Civil Engineering
1.36K subscribers
1.24K photos
21 videos
960 files
661 links
*ለሲቪል ; ለአርክቴክቶች÷ለኮንስትራክሽን ÷ ለሀይድሮሊክ መሀንዲሶች እና ተማሪዎች የተዘጋጀ ትምህርታዊ ቻናል ፡፡

@engineer03


http://www.Indiabix.com በዚህ ደግሞ ማንኛውንም ጥያቄና መልስ ታገኛላችሁ!

╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕
Download Telegram
💥የደህንነት ሄልሜቶች በቀለማት ሲለዩ


▪️ነጭ ሄልሜት፦ ለኢንጂነሮች፣ ለማናጀሮች፣ ለፎርማኖች፣ ለሱፐርቫይዘሮች
▪️ሰማያዊ ሄልሜት፦ ለኤሌክትሪሺያኖች ለአናፂዎችና ለቴክኒክ ሠራተኞች
▪️ቀይ ሄልሜት፦ ለእሳት አደጋ ሠራተኞች
▪️አረንጓዴ ሄልሜት፦ ለሴፍቲ ሠራተኞች
▪️ግሬይ ሄልሜት፦ ለሳይት ጎብኚዎች
▪️ቢጫ ሄልሜት፦ ለጉልበት እና ለግንባታ ማሽን ኦፕሬተር ሠራተኞች
▪️ ብራዎን ሄልሜት፦ ለበያጆችና ከፍተኛ ሙቀት ባለበት ቦታ ለሚሰሩ ሠራተኞች


ሠራተኞች በሥራ ወቅት በደህንነት ጉድለት ምክንያት የተለያዩ አደጋዎች እና ጉዳቶች ሲያጋጥሟቸው ይሰተዋላል፡፡ ይህንንም ችግር ለመቀነስ የተለያዩ የሕግ፣ የህብረተሰብ ጤና እና ማህበራዊ ግንዝቤ ሥራዎች ሲሞከሩ ይታያል፡፡

በተለይም እኤአ ከ1919 ዓ.ም ጀምሮ የዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (International Labour Organization/ILO) መቋቋምን ተከትሎ በርካታ ከሠራተኛ የሥራ ደህንነት ጋር የተያያዙ መርሆዎች እያደገ መምጣቱ አይዘነጋም፡፡

ይህንንም ተከተሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) ጠቅላላ ጉባዔ እኤአ በ1948 ዓ.ም ባወጣው ሁሉን አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መግለጫ (Universal Declaration of Human Rights-UDHR) የሥራ ላይ ደህንነት አንዱ የሠራተኞች መብት እነደሆነ ደንግጓል፡፡

የግንባታ ሥራ በራሱ እጅግ ውስብስብ ከመሆኑ ባሻገር በርካታ ሥራዎች በጉልበት የሚከናወኑ (labour intensive) በመሆናቸው ብሎም ከሥራው ባህሪ አንጻር ፈረጅ ብዙ የሥራ ክንውን የሚካሄድበት ስለሆነ በደህንነት ጉደለት ምክንያት በርካታ አደጋ እና ስጋት ሲያጋጥም ይሰታዋላል፡፡

እንደ ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (ILO) ሪፖርት ከሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየአመቱ በግንባታ ወቅት ቢያንስ 60ሺ ሠራተኞች ከደህንነት ጉደለት ጋር በተያየዘ ለሞት የሚዳረጉና ከባድ የአካል ጉዳት አደጋዎች እንዳሚያጋጥማቸው ጠቁሟል፡፡ ይህም ማለት በየአስር ደቂቃው ውስጥ አንድ ከባድ አደጋ ይደርሳል እንደ ማለት ነው፡፡ ሪፖርቱም በተለይ ከአጠቃላይ የሥራ ላይ አደጋዎች ውስጥ 17 ፐርሰንት ይህም ከስድስት አደጋዎች ውስጥ አንዱ የሚሆነው ገዳይ አደጋ በግንባታ ዘርፍ እንደሆነ ያትታል፡፡

የግንባታ ደህንነት ሲባል አንድ የግንባታ ፕሮጀክት ከጥንስሱ እስከ ፍጻሜው ድረስ በሚካሄዱ መጠነ ሰፊ የግንባታ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሊደረጉ የሚገባቸው እንዲሁም ሊወሰዱ የሚችሉ ጥንቃቄዎች የሚይዝ አሰራር ነው፡፡

የግንባታ ደህንነትን በተመለከተም በ2005 ዓ.ም የወጣው የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፖሊሲ፣ የኮንስትራክሽን ሥራ ደህንነት ጉዳይ ከኢንዱስትሪው ዕድገት ጋር ተያይዞ በትይዩ ትኩረት የሚሠጠው ቁልፍ ስራ መሆን እንዳለበት ይናገራል፡፡ በፈጻሚ አካላት የሚስተዋለው በፕሮጀክት ሳይቶች የሥራ አካባቢ ደህንነት ፖሊሲ ስርዓት እንዲኖር ለማድረግ የሚወጣው ወጪና የሚመደበው ጊዜ እንደተጨማሪ ወጪ አድርጐ የመመልከት እሳቤ በመሠረታዊነት መቀየር እንዳለበትና ለስራ አካባቢ ሰራተኞች ጤንነትና ደህንነት ጥበቃ የሚወጣ ወጪ የግንባታ ወጪ በመሆኑ ትርፍ እንዳልሆነ አጥብቆ ያሳስባል፡፡

በኮንስትራክሽን ሥራ አካባቢዎች መደረግ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች ባለመወሰዳቸው ምክንያት የሚደርሱ ከቀላል እስከ ከባድ የንብረትና ህይወት መጥፋት ጉዳቶች መከላከል ያሻል፡፡ እነዚን የመሰሉ አደጋዎች ለመከላለል የሚያስችል በግንባታ ሂደት መወሰድ ስለሚገባው ጥንቃቄ በቂ ስልጠናና አፈጻጸሙን መከታተል የዋናው ሥራ አካል ተደርጎ መፈጸም ይኖርበታል፡፡

የኮንስትራክሽን አካባቢ ደህንነት (Construction Site safety) የግንባታ ሂደቱ ጥራት፣ ቅልጥፍና እና ውጤታማነት መረጋገጥ ወሳኝ እርምጃ ተደርጐ መወሰድ ይኖርበታል፡፡ ስለዚህ በሀገራችን የኮንስትራክሽን ሥራ እንቅስቃሴ ደህንነት ማስፈን ፖሊሲው አጉልቶ ያስቀመጠበትን ሁኔታ መገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡


https://t.me/engineer03
💥የግንባታ ፕላን ፍቃድ ስለማቅረብ

Submission of Application and Plans

🌟የኢትዮጵያ የሕንፃ አዋጅ  ፮፻፳፬/፪ሺ፩ ክፍል ሁለት መሰረት “የግንባታ ሥራ ለማካሄድ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ለከተማው አስተዳደር ወይም ለተሰየመው  አካል ማመልከቻ ማቅረብ ይኖርበታል።

▶️ሕንፃን ለመገንባት የሚቀርብ ማመልከቻ የከተማው አስተዳደር ወይም የተሰየመው አካል ለዚሁ ብሎ ባዘጋጀው ቅፅ መሠረት ሆኖ ይህም  እንደ ሕንፃው ምድብ አይነት ዲዛይንና ሪፖርት የያዘ መሆን አለበት።

▶️ከማመልከቻው ጋር በአዋሳኝ ባሉ ስፍራዎች የሚገኙ ዋና መንገዶችንና የታወቁ ቦታዎችን ስም የሚገልፁ መረጃዎች መቅረብ ይኖርባቸዋል። አመልካቹ ሕንፃ በሚገነባበት ቦታ ወይም በንብረቱ ላይ የይዞታ መብት እንዳለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል

▶️የሚቀርቡት ሠነዶች በዚህ አዋጅና በሌሎች ሕጐች የተመለከቱት መሟላታቸውን ለማረጋገጥ በበቂ ሁኔታ የተሟሉ መሆን ይኖርባቸዋል”

🖱According to Proclamation No. 624/2009 “Any person intending to carry out construction shall submit an application to the urban administration or designated organ. The application to carry out construction shall be made on an application form prepared by the urban administration or designated organ and shall consist of a design and report according to the category of building in question.

The application shall be accompanied with a reference to main roads and names of prominent places. The applicant shall submit proof of possession rights to the land or property on which the construction will take place. The documents to be submitted shall be sufficiently complete to determine compliance with this Proclamation and other laws”

#ConstructionLaw

https://t.me/engineer03
💥የግንባታ ፍቃድ አጠያየቅ እና የወሰንተኛ ጉዳይ

🚧የማሻሻያ፣ የመጠቀሚያ ፈቃድ፣ ጊዜያዊ ግንባታ ወይም የማፍረስ ሥራ ለማከናወን የሚቀርብ የግንባታ ፈቃድ ጥያቄ ሲኖር በተናጠል በተዘጋጀላቸው (ማለትም  ለአዲስ ለማስፋፊያ ወይም ለማሻሻያ ግንባታ ቅፅ፣ ለግንባታ እድሳት ፈቃድ ቅፅ፣ ለግንባታ ማፍረስ ፈቃድ ቅጽ፣ ለአገልግልት ለውጥ ቅጽ፣ ለጊዜያዊ ግንባታ ቅጽ) በመሙላት የግለሰብ ከሆነ በአመልካቹ ተፈርሞ፣ በመንግስታዊ፣ በሕዝባዊ እና የመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተያዘ ወይም የሚተዳደር ከሆነ በኃላፊው ተፊርሞ እና የድርጅቱ ማህተም አርፎበት ጥያቄው መቅረብ ይኖርበታል።

🌟ማንኛውም የግንባታ ፈቃድ ጠያቂ ስለወሰንተኞቹ ትክክለኛ መረጃ በወሰንተኛ ግንባታ መግለጫ ቅጽ ላይ ወሰንተኛውን በማስሞላትና በማስፈረም ማቅረብ አለበት፣ ቅፁን ለመሙላት ፈቃደኛ በማይሆን ወሰንተኛ የከተማ አስተዳደሩ ቅፁን የማስሞላት ሃላፊነት አለበት።

▶️ወሰን ላይ የሚገነባ የምግብ ማብሰያና መሰል አገልግሎት ሰጪ ክፍሎች ግድግዳ የእሳት ቃጠሎን በተሻለ ሁኔታ መከላከል በሚችል ድፍን የግድግዳ ቁሳቁስ መገንባት አለበት። ጭስ እና እንፋልት ወደወሰነተኛ መውጣት የለበትም።

በተለያዩ አካባቢዎች የሚገነቡ አንድ ዓይነት ስታንዳርድ ፕላኖች ያላቸው ግንባታዎች የየራሳቸው የግንባታ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል።

▶️ከዚህም በተጨማሪ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ማካተት ይኖርበታል፣ ወለልና በላይ ያለው ማንኛውም ግንባታ (የምድር በታች ወለል ቢኖረውም ባይኖረውም) ከወሰን ሁለት ሜትርና ከዚያ በታች ተጠግቶ የሚሰራ ከሆነ በቅድሚያ የወሰን ላይ ግንባታ ቅጽ መሙላትና ስምምነት ማግኘት ይኖርበታል፣ ለፈቃድ የሚቀርበው ስትራክቸራል ዲዛይን የወሰንተኛውን ነባር ህንፃ መዋቅር ይዘት ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት፤ የሚቀርበው የዲዛይን ሠነድ የወሰንተኛውን ነባር ህንፃ መጠን ለምሳሌ የኃይል ሚዛን (Load) ከግምት ያስገባበት አግባብ ማመልከት አለበት፣ በወሰንተኛ ነባር ግንባታ ደህንነት ላይ ምንም አይነት መናጋት እንዳይፈጠር በቁፋሮና በግንባታ ሂደት መወሰድ የሚኖርበትን የሚያሳይ የጥንቃቄ ንድፍ ለፍቃድ ከሚቀርበው ሰነድ ጋር መቅረብ አለበት።

▶️አየር ማስገቢያ ሳይኖረው ብርሃን ብቻ የሚያስገባ ግንባታ ወሰን ላይ ለመሥራት ለዚሁ ተብለው በተዘጋጁና አሳልፈው በማያሳዩ ውፍረታቸው ከ5 ሳ.ሜ የማያንስ የመስታወት ግርግዳ መጠቀም ይቻላል።

▶️ይህም በሚቀርበው ዲዛይን ላይ በግልጽ መጠቀስ ሲኖርበት ወሰን ላይ የተሰራ ከሆነ ወሰንተኛው እንደማንኛውም ድፍን የግድግዳ አካል አስጠግቶ ሊሰራበት ስለማይከለከል የብርሃን ማስገቢያ መስፈርት ለሚጠየቅበት ተጨማሪ ወይም አማራጭ የብርሃን ምንጭ ማመልከት አለበት።

ማንኛውም ሰው ግንባታውን እስከ ወሠን አስጠግቶ ማከናወን ይችላል ሆኖም ወሠን ላይ ለመገንባት ያቀደ ሰው በአዋሳኙ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የሚያደርገውን የመከላከያ ዘዴዎች ለአጎራባቹ ማሳወቅ ይኖርበታል።

▶️ግንባታው ተጀምሮ እስኪጠናቀቀ ድረስ በአጎራባቹ አደጋና ችግር በማያስከትል ሁኔታ መከናወን አለበት። በማንኛውም ጊዜ ወሰንተኛው ግንባታውን እንዲከታተል መፍቀድ   አለበት።

▶️በማንኛውም የግንባታ ወቅት ለሚፈጠር ችግር ገንቢው ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳል።

▶️በአዋጁ፣ በደንቡ እና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ባረቀቀው የሕንጻ መመሪያ (Building Directives) እና በሌሎች የማስፈጸሚያ ሰነድች ላይ የተገለፁትን መስፈርቶች ያላሟላ የግንባታ ፈቃድ ጥያቄ በግንባታ መጠየቂያ ቅጽ ላይ በተመለከተው ቦታ ያልተሟላበትን ምክንያት በመግለፅ ተመላሽ መደረግ ይኖርበታል።

https://t.me/engineer03
1
2016 2ND QUARTER CONSTRUCTION WORKS (ONLY DIRECT COST).pdf
20.1 MB
🏷በ2016 ዓ.ም የ ሁለተኛ ሩብ ዓመት ተግባራዊ የሚደረግ የግንባታ ሥራዎች ይፋዊ ቀጥተኛ ዋጋ ተመን (2nd Quarter Construction Works of Direct Cost)

🔑በተለይ የዋጋ ተመን (BOQ - Priced bill of Quantities) ለምታወጡ የዲዛይን አማካሪዎች እና የፕሮጀክት መሐንዲሶች ይጠማችኋል።

💫በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የምትገኙ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችም እንደመነሻ ሀሳብ ይጠቅማችኋል።


https://t.me/engineer03
💥በያዝነው የፈረንጆች አዲስ አመት ግንባታቸው የሚጀምርና በግንባታ ላይ የሚገኙ ስድስት ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች የሚከተሉት ናቸው፦ ሦሰቱ ከግብጽ ሲሆኑ ኬንያ፣ አይቮሪኮስትና ኢትዪጵያ አንድ አንድ አስመዝግበዋል።

ከእነዚህ ውስጥ  ቁመቱ 270 ሜትር የአቢሲኒያ ባንክ የሚያስገነባው ዋና መሥሪያ ቤት በሁለተኛነት ደረጃ ተቀምጧል።

Tallest Buildings Under Construction in Africa  2024

1. Tour F
   - Height: 386 m (1,266 ft)
   - Location: Abidjan, Ivory Coast
   - Expected Completion: 2025

2. Bank of Abyssinia Headquarters
   - Height: 270 m (890 ft)
   - Location: Addis Ababa, Ethiopia
   - Expected Completion: 2025

3. Iconic Tower Alamein
   - Height: 250 m (820 ft)
   - Location: El Alamein, Egypt
   - Expected Completion: 2026

4. Capital Diamond Tower
   - Height: 239 m (784 ft)
   - Location: New Admin, Egypt
   - Expected Completion: 2026

5. Infinity Tower
   - Height: 200 m (660 ft)
   - Location: New Admin, Egypt
   - Expected Completion: 2024

6. 88 Nairobi Condominium Tower
   - Height: 176 m (577 ft)
   - Location: Nairobi, Kenya


https://t.me/engineer03
💥ግንባታ ከመጀመሩ በፊት Geo Technical site investigation ( የጂኦ-ቴክኒካል ምርመራ ) ለምን እናደርጋለን ጥቅሙስ ?

🌟የጂኦ-ቴክኒካል ምርመራ ዋና ዓላማ ግንባታ በሚካሄድበት ቦታ የአፈር ምርመራ ማድረግ ነው።

▶️በግንባታ መስክ ውስጥ ሊከተሏቸው ከሚገቡ ዋና ዋና ተግባራት መካከል የጂኦቴክኒካል ምርመራ አንዱ ነው።

▶️የጂኦቴክኒካል ምርመራዎች የሚከናወኑት በጂኦቴክኒካል መሐንዲሶች ወይም በምህንድስና ጂኦሎጂስቶች የመሬት ስራዎችን እና ለታቀዱ አወቃቀሮች ለመንደፍ እና ለመሬት ስራዎች እና አወቃቀሮች መሠረቶችን ለመንደፍ በአንድ ግንባታ ቦታ ዙሪያ ስላለው የአፈር እና የድንጋይ አካላዊ ባህሪያት መረጃን ለማግኘት ነው።

🚧ይህ ዓይነቱ ምርመራ የሳይት ምርመራ ተብሎ ይጠራል.

በተጨማሪም፣ የጂኦቴክኒካል ምርመራዎች እንዲሁም ለመሬት ስር ማስተላለፊያ መስመሮች፣ ዘይት እና ጋዝ ቧንቧዎች፣ ሬዲዮአክቲቭ የቆሻሻ አወጋገድ እና የፀሐይ ሙቀት ማከማቻ ፋሲሊቲዎች የሚፈለጉትን የአፈር ወይም የድጋሚ ሙሌት ቁሶች የሙቀት መቋቋምን ለመለካት ጥቅም ላይ ይውላሉ።

🖱የጂኦቴክኒካል ምርመራ ለምን አስፈላጊ ነው?

ሊያጋጥሙ የሚችሉ የመሬት ሁኔታዎችን ጥሩ ግምገማ ያቀርባል።

ግንባታው ለታለመለት ልማት ወይም መልሶ ማልማት ዓላማ ተስማሚ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ይሰጣል።

በጥሩ ምህንድስና አሠራር መሰረት ዲዛይን እና ግንባታን ለመርዳት ተስማሚ መለኪያዎችን ያቀርባል።

በፕሮጀክቱ የሕይወት ዑደት ውስጥ በአካባቢ ላይ ያለውን አደጋ እና በሰዎች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ፈልጎ እና ክትትል ያደርጋል።

⚡️በሁሉም የፕሮጀክት በጀት አወጣጥ ላይ ይረዳል፣ ቀልጣፋ ዲዛይን ይፈቅዳል፣ እና ግንባታው በምሰራበት ቦታ ላይ ሊከሰቱ ስለሚችሉ አደጋዎች አስቀድሞ ያስጠነቅቃል።

🫵በቀላል አነጋገር

የጂኦቴክኒካል ምርመራ ፕሮጀክቱ አዋጭ እንደሆነ እና በተቀላጠፈ መልኩ ሊቀረጽ እና ሊገነባ እንደሚችል እንደ ጠቃሚ ማረጋገጫ ሆኖ ያገለግላል።

📎የጂኦቴክኒክ መሐንዲሶች በአንድ ቦታ ላይ በታቀዱ የግንባታ መዋቅሮች ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉትን አደጋዎች በመለየት የተካኑ ናቸው።

🔗ይህንን በተለያዩ የምርመራ ቴክኒኮች፣ በጉድጓዶች ቀጥተኛ ናሙና እና የሙከራ ጉድጓዶችን እና ቀጥተኛ ያልሆኑ የጂኦፊዚካል ቴክኒኮችን ጨምሮ ሊያደርጉ ይችላሉ።

📝የጂኦቴክኒካል ትንተና ልዩ ሶፍትዌርን በመጠቀም የገሃዱ አለም እንቅስቃሴን እና የድርጊት ሁኔታን ለመገመት በጂኦቴክኒካል መለኪያዎች መሰረት መዋቅራዊ ባህሪን መምሰል ይችላል።


https://t.me/engineer03
An ideal vertical curve to join two gradients, is
Anonymous Quiz
59%
parabolic
16%
elliptical
10%
circular
12%
hyperbolic
4%
none of these.
💥ጥናት

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ጥራታቸው ተጠብቆ ባለመገንባታቸው፣ በዕጣ የቤት ባለቤት የሆኑ ዕድለኞች ለከፍተኛ ወጪ እየተዳረጉ መሆናቸውን የአፍሪካ ከተሞች የምርምር ጥምረት (ACRC) እና ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ (FSS) በጋራ ባደረጉት ጥናት ማረጋገጥ መቻላቸውን አስታውቀዋል።

ሁለቱ ተቋማት ጥናቱን ለአንድ ዓመት ያህል ነው ያደረጉት።

በጥናቱ ከ6 በላይ ከፍተኛ ተመራማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በኢኮኖሚ፣ በመዋቅራዊ ሽግግርና በወጣቶች አቅም ግንባታና በመኖሪያ ቤቶች ላይ የተደረገ ነው።

ጥናቱ ምን ይላል ?

- በአዲስ አበባ ከተማ ከመነሻውም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሲገነቡ ደረጃቸውን የጠበቁ አይደሉም፡፡

- መንግሥት 40/60 ወይም የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በዕጣ ለደረሳቸው ሲያቀርብ ጥራታቸውን በጠበቀ መንገድ ስለማይገነቡ፣ ዕድለኞች መልሰው አፍርሶ ለመሥራት ይገደዳሉ ለከፍተኛ ወጪ ይዳረጋሉ።

- የጋራ መኖሪያ ቤት የደረሳቸው ዕድለኞች ፦
* ለኤሌክትሪክ ኃይል ዝርጋታ፣
* የሲራሚክ ንጣፍ፣
* ለመፀዳጃ ቤት መስመር፣
* ግድግዳ እንደገና ለመሥራትና ሌሎች የጎደሉ ነገሮች ለማሟላት ለከፍተኛ ወጪ ይዳረጋሉ።

- እነዚህ ጉዳዮች ከፍተኛ ትኩረት የሚፈልጉ በመሆናቸው፣ መንግሥት ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ከግብዓት ጀምሮ እስከ ባለሙያ ድረስ ጥራታቸውን በመጠበቅ ማቅረብ ይኖርበታል።

በተጨማሪ ...

በአዲስ አበባ ከተማ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ለሥራ ተስማሚ የሆኑ ነገሮች እንደሌላቸው ታይቷል። ወጣቶች በኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ፣ በኢመደበኛ ዘርፍና በጤና ላይ ያላቸውን በጎ ተግባራትና ያሉባቸው ችግሮች ተለይተው በጥናቱ ተካተዋል።

በኢትዮጵያ ከዚህ በፊት አብዛኛውን የቤት አቅርቦት ተፈጻሚ የሚሆነው በመንግሥት ሲሆን በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ቤት አልሚ ድርጅቶች ተቋቁመው የማኅበረሰቡን የቤት ጥያቄ እየመለሱ መሆናቸው የሚበረታታ ነው።

በቤት አቅርቦት ላይ ለውጦች እየመጡ ቢሆንም አሁንም የመሬት አቅርቦት፣ እንዲሁም በዝቅተኛና በመካከለኛ ገቢ ላይ የሚገኙ ሰዎች ቤት ለመሥራት ቢፈልጉ የፋይናንስ አቅርቦት ችግር እየገጠማቸው ነው።

በአጠቃላይ ጥናት የተደረገባቸው ጉዳዮች ላይ ያሉትን ችግሮች ለመፍታትና በጥናቱ የቀረቡ ግኝቶች መሬት ወርደው ተግባራዊ እንዲሆኑ፣ ለፖሊሲ አውጪዎች የሚቀርቡ ይቀርባሉ ተብሏል።

#ሪፖርተር_ጋዜጣ
1
💥የፎርምወርክ ማፍረሻ ቀነ ገደብ

💫በቀድሞው የሀገራችን የሕንጻ እና መንገድ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ባለሥልጣን (Building and Transport Construction Design Aucthority – BaTCoDA Specification) ላይ በቁጥር 03244  ላይ እንደተመለከተው  ፎርምወርክ የሚነሳበት (የሚነቀልበት/የሚፈርስበት) ቀንን (Formwork Removal) በተመለተ እንደሚከተለው አስቀምጧል።

አቀባዊ የአርማታ ግድግዳዎች ( shear wall)፣ አምዶች (columns) እና aግዳሚ ጋንዴላዎች ወይም ምሰሶዎች (beams) = ከ16 ሰዓታት በኋላ

የወለል አርማታ ሙሌት የታችኛው አልጋ (slab soffit) = በ21 ቀናት ውስጥ

የወለል አርማታ የጎንዮሽ ማፈኛ (props of slab) = በ14 ቀናት

የአግዳሚ ጋንዴላ/ምሰሶ የታችኛው አልጋ (soffit of beam) = 21 ቀናት

የአግዳሚ ጋንዴላ/ምሰሶ የጎንዮሽ ማፈኛ (Props of beam) = 14 ቀናት

🖱ማሳሰቢያ፦ ለተዘረዘሩት የአርማታ ስትራክቸር ክፍሎች (Concrete skeletons) የተጠቀሱት ቀናት "ቢያንስ ቢያንስ" ተብሎ የተቀመጠ ዝቅተኛው የጊዜ ገደብ ነው።

https://t.me/engineer03
✍️ለአንድ ህንፃ መፍረስ መክንያት ይሆናል ተብለው  ብዙ ልህቃን የሚስማሙበት ጉዳይ:-

🚧አንድ ህንፃ የተለያዩ structural member (column , beam , slab..etc) ውቅር ነው ስዋቀርም ሁሉም የየራሳቸው አገልግሎት አላቸው የህንፃው ህልውና የመፍረስና ያለመፍረስ ዋስትና ተገብውን አገልግሎት በተገቢው መንገድ የመስጠት ሀላፊነትና የህንፃው የአገልግሎት እድሜ የሚወሰነው well designed structural member መሆኑ እሙን ነው። 

✍️The reasons a building collapses can be due to
✔️poor structural design,
✔️poor compliance with specifications
✔️poor quality control
✔️faulty construction methodology foundation failure
✔️extraordinary loads and corruption. Natural disaster is also identified as a cause of building collapse.

✍️በመሆኑም በእኛ አገር በስፋት ከሚስተዋለው ምክንያቶች መሀከል
☑️ poor structural design
☑️faulty construction
☑️poor quality control and corruption ዋነኞቹ ናቸው።

👉አንድ ህንፃ እኛ ዲዛይን ካደረግንበት ባነሰና በጣም ትንሽዬ በሆነ ሎድ ሊፈርስ ይችላል ? እንዴት??

#⃣ህንጻው መሸከም ከሚችለው ባነሰ በትንሽዬ ሎድ ሊፈርስ የሚችለው በሁለት ምክንያቶች ነው
1,በ Fatigue
2, Creep ነው

1,Fatigue
✔️ሎዶቹ ትንንሽዬ ቢሆኑም እንኳን በሎድ ድግግሞሽ የተነሳ የህንጻው ጥንካሬ ሲደክም የሚፈጠር ነው፡፡ ይህ ሁኔታ በአብዛኛው የሚከሰተው ድልድዮች ላይ ነው - የመኪና ድግግሞሽ፡፡

2,Creep
✔️አንድ ሎድ አንድ ቦታ ላይ ለብዙ ጊዜ በመቀመጡ ሳቢያ Strain ሲጨምር የሚፈጠር ነው፡፡

https://t.me/engineer03
💥ስለንኡስ ተቋራጭነት(sub-contract)

-ንኡስ ተቋራጭነት(sub-contract) በፍትሀብሄር ህጉ አገላለጽ ከዋናው ተቋራጭ የተስማማ ሁለተኛ ተቋራጭ ይባላል፡፡ ይሄውም ዋናው ተቋራጭ የግንባታ ውሉን ስራ በከፊል ለማስፈጸም ከአንድ ሶስተኛ ወገን ከሆነ ሰው ጋር የሚደረግ ነው፡፡(የፍ/ህ/ቁ 3201(2)) 
-ውሎችን ለሌላ መልቀቅ(Assignment) ደግሞ ዋናው ተቋራጭ የግንባታ ውሉን ስራ በሙሉ እንዲፈጽምለት ለአንድ ሶስተኛ ወገን ለሆነ ሲያስተላልፍ ነው፡፡(የፍ/ህ/ቁ 3201(1))

-ስለዚህ ንኡስ ተቋራጭነት የግንባታ ስራ ተቋራጮች ከአሰሪው ጋር ሊገነቡት ግዴታ የገቡበትን የግንባታ ስራ በከፊል ለሌላ ተቋራጭ በውል በሚያሰሩበት ጊዜ የሚነሳ ጉዳይ ነው፡፡ውሎችን ለሌላ መልቀቅ የሚባለውም ከንኡስ ተቋራጭነት ጋር ሁኔታው አንድ አይነት ሲሆን ልዩነቱ ዋናው ተቋራጭ ለሌላ ተቋራጭ የሚያሰራው ሙሉውን የግንባታ ስራ ነው፡፡
-ንኡስ ተቋራጭነት ሁለት አይነት ነው፡፡በአሰሪው የሚታወቅ(Nominated sub-contracting) እና በአሰሪው የማይታወቅ(Non nominated sub-contracting)::ከውጤት አንጻር ተመሳሳይ ቢሆኑም ንኡስ ተቋራጭነቱን አሰሪው የፈቀደውና ያወቀው የሆነ እንደሆነ ልዩነቱ ዋናው ተቋራጭ ከመዘግየት ቅጣት ነጻ ይሆናል፡፡(የፍ/ህ/ቁ 3206)   
-ንኡስ ተቋራጮች ለሰሩበት ክፍያ ከማን መጠየቅ ይችላሉ?
-ንኡስ ተቋራጮች ለሰሩት ስራ በውላቸው መሰረት ከዋናው ተቋራጭ ክፍያ የመጠየቅ መብት ይኖራቸዋል፡፡(የፍ/ህ/ቁ 1755፣1756) ምክንያቱም ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል ህግ ነው፡፡(የፍ/ህ/ቁ1731)

-በተጨማሪም የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3040 በአንድ የህንጻ ስራ ተቋራጭነት ውስጥ የሚሰሩ ስራ ተቋራጮች ወይም ሰራተኞች የሰሩበትን ስራ ዋጋ ለመከፈል ክሳቸውን ባቀረቡበት ጊዜ አሰሪው ለስራ ተቋራጩ ሊከፍል በሚገባው ገንዘብ መጠን ባሰሪው ላይ በቀጥታ ገንዘባቸውን ለመጠየቅ መብት አላቸው በሚል ይደነግጋል፡፡ስለዚህ ከዋናው አሰሪ ላይም በቀጥታ ክፍያ ለመጠየቅ መብት ይኖራቸዋል ማለት ነው፡፡

https://t.me/engineer03
👍1
🪡 Post tension 

ከቃሉ ስንነሳ post - ድህረ ማለት ነው። concrete ከተሞላ በኋላ ብረቱን ስንወጥር post tension (ድህረ መወጠር) concrete ከመሞላቱ በፊት ደግሞ ሲወጠር pre-tension ይባላል።   ዛሬ ስለ post tension እናውጋ!

Post tension እዛው መስክ(site) ላይ የምናከናውነው የግንባታ ዘዬ ነው pretension ግን  በ precast ማምረቻ warehouseኦች ላይ ሚተገበር ነው።

በpost tension ጊዜ መጀመሪያ ብረት እናነጥፋለን(bottom bar) ኮለኖች አካባቢ lower reinforcement እናበጃለን ከዛም ኮለኖች አካባቢ punching shear reinforcement እናበጃለን (drop panel in exceptional case ካልሆነ አንጠቀምም) ከዛም chair bar (“ከበሌቶ”) ካረግን በኋላ strand እንዘረጋለን ከዛም በ side formwork በኩል  መወጠሪያ ብረቶቻችንን ካወጣን በኋላ anchorage እና grout vent እንዘረጋለን ከዛም እናጠብቃቸዋለን ከዛም top reinforcement (minimum reinforcement ለ shrinkage እና ለ temperature) ከዛም ኮንክሪት መሙላት ከዛም ያወጣነውን ቴንደን መወጠር ከዛም የተመዘዘውን መጠን መለካት ( measuring elongation) ከዛም የወጡትን የ strand ጫፎች መለካት ከዛም ክፍተቱን (void) በሲሚንቶ (cement screed) መሙላት።


https://t.me/engineer03
1👍1
የኮንስትራክሽን_ሥራዎች_ውል_አዘገጃጀት፣_ለሕግ_ባለሞያዎችና_ለምሕንድስና_ባለሞያዎች_በአማርኛ_የቀረበ፤.pdf
271.8 KB
💥ውል ለብዙ ስራዎች መቀላጠፍ መሰረት የሆነና የተለያዩ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ ችግሩን የመፍቻ ዘዴ ነው። የአገራችን ህዝብ ስለውል ያለው ግንዛቤ የዳበረ ነው ለማለት የሚከብድ ቢሆን የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች ባለሙያዎችን በማማከር ውል አዘጋጅተው ወደ ስራ የሚገቡበት ሁኔታ አለ። የሰው ልጅ በቃሉ ይታሰራል ነውና ውል ለሚያስፈልገው ጉዳይ ሁሉ ህጉን በተከተለ መልኩ አዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱ የተሻለ ነው።

💫የዉል ይዘቱም የተለያየ ሲሆን የኮንስትራክሽን ሰራ ውል ስናዘጋጅ መከተል ያለብንን መንገድ ይህ የተዘጋጀው ፅሁፍ አብራርቶ ያስቀምጣል

https://t.me/engineer03
💥የቅየሳ መሳሪያ/Surveying Equipment/
.
ቅየሳ/surveying/ በተፈጥሮ ሳይንስ የሚመደብ የስራ ሙያ ሲሆን ሁለት የተለያዪ መገኛዎችን ርቀት/distance/፣ ከፍታ
ልኬት/Elevation/ እና በሁለቱ መካከል የሚገኘውን ማዕዘን/ Angle/ ለማውጣት የምንጠቀምበት ዘዴ ነው።
.
ሁለት አይነት የቅየሳ መሳሪያ ይገኛሉ
1. ቴዶላይት/Thedolite/
2. ቶታል ስቴሽን/Total Station/

ቶታል ስቴሽን ጂፒስ፣ጨረር እና የከፍታ መለኪያ ሴንሰር በመጠቀም ትክክለኛ የከፍታ ልዪነት/Elevation difference እና ርቀትን ለመለካት ይጠቅመናል።

ቴዶላይት ደግሞ በሁለት ነጥቦች መካከል ያለውን የከፍታ ልዪነት ለመለካት ሲያገለግል በመካከላቸው ያለውን ርቀት ግን
መለካት አይችልም።
.
🚩ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን  SHARE  አድርጉልን።

https://t.me/engineer03
ከኢትዮጵያ አልፎ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት አርማ  ለሆነው 128ኛ ዓመት የአድዋ ድል መታሰቢያ እንኳን  አደረሳችሁ!!!!

የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ.ም
በአዲስ አበባ የኬብል ካር ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ😍

ኦቪድ ግሩፕ የትራንስፖርት ችግርን መፍታት የሚያስችል የኬብል ካር (በገመድ ላይ ተንጠልጣይ የህዝብ ትራንስፖርት) ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮናስ ታደሰ ገልጸዋል።

ኦቪድ ግሩፕ በቴክኖሎጂ የታገዙ ዘመናዊ ቤቶችን ከመገንባት ባሻገር የትራንስፖርት ችግርን ለመፍታት በአዲስ አበባ የኬብል ካር ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ የፕሮጀክት ጥናት ማጠናቀቁን ዋና ሥራ አስፈፃሚው አስታውቀዋል።

የባቡር እና የመኪና መሰረተ ልማቶችን ማፍረስ ሳያስፈልግ በገመድ ላይ ተንጠልጣይ የህዝብ ትራንስፖርት ወይም ኬብል ካር ቴክኖሎጂን በአዲስ አበባ ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል።

በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ የኢትዮጵያን ገጽታ የሚያጎሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው፤ ኦቪድ ግሩፕም በግንባታው ዘርፍ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ዘመናዊ ከተማ ለመገንባት በመንግስት የሚደረገውን ጥረት የበለጠ የሚደግፍ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ኦቪድ ሀገራዊ ልማትን ከማገዝ ባለፈ በግንባታው ዘርፍ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እና በአጭር ጊዜ የማጠናቀቅ ስራውን እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ተዘግቧል።
Team ethio construction  Wishes all Our Muslim Family & Frends

🌙 EID MUBARAK❤️
ECWC for fresh graduates
Ethiopian Construction and Works Corporation  invites certified and skilled candidates for the varied positions.
The Ethiopian Construction Works Corporation (ECWC) is a public enterprise established on 18 Dec. 2015 based mostly on Council of Ministers Regulation No. 366/2015 with a licensed capital of Birr 20,313,608,143.90. Out of which Birr 15,598,806,251.43 paid up in money and in sort. Council of Ministers Regulation No. 390/2016 has amended the institution of the company, on 28 Sep. 2016.
The company is a results of the amalgamation of three previously unbiased public enterprises, particularly the Ethiopian Road Construction Corporation, the Ethiopian Water Works Construction Enterprise and the Ethiopian Prefabricated Building Parts Production Enterprise.
Quick Details about 
Hiring Organization: Ethiopian Construction and Works Corporation
Shortly Known as: ECWC/ኢኮሥኮ/
Organization Type: Government Organization
Organization Size: 1001+ employees
Headquarters: Addis Ababa, Ethiopia
Official Website:www.ecwc.gov.et/

How to Apply
1. Ensure you fulfill the minimum set requirement.
. All these that do not fulfill the above requirements will probably be rejected robotically.
Only shortlisted candidates will probably be contacted.
1
የግንባታ_ሥራዎች_ይፋዊ_ቀጥተኛ_ዋጋ_ተመን.pdf
21 MB
‼️በ2016 ዓ.ም የ 3ኛ ሩብ ዓመት ተግባራዊ የሚደረግ የግንባታ ሥራዎች ይፋዊ ቀጥተኛ ዋጋ ተመን (3rd Quarter Construction Works of Direct Cost)

✔️በተለይ የዋጋ ተመን (BOQ - Priced bill of Quantities) ለምታወጡ የዲዛይን አማካሪዎች እና የፕሮጀክት መሐንዲሶች ይጠማችኋል።

✔️በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የምትገኙ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችም እንደመነሻ ሀሳብ ይጠቅማችኋል።

https://t.me/engineer03
1
#በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት የሚስችል ስልጠና ተሰጠ

በግንባታ ውስጥ የኮንትራት ስምምነት ችግር፣ የተጨማሪ ጊዜና የተጨማሪ ገንዘብ ጥያቄ፣ የባህርይ ችግር፣ ከልምድ ማነስ የሚፈጠር ቴክኒካዊ ችግር እንዲሁም የጥራት ግድፈት ምክንያቶች አለመግባባቶች፣ ግጭቶች እንዲሁም ሙግቶች የሚከሰቱባቸው አጋጣሚዎች አሉ፡፡

እነዚህ አለመግባባቶች፣ ግጭቶች እና ሙግቶች በአግባቡ መፍትሄ ካልተሰጣቸው የፕሮጀክቶች መጓተትና ዋጋ መጨመርን፣ በባለድርሻ አካላት መካከል የእምነት መታጣትን፣ ገፅታን ማጉደፍ፣ መልካም የስራ ግንኙነትን ማሻከር፣ የምርታማነት መቀነስን፣ የትርፍ መታጣትን እንዲሁም የጥራት ጉድለትን ያስከትላሉ፡፡

እነዚህን ችግሮች በመፍታት የግንባታ ፕሮጀክቶች ውጤታማ እንዲሆኑ አማራጭ የግጭት አፈታት ስርዓት ሚና ይጫወታል፡፡ 

አማራጭ የግጭት አፈታት ስርዓት በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ በግንባታ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ሂደት በተለያዩ ባለድርሻ አካላት መካከል የሚከሰቱ ውዝግቦች፣ አለመግባበቶች እና ሙግቶች ከመደበኛ ፍርድ ቤት ውጪ ገለልተኛ በሆኑ አካላት ሳይጓተቱና ለብዙ ወጪ ሳያጋልጡ ሚዛናዊ ውሳኔ ሚያገኙበት ሂደት ነው፡፡

ስርዓቱ ለሚገጥሙ ውዝግቦች ሰነዶችን በመፈተሸ፣ የእማኞችና የተሟጋችን መረጃዎች መሰረት በማድረግና በማረጋገጥ በሚሰጥ ሚዛናዊ ውሳኔ ላይ ተሟጋቾች ከተስማሙ ህጋዊ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 የተቋቋመና በደንብ ቁጥር 524/2015 ሥልጣንና ተግባራቱ ተዘርዝርው የተሰጡ ሲሆን የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ላይ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በአማራጭ የግጭት አፈታት ሥርዓት ከመደበኛ ፍርድ ቤት ሥርዓት ውጪ እልባት እንዲያገኙ እንደሚያደርግ በዚሁ ደንብ አንቀጽ 5(16) ላይ ተቀምጧል፡፡

በዚሁ መሰረትም የኮንስትራክሽን ግጭት አፈታት የስራ ክፍል በቅርቡ ተቋቁሞ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

የኮንስትራክሽን አማራጭ የግጭት አፈታት ዘዴ በዋናነት በክርክር ጊዜ የሚኖረውን መራዘም ለመቀነስ፤ በዘርፉ ያሉትን አማራጭ የግጭት መፍቻ በመጠቀም በፍጥነት ጉዳያቸውን እንዲያከናውኑ የሚረዳ ሲሆን ይህን ተግባር ውጤታማ ለማድረግ የሚስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰሞኑን ተሰጥቷል፡፡

ለ10 ቀናት የቆየ ስልጠናው ለስራ ክፍሉ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ የስራ ክፍሎች ለተውጣጡ አካላት የተሰጠ ነው፡፡

ስልጠናውን የሰጡት ዕውቀትና ልምድን ያዳበሩ እንዲሁም ሕግን እየተገበሩ ያሉ ዳኞችና ጠበቆች በመሆናቸው ውጤታማ ነው፡፡

የካምፓኒዎችና ፕሮጀክቶች ምዝገባ ዴስክ ኃላፊ የሆኑት አቶ ፀሐይ ክበበው ስልጠናውን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት በምህንድስና ሙያ ውስጥ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን የአፈታት ህጋዊና ሳይንሳዊ ዘዴዎችን ከኢትዮጵያ ሕግ አንፃር የተቃኘ እንዲሁም በቅርቡ የወጣውን አዋጅ 1237/ 2013 ን መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል።

የኢንዱስትሪው የግጭት አፈታት ተግባር ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በአዲስ መልክ የተሰጠው ኃላፊነት ከመሆኑ አንፃር ይህንኑ በውጤታማነት ለመወጣት የሚያግዝ እንዲሁም ለተጨማሪ ጥረት የሚያነሳሳ ስልጠና መሆኑንም አክለዋል፡፡

ሰልጣኞች በዘርፉ የሚከሰቱ ግጭቶችንና ሙግቶችን መፍታት የሚያስችሉ ሂደቶችን በመተግበር የማደራደር፣ የማስማማት እና የማስታረቅ ትግበራውን ለማሳካት የሚያስችሉ ንድፈሃሳባዊ እንዲሁም ተዛማጅ የሆነ ተግባር ተኮር ስልጠና መሰጠቱንም ገልፀዋል፡፡

Via Ethiopia Construction Authority


https://t.me/engineer03
1👍1