Civil Engineering
1.37K subscribers
1.26K photos
20 videos
962 files
673 links
*ለሲቪል ; ለአርክቴክቶች÷ለኮንስትራክሽን ÷ ለሀይድሮሊክ መሀንዲሶች እና ተማሪዎች የተዘጋጀ ትምህርታዊ ቻናል ፡፡

@engineer03


http://www.Indiabix.com በዚህ ደግሞ ማንኛውንም ጥያቄና መልስ ታገኛላችሁ!

╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕
Download Telegram
Forwarded from አሥራት ሚዲያ Asrat Media ®🇪🇹
ውኃ ለመያዝ የሚያስችሉ ሥራዎች ከሳምንታት በኋላ ይጠናቀቃሉ

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ውኃ ለመያዝ የሚያስችሉ ሥራዎች ከሳምንታት በኋላ እንደሚጠናቀቁ የውኃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገለጹ።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከአንድ ወር በኋላ ውኃ እንዲይዝ የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆኑን ለኢቲቪ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ በቀጣይ ሳምንታት የሚከናወኑ ቀሪ ተግባራት ከተከናወኑ በኋላ ግድቡ የመጀመሪያውን ዙር ውኃ መያዝ እንደሚችል መናገራቸውን አሥራት ሚዲያ ዘግቧል።

ይህም በሚቀጥለው ዓመት የቅድመ-ኃይል ማመንጫ ተግባሩን ለማከናወን ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ነው ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የተናገሩት።

ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ከሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ጋር ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በጎበኙበት ወቅት ነው።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ከጉብኝታቸው በኋላ ግድቡ በሚከናወንበት ስፍራ ላይ ችግኞች ተክለዋል።

ሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ.ም

https://t.me/Asrat_News
https://t.me/Asrat_News
ኢትዮጵያ Ethiopia

Addis Ababa around bole

🗣 🏗 ᏚᎻᎪᎡᎬ & JᏫᏆN ᏌᏚ 🚧
. @engineer03
Building construction

Basic elements of pitched roof

1. Span : It is the clear distance between the supports of an arch, beam or roof truss.

2. Rise : It is the vertical distance between the top of the ridge and the wall plate

3. Pitch : It is the inclination of the sides of a roof to the horizontal plane.

4. Ridge : It is defined as the apex line of the sloping roof.

5. Eaves : The lower edge of the inclined surfaces is called eaves. From eaves, the rain water from the roof surface drops down

6. Hip : It is the ridge formed by the intersection of two sloping surfaces, where exterior angle is greater than 180°

7. Valley : It is a reverse of a hip. It is formed by the intersection of two roof Surfaces, making an external angle less than 180°.

8. Hipped end : It is the sloped triangular surface formed at the end of a roof.

9. Verge : The edge of a gable, running between the eaves and ridge, is known as a verge.

10. Ridge piece or ridge beam or ridge board : It is the horizontal wooden member, in the form of a beam or board, which is provided at the apex of a roof truss. It supports the common rafters fixed to it.

11. Common rafters or Spars : These are inclined wooden members running from the ridge to the eaves. Depending upon the roof covering material, the rafters are Spaced 30 to 45 cm centre to centre.

12. Purlins : These are horizontal wooden or steel members, used to support common rafters of a roof when span is large. Purlins are supported on trusses or walls.

13. Hip rafters : These are the sloping rafters which form the hip of a sloped roof

14. Battens : These are thin strips of wood, called scantling, which are nailed to the rafters for lying roof materials above.

15. Boardings : They act Similar to battens and are nailed to common rafter to support roofing material.

16. Template : This Is a square or rectangular block of stone or concrete placed under a beam or truss, to spread the load over a larger area of the wall.

17. Cleats : These are short sections of wood or steel (angle iron), which are fixed on the principal rafters of trusses to support the purlins.

18. Truss : A roof truss is a frame work, usually of triangles, designed to support the roof covering or ceiling over rooms
.
Forwarded from አሥራት ሚዲያ Asrat Media ®🇪🇹
#Live ከላሊበላ

የፀሀይ ግርዶሽ

ሰኔ 14 ቀን 2012 ዓ.ም
https://t.me/Asrat_News
https://t.me/Asrat_News
በአዲስ አበባ ከተማ የሲሚንቶ ዝርዝር ዋጋ

መንግስት ካስቀመጠው የሲሚንቶ ዋጋ በላይ በሚሸጡ የሲሚንቶ አከፋፋዮች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ ፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በሲሚንቶ ግብይት ውስጥ ያሉ ህገ-ወጥ ደላሎችን ከገበያ ሰንሰለቱ በማስወጣት እየናረ የመጣውን የሲሚንቶ ዋጋ ለማስተካከል የመሸጫ ዋጋ በመተመን ከፋብሪካ አውጥተው የሚያከፋፍሉ የመንግስት የልማት ድርጅቶችና መመሪያውን አክብረው ለመስራት የተስማሙ የግል ነጋዴዎች ተመርጠው በቅርቡ ወደ ስራ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮው አላስፈላጊ የሲሚንቶ ዋጋ ንረትን በመቆጣጠርና ዋጋ በመተመን የኮንስትራክሽን ዘርፉ እንዳይዳከም በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ከፋብሪካዎች ተረክበው የሚሸጡ አከፋፋዮች የሚሸጡበት የአንድ ኩንታል ዋጋ እንደየርቀቱ ከ240.20 ብር እስከ 388.10 ብር እንዲሆን የተወሰነ ቢሆንም አንዳንድ አከፋፋዮች ግን ከተቀመጠው ዋጋ በላይ በመሸጥ ላይ እንደሚገኙ በተደረገ የመስክ ምልከታ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

መንግስት ባስቀመጠው የሲሚንቶ ዋጋ መሰረት ግብይት በማይፈጽሙ የሲሚንቶ አከፋፋዮች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወሰድ ቢሮው ገልጿል፡፡

VIA-Addis Ababa press secretary office

የአ/አ/ከ/አ/ኮንስትራክሽን ቢሮ ሰኔ 16/2012 ዓ/ም

https://t.me/engineer03
https://t.me/engineer03
የሀንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ የመብራትና ማብሪያ/ማጥፊያ ፣የሶኬት፣ የደወል ወዘተ ዝርጋታዎችን ያጠቃልላል። ስለዚህ አንድ በአንድ እናያለን።


🔸የቻናላችን ቤተሰብ ለመሆን
👇

https://t.me/engineer03

"ለሌሎች ለውጥ ምክንያት እንሁን!"
🔸ለወዳጅዎም ያጋሩ!
🔹እናመሰግናለን!
🔹1.የኤሌክትሪክ መብራት መስመር ዝርጋታ:-

🔸የምንጠቀማቸው የመብራት ብዛትና መብራቱን የምናበራበትና የምናጠፋበት መንገድ እንደ ክፍሎች ስፋት እና እንደሚሰጡት አገልግሎት ይለያያል። 🔸በዚህም መሰረት በብዛት የምንጠቀምባቸውና በጣም አስፈላጊ የሆኑትን እንዲሁም የትኛው ሰርኪዩት ለየትኛው ክፍል እንደምንጠቀም እናያለን

🔹1.1. አንድን አምፖል ከአንድ ቦታ በነጠላ ማብሪያ ማጥፊያ መቆጣጠር (Controlling a single Lamp from one position):-
🔸ከላይ ምስሉ ላይ እንደምናየው የምልክቶች ትርጉም በመፍቻው ተገልጿል።
🔸የመጀመሪያው ስዕል ላይአውት ሲሆን ሁለተኛው ዋየሪንግ ስዕል ነው።
🔸ዋየሪንግ ስዕሉ ላይ እንደምናየው ነጠላ ማብሪያ/ማጥፊያ 2 ተርሚናል ውይም ፒን ሲኖረው አንደኛው እሳት/phase ሲሆን ምልክቱም L ነው። ሁለተኛው ደግሞ ወጪ/ተመላሺ (Return)የምንለው ሲሆን ምልክቱም 1 ይሆናል።
🔸 ስለዚህ እሳቱ(P) በቀጥታ የማብሪያ/ማጥፊያው P ላይ ይታሰራል።
🔸የማብሪያ/ማጥፊያው ወጪ/ተመላሺ ደግሞ በየኤሌክትሪክ ሽቦ በቀጥታ የአምፖል ማቀፊያችን እንደኛው ጫፍ ላይ ይታሰራል።
🔸ውሃ(Neutral) በፍፁም ማብሪያ/ማጥፊያ ውስጥ አይገባም(❗️)።
🔸ውሃ(Neutral) በቀጥታ ከቆጣሪ ወይም ከከፊል ሀይል ማከፋፈያችን ወሰደን የአምፖላችን ማቀፊያ ሁለተኛው ጫፍ ላይ እናስረዋለን።
🔸አሁን አምፖላችን ገጥመን እጨርሳለን ማለት ነው።
🔹ነገር ግን የሰራነው ስራ ልክ መሆኑንና አለመሆኑን ሃይል ከመስጠታችን በፊት ማራጋገጥ አለብን(❗️)።
🔸የምንጠቀምበት ቦታም:-
🔘ለመታጠቢያ ክፍል/bath room
🔘ለመፀዳጃ ክፍል/Toilet room
🔘ለምግብ ማብሰያ ክፍል/kitchen
🔘ለማከማቻ ክፍል/Store room
ወዘተ ናቸው።

ይቀጥላል ......
🔹1.2. ሁለት አምፖሎችን ከአንድ ቦታ በነጠላ ማብሪያ/ማጥፊያ መቆጣጠር(Controlling two lamps from one position):-
🔸ከላይ በ1.1 ከተገለፀው ተመሳሳይ ሲሆን ልዩነቱ ሁለት አምፖል መሆኑ ብቻ ነው።
🔸 ስለዚህ መጀመሪያ እንዳየነው ሌላው ነግር ተመሳሳይ ሆኖ ለመጀመሪያው ከሰጠነው ሁለት ኤሌክትሪክ ሽቦዎች ላይ ሌላ ሁለት ገመዶች በመቀጠል ለሁለተኛው አምፖል መስጠት ነው።
🔸ለበለጠ መረጃ ከላይ ያሉትን ስዕሎች ይመልከቱ።
🔸አገልግሎቱም ከላይ የጠቀስናቸው በተለይ ማከማቻና የምግብ ማብሰያ ክፍሎች ሰፊ ከሆኑና አንድ መብራት በቂ ካልሆነ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ አምፖሎችን በነጠላ ማብሪያ/ማጥፊያ በመቆጣጠር መጠቀም እችላለን።

https://t.me/engineer03
https://t.me/engineer03
🔹1.3. አንድን አምፖል ከሁለት ያተለያዩ ቦታዎች በባለ ሁለት አቅጣጫ ማብሪያ/ ማጥፊያ መቆጣጠር (Controlling a Light bulb from two different locations Using SPDT Switches):-

🔸ከላይ ምስሉ ላይ እንደምናየው የምልክቶች ትርጉም ከታች ባለ መፍቻው ተገልጿል።
🔸የመጀመሪያው ስዕል ላይአውት ሲሆን ሁለተኛው ዋየሪንግ ስዕል ነው።
🔸ዋየሪንግ ስዕሉ ላይ እንደምናየው ባለሁለት አቅጣጫ ማብሪያ/ማጥፊያ 3 ተርሚናል ውይም ፒን ሲኖረው አንደኛው እሳት/phase ሲሆን ምልክቱም "L" ወይም "Com" ሊሆን ይችላል። ይህም ማለት ለመጀመሪያው ቀጥታ እሳቱ የሚገባበት ሲሆን ለሁለተኛው ማብሪያ ማጥፊያ ደግሞ ተመላሺ የምነለው ኤሌክትሪክ ሽቦ ቀጥታ ከአምፖል ጋር የሚገኛኝበት ነው።
🔸ቀሪዎቹ ሁለት ፒኖች ወጭ ሲሆኑ ዋየሪንግ ምስሉ ላይ እንደምናየው እናገናኛለን።
🔸ውሃ(Neutral) በቀጥታ ከቆጣሪ ወይም ከከፊል ሀይል ማከፋፈያችን ወሰደን የአምፖላችን ማቀፊያ ሁለተኛው ጫፍ ላይ እናስረዋለን።
🔸አሁን አምፖላችን ገጥመን እጨርሳለን ማለት ነው።
🔹ነገር ግን የሰራነው ስራ ልክ መሆኑንና አለመሆኑን ሃይል ከመስጠታችን በፊት ማራጋገጥ አለብን(❗️)።
🔸የምንጠቀምበት ቦታም:-
🔘ለመኝታ ክፍል/Bed room
🔘ለኤሌክትሪክ እቃዎች/Electrical Equipments
🔘ለደረጃ መብራት/ Stair lights
🔘ሁለት መግቢያና መውጫ በር ላላቸው ክፍሎች/Rooms having two entry and exit ወዘተ ናቸው
።


https://t.me/engineer03
🔹1.4. ሁለት አምፖሎችን ከአንድ ቦታ በ ሁለት ባለአንድ አቅጣጫ ማብሪያ/ማጥፊያ መቆጣጠር (Controlling two lamps from one location Independently):-

🔸በንዑስ ክፍል 4 ስለማብሪያ ማጥፊያ በሰፊው ተወያይተናል። ስለዚህ ወደኋላ ተመልሳችሁ አንብቡት።
🔸ይህ ማብሪያ ማጥፊያ 4 ተርሚናል አለው።
🔸ዋየሪንግ ስዕል ላይ እንደሚታየው L1 እና L2 ገቢ ሲሆኑ 1 እና 2 ደግሞ ወጪ /ተመላሺ ናቸው።
🔸 ለ L1 እና L2 ሁለት እሳት ወይም ገቢ መውሰድ አይጠበቅብንም ለአንዱ ገቢ ሰተን ከሁለተኛው ጋ ማገናኘት ነው።
🔸ለበለጠ መረጃ ከላይ ያሉትን ስዕሎች ይመልከቱ።
🔹 የምንጠቀምበት ቦታም:-
🔘ለበረንዳ መብራት/Balcony light
🔘ለምግብ ማብሰያ ክፍል/kitchen
🔘ለሳሎን ወይም ለትምህርት ቤት መብራቶች
🔘ለስቶር መብራትና ለመፀዳጃ ቤት መብራት ሁለቱ ተከታታይ ከሆኑ ወ.ዘ.ተ. ልንጠቀምበት እንችላለን።

https://t.me/engineer03
https://t.me/engineer03
🔹1.5. አንድን አምፖል ሶስት ቦታዎች ላይ መቆጣጠር (Controlling a light bulb from three locations):-

🔸በንዑስ ክፍል 4 ስለማብሪያ ማጥፊያ በሰፊው ተወያይተናል። ስለዚህ ወደኋላ ተመልሳችሁ አንብቡት።
🔸ይህ ሰርኪዩት ሁለት ባለ 2 አቅጣጫ ማብሪያ ማጥፊያ እና አንድ ባለ 4 አቅጣጫ ማብሪያ ማጥፊያ አካቷል።
🔸ዋየሪንግ ስዕሉ ላይ እንደሚታየው L ለመጀመሪያው ማብሪያ ማጥፊያ (SW-1) ገቢ ሲሆን ለሶስተኛው (SW-3) ደግሞ ወጭ/ተመላሺ ይሆናል።
🔸የመጀመሪያው ማብሪያ ማጥፊያ (SW-1) ተርሚናሎች 1 ና 2 ከ ባለ 4 አቅጣጫው ማብሪያ ማጥፊያ (SW-2) ሁለቱ ተርሚናሎች ጋ ይያያዛል።
🔸ቀሪዎቹ የባለ 4 አቅጣጫው ማብሪያ ማጥፊያ ሁለት ተርሚናሎች ደግሞ ከሶስተኛው(SW-3) 1ና2 ተርሚናሎች ጋ ይታሰራሉ።
🔸እንደተለመደው ውሃ(Neutral) ከጥታ አምፖሉ ጋ ይገባል።
🔸አሁን ከነዚህ ሶስት ማብሪያ ማጥፊያዎች የሚቀርበንን በመጠቀም ማብራትም ማጥፈትም እንችላለን።
🔸ለበለጠ መረጃ ከላይ ያሉትን ስዕሎች ይመልከቱ።
🔘የምንጠቀምበት ቦታም:-
🔹ለአዳራሽ መብራቶች
🔹ለመኪና ማቆሚያ ቦታ መብራቶች
🔹ለደረጃ መብራቶች ወ.ዘ.ተ. ልንጠቀምበት እንችላለን።
ማሳሰቢያ:- አንድና ከአንድ በላይ የሆኑ አምፖሎችን ከሁለት ቦታ በላይ መቆጣጠር ከፈለግን መሃል ላይ የፈለግነውን ያህል ባለአራት አቅጣጫ ማብሪያ ማጥፊያዎችን ተጠቅመን ዳርና ዳር ላይ ደግሞ ባለ ሁለት አቅጣጫ ማብሪያ ማጥፊያዎችን በመጠቀም የምንፈልገው ቦታ ድረስ መቆጣጥር እንችላለን።

https://t.me/engineer03
https://t.me/engineer03
Civil Engineering pinned «የሀንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ የመብራትና ማብሪያ/ማጥፊያ ፣የሶኬት፣ የደወል ወዘተ ዝርጋታዎችን ያጠቃልላል። ስለዚህ አንድ በአንድ እናያለን። 🔸የቻናላችን ቤተሰብ ለመሆን 👇 https://t.me/engineer03 "ለሌሎች ለውጥ ምክንያት እንሁን!" 🔸ለወዳጅዎም ያጋሩ! 🔹እናመሰግናለን!»
_*📌▪ _*📌▪Some important points related to Surveying▪*_

▪The *basic principle of surveying* working from whole to part

👉 Prevents accumulation of errors and localised minor errors

▪An Equilateral triangle is considered to be the best well conditional triangle
( 30° to 120° )

▪The best shape of triangle in triangulation is isosceles with base angle 56°14'

▪A good draftsman can plot a distance as small as a 0.25mm

▪ Control survey for fixing the points on the boundary

▪ land/Cadstral survey to measure the area of land ,
To Fix the legal boundaries and to locate the reference points

▪ Astronomical survey
Study about celestial body,
Determination of latitude and longitude.

▪ Archaeological survey
To Know The civilization of People.

👉The principle involved in chain survey is of triangulation

👉 Compass survey uses the principle of traversing . 

👉The principle of plane table survey is parallelism . 

👉The principle of Tacheometer is based on property of isosceles triangle, where ratio of the distance of the base from the apex and the length of the base is always constant .

*▪Least Count Of Surveying Instruments*

👉Prismatic Compass = 30'

👉 Surveyor Compass = 15'

👉 Total station= 1sec

👉Theodolite = 20"

👉 levelling Staff = 5mm

👉 Dummy level=5mm


*▪Important Points in surveying.*

👉Horizontal plane tangential to the level surface.

👉Level surfaces parallel to the mean spheroidal surface of the earth

👉RL of the line of collimation is known as the height of instrument

👉 Differential levelling also known as compound levelling or continuous levelling

👉Fly levelling is used to connect the benchmark to the starting point of alignment of any project

👉 Check levelling is the fly levelling done at the end of the days work to connect the point with starting point on that particular day to check the accuracy of the days work.


https://t.me/engineer03
በኮንስትራክሽን ውል የግንባታ መዘግየት ቅጣት/Liquidated damage/
------------- --------- ---------------

#በኮንስትራክሽን ውል ላይ የውሉ የግንባታ ስራ ተብሎ የተቀመጠውን በዲዛይኑ እና ዝርዝር ስቴስፊኬሽኑ መሰረት በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሰርቶ ማጠናቀቅ የተቋራጩ ሀላፊነት ነው፡፡

#ተቋራጩ የውሉን የግናባታ ስራ በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በወቅቱ ሰርቶ ያላጠናቀቀ እንደሆነ ከውሉ ማጠናቀቂያ ጊዜ/completion date/ በኋላ ግንባታው እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ ለእያንዳንዱ ቀን ተቋራጩ የግንባታ መዘግየት ቅጣት/Liquidated damage/ የመክፈል ሀላፊነት ይኖርበታል፡፡

#በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሲባል ምን ማለት ነው? አንዳንድ አሰሪዎች/client/ በግንዛቤ እጥረት በውሉ ላይ የተቀመጠው ተቋራጩና አሰሪው ለግናባታው ማጠናቀቂያ የተስማሙበትን የቀን ብዛት/የጊዜ እርዝማኔ/ መቆጠር የሚጀምረው ውሉ በግራ ቀኙ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ እንደሆነ ይረዱታል፡፡ይሄ አረዳድ ስህተት ነው፡፡

#በኮንስትራክሽን ውል ስለ ጊዜ አቆጣጠር በተለይ የግንባታ ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ ፣ሞቢላይዜሽን ፔሬድ/mobilization period/፣የሳይት ርክክብ/site handover/፣ የስራ መጀመሪያ ቀን/commencement date/ እና የስራ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ የሚሉትን መረዳት የግንባታ መዘግየት ቅጣት/Liquidated damage/ የሚለውን በአግባቡ ለማወቅ ይጠቅማል፡፡

#በመሰረቱ በውሉ የተቀመጠው የስራ ማከናወኛ የጊዜ ገደብ መቆጠር የሚጀምረው ተቋራጩ የግናባታውን ሳይት ከአሰሪው ከተረከበ በኋላ ነው፡፡ይሄውም ከሳይት ርክክብ በኋላ የስራ መጀመሪያ ቀን /commencement date/ በመሀንዲሱ የሚወሰን እና ለተቋራጩ የሚገለጽለት ይሆናል፡፡

#እንግዲህ ከዚሁ በመሀንዲሱ ከሚወሰነው የስራ መጀመሪያ ቀን ጀምሮ በውሉ ላይ የተቀመጠው ቀን ይቆጠርና የስራ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ መቸ እንደሆነ ለማወቅ ያስችላል ማለት ነው፡፡

#እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ነገር በኮንስትራክሽን ውሉ ላይ የተወሰነውን የስራ ክፍል ከውሉ የማጠናቀቂያ ጊዜ አስቀድሞ ለማጠናቀቅ ውል ሊደረግ የሚችልበት እድልም አለ፡፡/part work completion/ ማለት ነው፡፡የቀን አቆጣጠሩ ከላይ እንደተብራራው የሚሰላ ይሆናል፡፡

#ስለሆነም የግንባታ መዘግየት ቅጣት የሚለው ጉዳይ የሚመጣው ተቋራጩ የውሉን የግንባታ ስራ በውሉ ስራ የማጠናቀቂያ ጊዜ /completion date/ ሳያጠናቅቅ የቀረ እንደሆነ ነው፡፡የገንዘብ ቅጣቱ የሚጣለው በተቋራጩ ላይ ነው፡፡ተቋራጩ ግንባታውን ላዘገየበት ለእያንዳንዱ ቀን በውሉ የተቀመጠውን የግንባታ መዘግየት ቅጣት የሚከፍል ይሆናል፡፡በነገራችን ላይ እየተቀጡ መስራት ለተቋራጩ መብትም ጭምር ነው፡፡ይህ ማለት አሰሪው የውሉ ማጠናቀቂያ ጊዜ ስላለቀ ውል አቋርጣለሁ ማለት አይችልም፡፡በውሉ ላይ የተቀመጠው የመዘግየት ቅጣት ጣሪያ መጠን ከሞላ በኋላ ግን አሰሪው ውል ማቋረጥ ይችላል፡፡ውል ከተቋረጠ በኋላ የመዘግየት ቅጣት የሚባል ነገርም የለም፡፡

#ሌላው ተቋራጩ ወደ መዘግየት ቅጣት እንዲገባ ከመደረጉ አስቀድሞ በአግባቡ መረጋገጥ ያለበት ነገር መሀንዲሱ ለተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ/time extension/ ፈቅዷል ወይስ አልፈቀደም የሚለው ነጥብ ነው፡፡ምክንያቱም ለተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ ተፈቅዶለት ከሆነ የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜውም አብሮ ስለሚራዘምና ቀኑ ስለሚቀየር ነው፡፡

#የሀገራችንን የህግ ማእቀፍ በዚህ ረገድ ምን ይላል? የሚለውን ለመመለስ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1887 እስከ 1895 ድረስ የተደነገጉትን መዳሰስ ይጠይቃል፡፡
*በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1889 ላይ ተዋዋዮች በውላቸው ምናልባት አንደኛው ወገን እንደውሉ ግዴታውን ያልፈጸመ እንደሆነ ወይም አጓድሎ የፈጸመ እንደሆነ ወይም አዘግይቶ የፈጸመ እንደሆነ የሚከፍለውን የመቀጮ መጠን አስቀድመው በውላቸው ለመወሰን እንደሚችሉ በሚፈቅድ መልኩ ተደንግጓል፡፡እዚህ ላይ የውል ግዴታን አዘግይቶ መፈጸም ስለሚያስከትለው ቅጣት የሚዋዋሉት በተለይ የግንባታ መዘግየት ቅጣት/liquidated damage/ የሚመለከት ይሆናል፡፡

*የመዘግየት ቅጣት ስምምነት ባለ ጊዜ አሰሪው የውሉ ስራ እንዲፈጸምና የቅጣት ገንዘቡንም ለመቀበል መብት እንደሚኖረው የፍ/ህ/ቁ 1890(2) ይደነግጋል፡፡እንደዚሁም አሰሪው ኪሳራ ባይደርስበት እንኳ የመዘግየት ቅጣት ገንዘቡ ሊከፈለው እንደሚገባ የፍ/ህ/ቁ 1892(1) ይደነግጋል፡፡እንግዲህ ተቋራጩ ግንባታውን በወቅቱ ያላጠናቀቀው አሰሪውን ሆነ ብሎ ለመጉዳት አስቦ ጉልህ በሆነ ቸልተኝነት ወይም በከባድ ጥፋት መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ አሰሪው በውሉ ከተቀመጠው የቅጣት ገንዘብ በላይ በደረሰበት ትክክለኛ ጉዳት መጠን ልክ ከተቋራጩ ላይ ኪሳራ ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህ/ቁ 1892(2) ይደነግጋል፡፡

*ሌላው የመዘግየት ቅጣት መጠን በዳኞች ሊቀነስ የሚችልበት እድል ስለመኖሩ የፍ/ህ/ቁ 1893 ይደነግጋል፡፡ይሄውም ተቋራጩ ግዴታውን በከፊል የፈጸመ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ይህ ማለት ተቋራጩ ባከናወነው ስራ ሁሉ ቅጣት የሚጣልበት አይሆንም ማለት ነው፡፡

*በዚህ ረገድ በሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ አንቀጽ 47(1) ላይ ተቋራጩ ስራውን በውሉ የማጠናቀቂያ ጊዜ ካላጠናቀቀ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ቀን የውሉን ዋጋ 1/1000 እንደሚከፍል እና ይሄውም አጠቃላይ መጠኑ ከውሉ ዋጋ ከ20% መብለጥ እንደማይችል ይደነግጋል፡፡ሆኖም ግን በከፊል ለተከናወነው ስራ መሀንዲሱ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት በሰጠ ጊዜ የቅጣቱ መጠን የሚሰላው ባልተከናወነው ስራ መጠን ዋጋ ላይ በመመስረት ይሆናል ማለት ነው፡፡

#በመጨረሻም የመዘግየት ቅጣት በኛ ሀገር ከላይ እንዳየነው እንደቅጣት የሚቆጠርና በህጉ ቅጣቱ እውቅና የሚሰጠው ሲሆን በኮመን ሎው የህግ ስርአት ግን ቅጣት አይደለም፡፡በኮመን ሎው ሊኩዴትድ ዳሜጅ በአሰሪው ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋር እኩል ሆኖ መመዛዘን የሚኖርበት ሲሆን የቅጣት አይነት ባህሪ ካለው ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡

ሰኔ 21/2012 ዓ/ም
#share
https://t.me/engineer03
https://t.me/engineer03


@Civil_Enginering_bot