቱም

የተወደድክ እባክህ ለማንበብና ለማስተላለፍ ሞክር፡ እውነተኛ ታሪክ ነውና።
አንድ የታመመች ሴት ነበረች በህልሟም የድንግል ልጅ ጌታችን መደኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትጠጣ ውሀ ሲሰጣት አየች፡ ..................

የሚል ነበር ሙሉዉን ከላይ ለቅቄላች ኋለሁ

እባክህን ይሄን መልዕክት ለ 13 እና ከዛ በላይ ለሆኑ ለምታውቃቸው ሰዎች ላክ እና እመነኝ የሆነ ነገር በህይወትህ ይክሰታል።
ይቅርታ ስለረበሽኩህ ፡ እኔ አምላክህ ነኝ፡

✔️የገረመኝ አምላክ ከመቼ ጀምሮ ነው ጹሁፍ መጻፍ የጀመረው
@eotcy
ጸልይ አልልህም ብቻ አወድሰኝ(አሞግሰኝ) እና እባክህ እስከ ሌሊት በቻልከው መጠን ለአለም ሁሉ ይሄን መልእክት ላክ።
@eotcy
✔️የሰው ልጅ ካልጸለየ አምላኩ ጋር በምን ይገናኛል አስተውሉ ወገኖቼ

በእግዚአብሔር የምትተማመን ከሆን መልእክቱን ላክ ነገህ ደሰ የሚያሰኝ ይሆንልሀል።
✔️እኛ ኦረቶዶክሳዊያን ሁሌም በእግዚአብሔር እንተማመናለን
@eotcy
ግን በህይወትህ ለእግዚአብሔር ቅድሚያ ትሰጣለ? አዎ ከሆነ መልስህ አሁን የምትሰራውን ነገር ሁሉ ትተህ ይሄን መልእክት ለ12 ሰዎች አሁኑኑ ላክ

✔️ለእግዚአብሔር ቅድሚያ የሚሰጠው ጹሁፍ ባሰራጨ ሳይሆን ለስሙበመዘመር
ጾም በመጾም ጸሎት በማድረግ እና
ኦርቶዳክሳዊ ሰነምግባር በመላበስ ነው
@eotcy
መልእክት ለ12 ሰዎች አሁኑኑ ላክ ከዛ ጌታ ነገ ምን እንደሚያደርግልህ ታያለህ እግዚአብሔር ይወድሀል። እመነኝ ከ 7 ቀን በኋላ ህልምህ እውን ይሆናል።

☑️እዩት በጣም ውሸት መሆኑን ከዚ እንረዳለን ለ 12 ሰዎች ስለተላከ ምንም አይነት ህልም እውን እንደማይሆን አጥብቄ እነግራችኋለሁ
@eotcy
ይህን የውሸት ጹሁፍ መንፈሳዊ አስመስለው የእናታችንን ድንግል ማርያምን ስም ከተው ኦርቶዳክሳዊያን እህት ወንድሞቻችንን ሲያታሉ አመታት ተቆጥረዋል አሁን ግን ከዚህ ተረድታቹ የሚላክላችሁን ጹሁፍ ትክክል መሆኑን አባቶችን በመጠየቅ ተረድታቹ ነው ለሰው ሼር ማረግ ያለባቹ
ባላቹሁበት በሰላም ቆዩልኝ

ህይወት የሚሰጠንን ቅዱስ ቃሉን ብቻ ሼር እናድርግ

👉 @eotcy 👈
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
#ሦስት_ስገድ
___
አንድ ሰው በጣም ይጸጸት እና ንስሐ ገብቶ ተገቢውን ቀኖና (ቅጣት) ተቀብሎ ፈጣሪውን እያስደሰተ ለመኖር ወስኖ ወደ አንድ ካህን ይመጣል።
ካህኑም ተገቢውን የአባትነት አቀባበል አድርገውለት ሲያበቁ የመጣበትን ጉዳይ ማስረዳት ቀጠለ ። ከዚያም ልቦናውን ታዛቢ ፣ አንደበቱን ከሳሽ ፣እግዚአብሔርን ዳኛ አድርጎ የሠራውን ልዩ ልዩ ዘግናኝና ከባባድ ኃጥያት አንድ በአንድ በዝርዝር ተናገረ ። እኒያ አባት ሁሉን በትእግስት ካዳመጡ ቡኃላ ተገቢውን ምክርና ተግሳጽ ሰጥተው ሲጨርሱ
"በል ሦስት ስገድ " ይሉታል ። ሰውዬውም
" በየቀኑ ሦስት ሦስት ማለትዎ ነው አባቴ ?" ይላቸዋል ። ካህኑም "የለም የለም ሦስት ብቻ ስገድ " አሉት ።
በዚህ ጊዜ ሰውዬው በጣም ተገርሞ " እንዴ አባቴ ሦስት ነው ወይስ ሶስት መቶ ነው ? " ሲል አስረግጦ ይጠይቃቸዋል ። ካህኑም " ኧረ ሦስት ነው ያልኩህ ልጄ የምን ሶስት መቶ አመጣህብኝ እንዴ ያላልኩትን? #ብቻ_ስትሰግድ_በደልህን እያሰብክ የፈጣሪህን ምህረት እና ይቅርታ ከልብህ እየተማጸንክ በልብህ ጉልበት ጭምር ስገድ " ይሉታል ። ሰውዬውም በጣም እየተገረመ እና እየተደነቀ የካህን ትዕዛዝ ነው እና አመስግኖ ተነስቶ ይሔዳል። ከዚያም እግዚአብሔር ለካህኑጨ(ለንስሐ አባቱ) ይገለጥለት እና
" እንዴት እንዴት ነው ያን ሁሉ ኃጥያት ነግሮህ ሲያበቃ ሦስት ብቻ ስገድ የምትለው ? " ሲል ይጠይቃቸዋል ። እኒያ አባትም ፈገግ እያሉ
" አይ ፈጣሪዬ ይሄንንም እኔ ሁኜ ነው እንጂ አንተ ብትሆን እኮ በነጻ ነበር የምታሰናብተው " አሉት ይባላል ።
.........................

ይኼ የእግዚአብሔርን ከባቴ አበሳነት በሚገባ የሚያስረዳ ምናባዊ ታሪክ ነው ።
እንዲህ ሲባል ንስሐ አያስፈልግም ማለት ሳይሆን ያለ እግዚአብሔር ቸርነት ሦስትም ሦስት መቶም ብንሰግድ ጥቅም እደሌለን እድናውቅ ነው።
👉 ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የእግዚአብሔርን መሐሪነት እዲህ ይገልጠዋል። " የራበው ሰው ለምግብ፤ የጠማው ሰው ለመጠጥ እደሚቸኩል እግዚአብሔርም እኛን ለመማር / ምህረት ለመስጠት / ይቸኩላል" አባቶቻችንም የእግዚአብሔርን የምሕረቱን ጥግ ስለሚያውቁ ርህሩህ ናቸው።
እንደ ኃጥያታችን ክፋት አይቶ ምህረቱን ከኛ ያላራቀ የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው ። " ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምህረት የተነሳ ነው፤ ርኀራኄው አያልቅምና" ኤር 3፥23

.....እነሆ የተወደደወ ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው🤲
-1ኛ ቆሮ6÷2

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 ይህን በመንካት ይቀላቀሉን 👈
👉 ይህን በመንካት ይቀላቀሉን 👈
👉 ይህን በመንካት ይቀላቀሉን 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
" #ከምታማኝ_ስመለስ_ምከረኝ "
.......................................

ይህንን ጥቅስ ዛሬ በታክሲ ተሳፍሬ ወደ ቤቴ ስጓዝ ተለጥፎ ተመለከትኩ። ሀሳቡ ስለገዛኝ ደጋግሜ አብሰለሰልኩት። ትልቅ መልእክት ነው።

ሐሜት ማለት በቁሙ ዐሚታ ፣ነቀፋ ፣ስድብ ፣ክፉ ነገር፣ ገመና ፣ነውር ፣ስም የሚያጠፋ ፣የሚሰብር በእውነት ወይም በሐሰት የሚነገር ማለት ነው፡፡
ሐሜት ሰውን ያለመሳሪያ የሚገድል መሳሪያ ነው።

ሐሜት በራሳቸው የማይተማመኑ ስለሚያወሩት ነገር እንኳን እርግጠኛ ያልሆኑ ማስረጃቸውን እንኳን "በአሉ" የሚያቀርቡ የራሳቸው ሀሳብ የሌላቸው የዝቅተኛ አስተሳሰብ ባለቤት የሆኑ ሰዎች የስራ ዘርፍ ነው።

<< ለሐሜት የሚሄድ ሚስጢሩን ይገልጣል ፣ በመንፈስ የታመነ ግን ነገሩን ይሰውራል " ምሳ 11÷13
እንደሚል ቅዱስ ቃሉ ሐሜተኛ ሰው #በእግዚአብሔር በሰውም ዘንድ የተጠላ ነው። ስለዚህ ሰውን ከምናማው ይልቅ ጥፋቱን እንገረው ምን አልባት ጥፋታቸው
ሲነገራቸው የማይቀበሉ፣ የማይሰሙ፣ የሚያኮርፉ፣ የሚናደዱ እና
የሚጠሉንም ጭምር ይኖራሉ እኛ ግን ይህን ሁሉ ቢያስቡም ከምናማቸው
መንገር ብቻ ነው ትክክለኛ መፍትሔው መምከርም ጭምር ያስፈልጋል ሐሜት በጥቅሉ አላስፈላጊ ነገር ነው
#ሐዋርያው_ቅዱስ_ጴጥሮስ እንደተናገረ
"እንግዲህ ክፋትን ሁሉ ተንኮልንም ሁሉ ግብዝነትም ቅንዓትም ሐሜትንም ሁሉ አስወግዳችሁ ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደሆነ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደተወለዱ ህጻናት ተንኮል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ"
1ኛ ጴጥ 2÷1-3

እንደተባለ #ከእግዚአብሔር ለመገናኘት ህጉንና ትዕዛዛቱን በመፈጸም እንደ ህጻናት ልንሆን ያስፈልጋል
" እንደ ሕፃናት ካልሆናችሁ ከቶ የእግዚአብሔርን መንግሥት አትወርሱም " ማቴ 18÷3 ከሐሜት መራቅ ያስፈልጋል።

ሌሎች ሰዎችም ሐሜት ሲጀምሩልን እንደ ሶቅራጥስ ይህንን እንጠይቃቸው...

በአንድ ወቅት ወደ ታላቁ ፈላስፋ ወደ ሶቅራጥስ አንድ ሰው መጥቶ እንዲህ አለው ፡-

‹‹እገሌ ስለተባለው ወዳጅህ የሠማሁት ደስ አይልም›› አለው፡፡ ሶቅራጦስ ግን ዝም አለ፡፡ ሠውየውም እንደገና፡- ‹‹ይገርማል ከእርሱ አይጠበቅም፤ በጣም ገርሞኛል›› አለው፡፡

ሶቅራጠስም እንደማይለቀው ስለተረዳ፡-
‹‹ ስለ ወዳጄ ልትነግረኝ የፈለግከውን ልሠማው የምችለው ሶስት ጥያቄዎች አሉኝ፤ እነርሱን ስትመልስልኝ ብቻ ነው›› አለው፡፡ ሠውየውም ተስማማ፡፡

1,‹‹የመጀመሪያው ጥያቄዬ የእውነት ጥያቄ ነው፡፡

" ስለወዳጄ የሠማኸው መቶ በመቶ እውነት ነው ወይ?›› አለ፡፡

ሠውየውም፡- ‹‹መቶ በመቶ እርግጠኛ መሆን አልችልም››አለው፡፡ ያው እንግዲህ " አሉ " እያለ ሊያወራ ነበር።

ሶቅራጦስም ቀጠለ፡-

2,‹‹ልትነግረኝ የፈለግከው እርግጠኛ ያልሆነነገር ነው ማለት ነው፤ ሁለተኛው ጥያቄዬ የመልካምነት ነው፡፡ " የምትነግረኝ መልካም ነገር ነው ወይ?›› አለው፡፡

ሰውየውም፡- ‹‹እርሱማ መልካም አይደለም›› አለው፡፡

ሶቅራጦስም፡-

3,‹‹አንደኛ እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፤ ሁለተኛ መልካም ያልሆነ ነገር ልትነግረኝ ፈልገሃል፡፡ ሶስተኛ ጥያቄ አለኝ?›› አለው፡፡
ሠውየውም፡- ‹‹እሺ›› አለ፡፡

ሶቅራጦስም፡-

4,‹‹ለእኔ የሚጠቅመኝ ነገር አለው ወይ?››አለው፡፡

ሠውየውም፡- ‹‹የለም›› ብሎ መለሠ፡፡ሶቅራጦስም በመጨረሻ፡-

5,‹‹እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፤ መልካም ያልሆነ፤ ለእኔ የማይጠቅም ነገር አልሠማም››አለው ይባላል፡፡

ወዳጆቼ እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፣ መልካም ያልሆነ እና በሕይወታችን ላይ ጉልህ ሚና የሌለው ነገር ላይ ጊዜን ማጥፋት ትልቅ ብክነት ነው፡፡አንዳንድ ሠዎች በማይመለከታቸው ነገር እድሜአቸውን ይገፋሉ፡፡ በዚህም መልሠው ማግኘት የማይችሉትን ውዱን ጊዜአቸውን የሰውን ሥጋ በመብላት ያባክናሉ።

ሐሜት የሰውን ስጋ እንደመብላት ስለሆነ ሁላችንም ከሐሜት እራሳችንን ልናርቅ ይገባል !!

መልካም ምሽት ይሁንላችሁ 🙏




🟢 @eotcy 🟢
🟡 @eotcy 🟡
🔴 @eotcy 🔴
ዛሬ ይህቺን ልበላችሁ👇👇


👉እጅህ ላይ ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።


👉በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቀም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።


👉ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5


👉የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።


👉በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።


👉ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ. 29፥27

👉በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።


በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።

#ልብ_በሉ

ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው።

ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።

በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

(አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ - መንፈሳዊው መንገድ መጽሐፍ አያሌው ዘኢየሱስ እንደተረጎመው።)
🌻
የሕይወት ፡ እናቱ ፡ ሆይ፤ ተቀዳሚ ፡ ተከታይ ፡ በሌለው ፡ በአንድ ፡ ልጅሽና ፡ በእኛ ፡ መካከል ፡ አስታርቂን።

እነሆ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው
-1ኛቆሮ 6÷2

Join @eotcy
ንጉስ ሰሎሞን እና ጉንዳኗ

ንጉስ ሰሎሞን ለተፈጥሮ ባለው ፍቅር ይታወቃል እርሱ በየጊዜው በአትክልት ስፍራዎቹ በወንዝ ዳርቻዎችና በተራራዎች ላይ ይዘዋወር ነበር።

እርሱ እንስሳትን ወፎችን ዓሳዎችንና ነፍሳትን በፍላጎት በመመልከትና በደመ ነፍሳቸው ውስጥ የተገለጠውን የጥበባቸውን ጠባይ በማየት እግዚአብሔር ለእነርሱ ያለውን እንክብካቤ ያረጋግጥ ነበር።

ከዕለታት አንድ ቀን ታዲያ ትኩረቱ በአንዲት ትንሽ ጉንዳን ላይ ያርፋል። ጉንዳጊቱ ከእርሷ ክብደት ብዙ እጥፍ የሚበልጠውን የጥሬ ግማሽ ተሸክማ እየሄደች ነበር። ጉንዳኗ ይህን የጥሬ ስባሪ ተሸክማ የምትጓዘው በጉንድጓዷ ውስጥ ለማከማቸት ነበር።
@eotcy
በዚህ ጊዜ ንጉሡ እጅግ ስለተደነቀ ይህቺን ጉንዳን ለምንድን ነው የማላስደስታት ይላል። እርሱ ይህን ያለው ያላትን ጉልበት ሁሉ ከዚህ የጥሬ ድቃቂ ላይ ስታጠፋ ስለተመለከተ ነበር።
"እግዚአብሔር ይህን ያህል ታላቅ ሃብት ለእኔ የሰጠኝ ደስታን ለህዝቤ ብቻ እንድሰጥ ሳይሆን ለእንስሳትም ለወፎችም ለነፍሳት ጭምር እንድሰጥ ነው።
@eotcy
ንጉሡ ይህን ብሎ ጉንዳኒቱን ካነሳ በኋላ ውስጡ እጅግ ለስላሳ በሆነ ሐር የተነጠፈ የወርቅ ሳጥን ውስጥ ያስቀምጣታል። ከእርሷ ጋር በወርቅ ሳጥኑ ውስጥ አንድ የስንዴ ቅንጣት ካስቀመጠላት በኋላ ከፈገግታ ጋር በየዕለቱ ምንም ሳትደክሚ የምትበይውን የስንዴ ቅንጣት ስለምሰጥሽ ከእንግዲህ በኃላ አትደክሚም በጎተራዬ ውስጥ የተትረፈረፈው ጥሬ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን እንስሳትን ወፎችንና ነፍሳትን የሚመግብ ነው አላት።

ንጉሡ እንዲህ ያለውን መልካም እንክብካቤ ለእርሷ ስላደረገላት ጉንዳኒቱ ታመሰግለዋለች።
@eotcy
በሚቀጥለው ቀን ንጉሡ ወደ ጉንዳኒቱ ተመልሶ ሲመጣ የተመገበችውን የአንዱን ቅንጣት ስንዴ ግማሽ እንደሆነ ሲመለከት እጅግ ይደነቃል። ሌላ አንድ የስንዴ ቅንጣት አስቀምጦላት በሚቀጥለው ቀን ተመልሶ ሲመጣ ጉንዳኗ ግማሹን ቅንጣት ተመግባ ግማሹን እንዳስቀመጠች ይመለከታል።

ይህ ሁኔታ እየተደጋገመ መሄዱን የተመለከተው ንጉሥ ሰሎሞን ጉንዳኗን ለምንድን ነው ሁል ጊዜ የአንዱን ቅንጣት ስንዴ ግማሽ የምታስቀልጭው? በማለት ይጠይቃታል።
@eotcy
ጉንዳኒቱም እንዲህ በማለት መለሰችለት እኔ በየዕለቱ የስንዴውን ግማሽ የማስቀምጠው ለመጠባበቂያ ነው አንተ ለእኔ ምን ያህል እንክብካቤ እንዳደረክልኝና በጎተራዎችህ ውስጥ ምን ያህል የበዛ ጥሬ እንዳለህ አውቃለሁ ይሁን እንጂ አንተ ሰው ስለሆንክ በየዕለቱ የምትከውነው የስራህ ብዛት እኔን እንድትረሳኝ ያደርገሃል ይሄ በሚሆንበት ጊዜ ያስቀመጥኳትን የስንደ ቅንጣት ከረሃብ ትታደግልኛለች ምግቤን በድካሜ እንዳገኝ የተወኝ እግዚአብሔር አይረሳኝም አንተ ግን ልትረሳኝ ትችላለህ።

በዚህ ጊዜ ንጉሡ ጉንዳኗን ወደ ቀደመ ሕይወቷ ተመልሳ ኑሮዋን እንዴትቀጥል ይለቃታል
እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያስቀመጠውን ነገር ለእርሷ እንደሰጣት ተገንዝቧልና።

ፈጥሮ የማይጥል ወዶ የማይጠላ እግዚአብሔር ብቻ ነው።
ክርስቲያኖች ሰው እንደተሰባሪ ብርጭቆ ነው።
እግዚአብሔርን የተመረኮዘ አይወድቅም።

.......የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ የመዳን ቀን አሁን ነው
-2ኛ ቆሮ6÷2

💚 @eotcy 💚
💛 @eotcy 💛
@eotcy
📌 ታላቅ የንግስ በዓል ጥሪ
ሰማዕታት የዚህችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ
ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ
ስለ መንግስተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ
ውዳሴ ማርያም የሐሙስ

👉የሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስና የዓለም ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ሐምሌ 5 የእረፍት መታሰቢያ በዓልን ታስቦ ይውላል። ይህንን ታላቅ በዓል በስማቸው በተሰየመው በጥንታዊውና አንጋፋው ደብር በብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስወ ጳውሎስ እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ይከብራልእርሶም ከወዳጆቾ ጋር በመምጣት ከቃልኪዳናየው የሳተፉ ዘንድ በአምላከ ጴጥሮስወ ጻውሎስ ስም ተጋብቻችኃል።

አድራሻ 👉 ከፒያሳ ወደ አስኮ ሲመጡ ዊንጌት ዊንጌት ኮሌጅ አጠገብ
👉 ከጦርኃይሎች መስመር ለሚመጡ እንዲሁ ከሁሉም አቅጣጫ ለሚመጡ ዊንጌት አደባባይ ገባ ብሎ
💚 @eotcy 💚
💛 @eotcy 💛
@eotcy
#ካልባረከኝ_አለቅህም

ከመጽሐፍ ቅዱስ ቅምሻ
@eotcy

ዘፍጥረት 32፥26

#እንዲህም አለው፡— ሊነጋ አቀላልቶአልና ልቀቀኝ። #እርሱም፡— ካልባረክኸኝ አልለቅቅህም፡ አለው።
@eotcy
ያዕቆብም ወደ እናትና አባቱ ምድር ሲመለስ ላሞችንም አህዮችንም በጎችን ወንዶች ባሪያዎችንም ሴቶች ባሪያዎችንም ሚስቶችና ልጆችን ሁሉ ይዞ ተመለሰ ግን ዔሳው እንዳይገድለው ፈራ።
ያዕቆብም እጅግ ፈርቶ ተጨነቀ፤ ከእርሱም ጋር ያሉትን ሰዎች መንጎችንም ላሞችንም ግመሎችንም በሁለት ወገን ከፈላቸው፤
#እንዲህም አለ፡— ዔሳው መጥቶ አንዱን ወገን የመታ እንደ ሆነ የቀረው ወገን ያመልጣል።
በዚያች ሌሊትም ተነሣ፥ ሁለቱን ሚስቶቹንና ሁለቱን ባሪያዎቹን አሥራ አንዱንም ልጆቹን ወስዶ የያቦቅን ወንዝ ተሻገረ።
ያዕቆብ ኑሮው ሀብቱና ብቸኝነቱ ተቀይሯል እንጂ ማንነቱና ስሙ አልተለወጠም ነበር።
ያዕቆብም ለብቻው ቀረ፤ አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታገለው ነበር።
እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ የጭኑን ሹልዳ ነካው፤
#እንዲህም አለው፡— ሊነጋ አቀላልቶአልና ልቀቀኝ። #እርሱም፡— #ካልባረክኸኝ_አልለቅቅህም፡ አለው። አይገርምም ይህን ሁሉ ሀብትና ሰው ሰጥቶት አሁንም በረከትን ይፈልጋል ምክንያቱም አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲሱ አቁማዳ ነው።
#እንዲህም_አለው፡— ስምህ ማን ነው? እርሱም፡— ያዕቆብ ነኝ፡ አለው።
#አለውም፡— #ከእንግዲህ_ወዲህ_ስምህ_እስራኤል_ይባል_እንጂ_ያዕቆብ_አይባል_ከእግዚአብሔር_ከሰው_ጋር_ታግለህ_አሸንፈሃልና።ብሎ በዚያም ስፍራ ባረከው።
#ያዕቆብም፡— እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች አለ ይህን ሲል ያዕቆብ እያነከሰ ነበር ታዲያ እያነከሰ እንዴት ሰውነቴ ድና ቀረች ይላል?
ያዕቆብ በመነካቱ የተለወጠው ድሮ ሲወጣ የነበረው አጭበርባሪው ማንነቱ ሲሆን ፤ ሌላው ደግሞ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አይቶ በህይወት የሚኖር የለምና እኔ ግን ድኛለው አለ። ወንዙን ባለፀጋ በመሆን ብቻ ሳይሆን እስራኤል ተብሎ የተመረጠ የእግዚአብሔር ህዝብ አባት ሊሆን ተሻገረ። ዔሳውም ጋር በሰላም ተገናኘ ምክንያቱም አሁን የትናንቱ ያዕቆብ አይደለም።
እኛም አመታትን ስናስቆጥር በቁስ ብቻ መለወጥ ሳይሆን የትናንቱ ጉድፍ ማንነት ከኛ ላይ እንዲወድቅና ስማችንን እንዲቀይር አዲስን ማንነት እንዲሰጠን ሁሉን ቻይ ነውና እግሮቹ ስር ወድቀን ካልባረከን አንለቅህም እንበለው።
@eotcy
☝️እርግጠኛ ነሽ ግን ፀንሰሻል?!

ዝኆን እና ውሻ በተመሳሳይ ጊዜ ይፀንሳሉ ፡፡ ከ3 ወራቶች በኋላ ውሻዋ ቡችላዎችን ወለደች፡፡ ዝኆኗ እንጸነሰች ከስድስት ወራት በኋላም ውሻዋ በድጋሚ ፀነሰችና ብዙ ቡችሎች ወለደች፡፡

🐕 . . . በ18ኛው ወር ውሻዋ ወደ ዝኆኗ ጥያቄ ይዛ ቀረበች ÷ “እርግጠኛ ነሽ ነፍሰ ጡር ነሽ?! አሁን በሆድሽ ጽንስ አለ? በተመሳሳይ ቀን ነፍሰ ጡር ሆነን ነበር ፥ እኔ ከ16 በላይ ቡችሎች ወለድኩኝ ። አሁን ግማሾቹ በዚህ ሰዓት አድገው ትልልቅ ውሾች ሆነዋል : ግን አንቺ አሁንም ነፍሰ ጡር ነኝ ትያለሽ፡፡ የጤና ነው?"
@eotcy
🐘 ዝኆኗም መለሰች “ልታውቂው የሚያስፈልግሽ አንድ ነገር ÷ በማህጸኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝኆን ነውና በ2 ዓመት ውስጥ አንድ ብቻ እወልዳለሁ፡፡ የምወልደው ግን ተራ እንስሳ አይደለም! ልጄ መሬቱን ሲመታ ምድር ይሰማታል፡፡ ልጄ መንገዱን አቋርጦ ሲሻገር የሰው ልጅ ቆሞ እያደንቀው ይመለከታል ፤ እርሱ ሲንቀሳቀስ ሁሉም ይንቀጠቀጣል። የእኔ ልጅ የፍጥረትን ትኩረትን ሁሉ የሚስብ ኃያል ነው።" ስትል፡፡
@eotcy
አንዳንዶች ምድራዊ በረከቶችን በመመልከት ታላላቅ ዋጋ የሚያሰጡን የበጎ ምግባራትና ትሩፋት ዋጋዎችን የምንቀበልበት ጊዜ ÷ በብዙ መቃተት የተሸከምናቸው ፈተናዎቻችንንም የምንገላገልበት ቀን ይዘገይብናል ÷ የፀሎት ልመናችን መልስ ይርቀናል ። ነገር ግን ፈጣሪያችን ቢዘገይ የሚቀድመው የሌለ ÷ የጊዜያት ቀመር ስንኳ ለእርሱ ውብ ሥራ ገደብ የሚሆኑበት አይደለምና በሚታይ አገልግሎት ውስጥ የማይታዩ መንፈሳዊ ጸጋዎችን ተስፋ ማድረግን ለዘወትር አንርሳ! ያን ጊዜ ያለ ማንጎራጎር በማመስገን እንኖራለን። ደሃውና ምስኪኑ አልአዛር ስለ ድኅነቱ ቢመረር እንኳ ባለማማረሩ በአብርሃም እቅፍ እንደገባ እግዚአብሔር የሁላችንን ዋጋ አይረሳምና!

'በኀዘን ጊዜ የማያጉረመርሙ ከንፈሮች ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋር እኩል ናቸው!'

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@eotcy
📌🛎 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

🕯እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

🕯ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ

📖 ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)

የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር:: ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ በዚህች ቀን (ሰኔ 30) ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

👉መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ

❇️ የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ
❇️ በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
❇️ በበርኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
❇️ እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
❇️ የጌታችንን መንገድ የጠረገ
❇️ ጌታውን ያጠመቀና
❇️ ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::

🕯ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን ነቢይ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ጻድቅ: ገዳማዊ: መጥምቀ መለኮት: ጸያሔ ፍኖት: ቃለ ዐዋዲ ብላ ታከብረዋለች::

🕯 አባ ጌራን ሕንዳዊ

👉 ዳግመኛ በዚህች ቀን ሕንድ ካፈራቻቸው ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት ጻድቁ አባ ጌራን ይታሰባሉ:: የእኒህ ቅዱስ ታሪክ አሳዛኝ ነው:: ቅዱሱ በሕንድ ተወልደው: በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አድገው: ገና በወጣትነታቸው መንነው: ደሴት ውስጥ ወደሚገኝ አንድ በርሃ ገብተዋል:: ከገድላቸው ጽናት: ከቅድስናቸውም ብዛት የተነሳ በሃገረ ሕንድ ሰይጣን እንዳይገባ: ጠብ ክርክር እንዲጠፋ: ሰው ሁሉ በፍቅርና በሰላም እንዲኖር ማድረግ ችለው በጣም ተወዳጅ ነበሩ::

🕯 በዚህ የተበሳጨ ሰይጣን ግን ባልጠረጠሩት መንገድ መጣባቸው:: አንዲት ሴት ወደ እርሳቸው መጥታ (የንጉሡ ልጅ ነኝ በሚል) አስጠግተዋት ነበር:: አንድ ሌሊት ላይ ግን አውሬ ያባረራት በመምሰል ሩጣ ወደ ቤታቸው ገብታ አቀፈቻቸው:: በዚያ ቅጽበት ፍጡር ደካማ ነውና ታላቁ አባ ጌራን ተሰነካከሉ:: ከአፍታ በሁዋላ የሆነውን ሲያውቁ ደም አለቀሱ::

🕯 ልብሳቸውን ቀደው: እንባቸው እንደ ዥረት እየፈሰሰ አለቀሱ:: ራሳቸውን በትልቅ ድንጋይ እየቀጠቀጡት የጭንቅላታቸውና የደረታቸው አጥንቶች ተሰባበሩ:: እርሱ እግዚአብሔር መሐሪ ነውና ይቅር ብሎ: የቅድስና ስም ሰጥቶ በዚሕች ቀን ወደ ገነት አሳርጉዋቸዋል:: ለዚህ ነው መጽሐፉ "ጻድቅ 7 ጊዜ ይወድቃልና: ይነሣማል" ያለው:: (ምሳ. 24:16)

🕯 አምላካችን ከቅዱሱ ቤተሰብና ከጻድቁ አባ ጌራን በረከት ይክፈለን::

🕯ሰኔ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=

1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ልደቱ)
2.ቅዱሳን ዘካርያስና ኤልሳቤጥ (ወላጆቹ)
3.አባ ጌራን መስተጋድል (ሕንዳዊ)
4.ቅዱሳት ደናግል ማርያና ማርታ (ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት-የአልዓዛር እህቶች)

🕯ወርኀዊ በዓላት @eotcy

1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ)
2.አባ ሣሉሲ ክቡር
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
@eotcy
📖 ደግሞም አንተ ሕጻን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ:: መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሔዳለህና:: እንደዚህም የኃጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ:: ይሕም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው::(ሉቃ. 1:76)

💚 ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@eotcy
+ ይህ ሕፃን ምን ይሆን? +

በመጥምቁ ዮሐንስ ልደት ዙሪያ ለአንድ መንፈሳዊ መጽሔት የሚሆን ጽሑፍ በአስቸኳይ እንዳዘጋጅ አንድ ወዳጄ ጠየቀኝ፡፡ ‘አደራ ያልታተመ አዲስ ጽሑፍ’ የሚል ማሳሰቢያም አከለበት፡፡ በመጥምቁ ዙሪያ በርከት ያሉ ጽሑፎች ቢኖሩኝም ሁሉም ወይ በመጽሔት ወይ በኢሚዲያ የታተሙ ናቸው፡፡ አዲስ ጽሑፍ ለመጻፍ ደግሞ የነበርኩበት ውጥረትና ጻፍ ጻፍ የሚል ውስጣዊ ግፊት ስላጣሁ ልጽፍ ‘ዮሐንስ’ የሚል የጽሑፍ ፋይል ከፍቼ ጀምሬ መንፈሳዊ ነገር በትግል አይሆንምና ተውሁት፡፡ በዓሉም ካለፈ ወዳጄም ካኮረፈ በኋላ ግን ‘ዮሐንስ...’ ብቻ ብዬ የተውኩትን ፋይል ዛሬ ስከፍተው አንድ ነገር ትዝ ብሎኝ ተደመምኩ፡፡

ስለ ዮሐንስ ለመጀመሪያ ጊዜ የጻፈለት ማን ነው? የመጥምቁ ዮሐንስ ነገር በአራቱም ወንጌላት ተብራርቶ ሳይጻፍ በፊት ፣ በገድለ ዮሐንስ መጥምቅ ሳይዘረዘር በፊት ፣ ማሕሌት ሳይቆምለት ፣ ቅኔ ሳይዘረፍለት በፊት ስለ ዮሐንስ ለመጀመሪያ ጊዜ መጻፍ የተጀመረው መቼ ነበር? ስለ መጥምቁ ብዕሩን ያነሣው የመጀመሪያው ጸሐፊስ ማን ነበር? ምን ብሎስ ስለ እርሱ ጻፈ? የሚለውን አስታወስሁ፡፡

ስለ መጥምቁ ዮሐንስ የተጻፈው የመጀመሪያው ጽሑፍ በብራና ነበረ፡፡ ጸሐፊው ደግሞ አባቱ ዘካርያስ ነበር፦
‘ብራናም ለምኖ። ስሙ ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያንጊዜም አፉ ተከፈተ መላሱም ተፈታ እግዚአብሔርንም እየባረከ ተናገረ፡፡ ለጎረቤቶቻቸውም ሁሉ ፍርሃት ሆነ፤ ይህም ሁሉ ነገር በይሁዳ በተራራማው አገር ሁሉ ተወራ፤ የሰሙትም ሁሉ። እንኪያ ይህ ሕፃን ምን ይሆን? እያሉ በልባቸው አኖሩት’ ሉቃ. 1፡63

ጎረቤቶቹ ‘ይህ ሕፃን ምን ይሆን?’ አሉ፡፡ እውነታቸውን ነው ፤ ገና በተወለደ በስምንት ቀኑ ገድሉ በብራና መጻፍ የተጀመረለት ሕፃን እንደምን ያለ ነው? አፉን ሳይፈታ በእግሩ መሔድ ሳይጀምር ብራና የሚለመንለት ሕፃን እንደምን ያለ ነው? ነገሩን አልኩ እንጂ ዮሐንስ ገና ከማሕፀን ሳይወጣ ስግደት የጀመረ መናኝ ፣ የድንግል ማርያምን ድምፅ ከሌላ ሰው ድምፅ ለይቶ ሰላምታዋን ሲሰማ የሚዘል ሕፃን ነበርና የሱ ነገር ከሥር ከሥር ካልተጻፈ አይዘለቅም፡፡

አባቱ ስለ ዮሐንስ ብዙ አልጻፈም፡፡ ‘ስሙ ዮሐንስ ነው’ ብቻ ብሎ አበቃ፡፡ መጥምቁን ለማክበር ‘የእግዚአብሔር ጸጋ የእግዚአብሔር ሥጦታ’’ ብሎ ከመጥራት በላይ ምን ውዳሴ ሊቀርብ ይችላል፡፡ እርሱ ዮሐንስ ነው፡፡

ዘካርያስ የልጁን ስም በብራና ላይ ሲጽፍ የተዘጋ ‘አፉ ተከፈተ መላሱ ተፈታ’ ስሙን ብቻ ጽፎ የተዘጋ አፉ ከተከፈተ ጨምሮ ቢጽፍ ምን ይከፈትለት ይሆን? ‘የሚጮህ ሰው ድምፅ ነኝ’ ያለው ዮሐንስ ስሙ በመጻፉ ብቻ ለአባቱ ድምፅ ሠጠው፡፡ ዘካርያስ ስሙን ጽፎ እንዲህ አንደበቱ ከተከፈተ የዮሐንስን ገድሉን መልኩን የጻፉ ምስጋናውን የደረሱ ሰዎች ምን ይከፈትላቸው ይሆን?

መጥምቁ ዮሐንስ ሆይ ስለ አንተ ከፍቅር በቀር ምንም እውቀት የለኝም:: ምንም ቅኔ ምንም ምስጋና ባልጽፍልህ እንደ አባትህ ዘካርያስ ስምህን ብቻ መጻፌን አይተህ እዘንልኝ፡፡ አንደበቴ ባይዘጋም የተዘጋው ልቤን ክፈትልኝ ፤ ምላሴ ባይታሰርም በኃጢአት የታሰረች ነፍሴን ፍታልኝ፡፡ ለጌታ መንገድ የጠረግህ አንተ ለነፍሴ መንገድዋን ጥረግላት፡፡

በንስሓ ጥምቀትህ እጠበኝ ፤ ግራና ቀኝ እንዳላይ እነሆ ብለህ ኃጢአትን ወደሚያስወግደው ወደ እግዚአብሔር በግ አመልክተኝ ፤ በሔሮድያዳ ልጅ ትርዒት የታወረውን የልቤን ሔሮድስ እንደልማድህ ገሥጽልኝ፡፡

አንተ ለአባትህ ያደረግከውን አድርግልኝ እንጂ ፤ አንተ የተዘጉ ነገሮቼን ሁሉ ክፈትልኝ እንጂ ስምህን ደግሜ ደግሜ እጽፈዋለሁ፡፡ ዮሐንስ ዮሐንስ ዮሐንስ ዮሐንስ ዮሐንስ !

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

የቴሌግራም ቻናል : https://t.me/eotcy


በድሮ ጊዜ አንድ ሰው ጥፋት ያጠፋና ዳኛ ፊት ይቀርባል.. ታድያ ዳኛው ሦስት ዓይነት የቅጣት ምርጫ አቀረቡለት...፡፡

አንድ ኪሎ ሽንኩርት እየላጠ መብላት፣ አንድ መቶ ጅራፍ መገረፍ፣ ወይንም አምስት መቶ ብር መክፈል...፡፡ ሰውዬው ለማሰብ የሚሆን ልቡና የሌለው ነበርና የመጀመርያ ምርጫ ሆኖ ስላየው ብቻ «ሽንኩርቱን እበላለሁ» አላቸው...፡፡

ቀረበለት አንድ ኪሎ ሽንኩርት...፡፡ ገና አንድ ሁለት መብላት ሲጀምር ታድያ ዓይኑ ማልቀስ ለሐጩም መዝረብረብ ጀመረ፡፡ አልቻለም ከመቀመጫው ተስፈንጥሮ ተነሣና፡፡ «መቶ ጅራፍ መገረፍ ይሻለኛል» አላቸው፡፡ ወዲያው ኃይለኛ ገራፊዎች ተጠሩና እየተፈራረቁ ይለበልቡት ጀመር፡፡ ግማሽ
እንደደረሰ አልቻለም፡፡ እጁን ወደ ላይ አነሣ፡፡

«እህሳ» አሉት ዳኛው «አልቻልኩም» አላቸው፡፡
«ታድያ ምን ይሻላል» አሉት እየሳቁ፡፡«በቃ አምስት መቶ ብሩን እከፍላለሁ» አለ ከተኛበት እየተነሣ፡፡

«ያንተ ትልቁ ጥፋት መጀመርያ ወንጀል መሥራትህ ብቻ አይደለም፡፡ ማሰብ አለመቻልህ እንጂ፡፡ ምናለ አስበህ ከሦስቱ አንዱን ብትመርጥ ኖሮ፡፡ እኔ ከሦስቱ አንዱን እንድትቀጣ ነበር
የወሰንኩት፡፡ አንተ ግን መናገር እንጂ ማሰብ ባለመቻልህ ሦስቱንም ተቀጣህ፡፡» አሉት።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

"አስቦ የሚራመድ ብዙ ርቀት ይጓዛል" ይላሉ አበው።
👉 ክርስቲያን መንገዱን ሙሉ አስቦ ነው ሚራመደው አስቸዋይ እንሁን

" ጥበብን የሚያገኝ ሰው ምስጉን ነው፥ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ፤ "
(መጽሐፈ ምሳሌ 3:13)

" ከማስተዋል መንገድ የሚሳሳት ሰው በሙታን ጉባኤ ያርፋል። "
(መጽሐፈ ምሳሌ 21:16)


@eotcy @eotcy @eotcy
@eotcy @eotcy @eotcy
@eotcy @eotcy @eotcy
#ሐምሌ #ታልቅ_ቀን 5/2014
#ምህረት
#የፍቅር ቀን
ውስተ ኵሉ ምድር ወጽአ ነገሮሙ
ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ
ጳውሎስ ወጴጥሮስ እለ ከዓዉ ደሞሙ
በሞቶሙ ወበሕይወቶሙ ኢተሌለዩ ቀዲሙ
በድሮሙ ወስምዖሙ ኅቡረ ፈጸሙ
ትርጉም፦
ድምፃቸው በምድር ላይ ተሰማ
ቃላቸውም ሁሉ እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ
ስለ መንግሥተ ሰማያት ክብር ደማቸውን ያፈሰሱ ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ በሞታቸውም በሕይወታቸውም ከቀድሞ ጀምሮ አልተለያዩም ሩጫቸውን እና ምስክርነታቸውን በአንድነት ፈጸሙ

ሙሉውን ታሪክ በዕለቱ ስትመጡ ትሰሙታላችሁ ግን ከብዙህ በጥቂቱ ለምን ይከበራል ለሚለው እነሆ👇👇👇
ሁላችሁም የክርስቶስ ቤተሰቦች ይህ ቀን(ሐምሌ ፭(5) በየዓመቱ) እስከ ሞት ድረስ የጸና የወንድማማችነትን ፍቅር የምናይበት ታላቅ የመታሰቢያ ቀን ነው
እንደዚሁም ደግሞ ይህ ቀን በዘመናዊው እሳቤ collaboration (win-win) እየተባለ የሚጠራው በአንድነት ድል ማድረግን የምንማርበትና ከዚህ በዓል የተቀነጨበ እሳቤ እንደሆነ ልብ ሊሉ ይገባል!!!
አዎ በዚህ ቀን በሮም አደባባይ ቅዱስ ጳውሎስ ቅዱስ ጴጥሮስን በፍጹም ትህትና መምህሬ! አለቃዬ! አንተ የሐዋርያት ራስ ነህና የፍጥረታት ሁሉ ራስ እንደ ሆነው አምላክህ ክርስቶስ ልትሰቀል ይገባኻል ሲለው ቅዱስ ጴጥሮስም የትህትና ባለቤት ከሆነው ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግር ሥር ቁጭ ብሎ እግሩን እየታጠበ ትህትናን ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ ተምሯልና ርእሰ ሐዋርያት እኔ እንዴት እሰቀላለሁ ሳይል አዎ ትክክል ብለሃል!
ነገር ግን እኔ ራሴ እንደሆነው ክርስቶስ ሳይሆን ቁልቁል ነው የምሰቀለው በማለት ደስታን በተሞላ አንደበት ሲመልስለት ያንን በሞት የማሸነፍ ቀን በምናብ እንመለከታለን።አስከትሎም በአለቅልነት አንደበት ሳይሆን እስከ ዓለም ዳርቻ በደረሰ በወንድማዊነት ድምጽ ቅዱስ ጳውሎስን አንተስ ምን አሰብክ ብሎ በትህትና ይጠይቀዋል።
ቅዱስ ጳውሎስም መልሶ እኔ እንኳ ለሁለቱም የማልበቃ ራስ ልቆርጥ ሲሄድ በክርስቶስ ፍቅር እራሴን ተቆርጬ፣ ላሳድድ ስገሰግስ የመብረቅ ብልጭታ በሚመስል የሰማይ ብርሃን ከነበሩኩበት የማሳደድ ሃይማኖት ተሳድጄ የተመለስኩ የክርስቶስ የፍቅሩ እሥረኛ ነኝ እና ሌላውን ለመሠዋት ያሰበውን እራሴን መሥዋዕት አድርጌ መስጠት አለብኝ ብሎ ይመልስለታል። ከዛም መልካም! ጥሩ! ተባብለው ቅዱስ ጴጥሮስ ቅልቁለቱን ይወርድ ጀመር ቅዱስ ጳውሎስም ላብ አይሉት ደም በሰውነቱ እየፈሰሰ የሮምን ዳገት መግፋቱን ተያያዘው።
በመጨረሻም ምንም አንደኛው ወደ ታች ቢሮጥ ሌላኛው ደግሞ ወደ ላይ ቢወጣ ልጅ ይሮጣል እንጂ አባቱን አይቀድምም ሳይባባሉ የሚሮጡበት የሩጫቸው መዳረሻ መንግሥተ ሰማያት ክርስቶስ ነውና ሁሉቱም እኩል አሸንፈው "ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ" ተብለው ተጠሩ።
እናም የክርስቶስ ቤተሰቦች ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ ሕይወታቸውን ሰጥተው በዚህ ቀን ያገኙትን ክብር እኛ ደግሞ ግፋ ቢል የአንድ ቀን ጊዜያችንን በመስጠት እና ይደረግልኛል በማለት የእነርሱን ዋጋ የምናገኝበት ታላቅ የቃል ኪዳን ቀን ነውናከሐምሌ 4/2014 ዓ/ም ከዋዜማ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 5/2014 ዓ/ም አዲስ አበባ ዊንጌት በሚገኙት ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ እና ቅዱስ ገብርኤል አብያተ ክርስቲያናት ተገኝታችሁ የበረከታቸው ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ ተጠርታችኋል።
ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር
💚 @eotcy 💚
💛 @eotcy 💛
@eotcy
🛑#የድንግል_ትህትና🛑

“…..ውኃዋን ቀድታ ማድጋዋን ሞልታ ስትመለስ የተጠማ ውሻ ውኃ ፈልጎ እያቃሰተ መጣ፡፡ ከዚያ የነበሩ ሴቶች ግን ድንጋይ እየወረወሩ አባረሩት፡፡እነርሱ ሲያባርሩት እሱ ተስፋ ባለመቁረጥ እየተመላለሰ ለመጠጣት ሲሞክር፤ የእነርሱ ጭካኔ የእርሱን ጭንቀት አይታ ይህንስ የፈጠረው እግዚአብሔር አይደለምን; ለምን አታጠጡትም ብትላቸው እኛ ሥራ አለብን ወደ ስራችን ልንሔድ ነውና አንቺ አጠጪው አሏት፡፡

እርሷም ማድጋዋን አውርዳ ማጠጫ ብታጣ የወርቅ ጫማዋን አውልቃ አጠጣችው፡፡ እንግዲህ ይህንን ከሕሊና በላይ የሆነ የትህትና ሥራ እናሰተውል፡፡ ከዚያ የነበሩ ሴቶች እኛ ሥራ አለብን ሲሏት እርሷ ግን የኔማ እንጂ ሥራዬ የተቸገሩትን መርዳት ነው ማለቷን በተግባር መለሰችላቸው፡፡ ምስጢሩም ከማድጋዋ የቀዳችውን ውኃ ለውሻው መስጠቷ ከእርሷ የተገኘ የአምላክ ሥጋና ደም ለኃጥአን የመሰጠቱ ምሳሌ ነው፡፡

እንደኔ ኃጢአተኛ የሆንክ ወንድሜ ሆይ! ልብህን አጽንተህ፤ ሕሊናህን አንቅተህ፣ እመብርሃንን እንዲህ በላት፡፡
‘ እመቤቴ ሆይ ለውሻው የሚያስጠማን ውኃ አጠጣሺው፤ ለኔ ግን ከውሻ ብከፋም ለዘለዓለም የማያስጠማውን የሕይወት ውኃ አጠጣሽኝ፡፡ ለውሻው በወርቅ ጫማ አጠጣሺው፤ ለእኔ ግን እስከ ዓለም ፍጻሜ የማያልቀውን የሕይወት ውኃ አጠጣሽኝ፡፡ ለውሻ ውኃ ብቻ ሰጠሽው፤ ለእኔ ግን የሕይወት ውኃን ከቅዱስ ሥጋው ጋር ሰጠሽኝ፡፡ ለዚህ ቸርነትሽና ፍቅርሽ አንክሮ ይገባል፡፡

ዳግመኛም ውሻው ‘አሁን ያባርሩኛል አሁን ይመቱኛል’ እያለ በሥጋትና በጭንቀት ሆኖ የሰጠሽውን ውኃ ጠጣ፡፡እኔ ግን ከደስታዬ ብዛት የተነሳ ‘እግዚአብሔር ይጠብቀኛል፤ የሚያሳጣኝም የለም’፤ እያልኩ እየዘመርኩ ጠጣሁ፡፡ ለውሻው ለአንድ ቀን ብቻ የሚያረካ ውኃን ሰጠሽው፡፡ ለእ ግን ለዘላለም ጽምዓ ነፍስን- የነፍስን ጥም የሚያስወግድ የሕይወት ውኃን አስገኘሽልኝ፡፡ ውሻው የሰጠሸውን ውኃ ላይከብርበት ጠጣ፡፡ እኔ ግን ክብረ ነፍስን ልቀዳጅበት፣ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስን ላገኝበት ጠጣሁት፡፡

ውሻው ከማድጋሽ ያለውን ውኃ ስለ ተጠማና መጠጣት ስለፈለገ እንደ ሆነ ሁሉ፤ እኔም ከአንቺ የተገኘውን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም ለመብላትና ለመጠጣት ንስሐ ገብቼ ፍቅርሽን ተጠምቼ ልቀርብ የሚገባ መሆኑን መጻሕፍት ለመላልሰው ይነግሩኛል፡፡ሆኖም በሥጋ ፍላጎት ተጽዕኖ ውስጥ የምኖር ኃጢአተኛ ስለሆንኩ ከአንቺ የተገኘ የሕይወት ውኃን እጠጣ ዘንድ አማላጅነትሽ አይለየኝ፡፡ ከውሻ የከፋሁ ስሆን ማለቴ ግን፡- ውሻ ጌታውን ያውቃል፤ የጌታውን ቤት ይጠብቃል፤ መልካም ያደረገለትን አይረሳም፤እኔ ግን የእግዚአብሔር ቤት የሆነ ልቡናዬን ከክፉ ነገር አልጠብቅም፤ መልካም ነገርን ሁሉ ያደረጉልኝን ወገኖቼን እረሳለሁ፡፡ ውሻ ቁስሉን በምላሱ ያደርቃል፤ እኔ ግን ቁስሌን በምላሴ አሰፋለሁ፡፡ ከውሻ ያነስ መሆኔ በዚህ ይታወቃል፡፡ እናም አማላጅነትሽ እንዳይለየኝ የእናትነት ፍቅርሽ እንዳይለየኝ እማጸንሻለሁ… በላት፡፡”

🦋የእመቤታችን ልመናዋ በረከትዋ አይለየን!
----------------------------------------------
#Share_Share
♡ ㅤ   ⎙ㅤ   ⌲
ˡᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ