የቅዱሳን ስዕለ አድህኖ እንዲሁም ሀይማኖታዊ ፅሁፎች
187 subscribers
1.81K photos
128 videos
14 files
213 links
ይህ ቻናል በየቀኑ የቅዱሳን ስዕለ አድህኖ እንዲሁም ሀይማኖታዊ ፅሁፎች የሚለቀቁበት ቻናል ነው።
Download Telegram
እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ አመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን።
ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ከእርኩስ መንፈስ አጋንንት ክፉ ሀሳብ ይሰውረን፣የልቦናችንን መሻት ይፈፅምልን፣ለነፍስ እና ለስጋችን ዋስ ጠበቃ ጋሻ መከታ ይሁነን!!!
አሜን አሜን አሜን!!!
#ጥቅምት17
በይስሐቅ ፋንታ
ሊቀ መዘምር ይልማ ኃይሉ
በይስሐቅ ፈንታ
የበገና መዝሙር

በይስሐቅ ፈንታ ኢየሱስ ታረደ/2/
ደሙን ከፈለና አዳምን ታደገ/2/

ተጨነቀ ጌታ ተሰቃየ ጌታ
የኔ መድኃኔዓለም የአዳም ልጅ አለኝታ
እንደሚታረድ በግ ተነዳ ወደ ሞት
ንፁህ ኢየሱስ በደል የሌለበት

በማመን ሲሸከም የአዳምን መከራ
ስቃይ ተቀበለ ደሙ እየተዘራ
ለሚገርፋት ሁሉ ምህረትን ሲቸር
እርሱ ግን ሲገረፍ ብዙ ተቸገረ

የሰማነውን ድምፅ ማን ሰው እኮ አምኗል
የእግዚአብሔርስ ክንድ ለነማን ተገልጿል
ባየነው ጊዜ ህመም ተሸክሞ
ስለበደላችን ተገርፎና ታሞ

እጁ የታሰረው ይስሀቅ ተፈቶ
ኢየሱስ ቀረበ በሰው ልጆች ፈንታ
ንፁህ በግ ቀረበ በደል የሌለበት በደለኛ ሆኖ
ሊሰቀል ሊገደል መስቀሉን ተጭኖ

በእውነት ደዌያችንን እርሱ ተሰቀለ
በሰው ልጆች ፈንታ በእንጨት ተሰቀለ
እኛ ግን ከሰስነው እንደ ወንጀለኛ
ስለ እኛ ቢሰቀል ሰማያዊው ዳኛ

ለሰው ልጆች ህይወት የታሰበውን ሰይፍ
አይተናል ሰምተናል በኢየሱስ አንገት ሲያልፍ
የመስቀሉ ስዕል ኧረ እንዴት ይገርማል
እዩት ንፁህ በግ በአርምሞይነዳል

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
እሁድ/16-03-16/ በፉሪ ፈለገ ዮርዳኖስ ማሩ መጥምቁ ዮሐንስ እና ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን (ጀሞ 3 መስታወት ፋብሪካ ማርያም) የበዓታ ለማርያም ፅላት ስለሚገባ ሁላችንም ተገኝተን የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን በልዑል እግዚአብሔር ስም ተጋብዘናል ። 
ሼር በማድረግ ላልሰሙ ወንድም እና እህቶቻችን እናድርስ!
Forwarded from ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube (Ⓕⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪)
የኅዳር ጽዮን 21 የነግህ (የማኅሌት)

😍ምስባክ 😍

ዕግትዋ ለጽዮን ወሕቀፍዋ:
ወተናገሩ በውስተ ማኅፈዲሃ:
ደዩ ለበክሙ ውስተ ኀይላ::

    ዲ/ን አቤል (ፍቅረ አብ)
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube
https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
💛 @seratebtkrstian    💚
💛 @seratebtkrstian    💚
💛 @seratebtkrstian    💚
💙💙💙💙💙💙💙💙💙
     🙏join👍
ለጥያቄ ለአስተያየት 👇
@Men_Lerdawobot
#ሼርርርርርርርርርርር
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ህዳር ፅዮን ዓመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!!!
የእናታችን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ፣የልጇም ቸርነት ከእኛ ከሁላችን ጋር ይሁን፣የልቦናችንን መሻት ትፈፅምልን፣ለነፍስ እና ለስጋችን ዋስ ጠበቃ ጋሻ መከታ ትሁነን!!!
አሜን አሜን አሜን!!!
#ህዳር21