Civil Engineering
1.36K subscribers
1.24K photos
21 videos
960 files
661 links
*ለሲቪል ; ለአርክቴክቶች÷ለኮንስትራክሽን ÷ ለሀይድሮሊክ መሀንዲሶች እና ተማሪዎች የተዘጋጀ ትምህርታዊ ቻናል ፡፡

@engineer03


http://www.Indiabix.com በዚህ ደግሞ ማንኛውንም ጥያቄና መልስ ታገኛላችሁ!

╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕
Download Telegram
oh My God Whats this work Plumber name pls🫣
💥ስለ ኮንክሪት እና የኮንክሪት ግሬዶች
.
ኮንክሪት (concrete) ስሙን ያገኘው ከጥንት ሮማኖች ሲሆን
ቃሉም የመጣው ኮንክሪተስ (Concretus) ከሚለው የሮማኖች ቃል ነው የቃል በቃል ትርጉሙ ተያይዞ ማደግ / አንድ ላይ ማደግ የሚለውን ይወክላል።
.
*ኮንክሪት በአለም ላይ በብዛት የምንጠቀመው የግንባታ ቁስ ነው።
ኮንክሪት የሲሚንቶ የአሸዋ እና የጠጠሮች ውህድ ነው ።
የኮንክሪት የእመቃ ጥንካሬ (compressive strength)
ሚለካው በግሬዱ ነው (Grade)። የተለያዩ የኮንክሪት ግሬዶች
አሉ C-5 ፣ C-15 C-25 C-30 ወዘተ የኮንክሪት ግሬድ ማለት
ኮንክሪቱ ከሃያ ስምንት ቀን በኋላ የሚኖረው የእመቃ ጥንካሬ
(compressive strength ) ማለት ነው ለምሳላ C-25 የሆነ
ኮንክሪት ግሬድ ከ28 ቀን በኋላ የሚኖረው የእመቃ ጥንካሬ
25N/mm^2 ይሆናል ማለት ነው የC-30 ግሬድ ደግሞ
ጥንካሬው 30N/mm^2 ነው
.
*ለውሃ ስራዎች ብዙን ግዜ ተመራጩ የኮንክሪት ግሬድ ከ C-30 በላይ ነው
.
*አንዳንድ ግዜ የኮንክሪት ግሬዶች በተለያዩ መፅሃፎች በተለያየ
መልክ ይጠቀሳሉ ለምሳሌ አንዳንድ መፅሃፎች C-30 C-15
የሚለውን አጠቃቀስ ሲጠቀሙ አንዳንዶቹ ደግሞ M-30 M-15
የሚለውን ይጠቀማሉ (ከታች በምስሉ እንደተጠቀሰው) ....በ
«C»የሚጠቀሱ የኮንክሪት ግሬዶች በC መጠቀሳቸው የእመቃ ጥንካሬያቸው የተለካው በሲሊንደሪካል ፍተሻ (CYLINDRICAL test ) ስለሆነ ነው በM የሚጠቀሱት ደግሞ ፍተሻው (test) የተደረገው በኪውቢክ ፍተሻ (cubic test) ስለሆነ ነው። በሁለቱ የፍተሻ አይነቶች የሚደረጉ የኮንክሪት ግሬዶች የእመቃ ጥንካሬአቸው ይለያያል። ሲሊንደሪካል ፍተሻ በአንፃራዊነት የኮንክሪትን ትክክለኛ እምቅ ጥንካሬ ይገልፃል ስለዚህ ከኪውቢክ ፍተሻው የተሻለ ነው ማለት ነው።

https://t.me/engineer03
💥መሰረት /Foundation/

1) ቁፋሮ እና አፈር ሙሌት

መሰረት ሁልጊዜ የተረጋጋ መሬት ላይ ሊቀመጥ ይገባል።
ጥሩ አፈር ካልሆነ በተመረጠ እና ከሌላ ቦታ በመጣ አፈር በሚገባ
ተጠቅጥቆ እና ተደልድሎ ሊቀመጥ ይገባል።

የተመረጠው አፈር ንብርብር/layer/ በየ 25 ሴ᎐ሜ በሚገባ
ሊጠቀጠቅ ወይም ሊደለደል/compact/ ሊደረግ ይገባል።

በሚደለደልበት ወቅት በተወሰነ ረገድ እያንዳንዱን ንብርብር ለተሻለ ጥቅጠቃ እንዲያመች እርጥበት እነዲያገኝ ውሀ ማርከፍከፍ ያስፈልጋል

2) አርማታ ሙሌት እና የብረት ስራ

ቀጭን አርማታ/lean Concrete/ ከተመረጠው አፈር ሙሌት በላይ ሊደረግ ይገባል እንደ አስፈላጊነቱም እርጥበተ መከላከያ/water proof/ ሊደረግ ይችላል።

አርማታ ሙሌት ለመሰረት፣ ቢም፣ ኮለን እና ወለል ስራ የአርማታ ጥንካሬ በትንሹ C25 ሊኖረው ይገባል በተጨማሪ እንደ ስትራክቸራል ዲዛይኑ ሊለያይ ይችላል።

የቢም ብረት የላይኛው ብረት መሀል ላይ የታችኛው ደግሞ ኮለን ድጋፍ/support/ ላይ ሊሆን ይገባል እንዲሁም ማት ፋውንዴሽን ላይ የዚህ ተቃራኒ ይሆናል።

ብረት 4D የብረቱን ውፍረት በአራት በማባዛት የሚሰጠንን ርዝመት በመደረብ መተላለፍ ይተበቅበታል።

ዲዛይን ላይ በተቆራረጠ መስመር
/hidden line የሚቀመጡ ብረቶች ሁልጊዜ የታች ብረት ሆነው ይቀመጣሉ።

የአርማታ ሽፋን/concrete cover/አብዛኛውን ግዜ 5ሴ᎐ሜ ይሆናል ከመሬት በላይ ግን በ 2᎐5ሴ.ሜ ይሰራል።

በአርማታ ወይም በብረት የሚሰራ ክፍተት መስጫ spacer/ ልንጠቀም ይገባል።

#Foundation

https://t.me/engineer03