Civil Engineering
1.37K subscribers
1.26K photos
20 videos
962 files
674 links
*ለሲቪል ; ለአርክቴክቶች÷ለኮንስትራክሽን ÷ ለሀይድሮሊክ መሀንዲሶች እና ተማሪዎች የተዘጋጀ ትምህርታዊ ቻናል ፡፡

@engineer03


http://www.Indiabix.com በዚህ ደግሞ ማንኛውንም ጥያቄና መልስ ታገኛላችሁ!

╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕
Download Telegram
Con'd......


▶️በመጨረሻም.... @engineer03
.
*መንግስት ጊዜ መፍጀት ሳያስፈልገው የፍትሀብሄር ስነስርአት ህጉ አንቀጽ 315 ድንጋጌን በማስተካከል የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በግልግል እንደማይታዩ የሚደነግገውን እንዲያሻሽለው ለመጠቆም እወዳለሁ፡፡
*በሀገራችን 80 በመቶ የሚሆነው ግንባታ በመንግስት አሰሪነት የሚከናወን እንደመሆኑ እና አለማቀፉን የአርቢትሬሽን ውሳኔ ማስፈጸሚያ ኮንቨየንሽን ለማጽደቅ እየተንቀሳቀስን ባለንበት ሁኔታ የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በአማራጭ የግጭት መፍቻ መንገድ እንደማይፈቱ የሚደነግገውን የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 315 ባለበት ማስቀጠል አስፈላጊ አይደለም፡፡
*ከዚህ ጋር በተያያዘ በጣና ውሀ ጉድጓድ ቁፋሮ እና ድሬዳዋ አስተዳደር ውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን መካከል በሰ/መ/ቁ 127459 በቀን መስከረም 23/2010ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው አስገዳጅ ውሳኔም መታየት አለበት፡፡ይዘቱም የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 315(2) የአስተዳደር ውልን አስመልክቶ የሚነሳ አለመግባባትን ለመዳኘት የማይችለ ው የግልግል ዳኝነት አካል ወይም አርቢትሬተር ነው ይላል፡፡አርቢትሬተር የአስተዳደር ውሎችን እንዳይዳኝ በህግ ክልከላ ከተደረገበት አላማ አንጻር አጁዲኬተርም ሊፈቀድለት አይገባም ምክንያቱም የሁለቱም ውሳኔአቸው አስገዳጅነት ያለው ስለሆነ እና ከመደበኛ ፍርድ ቤት ውጭ አለመግባባት የሚፈታባቸው ናቸው ይላል፡፡ስለዚህ በዚህ ውሳኔ መሰረት የአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ውል ጉዳይ በግልግል ዳኝነት አይታይም ማለት ነው፡፡ይህ ውሳኔ ተራማጅ የሆነውን አማራጭ የሙግት መፍቻ መንገድ በአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች ጉዳይ ተፈጻሚ እንዳይሆን በማድረግ ምእራፉን የዘጋ ነው፡፡
*ስለሆነም ምእራፉ የተዘጋው አማራጭ የሙግት መፍቻ መንገድ ተፈጻሚነት ዳግም እንዲነሳ እና ከአለማቀፉ እድገትና ዝማኔ ጋር መራመድ እንችል ዘንድ መንግስት የኒውዮርክ ኮንቨየንሽንን ለማጽደቅ በጀመረው አግባብ ጎን በጎን የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 315(2) እና በሰ/መ/ቁ 127459 በቀን መስከረም 23/2010ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ(ህግ ስለሆነ) የህግ ማእቀፉን ሊያስተካክለው ይገባል፡፡
.
http://t.me/engineer03
👉በኮንስትራክሽን ውል የስራ ለውጥ/Variation. @engineer03
============ =============
▶️ቫሬሽን/variation/ ምን አይነት ትርጉም ሊሰጠው ይችላል?
*በኮንስትራክሽን ውል የስራ ለውጥ(variation) የሚባለው በዋናነት የግንባታ ስራ ጥራትን፣መጠን፣ዲዛይን፣የግንባታ ቁሳቁስ፣የስራ ጊዜ፣የግንባታ ማከናወኛ ቦታ መጠን የመሳሰሉትን የማሻሻል፣የመጨመር ወይም የመቀነስን የሚመለከት የኮንስትራክሽን ውል መሰረታዊ ነጥብ ነው፡፡
*ስለዚህ ቫሬሽን የዋናውን የኮንስትራክሽን ውል ይዘት/object of the contract/ በመጠኑ የመለወጥ ባህሪ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡
*PPA 2011 ክሎስ 15.1 ይሄንኑ አረዳድ በሚያጠናክር ሁኔታ ለቫሬሽን ትርጉም ይሰጠዋል፡፡
▶️ቫሬሽን ኦርደር/variation order/ የሚባለውስ ምንድን ነው? ማነው ኦርደር ሰጭው? በቃል ኦርደር መስጠት ይቻላል? በምን አይነት መልኩ ነው ትእዛዝ የሚሰጥ? በዚህ ረገድ ህጉ ምን ይላል?
*ቫሬሽን ኦርደር ከመሀንዲሱ ለተቋራጩ በጽሁፍ የሚሰጥ የስራ ለውጥ ትእዛዝ ነው፡፡
*አማካሪ መሀንዲሱ ለግንባታ ስራው መልካም አፈጻጸም ሲባል የስራ ለውጥ ትእዛዝ አስፈላጊ ነው ብሎ ካመነ ትእዛዝ መስጠት ይችላል፡፡
*በመጀመሪያ ግን በአማካሪ መሀንዲሱ አማካይነት ለተቋራጩ ስለለውጥ ስራው ባህሪና ምንነት ማሳወቂያ/ኖቲስ/ እንዲደርሰው ይደረጋል፡፡ኖቲስ እንደደረሰው ተቋራጩ የለውጥ ስራውን አስመልክቶ ትሮፖዛል ያቀርባል፡፡ፕሮፖዛሉም የጊዜ ማራዘሚያ/ስኬጁል፣የዋጋ ሁኔታን የሚያካትት ይሆናል፡፡(PPA 15.3)
*የስራ ለውጥ ትእዛዝ በጽሁፍ ነው መደረግ እንዳለበት PPA 2011 ክሎስ 15.2 ያስቀምጣል፡፡አንዳንዴ ግን አማካሪ መሀንዲሱ በቃል የቫሬሽን ትእዛዝ መስጠት እንደሚችል PPA 2011 ክሎስ 15.2(a) ላይ ፈቃጅ ሆኖ ተቀምጧል፡፡ ነገር ግን በቶሎ የለውጥ ስራ ትእዛዙ ወደ ጽሁፍ መቀየር ይኖርበታል፡፡
እዚህ ጋር አብሮ የሚታየው ነገር የአስተዳደር መስሪያ ቤት ጋር የሚደረጉ ውሎች በጽሁፍ መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡ይሄውም ስለውሎች በጠቅላላው በሚመለከተው የውል ህግ አንቀጽ 1724 ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡
*አንድ ውል የሚሻሻለው ደግሞ ከመጀመሪያው ውል ጋር ተመሳሳይ በሆነ ፎርም ነው፡፡በዚህ ረገድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1722 ላይ "ዋናውን ውል የመለወጥ ጉዳይ ለዚሁ ውል በተደነገገው አጻጻፍ(ፎርም) መሰራት አለበት፡፡" በሚል የተደነገገው የሚያስገነዝበውም ቫሬሽን ዋናውን ውል በከፊል የመለወጥ ሁኔታ ስለሚኖረው ከዋናው የኮንስትራክሽን ውል ጋር በተመሳሳይ የአጻጻፍ ፎርም በጽሁፍ መደረግ ይኖርበታል ማለት ነው፡፡ለዚህ ነው በመርህ ደረጃ ቫሬሽን በጽሁፍ መደረግ አለበት የሚባለው፡፡
▶️የስራ ለውጥ ውል/change agreement/ ምን ማለት ነው? ከህግ አንጻር በዚህ ረገድ ምን ነጥቦች ሊነሱ ይችላሉ?
*PPA 2011 ክሎስ 15.9 ላይ እንደተቀመጠው በየስራ ለውጥ ውል የሚባለው ከቫሬሽን ኦርደር በኋላ አሰሪው/ተወካይ መሀንዲሱ እና ተቋራጩ በጽሁፍ የሚስማሙበት የማሻሻያ ውል ነው፡፡ ሆኖም በዚህ የፒፒኤ ትርጉም ጸሀፊው አይስማማም፡፡ምክንያቱም አማካሪው ስራ ለመቆጣጠር እንጅ ውል ለመዋዋል በአማካሪነት ውሉ ላይ ብዙ ጊዜ ስልጣን አይኖረውም፡፡በተቋራጭና አሰሪ መካከል የተደረገ የኮንስትራክሽን ውል በአሰሪና ተቋራጭ በሚደረግ ስምምነት/ውል ሊሻሻል ከሚችል በስተቀር አማካሪ መሀንዲሱን ውል እንዲዋዋል እስከመፍቀድ የሚደርስ ትርጓሜ መሰጠቱ ተገቢነት የለውም፡፡
*የስራ ለውጥ ውሎች ቀን፣ቁጥርና ቅደምተከተል ይሰጣቸዋል፡፡(ፒፒኤ15.10)
*ሌላው የስራ ለውጥ ውል ወደኋላ ሄዶ እንደማይሰራና ውሉ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ብቻ አስገዳጅ እንደሚሆን PPA 2011 ክሎስ 15.10 ላይ ተቀምጧል፡፡
▶️በቫሬሽን የተሰሩ ስራዎች የዋጋ አወሳሰን/Valuation of variation/ በምን ሁኔታ ይከናወናል?
*የተሰራው ተጨማሪ ስራ ከሆነ እና በቢል ኦፍ ኳንቲቲ ላይ ዋጋ ተተክሎለት ካለ በዚያው የዋጋ ሬት የሚሰላ እንደሚሆን PPA 2011 ክሎስ 15.5(a) ላይ ተቀምጧል፡፡
*በቫሬሽን የሚሰራው ስራ በቢል ኦፍ ኳንቲቲ ያልተካተተ አዲስ የስራ አይተም ከሆነ በመሀንዲሱና ተቋራጩ በስምምነት በወቅታዊ ዋጋ የሚሰላ እንደሚሆን PPA 2011 ክሎስ 15.5(b) ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡
*በቫሬሽን የተካተተው የስራ አይተም ዋጋው በቢል ኦፍ ኳንቲቲ ላይ የተካተተ ቢሆን እንኳ የተጋነነ ከሆነ በመሀንዲሱ ሊስተካከል እንደሚችል ደግሞ PPA 2011 ክሎስ 15.5(c) ይገልጻል፡፡
*ቫሬሽኑ የተከሰተው በተቋራጩ ጥፋት ከሆነ ደግሞ በአሰሪው ለተቋራጩ ዋጋ አይከፈልበትም በሚል PPA 2011 ክሎስ 15.5(d) በግልጽ አስቀምጦታል፡፡
▶️ቫሬሽን እስከስንት ፐርሰንት ይፈቀዳል? በፍርድ ቤቶች አካባቢ ያለው የህጉ አረዳድስ ምን ይመስላል?
*የቫሬሽኑ መጠን ከ25% በላይ በሆነ ጊዜና ከተቋራጩ ጥፋት ባልሆነ ሁኔታ የተከሰተ ከሆነ አማካሪ መሀንዲሱ ስለብልጫው መጠንና ስለዋጋው ከአሰሪው መስሪያ ቤት ጋር በመመካከር ይወስናል በሚል PPA 2011 ክሎስ 15.7 ላይ ተቀምጧል፡፡
የቫሬሽን መጠን ከመጀመሪያው ዋጋ ከ30% በላይ መብለጥ እንደሌለበት በአስገዳጅ ሁኔታ PPA 2011 ክሎስ 15.8 ላይ ተቀምጧል፡፡
*በዚህ በጀኔራል ኮንዲሽን ከተቀመጠው ተርሰንት/ከገደቡ በላይ በቫሬሽን ስራ ተሰርቶ ቢገኝስ ምን ይሆናል? እንግዲህ በዚህ ረገድ ጀኔራል ኮንዲሽኑም ሆነ አግባብነት ያለው የግዥ አዋጅና መመሪያ ግልጽ ምላሽ አያስቀምጥም፡፡ ሆኖም ግን ተቋራጩ ስራውን እስከሰራው ድረስ አሰሪው አላግባብ በተቋራጩ ድካምና ገንዘብ በልጽጐ እንዲቀር ፈቃጅ ህግ ሊኖር አይችልም፡፡ፍትሀዊም አይሆንም፡፡
*ስለዚህ በዚህ ረገድ በአማካሪ መሀንዲሱ እውቅና እና ትእዛዝ በቫሬሽን ለተሰሩ ስራዎች ከገደቡ በላይ ያለፈ ቢሆንም እንኳ አሰሪው ለተቋራጩ ሊከፍለው እንደሚገባ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በ5ዳኞች እንደህግ በሚቆጠር ሁኔታ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡ ይሄውም አስገዳጅ ውሳኔ በሰ/መ/ቁ 71972 ቅጽ 14 ገጽ 25 ላይ ይገኛል፡፡
▶️ቫሬሽን ከሙስና ጋር ምን ያገናኘዋል?
*በዚህ ረገድ የኢፌዴሪ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የኪራይ ሰብሳቢነት መንስኤዎችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች በሚል በመስከረም 2010ዓ.ም ባዘጋጀው የውይይት ሰነድ ላይ ቫሬሽን ለሙስና አንዱ ምንጭ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
*ይሄውም ለምሳሌ ያህል የማይጣጣሙ ዲዛይኖችና የስራ ዝርዝር መኖር አንዱ ነው፡፡
*ሌላኛው ደግሞ ሆነ ብሎ የስራ ዝርዝር መዝለል/omission of work item/ ነው፡፡
▶️በአይነቱ አዲስ የሆነ ተጨማሪ ስራ/unrelated and new item of additional work/ ሲያጋጥምስ በየትኛው ህግ የሚታይ ይሆናል?
*በመርህ ደረጃ አሰሪው መስሪያ ቤት በውል ውስጥ የሌሉትን ስራዎች በአዲስ ዋጋ እንዲሰራቸው ስራ ተቋራጩን ለማዘዝ እንደሚችል በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3284(1) ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Con'td....

*ሆኖም ግን በአንቀጽ 3284(2) ላይ በአስገዳጅና በልዩ ሁኔታ እንደተቀመጠው አሰሪ መስሪያ ቤቱ በውሉ ከተመለከተው ስራ ፍጹም ልዩ የሆነና ወይም ከዚሁ ስራ ጋር ግንኙነት የሌለውን ስራ እንዲሰራ ስራ ተቋራጩን ሊያዘው አይችልም፡፡ይህ ማለት እንደዚህ አይነት ትእዛዝ ባጋጠመው ጊዜ ስራ ተቋራጩ የመቃዎም መብት ይኖረዋል ማለት ነው፡፡
▶️PPA 2011,FIDIC, MoWUD 1994 እና ሌሎች ጀኔራል ኮንዲሽኖች ህግ ናቸው ወይስ?ታዲያ እንዴት ነው አስገዳጅ የሚሆኑት?
*ጀኔራል ኮንዲሽኖች በሙሉ ህግ አይደሉም፡፡ ምክንያቱም አዋጅ፣ደንብ ወይም መመሪያ አይደሉም፡፡
*ሆኖም በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1731 ላይ ውል በተዋዋዮች መካከል እንደህግ ይቆጠራል በሚል በግልጽ ተደንግጓል፡፡ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ደግሞ በኮንስትራክሽን ውሎች እንደ አንድ የውል አካል ሁነው ይካተታሉ፡፡ ስለዚህ በኮንስትራክሽን ውል ውስጥ የውል አካል ሆኖ የተካተተ ጀኔራል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ውሉን በተዋዋሉት አሰሪና ተቋራጭ መካከል እንደ ህግ ሆኖ ያገለግላል ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ተዋዋይ ያልሆኑ ወይም ጀኔራል ኮንዲሽኑን በውላቸው ያላካተቱ አካላትን ግን አያስገድዳቸውም ማለት ነው፡፡
▶️በአጠቃላይ @ETCONp
*በኮንስትራክሽን ውል አተገባበር ሂደት የስራ ለውጥ/ቫሬሽን/ አብዛኛውን ጊዜ መከሰቱ አይቀሬ ነው፡፡ቫሬሽንን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡
*እንዲሁም ቫሬሽን ብዙ ጊዜ በአሰሪና በተቋራጭ መካከል ለግጭትና ለውል መቋረጥ መነሻ ሲሆን ይታያል፡፡ ምክንያቱም ቫሬሽንን በአግባቡ በውል መቆጣጠር ካልተቻለ በውሉ የግንባታ ስራ ላይ የማጠናቀቂያ ጊዜ መዘግየትን እና የግንባታ ወጭ የመጨመርን ያስከትላል፡፡ ይሄውም ከውጤት አንጻር አሰሪውንም ሆነ ተቋራጩን የሚያስከፋ መሆኑ እና ወደ አለመግባባት ማምራቱ አይቀሬ ይሆናል፡፡
*ብዙውን ጊዜ በኛ ሀገር የተለመደው የኮንስትራክሽን ውል አይነት Design bid build(DBB) መሆኑ ነው እንጅ በኢትዮጽያ መንገዶች ባለስልጣን አልፎ አልፎ ጥቅም ላይ እንደሚውለው Design build(DB) የውል አይነትን ተግባራዊ ማድረግ የሚቻልበት አሰራር ቢኖር የተሸለ ነው፡፡ምክንያቱም በ Design build(DB) ፕሮጀክቶች አሰሪው በልዩ ሁኔታ ፈልጐት ማሻሻያ ካላደረገ በስተቀር ቫሬሽንን በጣም መቀነስ ያስችላል፡፡
*ስለዚህ የቫሬሽን ጉዳይ የህግ ማእቀፉን በአግባቡ መረዳትና ክፍተቶችን ለይቶ አሰሪና ተቋራጭ እንዲሁም የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ብሎም ሌሎች የኮንስትራክሽን ህግ ባለሙያዎችን እና ችፍ ኢንጅኒየሮችን በማሳተፍና በማወያየት ህጉን እና PPA 2011 ጀኔራል ኮንዲሽኑን በየጊዜው ማዘመን አስፈላጊ ነው፡፡
*ከተቻለ ደግሞ በፍትሀብሄር ህግ፣በህንጻ አዋጅ፣በግዥ አዋጅና መመሪያ እንዲሁም በጀኔራል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ተበታትነው የሚገኙ የኮንስትራክሽን ውል ህግ ጉዳዮችን በማጠቃለል ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም እንደመነሻ ሆኖ የሚያገለግል ደረጃውን የጠበቀ የኮንስትራክሽን ኮድ/Construction code/ የሚዘጋጅበት ሁኔታ ቢኖር ትልቅ ለዘርፉ እድገት አጋዥ ይሆናል የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡
*በተጨማሪም ሀገራችን COMESA አባል እንደመሆኗ፣WTO ለመቀላቀል እንቅስቃሴ ላይ እንደመሆኗ እና የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ለመመስረት እንቅስቃሴዎች የተጀመሩ እንደመሆኑ የቀጠናውን ነጻ የገበያ ውድድርን አሸንፈው ለዜጐችም ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥሩ ግዙፍና ተወዳዳሪ መንግስታዊ እና የግል ተቋራጭ ድርጅቶች ከወዲሁ ሊኖሩን ይገባል፡፡ስለዚሁም መንግስት ተቋራጮችን በመደገፍ ማብቃት ይኖርበታል ::

http://t.me/engineer03
#Bahirdar International stadium,Ethiopia
roof cover ሊሠራ ጫራታ ላይ ወጣ
ውብ ምሽት
👉በኮንስትራክሽን ውል አሰሪው የተቋራጩን ክፍያ አዘግይቶ መክፈል ጉዳይ /Delay payment/
------------- ---------------
▶️የኮንስትራክሽ ውል መሰረታዊ ባህሪው ሲታይ በዋናነት አሰሪና ተቋራጭን በተዋዋይነት የሚይዝ ሲሆን ጉልህ የሆነው ግዴታቸው ሲታይ ደግሞ ተቋራጩ በውሉና ዲዛይኑ/ስፔስፊኬሽኑ መሰረት ግንባታውን የማከናወን ሀላፊነት የሚኖርበት ሲሆን ክፍያ የመክፈል ጉዳይ ደግሞ ለአሰሪው ዋናውና ትልቁ ግዴታው ነው፡፡የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2610፣3019እና 3020 እንዲሁም 3244 ተገናዝቦ ሲታይ ይሄን ሁኔታ ያስገነዝባል፡፡
*የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020(1) ላይ "ሁለቱ ወገን ተዋዋዮች ስለሚፈጽሙት ስራዎችና ስለዋጋው ካልተስማሙ በቀር የተቋራጭነት ውል አለ አይባልም" በሚል የተደነገገው በኮንስትራክሽን ውል ለተቋራጩ የሚከፈለው ክፍያ ጉዳይ የውሉ መሰረታዊ ነጥብ መሆኑን የሚጠቁም ነው፡፡ ስለክፍያ አይነቶች የህጉን ጉዳይ ወደፊት በሌላ ጽሁፍ የምናየው ይሆናል፡፡
*አሰሪው ለተቋራጩ ክፍያ የመክፈሉን ሁኔታ ያለበቂ ምክንያት ማዘግየት አይችልም፡፡
*አማካሪ መሀንዲሱ በተለይ ከተቋራጩ የክፍያ ጥያቄ በቀረበለት ጊዜ የማረጋገጥና የማጽደቁን ስራ በ7(ሰባት) ቀናት ውስጥ የማጠናቀቅ ግዴታ አለበት፡፡(የመመሪያው አንቀጽ 28.5(d)
*አሰሪው መስሪያ ቤት ደግሞ በአማካሪ መሀንዲሱ የጸደቀ የክፍያ ሰርተፍኬት በደረሰው በ14(አስራ አራት) ቀናት ውስጥ ለተቋራጩ ክፍያ የመፈጸም ግዴታ አለበት፡፡(የመመሪያው አንቀጽ 28.5(e)
*አማካሪ መሀንዲሱ በተቋራጩ የቀረበውን የክፍያ ጥያቄ በሰባት ቀናት ውስጥ የማረጋገጥና የማጽደቅ ስራ ባይፈጽም ምን ውጤት ይኖረዋል?
*በዚህ ረገድ የመመሪያው አንቀጽ አንቀጽ 28.5(f) ግልጽ ምላሽ አስቀምጧል፡፡
*ይሄውም ተቋራጩ በዚህ ምክንያት ከአሰሪው ላይ ተጨማሪ ክፍያ/additional payment/ የጠየቀ እንደሆነ አማካሪ መሀንዲሱ ይህን ተጨማሪ ክፍያ የመሸፈን ግዴታ ይኖርበታል፡፡
*ሆኖም ግን አማካሪ መሀንዲሱ ለሚሰጠው አገልግሎት ከሚከፈለው ክፍያ በላይ የሆነ ክፍያ ለመክፈል ሀላፊነት አይኖርበትም፡፡
*በዚህ ረገድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2636 የአማካሪ መሀንዲሱን የእውቀት ስራ ውል ግዴታ ይደነግጋል፡፡ይሄውም አማካሪው "የኪነ ጥበብን ደንቦች በማፍረስ ጥፋት ጥፋት ካላደረገ በቀር በአሰሪው በኩል ስራ ተቋራጩን ሀላፊነት አይነካውም" በሚል ተቀምጧል፡፡(2636(2)) እንደዚሁም አማካሪው ሳይሰራ ከመቅረቱ የተነሳ ወይም በአሰሪው ላይ ጉዳትን የሚያመጣ ስራ ያደረገ እንደሆነ አጥፊ ነው ለመባል እንደሚችል የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2636(3) ይደነግጋል፡፡ ስለዚህ አማካሪው ክፍያ የማረጋገጥ እና የማጽደቅ ስራውን በህጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ባለማከናወኑ አሰሪው ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍል በተቋራጩ የተጠየቀ እንደሆነ አማካሪው አጥፊ ነው ሊባል ያስችለዋል ማለት ነው፡፡
*አሰሪው በአማካሪው የጸደቀው የክፍያ ሰርተፍኬት በደረሰው በ14 ቀናት ውስጥ ለተቋራጩ ክፍያ ባይፈጽም ምን ውጤት ይኖረዋል?
*አሰሪው ያለበቂ ምክንያት ክፍያ ያዘገየ እንደሆነ ለተቋራጩ ተጨማሪ ክፍያ/additional payment/ ለመክፈል ሀላፊነት እንደሚኖርበት የፌዴራል የግዥ መመሪያ/Federal public procurement directive/ አንቀጽ 28.5(g) ይደነግጋል፡፡
*ተጨማሪ ክፍያ ሲባልስ ምንን ያጠቃልላል? የሚለው ሲታይ በዋናነት ወለድ የመክፈል ሀላፊነትን የሚመለከት ይሆናል፡፡በዚህ ረገድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3268 ተቋራጩ መክፈልን በማዘግየት የሚታሰበውን ወለድ እንዲያገኝ መብት ይሰጠዋል፡፡የወለዱ መጠንም በውል ያልተወሰነ የሆነ እንደሆነ በአንቀጽ 1751 መሰረት ህጋዊ ወለድ በአመት 9(ዘጠኝ) በመቶ ሆኖ የሚሰላ ይሆናል፡፡
*ሌላው እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ነጥብ ተዋዋዮች በውላቸው ላይ ክፍያን ማዘግየት የሚኖረውን ውጤት አስመልክቶ የቅጣት ስምምነት/penality clause/ ያካተቱ ከሆነ የፍትሀብሄር ህጉ አንቀጽ 1889 እና ተከታዮቹ ድንጋጌ እውቅና ስለሚሰጠው እና በአንቀጽ 1731 መሰረት ውል በተዋዋዮች መካከል እንደ ህግ ስለሚቆጠር ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡
*አንዳንድ ክልሎችም በዚህ ረገድ በግዥ መመሪያቸው ላይ ዝርዝር ውጤቱን ያስቀምጣሉ፡፡
*አሰሪው ክፍያ በወቅቱ ባለመፈጸሙ ምክንያት ከወለድ ባለፈ ሌላም ጉዳት የደረሰበት ተቋራጭስ ከጉዳቱ ጋር እኩል የሆነ ኪሳራ ሊከፈለው አይገባም ወይ? የሚል ጥያቄም ሊነሳ ይችላል፡፡ምክንያቱም የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2091 እና 1790(2) ለደረሰው ጉዳት ሀላፊ መሆኑ በህግ የታወቀ ሰው የሚከፍለው የጉዳት ካሳ ሀላፊነቱን ያመጣው ጉዳይ በተበዳዩ ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋር እኩል ሆኖ መመዛዘን አለበት በሚል በግልጽ ይደነግጋል፡፡
▶️በአጠቃላይ አሰሪው በማናቸውም ምክንያት የተቋራጩን ክፍያ በሚያዘገይበት ጊዜ ተቋራጩን ለውድቀት የማጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው፡፡ምክንያቱም በሀገራችን አብዛኛው ተቋራጭ ድርጅት የፋይናንሽያል ማኔጅመንት ስርአት የለውም፡፡ተቋራጮቻችን የገንዘብ አቅማቸውም ደካማ ነው፡፡አብዛኛው ተቋራጭ ለአንዱ ፕሮጀክት የሚወስደውን የቅድሚያ ክፍያ ሌላ ፕሮጀክት ላይ ይጠቀምበታል፡፡በዚህ ምክንያት አንድ ተቋራጭ ሲከስር ብዙ ሰራተኛ እንደሚበተን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ስለዚህ በአሰሪዎች በኩል ተቋራጮች የሰሩበትን ክፍያ በወቅቱ እና በተሰራው ስራ ልክ አንዲከፈላቸው ለማድረግ እና በህጉ የተቀመጠው የክፍያ የጊዜ ገደብ እንዲከበር ጠንከር ያለ አቋም ወስዶ መስራት ይጠበቅበታል፡፡
፡
https://t.me/engineer03
Civil Engineering
Photo
የአዲስ አበባ ከተማ ልዩ መገለጫ ይሆናል የተባለው የመሶብ ታወር ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር ተነግሯል!

የመሶብ ታወር ሥራ አስኪያጅ አቶ ፀጋዬ ተክሉ እንደተናገሩት ከዓመት በፊት በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ይፋ የተደረገው የመሶብ ቅርጽ ያለው ታወር ግንባታው ከመጪዎቹ አራት ወራት በኋላ ይጀመራል።

እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለጻ ፕሮጀክቱ ሁለት ሕንፃዎችን የሚያካትት ነው። የመጀመሪያው በመሶብ ቅርፅ የሚሠራው ባለ 70 ወለል ሕንፃ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሙዳይ ምስል ቅርፅ የሚሠራውና ባለ 20 ወለል ሕንፃ ነው።

ግንባታው በአዲስ አበባ በተለምዶ ሜክሲኮ በሚባለው አካባቢ በሚገኘውና ገነት ሆቴል ያለበት ሥፍራ ላይ የሚከናወን መሆኑን የገለፁት አቶ ፀጋዬ ከፕሮጀክቱ የግንባታ ወጪ ከ40 እስከ 49 በመቶ የሚሆነው የሚሸፈነው ከውጪ ሀገራት በሽርክና ሊሠሩ ከሚችሉ አካላት ሲሆን እስከ 51 በመቶ የሚደርሰው ወጪ ደግሞ በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ተሳትፎ የሚሸፈን መሆኑን አስታውቀዋል።

Via ኢ.ፕ.ድ
Ethio-Djibouti Standard Gauge Railway S.C
SUPERVISOR, CIVIL & ELECTRIC WORKS
MAINTENANCE
Address: Lebu, Adama, Diredawa, Dewanle Railway stations
Contract February 29, 2020 - March 11, 2020
Const. & Architecture - Engineering -
Maintenance, Skilled Labor & Manufacturing
JOB OVERVIEW
JOB DESCRIPTION
in charge of electric service and public works maintenance
JOB REQUIREMENT
Qualification: College degree in civil or electric engineering
Experience: 3/5 years
No.4
Monthly salary during training: 8820
Monthly salary: 12600
Working Place : Mieso(1), Metehara(1), Diredawa(1)
N.B
Application from private company’s /NGO/ should bring a
letter from tax duties, salary and job title has been
mentioned
Work experience should be after graduation and relevant
Transportation, food and accommodation is not covered
by the the company
A minimum of 6 month training period.
HOW TO APPLY
Application date within 7/seven/ working days from the
date of this vacancy announcement
Interested and qualified applicants should bring their
original documents with non-returnable copies of
application letter, CV and all necessary documents in
Lebu, Adama, Diredawa, Dewanle Railway stations
After the full training, only the qualified one will be
employed

https://t.me/Construction_Job
👉 ሙሉ የ G+3 መኖርያ ህንፃ MODELING ፣ ANALYSING እና DESIGNING በ ETABS እንዴት መስራት እንደምንችል ቲቶርያል ቪድዮ ከነ ሌክቸር ኖቱ ይሀውላቹ፡፡
፡
🅾አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።
፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇USE Wi-Fi
SIMON part 1 (1).rar
569.6 MB
✅G+3 መኖርያ ህንፃ MODELING ፣ ANALYSING እና DESIGNING በ ETABS @engineer03
SIMON part 1 (2).rar
330.1 MB
✅G+3 መኖርያ ህንፃ MODELING ፣ ANALYSING እና DESIGNING በ ETABS
👉 @engineer03
SIMON part 1 (3).rar
301 MB
✅G+3 መኖርያ ህንፃ MODELING ፣ ANALYSING እና DESIGNING በ ETABS
👉 @engineer03
SIMON part 1 (4).rar
30.5 MB
✅G+3 መኖርያ ህንፃ MODELING ፣ ANALYSING እና DESIGNING በ ETABS
👉 @engineer03
SIMON part 1 (5).rar
318.4 MB
✅G+3 መኖርያ ህንፃ MODELING ፣ ANALYSING እና DESIGNING በ ETABS
👉 @engineer03
SIMON part 1 (6).rar
398.6 MB
✅G+3 መኖርያ ህንፃ MODELING ፣ ANALYSING እና DESIGNING በ ETABS
👉 @engineer03
Forwarded from Civil Engineering
😳👌Hello Dear Members,
As per your request working on projects in detail,
we ll start Etabs 👇👇👇
👇join here👇
@engineer03
@engineer03
#share it
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Forwarded from Civil Engineering
PROJECT 1 AR DWG.dwg
589.3 KB
☝️☝️Here is the AR drawing for etabs analysis to follow.

Tip👉 @engineer03