Civil Engineering
1.36K subscribers
1.24K photos
21 videos
960 files
661 links
*ለሲቪል ; ለአርክቴክቶች÷ለኮንስትራክሽን ÷ ለሀይድሮሊክ መሀንዲሶች እና ተማሪዎች የተዘጋጀ ትምህርታዊ ቻናል ፡፡

@engineer03


http://www.Indiabix.com በዚህ ደግሞ ማንኛውንም ጥያቄና መልስ ታገኛላችሁ!

╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕
Download Telegram
How to select suitable type of foundations?

1. ADEQUATE DEPTH
The foundation must have an adequate depth to prevent frost damage. For such foundations as bridge piers, the depth of the foundation must be sufficient to prevent undermining by scour.

2. BEARING CAPACITY FAILURE
The foundation must be safe against a bearing capacity failure.

3. SETTLEMENT
The foundation must not settle to such an extent that it damages the structure.

4. QUALITY
The foundation must be of adequate quality so that it is not subjected to deterioration, such as fromsulfate attack.

5. ADEQUATE STRENGTH
The foundation must be designed with sufficient strength that it does not fracture or break apart under the applied superstructure loads. The foundation must also be properly constructed in conformance with the design specifications.

6. ADVERSE SOIL CHANGES
The foundation must be able to resist long-term adverse soil changes. An example is expansive soil, which could expand or shrink causing movement of the foundation and damage to the structure.

7. SEISMIC FORCES
The foundation must be able to support the structure during an earthquake without excessive settlement or lateral movement.


https://t.me/engineer03
#ባህርዳር!

ለውቢቷ ባህርዳር ተጨማሪ ድምቀት የሆነው የአባይ ወንዝ ድልድይ በምሽት!

https://t.me/engineer03
" በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ ላሉ ባለሙያዎች #የብቃት_ምዘና ይጀመራል " -  ወንድሙ ሴታ (ኢንጂነር)

በኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዘርፍ ውስጥ ላሉ ባለሙያዎች #የብቃት_ምዘና እንደሚጀመር ተገለጸ፡፡

በዘርፉ ብቃት ሳይኖራቸው፣ አቅማቸው ሳይረጋገጥና ማረጋገጫ ሳያገኙ ራሳቸውን
#መሐንዲስ እያሉ የሚጠሩበትን አሠራር ያስቀራል የተባለለት እንዲሁም የባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት የሚረዳ የማሠልጠኛ ማንዋልና የሚመዘኑበት መመርያ መዘጋጀቱን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሚኒስትር  ደኤታ ወንድሙ ሴታ (ኢንጂነር) ምን አሉ ?

- በኮንስትራክሽን ዘርፍ ተመርቆ ወደ ሥራ የሚገባ አንድ ባለሙያ በሚሠራበት ተቋም ውስጥ በቆየ ቁጥር የሙያ ደረጃዎች ከመስጠት ባለፈ መመዘኛ ሥርዓት ባለመኖሩ፣ ባለሙያው ለሚጠበቅበት ዕውቀትና ክህሎት ብቁ ነውወይ ሚለው አይታወቅም።

- ከኢፌዴሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እየተዘጋጀ ያለው መመርያ በቅርቡ ለፍትሕ ሚኒስቴር ተልኮ ይፀድቅና ወደ ሥራ ይገባል።

- የሚወጣው መመርያ ባለሙያዎች የሚሠለጥኑበት ፣ የሚገመገሙበትና ዕውቅና የሚያገኙበት ከመሆኑም በላይ የሙያ ግድፈት ሲገኝባቸውም የሚቀጡበትን አሠራር አካቷል።

- አገሪቱ አሁን ባለችበት የኮንስትራክሽን ቁመና የግንባታ ጥራት አደጋ ውስጥ ነው። ሥራ ከተጀመረ በኋላም ሆነ ከመጀመሩ በፊት የሚታየው የጥራት መጓደል አሁን ካልተፈታ በቢሊዮን ዶላሮች የሚፈስበት ዘርፍ ተመልሶ የማይወጣበት ችግር ውስጥ ይገባል።

- በኮንስትራክሽን ዘርፉ የባለሙያ አቅምና የሙያ ሥነ ምግባር እየተሻሻለ ከመሄድ ይልቅ እየባሰበት ነው የሄደው ፤ ባለሙያው ከአዳዲስ ዕውቀትና ቴክኖሎጂ ጋር የሚተዋወቅበትና ራሱን የሚያበቃበት ሳይሆን እያጠፋ የሚማርበት ሆኖ ቀጥሏል።

- በዘርፉ በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ባለሙያዎች የሉም። ባለሙያዎቹ ወደ ሥራ ከገቡ በኋላ ብቃታቸው ሊያድግ የሚችለው በራሳቸው ጥረት እንጂ፣ ከዘርፉ በሚያገኙት ትምህርትና ተቋማዊ ዕውቀት አይደለም።

- በአገር ውስጥ የበቁ የሚባሉት እና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ወደ ሌሎች አገሮች እየተሰደዱ ናቸው። በተለይም በምሥራቅና በደቡብ አፍሪካ አገሮች ተፈላጊ ናቸው። በአገር ውስጥ ያሉ ባለሙያዎችም ባሉበት ተቋም ለረዥም ጊዜ ረግተው አይቆዩም። በበገበያ ውስጥም የዋጋ ጭማሪን በየጊዜው መተንበይ በማይቻልበት ሁኔታ የግንባታ መሣሪያዎች ዋጋ አልቀመስ ብሏል።

- ግዙፍ ፕሮጀክቶች አብዛኞቹ የውጭ ኮንትራክተሮች ብቻ የሚይዟቸው፣ የአገር ውስጥ ባለሙያዎች የውጭ ኮንትራክተሮች በሚይዟቸው ፕሮጀክት ውስጥ ገብተው ዕውቀት እንዲቀስሙ የሚያደርግ አሠራር አልተዘረጋም ይህ የዘርፉ ሌላው ተግዳሮት ነው።

- በኮንስትራክሽን ዘርፍ የግዥ ሥርዓትን ጠንቅቆ የሚያውቅ ባለሙያ አለመኖሩ ፤ ሁሉም ባወቀውና በገባው ልክ እንጂ በትክክል ሥራውን ተገንዝቦ የሚሠራ የለም።

- በኮንትራት አስተዳደር የተሰማሩ ባለሙያዎች በአንድ ጉዳይ ባለመግባባታቸው ምክንያት ክስ ሲመጣ ተመልሶ ውልን ከመቃኘት ውጪ፣ ከጅምሩ የኮንትራት ውል አስተዳደርን ዝርዝር ጉዳይ ተረድቶ የሚያስረዳ ባለሙያ የለም።

- ለኮንስትራክሽን ጥራት መጓደል ፦ በግዥ ሥርዓቱ ላይ ያለው አሠራር፣ የፕሮጀክቶች ዲዛይን የተሟላና የተደራጀ አለመሆን የራሳቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው። ወደ አፈጻጸም ሲገባ ባሉት ኮንትራክተሮችና አማካሪዎች የአቅም ውስንነት የተነሳ የሚታሰበውን ጥራት ለማረጋገጥ አዳጋች ሆኗል።

- በኢትዮጵያ የግንባታ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከመሬት ልየታ ጀምሮ ሕንፃው ተገንብቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ መሟላት ያለባቸው ዓለም አቀፍ መሥፈርቶች፣ አጠቃላይ ይዘትና ቁመናው ምን መምሰል እንዳለበት የተቀመጡ ስታንዳርዶች የሉም። በዚህም በኢትዮጵያ ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ያሉ የመኖሪያ ቤቶች ሲገመገሙ፣ የመኖሪያ ቤት ለመባል የተሟላ ቁመና ያላቸው ከ25 በመቶ የማይበልጡ ናቸው። 75 በመቶ ያህሉ ከደረጃ በታች ናቸው።

- ለቤቶቹ ጥራት መጓደል ምክንያት ከመጀመሪያው የግንባታ ዕቅድ ጀምሮ ግንባታ እስከሚጠናቀቅ ድረስ፣ መሟላት ባለባቸው ዓለም አቀፍ መሥፈርቶች የተቃኙ አለመሆናቸው ነው።

- ከዚህ በኋላ በሀገሪቱ ሚገነቡ ቤቶች ለሰው መኖሪያ ለመባል የሚያስችሉ ዓለም አቀፍ መሥፈርቶችን ባሟላ መንገድ እንዲሆን፣ የሕግ ማዕቀፍና ስታንዳርድ ይዘጋጃል። በአሁኑ አሠራር ግን ማንኛውም የሥራ ተቋራጭ ውል ገብቶ ግንባታ ከጀመረ በኋላ ፣ በጥራትና በጊዜው ያጠናቅ ወይም አያጠናቅ መቆጣጠር የሚያስችል ሥርዓት የለም ብለዋል፡፡

ይህ መረጃ ከሪፖርተር ጋዜጣ የተወሰደ ነው።


https://t.me/engineer03
💥ብዙ የኮንስትራክሽን ባለሞያዎች መሰንጠቅ በMix design ትክክል አለመሆን ብቻ የሚመጣ ይመስላቸዋል ነገር ግን ለመሰንጠቅ (cracking ) ምክንያት የሚሆኑ መንስኤዎችን ከዚህ በታች እንዲህ ዳስሰናል :-

[1] - አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ
.
አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ መሰንጠቅ (cracking ) ይፈጠራል ስለዚህ የምንጠቀማቸውን ለኮንክሪት ግብዓት የሚሆኑ ቁሶችን (ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ ኮረኮንች) ጥራት መፈተሽ አለብን ኮንክሪቱ የብረት መዋቅር (reinforcement ) ያለው ከሆነ የብረቱን ጥራት መገምገም አለብን።
.
[2] - መኮማተር (Shrinkage )
.
ኮንክሪቱን በምንደባልቅበት እና ውሃ በምናጠጣበት ግዜ (Curing ) ተገቢውን ጥንቃቄ ካልወሰድን መኮማተር (shrinkage) መሰንጠቅን(cracking)   ያስከትላል ።
መኮማተር (shrinkage) ለትልቅ የኮንክሪት ጥንካሬ በጣም አስፈላጊ ነው አስፈላጊውን የውሃ-ሲሚንቶ መመዛዘን (water cement ratio) ካልተጠቀምን በመኮማተር አማካኝነት መሰንጠቅ ሊፈጠር ይችላል ።
.
[3] - ጥራት ያለው Aggregate የማንጠቀም ከሆነ
.
Aggregate የኮንክሪትን አጠቃላይ ጥንካሬ ይወስንልናል ጥራቱ ጥሩ ያልሆነ Aggregate የምንጠቀም ከሆነ ከሲሚንቶ ጋር ተፈላጊውን ጥምረት (bond) ስለማይፈጥር ግንባታችን ሊሰነጠቅ ይችላል።
.
[4] - መዋቅራችን ከአቅም በላይ የሆነ ክብደት ሲያስተናግድ
.
ግንባታው / መዋቅሩ ተገቢውን ጥንካሬ ሳያገኝ በፊት ለትልቅ ክብደት የሚጋለጥ ከሆነ መሰንጠቅ ይከሰታል። በተጨማሪም መቀሰቻዎችን እና ቅስቱን (formwork ) ያለጊዜው የሚነሳ ከሆነም ግንባታችንን ለስንጣቆ ያጋልጠዋል።
.
[5] - በትክክል ውሃ እንዲጠጣ የማይደረግ ከሆነ (improper curing )
.
ይህ በአገራችን ከሚስተዋሉ ለመሰንጠቅ ከሚዳርጉ ምክንያቶች ቀዳሚው ነው - ውሃ በትክክል አለማጠጣት።
ኮንክሪት እንደተገነባ በተገቢው ጊዜ እና መጠን ውሃ መጠጣት አለበት ።
«ወንድና ሲሚንቶ ካልጠጣ ይሰነጠቃል» አይደል ሚሉት ሰካራም ወንዶች :
.
[6] - የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) አለመመጣጠን
.
በጣም ትልቅ የሆነ የብረት መዋቅርን Mix ratioው ትንሽ በሆነ ኮንክሪት የሙሌት ስራ ስንሰራ በብረቱ እና በኮንክሪቱ መካከል ያለ የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) non linear ይሆናል ይህ ደግሞ መሰንጠቅን ያስከትላል።
.
[7] - በሳይት ላይ የሙሌት (casting ) ስራ ሲሰራ ተገቢ ጥንቃቄ ካልተደረገ እና ለስራው ተገቢ የሆነ ባለሞያ (የቀን ሰራተኛን ጨምሮ) ካልተመደበ መሰንጠቅ (cracking) በሚሰራው ኮንክሪት ላይ መፈጠሩ አይቀርም።

https://t.me/engineer03
🌟ስለ አፈር ጥቅጠቃ ስራ /Soil Compaction/ በጥቂቱ

Soil Compaction: - በሜካኒካል መንገድ የአፈርን የመሸከም አቅምን የምንጨምርበት መንገድ ነው።

እንዴት?

አፈሩን ስንጠቀጥቅ የአፈር ፓርቲክሎች  ጥግግቶሽ ወይም ትፍፍግ/density/ እንዲጨምር እናደርጋለን።ይህም በአየርና ውሃ የተያዙ ቦታዎች /water and air voids/በአፈር እንዲተኩና እየዲቀንሱ ማድረግ ማለት ነው።

💥ይህም በመሆኑ:

*የአፈሩን የመሸከም አቅም/Load bearing capacity of soil/ ከፍ እናደርጋለን።

*በውስጡ የውሃ ማንሸራሸር አቅሙን/permeability/ እንቀንሳለን።

*ስምጠት እንዳይኖር ያደርጋል/reduce future settlement/

⚡️የደረቅ አፈር ከፍተኛ እፍግታ መጠን/Maximum dry density of soil/

⚡️የደረቀ አፈር /ከድንግል መሬት/ ከፍተኛ እፍግታ መጠን/density/=1900kg/m3 ነው።

⚡️በሰው ሰራሽ ጥቅጠቃ/Artificial Compaction/ በላቦራቶሪ ሙከራ  የምናገኘው እፍግታ
/Proctor density/ ደግሞ ቢያንስ 95% እንዲመጣ ይጠበቃል።ከ95% በታች ከመጣ ወዳቂ ሆኖ የጥቅጠቃ ስራው እንደገና መሰራት ይኖርበታል።

🤞ማስታወሻ:- ደረቅ አፈር ስንል በማድረቂያ ማሽን/Oven/ ውስጥ የደረቀ ማለታችን ነው።

የአፈር እፍግታ ማወቂያ መንገዶች/methods of testing soil density/

⚡️በዋናነት በሁለት ይመደባሉ።

-በሳይት ላይ የሚተገበሩ
/Field test/: Sand cone test, Rubber balloon method, Nuclear density, Time domain reflectometry, Shelby tube/ባብዛኛው ጥቅም ላይ የማይውል/ናቸው።

-በቤተ ሙከራ የሚተገበሩ/Laboratory tests/: Proctor test, Modified proctor test... 

ለዛሬ በሳይት ላይ የአፈርን እፍግታ ስለምንፈትሽበት መንገድ እናያለን።

⚡️Field density of soil/Cone test/Sand replacement test/

ተጠቅጥቆ የተጠናቀቀውን አፈር በሳይት ላይ እፍግታውን የምንፈትሽበት መንግድ ነው።

* *የሚያስፈልጉ እቃዎች/Apparatuses/

የአሸዋ እቃ/ክብ ጀሪካን መሳይ/Sand pouring cylinder equipment/: ዲያሜትሩ 15cm ቀመቱና 45cm የሆነ ጃር

መቆፈሪያ፣ማፅጃና ማስተካከያ እቃ/Tools for levelling and excavation/

ማንኛውም ማጠራቀሚያ ሰሃን ወይም ሳጥን/Container/:

ንፁህ አሸዋ

ወንፊት

ሚዛን/Balance/

ዳታ መመዝገቢያ ቅጽ

* *የስራ ቅደም ተከተል/Procedure/

1ኛ.የአሸዋ ጃሩንና አፈር ለማውጫ የተዘጋጀውን ሰሃን ባዶውን መመዘንና መመዝገብ።

2ኛ. ጃሩን አሸዋ መሙላትና ከነአሸዋው መመዘንና በመመዝገቢያ ቅጹ ላይ መሙላት።

3ኛ. በ15cm ዲያሜትርና በ20cm ጥልቀት የተጠቀጠቀውን ሙሊት አፈር በጥንቃቄ መቆፈርና ሳይባክን እያወጡ በተዘጋጀው ሰሃን ላይ በማድረግ መመዘንና መመዝገብ።

ማስታወሻ:- የጉድጓዱን ልክ ለመወሰን በልክ የተዘጋጀ ፕሮፋይል ልንጠቀም እንችላለን።ምስል 5 ን ይመልከቱ

4ኛ. የአሸዋ ጃሩን ከታች በምስል 1 ላይ በተቀመጠው መሰረት በማድረግ ወደተቆፈረው ጉድጓድ ላይ በማድረግና መዝገያውን በመክፈት አሸዋው ጉድጓዱን እስኪሞላ ጠብቆ መዝጊያውን በመቆለፍ ጃሩን ማንሳትና ቀሪውን መመዘንና መመዝገብ።

5ኛ. አሸዋውን ደግሞ ለመጠቀም ካስፈለገ ከጉድጓዱ ጠርጎ ማውጣትና በወንፊት እየነፉ በስቀመጫው እቃ ማከማቸት።

6ኛ. የተሰበሰበው ዳታ በመጠቀም. የሳይት ላይ እፍግታውን/Bulk density/ ማወቅ እንችላለን። በቀጣይ ጽሁፍ የሚወጣውን ምሳሌ መመልከት ይቻለል።

7ኛ. ከፍተኛው የደረቅ እፍግታ ልኩን/MDD/ በቤተ ሙከራ ለመስራት ከሰሃኑ ላይ ለናሙና 1/3ኛ ያህሉን በንፁህና ደረቅ ላስቲክ በማድረግ ማዘጋጀት።

ማስታወሻ:-የተወሰደው ናሙና ባእድ ነገር እንዳገባበትና ከሌላ ናሙና ጋር ለመለየት እንዲያስችለረ በጥንቃቄ መታሸግና እላዩ ላይ መለያ ኮድ መጻፍ ይገባል።

እንደስራው ደረጃና የሳይቱ ስፋት መጠን ከላይ የተጠቀሰውን አካሄድ ቢያን ሶስትና ከዚያ በላይ በመሃንዲሱ በተመረጡ ቦታዎች ላይ መስራት ይገባል።

⚡️የአፈር ጥቅጠቃ ስራ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው?

የአፈሩ ዓይነት/soil type/

ለምሳሌ: ኮረታማ/ጠጠርማ/Gravel/Granular/ አፈር ለመጠቅጠቅ ምቹና በጣም ጥሩ ውጤት የሚያስገኝ ሲሆን፣በተቃራኒ ጥቁርና ብስባሽ ያለው አፈር ደግሞ ለመጠቅጠቅ የማይሆንና የማይች በመሆኑ ለማንኛውም ስትራክቸራል ሙሊት ስራ የማይመረጥ ነው ይሆናል ማለት ነው።ከታች በምስል 4 ላይ የተቀመጠውን ይመልከቱ።

⚡️የአፈሩ ውሃ ይዘት/soil water content/:

⚡️አፈሩ በጣም ውሃ ያዠ ወይም ከልክ በላይ የደረቀ መሆን የምንፈልገውን እፍግታ ማግኘት እንዳንችል ያደርጋል ማለት ነው።

⚡️የጥቅጠቃ ሃይል/Compaction Effort/


https://t.me/engineer03
1
💥አንድ የስራ ተቆጣጣሪ ባለሞያ የኮለን ኮንክሪት ከመሞላቱ በፊት ፎርምወርክ ስራው ላይ መሟላታቸውን ማረጋገጥ የሚገባው መሰረታዊ ነጥቦች:

[Elements of good Column formwork finish]

1.ጥብቅ መሆኑን/Formwork rigidity/
የተዘጋጀው ፎርምወርክ የራሱን ክብደት/self weight/፣የብረቱን ክብደት፣የርጥብ ኮንክሪቱን ክብደት፣ የኮንክሪት ሰራተኞች፣ የንፋስ ግፊት፣ የስራ መሳሪያዎችና ሌሎች ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጫናዎችን የሚቋቋም ሆኖ በቂ ጥንካሬ ኖሮት መሰራቱን ማረጋገጥ የመጀመሪያ ስራ ይሆናል።

2.የፎርምወርክ ጥራት/Quality of formwork material/
ለፎርምወርክ ስራ ጥቅም ላይ የዋለው እቃ ያልተጣመመ፣ ያላበጠና ያልጎበጠ ፣ወጥነት ያለው ፣ያልተቀደደና ጥሩ ጥንካሬና የመሸከም አቅም ያለው መሆኑን ማረጋገጥ ሌላ አስፈላጊ ስራ ነው።

3.አቀባዊ ሊኛ/Vertical alignment/
የተዘጋጀው ኮለን ፎርምወርክ ዲዛይኑ እንደሚጠይቀው ልክ በሚገባ ወደላይ ቀጥ ማለቱን ማረጋገጥ አለበት።

4.አግድም ሊኛ/Horizontal alignment/
የተዘጋጀው ኮለን ፎርምወርክ ዲዛይኑ እንደሚጠይቀው ከሌሎች ኮለኖች አንጻር ያለው አቀማመጥ፣ ከታወቀ መነሻ በሚገባ ወጥነት ያለው ሆኖ መቀመጡን ማረጋገጥ አለበት።

5.የኮለን ወርድና ስፋት ልክ/Design dimension/
በዲዛይኑ መሰረት የኮለኑን ወርድና ስፋት ከፎርምወርኩ አቀናንሶ ትክክል መሆኑን ማረጋገጥ።

6.ከመነሻው ያለው ርቀት/Distance from reference/center to center/
ከታወቀ መነሻ በመነሳት አንዱ ኮለን ከሌላው ኮለን ርቆ የተቀመጠው በዲዛይኑ መሰረት መሆኑን ማረጋገጥ።

7.መሃል ገጠምነት/Eccentricity/
ተንጠልጣይ ወለል/Suspended floors/ በሚኖራቸው ግንባታዎች ላይ የላይኛው ወለል ኮለን ከታችኛው ወለል ኮለን ጋር ሴንተራቸው ፍፁም መሃል ገጠም/eccentric/ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።

8.ከብረቱ ያለው ተገቢ ርቀት
/Concrete cover/
ለኮንክሪት ሽፋን ዲዛይኑ የሚጠይቀው ተገቢ መጠን፣ በፎርምወርኩና በብረቱ መሃል በልዩ ጡብ/Spacers/ መለየቱን ማረጋገጥ ሌላው በጣም አስፈላጊው ነጥብ ነው።


https://t.me/engineer03
👍1
🪐ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(Design bid build)(DBB) VS ዲዛይን ቢዩልድ(Design build)(DB)
               
1, ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(Design bid build)(DBB)

በኮንስትራክሽን ጉዳይ በአብዛኛው በሀገራችን የሚሰራበት የፕሮጀክት አይነት ዲዛይኑን አሰሪው በራሱ መንገድ እንዲዘጋጅ ካደረገ በኃላ ግንባታውን በተቋራጭ እንዲከናወን የሚያደርግበት ነው።ይሄውም ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(Design bid build)(DBB) በመባል ይታወቃል፡፡በዚህ የፕሮጀክት አይነት የታቀደውን ግንባታ ዲዛይኑን አሰሪው በራሱ አርክቴክት ወይም በሌላ ሶስተኛ ወገን/ በሌላ አርክቴክት ድርጅት/ እንዲከናወን ያደርጋል፡፡
በመቀጠልም በተዘጋጀው ዲዛይን መሰረት ግንባታውን የሚያከናውን ተቋራጭ ወደመምረጥ ሂደት ይገባል፡፡የግንባታው ባለቤት የመንግስት መስሪያ ቤት የሆነ እንደሆነ ግንባታውን የሚያከናውን ተቋራጭ የመምረጡ ስራ የሚከናወነው በግዥ ህግ መሰረት ይሆናል፡፡ይሄ አይነቱ ፕሮጀክት በሀገራችን የተለመደ ነው፡፡
              

2, ዲዛይን ቢዩልድ(Design build)(DB)

🌟በሌላ በኩል ደግሞ ተቋራጩ ዲዛይኑን እና ግንባታውን በራሱ የሚያከናውንበት የፕሮጀክት አይነትም አለ።ይሄውም ዲዛይን ቢዩልድ(Design build)(DB) ይባላል፡፡በዚህ የፕሮጀክት አይነት ተቋራጩ የታቀደውን ግንባታ ዲዛይኑን በራሱ አርክቴክት ወይም በሌላ የአርክቴክት ድርጅት አማካይነት ያከናውናል፡፡የአርክቴክት ስራው የሚያስከትለው ሀላፊነት የተቋራጩ ይሆናል፡፡ከዲዛይን ስራው ጋር የተያያዘ ችግር የሚያስከትለው ሀላፊነት አሰሪውን/የግንባታውን ባለቤት አይነካውም፡፡ሆኖም ተቋራጩ ዲዛይኑን ያሰራው በሌላ የአርክቴክት ድርጅት አማካይነት የሆነ እንደሆነ ከአርክቴክቸር ስራው ጋር በተያያዘ ተቋራጩ ለአሰሪው የሚኖርበት ሀላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ አርክቴክቱም ለተቋራጩ በፍትሀብሄር ህጉ ስለእውቀት ስራ ውል በተደነገገው አግባብ ሀላፊነት ይኖርበታል ማለት ነው፡፡
በዚህ አይነት ፕሮጀክት የግንባታው ባለቤት/አሰሪው ሙሉ በሙሉ የኮንስትራክሽን ስጋቶችን/risks/ ወደ ተቋራጩ ያስተላልፋል፡፡ይህ ማለት አሰሪው ውጤቱን ማለትም ግንባታውን በመጀመሪያ በቀረበለት ዲዛይን አግባብ በጥራት ተከናውኖለት ከመረከብና በውሉ የተቀመጠውን የግንባታ ዋጋ ከመክፈል ባለፈ ማናቸውም አይነት ሀላፊነት አይኖርበትም ማለት ነው፡፡ለአብነት ለመጥቀስ ያህል የኢትዮጽያ መንገዶች ባለስልጣን(ERA) ዲዛይን ቢዩልድ የመንገድ ፕሮጀክት ሲኖረው ተወዳዳሪ ተቋራጮች የሰርቨየይንግና ዲዛይን ስራዎችን በራሳቸው ከሰሩ በኋላ በዋጋ ይወዳደራሉ፡፡ተቋራጮቹ ዲዛይኑን ሲሰሩ አሮጌ ድልድዮች ካሉ እና ተጠግነው በአዲስ ድልድይ የጥራት ደረጃ መድረስ የሚችሉ ከሆነ ተቋራጮች እንደየፍላጐታቸውና ሙያዊ ምርመራቸው/ምክንያታቸው ተጠጋኝ ድልድይ እና በአዲስ የሚገነባ ድልድይ እያሉ በዝርዝር በዲዛይን አካተው የሚያቀርቡ ሲሆን ምንም ሆነ ምን በውጤት ደረጃ አሰሪው በሚፈልገው የጥራት ደረጃ/ስታንዳርድ መገንባቱ እና ይሄውም በአማካሪው መረጋገጡ ግን የግድ ነው፡፡ምናልባት ተጠግኖ በሚፈለገው የጥራት ደረጃ ይደርሳል የተባለው አሮጌ ድልድይ በጥገና ወቅት ቢፈርስ እንኳ አሰሪውን ክፍያ የመጨመር ሀላፊነት አያስከትልበትም፡፡ስለዚህ ዲዛይን ቢዩልድ ፕሮጀክት ለአሰሪዎች ሪስክ ፍሪ/ከስጋት ነጻ የሆነ የፕሮጀክት አይነት ነው፡፡
           
⚡️ሌላው ሁለቱም የፕሮጀክት አይነቶች ለኮንስትራክሽን ውላቸው የሚጠቀሙት ጀኔራል ኮንዲሽን የተለያየ ነው።FIDIC በዚህ ረገድ የግንባታ ውል ዝግጅትን በማቅለል ለአለማችን ትልቅ ስጦታ ነው። አለበለዚያ አሰሪና ተቋራጭ በየአንዳንዱ ውል ዝግጅት ወቅት በሁሉም የውል ሁኔታወች ላይ መደራደርን ይጠይቃቸው ነበር።ዛሬ ላይ ግን ለውሉ ጥቅም ላይ የሚውለውን ጀኔራል ኮንዲሽን አስመልክቶ FIDIC ቨርሽን መረጣ እና በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት በሚካተቱ ነጥቦች ላይ ብቻ መወያየት በቂ ነው።

በተጨማሪም በዲዛይን ቢዩልድ ፕሮጀክት የኮንስትራክሽን ስጋት/ሪስክ ሙሉ በሙሉ ወደ ተቋራጩ የሚተላለፍ በመሆኑ ልዩ የዋስትና ሽፋን ያስፈልገዋል፡፡ስለዚሁም ተቋራጩ በግንባታው ዋጋ ልክ All risk insurance እንዲገባ እና ለዲዛይን ስህተት፣ለስራው ብልሽትና በተቋራጩ ባለሙያወች የስራ ስህተት ለሚከሰት ጉዳትና ኪሳራ ደግሞ professional indemenity insurance እንዲገባ FIDIC ዲዛይን ቢዩልድ ፕሮጀክት ኮምፖቴብል የሆነው ተርንኪ ጀኔራል ኮንዲሽን ግዴታ ያስቀምጣል።

በሀገራችን ዲዛይን ቢዩልድ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ብዙም የተለመደ አይደለም።ሆኖም በመንገድ ግንባታ ውሎች የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አልፎ አልፎ ይጠቀምበታል።
⚡️በአጠቃላይ በሀገራችን በኮንሰትራክሽን ዲዛይኒንግ እና የውል አስተዳደር ረገድ ሰፊ የእውቀት ክፍተት ያለ በመሆኑ እና ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና ገንዘብ የማይጠናቀቁበት ሁኔታ በሰፊው የሚስተዋል እንደመሆኑ ሙሉ የኮንስትራክሽን ሪስክ/ስጋት ወደ ተቋራጩ በማስተላለፍ  መንግስታዊ ግንባታዎችን በዲዛይን ቢዩልድ የፕሮጀክት አይነት እንዲከናወኑ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ሊሆን እንደሚችል ለመጠቆም እወዳለሁ።
                

https://t.me/engineer03
💥የአንድን ፕሮጀችት አርክቴክቸራል ዲዛይን ንድፍ (drawings) ማረጋገጥ ያለብን ነጥቦች

🌟1ኛ. ልኬት

ማንኛውም ርክቴክቸራል ንድፍ (AR drawings) በንድፉ ላይ የተመለከቱ ማንኛውንም መስመሮች በተናጠል ልኬት (in-to-in)፣ ከማዕከል ማዕከል (center-to-center)፣ በንዑስ ክፍል (sub-section) እና ውጪ (out-to-out)፣ እና ቀጤ/አቀባዊ ሊኛ (vertical elevation) ልኬት ማስቀመጥ አለበት። 

🌟2ኛ. የግብአት ዝርዝር መረጅ (material detail)

አንድ የሕንጻ አርክቴክቸራል ንድፍ የሚጠቀማቸውን የግንባታ ግብአት አይነቶች (type)፣ ጸባይ (properties)፣ እና መዋቅር (connection) በግልጽ ማስቀመጥ አለበት።

🚧ለምሳሌ፦ የግድግድ ቀለም አይነት (paint specification)፣ የግድግዳ ልስን (number of coats of plastering)፣ የተከፋችና ብርሃን ሰጪ ክፍሎች ማለትም የበር፣ የመስኮትና የዝግ መስታወት መረጃ (openings detail)፣ የመስታወት ዝርዝር (thickness and type of glass)፣ የጣሪያ መዋቅሮች ዝርዝር ልኬት ማለትም የማገር፣ የወራጅ፣ የገንዴላ፣ የምሰሶ፣ የጣሪያ ሽፋን መረጃ፣ የኮርኒስ ግብአቶች አይነትና ልኬት (type and size of ceiling batten and covers) ... በአጠቃላይ በንድፉ ላይ በቅርጽ የተመለከቱ ክፍሎች የሚጠቀሙትን የግንባታ ግብአት ዝርዝር መረጃ አርክቴክቱ ማስቀመጥ አለበት።

🌟3ኛ. የተሟላ የሕንጻ ምልከታ ንድፎችን ማካተት

አርክቴክቱ በሕንጻው ላይ ያሉ ምልከታዎችን (views) በሙሉ ማስቀመጥ አለበት ይህም ማለት የወለል ንድፍ (Floor plans)፣ ተንጠልጣይ ወለሎች (mezzanine floors plans)፣ የፊት የኋላ የግራ የቀኝ አቀባዊ እይታዎች  (elevations)፣ አቀባዊ ቀርጥ (sections)፣ የጣሪያ ወለላዊ እይታ (roof plan)፣ የግንባታ ቦታው ሥዕል (site plan) ከነዝርዝር ልኬታቸው በሚገባ መቀምጥ አለባቸው።

🖱የአርክቴክቸራል ዲዛይን አጽዳቂ ቢሮ ደግሞ ከዚህም አለፍ ብሎ የክፍሎችን አቀማመጥና እርስ በእርስ ያላቸውን የአገልግሎት ጥምርታ functional room arrangement/፣ የክፍሎች አላስፈላጊ አቀማመጥን እስከማስተካከል ድረስ ማረጋገጥ ይችላሉ::


https://t.me/engineer03
👉ኮንስትራክሽን "Construction” ስለሚለው ቃል የኢትዮጵያ ሕጎች ይስማማሉ ወይ?

🌟የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል “ለመኖሪያም ሆነ ለሌላ አገልግሎት እንዲሆን ከድንጋይ ከሸክላ ከብረትና ከመሳሰሉት ነገሮች የሚሰራ ፎቅ ያለው ወይም የሌለው ቤት” ሕንጣ ይባላል እንጂ ኮንስትራክሽን የሚል ስያሜ አልሰጠውም (የኢ.ቋ.ጥናትና ምርምር, 1993)።

በተጓዳኝ ደግሞ BATCODA Specification በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 327/1979 አንቀጽ 2(1) ኮንስትራክሽን የሚለውን ቃል ለሁለት ክፍል ሰጥቶ የሕንጻ ኮንስትራክሽን እና የመንገድ ኮንስትራክሽን በማለት ይከፍለዋል።

▶️የሕንጻ ኮንስትራክሽን የሚለውን ሀረግ “ማንኛውም በከፊል ወይም በሙሉ የወለል የግድግዳና የጣሪያ ሥራ ያለው ለመኖሪያ ወይም ለሌላ አገልግሎት የሚውል ሕንጻና ተዛማጅ ሥራዎችን የመስራት ወይም የማሻሻል ሥራ ው” የሚል ብያኔ የሰጠ ሲሆን በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 327/1979 አንቀጽ 2(2) ሥር የትራንስፖርት ኮንስትራክሽን በሚል ዘርፍ “የሐረግ መንገዶች፣ ድልድዮች፣ የባቡር ሀዲዶች፣ የአውሮፕላን ማረፊያዎች፣ የወደቦችና የየብስ ማመላለሻ ተርሚናሎች የመሥራት ወይም የማሻሻል ሥራ” እንደሆነ ተርጉሟል።

የኢ.ፌ.ድ.ሪ መንግሥት የግንባታ ግዢና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 430/1997 አንቀጽ 2(ሐ) እና አዋጁን በሻረው አዋጅ ቁጥር 649/2001 አንቀጽ 2(3) “የግንባታ ዘርፍ” ለሚለው ትርጉም “የግንባታ ዘርፍ ሥራ ማለት ከሕንጻ፣ ከመንገድ ወይ ከመሰረተ ልማት ሥራ ጋር በተያያዘ የሚከናወን አዲስ ግንባታ፣ የመልሶ ግንባታ፣ ደረጃ የማሳደግ፣ የማፍረስ፣ የጥገና፣ የማደስ ሥራ እንዲሁም ተጓዳኝ የሆነና ከዋናው ሥራ ያልበለጠ ዋጋ ያለው አገልግሎት ሲሆን፣ የመገንባት፣ በባለቤትነት የመያዝ፣ ሥራውን የማንቀሳቀስ፣ የማስተላለፍ ወይም የመገንባት፣ የማንቀሳቀስ የማስተላለፍ ወይም የመገንባት፣ በባለቤትነት የመያዝ የማንቀሳቀስ ውል” በማለት ኮንስትራክሽን የሚለውን ቃል ምን ያክል ሰፊ እንደሆነ በሚያስገነዝብ መልኩ አስቀምጦታል።

▶️በ2006 ዓ.ም በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ ደግሞ  “ኮንስትራክሽን ማለት የመሬት ውስጥ ወይም ከመሬት በላይ ያለ ንብረትና አገልግሎትን የሚፈልግ የማሳደግ፣የማስፋፋት፣ የመዘርጋት፣ የመልሶ ግንባታ፣ የጥገና፣ የዕድሳት፣ የማበልጸግ፣ የመቀየር፣ የቁፋሮ፣ የመንቀል ወይም የማፍረስ የሕንጻ ወይም የማንኛውም ምህንድስና ሥራ ነው - Construction” means a provisions of combination of goods and services carried out under or  over ground for the development, extension, installation, repair, maintenance, renewal, renovation,  alteration, excavation, dismantling or demolition of a fixed asset including building and  engineering infrastructure.” ይላል።

🚧በ2001 ዓ.ም የወጣው የሕንጻ አዋጅ ቁጥር 324/2001 አንቀጽ 2(9) ደግሞ ግንባታ ማለት አዲስ ሕንጻ መገንባት ወይም ነባር ሕንጻ ማሻሻል ወይም አገልግሎቱን መለወጥ ነው - Construction" means the construction of a new building or the modification of an existing building or alteration of its use” በማለት አስቀምጧል።

#ConstructionLaw

https://t.me/engineer03
💥አንድ ከመሬት ወለል ውጪ ያለ ኮንክሬት ወለል ፎርምወርክ ሥራ ላይ መሐንዲሱ ቁጥጥር ማድረግ ያለበት መሰረታዊ ነጥቦች

🚧1. ልኬቱ ከንድፉ ጋር ስለመስማማቱ/Size as per drawing/

የተሰራው የወለል ፎርምወርክ የሚሸፍነው የአየር ክልል በአርክቴክቸራል እና በስትራክቸራል ዲዛይኑ ላይ ከተመለከቱት የተጓዳኝ ወልል ስፋት (Respective floor area) ጋር የተጣጣመ መሆኑ ማረጋገጥ አለብን።

🚧2. የቀጤነት እና አግዳማዊ አንግል መጠበቁን (Horizontal and Vertical angles as required)

ብዙ ሕንጻዎች ቀጥታ በአግዳማዊ ገንዴላ (beam) የታጠሩ አይደሉም።

▶️ከቢም ውጪ የሆኑ ተንጠልጣይ ባለ ሦስት ጎን፣ ወይም ግማሽ ክብ፣ ወይም ሌላ ቅርጽ ያላቸው የኮንክሬት ወለሎች አሉ እነዚህ የኮንክሬት ወለሎች የሚሰሩበት ፎርምወርክ ትክክለኛውን በዲዛይን ላይ የተመለከተ አንግል መከተላቸውን ማረጋገጥ ይገባል በተለይ የወለል ፎርምወርክ ውሃልክ መጠበቅ፣ እንዲሁም የዶም፣ ትራፒዞይድ እና ሦስት ጎን ቅርጽ ያላቸው ወለሎች ልኬት ምንም አይነት ስህተት የማይታገሱ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

🚧3. የጠበቀ ሥራ መሆኑን/rigidity/

የኮንክሬት ወለል ለመስራት የተሰራው ፎርምወርክ የተሸካሚውን ጥብቅነትና ቻይነት (scaffolding rigidity and material capability)፣ የወለል ፎርምወርክ ጥብቅነት እና የመሸከም አቅም አግባብነት (Formwork rigidity and appropriateness of materials) ማረጋገጥ አለብት።

▶️እንደሚታወቀው የኮንክሬት ወለል ሲሰራ የኮንክሬት ክንደት፣ የብረት ክብደት፣ የሰራተኛ ክብደት፣ የማሽን እና ዕቃዎች ክብደት፣ የንፋስ ጫና እና ሌሎች የሚደርሱበትን ግፊት መቋቋም መቻል ያለበት መሆኑ ማረጋገጥ ተገቢ ነው።

🚧4. ፎርምወርኩን ከብረቱ ጋር መለያ በአግባቡ መቀመጡን (Spacer)

የወለል ኮንክሬት ሙሌት ከመከናወኑ በፊት በብረት /ፌሮ/ እና በታችኛውና በጎንዮሽ የወለል ፎርምዎርክ መካከል (between reinforcement and formworks panels) በየትኛውም የወለል ነጥብ ላይ ቢያንስ 2.5ሴ.ሜ የሆነ ክፍተት (space) መኖር አለበት።

▶️ይህ የሚረጋገጠው የመለያ ግብአቶች (spacers) በአግባቡ እና በተመጣጣኝ ርቀት (appropriately and in reasonable distance) ላይ ከተቀመጡ ብቻ ነው።

🚧5. ፎርምወር ግብአት ትክክለኛነት (Formwork panels compatibility)

ለፎርምወርክ ግብአትነት የምንጠቀመው ግብአት  አንድ ከሌላው የተጣጣመ፣ የተስማማ መሆን አለበት። በተናጠል ደግሞ የፎርምወርክ ፓኔሎቹ ያልተመሙ፣ አባጣ ጎባጣ ያልሆኑ፣ በዲዛይኑ የተቀመጣ ካልሆነ በቀር አንዱ ከሌላው የከፍታ ልዩነት የሌላቸው መሆን አለባቸው።

🚧6. የወለል መለያ (expansion joint)

በኮንክሪት ወለል መካከል እንደአስፈላጊነቱ ስንጥቆችን ለመከላከል የመለያ መገጣጠሚያዎች አስፈላጊ ናቸው።

▶️ኮንክሪት ከተፈሰሰ በኋላ በስንጥቅ ለመጋለጥ በጣም የተጋለጠ የሚሆንበት ጊዜ ይኖራል በዚያን ሰዓት እንደየአካባቢው ሙቀት መጠን የሚስፋፋውን የመለያ መገጣጠሚያዎች የተቀመጡ ከሆነ የእነርሱን መገኛ ቦታ፣ መጠን እና ትክክለኛነት መለካት ግድ ነው።

🚧7. የዘይት ቅብእ ሥራ (Oiling of shuttering)

የወለል ፎርምወርክ ኮንክሬቱ በሚያገኘው የውስጠኛው ክፍል በሙሉ በተለምዶ ኦሊዮ (Olio) የምንለውን ወይም ኮንክሬቱ ከፎርምወርኩ ጋር የሚፈጠረው ጠንካራ ትስስር እንዳይኖር የሚያደርግ (preventing bonding contact of concrete with formwork surface) ዘይት መቀባቱን ማረጋገጥ አለበን።

https://t.me/engineer03
👍1
💥ካዳስተር ማለት ምን ማለት ነው?

🌟ካዳስተር ማለት መሬት ይዞታን መሰረት ያደረገ የመሬት መረጃ ሥርዓት ሲሆን የሚደራጁት መረጃዎችም በዋናነት ሁለት ዓይነት ናቸው፡፡ ይኸውም የካርታ መረጃ (spatial data) የይዞታውን መገኛ ቦታ፣ ወሰኑን፣ ስፋቱንና ቅርፁን፣ አጎራባች ይዞታዎችን እና አዋሳኝ መንገዶችን የሚያሳይ ሲሆን ሌላኛው ገላጭ መረጃ (non-spatial data) በመባል የሚታወቀው የባለይዞታውን ማንነት (ስም፣ አድራሻ፣ ጾታ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ ወዘተ.)፣ በይዞታው ላይ ያለው መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት፣ የቦታው አገልግሎትና ደረጃ፣ ወዘተ… እንደ ካዳስተር ዓይነቱ ተዘርዝረው የሚያዙ መረጃዎችን ያካትታል፡፡

እነዚህ ሁለት የመረጃ ዓይነቶችም በልዩ የይዞታ መለያ ኮድ እንዲገናኙ ይደረጋል፡፡

▶️ካዳስተር በሦስት ዓይነት ይከፈላል፡-

🚧አንደኛው ህጋዊ ካዳስተር ሲሆን ለእያንዳንዱ ህጋዊ ወሰን ለተለየለት ይዞታ፣ የይዞታ መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት የሚያመለክት መረጃ ከይዞታው ካርታ ጋር አጣምሮ የያዘ ወቅታዊ የመሬት ይዞታ መረጃ ሥርዓት ሲሆን አስፈላጊነቱም ዬትኛው ይዞታ በማንና በምን አግባብ ተይዟል የሚለውን በማጣራት የባለይዞታውን የይዞታ ዋስትና ለማረጋገጥ ነው፡፡

🚧ሁለተኛው ዓይነት ፊስካል ካዳስተር ሲሆን በይዞታው ላይ ስላረፈው ቋሚ ንብረት ዝርዝር መረጃ እና የመሬቱን ወቅታዊ ግምት ከይዞታው ካርታ ጋር የሚይዝ ሆኖ ለቦታና ለንብረት ግብር ክፍያ የሚያገለግል ሥርዓት ነው፡፡

🚧ሦስተኛው ዓይነት ካዳስተር ሁለገብ/ሁሉን አቀፍ ካዳስተር/ የሚባለው በሁለቱ የካዳስተር ዓይነቶች የተገለፁትን መረጃዎች የሚይዝ ሆኖ በተጨማሪም የመሰረተ ልማት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና ሌሎች መረጃዎችን እና ካርታን አካቶ የሚይዝ የመረጃ ሥርዓት ነው፡፡

የካዳስተር ሥርዓት በመገንባት ሂደት በርካታ ልምድ ያላቸውና ብዙ ርቀት የሄዱ አገሮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በዚህ የግንባታ ሂደት እያንዳንዱ አገር ከራሱ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር አጀማመሩና አካሄዱ የተለያየ ነው፡፡

አንዳንድ ሀገሮች ከፊስካል ካዳስተር ጀምረው ወደ ሁለገብ የሄዱ አሉ ለምሳሌ ፈረንሳይ፤ ሌሎች ደግሞ ከህጋዊ ካዳስተር ጀምረው ወደ ሁለገብ የካዳስተር ሥርዓት የተሸጋገሩበት ሁኔታም አለ ለምሳሌ ኔዘርላንድ፡፡ በእኛ አገር ደረጃም ከዚህ ቀደም በከተማ ደረጃ ሥርዓቱን ለመዘርጋት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ የተሞከሩትም ሁለገብ ካዳስተርን በመዘርጋት ነበር ሆኖም ግን የሚፈለገውን ውጤት ሊያመጣና የሥርዓቱን ዘለቄታዊነት የሚያረጋግጥ ሊሆን አልቻለም፡፡

በመሆኑም በቅድሚያ ባለይዞታውን ተጠቃሚ የሚያደርገው ከተማ አስተዳደሮችም መሬታቸውን ቆጥረው ሊያውቁ የሚችሉበትን የህጋዊ ካዳስተር በመዘርጋት በመቀጠልም የፊስካል ካዳስተር ብሎም ወደ ሁለገብ ካዳስተር የሚያድግ ሥርዓት መዘርጋቱ ሥርዓቱን ቀጣይ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ ተመርጧል፡፡ በዚህ ሂደት የካርታው መረጃ አንድ ጊዜ የሚዘጋጅ ሲሆን ለውጥን ተከትሎ ወቅታዊ ማድረግ የሚያስፈልግ ሆኖ ሁሉም የካዳስተር ዓይነት መሰረት የሚያደርገው በህጋዊ ካዳስተር የተዘጋጀውን የካዳስተር ካርታ ነው:: ሌሎች መረጃዎች ተደማሪ እየተደረጉ ወደ ሁለገብ ካዳስተር ሥርዓት የሚያድግ ይሆናል፡፡


https://t.me/engineer03
💥ዲዛይን ስታረጉ ማስታወስ ያለባችሁ ህግ

1. መስኮት ስታበጁ ከ አጎራባች 2 ሜትር ገባ
  በሉ
2. ለ ሽንትቤት ከ 60 ሳንቲም በታች የሆነ መስኮት ስታበጁ 1.5 ሜትር ገባ በሉ

Here is some tips you need to remember designing in Addis Ababa

1. To provide a window you need to
   offset 2 meter from your boundary line
2. To provide bathroom window <60 cm you need to offset 1.5 meters


https://t.me/engineer03
💥ግጭቶችን የመፍታት ሂደት ላይ የፍርድ ቤት ውሳኔ ተግባቦት (Arbitration)

🌟በኮንስትራክሽን ውሎች አፈጻጸም ላይ የሚከሰቱ ያለመግባባቶች ሊፈቱ ከሚችልባቸው ዘዴዎች አንዱ የሆነው የግልግል ሥርዐትም (Arbitration) አከራካሪነቱ የሰፋ ነው።

የፍትሐ ብሔር ስነስርዓት ሕጋችንና ሌሎች የግልግል ስርዓትን የሚገዙ ህጎቻችን የማይጣጣሙባቸው አጋጣሚዎች ያሉ መሆኑ ይታወቃል።

የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 315(2) (4) ሲታዩ የአስተዳደር ውሎች በግልግል የማይታዩ መሆናቸውን ሲያስገነዝቡ የፍትሐ ብሔር ህጉና ሌሎች በሥራ ላይ ያሉት የመንግሥት ተቋማት ማቋቋሚያ ደንቦች ግን በዚህ ረገድ ግልጽ ክልከላ አላደረጉም።

▶️እንዲሁም የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁጥር በሰ/መ/ቁ 16896 በቀን 16/02/1998 ዓ.ም (ቅጽ 2 ገጽ 75-78 ይመለከታል)።

የአስተዳደር ውሎችን በግልግል ለመጨረስ ስምምነት ማድረግ የሚቻል መሆኑን የሚአይስገነዝብ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶ የነበረ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ደግሞ የቀደመውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም በግልጽ ሳይሻር የአስተዳደር ውሎች የግልግል ሊታዩ የማይችሉ መሆኑን የሚያሳይ ትርጉም በሰ/መ/ቁጥር 127459 መስከረም 23/2010 ዓ.ም በዋለው ችሎት ሰጥቷል።

▶️የዚህ ውሳኔ ይዘቱ ሲታይም የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቂ 315 (2) የአስተዳደር ውልን አስመልክቶ የሚነሳ አለመግባባትን ለመዳኘት የማይችለው የግልግል ዳኝነት አካል ወይም (Arbitrator) ነው የሚል ነው።

ይህ ችሎት በአዋጅ ቁጥር 454/97 የታሰበውን የውሳኔዎች ተገማችነት ዓላማ የሚቃረን ውሳኔ መስጠቱን ከማሳየቱም በላይ በኮንስትራክሽን ውሎች የሚፈጠሩ አለመግባባቶች የሚፈቱባቸውን መንገዶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳርፍ እና ዓለም አቀፍ ነባራዊ ሁኔታ ጋርም አብሮ የማይሄድ ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ጉዳይ ነው (አልማው ወሌ, 2019)

#ConstructionLaw

https://t.me/engineer03