Civil Engineering
1.37K subscribers
1.26K photos
20 videos
962 files
673 links
*ለሲቪል ; ለአርክቴክቶች÷ለኮንስትራክሽን ÷ ለሀይድሮሊክ መሀንዲሶች እና ተማሪዎች የተዘጋጀ ትምህርታዊ ቻናል ፡፡

@engineer03


http://www.Indiabix.com በዚህ ደግሞ ማንኛውንም ጥያቄና መልስ ታገኛላችሁ!

╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕
Download Telegram
የመንግስት ኮንስትራክሽን ግንባታ ስራዎችን ያለጨረታ ስለማከናወን
======================
____________________________


#የመንግስት የኮንስትራክሽን ስራዎችን ያለጨረታ ለመረጠው ተቋራጭ እየሰጡ የማሰራት ሂደት በሀገራችን በተግባር እየተለመደ መጥቷል፡፡ይሄውም በማህበረሰቡ ዘንድ ግርታን እየፈጠረ ይገኛል፡፡ስለሆነም በጉዳዩ ላይ የህግ ማእቀፉን በመዳሰስ በእርግጥ መንግስት ይሄን ለማድረግ ፈቃጅ ህግ አለው ወይ? የሚለውን ነጥብ በዚህ ጽሁፍ ምላሽ ለመስጠት ተሞክሯል፡፡

#የግንባታ አገልግሎት ግዥን ጨምሮ ለመንግስት ግዥ ተፈጻሚ የሚሆነው የፌዴራል የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 649/2001 ነው፡፡የዚህ አዋጅ የተፈጻሚነት ወሰን በአንቀጽ 3 ላይ እንደተቀመጠው አዋጁ በፌዴራል ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ለአዋጁ ማስፈጸሚያ ደንብም ወጥቶ በስራ ላይ ውሏል፡፡ክልሎች የየራሳቸው የግዥ እና ንብረት አስተዳደር የህግ ማእቀፍ አላቸው፡፡በዚህ ጽሁፍ ግን የፌዴራሉን የህግ ማእቀፍ ብቻ የምንዳስስ ይሆናል፡፡

#በአዋጁ አንቀጽ 3(2) ላይ በብሄራዊ ደህንነት እና በሀገር መከላከያ ምክንያት ግዥ በተለየ ዘዴ ሊፈጸም እንደሚችል ያስቀምጣል፡፡ሆኖም ለአፈጻጸሙ ዝርዝር መመሪያ እንደሚወጣለት ይገልጻል፡፡አዋጁ በመንግስት ለመንግስት ግዥ ላይም ተፈጻሚ እንደማይሆን ተደንግጓል፡፡ስለዚህ እነዚህን ልዩ ሁኔታዎች በሚመለከት አዋጁ ተፈጻሚ ስለማይሆን ግዥው አዋጁ ካስቀመጠው የግዥ ዘዴ ውጭ እንዴት መፈጸም እንደሚገባው ዝርዝር መመሪያ ካለ መፈተሽ አስፈላጊ ይሆናል ማለት ነው፡፡በእርግጥ የኮንስትራክሽን ስራ ከብሄራዊ ደህንነት እና ከሀገር መከላከያ አንጻር ታይቶ በልዩ የግዥ ዘዴ እንዲፈጸም የሚያስገድድበት ሁኔታ አለ ወይ?ብሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

#ሌላው በአዋጁ አንቀጽ 6 ላይ አለማቀፍ ግዴታወችን በሚመለከት የተደነገገውን መመልከት ያስፈልጋል፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 6(1) ላይ "ይህ አዋጅ የፌዴራል መንግስት ከአንድ ወይም ከአንድ በላይ ከሆኑ መንግስታት ወይም ከአለማቀፍ ድርጅቶች ጋር ባደረገው ወይም በሚያደርገው ስምምነት ወይም ከስምምነቱ ከመነጨ ግዴታ ጋር የማይጣጣም ከሆነ በስምምነቱ የተመለከተው ይጸናል፡፡" በሚል ተደንግጓል፡፡ስለዚህ በስምምነቱ እና በግዥ አዋጁ መካከል አለመጣጣም አለ ወይስ የለም የሚለውን መጀመሪያ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡በስምምነቱ እና በግዥ አዋጁ መካከል አለመጣጣም ከሌለ የግዥ አዋጁ ሙሉ በሙሉ መተግበር አለበት ማለት ነው፡፡

#በዚህ በአዋጁ አንቀጽ 6(1) ድንጋጌ መሰረት በተለይ አለማቀፍ አበዳሪ አካላት ወይም እርዳታ ሰጭ አካላት ከመንግስት ጋር በሚያደርጉት ስምምነት ምናልባት በአዋጁ ከተቀመጠው የግልጽ ጨረታ ውድድር ውጭ የግንባታ ስራው በፈለጉት ተቋራጭ እንዲሰራ ተስማምተው ከሆነ ስምምነቱ መከበር ይኖርበታል ማለት ነው፡፡ለምሳሌ የቻይና ባንክ ለአንድ የግንባታ ፕሮጀክት የብድር ወይም እርዳታ ገንዘብ ለመስጠት ቢፈቅድ እና ግንባታው ግን በአንድ የቻይና ድርጅት ያለጨረታ እንዲከናወን ቅድመ ሁኔታ ቢያስቀምጥ፣የኢትዮጵያ መንግስት ያለው አማራጭ ወይ ብድርና እርዳታውን መተው አለበለዚያ ደግሞ ቅድመ ሁኔታውን ተቀብሎ የብድርና እርዳታውን ስምምነት መፈራረምና በስምምነቱ መሰረት መፈጸም ነው፡፡እንግዲህ መንግስት ቅድመ ሁኔታውን ተቀብሎ ስምምነት ከተፈራረመ በስምምነቱ መሰረት ለመፈጸም የግዥ አዋጁን መጣስ ግድ ስለሚሆንበት እንደዚህ አይነቱን ሁኔታ በህግ ማእቀፍ እውቅና ለመስጠት የአዋጁ አንቀጽ 6(1) ፈቃጅ ሆኖ ተደንግጓል ማለት ነው፡፡

#የአለማቀፍ ባይላተራል ኤይድ ኢንስቲትዩሽን በሚባሉት (ለምሳሌ እንደ USAID) ሁለት አይነት የግዥ ዘዴ ይኖራል፡፡አንደኛው እራሱ እርዳታ ሰጭው ጨረታውን አከናውኖ እርዳታ የሚሰጥበት አግባብ ይኖራል፡፡ሌላኛው ደግሞ በእርዳታ ተቀባዩ ሀገር ጨረታው የሚከናወንበት አግባብ ነው፡፡ሆኖም በዚህ በሁለተኛው ሂደት እርዳታ ተቀባዩ ሀገር መከተል የሚገባው የግዥ ፖሊሲ ይኖራል፡፡

#በመልቲላተራል ዴቨሎፕመንት ኢንስቲትዩሽን(ለምሳሌ እንደ World bank) ባሉት ላይ የግዥ ሂደት በተበዳሪ ሀገራት የሚከናወን ይሆናል፡፡በዚህም ባንኩ የውል አካል አይሆንም፡፡የአበዳሪውን ባንክ የግዥ ፖሊሲ መከተል ግን የግድ ይሆናል፡፡በአብዛኛው የባንኩ የግዥ ፖሊሲ በብድር ስምምነት ውስጥ የሚቀመጥ ጋይድላይን ላይ ይካተታል፡፡ባንኩ የሱፐርቫይዘርነት አስተዋጽኦ ብቻ ይኖረዋል፡፡እንግዲህ ባንኩ የጨረታ ሂደቱን ካልተስማማበት ብድሩ ይሰረዛል ማለት ነው፡፡በመሰረቱ በአለም ባንክ ፕሮክዩርመንት ሪጉሌሽን ላይ አለማቀፍ የጨረታ ውድድር(international competitive bidding) መርህ ነው፡፡ሆኖም ውስን ፋይዳ(minor value) ላላቸው ግዥዎች የሀገር ውስጥ የጨረታ ውድድር(local compitative bidding) የሚፈቀድበት አግባብ ይኖራል፡፡ሌላው የወርልድ ባንክ ፕሮክዩርመንት ሪጉሌሽን የዶመስቲክ ሩል የበላይ ይሆናል የሚለው መርህ ነው፡፡ይሄውም በግዥ አዋጅ አንቀጽ 6(2) ጭምር እውቅና ተሰጥቶታል፡፡

#እንግዲህ የአለማቀፍ ባይላተራል ኤይድ ኢንስቲትዩሽን ሆነ መልቲላተራል ዴቨሎፕመንት ኢንስቲትዩሽን የሚተገብሩት የግዥ ዘዴ ከላይ እንደተመለከተው የጨረታ ውድድርን የሚጋብዝ ነው፡፡

#በተጨማሪም ልዩ ግዥን በተመለከተ በአዋጁ አንቀጽ 60 ላይ አገራዊ ጠቀሜታ ያላቸው ከፍተኛ ግዥዎች የሚፈጽም አካል ሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ እንደሚቋቋም ተደንግጓል፡፡በዚህ በሚቋቋመው አካል የሚፈጸሙ የግዥ አይነቶችም በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚንስትር የሚወሰኑ ይሆናል፡፡እንግዲህ የኮንስትራክሽን ስራ አገልግሎት ግዥ በልዩ ግዥ የሚካተት ይሆናል ወይ? በሚል መጠየቅ ይቻላል፡፡ምላሹን ለማግኘት ደግሞ ልዩ ግዥ ፈጻሚ አካል ተቋቁሟል ወይ? በልዩ ግዥ የሚፈጸሙ የግዥ አይነቶች ዝርዝር በሚኒስትሩ ተወስኗል ወይ?የሚለውን ማንሳት ይጠይቃል፡፡ልዩ ግዥ ቢሆንስ ያለጨረታ ውድድር ሊከናወን ይችላል ወይ?የሚለውም ሌላው በዝርዝር ምላሽ ማግኘት የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ልዩ ግዥን በተመለከተ በፌዴራል ፐብሊክ ፕሮክዩርመንት ዳይሬክቲቭ አንቀጽ 26 ላይ በዝርዝር ተመልክቷል፡፡በእርግጥ የኮንስትራክሽን ስራን በቀጥታ ያለጨረታ በተቋራጭ የማሰራት ሁኔታ በዚህ የህግ ማእቀፍ ውስጥ የተፈቀደ ሆኖ ይካተታል የሚል እሳቤ የለኝም፡፡

#እንግዲህ በግዥ አዋጁ አንቀጽ 33(1) ላይ እንደተመለከተው በመንግስት ግዥ አፈጻጸም ስድስት አይነት የግዥ ዘዴዎች ሲኖሩ ይሄውም ግልጽ ጨረታ፣በመወዳደሪያ ሀሳብ መጠየቂያ የሚፈጸም ግዥ፣በሁለት ደረጃ ጨረታ የሚፈጸም ግዥ፣ውስን ጨረታ፣በዋጋ ማቅረቢያ የሚፈጸም ግዥ፣ እና ከአንድ አቅራቢ የሚፈጸም ግዥ ያካትታል፡፡

#በመርህ ደረጃ በአዋጁ አንቀጽ 33(2) ላይ እንደተቀመጠው የመንግስት መስሪያ ቤቶች ማናቸውም ግዥ በግልጽ የጨረታ ዘዴ መፈጸም አለባቸው፡፡ሆኖም በአዋጁ በተፈቀዱ ልዩ ሁኔታዎች ከግልጽ ጨረታ ውጭ ግዥ መፈጸም ይቻላል፡፡
#ሌላው ሊነሳ የሚችለው ነጥብ በግዥ አዋጁ አንቀጽ 51(1)(ረ) ላይ የመንግስት መስሪያ ቤቶች "በጣም አስቸኳይ ከመሆኑ የተነሳ ከባድ ችግር የሚፈጥርና በመስሪያ ቤቱ ስራ አፈጻጸም ላይ ጉዳትን የሚያስከትል በመሆኑ ምክንያት በመስሪያ ቤቱ የበላይ ሀላፊ የተፈቀደ ግዥ" በሚመለከት ከአንድ አቅራቢ ግዥ ሊፈጽሙ እንደሚችሉ የተደነገገው ነው፡፡ምናልባትም መንግስት በተግባር የግንባታ ስራዎችን ለተመረጠ ተቋራጭ ያለጨረታ የሚያሰራበት አግባብ ይህ ድንጋጌ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡

#ስለዚህ በሀገራችን የኮንስትራክሽን ስራዎች ያለጨረታ ለተቋራጭ የሚሰጡ በየትኛው ፈቃጅ ህግ ነው? የሚለው ሲታይ ምናልባት በአዋጁ አንቀጽ 3(2)፣6(1)፣60፣እና 51(1)(ረ) የተመለከቱት ጠባብ ሁኔታወች ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ሆኖም በሀገራችን በመንግስት አስተዳደራዊ ውሳኔ እየተሰራበት ያለው ያለጨረታ ለተቋራጭ ሰጥቶ ግንባታ የማከናወን ሂደት በእርግጥ በእነዚህ ፈቃጅ የህግ ሁኔታዎች የተፈቀደና የታቀፈ ነው ወይ? የሚለው በተግባር ዝርዝር ፍተሻ ይጠይቃል፡፡

#በመጨረሻም በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3147 ላይ የመንግስት አስተዳደር መስሪያ ቤቶች ውል ለማድረግ አሸናፊውን ድርጅት በጨረታ ስነስርአት ሊመርጡ እንደሚችሉ ተቀምጧል፡፡ስለዚሁም በህጉ ላይ የጨረታ ስነስርአት እንዲፈጸም በተደነገገ ጊዜ ውሎች በጨረታ ካልተሰጡ ፈራሽ ናቸው በሚል በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3147(2) ላይ ተደንግጓል፡፡

#በአጠቃላይ የመንግስት ግንባታ ስራዎችን ያለጨረታ ለሚፈለገው ተቋራጭ መስጠት በህግ ረገድ ጠባብ ፈቃጅ ሁኔታዎች ያሉት ነው፡፡ስለዚህ ሲተገበርም በጠባቡ ሊሆን ይገባል፡፡


በጉባኤ አሰፋ የተዘጋጀ
የአ/አ/ከ/አ/ኮንስትራክሽን ቢሮ
ሐምሌ 20/2012 ዓ/ም


https://t.me/engineer03
Disadvantages of Plastic mold formwork:

• Cost is very much higher.
• It is heavy in weight and requires lifting equipment for large structure formworks.
• Corrosion will occur when there is a frequent contact with water.
• The size and shapes of forms available are limited


https://t.me/engineer03
📌▫️Some Very Important terms in Civil Engineering.

- Height of Parapet wall should be = 1m

- Thickness of DPC = 2.5cm OR 1 inch

- Height of Building = 3.15m

- Height of Window = 2.1m

- One bag of cement = 1.25cubic feet and 0.0347 m3

- Weight of one cement bag = 50kg

- Minimum thickness of slab = 125mm

- No.of cement bags in 1m3 = 28.8bags

- Lintel thickness = 15cm (min)

- Lintel is provided at = 2.4 m in case of brick wall

- Minimum diameter of bars used in slab = 8mm

- Minimum diameter of bars used in column = 12mm

- Minimum diameter of bars in Dowel bars = 12mm

- Maximum diameter of bars in slab = 1/8 x thickness of slab

- Maximum chair spacing = 1m

- Dimensional tolerance of cube = +2mm -2mm

- Maximum water absorption should not be more than 20%

- Initial setting time of cement = 30 minutes

- Final setting time of cement = 10 hrs 600 minutes

- DPR = Detailed project report

▫️Unit Weight

- RCC = 25 kN/m3 = 25000N/m3

- PCC = 24 kN/m3= 24000 N/m3

- Steel = 7850 kg/m3

- 1 Gallon = 3.78 liters

▫️Minimum no of bars

- For square column or rectangular = 4 bars

- For circular column = 6 bars
1 Yard = 3 feet

- Weight of steel = D2/162.2 kg/m

- Weight of steel = D2/533 kg / ft

- Slope of staircase = 25degree to 40 degree

- Size of concrete testing cube = 150x150x150 mm

- Concrete cube is filled in =3 layers

- Slump cone is filled in = 4 layers

- Cement should be used within three months of manufacturing.

- Minimum thickness of shear wall = 150mm

- Maximum thickness of shear wall = 400mm

- Universal testing machine is used for compression test of concrete tensile test of steel reinforcement.

- Minimum curing period
7 Days Normal weather condition.
10 Days not weather condition.

- Minimum percentage of steel column = 0.8 % of cross area

- Max % of steel in column = 6% of gross area

▫️Nominal Cover

Footing = 50mm

Column = 40mm

Slab = 20mm

Beam = 25mm

- Lapping is not allowed in bars of diameter 36mm or more welding is preffesed.{Old}

- Lapping of bar is not allowed for dia> 32mm as per new amendment

▫️No.of stirrups in beam = clear span/c/c/ spacing + 1

- R.C.C is affected by water because of corrossion of reinforcement bars.

- P.C.C is not affected by the water.


https://t.me/engineer03
ክለብ ክሪስታል ፓላስ ሊጉ መጠናቀቁን ተከትሎ በትላንትናው ዕለት የተለያዩ አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል ።

ጋናዊው የፊት መስመር አጥቂ ጆርዳን አዩ በሶስት ዘርፎች አሸናፊ መሆኑን ክለቡ በይፋ አሳውቋል ።

ጆርዳን አዩ የተጫዋቾች የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ፣ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች እንዲሁም የዓመቱ ምርጥ ጎል አሸናፊ በሚሉት ዘርፎች ማሸነፉ ታውቋል ።

ሐምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም
....More...
........open.....
........click here...
...have A good time...
ዒድ ሙባረክ!


Civil Engineer's work

እንኳን ለ1441ኛው ለታላቁ የዒድ አል-አድሐ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ ለማለት ይወዳል።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር ፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ ይሆንልን ዘንድ ከልብ እንመኛለን!

በዚህ አጋጣሚ በዓሉን ስናከብር የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ የመከላከያ መንገዶችን መተግበር #እንዳንዘነጋ ልናስታውሳችሁ እንወዳለን።

ሐምሌ 24 ቀን 2012 ዓ.ም

https://t.me/engineer03
https://t.me/engineer03
#ብዙ የኮንስትራክሽን ባለሞያዎች መሰንጠቅ በMix design ትክክል አለመሆን ብቻ የሚመጣ ይመስላቸዋል ነገር ግን ለመሰንጠቅ (cracking ) ምክንያት የሚሆኑ መንስኤዎችን ከዚህ በታች እንዲህ ዳስሰናል ~ መልካም ንባብ!
.
[1] - አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ
.
አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ መሰንጠቅ (cracking ) ይፈጠራል ስለዚህ የምንጠቀማቸውን ለኮንክሪት ግብዓት የሚሆኑ ቁሶችን (ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ ኮረኮንች) ጥራት መፈተሽ አለብን ኮንክሪቱ የብረት መዋቅር (reinforcement ) ያለው ከሆነ የብረቱን ጥራት መገምገም አለብን።
.
[2] - መኮማተር (Shrinkage )
.
ኮንክሪቱን በምንደባልቅበት እና ውሃ በምናጠጣበት ግዜ (Curing ) ተገቢውን ጥንቃቄ ካልወሰድን መኮማተር (shrinkage) መሰንጠቅን(cracking) ያስከትላል ።
መኮማተር (shrinkage) ለትልቅ የኮንክሪት ጥንካሬ በጣም አስፈላጊ ነው አስፈላጊውን የውሃ-ሲሚንቶ መመዛዘን (water cement ratio) ካልተጠቀምን በመኮማተር አማካኝነት መሰንጠቅ ሊፈጠር ይችላል ።
.
[3] - ጥራት ያለው Aggregate የማንጠቀም ከሆነ
.
Aggregate የኮንክሪትን አጠቃላይ ጥንካሬ ይወስንልናል ጥራቱ ጥሩ ያልሆነ Aggregate የምንጠቀም ከሆነ ከሲሚንቶ ጋር ተፈላጊውን ጥምረት (bond) ስለማይፈጥር ግንባታችን ሊሰነጠቅ ይችላል።
.
[4] - መዋቅራችን ከአቅም በላይ የሆነ ክብደት ሲያስተናግድ
.
ግንባታው / መዋቅሩ ተገቢውን ጥንካሬ ሳያገኝ በፊት ለትልቅ ክብደት የሚጋለጥ ከሆነ መሰንጠቅ ይከሰታል። በተጨማሪም መቀሰቻዎችን እና ቅስቱን (formwork ) ያለጊዜው የሚነሳ ከሆነም ግንባታችንን ለስንጣቆ ያጋልጠዋል።
.
[5] - በትክክል ውሃ እንዲጠጣ የማይደረግ ከሆነ (improper curing )
.
ይህ በአገራችን ከሚስተዋሉ ለመሰንጠቅ ከሚዳርጉ ምክንያቶች ቀዳሚው ነው - ውሃ በትክክል አለማጠጣት።
ኮንክሪት እንደተገነባ በተገቢው ጊዜ እና መጠን ውሃ ሊጠጣት አለበት ።
«ወንድና ሲሚንቶ ካልጠጣ ይሰነጠቃል» አይደል ሚሉት ሰካራም ወንዶች :D
.
[6] - የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) አለመመጣጠን
.
በጣም ትልቅ የሆነ የብረት መዋቅርን Mix ratioው ትንሽ በሆነ ኮንክሪት የሙሌት ስራ ስንሰራ በብረቱ እና በኮንክሪቱ መካከል ያለ የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) non linear ይሆናል ይህ ደግሞ መሰንጠቅን ያስከትላል።
.
[7] - በሳይት ላይ የሙሌት (casting ) ስራ ሲሰራ ተገቢ ጥንቃቄ ካልተደረገ እና ለስራው ተገቢ የሆነ ባለሞያ (የቀን ሰራተኛን ጨምሮ) ካልተመደበ መሰንጠቅ (cracking) በሚሰራው ኮንክሪት ላይ መፈጠሩ አይቀርም።



https://t.me/engineer03
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ እና የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ግንባታን ጎበኙ፡፡
==================
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ተክለወልድ አጥናፉ፣ ሌሎች የባንኩ ቦርድ አባላት እና የባንኩ ፕሬዘዳንት አቶ አቤ ሳኖ፣ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ግንባታ አሁን የደረሰበትን ደረጃና እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም እስካሁን በግንባታው ሂደት ያጋጠሙ ውስን ችግሮች መቀረፉቸውና ግንባታው በፍጥነት በመከናወን ላይ መሆኑን ተመልክተዋል፡፡

የህንፃው ግንባታ የማጠናቀቅ ሥራዎች በፍጥነት እንዲከናወኑ እና እስከ ስድስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንዲጠናቀቅ ግንባታውን በማካሄድ ላይ ከሚገኘው የቻይና መንግስት ኮንስትራክሽን ኢንጅነሪንግ ኮርፔሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ሞንግ ጋርም ተወያይተዋል፡፡

https://t.me/engineer03
የኮንስትራክሽን ቢሮ ማኔጅመንት አባላት በቢሮው የ 2 ወር አስቸኳይ ጊዜ ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አደረጉ፡፡
የዝግጅት ምዕራፍ ተብሎ በሚጠቀሰውና እስከ መስከረም 30/2013 ዓ/ም ድረስ በከተማ ዓቀፍ ደረጃ ሊተገበር የታቀደው የ 2 ወር አስቸኳይ ጊዜ ዕቅድን አስመልክቶ ቢሮው ባቀደው ዕቅድ ላይ የማኔጅመንት አባላቱ ውይይት አድርገዋል፡፡
የየዘርፉ ዕቅድ ኃላፊዎቹ በተገኙበት የቀረበ ሲሆን ዕቅዶቹም የሚለኩና በቁጥር የሚገለፁ በመሆናቸው አፈፃፀማቸውን ለመገምገም አመቺ እንደሆኑ ለማየት ተችሏል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ከ2008-2012 በጀት ዓመት የቆየው የቢሮው ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡በውይይቱ ላይም በዕቅድ ተይዘው የነበሩት 16 ግቦች አፈፃፀማቸው የነበሩ ተግዳሮቶች ቀርበዋል፡፡
የአ/አ/ከ/አ/ኮንስትራክሽን ቢሮ ሐምሌ 05/2012 ዓ/ም
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
📌የጨረታ ማስታወቂያ

የአ/አ/ከ/አ/ኮንስትራክሽን ቢሮ

ነሐሴ 08/2012 ዓ/ም

https://t.me/engineer03
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
The color of statuary marble used for sculptor’s work is____________.?
Anonymous Poll
10%
Red
68%
White
10%
Green
13%
Block
2. Bitumen paints offer_______________.
Anonymous Poll
14%
Pleasing surface
14%
Hard surface
37%
Smooth Surface
35%
Protective surface
🏗 የሸገሩ አዲስ አርማ💡
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

የሸገሩ አዲስ አርማ..........
👉 አዎ ሰማይ ጠቀስ ነው፤ 200 ሜትር ቁመት ባለ 48 ወለል ነው !!
👉 አዎ ግዙፍ ነው ፤ 18 ሺህ ካሬ ላይ አርፏል !!
👉 አዎ ውብ ነው፤ ዘመንኛ የኪነ ህንፃ ጥበብን ተላብሷል !!
👉 አዎ ውድ ነው፤ 298 ሚሊየን ዶላር ወይም 9 ቢሊየን ብር ወጪ ተመድቦለታል።
🕹ከአለም አስር ምርጥ የኮንስትራክሽን ተቋራጮች አንዱ በሆነው ኩባንያ ነው እየተገነባ ያለው።
በመጠናቀቅ ላይ ያለው የሸገሩ አርማ ውጤቱ ያማረ እንደሚሆን ገና ከጅምሩ አያያዙ መስካሪ ነው።
እንደ እኔ እንደ እኔ ሰማይ ጠቀሱ የንግድ ባንክ ማማ ፋይዳው ሊመዘን የሚገባው ቆሞ ከሚታየው ህንፃ ባሻገር ሃገር ከስራው ምን እንዳተረፈ ሲታወቅ ነው።

በዚህ ህንፃ ግምባታ ሂደት ወስጥ መሀንዲሶቻችን እና ገምቢዎቻችን ምን አተረፋ ብለን መጠየቅ ተገቢ ነው ?
• ስለ ግምባታ ደህንነት
• የግምባታ ግብአት አጠቃቀም
• የኮንትራት ማኔጅመንት
• ስለ ስራ ባህል እና ምግባር
• ስለ ጥራት......ወዘተ የሃገር ሰው ምን አተረፋችሁ ?? ምንስ ሙያዊ እሴትን ጨመራችሁ ??
🕹የዘመኑ የኪነ ህንፃ ጥበብ ( state of the art ) ውልድ የሆነው የዚህ ህንፃ ትልቁ ትርፍ ከውጤቱ ይልቅ ከሂደቱ የሚገኘው ነው ብዬ አምናለሁ።
ይህም ማለት በግምባታው ተሳታፊ የሆኑ የሃገራችን ሙያተኞች ከግምባታው ያገኙት እውቀት እና ለራሳቸው የጨመሩት እሴት ነው ዘላቂው ሃብት!!

#Commercial_Bank_of_Ethiopian_Head_office


https://t.me/engineer03