Civil Engineering
1.36K subscribers
1.24K photos
21 videos
960 files
661 links
*ለሲቪል ; ለአርክቴክቶች÷ለኮንስትራክሽን ÷ ለሀይድሮሊክ መሀንዲሶች እና ተማሪዎች የተዘጋጀ ትምህርታዊ ቻናል ፡፡

@engineer03


http://www.Indiabix.com በዚህ ደግሞ ማንኛውንም ጥያቄና መልስ ታገኛላችሁ!

╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕
Download Telegram
📱እንዴት በደላሎች ይዘወራል?

📱የመንግስትና የግል ሽርክና ውጤቱ "ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ" በደላሎች ሴራ እየታመሰ ነው ተባለ

የመንግስትና የግል ባለሀብቶች በጋራ ሽርክና (Joint Venture) የመሰረቱትና የሀገሪቱ ትልቁ የኢንዱስትሪ ተስፋ የሆነው ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ምርት፣ በደሴ ከተማም ሆነ ኮምቦልቻ በደላሎችና ስግብግብ ነጋዴዎች "የዋጋ ቁማር" ሰለባ መሆኑን የምርቱ ተጠቃሚዎች ገልፀዋል።

📱ይህ በሰሜን ሸዋ ለሚ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው ግዙፍ ፋብሪካ፣ አንድ ኩንታል ሲሚንቶን በ1,140 ብር እያከፋፈለ ቢሆንም፤ በደሴና ኮምቦልቻ ከተማ ግን ምንም ዓይነት ይፋዊ የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግ በ2,400 ብር እንዲሸጥ እየተደረገ ይገኛል በማለት ነው ጥቆማ አቅራቢዎቹ ያስረዱት።

የመንግስትና የግል ሽርክና የሆነው ኩባንያ ለምን በደላላ ቁጥጥር ስር ወደቀ?


ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት የመንግስት ድርሻ ያለበትና የህዝብን የግንባታ ፍላጎት ለማርካት የተቋቋመ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም ግን፣ ቀደም ሲል ምርቱ ደሴና ኮምቦልቻ ሲደርስ የትራንስፖርት ወጪ ተጨምሮበት በ1,500 ብር ሲሸጥ የቆየው ሲሚንቶ፣ አሁን ላይ በኩንታል የ900 ብር ልዩነት ታይቶበታል። ይህ ድንገተኛ "ዝርፊያ" የመንግስትና የግል አጋርነቱን ዓላማ የሚጻረርና የዜጎችን የመኖሪያ ቤት የመስራት ህልም የሚያጨልም ሆኖ ታይቷል።

በከተማዋ የሚገኙ ግንባታ አቅራቢዎችና ተጠቃሚዎች እንደገለጹት፤ በደላሎችና በወኪል አከፋፋዮች መካከል በተፈጠረ "ያልተገባ የጥቅም ትስስር" ሳቢያ ዋጋው ከአቅም በላይ ሆኗል።በዚህም  "የግንባታ ዘርፉ ክፉኛ ፈተና ላይ ወድቋል"ብለዋል። በከተማዋ የተጀመሩ የግልና የመንግስት ግንባታዎች "ቀጥ" ብለው መቆማቸውን ጠቁመዋል።

"የመንግስት እጅ ያለበት ፋብሪካ ምርት እንዴት በደላሎች ይዘወራል?" የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎች፣ መንግስት አስቸኳይ ጣልቃ በመግባት  ይህን የገበያ ምስቅልቅል እንዲያስተካክልና ወንጀለኞችን ተጠያቂ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።


📱 https://t.me/engineer03
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
3
⭐️የ mat foundation አይነቶች

1. Flat plate -
እንደ ፓድ ፋውንዴሽን  ሆኖ ሙሉ ህንፃው ሚያርፍበትን ቦታ ይሸፍናል።

ብረት ደግሞ ኮለን እና ሺር ዎል ያለበት ጋር spacing ማጥበብ (ብረት ጨመር ማረግ)

2. Plate thickened under the column
የ ኮለኖቹ ሚመጣው ክብደት በ ሶሌታው ውፍረት ብቻ ልንቋቋመው ካልቻልን የኮለኖቹን ረድፍ ከ ሶሌታው ስር ጥልቀቱን እንጨምራለን

3. Piled raft foundation
ማታችን በ pile ቢደገፍ ልክ እንደ pile cap ሆኖ ግን ጥልቀት የሌለው shallow

4. Beam and slab two way raft foundation

ሶሌታችን ላይ ግሬድ ቢም ሲረበረብ አይነት ነገር

5. Ridged
/cellular raft foundation
ፋውንዴሽኑን እንደ ቤዝመንት ስንጠቀመው

6. Plate with pedestal
- ኮለኖቹ ላይ ከ ሶሌታው በላይ ኮርቻ ሲኖረው
🏗️ ከበዓል መልስ የኮንስትራክሽን ሳይት ማኔጅመንት፦ የሰኞ ማለዳ ስንቅ

በዓላትን አክብሮ ወደ ሥራ የሚመለስ ሠራተኛ ላይ ድካም፣ ትኩረት ማጣትና መዘናጋት ሊታይ ይችላል። ይህ ደግሞ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለአደጋና ለሥራ መጓተት ዋነኛ መንስኤ ነው። ሰኞ ማለዳ ሥራ ከመጀመሩ በፊት የሚከተሉትን ነጥቦች መተግበር ውጤታማ ያደርጋል፦

1. የደህንነት ንቃተ-ተሃድሶ (Safety Toolbox Talk)


በመጀመሪያው ቀን ጠዋት ሁሉንም ሠራተኞች በማሳተፍ አጭርና ግልጽ የሆነ የደህንነት ገለፃ ማድረግ።

የትኩረት ነጥብ፦ ስለ ግል ደህንነት መጠበቂያ (PPE) አጠቃቀም፣ ስለ ሳይቱ አደገኛ ቦታዎች እና ስለ ተገቢ የሥራ ሂደቶች ማስታወስ።

አላማ፦ የሠራተኛውን አእምሮ ከበዓል ድባብ አውጥቶ ወደ ሥራው ደህንነት እንዲመለስ ማድረግ።

2. የማሽነሪዎችና የሳይቱ ፍተሻ (Site Inspection)


ሥራ ከመጀመሩ በፊት ለተወሰነ ጊዜ ተዘግቶ የነበረው ሳይትና ማሽነሪዎች በጥንቃቄ መፈተሽ አለባቸው።

ማሽነሪዎች፦ ኤክስካቫተሮች፣ ዶዘሮችና ሌሎች ከባድ ማሽኖች ለብልሽት ወይም ለስርቆት አለመጋለጣቸውን ማረጋገጥ።

መሠረተ ልማት፦ የኤሌክትሪክ መስመሮች፣ ስካፎልዲንግ (Scaffolding) እና ጉድጓዶች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን መፈተሽ።

3. ድካምንና ሞራልን ማመጣጠን


ሠራተኞች በበዓል ምክንያት ሊደክሙ ስለሚችሉ ሥራውን ቀስ በቀስ ማስጀመር።

ቀላል ጅምር፦ በመጀመሪያው ቀን ከባድና እጅግ ውስብስብ የሆኑ ሥራዎችን ከመጀመር ይልቅ ቀለል ያሉና የዝግጅት ሥራዎችን መስራት።

ንቃት፦ የሠራተኞችን ንቃት መከታተል፤ በድካም ምክንያት የሚመጡ ስህተቶችን ለመቀነስ የአጭር ጊዜ እረፍቶችን መስጠት።

4. የሰው ኃይል ብቃትና ዝግጁነት


እያንዳንዱ ሠራተኛ ለሥራው ብቁና በአካልም ሆነ በአእምሮ ዝግጁ መሆኑን ማረጋገጥ።

ከበዓል መልስ የሚታዩ የጤና መጓደሎችን ወይም ከፍተኛ የትኩረት ማጣትን መለየት።

5. የሥራ ዕቅድ ክለሳ (Resource Planning)


በበዓል ምክንያት የተቋረጡ ሥራዎችንና የቀሩ የጊዜ ገደቦችን (Deadlines) መገምገም።

ሠራተኛውን ሳያስጨንቁ ፕሮጀክቱ በታቀደለት መሠረት እንዲቀጥል የጊዜ ሰሌዳውን ማስተካከል።

ለማስታወስ፦ "ደህንነቱ የተጠበቀ ጅምር፣ የተሳካ ፕሮጀክት መሠረት ነው።"
👍2