Civil Engineering
1.37K subscribers
1.26K photos
20 videos
962 files
674 links
*ለሲቪል ; ለአርክቴክቶች÷ለኮንስትራክሽን ÷ ለሀይድሮሊክ መሀንዲሶች እና ተማሪዎች የተዘጋጀ ትምህርታዊ ቻናል ፡፡

@engineer03


http://www.Indiabix.com በዚህ ደግሞ ማንኛውንም ጥያቄና መልስ ታገኛላችሁ!

╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕
Download Telegram
👉 የአፈርን የመሸከም አቅም (BEARING CAPACITY) እንዴት እንጨምር?? ላላችሁን...
.
* ሶስት አይነት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከያ ቴክኒኮች አሉ - mechanical, chemical & other stabilization techniques
.
A) ሜካኒካል ውስጥ :-
.
1. Compaction - አፈሩን ስንጠቀጥቀው density/ unit
weight ይጨምራል ያ ማለት ደግሞ አፈርን የመሸከም አቅም ጨመረ ማለት ነው::
.
2. Excavation and Replacement – expansive soil ከሆነ ወይም ሌላ አስቸጋሪ አፈር ከሆነ ይህን መጠቀም እንችላለን
.
3. Mixing of Different Soils - ሳይታችን ላይ ያለው አፈር
coarse ወይም fine ብቻ ከሆነ ወይም ደግሞ አፈሩ አንድ አይነት
ብቻ ፀባይ ካለው ከተለያዩ አፈሮች ጋር በመደባለቅ የተሻለ የአፈር
ፀባይ ማግኘት እንችላለን
.
B) ኬሚካል :-
.
1. Lime stabilization - ይህንን የምንጠቀመው በአብዛኛው
ለexpansive soil ነው፡፡ አፈሩን ከ Lime ጋር በመደባለቅ
plasticity መቀነስ እንችላለን፡፡ የlime መጠኑ ከሚያስፈልገው
በላይ ከበዛ ግን B.C. ይቀንሳል፡፡
.
2. Cement stabilization - ሲሚንቶን ከአፈር ጋር በመደባለቅ
የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት መንገድ ነው፡፡ concrete
pavement ስር መጠቀም እንችላለን በአብዛኛው ለአየር
መንገዶች ፤ ለአውራ ጎዳናዎች ፤ ግድቦችን ከሽርሸራ ለመከላከል
ወ.ዘ.ተ. መጠቀም እንችላለን፡፡
.
3. Asphalt stabilization - አስፓልትን ከአፈር ጋር በመደባለቅ
የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት ዘዴ ነው በተለይም ለcohesive
አፈሮች፡፡ አፈሩን water proof በማድረግና ውሃማነትን በመቀነስ
B. Cን መጨመር እንችላለን፡፡ በአብዛኛው ይህንን ድብልቅ
ለመንገዶች እንደ base course መጠቀም እንችላለን፡፡
.
.
C) ሌሎች የአፈርን ባህሪ ማስተካከያ መንገዶች:-
.
1. Drainage - ፓይፖችን አፈር ውስጥ በመቅበር ወይም
ጉድጓዶችን በመጠቀም ground water የምንቆጣጠርበት ነው
.
2. Precompression - ግንባታ ከመጀመራችን በፊት አፈሩ ላይ
ሎድ በመጫን ኮምፓክት የምናደርግበት ዘዴ ነው
.
3. Dynamic Stabilization
.
ሀ) Blasting - ቦምብ ወደውስጥ በመቅበር በፍንዳታው አፈሩ ይጠቀጠቃል::
.
ለ) Compaction Piles - ፓይሎችን ወደውስጥ በማስገባት
አፈሩ ወደ ጎን እንዲሸሽና እንዲጠቀጠቅ ማድረግ ይቻላል፡፡
ፓይሉን ስናስወጣውም በተቦረቦረው ጉድጓድ ውስጥ የተሻለ አፈር በማስገባት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከል እንችላለን፡፡
.
4. Injection And Grouting - አፈሩን በሲሚንቶ ወይም
በተለያዩ chemical ውህዶች በpressure በመምታት ground
water ና settlement መቆጣጠር እንችላለን፡፡
.
የተሻለውን ዘዴ ለመምረጥ የአፈሩንና የአካባቢውን ሁኔታ ፤
ኢኮኖሚ ፤ ሴፍቲና የመሳሰሉትን ነገሮች ማጤን አለብን፡፡
.
👉FOR MORE UPDATED AMHARIC CONSTRUCTION INFO JOIN US HERE 👇
http://t.me/engineer03
🎯 TYPES OF FLUID FLOW

🔰 STEADY:- If fluid preoperties does not changes with respective to time

🔰 UNSTEADY:- If fluid properties changes with respective to time

🔰 UNIFORM:- If fluid velocity does not changes with respective to space or distance

🔰 NON-UNIFORM:- If fluid velocity changes with respective to space or distance

🔰 INCOMPRESSIBLE:- If fluid density does not change with respective to pressure

🔰 COMPRESSIBLE:- If fluid density change with respective to pressure

🔰 IRROTATIONAL:- If fluid particles does not rotate about their C.G. during the flow

🔰 ROTATIONAL:- If fluid particles rotate about their C.G. during the flow

🔰 LAMINAR:- If two layer of fluid does not mixed with each other. Also called as viscous flow

🔰 TURBULENT:- If two layer of fluid mixed with each other. Also called as Non-viscous flow

http://t.me/engineer03
👉የቻይናው Three Gorges Dam አስገራሚ ቁጥሮች @engineersWorks
.
* የግድቡን መሰረት ለመስራት 80,000 ድማሚት ሲጠቀሙ ይህ
ማለት ከ20 የሂሮሺማ የኒውክሌር ጥቃቶች ጋር እኩል ነው፡፡
.
* የግድቡ Reservoir ርዝመት 660ኪ.ሜ ነው - ይህም ማለት
ከአ.አ ማይጨው እንደማለት ነው፡፡
.
*18200 MW ያመነጫል ይህም 7965mw ከሚያመነጨው
የጃፓኑ Kashiwazaki-Kariwa የዓለማችን ትልቁ የኒውክሌር
ማብሊያ 230 ፐርሰትን ይበልጣል፡፡ ከህዳሴ ግድብ ደሞ 300 ፐርሰት/ 3 እጥፍ ይበልጣል፡፡
.
*ግንባታው 30 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ኮንክሪት ፈጅቷል - ይህም
ማለት 30 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ኮንክሪት ተጠቅመን 1 ሜትር
ዲያሜትር ያለው ድፍን ኮንክሪት pipe ብንሰራ ዓለምን አንድ ዙር
መዞር ይችላል፡፡
.
*463,000 ቶን ብረት የተጠቀሙ ሲሆን - ይህን ያህል ቶን ብረት
ተጠቅመን 63 ኤፍል ታወሮችን መገንባት እንችላለን፡፡
.
*በአማካኝ 77.5 ሜትር width ሲኖረው ይህም ከማንኛውም
አቅጣጫ የሚመጡ የሚሳኤል ጥቃቶችን እንዲቋቋም
ያደርገዋል፡፡ በተጨማሪም ከግዝፈቱ የተነሳ የቀን እርዝመት
በማይክሮ ሰከንድ እንዲጨምር አድርጓል፡፡ ከታላቁ የቻይና ግንብ
ቀጥሎ ከስፔስ ላይ የሚታይ የቻይና ሁለተኛው የሲቪል
ኢንጂነሪንግ ውጤት ነው፡፡
.
*ግንባታው ከ630 ቢሊየን ብር በላይ ሲፈጅ በ 2012 ተጠናቆ ከ1 ዓመት ከ6 ወር በኋላ ሙሉ ወጪውን መልሷል፡፡
.
*ሀብታሟ ሀገር ሳውዲ አረቢያ ከነዳጅ ፣ ከእንፋሎት ወዘተ
55000MW ስታመነጭ ሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ በትንሹ
45000MW ከውሃ ብቻ ማመንጨት ትችላለች
* እስካሁን ባለው 4000MW አይሆንም የምናመነጨው፡፡
18200 MW የሚያመነጨው 630 ቢሊየን ብር ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የመለሰ ኢትዮጵያ 45000 MW ስታመነጭ ምን ያህል
ብር ማግኘት እንደምትችል አስቡት።
ለማንኛውም Hydraulic Engineering ይህን ያህል ተፅዕኖ መፍጠር ይችላል፡፡

http://t.me/engineer03