ወዳጄ!
ከሁሉ በፊት ሰላምታ ይቀድማልና አንተ እግዚአብሔርን ብታውቀውም ባታውቀውም በቅድምያ በእግዚአብሔር ፍጹም ሰላም ሰላም ብያለሁ፡፡
.
ለነገሩ እግዚአብሔርን ባታውቀውም እርሱ ግን ያውቅሀል፡፡
.
ደግሞም የአንተ አለማመን የእግዚአብሔርን ታማኝነት አያስቀረውም፡፡ ሮሜ.3፡3
.
ይሁን እንጂ የፈጠረህን ጌታ ካላወቅኸው ሰው መሆንህ በራሱ ያጠራጥራል፡፡
.
በዚህ ምድር ላይ እኮ አንተ አንተ ብቻ ነህ፡፡
.
እንግዲህ መኖሮህ ካልቀረ ለነፍስህ ኑርላት፡፡
.
ደግሞም ለአንተ ነፍስ አንተ ካላሰብክላት ማን ሊያስብላት ነው?
.
አንድ ቀን ባደርክ ቁጥር ከእድሜህ ላይ አየተቀነሰ መሆኑንም አትርሳ፡፡
.
ስለዚህ የኖርክበት ዘመን እየጨመረ ሲሔድ የምትኖር ጊዜ ደግሞ እያጠረ ይሔዳል፡፡
.
እኔ ግን ጥያቄ አለኝ ከሀጢአትህ የማትመለስ ከሆነ ዕድሜህ ቢበዛ ምን ያደርግልሀል?
.
ክርስትና እኮ ሞኝነት ሳይሆን የዋህነት ነው፡፡
.
በክርስትና ሕይወት ውስጥ ምንም እንኳን ከምድር ትብያ ላይ የተፈጠርክ ብትሆንም ዜግነትህ ግን ሰማያዊ ነው፡፡
.
ምናልባት በዚህ ምድር ላይ ኪራይ አየከፈልክ በኪራይ ቤት ብትቀመጥም እንኳ በተዋሕዶ ሃይማኖትህ ከጸናህ በሰማይ ለአንተ የሚሆን ልዩ ሥፍራ እንደ ተዘጋጀልህ ግን እመነኝ፡፡
.
ዓይኖችህ በቀራንዮ ላይ የተከፈለልህን ውለታ መመልከት ካልቻሉ እንደ ተቃጠለ አምፖል ቁጠራቸው፡፡
.
ልብህ ከእግዚአብሔር ከሸፈተ ከሰይጣን ጋር ጋብቻ መሥርቷል ማለት ነው፡፡
.
ሀሳብ የለሽ አትሁን!
ሀሳብ የለሾች ጭንቅላታቸው ለሻሽና ለባርኔጣ ብቻ የተፈጠረ ይመስላቸዋል፡፡
.
ጆሮአቸውም የእግዚአብሔርን ቃል ከመስማት ይልቅ ለጉትቻና ለመነፀር ማስቀመጫ ብቻ የተፈጠረ ይመስላቸዋል፡፡
.
ብዙ ጊዜም ወርቅ፡ ብር፡ ሎቲ... እያልን የብረታብረት መአት በጆሮአችን ላይ እናግበሰብሳለን፡፡ ነገር ግን አለመታደል ሆነና ከወርቅ፡ ከአልማዝና ከዕንቁ በላይ ውድ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ግን ወደ ጆሮአችን አናስጠጋውም፡፡
.
አንተ ግን አንድ እርምጃ ወደ እግዚአብሔር መራመድ ከጀመርህ ሰይጣን ሦስት እርምጃ ከአንተ እየራቀ እንደ ሚሔድ እመን!
.
ከጨለማ ጋር የነበረህን ውል ካፈረስህ እግሮችህ ወደ ብርሃን አቅንተዋልና በርታ ወዳጄ!
.
መዝረፍ የለመደ እጅ መመጽወትን እንደ ኃጢአት ይቆጥረዋል፡፡ ስለዚህ መዝረፍን ለእጅህ አታለማምደው!
.
ደግሞም ዛሬ የምትሠራው ኃጢአት ትናንት የሠራኸውን የጽድቅ ሥራ ያበላሽብሀልና ተጠንቀቅ!
.
የሰው ትልቅነቱ የሚመዘነው በሀሳቡ እንጂ በቁመቱ አይደለምና ምናልባት ረጅም ከሆንህ አጫጭሮቹ እንደ ማያስቡ አድርገህ አትገምት!
ምክንያቱም ስንት ረጅም ሆኖ አጭር የሚያስብ አጭር ሆኖም ረጅም የሚያስብ ሰው ሞልቷልና፡፡
.
ሰው ሞተ የሚባለው ከእግዚአብሔር ሲለይ እንጂ ከዚህ ዓለም ሲለይ አይደለም፡፡
ስለዚህ ከእግዚአብሔር ተለይተህ ከሆነ መሞትህን አትንገረኝ በቃ!
.
ጸሎት ጥያቄን ይዞ ሔዶ መልሱን ይዞ የሚመጣ መሣርያ ነው፡፡
.
ስለዚህ ጸሎተኛ ለመሆን ጸሎተኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡
.
ዳሩ ግን ጸሎት ከመጸለይህ በፊት በቅድምያ ጸሎትህን ተቀብሎ መፍትሔውን ሊሰጥህ የሚችል አካል መኖሩን ሳታረጋግጥ አትጸልይ!
ምክንያቱም ከጸሎት በፊት መማን ይቀድማልና፡፡
.
እስኪ ጥያቄ ልጠይቅህ!
እኔ መንግሥተ ሰማያት ለአንተ እንደ ተዘጋጀች እወራረዳለሁ፡፡ አንተስ ለመንግሥተ ሰማያት መዘጋጀትህን ትወራረዳለህ?
.
በመንፈሳዊ አገልግሎትህ ውስጥ ፍጠን እንጂ አትቸኩል!
ምክንያቱም ችኮላ እቃ ይሰብራል፡፡ ፍጥነት ግን ጊዜን ይቆጥባል፡ ሥራን ያቀላጥፋል፡፡
በፍጥነትና በችኮላ መካከል ያለውን ርቀት ደግሞ በዱባና በቅል መካከል ያለውን ልዩነት አይቶ መገመት ይቻላል፡፡
.
ክርስቲያን አይዋሽም ከዋሸ ግን ክርስቲያን አይደለም፡፡
.
መብራት መብራት የሚባለው ብርሃን ሲኖረው ነው፡፡ እምነትም እምነት የሚባለው ምግባር ሲኖረው ነው፡፡ ነገር ግን ምግባር የሌለበት ከሆነ "ም" ወደ "ብ" "ነ" ወደ "ደ" ይቀየርና "እምነት" የነበረው "እብደት" ተብሎ ይነበባል፡፡
ምክንያቱም ከምግባር የተራቆተ እምነት የስሌቱ ውጤት እብደት ነውና፡፡
.
እንግዲህ ንሰሐ ለመግባት የሚያስፈልገው ትልቁ ነገር ንሰሐ መግባት ብቻ ነው፡፡
.
ደግሞም ከልብ የሆነ ንሰሐ በኃጢአት ላይ ጉልበት አለው፡፡
▄ ▃ ▂ ▁✞▁ ▂ ▃ ▄
@embtee

#እንኳን_ለፆመ_ሀዋርያት_በሰላም_አደረሳችሁ
ፆመ ሀዋርያት የሰኔ ፆም በመባል ይታወቃል። ሀዋርያት ጌታችን ባረገ በ10ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ ወርዶላቸው የፆሙት ፆም ነው።
ሀዋርያት መንፈስ ቅዱስ ከተቀበሉ በኃላ እግዚአብሔር ስራቸውን ያቀናላቸውና ይባርክላቸው ዘንድ የፆሙት ፆም ስለመሆኑ ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖችም ስራችንን የተቃና መንገዳችን የተስተካከለ ሀሳባችን የተሳካ ለጅማሬ አችን ለፍፃሜ የሚያበቃ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የምንጓዝበት እንድሆን ቤተ ክርስቲያን እንድን ፆም ታዛለች።
ለአገልግሎት ፀጋና ብርታት ከጌታ የምንቀበልበት። ሐዋ ፲፫ ÷፩ ~፫
ለሀዋርያት በረከትን እንደላከላቸው ለኛም ይላክልን።
ወስበሀተ ለእግዚአብሔር።
@embtee @embtee

✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞ via @like
ቅድስት አፎሚያ
ሰኔ 12 ቀን 2006 ዓ.ም.
በወርኃ ሠኔ መታሰቢያ ከሚደረግላቸው ቅዱሳን መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራ
የአስተራኒቆስ ሚስት የሆነች የቅድስት አፎምያን ታሪክ በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡
ቅድስት አፎምያ በትዳር በነበረችባቸው ዘመናት እግዚአብሔርን ከሚወድ
ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ነበረች፡፡ በየወሩ በ29
ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12
የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ እንደነበር ታሪካቸው
ይነግረናል፡፡
ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ
ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ
እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል
ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡
ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት
ቀጠለች፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት
ስትበረታ ባያት ጊዜ ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ በመጀመሪያ ባል ሳታገባ
ማገልገሏን ትታ፣ ሌላ ባል አግብታ፣ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል
ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ
አስመስሎ ነገራት፡፡
ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች
ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ፤ እነሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው
ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው
ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ
ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ
አባረረችው፡፡ እሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ፤
እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡
በሠኔ ፲፪ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ
መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ
የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም
የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን
አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ
መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም
አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ
እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት፡፡
ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት
ታምና “የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው
የመስቀል ምልክት የታለ?” በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል
የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው፡፡
ለጊዜው “በኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም” ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን
ሊያስቀይራት ሞከረ፡፡ ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት
አብራርታ የእሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ ከቤቷ ላለው
ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ
ትክክለኛ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም
የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን “ድረስልኝ” እያለች በጠራችው ጊዜ
መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት፡፡
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት
አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ
አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና
ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና
ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን
አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡
ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሠኔ ፲፪
ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡
ይህች የታመነች ቅድስት አፎምያ በሰላም እስክታርፍ ጊዜ ድረስ የተጓዘችበትን
መንፈሳዊ ጎዳና አስተውለን ይሆን? አስቀድማ ከባሏ ጋር አንድ ሆና በታማኝነት
ፈጣሪዋን አገለገለችው፡፡ በኋላም የባሏን ኑዛዜ አክብራ ምንም እንኳን ኃጢአት
ባይሆንባትም በሁለተኛ ትዳር ራስዋን ማጠላለፍ አልፈለገችም፡፡ በጎ ሥራ
አብልጣ በመሥራት እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ተፋጠነች እንጂ፡፡
ሰይጣን ልጅ አለመውለዷን ተጠቅሞ ያቀረበላትን የጋብቻ ጥያቄ ውድቅ
በማድረግ “መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ መናፍስት ከእግዚአብሔር እንደሆኑ
መርምሩ” ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የታዘዘውን መመሪያ ተጠቅማ ሰይጣንን
በተወክሎ እግዚአብሔር ተቃውማ አሸነፈችው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን ርዳታ
ያገኘችውና በሰላም ዐርፋ ወዳገለገለችው እግዚአብሔር በክብር የሔደችው
በጽናት ተጋድላ ነው፡፡
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በጸሎቷ ይማረን፤ የቅዱስ ሚካኤል
የረድኤቱ ኃይል ሁላችንንም ይጠብቀን፣ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
https://t.me/embtee

Telegram
✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
✝ ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ ✝
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee
@Binyama1
@yitayal_bot
Contact @Maryamawit_bot

✨🔥✨🔥✨🔥✨🔥✨🔥✨🔥
• ..✞•የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ•✞ •
አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች
መርጠው በመቀላቀል መንፈስወን ያድሱ።
🌀 Todays promo sponsor 🌀
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን የመዝሙር
ግጥሞችን ከነዜማቸው በየቀኑ
ወደናንተ ያቀርባል፡፡
• ..✞•የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ•✞ •
አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች
መርጠው በመቀላቀል መንፈስወን ያድሱ።
🌀 Todays promo sponsor 🌀
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን የመዝሙር
ግጥሞችን ከነዜማቸው በየቀኑ
ወደናንተ ያቀርባል፡፡
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ተዋሕዶ ሐይማኖቴ የተቀበልኩሽ ከአባቴ እኔ አላፍርም ባምልኮቴ
በጌታ እናት በእመቤቴ
የተዋህዶ ልጅ የሆነ ሁሉ ሊያያቸው የሚገቡ ቻናሎች
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ተዋሕዶ ሐይማኖቴ የተቀበልኩሽ ከአባቴ እኔ አላፍርም ባምልኮቴ
በጌታ እናት በእመቤቴ
የተዋህዶ ልጅ የሆነ ሁሉ ሊያያቸው የሚገቡ ቻናሎች
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ይቅርታ መጠየቅ የምትፈልጉት ሰው ካለ
ስሙን ✍
ፎቶውን 🖼
እና
Voice ይፈቀዳል
ይቅርታቹን አጠር አድርገው 👇
@Zorryy_sorry
@Zorryy_sorry
@Zorryy_sorry
ልትልኩልን ትችላላችሁ !!!
፨ይቅርታ ማለት ታላቅነት ነው!!!
@Zorryy_sorry
@Zorryy_sorry
@Zorryy_sorry
@Zorryy_sorry
ስሙን ✍
ፎቶውን 🖼
እና
Voice ይፈቀዳል
ይቅርታቹን አጠር አድርገው 👇
@Zorryy_sorry
@Zorryy_sorry
@Zorryy_sorry
ልትልኩልን ትችላላችሁ !!!
፨ይቅርታ ማለት ታላቅነት ነው!!!
@Zorryy_sorry
@Zorryy_sorry
@Zorryy_sorry
@Zorryy_sorry