✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.06K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
ካላንደር ሳይዘጋው መንገድ የዘጋው ሜክሲኮ ልደታ።
+ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ +

አንድ ሰው እኔ ክርስቲያን ነኝ ሲል በአንድ ቃል ዜግነቱንና ቤተሰቡን ሥራውን ጠቅልሎ ተናገረ ማለት ነው:: የሚያምን ሰው ከሰማያዊት ኢየሩሳሌም በቀር ምድራዊ ከተማ የለውም"

🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

"እግዚአብሔር የሚጠይቅህ ጥቂት ነው የሚሠጥህ ግን ብዙ ነው

🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

"የዚህ ዓለም ኑሮ እንደ እንቅልፍ ነው:: በዚህ ሕይወት የሚሆኑት ሁሉ ሕልም ናቸው::
በሕልምህ ባለጸጋ ብትሆን ምን ጥቅም አለው? በእንቅልፍ ልብ ሆኖ በቅዠት የሚናገር ሰው ስለ ንግግሩ አይፈረድበትም:: እኛ ግን በዚህ የእንቅልፍ ዘመን የምንናገረው ሁሉ የዘላለም ሕይወትን ሊያሳጣን ይችላል"

🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

"በድህነት እና በረሃብ የሚሰቃዩ ሰዎች እንደ ሠለስቱ ደቂቅ ናቸው:: ከድህነት የበለጠ ምን እሳት አለ? ከረሃብስ የሚበልጥ ምን ነበልባል አለ?
ሦስቱ ወጣቶች እሳት ውስጥ ሆነው እንደዘመሩ በመከራ ውስጥ ሆኖ ፈጣሪን የሚያመሰግን ሰው የመከራው እሳት ውኃ ይሆንለታል:: ለድሆች ምጽዋትን የሚሠጥ ሰው ደግሞ ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት የታደገውን የእግዚአብሔር መልአክን ይመስለዋል"

🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

በትንንሽ ነገሮች ማመስገንን ከለመድህ ትንንሽ ነገሮች ብዙ ስለሆኑ ሕይወትህ ምስጋና ይሆናል"

🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

በኀዘን ጊዜ የማያጉረመርሙ ከንፈሮች ከቅዱሳን ሰማዕታት እኩል ናቸው

🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

ሕይወታችን ለሌሎች የሚያበራ ቢሆን ኖሮ ስብከት ባላስፈለገ ነበር:: በምግባራችን መመስከር የምንችል ብንሆን ኖሮ ቃላት ባላስፈለጉ ነበር:: እውነተኛ ክርስቲያኖች ብንሆን ኖሮ አረማውያን ባልበዙ ነበር

ግንቦት 12 ተዝካረ ዕረፍቱ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ወፍልሰተ አጽሙ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ወበዓላ ለቅድስት እምነ ክርስቶስ ሠምራ

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ና ብፁዕ አቡነ አብርሀም
የተሰጣቸውን የስራ ሃላፊነት በትህትና ሲቀበሉና ከቅዱስ ፓትርያርኩና ከብፁዓን አበው ሥር ወድቀው ቡራኬ ሲቀበሉ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ምክንያት አለን ድንግል አንቺን የያዝንበት
​​ፆመ ሐዋርያት

አንዳንዶች የሰኔ ፆም የቄስ ፆም ነው በሚል ከመፆም ወደኋላ ሲሉ ይታያሉ ነገር ግን ቅድስት ቤተክርስቲያን በአዋጅ ከምትፆማቸው ሰባት አፅዋማት አንዱ እንደመሆኑ መጠን እያንዳንዱ ክርስቲያን ቢፆመው እጅግ በርካታ በረከቶችን ያገኝበታል ከነዚህም ጥቂቶችን እነሆ

1.በረከተ ሐዋርያት ይገኝበታል
ይህን ፆም መጀመርያ ፆመው እንድንፆመው ሰርዐት የሰሩልን ሐዋርያት ናቸዉ ስለዚህም ፆሙ መታሰቢያነቱ የሐዋርያት ነው የጻድቅ መታሰቢያ ደግሞ ለበረከት ነው ። ምሳ.10፥7 እኛም የሰኔን ፆም ብንፆም የሐዋርያቱን በረከት እናገኛለን ሐዋ.13፥1-3 ሐዋ.14፥23

2. በስራችንና በአገልግሎታችን በረከት እናገኛለን
ሐዋርያት ይህን ፆም የፆሙት አገልግሎታቸው እንዲከናወንላቸው እንዲባረክላቸው ነው ነብዩ ነህምያም እየሩሳሌምን የመስራት ተግባሩ እንዲባረክለት በፆመው ፆም ስራው ሁሉ ተባርኮለታል። ነህም.1፥4። እኛም የሰኔን ፆም ብንፆም በዕለት ተዕለት ተግባራችን በረከት እናገኛለን።

3. ዝናብ ምህረትን ጠለ በረከትን እናገኛለን
የሰኔ ፆም በአገራችን የክረምቱ መግቢያ ላይ የሚፆም ፆም ነው ይህም መጪው የክረምቱ ወራት የተስተካከለ የምህረት ዝናም እንዲኖረው ያደርጋል በነብዩ ኢዩኤል ዘመን ዝናብ ጠፍቶ ዛፎቹ ሳይቀር በደረቁ ጊዜ በፆም በፀሎት ወደ እግዚአብሔር በተማፀኑ ሰዓት ዝናመ በረከትን አግኝተዋል። ኢዩ.1፥13-14

4. በረከተ ምርትን እናገኛለን
የሰኔ ፆም በሃገራችን ገበሬው ዘር መዝራት በሚጀምርበት ጊዜ የሚፆም ፆም ነው ሰለዚህም በዚህ ሰዓት የሚፆመው ፆም ዘርን እንዲባረክ በረከት እንዲበዛ ያደርጋል ይህም አገር ወገን ከረሃብ ከችግር ነፃ እንዲወጣ ያደርጋል በነብዩ ኢዩኤል እንደተገለጸው በፆም የዕህል የመጠጥ በረከት ይገኛል ። ኢዩ.2፥12-14

5. የነፋስ በረከትን እናገኛለን
ፆም በመንፈስ የደከመች የዛለች ነፍስን ያበረታል የነፍስን ቁስል ይፈውሳል ስጋዊ ኃይልን ያደክማል የሥጋን ፈቃድ ለነፍስ ያስገዛል መዝ.108፥24 ፤ ገላ.5፥24 የዓለምን ሃሳብ ያስወግዳል ከእግዚአብሔር ያስታርቃል ማቴ. 17፥21 ሚስጥር ይገልጣል ዘስ.34፥27-28 ፤ ዳን. 10፥1-3 "በአምላካችን ፊት እራሳችንን እናዋርድ ዘንድ ከርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ ...... ፆምን አውጃለሁ " መጽሐፈ ዕዝራ.8፥21 ከመዋዕለ ፆሙ ረድኤት በረከት ያሳትፈን !

ፆሙን የኃጢአት መደምሰሻ የዲያብሎስ ድል መንሻ የመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ያድርግልን አሜንንንን !!!

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur
ደብረ ዕንቁ ልደታ ማርያም
"…ዝርዝሩን በምሽቱ የራስ ሚዲያ መርሀ ግብሬ ላይ እመጣበታለሁ። የኦሮሞ የወሀቢይ እና የኦሮሞ ጴንጤ የብልፅግና የጥፋት ነውረኛ ጦር ግን የሌለ እያፈላ ያለ ቢሆንም ታላቋን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ግን እንደማያናውጣት ከወዲሁ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።

"…የተፈለገው ቅዱስነታቸውን አሸማቅቆ ከተቻለ በዚያው ለማስቀረትና በመጅሊሱ ላይ የሞከሩትን መፈንቅለ ሙፍቲና የኦሮሞ ወሃቢ የቱፋን ልጅ የሾመው የዐቢይ መንግሥት አሁን ደግሞ ወደ መፈንቅለ ሲኖዶስ በመዞር የዕድሉን ሊሞክር እንደሆነ ይገመታል። ለዚህ ነው ከሌሊት ጀምሮ የብልፅግና መንግሥት አክቲቪስቶች እነ ጌጡ ተመስገንን ጨምሮ " ቅዱስነታቸው ወደ ሀገረ አሜሪካ ሲወጡ ወርቅን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች በቦሌ አውሮጵላን ጣቢያ ተያዙ" በማለት ሲያጮሁት ያረፈዱት።

"…ሲጀመር የደህንነት መሥሪያ ቤቱ ቪድዮ ቀርጾ ለዘ ሀበሻ የሚሰጠው በምን አግባብ ነው? ሃገሪቱ እንደሆነ አንድ ጊዜ በማይረቡ አልባሌ ተራ አውርቶ አደር ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ ተዋሕዶ በሆኑ ስብስቦች እጅ ወድቃለች። እናም ከዚህም ሌላ ቢባል አይደንቀንም። የትግሬ ጥላቻ ናላቸውን ያዞራቸው የብአዴን ቡችሎችም እንዲሁ ሲላላጡና ቅርሻታቸውን ሲተፉ ነበር የዋሉት።

"…እኔ እንኳን በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የከፋ ነገር ካልመጣ በቀር አልገባም ብዬ ነበር። ሆኖም ግን እንዲህ ከአቅም በላይ የሆነ ጦር ሲበዛ ዝም ማለቱ አዋጭ ስላልሆነ ነው ብቅ ያልኩት። የተዘረፈ ንብረት የለም። ሁሉም መንግሥት የሚያውቀው ነው። የሕግና የሥርዓት ቤት የሆነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት የምትጥስበት ሞራልም፣ ቀኖናም የላትም።

"…ፓትርያርኩን በተመለከተ በአሜሪካ ምን ሊፈጠር ይችላል ለሚለው በኋላ በራስሚዲያ የግል ሃሳቤን አቀርባለሁ። ለአሁኑ ግን እነ ጌጡ፣ እነ ዘሀበሻ እረፉ። እጃችሁን ከቤተ ክርስቲያን ላይ አንሡ።
Watch "ድንግል ማርያም #ማርያም #shorts ##subscribe #ማኀቶት" on YouTube
https://youtu.be/IZDg9MeQ7CQ
🎬 ©ንስሀ" ሐና ዳኘው |Niseha| Hana dagnew

⭕️ሊደመጥ ሚገባ⭕️

👤 ኪነ ተዋህዶ ቲዩብ

⚠️ ለማዳመጥ ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
🛑👇👇🛑
https://youtu.be/QzrSmQi4Qp0
https://youtu.be/QzrSmQi4Qp0
https://youtu.be/QzrSmQi4Qp0
🎬 ©ፈፅሞ ልትረሳቸው ማይገቡ ጉዳዮች" ሐና ዳኘው | Hana dagnew

👤 ኪነ ተዋህዶ ቲዩብ

⚠️ ለማዳመጥ ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/cb164bbwcKU
https://youtu.be/cb164bbwcKU
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
የመስቀል ደመራ በዓል ታሪክና አከባበር

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ከወደቀበት መርገም ያድነው ዘንድ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በ33 ዓመቱ በራሱ ፈቃድ በመስቀል ላይ ተሰቀለ፡፡ በመገረፉ ቁስል እኛ ተፈወስን (1ጴጥ 2፥24):: በስቅለቱም ዲያብሎስን ድል ነሥቶ በወህኒ /በሲዖል/ ለነበሩ ነፍሳት ነጻነትን ሰበከላቸው (1ጴጥ 3፥18-19):: የሰው ልጅ በሙሉ ከዲያብሎስ ባርነት ፍጹም ነጻ ወጣ:: ሰላምንም ያደርግ ዘንድ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ ሕዝብና አሕዛብን በአንድ አካል ከራሱ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀ (ኤፌ 2፥16)፡፡ ከፍተኛ ወንጀል የሠሩ ሰዎች ብቻ ይሰቀሉበት የነበረው መስቀል ከጌታ ስቅለት በኋላ የመዳን ምልክት ሆነ::
ዳሩ ግን ጌታ የተሰቀለበት መስቀል ተአምራትን በማድረጉ የታወኩ አይሁድ መስቀሉን ከሰዎች እይታ ለመሠወር ወሰኑ:: ጉድጓድ ቆፍረው ቀበሩት:: መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ ለ300 ዓመታት ያህል የቆሻሻ መጣያና ማከማቻም አደረጉት:: ምንም እንኳን አይሁድ ለጊዜው መስቀሉን ከዐይን ለመሰወር ቢችሉም ከክርስቲያኖች ልቡና ግን ሊያወጡት አልቻሉም:: የመስቀሉ ብርሃን በልቡናቸው የሚያበራ ክርስቲያኖች እየበዙ መጡ:: መስቀሉንም መፈለግ ጀመሩ::

#ለወዳጆ_ሼር_ያድርጉ
╔═★══════════📄══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══📃══════════★═╝
የንግሥት እሌኒ ድካምና ፍሬ

ንግሥት እሌኒ ልጇን ቆስጠንጢኖስን ከልጅነቱ ጀምሮ ስለ ክርስትና ሃይማኖትና ስለ ክርስቲያኖች መከራ ታስተምረው ስለነበር በክርስቲያኖች ላይ የነበረው አመለካከት በሮም ከነገሡት ቄሣሮች ሁሉ የተሻለ ነበር፡፡ ቆስጠንጢኖስ የሮም ንጉሠ ነገሥት ከሆነ በኋላ በ300 ዓመታት ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ ለክርስቲያኖች የነጻነት ዐዋጅ ዐወጀ፡፡ ክርስትናም ብሔራዊ ሃይማኖት ሆነች፡፡ ንግሥት እሌኒም የተፈጠረውን አመች ሁኔታ በመጠቀም የጌታችንን መስቀል ከተቀበረበት ለማውጣት በ327 ዓ/ም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች፡፡
ንግሥት እሌኒ ልጇ ቆስጠንጢኖስ ክርስቲያን ከሆነላት ወደ ኢየሩሳሌም ሔዳ መስቀሉን ለመፈለግ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ያሉ ቅዱሳት መካናትንና አብያተ ክርስቲያናትን ለማሳነፅ ለእግዚአብሔር ተሳለች፡፡ ከዚህ በኋላ ቆስጠንጢኖስ አምኖ በ337 ዓ/ም ተጠመቀ፡፡ ቅድስት እሌኒም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች እንደደረሰችም ስለ ክብረ መስቀል መረመረች ጠየቀች፡፡ ቦታውን የሚያስረዳት ግን አላገኘችም፡፡ አይሁድ የተቀበረበትን ቦታ ለማሳየት ባይፈልጉም በኋላ ባደረገችው ጥረት አረጋዊው ኪራኮስ የጎልጎታን ኮረብታ አመላከታት ዳሩ ግን ኪራኮስ ዘመኑ ከመርዘሙ ጋር ተያይዞ በአካባቢው ከነበሩት ከሦስቱ ተራሮች ውስጥ መስቀሉ የሚገኝበት የትኛው እንደሆነ ለይቶ ማወቅ አልቻለም፡፡
ንግሥት እሌኒ ከሦስቱ ተራሮች የቱ እንደሆነ ለመለየት በእግዚአብሔር መልአክ እርዳታ ደመራ አስደምራ ብዙ እጣንም በመጨመርና በማቃጠል ጸሎት ተያዘ፡፡ የእጣኑ ጢስ ወደ ሰማይ በመውጣት በቀጥታ ተመልሶ መስቀሉ ባለበት ተራራ ላይ በማረፍና በመስገድ መስቀሉ ያለበትን ትክክለኛ ስፍራ አመለከታት፡፡ ቅዱስ ያሬድም ጢሱ ሰገደ ብሎታል፡፡ ከዚያም መስከረም 16 ቀን ቁፋሮው እንዲጀመር አዘዘች፡፡ ሰባት ወር ያህል ከተቆፈረ በኋላ መጋቢት 10 ቀን ሦስት መስቀሎች በአንድነት ተገኙ፡፡የክብር ባለቤት ጌታችን የተሰቀለበት የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ተቸገሩ፡: መስቀሎቹን ወስደው በሞተ  ሰው በተራ ቢያስቀምጡ ጌታችን የተሰቀለበትና በዕለተ ዐርብ ተሰቅሎ የዋለበትና በደሙ መፍሰስ የተቀደሰው መሰቀል የሞተውን ሰው በማስነሣት በሠራው ተአምር ሌሎቹ ሁለቱ ታምራት ባለማድረጋቸው የጌታን መስቀል ለይቶ ማወቅ ተችሏል። እሌኒና ክርስቲያኖች ሁሉ ለመስቀሉ ሰገዱለት፡፡ በየሀገሩ ያሉ ክርስትያኖች ሁሉ የመስቀሉን መገኘት በሰሙ ጊዜ መብራት አብርተው ደስታቸውን በመግለጥ ለዓለም እንዲታወቅ አደረጉ፡፡ ንግሥት እሌኒ ለመስቀሉ ቤተ መቅደስ ከሠራችለት ጊዜ ጀምሮ በመስከረም 17 ቀን አሁን በኢትዮጵያ እንደሚከበረው በክርስቲያኖች ዘንድ መስቀል ይከበር ነበር።

#ለወዳጆ_ሼር_ያድርጉ
╔═★══════════📄══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══📃══════════★═╝
ግማደ መስቀሉ ወደ ኢትዮጵያ እንዴት መጣ? 

የጌታ መስቀል ለብዙ ዓመታት በኢየሩሳሌም ከቆየ በኋላ ነገሥታት መስቀሉን ለመውሰድ ጠብ ፈጠሩ፡፡ በዚህ ጊዜ የአንጾኪያ፣ የኤፌሶን፣ የአርማንያ፣ የግሪክ፣የእስክንድርያ፣ የመሳሰሉት የሃይማኖት መሪዎች ጠቡን አበረዱት:: ከዚያም አያይዘው በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የክርስቶስን መስቀል ለዐራት ከፍለው በስምምነት ተካፍለው ከሌሎች ታሪካዊ ንዋያተ ቅድሳት ጋር በየሀገራቸው ወስደው በክብር አስቀመጡት:: የቀኝ ክንፉ የደረሰው ለአፍሪቃ ስለነበር ከታሪካዊ ንዋየ ቅድሳት ጋር በግብፅ የሚገኘው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ተረክቦ ወስዶ በክብር አስቀመጠው፡፡
ኢትዮጵያዊው ንጉሥ ዳግማዊ ዳዊት የግብፅ ክርስቲያኖች በአማሌቃውያን ከሚደርስባቸው ተጽዕኖ ነጻ እንዲወጡ በማድረጋቸው የግብፅ ፓትርያርክ የከበሩ ስጦታዎችን ላኩላቸው:: ንጉሥ ዳግማዊ ዳዊት ግን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የምትፈልገው ወርቅ ሳይሆን ጌታ የተሰቀለበትን መስቀሉን እንደሆነ ገለጹላቸው:: በመሆኑም የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ግማደ መስቀሉን ከሌሎች ንዋየ ቅድሳት ጋር ለኢትዮጵያ ሰጥታለች:: ይህ ግማደ መስቀል በግሸን ማርያም ገዳም በእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ሆኖ ኢትዮጵያን እየባረከ ይገኛል::
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መስቀልን ከሐዋርያት በተማረችው መሠረት የወርና የዓመት በዓል ሠርታ ታከብረዋለች:: መስከረም 16 ቀን ደመራ ደምራ ጸሎትና ምሥጋና ታቀርባለች። ቅዱስ መስቀል ከተቀበረበት መሬት በእሌኒ አማካኝነት መገኘቱን ስታስብ በአሁኑ ዘመን ከብዙ ሰዎች ልቡና የተሠወረው መስቀል እንዲገለጥላቸው ትጸልያለች:: በመስቀል የሚገኘውን በረከት እየተቀበለች በመስቀል የሚመሰለውን መከራ ሁሉ ትታገሣለች:: መስቀል በካህናት በምእመናንና በምእመናት ልቡና ተስሏል:: በአንገታቸውና ልብሳቸውም መስቀል አለ:: ሥራ ሲጀመርና ምግብ ሲቀርብ በመስቀል አምሳያ ይማተባል:: መስቀል ለሁሉም ነገር መጀመሪያና መጨረሻ  ነው:: “እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ” (ማቴ 16፡24) እንዳለ ጌታችን ቤተ ክርስቲያናችን ዕለት ዕለት መስቀሉን ትሸከማለች።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ መስከረም 16 ቀን የምትደምረው ደመራ አገራዊ አንደምታም አለው:: የመስቀል ደመራ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት: የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) እውቅና ተሰጥቶት ዓለም አቀፋዊ ቅርስ ተብሎ ተመዝግቧል::
ከሀገር ቤት ርቀን የምንገኝ ኢትዮጵያውያንም የበዓሉን ታላቅነት ለልጆቻችንና ለምንኖርበት የኖርዌይ ኅብረተሰብ ማስረዳትና የበዓሉ ታዳሚ እንዲሆኑ ማድረግም ይጠበቅብናል። «የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚብሔር ኃይል ነው» (1ቆሮ 1፥18) እያልን ልናከብረውና ልንጠብቀው ይገባናል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

#ለወዳጆ_ሼር_ያድርጉ

╔═★══════════📄══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══📃══════════★═╝
"አባ አባ ተክለሃይማኖት"
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
አባ አባ ተክለሃይማኖት

አባ አባ ተክለሃይማኖት አቡዬ /2/
በለኒ በለኒ ወልድየ /2/
አዝ
አባ አባ - - - እንኳን ሰው ምድሪቱን
አባ አባ - - - ጦም አያሳድርም
አባ አባ - - - አምላከ ተክልዬ
አባ አባ - - - ብዬ አፍሬ አላውቅም
አባ አባ - - - ምድራዊ መልዓክ ነህ
አባ አባ - - - የእቲሳ አምበሳ
አባ አባ - - - ለደብረ ሊባኖስ
አባ አባ - - - አንተ ነህ ሞገሷ
አዝ
አባ አባ - - - ስማኒ ብያለው
አባ አባ - - - ሳለ በሰማይ
አባ አባ - - - ከኪሩቤል ተርታ
አባ አባ - - - ሆነህ ስትታይ
አባ አባ - - - ስምህም ሲጠራ
አባ አባ - - - ገድልህ ሲነገር
አባ አባ - - - እፁብ ድንቅ ያሰኛል
አባ አባ - - - የተሰጠህ ክብር
አዝ
አባ አባ - - - አባቴ እልሃለው
አባ አባ - - - ልጄ ሆይ በለኝ
አባ አባ - - - የአባትና የልጅ
አባ አባ - - - ፍቅርህ ይጽናልኝ
አባ አባ - - - ንፍሮ ውሃ ጠጥቼ
አባ አባ - - - ታምር አይቻለሁ
አባ አባ - - - እባብና ጊንጡን
አባ አባ - - - ተረማምጃለሁ
አዝ
አባ አባ - - - እለት በለት ሄጄ
አባ አባ - - - ደጅ ስጠናው
አባ አባ - - - ይሰማል ተክልዬ
አባ አባ - - - ዛሬም ህያው ነው
አባ አባ - - - እንቆቅልሽ ፈቶ
አባ አባ - - - ደስ አሰኝቶኛል
አባ አባ - - - የተክለሃይማኖት
አባ አባ - - - ቡራኬው ደርሶኛል
ጌታችን ኢየሱስ🥹🤗🙏

እሰይ ተወለደ..
Audio
እሠይ_ተወለደ_የአለም_መድሀኒት||የገና መዝሙር|| orthodox_Ethiopia ||