የሐዋሳ ሰ/ም/ቅ/ማ/ቤ የውሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ቻናል
97 subscribers
412 photos
8 videos
72 files
9 links
የሐዋሳ ሰ/ም/ቅ/ማ/ቤ የውሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ቻናል ነው በዚህም መንፈሳዊ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን የጠበቁ ትምህርቶችን የምንማማርበት ነው ፡፡
Download Telegram
አባ ሄሮኒመስ እንደ ነገረን ስንጸልይእግዚአብሔርን እናናግረዋለን፤ ስናነብ ደግሞ እግዚአብሔር እኛን ያናግረናል፡፡ ስንጸልይ ቅዱሳንን እናናግራቸዋለን፤ ጽሑፎቻቸውን ስናነብ ደግሞ ቅዱሳኑ እኛን ያናግሩናል፡፡ ታዲያ እነ ቅዱስ ኤፍሬም፣ እነ ቅዱስ አትናቴዎስ፣ እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ እነ ቅዱስ ቄርሎስ፣ እነ ቅዱስ ያሬድና እነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እንዲያነጋግሩት ማይሻ ማን ጎስቋላ ሰው ነው? እግዚአብሔር እንዲያናግረው የማይፈልግ ማን ምስኪን ሰው ነው?

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለ

በንባብ ተግተን ራሳችንም ሌሎችንም

እናድን ዘንድ የእግዚአብሔር ቸርነት

የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳን

ኹሉ ቃል ኪዳን ተራዳኢነት አይለየን፡፡ አሜን!
👉 አደራህን ጠብቅ🤚
1ኛ ጴጥሮስ 1፥3: ".... ዘወለደነ በብዝኀ ምሕረቱ ለተስፋ እንተ ባቲ ነሐዩ በተንሥኦቱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ እምነ ምዉታን።“ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን ..." እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
👉አደራህን ጠብቅ🤚
አንተ ሰው !
ቃለ እግዚአብሔርን ተማር !
ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር !
ኹልጊዜ ተማር !
ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር!
ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ ። ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፡፡ ስለዚህ ተማር! ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለህ፡፡ ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፡፡ አንድ ቀን ወደ ንስሐ ትመራሃለች !!!
 
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
💚💛❤️አደራህን ጠብቅ💚💛❤️
ነገ ረቡዕ ነው
ለመምጣት ይጸልዩ፣ይወስኑ፣ይምጡ
👉ይጸልዩ ያመስግኑ ይማሩ
ዛሬ ረቡዕ ነው በእግዚአብሔር ቤት እንገናኝ🎯