✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.06K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
Audio
እሠይ_ተወለደ_የአለም_መድሀኒት||የገና መዝሙር|| orthodox_Ethiopia ||
እኛስ በሥጋ ከማርያም #የተወለደውን ክርስቶስን እንሰብካለን
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መግለጫ ተሰጠ ።

መግለጫውን ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) የሠጡት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፖትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት; ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ : በመንበረ ፓትርያርክ የተገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው።

ቅዱስነታቸው ዛሬ ማለዳ በተሰማው ሕገ ወጥ "ሢመተ ጳጳሳት" ጉዳይ በሰጡት መግለጫ ጉዳዩ ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ በሕገወጥነት የተከናወነ መሆኑን በመግለጽ :-
1. በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት በአስቸኳይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ እንዲመጡ ጥሪ ቀርቧል።
2. መንግሥት ክስተቱ በሀገር ላይ ጭምር የሚያስከትለውን ጉዳት ተመልክቶ በጉዳዩ ላይ ሕጋዊ ሓላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።
3. ምዕመናን ቤተክርስቲያንን ከመቸውም ጊዜ በላይ በንቃት በሀሣብና በጸሎት እንዲጠብቁ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ: EOTC TV
ከማኅበረ ቅዱሳን በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ
#ልዩ_መረጃ

በ"አባ" ሳዊሮስ አማካይነት ከታች የተዘረዘሩት አህጉረ ስብከት ላይ የስምዝርዝራቸው የሚገኘው መነኮሳት የአህጉረ ስብከቱ መንበረ ጵጵስ እና ከቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድና እውቅና ውጭ ወረራ እንዲፈጸምበት ስምሪት የተሰጠ በመሆኑ በየአካባቢው የምትገኙ ካህናትና ምዕመናን መንበረ ጵጵስና አህጉረ ስብከቱን እንድትጠብቁ ጥሪ ቀርቧል!

1."አባ" ገ/ማርያም ነጋሳ - ምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት
2."አባ" ተ/ሃይማኖት ወልዱ - ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት
3."አባ" ገብርኤል ወ/ዮሐንስ - ጉራጌ ሶዶ ሀገረ ስብከት
4."አባ" ገ/እግዚአብሔር ታደለ - ምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት
5."አባ" ሚካኤል ገ/ማርያም - ከምባታ ሀገረ ስብከት
6."አባ" ኃይሉ እንዳለ - ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት
7."አባ" ተ/ማርያም ስሜ - ጉጂ ሊበን ሀገረ ስብከት
8."አባ" ኃ/ኢየሱስ መንግስቱ - ከፋ ሀገረ ስብከት
9."አባ" ወ/ኢየሱስ ኢፋ - ቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት
10."አባ" ጳውሎስ ከበደ - ሀዲያ ሀገረ ስብከት
11."አባ" ኃ/ኢየሱስ ተስፋዬ - ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት
12."አባ" ገ/ኢየሱስ ገለታ - ሆሮ ጉዱሩ ሀገረ ስብከት
13."አባ" ጸጋዘአብ አዱኛ - ምሁር ኢየሱስ ገዳም "የበላይ ጠባቂ"
14."አባ" ኃ/ማርያም ጌታቸው - ምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት
15."አባ" ወ/ጊዮርጊስ ኃ/ሚካኤል - ከሚሴ ሀገረ ስብከት
16."አባ" እስጢፋኖስ ገብሬ - ባሌ ሀገረ ስብከት ረዳት
17."አባ" ገ/መድኅን ገ/ማርያም - ጎፋ ባስኬቶ ሀገረ ስብከት
18."አባ" ኃ/ሚካኤል ንጉሤ - ጊኒር ሀገረ ስብከት
19."አባ" አብርሃም መስቀሌ - ዳውሮ,ኮንታ ሀገረ ስብከት
20."አባ" ንዋየ ሥላሴ አክሊሉ - ምዕራብ ጉጂ ሀገረ ስብከት
21.አባ ኪ/ማርያም ቶሎሳ - ጅማና የም ሀገረ ስብከት
22."አባ" ወ/ማርያም ጸጋ - ቦረና ሀገረ ስብከት
23."አባ" አምደሚካኤል ኃይሌ - አርሲ (አሰላ) ሀገረ ስብከት
24."አባ" መርሐጽድቅ ኃ/ማርያም - ጌዴኦ,ቡርጁ,አማሮ ሀገረ ስብከት
25."አባ" ሞገስ ኃ/ማርያም - መናገሻ አምባ ቅድስት ማርያም ፣ ጋራ መ/ዓለምና ደ/ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ "የበላይ ጠባቂ"
26."አባ" ገ/ኢየሱስ ንጉሤ - ቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት

መረጃው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ነው
መልዕክቱን ለሁሉም በማዳረስ ግዴታዎን ይወጡ ።
“ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያ እንተ ላዕለ ኲሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት፤ ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን”
ጸሎተ ሃይማኖት

#አሐቲ_ቤተ_ክርስቲያን
#አሐዱ_መንበር
#አሐዱ_ሲኖዶስ
#አሐዱ_ፓትርያርክ
የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ቀኖናዊት ናት!

ማኅበረ ቅዱሳን

https://t.me/mahibere_kidusan
“ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያ እንተ ላዕለ ኲሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት፤ ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን”
ጸሎተ ሃይማኖት
#አንዲት_ቤተ_ክርስቲያን!
#አንድ_መንበር
#አንድ_ሲኖዶስ
#አንድ_ፓትርያርክ
የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ቀኖናዊት ናት!
ማኅበረ ቅዱሳን
https://t.me/mahibere_kidusan
ዐዋጅ… ዐዋጅ…ዐዋጅ… !

"…የሰማ ይስማ…! ልሰማም ያሰማ…!!

"…በዛሬው ዕለት የቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ቅድስት ማርያም ገዳም ከተጠናቀቀ በኋላ ሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በያሉበት ክፍለዓለም ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሦስት ቀናት የጸሎትና የሱባኤ ጊዜ እንዲሆን ዐዋጅ መታወጁን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገልጸዋል፡፡

"…ከነገ ሐሙስ ጀምሮ እስከ መጪው ቅዳሜ ድረስ ጠዋት ጠዋት ከጸሎተ ኪዳን በኋላ፣ መታ ሰርክ ጉባኤ ሲያበቃ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ በአጥቢያው ቢተ ክርስቲያን ተገኝቶ በጸሎተ ምሕላው ይሳታፍ። የቻለ ከአልጋ ወርዶ መሬት ይተኛ፣ የጣመ የላማ መብላት ያቁም። ጸሎት የማይለውጠው ነገር የለም እና ከመውደቅ ከመነሣት ከእንባም ጭምር እንጸልይ። ከዚያ ደግሞ እሑድ አስተርእዮ ማርያም ናት። ዘመነ መገለጥም አይደል። ሃሴት እናደርጋለን።

"…ይህ የአባቶቻችን የሐዋርያት ትእዛዝ ነው። ሰው በልቦናው ቂምንና በቀልን ቅንዓትንና ጠብን በባልንጀራው ላይ በማንም ላይ ቢሆን አይያዝ። መጽሐፈ ቅዳሴ። አምላካችን ሆይ…! እንደቸርነትህ ነው እንጂ እንደ በደላችን አይሁን። አሜን…!

"…ሰምታችኋል ጓደኞቼ? ዝግጁ ናችሁ? እስቲ ዓለሙ ሁሉ ይመልከተን ዝግጁነታችሁን ግለጹ።
Forwarded from Solomon Admasu (Dn)
#ኦርቶዶክሳዊ ቻሌንጅ

ውድ ተመልካቾቻችን ይህ የማህበረ ቅዱሳን ቻናል ለእናንተ በየሰዓቱ መረጃዎችን በማቅረብ ይገኛል።ነገር ግን ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን መዳረስ እየቻለ ስላልሆነ ይህን መልዕክት ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን በመላክ ቻናሉን እንዲቀላቀሉና መረጃዎቹን እንዲያገኙ አድርጉ።

ቻሌንጁ ማን ብዙ ሼር ያደርጋል ነውና ያላችሁበት ቻናልና ግሩፕ ላይ ሁሉ ሼር አድርጉ።

https://t.me/mahibere_kidusan
https://t.me/mahibere_kidusan