Civil Engineering
1.37K subscribers
1.26K photos
20 videos
962 files
673 links
*ለሲቪል ; ለአርክቴክቶች÷ለኮንስትራክሽን ÷ ለሀይድሮሊክ መሀንዲሶች እና ተማሪዎች የተዘጋጀ ትምህርታዊ ቻናል ፡፡

@engineer03


http://www.Indiabix.com በዚህ ደግሞ ማንኛውንም ጥያቄና መልስ ታገኛላችሁ!

╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕
Download Telegram
👉 የትኛው ኢኮኖሚካል ነው ?? => Flat Plate, Waffle, Flat
with Drop or Solid Slab


🚩ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
https://telegram.me/engineer03
👆👆👆👆👆

.
.
በጠቅላላው በፍሎር ደረጃ ኢሄኛው የተሻለ ኢኮኖሚካል ነው
አይደለም ለማለት Quantity ካልሰራን ለማወቅ አስቸጋሪ ነው ….
በፓኔል ደረጃ ( ስለአንድ እስላብ ብቻ ) ካወራን ግን EBCS
ሪኮመንድ የሚያረጋቸው የስላብ አይነቶች አሉ ፡፡ ሪኮመንዴሽኑ
100 ፐርሰንት ትክክል ነው ማለት አይደለም - ኢኮኖሚካል ነው
ለማለት ጂኦሜትሪንና የፌሮ ብዛትን ግምት ውስጥ ማስገባት
አለብን - ስለዚህ አሁንም 100 ፐርሰንት እርግጠኛ የምንሆነው
ኳንቲቲ በመስራት ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ኮዱ ባደረገው ጥናት
መሰረት ከኮለን እስከ ኮለን ያለውን ርቀት መሰረት አድርጎ
ኢኮኖሚካል ነው ያለውን የስላብ አይነት አስቀምጡዋል፡፡
እነዚህም፡
.
.
1. Flat Plate - ሎዱ ቀላል ከሆነና ከኮለን ሴንተር እስከ ኮለን
ሴንተር ከ4.5 እስከ 6ሜ ለሆነ ስላብ ኢኮኖሚካል ነው
.
2. Flat Slab With Drop - ከባድ ሎድ ካለና ከሴንተር -
ሴንተር ከ6 እስከ 9ሜ. ለሆነ እስላብ ኢኮኖሚካል ነው፡፡
.
3. Waffle Slab - ለትልቅ እስፓን ከ7.5 – 12ሜ………
ለትልቅ እስፓን ከmoment ይልቅ vertical load ገቨርን
ስለሚያደርግ መሃል ስፓን ላይ ያለውን የስላብ ውፍረት መቀነስ
እንችላለን - ዋፍል ስላብ በመጠቀም ማለት ነው፡፡
.
4. Ribbed Slab -ትልቅ ስፓን ላላቸውና ከቀላል እስከ
መካከለኛ የሆነ ተንቀሳቃሽ ሎድ ላላቸው ፓኔሎች ኢኮኖሚካል
ነው፡፡
.
5. Solid Slab - የስፓኑ ርዝመት በጨመረ ቁጥር ኢኮኖሚካል
አይደለም፡፡ ፍላት ስላቦች ናቸው ኢኮኖሚካል የሚሆኑት
ምክንያቱም የፍላት ስላብ ብረት አቀማመጥ በ Strip ስለሆነ
የፌሮ ብዛት ይቀንሳል::

✅ሌሎችንም መረጃዎች እንዲደርስዎት ለሌሎች ሼር ያድርጉ
👇👇👇👇👇👇
https://telegram.me/engineer03
➡Center of gravity Vs Centroid @engineer03
Center of Gravity = አንድ አካል በብዙ ጥቃቅን አካላት
የተመሰረተና የእነዚህ አካላት ስብስብ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እናም
እነዚህ አካላት የየራሳቸው weight ወይም ክብደት አላቸው -
weighታቸውንም በአንድ weight መወከል እንችላለን ይህም
Resultant ይባላል፡፡ ይህ Resultant act የሚያደርግበት ቦታ
Center of Gravity ይባላል፡፡
.
Center of Mass = ከCenter of Gravity ጋር የሚለያየው በ
‘Weight’ ቦታ ‘Mass’ ስናስገባበት Center Of Mass
እናገኛለን (W = mg)
.
Centroid = የአንድ አካል ቅርፅ ላይ ( length , width &
height ) ላይ የሚመሰረት የአካሉ መሃከለኛ ቦታ ነው፡፡ እንዲሁ
በተለምዶ የአንድ አካል መሃል ነው የምንለው ነጥብ Centroid
ነው፡፡ ለምሳሌ የአራት መአዘን መሀል አሳይ ስትባል የምታሳየው
ቦታ
.
Centroid of a Volume = centroid of ቁመት - ርዝመትና
ወርድ ያለው አካል ወይም 3D object
Centroid of an Area = 2D ወይም ስፋትና ርዝመት ብቻ
ያለው አካል centroid
Centroid of a Line = ርዝመት ብቻ ያለው አካል centroid
ለምሳሌ ገመድ
.
Centroid ና Center of Gravity አንድ ነጥብ ላይ የሚሆኑት
አካሉ ሙሉ ለሙሉ አንድ ወጥ ከሆነ material ከተሰራ ነው -
density ከተለያየ ሁለቱ ነጥቦች የሚያርፉበት ቦታም ይለያያል፡፡

✅ሌሎችንም መረጃዎች እንዲደርስዎት ለሌሎች ሼር ያድርጉ
👇👇👇👇👇👇
https://telegram.me/engineer03
👉Load Combination
.
Load Combination - አንድ ፎቅ ላይ የሚመጡ ሎዶችን Analyze ስናደርግ ሁሉም ሎዶች (LL,DL,EQ,WL, etc)
በተመሳሳይ ሰዓት ይከሰታሉ ተብሎ አይታሰብም እንደዛ ቢሆን ኖሮ ለትንንሽ ፎቆች ትልልቅ size ያላቸው Beam, Column እና
Slab ባስፈለገንና Uneconomical በሆንን ነበር፡፡ እንትን ሎድና እንትን ሎድ አንድ ላይ ሲከሰት ወዘተ እያልን Load
Combination እናወጣለን፡፡ ሎዶቹንም በ Factor እናባዛቸዋለን:: Factor ያስፈለገበትም ምክንያት Load
occurrence probability እና በተለያዩ ምክንያቶች የሚፈጠሩ
Load Uncertainties ለማስወገድ ነው፡፡
.
ስንት Load Combination አለ??
.
.
ብዙ ምሁራን በ Load Combination ብዛት ሲወዛገቡ ይታያል፡፡
አንዳንዶች 2 ነው ይላሉ ፤ ሌሎች 7 ነው ይላሉ ፤ ሌሎሎሎች 5
፤ ሌሎሎሎሎሎች 11……..ለማንኛውም ሰባትና ዘጠኝ ናቸው!!!
.
.
ሰባት የሚሆነው Earth Quake እና Wind Loadን እኛ
ካልኩሌት አድርገን ከሁለቱ Govern የሚያደርገውን ከለየን በኋላ
Governing ሎዱን በቁጥር ለሴፍትዌሩ (SAP/Etabs)
ስንሰጠው ሰባት ነው፡፡
.
.
ዘጠኝ የሚሆነው የ Earth Quake ወይም Wind ሎዱን የተለያዩ ፋክተሮች ለሶፍትዌሩ እንሰጠውና እራሱ ሶፍትዌሩ ሎዱን ካልኩሌት አድርጎ አንዲጠቀም ከፈለግን ዘጠኝ Combo እንጠቀማለን፡፡

@engineer03

✅ሌሎችንም መረጃዎች እንዲደርስዎት ለሌሎች ሼር ያድርጉ
👇👇👇👇👇👇
https://telegram.me/engineer03
👉በሚያመነጩት ሃይል የአለም 10 ታላላቅ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቦች: @engineer03

1.Three Gorges(China)
⚡22500MW

2.Itaipu(Paraguay & Brazil
⚡14000MW

3.Guru(Venezuela)
⚡10,200MW

4.Tucurui(Brazil)
⚡8,370MW

5.Grand Coulee(USA)
⚡6809MW

6.Sayano-Shushenskaya (Russia)
⚡6400MW

7.Longtan(China)
⚡6300MW

8.Krasnoyarsk (Russia)
⚡5988MW

9.Robert-Bourassa(Canada)
⚡5616MW

10.Churchill Falls(Canada)
⚡5428MW

========================
@engineer03
@engineer03
===============
https://telegram.me/engineer03
👉ስለ ክርስቲ
.
- ቢሙ ካስት ሲደረግ በዋነኝነት የቢሙን ሎድ የሚሸከም በአራት አጠናዎች የተዋቀረ ነው፡፡
‹ ዋ › ፊደልን ይመስላል፡፡
.
ቢም ካስት ከማድረጋችን በፊት የምንከተላቸውን እስቴፖች
ቀጥለን እንመለከታለን፡፡
.
1. በመጀመሪያ ጎማ ውሃ ልክ አዙረን ቢሙ የሚያርፍበትን ቦታ
already ካስት የተደረጉ ኮለኖች ላይ ምልክት እናደርጋለን፡፡
.
2. በኮለኖች መሃል ምልክት የተደረገባቸውን ቦታዎች በሲባጎ
እናገናኛለን - ሲባጎው የሚያርፍበት ቦታ የቢሙ ስር ወይም ቂጥ ነው
.
3. በሁለት ኮለኖች መሃል - ኮለኖቹ ጥግ ላይ ሁለት ክርስቲ
አቁመን ወገባቸውን እናሲዛለን
.
4. በሁለት ኮለኖች መሃል የሚያስፈልገውን ያህል ክርስቲ
እንደረድርና በዳርኞቹ ክርስቲዎች ውስጥ ሁለት ማገሮች እናስገባለን፡፡ በመቀጠልም መሃል ላይ ያሉትን ወይም ወገባቸውን
ያልያዙትን ክርስቲዎች ከማገሩ ውጪ በማድረግ ወገባቸውን
በሚስማር እናሲዛለን
.
5. ክርስቲዎቹ አናት ላይ በሁለቱም በኩል ማገር እንመታለን
.
6. ሌላ ትይዩ ቢም ካለ ከእስቴፕ 1-5 ያለውን እንሰራለትና
ከዚኛው የክርስቲ ግሩፖች ጋር በማገር እናያይዛቸዋለን
.
7. በተወሰነ ርቀት ላይ ስላቡ የሚያርፍበትን ቋሚዎች እናቆማለን
.
8. ለውሃ ልክ የዘረጋነው ሲባጎና የክርስቲው አናት ልክ ከመጣልን
እንደዛው እንተወዋለን - ልክ ካልመጣ ግን ‹ ኩኞ › በክርስቲውና
በሲባጎው (ፎንዶው ስር) መሃል እናስገባለን
.
9. ፎንዶውን የቢሙን alignment ጠብቀን እናስቀምጣለን
.
10. ስፖንዳ እንመታለን - እስፖንዳውን በአጠና እንደግፈዋለን
.
11. የቢሙን reinforcement አስገብተን ቢሙን ካስት
እናደርጋለን
.
--ኩኞ -ቁርጥራጭ አጠና
-ፎንዶ - ቀጥታ ከቢሙ ስር የሚያርፍ ተሸካሚ ፎርም ዎርክ
-እስፖንዳ - ቢሙን ከጎን የሚይዝልን ፎርም ዎርክ
.
Join for more updates via the link below;👇👇👇
https://telegram.me/engineer03
👉What is Liquidated damage? @engineer03
.
➡ስራ ተቌራጩ ለወሰደው ውል በግዜ ላለመጨረሱ ለባለቤት
ወይም ለውል ሰጪው አካል የሚከፍለው የካሳ ክፍያ ሲሆን∷
የጠቅላላ ኮንስትራክሽን ውል ይህ ሳይሆን ሲቀር ከዚህ በታች
በተጠቀሰው ቅጣት መሰረት ስራ ተቌራጩ መቅጣት እነደሚቻል
ይጠቅሳል።
1. ቅጣቱ 0.1 ፐርሰንት ወይም የጠቅላላ ፕሮጀክቱን አንድ አንድ
ሺኛ (1/1000) ላልፈፀመው ስራ ቀናት በየቀኑ ሊቀጣ ይገባል።
2. ነገር ግን ስራ ተቌራጩ በጠቅላላው ሊቀጣ የሚችለው
የፕሮጀክቱን አስር 10% (አስር ፐርሰንት). ሊበልጥ አይገባም።

⏩"Liquidated damages" means the compensation
stated in the contract as being payable by Contractor to the Public Body for failure to perform
the contract or part thereof within the periods under
the contract, or as payable by Contractor to the Public Body for any specific breach identified in the contract;
(a) A penalty of 0.1% or 1/1000 of the value of
undelivered Service for each day of delay until
actual delivery or performance,
(b) The cumulative penalty to be paid by the Contractor shall not exceed 10% of the contract price.
.
🚩ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
https://telegram.me/engineer03
👆👆👆👆👆
👉አሁን ደሞ Unit Weight Of Building Materials እንይ
.
*Water- 1000 Kg/ m3
*Bricks (broken) - 1420 Kg/ m3
*Bricks(common) -1600 Kg/ m3
*Cement(ordinary)- 1440 Kg/ m3
*Cement (rapid hardening)- 1250 Kg/ m3
*Cement Mortar - 2000 Kg/ m3
*Cement Concrete (Plain) - 2400 Kg/ m3
*Cement Concrete (Reinforced) -2500 Kg/ m3
*Glass - 2500 Kg/ m3
*Lime Concrete - 1900 Kg/ m3
*Cement Plaster - 2000 Kg/ m3
*Lime Plaster - 1700 Kg/ m3
*Stones (Ballast) - 1720 Kg/ m3
*Stones (Aggregates)- 1750 Kg/ m3
*Stones (Basalt)- 2850 Kg/ m3
*Stones (Granite) - 2450 Kg/ m3
*Stones (Marble)- 2650 Kg/ m3
*Timber (Oak, Sal) - 510 Kg/ m3
*Timber (Mango) - 650 Kg/ m3
*Timber (Teak)- 625 Kg/ m3
*Coal- 600 Kg/ m3 *Plastics- 1250 Kg/ m3
*Oils- 800 Kg/ m3
*Ashes- 650 Kg/ m3
*Clinker- 750 Kg/ m3
*Rubber- 1300 Kg/ m3
*Slag- 1500 Kg/ m3
*Clay Soil- 1900 Kg/ m3
*Sand (dry) - 1540 to 1600 Kg/ m3
*Sand (wet)- 1760 to 2000 Kg/ m3
*Steel- 7850 Kg/ m3
*Chalk- 2100 Kg/ m3
*Bitumen- 1040 Kg/ m3
.
👇👇👇👇👇
🚩ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
https://telegram.me/engineer03
👆👆👆👆👆
➡Hydraulics and water supply
.
👉ለዛሬ ደሞ የ ላየኛው የምድር ውሃ (surface water) ለማጣራት የምንጠቀማቸው ዘዴዎች ኣዘጋጅተናል 👇
.
⓵ስክሪኒንግ (screening) - ይህ የመጀመረርያው የማጣራት
ደረጃ ሲሆን በዚህ የማጣራት ዘዴ ውስጥ በውሃው ላይ የሚንሳፈፉ ግዙፍ አካላትን ለምሳሌ የዛፍ ጉቶ ፣ግንድ፣ ቅጠል እና ልዩ ልዩ የፕላስቲክ ተንሳፋፊ ቁሳቁሶች ወደ ዋናው የማጣሪያ ገንዳ እና ስርዓት
እንዳይገቡ ያግዳል ።
.
⓶ማርጋት (Coagulation )፦ በዚህ የማጣራት ደረጃ ላይ
ለአይን እይታ ያነሱ ጥቃቅን
አካላትን (Particle size 10^-7cm የሚሆኑ) በማርጋት እና
የኬሚካል ቻርጃቸውን ኒውትራላይዝ የሚያረግ ኬሚካል በመጨመር እርስ በእርሳቸው
እንዲሳሳቡ ማድረግ ነው ።
ለዚህ የአልሙኒየም ፖሊመሮች (Alum) እና አይረን (Fe+3)
አገልግሎት ላይ ይውላሉ።
እንደ የቁልቋል ተክል ያሉ የተፈጥሮ አርጊዎች (coagulants) መጠቀምም ይቻላል
.
⓷ጉግለት (Flocculation)፦ ይህ እርከን ፤ ማርጋት
(coagulation ) ወቅት የረጉ ጥቃቅን አካላትን እርስ በእርሳቸው ቦንድ እስኪፈጥሩ እና እርስ በእርሳቸው ተጣብቀው እስኪጓግሉ ውሃው በተለያየ ፍጥነት የሚማሰልበት ነው።
ይህ ዘዴ ሜካኒካል ወይም ማኑዋል በሆነ መልኩ ይተገበራል።
.
⓸መዝቀጥ/ማዝቀጥ (sedimentation) ፦ በፍሎኩሌሽን ወቅት የጓጎለው ጥቃቅን አካላት በዚህን የማጣራት ደረጃ እንዲዘቅጡ ይደረጋል ። ይህ ዘዴ የሚተገበረው የሚጣራው የውሃን ፍጥነት በመቀነስ ግራቪቲን ተጠቅሞ እንዲዘቅጥ ማድረግ ነው።
በግራቪቲ ለማዝቀጥ የሚከብዱ እጅግ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን በፍሎኩሌሽን ወቅት ስንጠቀማቸው የነበሩ ኬሚካሎችን በመጠቀም እንዲዘቅጡ ይደረጋል።
.
⓹ ማጥራት (filtration ) ፦ በዚህ የማጥራት ደረጃ ከማዝቀጥ
ደረጃ ያለፉ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን እጅግ ጥቃቅን ቀዳዳዎች ባሉት አካል (medium ) እንዲያልፍ በማድረግ የድፍረስነቱን መጠን እጅግ መቀነስ ነው።
.
⓺ማከም (Disinfection) ፦ ከላይ በተጠቀሱ የማጣሪያ ሂደቶች የተጣራው ውሃ
(በዋነኛነት ከተለያዩ ህይወት ከሌላቸው ጥቃቅን ቆሻሻዎች)
ለህብረተሰቡ ለአገልግሎት
ከመድረሱ በፊት በዚህ ሂደት (ዲስኢንፌክሽን) ማለፍ አለበት ።
ምክንያቱም ውሃው ለአገልግሎት የሚቀርበው ከተለያዩ በአይን ከማይታዩ በሽታ አምጪ ተህዋስያን ነፃ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው ። ዲስኢንፌክሽን ውሃውን በማፍላት ፣ ሚካኒካል
በሆነ መልኩ ፣ ለጨረር በማጋለጥ (radiation ) እንደሁም በኬሚካል ሊከናወን ይችላል።
በሃገራችን በዋነኛነት
ሃሎጅኖችን (ብሮሚን ክሎሪን እና አይኦዲን ) በመጠቀም
ኬሚካል በመጠቀም ውሃን እናክማለን ።
፟
➡ከዚህ ሁሉ የማጣራት ሂደት በኋላ የተጣራው ውሃ ይጠራቀምና
ለተጠቃሚዎች ይዳረሳል።
.
▶ስለ surface waterን የማጣራት ሂደቶች ጥቂት የሆነ ገለፃን እንዳደረግንላችሁ ተስፋ
እናደርጋለን ። ርእሱ ሰፊ እንደመሆኑ ዳግመኛ በጥልቀት ለመዳሰስ ቃል እንገባለን✌
.
👇👇👇👇👇
🚩ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
https://telegram.me/engineer03
👆👆👆👆👆።
👉10 የ ዓለማችን ረዣዥም ህንፃዎች
▶1) Burj Khalifa =Dubai
▶2) Shanghai tower =China
▶3) abraj Al-bait clock tower =Saudi Arabia
▶4) ping An finance centre =China
▶5) Lotte world tower =south Korea
▶6) one world trade center =United States
▶7) Guangzhou CTF finance centre = China
▶8) Taipei 101 = Taiwan
▶9) Shanghai world financial center = China
▶10) international commerce center =China
❤ሽጋ ቀን ይሁንላቹ😍
#share to anther
@engineer03
@engineer03
@engineer03
ለሌሎችም ሼር ድርጉ