Civil Engineering
1.36K subscribers
1.24K photos
21 videos
960 files
661 links
*ለሲቪል ; ለአርክቴክቶች÷ለኮንስትራክሽን ÷ ለሀይድሮሊክ መሀንዲሶች እና ተማሪዎች የተዘጋጀ ትምህርታዊ ቻናል ፡፡

@engineer03


http://www.Indiabix.com በዚህ ደግሞ ማንኛውንም ጥያቄና መልስ ታገኛላችሁ!

╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕
Download Telegram
Fluid Mechanics Books Collection

1. Introduction to Fluid Mechanics and Fluid Machines by S.K. Som, Gautam Biswas
https://www.enggebookz.com/pdf-introduction-to-fluid-mechanics-and-fluid-machines-by-s-k-som-gautam-biswas/

2. Fluid Mechanics by Yunus A. Cengel, John M. Cimbala
https://www.enggebookz.com/pdf-fluid-mechanics-by-yunus-a-cengel-john-m-cimbala/

3. Fluid Mechanics by Pijush K.Kundu, Ira M Cohen
https://www.enggebookz.com/pdf-fluid-mechanics-by-pijush-k-kundu-ira-m-cohen/

4. Introduction to Fluid Mechanics by Robert W. Fox
https://www.enggebookz.com/pdf-introduction-to-fluid-mechanics-by-robert-w-fox/

5. Engineering Fluid Mechanics by T. Al-Shemmeri
https://www.enggebookz.com/pdf-engineering-fluid-mechanics-by-t-al-shemmeri/

6. Fundamentals of Fluid Mechanics by Bruce R. Munson, Donald F. Young
https://www.enggebookz.com/pdf-fundamentals-of-fluid-mechanics-by-bruce-r-munson-donald-f-young/

7. Fluid Mechanics and Machinery by C.P. Kothandaraman, R.Rudramoorthy
https://www.enggebookz.com/pdf-fluid-mechanics-and-machinery-by-c-p-kothandaraman-r-rudramoorthy/

8. Engineering Fluid Mechanics by Clayton T.Crowe, Donald F.Elger
https://www.enggebookz.com/pdf-engineering-fluid-mechanics-by-clayton-t-crowe-donald-f-elger/

9. 2500 Solved problems in Fluid Mechanics & Hydraulics
https://www.enggebookz.com/pdf-2500-solved-problems-in-fluid-mechanics-hydraulics/

10. Hydraulics and Fluid Mechanics including Hydraulic Machines By P.N.Modi and S.M.Seth
https://www.enggebookz.com/pdf-hydraulics-and-fluid-mechanics-including-hydraulic-machines-by-p-n-modi-and-s-m-seth/

11. Open Channel Flow By M.Hanif Chaudhry
https://www.enggebookz.com/pdf-open-channel-flow-by-m-hanif-chaudhry/

12. Fluid Mechanics By Streeter International Student Edition
https://www.enggebookz.com/pdf-fluid-mechanics-by-streeter-international-student-edition/

13. Fluid Mechanics for Engineers By P.S. Barna
https://www.enggebookz.com/pdf-fluid-mechanics-for-engineers-by-p-s-barna/

14. Engineering Fluid Mechanics International Student Edition By William Graebel
https://www.enggebookz.com/pdf-engineering-fluid-mechanics-international-student-edition-by-william-graebel/

15. Basics of Fluid Mechanics By Genick Bar-Meir
https://www.enggebookz.com/pdf-basics-of-fluid-mechanics-by-genick-bar-meir/

16. Centrifugal Pump Handbook By Sulzer Pumps
https://www.enggebookz.com/pdf-centrifugal-pump-handbook-by-sulzer-pumps/

17. Basic Concepts in Turbomachinery By Grant Ingram
https://www.enggebookz.com/pdf-basic-concepts-in-turbomachinery-by-grant-ingram/

18. Flow in Open Channels By K Subramanya
https://www.enggebookz.com/pdf-flow-in-open-channels-by-k-subramanya/

19. A Textbook Of Fluid Mechanics And Hydraulic Machines (Full Book) By Dr R K Bansal
https://www.enggebookz.com/pdf-a-textbook-of-fluid-mechanics-and-hydraulic-machines-full-book-by-dr-r-k-bansal/

20. Fluid Mechanics and Pipe Flow: Turbulence, Simulation and Dynamics By Donald Matos, Cristian Valerio
https://www.enggebookz.com/pdf-fluid-mechanics-and-pipe-flow-turbulence-simulation-and-dynamics-by-donald-matos-cristian-valerio/

21. Fluid Mechanics Book By Joseph Spurk, Nuri Aksel
https://www.enggebookz.com/pdf-fluid-mechanics-book-by-joseph-spurk-nuri-aksel/
👉Today Tip
.
1). Question - አንድ G+22 የሆነ ህንፃ እንዴት ነው ምንም አይነት Column ሳንጠቀም መገንባት የምንችለው??
.


.
2). Question - ከ36 ሚ.ሜ በላይ ለሆኑ ፌሮዎች ለምንድነው Lapping የማይፈቀደው??



.

3). Question - ሊፍቶች ውስጥ ለምንድነው መስታወት የሚገጠመው??
.
ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;

@engineer03

👆👆👆👆👆

add engineers from the group.
@engineersWorks
@engineersWorks
1
መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላችሁ!!!
Civil Engineering
👉Today Tip . 1). Question - አንድ G+22 የሆነ ህንፃ እንዴት ነው ምንም አይነት Column ሳንጠቀም መገንባት የምንችለው?? . . 2). Question - ከ36 ሚ.ሜ በላይ ለሆኑ ፌሮዎች ለምንድነው Lapping የማይፈቀደው?? . 3). Question - ሊፍቶች ውስጥ ለምንድነው መስታወት የሚገጠመው?? . ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን። 👇👇👇👇👇
መልስ

2). Answer - Shear wall በመጠቀም

2). Answer - ፌሮዎቹ ሳይዛቸው ትልልቅ ስለሆነ Lap ብናደርጋቸው ሎድ ትራንስፈር እንዲኖር ላፕ ሌንግዙ ረጅም መሆን አለበት በተጨማሪም ሁለቱን አንድ ላይ ማሰሪያ ትልቅ ዲያሜትር ያለው ፌሮ/ ሽቦ ያስፈልገናል - አስቸጋሪ ነው::


3). Answer - በግድግዳ የተከበበ በጣም ጠባብ ቤት ውስጥ ዝም ብለን ብንቆም ምን ይሰማናል??

ሊፍቶች ከጥበታቸው በተጨማሪ እንቅስቃሴ ስለሚያደርጉ ሰዎች ይሰጋሉ ምን አልባት አደጋ ከተከሰተ ፤ መብራት ከጠፋ l ምናምን ብለው - እናም ሰዎች ፀጉራቸውን እያስተካከሉ ፤ l ውበታቸውን እያደነቁ ምናምን ፈታ እንዲሉና ሃሳባቸውን እንዲሰረቅ ነው ሊፍት ውስጥ መስታወት የሚገጠመዉ::

🙏መልካም ምሽት🙏

@engineer03
Paris , France
ሰላም ውድ የCivil Engineering ቤተሠቦች 👋

ከእለት እለት ኑሯችን ጋር የሚዛመድ ምርት የቴክኖሎች ቻናል እናስተዋውቃችሁ::
Sime Tech ይባላል::

ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ወደ ቻናሉ በመግባት ተጠቀሙበት:: ከቴክኖሎጅ ጋር ይጓዙ::

#join 👇#here

@Simetube @Simetube
@Simetube @Simetube
@Simetube @Simetube
🚧How to calculate the volume of sand , aggregate and cement in 1m^3 of concrete? Take c-20 concrete

Answer

Example c-20 mix design (1:2:3) if we are given 1 m^3 concrete

First we add up 1+2+3=6

Means 1 cement
2 sand
3 aggregate

To calculate the the volume of sand

1 * 2/6= 2/6 m^3 =0.33m^3

To calculate the volume of aggregate (gravel)

1 * 3/6 = 0.5m^3

To calculate the volume of cement

1 * 1/6 = 0.167m^3

To calculate cement in piece

1 bag of cement is 0.036m^3 so divide the quantity of cement with a bag of cement

Bag of cement = 0.167 / 0.036 = 4.6

So we use 5 bag of cement

@engineer03 @engineer03
@engineer03 @engineer03
1
👉 የትኛው ኢኮኖሚካል ነው ?? => Flat Plate, Waffle, Flat
with Drop or Solid Slab


🚩ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
https://telegram.me/engineer03
👆👆👆👆👆

.
.
በጠቅላላው በፍሎር ደረጃ ኢሄኛው የተሻለ ኢኮኖሚካል ነው
አይደለም ለማለት Quantity ካልሰራን ለማወቅ አስቸጋሪ ነው ….
በፓኔል ደረጃ ( ስለአንድ እስላብ ብቻ ) ካወራን ግን EBCS
ሪኮመንድ የሚያረጋቸው የስላብ አይነቶች አሉ ፡፡ ሪኮመንዴሽኑ
100 ፐርሰንት ትክክል ነው ማለት አይደለም - ኢኮኖሚካል ነው
ለማለት ጂኦሜትሪንና የፌሮ ብዛትን ግምት ውስጥ ማስገባት
አለብን - ስለዚህ አሁንም 100 ፐርሰንት እርግጠኛ የምንሆነው
ኳንቲቲ በመስራት ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ኮዱ ባደረገው ጥናት
መሰረት ከኮለን እስከ ኮለን ያለውን ርቀት መሰረት አድርጎ
ኢኮኖሚካል ነው ያለውን የስላብ አይነት አስቀምጡዋል፡፡
እነዚህም፡
.
.
1. Flat Plate - ሎዱ ቀላል ከሆነና ከኮለን ሴንተር እስከ ኮለን
ሴንተር ከ4.5 እስከ 6ሜ ለሆነ ስላብ ኢኮኖሚካል ነው
.
2. Flat Slab With Drop - ከባድ ሎድ ካለና ከሴንተር -
ሴንተር ከ6 እስከ 9ሜ. ለሆነ እስላብ ኢኮኖሚካል ነው፡፡
.
3. Waffle Slab - ለትልቅ እስፓን ከ7.5 – 12ሜ………
ለትልቅ እስፓን ከmoment ይልቅ vertical load ገቨርን
ስለሚያደርግ መሃል ስፓን ላይ ያለውን የስላብ ውፍረት መቀነስ
እንችላለን - ዋፍል ስላብ በመጠቀም ማለት ነው፡፡
.
4. Ribbed Slab -ትልቅ ስፓን ላላቸውና ከቀላል እስከ
መካከለኛ የሆነ ተንቀሳቃሽ ሎድ ላላቸው ፓኔሎች ኢኮኖሚካል
ነው፡፡
.
5. Solid Slab - የስፓኑ ርዝመት በጨመረ ቁጥር ኢኮኖሚካል
አይደለም፡፡ ፍላት ስላቦች ናቸው ኢኮኖሚካል የሚሆኑት
ምክንያቱም የፍላት ስላብ ብረት አቀማመጥ በ Strip ስለሆነ
የፌሮ ብዛት ይቀንሳል::

ሌሎችንም መረጃዎች እንዲደርስዎት ለሌሎች ሼር ያድርጉ
👇👇👇👇👇👇
https://telegram.me/engineer03
እናት ባንክ headquarter

@engineer03
Hydraulics and water supply Lecture
.

👉 የ ላየኛው የምድር ውሃ (surface water) ለማጣራት የምንጠቀማቸው ዘዴዎች አዘጋጅተናል 👇
.
⓵ስክሪኒንግ (screening) - ይህ የመጀመረርያው የማጣራት ደረጃ ሲሆን በዚህ የማጣራት ዘዴ ውስጥ በውሃው ላይ የሚንሳፈፉ ግዙፍ አካላትን ለምሳሌ የዛፍ ጉቶ ፣ግንድ፣ ቅጠል እና ልዩ ልዩ የፕላስቲክ ተንሳፋፊ ቁሳቁሶች ወደ ዋናው የማጣሪያ ገንዳ እና ስርዓት
እንዳይገቡ ያግዳል ።
.
⓶ማርጋት (Coagulation )፦ በዚህ የማጣራት ደረጃ ላይ ለአይን እይታ ያነሱ ጥቃቅን አካላትን (Particle size 10^-7cm የሚሆኑ) በማርጋት እና የኬሚካል ቻርጃቸውን ኒውትራላይዝ የሚያረግ ኬሚካል በመጨመር እርስ በእርሳቸው እንዲሳሳቡ ማድረግ ነው ።
ለዚህ የአልሙኒየም ፖሊመሮች (Alum) እና አይረን (Fe+3) አገልግሎት ላይ ይውላሉ።

እንደ የቁልቋል ተክል ያሉ የተፈጥሮ አርጊዎች (coagulants) መጠቀምም ይቻላል
.
⓷ጉግለት (Flocculation)፦ ይህ እርከን ፤ ማርጋት (coagulation ) ወቅት የረጉ ጥቃቅን አካላትን እርስ በእርሳቸው ቦንድ እስኪፈጥሩ እና እርስ በእርሳቸው ተጣብቀው እስኪጓግሉ ውሃው በተለያየ ፍጥነት የሚማሰልበት ነው።
ይህ ዘዴ ሜካኒካል ወይም ማኑዋል በሆነ መልኩ ይተገበራል።
.
⓸መዝቀጥ/ማዝቀጥ (sedimentation) ፦ በፍሎኩሌሽን ወቅት የጓጎለው ጥቃቅን አካላት በዚህን የማጣራት ደረጃ እንዲዘቅጡ ይደረጋል ። ይህ ዘዴ የሚተገበረው የሚጣራው የውሃን ፍጥነት በመቀነስ ግራቪቲን ተጠቅሞ እንዲዘቅጥ ማድረግ ነው።
በግራቪቲ ለማዝቀጥ የሚከብዱ እጅግ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን በፍሎኩሌሽን ወቅት ስንጠቀማቸው የነበሩ ኬሚካሎችን በመጠቀም እንዲዘቅጡ ይደረጋል።
.
⓹ ማጥራት (filtration ) ፦ በዚህ የማጥራት ደረጃ ከማዝቀጥ
ደረጃ ያለፉ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን እጅግ ጥቃቅን ቀዳዳዎች ባሉት አካል (medium ) እንዲያልፍ በማድረግ የድፍረስነቱን መጠን እጅግ መቀነስ ነው።
.
⓺ማከም (Disinfection) ፦ ከላይ በተጠቀሱ የማጣሪያ ሂደቶች የተጣራው ውሃ (በዋነኛነት ከተለያዩ ህይወት ከሌላቸው ጥቃቅን ቆሻሻዎች)
ለህብረተሰቡ ለአገልግሎት
ከመድረሱ በፊት በዚህ ሂደት (ዲስኢንፌክሽን) ማለፍ አለበት ።
ምክንያቱም ውሃው ለአገልግሎት የሚቀርበው ከተለያዩ በአይን ከማይታዩ በሽታ አምጪ ተህዋስያን ነፃ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው ። ዲስኢንፌክሽን ውሃውን በማፍላት ፣ ሚካኒካል
በሆነ መልኩ ፣ ለጨረር በማጋለጥ (radiation ) እንደሁም በኬሚካል ሊከናወን ይችላል።
በሃገራችን በዋነኛነት
ሃሎጅኖችን (ብሮሚን ክሎሪን እና አይኦዲን ) በመጠቀም
ኬሚካል በመጠቀም ውሃን እናክማለን ።

ከዚህ ሁሉ የማጣራት ሂደት በኋላ የተጣራው ውሃ ይጠራቀምና
ለተጠቃሚዎች ይዳረሳል።
.
ስለ surface waterን የማጣራት ሂደቶች ጥቂት የሆነ ገለፃን እንዳደረግንላችሁ ተስፋ
እናደርጋለን ። ርእሱ ሰፊ እንደመሆኑ ዳግመኛ በጥልቀት ለመዳሰስ ቃል እንገባለን
.
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
https://telegram.me/engineer03
👆👆👆👆👆
አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።
👍1
የመስቀል አደባባይ ግንባታ የማጠናቀቂያ ምዕራፍ!

የአዲስአበባ ከተማ ም/ከንቲቫ የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ይጠናቀቃል አሉ።

የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች በመጠናቀቅ ላይ ያለው የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል።

ይህ የለውጡ ትሩፋት የሆነ የግንባታ ፕሮጀክት ባለፉት 9 ወራት በቀን ለ24 ሰአታት ሳይቋረጥ ሲከናወን የቆየ እና ትልቅ ግብ አስቀምጠን መስራት እና ማጠናቀቅ እንደምንችል ያሳየንበት ነው ያሉት ከንቲባዋ ወደፊትም ለወጣቶች ሰፊ የስራ እድል ይፈጥራል ብለዋል።

አዲሱ ግንባታ ስድስት ለማስታወቂያ አገልግሎት የሚዉሉ LED ስክሪኖች ፣ ከመስቀል አደባባይ እስከ መዘጋጃ ቤት 3.5 ኪ.ሜ የሚረዝም የእግረኛ እና የሳይክል መንገድም አደባባዩን ውብ እና ጽዱ ከማድረግ ባሻገር ፣ ፕሮጀክቱ ከወለል በታች ሱቆችን ፣ ከ1 ሺህ 400 በላይ ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚያስችል የመኪና ማቆሚያ፣ 155 መጸዳጃ ቤቶች፣ እና የተለያዩ መገበያያ ሱቆችን ያካትታል ተብሏል።

መስቀል አደባባይ የቀድሞ ይዘቱን ሳይለቅ ዘመናዊ ተደርጎ መሰራቱም ልዩ እንደሚያደርገው ከቲቫው በማህበራዊ ድረገፃቸው አስፍረዋል።

https://telegram.me/engineer03
☞በኮንስትራክሽን ስራ ውጤታማ ለመሆን የሚያስፈልጉ 10 ወሳኝ ነጥቦች...
.
1) የግንባታ እቃዎች ፍተሻ( TESTS OF BUILDING
MATERIALS) አንድ ጥሩ ኢንጅነር በሳይት ላይ የሚሰሩ
የግንባታ እቃዎችን ለመፈተሽ
የሚጠቅሙ የፍተሻ ስራዎችን የግድ ማወቅ ይጠበቅበታል።
ከታች የተለያዩ
አይነት የፍተሻ ቴክኒኮች ተጠቅሰዋል
የኮንክሪት ፍተሻ(Concrete Test):
•Slump test,
•compression test (cubic or cylindrical test),
•split tensile test, soundness etc.
የአፈር ፍተሻ (Soil Test):
•Core cutter test,
•compactiontest,sand replacement test, triaxial test,
consolidation test etc.
Bitumen Test:
•Ductility test, softening point
test, gravity test, penetration test etc.
(በእርግጥ እነዚህን ሁሉ እውቀቶች በየዮንቨርስቲዎች ውስጥ
አንማር ይሆናል
ነገር ግን ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ የግድ
መማር
ማወቅ አለብን ዩ ቲዩብ ገብተን ብንፈልግ በቪድዮ የተደገፉቁም
ነገሮችን እናገኛለን ጥቆማችን ነው ::
:
2) የአፈር ጥናት (INVESTIGATION OF SOIL)
የተለያዩ አይነት የፍተሻ ቴክኒኮችን ተጠቅመን የአፈሩን የመሸከም
አቅም እና
ርጉእነት (settlement and stability ) የምንገነባው አካል
ከመገንባቱ በፊት ልናውቅ እንችላለን።
እንደ ኢንጅነር የአፈር ጥናት ለማድረግ የሚጠቅሙ
በሳይት ላይ የሚከወኑ የፍተሻ ቴክኒኮችን ማወቅ ግዴታችን ነው።
:
3 የተለያዩ የሰርቬይን መሳሪያዎች አጠቃቀም ማወቅ(USES OF
SURVEYING INSTRUMENTS)
በእርግጥ በብዙ የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ ራሱን የቻለ
የሰርቬይ ባለሞያ መቅጠር አሁን አሁን የተለመደ ቢሆንም ነገር
ግን መሰረታዊ የሚባሉ የሰርቬይ
መሳራያዎች ለምሳሌ ቶታል ስቴሽን እና ቴዎዶላይት
አጠቃቀማቸውን አንድ ኢንጅነር የግድ ማወቅ አለበት። የግድ !
:
4). የተለያዩ የግንባታ ስታንዳርድ ኮዶች (STANDARD CODES
USED IN CONSTRUCTION)
ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ከመልካ ምድራቸው
የአየር፣የንፋስ፣የመሬት መንቀጥቀጥ ከባቢያዊ ፀባያቸው አንፃር
የሚያዘጋጁት የግንባታ መርህ
(Construction codes) አላቸው።
አንድ ኢንጅንየር ግንባታ የሚያደርግበት ሃገርን ስታንዳርድ ኮድ
የማወቅ ግዴታ አለበት ምክንያቱም የሚገነባው ቁስሃገሪቱ ባላት
ተፈጥሯዊ መሰናክል እንዳይሰናከል እና እንዳይወድም። እነዚህን
ኮዶች ወይም መመሪያዎች ሳይከተል የሚገነባ የትኛውም ግንባታ
የመፍረስአቅሙ በእጥፍ የጨመረ ነው።

5) BAR BENDING SCHEDULE
ባር ቤንዲንግ ስኬጁል ለኢንጅነየሮች ጠቃሚ የሆነ ቻርት (በተለይ
ኮንስትራክሽኑ ሬንፎርስመንት ካለው)። ይህ ቻርት ሬንፎርስድ
የሆነው የግንባታ
አካል ማለትም ቢም፣ኮለን፣ስላብ፣ዋል...የሚጠቀማቸውን ቤረቶች
የሚቆረጥበት ርዝመት ፣ በምን ያህል ርዝመት እንደሚታጠፉ እና
ምን ያክል ተመሳሳይ እጥፋትና ርዝመት ያላቸው ባሮች በዛ አካል
ውስጥ እንደሚኖሩ በግልፅ ይነግረናል ።
ይህ ቻርት ብረትን ያለብክነት እንድንጠቀም እና የስትራክቸሩን
ደህንነት (safety) እንድንጠብቅ ይጠቅመናል

6) የንድፍ እና ዲዛይን ንባብ (DRAWING AND DESIGN)
አንድ ሳይት ኢንጅነር ከምንም ከምንም በላይ የግንባታን ንድፍ
የማንበብ በጣም ትልቅ እውቀት ሊኖረው ይገባል።
ዲዛይን እና ንድፎችን በትክክል ማንበብ እናመተርጎም ከቻለ
ለሳይት ኢንጂንየርነት የሚያበቃውን 60% እውቀት አካብቷል
ማለት ነው።
ስለዚህ በተለይ ተማሪዎች ለቴክኒካል ድራዊንግ እና አውቶካድ
እውቀቶች የምትሰጡትን ክሬዲት ከፍ አርጉ የፔጃችን መልእክት
ነው::

7) ግምት እና ክፍያ ( ESTIMATION AND BILLS)
ግንባታው ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያወጣ ግምቱን
የሚያስቀምጠው የሳይት ኢንጅንየሩ ነው።
(እንዴት መገመት እንዳለብን ፎርማቱን ወደፊት እንፖስታለን)

8 የጥራት ቁጥጥር (QUALITY CONTROL) ከኢንጅነሪንግ መርሆች ውስጥ አንዱ ጥራት ነው።

ጥራቱን የጠበቀ ግንባታ ለተጠቃሚው አካል ገንብቶ ማቅረብ ግዴታችን ነው።
አንዳንዴ ለሆዳቸው ያደሩኢንጂንየሮች ጥራቱን ባልጠበቀ የግንባታ
መሳሪያ ገንብተው ያስረከቡት ህንፃ ምን አይነት ጉዳቶች እንዳደረሰ
የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው።
አንድ ሳይት ኢንጅነር የሚጠቀመውን የግንባታ ቁስ ጥራት
የማወቅ ግዴታ አለበት ኋላ በሃገርም በግለሰብም ላይ የሚደርስን
አደጋ ለመከላከል።

9) የሳይት ላይ አመራሮች (ON FIELD MANAGEMENT) እንዴት ፎርም ወርክ መታሰር እንዳለበት፣ የኮንክሪት አሰራር፣ለጥንቃቄ የምንሰራቸው ስራዎችን ጨምሮ የተለያዩ ነገሮች ማወቅ ግዴታችን ነው
:
10) ከጉልበት ሰራተኞች ጋር ያለን መናበብ መቀራረብ
(COORDINATION
WITHLABOR) የጉልበት ሰራተኞችን ጨምሮ ሌሎች የተማሩ
እና ያልተማሩ ሰራተኞችን እንዴትማስተዳደር እንዳለብን እውቀቱ
ሊኖረን ይገባል።
ትዛዝ ማስተላለፍ ብቻሳይሆን ወርዶ መስራትም ይጠበቅብናል።
ለስራችን መቀላጠፍ ከሁሉምጋ ተናቦና በፍቅር መስራት ወሳኝ እና
ወሳኝ ነገር ነው።
.
.
አንድ ጥሩ የሚባል CONSTRUCTION እንጅነር ማወቅ ስለሚገባው ነገሮች ትንሽም ቢሆን እውቀት ከትንሹ ይጀምራልና ሼር አድርጉ
@engineer03
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያው የወጣበት ቀን መጋቢት 19/2013 ዓ.ም
ምንጭ: ሪፖርተር ጋዜጣ
በሪፖርተር ጋዜጣ የሚወጡ የሥራ ማስታወቂያዎችን ለማግኘት https://ethiopianreporterjobs.com ይጎብኙ

https://telegram.me/engineer03