የሐዋሳ ሰ/ም/ቅ/ማ/ቤ የውሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ቻናል
97 subscribers
412 photos
8 videos
72 files
9 links
የሐዋሳ ሰ/ም/ቅ/ማ/ቤ የውሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ቻናል ነው በዚህም መንፈሳዊ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን የጠበቁ ትምህርቶችን የምንማማርበት ነው ፡፡
Download Telegram
1ኛ ጴጥሮስ 1፥3: ".... ዘወለደነ በብዝኀ ምሕረቱ ለተስፋ እንተ ባቲ ነሐዩ በተንሥኦቱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ እምነ ምዉታን።“ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን ..." እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
👉አደራህን ጠብቅ🤚
አንተ ሰው !
ቃለ እግዚአብሔርን ተማር !
ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር !
ኹልጊዜ ተማር !
ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር!
ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ ። ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፡፡ ስለዚህ ተማር! ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለህ፡፡ ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፡፡ አንድ ቀን ወደ ንስሐ ትመራሃለች !!!
 
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
💚💛❤️አደራህን ጠብቅ💚💛❤️
ነገ ረቡዕ ነው
ለመምጣት ይጸልዩ፣ይወስኑ፣ይምጡ
👉ይጸልዩ ያመስግኑ ይማሩ
ዛሬ ረቡዕ ነው በእግዚአብሔር ቤት እንገናኝ🎯
11:00 ሰዓት እየደረሰ ነው።
በዋዜማው ከእመብርሃን ደጅ አትቅሩ👐
✍️ለ2019 ዓመተ ምሕረት እንኳን አደረሰን⛪️
ዘመኑን የፍቅር የደስታ የሰላም የአንድነት የመተሳሰብ የመረዳዳት ያድርግልን🙏🙏🙏🙏🌼🌼🌼 ከድንቁርና ወደዕውቀት ከኃጢአት ወደ ጽድቅ ከክፋት ወደ ደግነት ከጸብእ ወደ ሰላም ከርኵሰት ወደ ንጽሕና ከስግብግብነት ወደመረጋጋት ከስርቆት ወደ ስጦታ ከራስ ወዳድነት ወደ ወንድም እኅቱን ወዳድነት ከውስልትና ወደ ቁም ነገር ከአመንዝራነት ወደ ተዐቅቦ ከጥቅም ፈላጊነት ወደ ሰው ወዳድነት የምንሸጋገርበት ዘመን ያድርግልን እግዚአብሔር አምላካችን ተምረን የምናውቅበት ሠርተን የምንለወጥበት ከውድቀት የምንነሣበት ያድርግልን በመልካሙ መንገድ ተጉዘን መልካም ፍሬን አፍርተን መንግሥቱን የምንወርስበት ዘመን ያድርግልን ዕርቅ፣ ሰላሙን፣ ይቅርታውን በእኛ ላይ ያሳድርልን ዐይነ ልቡናችንን ለበጎ ነገር ለዕውቀት ለትምህርት ያብራልን ትሕትና እና ፍቅር በተመላበት ትምህርት በልጽገን እያገለገልነው (እየተገለገልን) ስለስሙ እየመሠከርን እንድንኖር የእግዚአብሔር አምላካችን መልካም ፈቃድ ይሁን አሜን!!!🙏🙏🙏

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ፤
ወይጸግቡ ጠላት ገዳም፤
ወይረውዩ አድባረ በድው፤
በቸርተነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል። መዝ ፷፬፥ ፲፩,
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻