Civil Engineering
1.36K subscribers
1.24K photos
21 videos
960 files
661 links
*ለሲቪል ; ለአርክቴክቶች÷ለኮንስትራክሽን ÷ ለሀይድሮሊክ መሀንዲሶች እና ተማሪዎች የተዘጋጀ ትምህርታዊ ቻናል ፡፡

@engineer03


http://www.Indiabix.com በዚህ ደግሞ ማንኛውንም ጥያቄና መልስ ታገኛላችሁ!

╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕
Download Telegram
ማስታወቂያ

በድጋሚ ስራ ተቌራጮችን ለመመልመል የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ያወጣው ማስታወቂያ

https://t.me/engineer03
1
የአዲስ አበባ ሁሉንም FM ጣቢያዎች online ማዳመጥ ከፈለጋችሁ ደግሞ
https://qedamawi.vercel.app/
በጣም በቀላል ኔትዎርክ በጥራት ይሰማል።
🏗️ Heavy Construction Machinery Line-Up 🚧
A complete showcase of essential machines used in modern construction projects, each playing a vital role in building, lifting, mixing, and transporting materials efficiently ⚙️🚜
2
የባንክ ሒሳብን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር አላጣመሩም? ጊዜው እየሄደ ስለሆነ በቀጥታ ካሉበት ሆነው ኦንላይን ያጣምሩ።

ልብ ይበሉ፦ ሲስተም ላይ በነበረ መጨናነቅ ለቀናት ቆይቶ የነበረውም የመዘግየት ችግር በመፈታቱ ፣ ደንበኛ የሆኑበትን ባንክ ከታች በተዘረዘሩት ዝርዝር በመምረጥ ባለ 16 አኃዝ የፋይዳ ቁጥርዎን (FAN/FCN) በመጠቀም ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ለማጣመር (Harmonization) በነዚህ ሊንኮች ይጠቀሙ።

💸 አቢሲኒያ ባንክ: https://cs.bankofabyssinia.com/fayda_connect

💸 አዋሽ ባንክ : https://fayda.awashbank.com

💸 የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ: https://my.coopbankoromiasc.com/harmonization

💸 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡ https://cbefayda.cbe.com.et/

💸 ኦሮሚያ ባንክ ፡ https://obfayda.oromiabank.com/

💸 ወጋገን ባንክ : https://fayda.wegagenbanksc.com.et/harmonization

💸 ንብ ባንክ፡ https://fayda.nibbank.com.et/

💸 ፀሀይ ባንክ፡https://fayda.tsehaybank.com.et/FAYDA/home

💸 ስንቄ ባንክ : https://fayda.siinqeebank.com:7443

💸 ዘምዘም ባንክ : https://fayda.zamzambank.com.et

💸 አማራ ባንክ : https://fayda.amharabank.com.et
3🥰1
🤔🤔🤔
አፈርን ከሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ጥናት ተጠናቀቀ

ከትንሽ ሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ጥናት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ታምራት ሙሉ (ኢ/ር) ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ከሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተጠናው ይህ ጥናት ትኩረት ያደረገው በሐረሪ፣ በድሬዳዋ እና በጅግጅጋ አካባቢዎች የሚገኘውን አፈር ለቤት ግንባታ በሚውል መልኩ ማዘጋጀት ላይ ነው።

ቴክኖሎጂው የተለመደውን ብሎኬት ከመጠቀም ይልቅ፣ በአካባቢው የሚገኘውን አፈር ከትንሽ ሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ነው ብለዋል።

በእነዚህ አካባቢዎች ለሚኖሩ ከ6 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች የቤት ግንባታ ችግርን የሚቀርፍ መፍትሔ ይዞ መቅረቡን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ግንባታዎች ሙሉ በሙሉ በሲሚንቶ ላይ ብቻ የተንጠለጠሉ እንዳይሆኑ በማድረግ የግንባታ ወጪን በእጅጉ እንደሚቀንስም ተገልጿል።

ጥናቱ ሁሉንም የኢንጂነሪንግ መስፈርቶች አሟልቶ በቤተ-ሙከራ የተረጋገጠ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት "ለአካባቢያዊ ችግር አካባቢያዊ መፍትሔ" በሚል ስትራቴጂ ለመጨረሻ ማረጋገጫ ለውይይት ቀርቧል።

በታደሠ ብናልፈው

https://t.me/engineer03
👍1
የአደጋ_ደህንነት_ደንብ_ቁ_132_2014_የጸደቀ_250222_210150.pdf
327.8 KB
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ

📱 ማንኛውም ህንፃ እና ግንባታ በግንባታ ሂደት የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርበታል ፡-

ሀ) ለማንኛውም ህንጻ ወይም ግንባታ ወይንም መሰረተ ልማት የግንባታ ፍቃድ ከመሰጠቱ በፊት በስትራክቸራል ዲዛይን ውስጥ መሟላት ያለባቸው የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን የእሣት፣ የጎርፍ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ፣ አውሎንፋስ፣ የመስመጥ፣ መደርመስ እና የሌሎች አደጋ መከላከያና መቋቋሚያ መስፈርቶች መካተታቸውን በማረጋገጥ እንዲሁም የአገሪቱን የህንጻ ስታንዳርድን ከግምት ያስገባ የግንባታ ፈቃድ መሰጠት አለበት፤

ለ) ለእያንዳንዱ አዲስ ግንባታና ጥገና ለሚያካሂድ ሠራተኛ የአደጋ ጉዳት መከላከለያ እና የአደጋ ጥንቃቄ የግል መሳሪያዎች ሊሟላለት ይገባል፤

ሐ) በህንጻ ውስጥ ነዋሪዎች ወይም ተጠቃሚዎች እያሉ የጥገና ሥራ የሚከናወን ከሆነ ለጥገና ሥራ የሚውል ማንኛውም ቁሳ ቁስና መሳሪያ ስራ ላይ ሲውል አሠሪው አካል እና ተጠቃሚዎቹ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ግዴታ አለበት፡፡

📱 https://t.me/engineer03
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2👍1
648_የኮንስትራክሽን_ብቃት_ማረጋገጫና_ምዝገባ_መመሪያ.pdf
2.7 MB
👷‍♀️ የ ኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ መመሪያ 👷‍♂️
- ኮንትራክተር ከ ደረጃ 1 እስከ 10
- የአማካሪ መሃንዲስ ፈቃድ
- ባለሙያ ሁሉም አይነት

📱 https://t.me/engineer03
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1🙏1
2018 2nd Q Construction Works (Only Direct Cost)(1).pdf
22.7 MB
🚧 የ2018 ዓ/ም 2ኛ ሩብ ዓመት የኮንስትራክሽን ስራዎች ቀጥተኛ ዋጋ ጥናት

2018E.C  2nd Quarter Construction Works (Only Direct Cost)t

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ

📱 https://t.me/engineer03
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2
weekly Rebar price

📱 https://t.me/engineer03
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Addis_Ababa_City_Administration_Building_Permit_and_Control_Authority.pdf
2.6 MB
ስራ ላይ ያለው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የህንጻ መመሪያና ስታንዳርድ ቁጥር 127/2014.
Addis Ababa City Administration Building Permit and Control Authority Building Guidelines and Standards (Directive No. 127/2014).
FDRE-Procurement-Manual-Final-2018-NBGMS-1221.pdf
2.9 MB
73. የግንባታ ዘርፉ ስራ ግዥ ክፌያ አፆጻጸም - - - - - -
የመንግስት መ/ቤት የግንባታ ዘርፌ ስራ ግዥ ክፌያ የሚፆፀመው የግንባታውን የክንውን ዯረጃ መሰረት አዴርጎ እና የሚከተለውን አፆፃፀም ተከትል መሆን ይኖርበታሌ፡-
እንዯ ስራው ውስብስብነት ሇዚህ ዓላማ ከተቀጠረ አማካሪ ወይም ከመ/ቤቱ መሃንዲስ በሚሰጥ የክፌያ የምስክር ወረቀት መነሻነት ብቻ ይሆናሌ፡፡ የክፌያ የምስክር ወረቀት እንዱሰጠው ከሥራ ተቋራጩ ጥያቄ በቀረበበት በ7 (ሰባት) የሥራ ቀናት ውስጥ የቁጥጥር ስራውን የሚያከናውነው አማካሪ ወይም የመ/ቤቱ መሃንዲስ የምርመራውን ሥራ ማጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡
የክፌያ የምስክር ወረቀት በአማካሪው ወይም በመ/ቤቱ መሃንዲስ ተረጋግጦ ሲቀርብ መ/ቤቱ በ30 (ሰሊሳ) ቀናት ተገቢውን ክፉያውን ለሥራ ተቋራጩ መፈፀም አለበት፡፡

በክፌያ የምስክር ወረቀት መሰረት ከሚፈጸመው ከእያንዲንደ ክፌያ ላይ ለግንባታ ሥራው ጥራት ዋስትና እንዱሆን 7% (ሰባት በመቶ) በማያዣ መልክ ተቀንሶ ይያዘሌ፡፡ የግንባታ ስራው ሲጠናቀቅ እና ጊዜያዊ ርክክብ ሲደረግ በዚህ ንዐስ አንቀጽ ፉዯሌ ተራ /ሠ/ መሰረት ከሚያዘው ገንዘብ ሊይ 50% (ሃምሳ በመቶ) ለሥራ ተቋራጩ ይለቀቃል፡፡ ቀሪው 50% (ሃምሳ በመቶ) ጊዜያዊ ርክክብ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ በአንድ ዓመት የጥገና ጊዜ ተይዞ የሚቆይ ሲሆን፣ የስራ ተቋራጩ በ12 ወራት የሚቆይ በሁኔታ ሊይ ያልተመሰረተ ዋስትና ካቀረበ የተያዘው ገንዘብ ይለቀቅለታል፡፡
(the text is due to font problem , read page 133 for more.)
1🎉1
በጅግጅጋ የተገነባው ተለዋጭ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ሲገነባ የቆየው የ6.93 ኪሎሜትር ተለዋጭ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት መጠናቀቁን ተከትሎ፣ ደረጃውን የጠበቀ የትራፊክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተበሰረ።

መነሻውን የጅግጅጋ ከተማ መግቢያ አድርጎ ቶጎ-ጫሌ አደባባይ ላይ የሚያበቃው ይህ ግዙፍ የመንገድ ፕሮጀክት፣ 30 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ የተገነባ ነው። ግንባታው የእግረኛ እና የብስክሌተኞች መተላለፊያን ጨምሮ ዘመናዊ የከተማ መንገድ ሊያሟላቸው የሚገቡ መመዘኛዎችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።


የመንገዱን ግንባታ ሀገር-በቀሉ ይርጋለም ኮንስትራክሽን ያከናወነው ሲሆን፣ የማማከርና የቁጥጥር ሥራው ደግሞ በኤልዳ አማካሪ ድርጅት እና በዳምራ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ጥምረት ተከውኗል።

ለዚህ ታላቅ የመሠረተ ልማት ግንባታ ማስፈጸሚያ የዋለው 672 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ሙሉ በሙሉ በፌደራል መንግሥት በጀት የተሸፈነ መሆኑ ተረጋግጧል።


የመንገዱ መጠናቀቅ በተለይ በጅግጅጋ ከተማ መግቢያና መውጫ ላይ ይታይ የነበረውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ በከፍተኛ ሁኔታ ያቃልላል ተብሎ ይታመናል።

ለጭነት ተሽከርካሪዎች፦ ከቶጎ-ጫሌ እና ከደገሀቡር የሚመጡ ከባድና ቀላል የጭነት ተሽከርካሪዎች የከተማዋን መሃል ሳያቋርጡ እንዲያልፉ አማራጭ ሆኖ ያገለግላል።

ለከተማዋ ገጽታ፦ ፕሮጀክቱ የጅግጅጋን ሁለንተናዊ ዕድገትና ውበት ከማሳለጥ ባለፈ፣ የንግድ እንቅስቃሴውን ቀልጣፋ እንደሚያደርገው ተመልክቷል።

በአሁኑ ወቅት የመንገዱ ዋና ዋና ስራዎች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን፣ የትራፊክ ምልክቶች ተከላና ሌሎች ጥቃቅን የማጠናቀቂያ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ከወጣው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።
1
🛣️ የባቱ - አርሲ ነገሌ የፍጥነት መንገድ ግንባታ ዋና ዋና ሥራዎች ተጠናቀቁ!

የአዲስ አበባ - ሞያሌ - ናይሮቢ - ሞምባሳ ዓለም አቀፍ የመንገድ ኮሪደር አካል የሆነው የሞጆ - ሐዋሳ ክፍል 3 (ባቱ - አርሲ ነገሌ) የ57 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ ግንባታ በስኬት መጠናቀቁ ተበሰረ።

📍 የፕሮጀክቱ ዋና ዋና መረጃዎች፦


ርዝመት፦ 57 ኪሎ ሜትር

የመንገዱ ስፋት፦ 31.6 ሜትር (ከመካከለኛ አካፋይ ጋር)

ወጪ፦ 5.3 ቢሊዮን ብር (በዓለም ባንክ ድጋፍ የተሸፈነ)

ተቋራጭ፦ ቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ (CCCC)

🌟
ይህ የፍጥነት መንገድ ምን ፋይዳ አለው?


የጉዞ ጊዜን ይቀንሳል፦ ከሞጆ - ሐዋሳ የነበረውን የ4 ሰዓት ጉዞ ወደ 2 ሰዓት ዝቅ ያደርገዋል።

የንግድና ግብርና ትስስር፦ እንደ ስንዴ፣ ቲማቲም፣ ሽንኩርት እና ድንች ያሉ የግብርና ውጤቶች በፍጥነትና ሳይበላሹ ለገበያ እንዲቀርቡ ይረዳል።

ቱሪዝምን ያነቃቃል፦ ወደ ሐይቅ ዳርቻዎች (ደምበል፣ ላንጋኖ፣ አብያታ፣ ሻላ) እና ወደ ሐዋሳ ለሚሄዱ ጎብኚዎች ምቹና ፈጣን ጉዞን ያረጋግጣል።

ዓለም አቀፍ ትስስር፦
ይህ መንገድ 10,000 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የታላቁ የምስራቅ አፍሪካ ኮሪደር (ኬፕታውን ትራንስ አፍሪካን ሐይዌይ) ወሳኝ አካል ነው።

መንገዱ ዘመናዊ የትራንስፖርት ሥርዓት (ITS - Intelligent Transport System) የተገጠመለት በመሆኑ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ሆኗል።


የአካባቢው ማህበረሰብም ሆነ የሀገሪቱ የንግድ እንቅስቃሴ ከዚህ ታላቅ ፕሮጀክት ከፍተኛ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

እንኳን ደስ አለን! 🇪🇹
2