@እንደኔ እይታ.....
3.49K subscribers
3.95K photos
129 videos
18 files
55 links
የምናያቸውንና የምንሰማቸውን የርዕዮተ አለም፣ፖለቲካ እዲሁም ማህበረሰባዊ እውነታዋች በተጨማሪም
ግጥምና ወግም ከኛ እልፍኝ አይጠፋም
ለ እርሶዎም እናደርሳለን
ለአስተያየቶ @Endenaeytabot ይጠቀሙ
ለሀሳብና አስተያየት ወይም
ተጨማሪ መረጃ ካሎት
👇👇👇👇👇👇
@Endenaeytabot
Download Telegram
የአፍሪካ አገራት በዘረኝነት እና የፖሊስ ጭካኔ ላይ በአፋጣኝ በተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ሙግት እንዲደረግ ጠየቁ። በ54 የአፍሪካ አገራት ስም ጄኔቫ በሚገኙት በተባበሩት መንግሥታት የቡርኪና ፋሶ አምባሳደር የተጻፈው ደብዳቤ "በዘር ልዩነት ምክንያት ትውልዳቸው ከአፍሪካ በሚመዘዝ ሰዎች ላይ በሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እና የፖሊስ ጭካኔ" ላይ አፋጣኝ ሙግት እንዲደረግ ይጠይቃል። የአፍሪካውያኑ ደብዳቤው እንደሚለው ኢ-ፍትሐዊነት እንዲገታ በጠየቁ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተወሰዱ የኃይል እርምጃዎች ጭምር ውይይት ሊደረግባቸው ይገባል።

በተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ለሆኑት የኦስትሪያዋ ኤልሳቤጥ ቲቺ-ፊስልበርገር የተጻፈው ደብዳቤ ውይይቱ የምክር ቤቱ 43ኛ ስብሰባ በሚቀጥለው ሳምንት ሲጀመር እንዲካሔድ ጠይቋል።

@endenaendena
@endenaendena
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ ያነሷቸው ዐበይት ነጥቦች፦👇
"ከመቶ በላይ ፓርቲዎች በአንድ ላይ ተሰባስበው መንግሥት እናቋቁም የሚለው ሐሳብ አገሪቱን ወደመበታተን ሊያመራት ይችላል።" ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ ያነሷቸው ዐበይት ነጥቦች፦

👉ህወሃትን በተመለከተ የሚያሳፍር ነገር ነው እየሰማሁ ያለሁት። ልምድ እንዳለው ፖለቲከኛ ሆነው አላገኘኋቸውም። ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳትና በሰጥቶ መቀበል መርህ በመዳኘት አሁን እየፈጠሩት ያለውን ጡዘት ማርገብ ይጠበቅባቸው ነበር።

👉ሁልጊዜ እኔ ያልኩት ካልሆነ ሞቼ እገኛለሁ ማለት በአሁኑ ዘመን የሚያዋጣ የፖለቲካ አካሄድ አይመስለኝም። አጎንብሶ ማለፍ እኮ ደካማነት አይደለም። ህወሃት አሁን ላይ አገሪቱን የሚጎዳ አክራሪ አቋም ይዞ ተቀምጧል።

👉እኔ ሦስተኛ ዲግሪዬን የሠራሁት በተላላፊ በሽታዎች ዙሪያ ነው። እንደባለሙያ ስመለከተው የኮሮና ቫይረስ እጅግ አደገኛ የሆነ ቫይረስ ነው። በዓለም ላይ እንደታየውም ለበርካታ ሰዎች ህልፈት ምክንያት ሆኗል። ይህንንም በአግባቡ ስለምረዳ ምርጫው መተላለፍ እንዳለበት እኔም ሆንኩኝ ፓርቲዬ ጽኑ አቋም ይዘናል።

👉መድረክ ብሔራዊ አንድነት መንግሥት እንዲቋቋም አቋም መያዝ አለበት የሚል አቅጣጫ ሲያዝ እኛ እንደማንስማማ ተናግረን ወጥተናል። እኛ ባልተገኘንበት የኦፌኮ፤ የአረናና የሲአን አመራሮች ተሰብስበው ብሔራዊ አንድነት መድረክ ይቋቋም ማለታቸውን ሰምተናል።

👉በተለይም ደግሞ አሁን ያለው መንግሥት ጠንካራ በመሆኑ የብሔራዊ አንድነት መንግሥት ማቋቋም አያስፈልግም ብለን አቋም ይዘናል። ከመቶ በላይ ፓርቲዎች በአንድ ላይ ተሰባስበው መንግሥት እናቋቁም የሚለው ሐሳብ አገሪቱን ወደመበታተን ሊያመሯት ይችላሉ።

👉እኛ የአቶ ጀዋርን ወደ ኦፌኮ መቀላቀል የሰማነው ዘግይተን ነው። በእርግጥ መድረክ ውስጥ አባል የሚሆኑት ፓርቲዎች ናቸው ግለሰቦች አይደሉም። አንድ ፓርቲ ግለሰብን አባል አድርጎ ሲቀበል የፓርቲው ውሳኔ ነው እንጂ ሌሎቹን የጥምረቱን ፓርቲ አባላት የማማከርም ሆነ የማሳወቅ ግዴታ የለበትም።

👉 የአቶ ጀዋር ጉዳይ እየጎላ ሲመጣና የዜግነቱ ጉዳይ እየተነሳ መከራከሪያ ሲሆን መድረክን ለማዳን ስል ጉዳዩን ለማጣራት ወደ አሜሪካ ኤምባሲ ሄጄ ነበር። በኤምባሲው የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊውን በአነጋገርኩበት ወቅትም ጀዋር የአሜሪካ ዜግነት እንዳለው በግልጽ ነግሮኛል። ስለዚህም ጀዋር የውጭ ዜጋ ነው። አንድ የውጭ ዜግነት ያለው ሰው በሌላው አገር ፖለቲካ ውስጥ ግብቶ እንቅስቃሴ ማድረጉ አግባብ አለመሆኑን ስለምረዳ የሚመለከተው አካል አንዳች ውሳኔ እንዲያሳልፍ በግልጽ ተናግሬ ነበር። መንግሥት ለጉዳዩ በቂ ትኩረት የሰጠው አይመስለኝም፤ እስካሁን ምንም የተባለ ነገር የለም።

👉 ከመድረክ ፓርቲዎች መካከል ኦፌኮ፤ ሲአንና አረና ምርጫ መካሄድ አለበት ካልሆነም ብሔራዊ አንድነት መንግሥት መቋቋም አለበት የሚል አቋም ሲያራምዱ በእኔ የሚመራው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ እና የአፋር ህዝቦች ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የምርጫውን መራዘም ደግፈን ቆመናል።

👉በኦፌኮ በኩል መተዳደሪያ ደንቡን በጣሰ መልኩ የሚደረጉ ተግባራት ፓርቲውን ለውድቀት እየዳረገው ነው። የመድረክ መተዳደሪያ ደንብ የመድረክ አባላት ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር መዋሐድ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ጥምረት መፍጠር አይችሉም በሚል የትኛውንም የጎንዮሽ ግንኙነት እንዳያደርጉ ይከለክላል።

👉ኦፌኮ ግን ኦነግንና ሌሎች በኦሮሚያ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመሥራት እንዲመቸው ይህ አንቀጽ እንዲሻሻል ሙግት ሲያርግ ቆይቷል። እኛም የዚህ አንቀጽ መሻሻል ክፍተት እንደሚፈጥር በማመን አንቀፁ መሻሻል እንደሌለበት ብዙ ብንከራከርም የሌሎቹን ፓርቲዎች እገዛ ባለማግኘታችን አንቀፁ ሊሻሻል ችሏል።

👉አረናና ሲአን የራሳቸውን ቁመና ካጡና በኦፌኮ ተጽዕኖ ሥር ከወደቁ ስለቆዩ የኦፌኮ ሐሳብ ተፈፃሚ ሆኗል። ኦፌኮ ይህችን ቀዳዳ ተጠቅሞ በኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ጋር ጥምረት ፈጥሬያለሁ ብሎ መድረክ የማያውቀውን መግለጫ መስጠት ከጀመረ ውሎ አድሯል።
@endenaendena
@endenaendena
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በአንድ ዶክተር ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ

በጥቁር አንበሳ ዶ/ር ተገኝ ሞላ የተባለ ሀኪም ግድያ ሙከራ እንደተደረገበት በዚህ መልኩ በፌስቡክ ገፁ አስፍሮታል።

" ዶ/ር ተገኝ ሞላ እባላለሁ፤ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የነርቭ ስፔሻሊስት ሀኪም ነኝ። እዚያው በምሰራበት ቦታ የግድያ ሙከራ ተደርጎብኝ ተርፈለሁ። ወንጀሉ እጅግ የተቀነባበረ ነው። አሁንም ለህይዎቴ ስለምሰጋ መንግስት ህይዎቴን እንድታደገኝ እና ወንጀሉን እንድያጣራ ጥሪ አቀርባለሁ። እናንተም ይህን መልዕክት ሼር በማድረግ መልዕክቱ ለመንግሥት እንድደርስ እንድትረዱኝ አደራ እላለሁ። "
@endenaendena
@endenaendena
"የትግራይ ክልል ምክር ቤት ምርጫ ይካሄድ ብሎ መወሰኑ ህገ መንግስቱን የሚጻረር ስለሆነ መንግስት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ አክብሮ ያስፈጽማል።" አቶ ንጉሱ ጥላሁን የጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬስ ሴክሬታሪያት

"ምርጫ ቦርድ የተሰጠውን ህገመንግስታዊ ስልጣን ሁሉም አካል ሊያከብር ይገባል"

“አስፈፃሚ አካሉ በምርጫ ቦርድ ስራ እና ውሳኔ ጣልቃ በመግባት ቢፈትፍት ያለ ሀላፊነቱ መንቀሳቀስ ስለሆነ መንግስት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ያከብራል፣ይፈፅማል”
@endenaendena
@endenaendena
የጠቅላይ ሚኒሰተር ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬተርያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን "አስፈፃሚዉ አካል በምርጫ ቦርድ ስራ እና ዉሳኔ ጣልቃ በመግባት ቢፈተፍት ያለ ሃላፊነቱ መንቀሳቀስ ሰለሆነ መንግስት የምርጫ ቦርድን ዉሳኔ ያከብራል" ማለታቸውን ተከትሎ የትግራይ ክልል ኮሚውኒኬሽን ቢሮ መልስ ሰጥቷል።

ሙሉ መግለጫውን ከስር እለቃለው👇
@endenaendena
@endenaendena
አምባገነናዊ የቡድን ፍላጎት ለማርካት ሲባል የህዝብን የመወሰን ስልጣን መደፍጠጥ ፈፅሞ አይቻልም!

የትግራይ ህዝብ የሉዓላዊነቱ መገለጫ የሆነዉን የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ፣ ትላንት ሰኔ 5/2012 ዓ/ም ባካሄደዉ አምስተኛ ዘመን ሰባተኛ አስቸካይ ጉባኤዉ በኢፌድሪ ህገ-መንግስትና በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ህገ-መንግስት የተደነገጉ አንቀፆችን መሰረት አድርጎ ስድስተኛዉ ክልላዊ ምርጫ እንዲካሄድ የምክሪቤቱ አባላት በሙሉ ድምፅ አፅደቀዉታል።

ነገር ግን የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒሰተር ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬተርያት "አስፈፃሚዉ አካል በምርጫ ቦርድ ስራ እና ዉሳኔ ጣልቃ በመግባት ቢፈተፍት ያለ ሃላፊነቱ መንቀሳቀስ ሰለሆነ መንግስት የምርጫ ቦርድን ዉሳኔ ያከብራል" በማለት ዛሬ ሰኔ 6/2012 ዓ/ም መግለፁን በፌዴራል መንግስት በሚቆጣጠራቸዉ ሚድያዎቹ ተሰራጭተዋል። ሆኖም ይህ አባባል በራሱ ሲታይ የፈዴራል መንግስት ስልጣን የተቆጣጠረዉ አካል ካለፊት ሁለት አመታት ጀምሮ በኢትዮዽያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ያሳየዉ ማን አለበኝነትና ንቀት ዛሬም በትግራይ ህዝብ የላዕላዊነት መገላጫዉ በሆነዉ የተከበረዉ ምክርቤት መድገሙ በስልጣን ላይ ያለዉ ቡድን የአባገነንነት ባህሪዉ የከፋ ጫፍ ላይ መድረሱን ፍንትዉ አድርጎ የሚያሳይ ነዉ።

የኢትዮዽያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ስልጣንና ሃላፊነት ጠንቅቆ የሚያወቀዉ የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ስድስተኛ ክልላዊ ምርጫ እንዲካሄድ የወሰነዉ በኢፌድሪ ህገ-መንግስትና በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ህገ-መንግስት አንቀፅ 8፣ 9፣ 12፣ 38 እና በአንቀፅ 39 ንኡስ አንቀፅ 1 እና 2፣ እንዲሁም የኢትዮዽያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋምያ አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ዓ/ም አንቀፅ 4 እና በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ህገ-መንግስት አንቀፅ 48(2) መሰረት አድርጎ ነዉ። ሰለሆነም የራስን እድል የመወሰን ያልተገደበ ስልጣን ያለዉ የትግራይ ህዝብ የለዐላዊነቱ መገለጫ በሆነዉ ምክርቤቱ የወሰነዉ ዉሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ የሚከለክለዉ ማንም ሃይል ሊኖር አይችልም።

በመጨረሻ በኢፌድሪ ህገ-መንግስት በየትኛዉም አንቀፅ ያልተፃፈን ጉዳይ አይኑን ጨፍኖ በማንበብ አባገነናዊ የቡድን ፍላጎቱን ለማርካት ሲባል፣ የህዝብን የመወሰን ስልጣን ለመደፍጠጥ የሚደረግ ሩጫ በትግራይ ህዝብና ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክርቤት ፈፅሞ ተቀባይነት እንደሌለዉ ወዳጅም ጠላትም ሊያዉቅ ይገባል።

የትግራይ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
መቐለ: ሰኔ 6/2012 ዓ/ም

@endenaendena
@endenaendena
ግብፃዊው ቢሊየነር ናጉኢብ ሳዊሪስ "ኢትዮጵያ ወደ ምክንያታዊነት ካልመጣች እኛ ግብፃውያን ጦርነት እናውጃለን" ብለው በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል!

የኦራስኮም ቴሌኮም እና ሌሎች በርካታ ድርጅቶች ባለቤት ናጉኢብ የዛሬ ሁለት አመት ገደማ አዲስ አበባ ተገኝተው ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚፈልጉ ተናግረው ነበር። ድርጅታቸው በኢትዮጵያ ሊያፈስ አቅዶ የነበረውን 300 ሚልዮን ዶላር የዛሬ አራት አመት ገደማ ማዘግየቱ ይታወሳል።

በሌላ ዜና: በህዳሴ ግድብ ዙርያ የሚደረገው ውይይት ዛሬ ማምሻውን ጭምር ቀጥሎ እንደነበር መረጃ ደርሶኛል። የግብፅ ውሀ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እንደፈለገች ልትወስን ትፈልጋለች፣ ይህም ተቀባይነት የለውም ብሏል። ከኢትዮጵያው ተደራዳሪ ወገን የደረሰኝ መረጃ ደግሞ "እነርሱ ቀልዳቸውን ቀጥለዋል፣ ቢሆንም ውይይታችንን እያካሄድን ነው" ይላል።

#eliasmeseret
@endenaendena
@endenaendena
በአርጄንቲና በኮቪድ ምክንያት ህጉ ቤተክርስቲያናትን ዝግ: ምግብና መጠጥ ቤቶች ደግሞ ክፍት ይሁኑ ብሏል! ታዲያ ፓስተሮቹ ቤተክርስቲያናቱን ወደ ሆቴል ቤትነት ቀይረው መብልና መጠጥ እያስተናገዱ ስብከቱን ተያይዘውታል! ፈጠራ ወይስ መከራ?!

full story👇

Argentina pastor turns church into bar in protest at uneven coronavirus restrictions | Argentina | The Guardian
https://www.theguardian.com/world/2020/jun/13/argentina-pastor-turns-church-into-bar-in-protest-at-uneven-coronavirus-restrictions

@endenaendena
@endenaendena
የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ለወራት ከታወጀው የእንቅስቃሴ ገድብ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ህዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ መታየታቸው ተዘግቧል፡፡
ፑቲን ከሁለት ወራት በፊት ህዝባቸው ከእንቅስቃሴ እንዲታቀብ ከሰጡት ትዕዛዝ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ህዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ መታየታቸው ነው የተነገረው ፡፡
ፑቲን በሞስኮው ምዕራባዊ ክፍል በሰንደቅ ዓላማ ክብር በተንቆጠቆጠው ስርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር አሰምተዋል፡፡
ይሁንና ፑቲን በአደባባይ ሲታዩ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል አለማድረጋቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

ምንጭ፡-አሶሼትድ ፕሬስ ነው፡፡
@endenaendena
@endenaendena
#ማስጠንቀቂያ

#የአይን_ብሌናችንን_እንዳናጣ_ጥንቃቄ

የሰኔ 14/2012 ዓ.ም የፀሐይ ግርዶሽን በተመለከተ የቀረበ መረጃ፡፡

🌑የ2012 ዓ.ም ግርዶሽ የሚታየው፡-

- ሰኔ እሁድ 14/2012 ዓ.ም ነው፣
- በግርዶሹ 6፡00 ሰዓት የሚፈጅ ጨለማ ይታያል፡፡
- በመላ ኢትዮጵያ ይታያል፡፡
- በተለይ ወለጋ፣ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ አላማጣ፣ ኢንጂባራ 98% ጨለማ ሆኖ ይታያል፡፡
- የዓለምን አሰራር የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካን፣ የከፍተኛ የተፈጥሮ ኃይል ሊገኝ ይችላል ብለው ሳንቲስቶች ሀሳባቸውን እየሰነዘሩ ይገኛሉ፡፡

- ከምዕራብ ኢትዮጵያ እስከ ሰሜን ኢትዮጵያ ድረስ ግርዶሹ ይታያል፡፡
- ፀሐይ 98% ትሸፈናለች፡፡

🌑የሚታይበት እና የሚያበቃበት፡-

- ከማዕከላዊ አፍሪካ ከኮንጎ ይነሳል፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ የመን፣ ፓኪስታን፣ ታይዋን፣ ንድና ቻይናን አቋርጦ ፓስፊክ ውቂያኖስ ላይ ያበቃል፡፡


🌑ሙሉ ግርዶሹ የሚታይበት ወቅት

- ከሌሊቱ ሰኔ 14/2012 ዓ.መ
- 11፡00 ሰዓት ይጀምራል፣
- ከጠዋቱ 12፡45 እስከ ቀኑ 6፡33


‼️ማስጠንቀቂያ፡-

- በዓይን ለማየት አይቻልም ዐይን ያሳውራል፣
- በሱቅ ውስጥ የሚሸጥ መነጽር መጠቀም አይገባም፡፡
- ለፀሐይ ግርዶሽ ተብሎ የተዘጋጀ መነጽር አለ፡፡
- መነጽሩ አገር ውሰጥ አይገኝም፡፡
-ለፀሀይ ግርዶሽ የሚሆን መነፀር አለን ከሚሉ አጭበርባሪዎች ጥንቃቄ ያድርጉ
- ሲጨልም ማየት እንችላለን ነገር ግን ያለመነጽር ለማየት አንሞክር፣በጣም ጥንቃቄ ሊታከልበት ይገባል
- ዐይናችን ሊፈስ ይችላል፣


አብዛኛው ኢትዮጽያዊ መረጃው ስሌለው እና የፀሀይ ግርዶሽ የሚታይበት ቀን ስለደረሰ ቢያንስ ለ ሚወዷቸው 50 ሰወች ሼር በማድረግ መረጃው ለሁሉም እንዲደርስ በማድረግ ከህሊና ፀፀት ድነው የበኩልውን ይወጡ

🎖ዶ/ር ሊያ ታደሰ

@endenaendena
@endenaendena
እሁድ -ሰኔ 07- 10 - 2012 EC
…………………🌸……………………

የቻናላችን የሳምንቱ ምርጥ ፎቶ!!!
…………………🌸……………………
ይናገራል ሚስጥር

❤️ውብ አሁን❤️

┄┄┉✽̶»̶̥ ͜͡ ❀🌼❀ ͜͡»̶̥✽̶┉┄
@endenaendena
@endenaendena
┄┄┉✽̶»̶̥ ͜͡ ❀🌼❀ ͜͡»̶̥✽̶┉┄
Ab Bella

ሲዳማዎች ከጃዋር ጋር ይናበባሉ፡፡ወላይታዎች ከህወሀት ጋር ይናበባሉ፡፡ከአማራ ጋር የሚናበብ የለም፡፡ካለም እስክንድር ነጋ ነው፡፡እስክንድር እንደ ብዙሀኑ ተቃዋሚዎች አጭበርባሪ ባይሆንም ደም ፍላት አለበት፡፡ሲናደድ እንደ ትራምፕ እጁ ወደ ስልኩ ያመራል፡፡የማይሆን ነገር ይፖስታል፡፡የማይሆን ክርክር ያስጀምራል፡፡
የአማራ ፖለቲካ ስትራቴጂክ አጋሩ ማን እንደሆነ አይታወቅም፡፡ጠላቶቹ ጋር ሲፋጠጥ ይሉኝታ ያጠቃዋል፡፡ወዳጆቹን አልለየም ፥ ለማቅረብም ጥረት አላረገም፡፡የክልሉ ልሂቃን ከጊዜያቸው 90 በመቶ የሚሆነውን አዴፓን በመተቸት ያሳልፋሉ፡፡በተረፋቸው ጉልበት እርስ በርሳቸው በመዘላለፍ ያባክናሉ፡፡ሲላቸው የራሳቸውን ወገን ወታደራዊ ዘመቻ ዝርዝር ይለጥፋሉ፡፡
@endenaendena
@endenaendena
'የትግራይ ነፃነት ፓርቲ' የተባለው አዲስ የተመሰረተ የፖለቲካ ድርጅት ዛሬ በመቐለ መስራች ጉባኤው እያካሄደ ነው፡፡ "ያለ ነፃና ሉአላዊት ሃገረ ትግራይ፣ ብሔራዊ ክብርና ጥቅም ማረጋገጥ አይቻልም" ይላል የፓርቲው መስራች ጉባኤ መሪ ሐሳብ፡፡
@endenaendena
@endenaendena
🖌በትግራይ ተጨማሪ 9ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጧል።

በክልሉ ባለፉት 24ሰአታት በተደረገ 219 የላብራቶሪ ምርመራ 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የእድሜ ክልላቸውም 21-42አመት መሆኑ ተገልጿል።

በአጠቃላይ በክልሉ በተደረገ 5,399 የላብራቶሪ ምርመራ እስካሁን ድረስ 122ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተገለፀ ሲሆን አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 10 መድረሱን የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል።

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ
@endenaendena
@endenaendena
"በኢትዮጵያ ተጨማሪ 179 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ
@endenaendena
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 179 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4845 የላብራቶሪ ምርመራ 179 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3345 ደርሷል።
@endenaendena
@endenaendena
#አሳዛኝ_ዜና ❗️

በኮሮና ተጨማሪ 2 ሰው ህወት አለፈ ❗️

⚡️የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 30 (24 ከጤና ተቋም እና 6 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን በሁለት ናሙናዎች (1 ከጤና ተቋም እና 1 ከማህበረሰብ) የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

⚡️ ሁለቱም የአዲስ አበባ ነዋሪ የነበሩ ሴትና ወንድ ኢትዮጵያውያን ናቸው።

⚡️በአጠቃላይ በሀገራችን ። ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሀምሳ ሰባት (57) ደርሷል።

⚡️ በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማንን ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡
@endenaendena
@endenaendena
🖌የ179ኙ ታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 4845 የላቦራቶሪ ምርመራ 179 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3345 ደርሷል።

የታማሚዎችን ሁኔታ ስንመለከት
-176 ኢትዮጵያውያን እና 3የውጪ ዜጎች ሲሆኑ 116ወንድ እና 63ሴት ናቸው። እድሜያቸው ከ2ወር-80አመት መሆናቸው ተገልጿል።

የመኖሪያ ቦታቸውን ስንመለከት
_
•111ሰዎች- ከአዲስ አበባ
•9ሰዎች - ከትግራይ ክልል
•15ሰዎች -ከኦሮሚያ ክልል
•11ሰው - ከአፋር ክልል
•23ሰዎች- ከአማራ ክልል
•2ሰዎች- ከድሬዳዋ
•5ሰዎች- ከሱማሌ ክልል
•1ሰዎች- ከሀረሪ ክልል
•2ሰዎች- ከደቡብ ክልል

በትላትናው ዕለት ተጨማሪ 50ሰዎች(41ዱ ከአዲስአበባ እና 4ከአማራ ክልል ፣ 2ከትግራይ ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 545 ደርሷል።
@endenaendena
@endenaendena
በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ7.9 ሚሊዮን በለጠ

እስካሁን በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ 7 ሚሊዮን 903 ሺ የበለጠ ሲሆን ከነዚህም 433 ሺ የሚጠጋ የቫይረሱ ታማሚ ህይወት አልፏል፡፡ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ህይወታቸው ማለፉንም ወቅታዊ ቁጥራዊ መረጃዎችን የሚያወጣው ዎርልዶ ሜትር በድረ ገጹ ይፋ አድርጓል፡፡
በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ቁጥር አሜሪካ ፣ ብራዚል ፣ ሩሲያ ፣ ህንድ እና ብሪታንያ በቅደም ተከተል ከ1ኛ እስከ 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ ዋነኛዋ ተጠቂ አሜሪካ እስካሁን ከ 2 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ እና ነዋሪዎቿ በቫይረሴ ሲያዙ ከ117 ሺ በላይ የሚሆኑት ህይወታቸው ማለፉን ሪፖርት አድርጋለች፡፡
#by#aline
@endenaendena
@endenaendena