✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.06K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
ከበኩረ ሰባክያን ምህረተአብ አሰፋ የተላከ መልዕክት

ተደዋወል፣ተነጋገር፣ተመካከር፣ይበቃል በል።ሌላው በኛ ቤት እንደልቡ ሲሆን፣ምን ያመጣሉ፣አንድ ሰሞን ተንጫጭተው፣በዛው ይቀራሉ፣እያለ ሲናገር፣አንተ ግን በገዛ ቤትህ መሰብሰብና መፍትሄ ማፈላለግ ካቃተህ፣በእውነት የአቡነ ጴጥሮስ አጽም እሾህ ሆኖ እንዳይወጋህ፣ረቡዕ ጥር 4 በቦሌ መድኃኔዓለም እንገናኝ።

Share አድርጉ!!!! ስልክህ ተዓምር መስራት ይችላል!
ፈዘናል ፈዘናል ፈዘናል!!
ሲጠበቅ የነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ተራዘመ።
(ኢኦተቤ ቴቪ ጥር ፮ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም
ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር ፮ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ሊያደርግ ያሰበው ስብሰባ በቅዱስነታቸው አለመገኘት ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፏል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በገጠማቸው የጤና ችግር ምክንያት ሆስፒታል ስለገቡና ቅዱስነታቸው በመንበራቸው ላይ በሌሉበት ሁኔታ ጉባኤውን ማካሔድ ስለማይቻል የቅዱስ ፓትርያርኩ ጤና እስከሚመለስ ድረስ ጉባኤው ላልተወሰነ ጊዜ የተላለፈ መሆኑን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ገልጿል። እግዚአብሔር ለቅዱስነታቸው ምሕረቱን ሰጥቶ ወደ መንበራቸው ይመለስልን።
ፎቶ:- ከፋይል
“ከሕማሜ ይልቅ የመስቀል ዐደባባይ ነገር ይበልጥ ያሳስበኛል”

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

በእርሳቸው ሆስፒታል መግባት ከከንቲባዋ ይደረጋል የተባለው ስብሰባ ላልተወሠነ ጊዜ መተላለፉን ሲሰሙ የተናገሩት ነው።

፩. በእርሳቸው አለመገኘት ምክንያት ቀኑ ተላልፎ ተረሳስቶ እንዳይቀር ለዚህ ስብሰባ ብቻ ቀኖናው በሚፈቅደው መሠረት ከአረጋዊያኑ ወይም በፓትርያርኩ ውክልና የሲኖዶሱ ጸሐፊ እንዲመሩት ቢደረግ፣

፪. ከንቲባዋ እኔ ቢሮ ወይም ሸራተን እንሰብሰብ ማለታቸው የተሰማ ሲኾን አቡነ ዮሴፍ ግን ወደ መንበረ ፓትርያርክ እርሳቸው መምጣት እንዳለባቸው በጽኑ አሳስበዋል። አበው በዚህ አቋም ቢጸኑ፣

፫. ከከንቲባዋ ጋር የሚደረገው ውይይት ከመስቀል ዐደባባይ ከፍ ያለ ቢኾን።

፬. አሰላለፋቸውን ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ለቤተ መንግሥቱ ለማድረግ የሚራወጡ አንድ ጳጳስ ዐርፈው እንዲቀመጡ የመጨረሻ ተግሣጽ ቢሰጣቸው።

የቅዱስነታቸው ጤንነት ከፍተኛ መሻሻል እያሳየ መኾኑም ታውቋል።
ምንጭ# ከዲ/ን ዓባይነህ ካሤ ገፅ
Watch "አረሳት ኢትዮጵያን // Aresat ethiopian ሊቀ መዘምራን ይልማ ሐይሉ" on YouTube
https://youtu.be/H1Fc8nshWrI
ቋሚ ሲኖዶስ ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ የቤተክርስቲያንን መብትለማስከበር ይሰራል ።
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የመስቀል አደባባይ፣የጃንሜዳና ሌሎች የቤተክርስቲያን ይዞታዎች ጉዳይ በተመለከተ ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ
አዳነ ች አቤቤ ጋር ለመነጋገር ዛሬ ጥር 25/2014 ዓ.ም ይዞት በነበረው ቀጠሮ ዙሪያ ባካሔደው ስብሰባ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር የሚደረገው ውይይት ቋሚ ሲኖዶስ በሚያስቀምጠው አቅጣጫና ጊዜ ቀጠሮ መሰረት በተለዋጭ ቀጠሮ የሚካሔድ ይሆናል።
የከተማ አስተዳደሩም ቤተክርስቲያን በምታሳውቀው ጊዜ ቀጠሮ ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ዛሬ አስታውቋል።
ቅዱስ ሲኖዶስም ከሚቀጥለው ቀጠሮ ጀምሮ ሕጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ የቤተክርስቲያኒቱ ጥያቄ ሕጋዊ ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

ኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት
ቋሚ ሲኖዶስ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተወካዮች ጋር ባደረገው ውይይት በመጪው ማክሰኞ ከንቲባዋ በተገኙበት ለመወያየት ቀጠሮ ያዘ።
*****************************
የካቲት 4ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ለዛሬ ቋሚ ሲኖዶስ ከከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር ለመወያየት ቀጠሮ ተይዞበት በነበረው አጀንዳ ዙሪያ የከተማ አስተደዳደሩ ተወካዮቹ ከቋሚ ሲኖዶስ አባላት
ጋር ከተወያዮ በኋላ ከንቲባዋ ቀድሞ በተያዘው የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ስብሰባ ምክንያት ዛሬ መገኘት ስላልቻሉ ቀጣዩ ውይይት በመጪው ማክሰኞ የካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ከንቲባዋ በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርኩ የቋሚ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይቱን ለማድረግ እና ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቀጠሮ መያዙን ቅዱስ ፓትርያርኩና የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ በሰጡት የጋራ መግለጫ አረጋግጠዋል።
Watch "መጋቢ ብሉይ መምህር ገብረኪዳን ግርማ || Ethiopia ortodox mezmure" on YouTube
https://youtu.be/zRIpt8LHSRM
Watch "ዲያቆን ሄኖክ ሐይሌ |ንስሀ || diakon henok haile" on YouTube
https://youtu.be/idFk5EYi6FM
አሳዛኝ ዜና 😭😭😭😭

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አራተኛ ፓትርያሪክ ብፅእ አቡነ መርቆሪዎስ ከዚ አለም እረፍት ድካም አለፉ

በረከቶ ይደርብን
╔═★══════════📄══╗
@Zemaryan
@Zemaryan
@Zemaryan
╚══📃══════════★═╝
አትስጉን፣አትፍሩን፣እኛ ኦርቶዶክሳውያን ጥልን በክርስቶስ መስቀል ገለን፣ሰላምን ለዓለም የምናውጅ እንጂ የሰላም ሥጋት አይደለንም።በነገው የቅዱስ አባታችን የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ በመስቀል አደባባይ የምንገኝበት ምክንያት ፣ 1ኛ የቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሳቢ፣ የመንጋውና የቅድስት ቤተክርስቲያናችን መሪ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀዳማዊ ፓትርያርክ የሆኑት ታላቁ አባታችን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ በሥጋ ስለተለዩን ሀዘናችንን ለመግለጽ ነው። 2ኛ ቅዱስ አባታችን ታላቅ የበረከት አባት ስለሆኑ የቅዱስነታቸውን በረከት ለመቀበል ነው።ምክንያቱም እግዚአብሔር የቅዱሳኑን አጽም ስለሚጠብቅ፣በኤልሳዕ አጽም ሙት ያነሳና ተአምር ያሳየ እግዚአብሔር፣ ዛሬም በቅዱስ አባታችን አጽም ፣ለህዝባችንና ለሀገራችን ተአምር ይሰራል፣የኢትዮጵያንም ትንሳኤ ያረጋግጥልናል ብለን ስለ ምናምን ነው።የድንግል ልጅ ምን ይሳነውና?????????? 3ኛ ኦርቶዶክሳውያን ምን ያህል ክብረ ክህነትንና አባትን አክባሪ መሆናችንን ለዓለም ለማሳየት ነው።ብርሃናችሁ በሰው ሁሉ ፊት ይብራ እንዲል ቅዱስ ወንጌላችን። ስለዚህ ይህንንና ይህንን በመሳሰለው የተቀደሰ ዓላማ ነገ መጋቢት 3/2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት በመስቀል አደባባይ ተገኝተን ቅዱስ አባታችንን ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ እንሸኛለን። ይኸው ነው እንግዲህ ዓላማችን።እረኛው ሲለያቸው በጎች ይጮሀሉ። በጎቹ እረኛቸውን መቀማታቸው ሳያንስ፣ይባስ ብሎ ጩኸታቸውን መቀማት(ቀ ጠበቅ ብሎ ይነብብ) ግን የለባቸውም።የተዋህዶ እረኛ መርቆርዮስ ፣ሲጠብቃቸውና ሲንከባከባቸው ከኖረውና መንጋው ከሆኑት ከምዕመናን ሲለይ፣ጩኸት አለ፣መደናገጥ አለ፣ሀዘን አለ። ስለዚህ ሀዘናችን ይከበር። የጩኸቱ ምክንያት የእረኛው ከበጎች መለየት ብቻ ነውና ለጩኸቱ ምክንያት አይፈለግለት። የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ውሻ፣በንጉሡ ላይ ተንኮል አስቦ በመጣ እንግዳ ላይ ትጮሀለች የሚባል ነገር አለና።አንድ ምንም ክፋትና ተንኮል በንጉሱ ላይ ያላሰቡ ልበ ቀና ሰው ወደ ንጉሡ ሲመጡ አይታ፣ያቺ ልማደኛ ውሻ እኒህ ሰው ላይ እየዘለለች መጮህ ስትጀምር፣በነገሩ ግራ የተጋቡት እንግዳም "" ኸረ ጃንሆይ ይቺ ውሻ ሰው ያላሰበውን ታሳስባለች "" አሉ ይባላል። ስለዚህ ዛሬም አደራ የምንላችሁ ነገር ያላሰብነውን አታሳስቡን ነው።አላማችን ከላይ የገለጽኩት አንድ እና አንድ ነው።እርሱም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ የሆኑት ቅዱስ አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ናቸው።በእውነት የዱስነታቸው በረከት ይደርብን። ምሕረተአብ አሰፋ መጋቢት 3/2014/ዓ/ም
#ሰሙነ ሕማማት

ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ።

በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው።
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦

📖ሰኞ

መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል፦
በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል።

አንጽሖተ ቤተመቅደስ ይባላል፡-
ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና።

📖ማክሰኞ

የጥያቄ ቀን ይባላል፦
ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል።

የትምህርት ቀን ይባላል፡-
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።

📖ረቡዕ

ምክረ አይሁድ ይባላል፦
ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል።

የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል።

የእንባ ቀን ይባላል፡-
ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል።

📖ሐሙስ

ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፦
ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል።

የምስጢር ቀን ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።

የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡-
መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድህነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።

የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡-
ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል።

📖ዓርብ

የስቅለት ዓርብ ይባላል፦
ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።

መልካሙ ዓርብ ይባላል፡-
ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።

📖ቅዳሜ

ቀዳም ስዑር ትባላለች ፦
ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል።
ለምለም ቅዳሜ ይባላል፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል።

ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡-
ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል።
╔═★══════════📄══╗
@Zemaryan
@Zemaryan
@Zemaryan
╚══📃══════════★═╝
++ ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? ++

ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ፊት በዚያች ምሽት በጭንቀት ቆመዋል፡፡ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሠጠኛል ብሎ ነግሯቸዋል፡፡ ስለዚህ ተጨንቀዋል፡፡ ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? እያሉ ዐሥሩ ደቀ መዛሙርት ተራ በተራ ጠየቁት፡፡

የቀሩት ሊሸጠው ተስማምቶ የመጣው ይሁዳና ወንጌላዊው ዮሐንስ ናቸው፡፡ ይሁዳ እኔ እሆንን ማለቱ ልቡ እያወቀ ስለነበር ከዐሥሩ ጋር አብረን አንቆጥረውም፡፡ ዮሐንስ ደግሞ ለጌታ ካለው የፍቅር ጥልቀት የተነሣ እኔ እሸጠው ይሆን? የሚል ሥጋት ስላልነበረበት ‘’ጌታ ሆይ አሳልፎ የሚሠጥህ ማነው?’’ አለ እንጂ እኔ እሆንን አላለም፡፡ የሐዋርያቱ የጭንቀት ጥያቄ በማግሥቱ መልስ አግኝቷል፡፡ ሆኖም ይህንን ትሕትና የተሞላ ጥያቄያቸውን ለእኛ ሳይበጅ አይቀርም፡፡

በዙሪያችን ለተደረጉ ፣ ለሚደረጉ ክፉ ነገሮች ሁሉ ምክንያቱ ምንድር ነው? ጥፋቱ የማን ነው? መነሻው ምንድርን ነው? ብንባል ሁላችንም ጣት የምንቀስርበት ሰው አናጣም፡፡
አዳም ዕጸ በለስን ለመብላቱ ‘’ም ክን ያቴ ሔዋን ናት ‘’ አለ
ሔዋን ‘’ዕባብ አሳተኝ ‘ አለች
ዕባብም ጠያቂ ቢያገኝ ሰይጣን ማለቱ አይቀርም ነበር፡፡
አንዳቸውም ‘’ጌታ ሆይ እኔ እሆንን?’’ ማለት አልቻሉም፡፡ እንደ ዳዊት ‘’እኔ መተላለፌን አውቃለሁ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊትህ ነው’’ ማለት ያስፈልጋል፡፡ ለሚሆኑ ነገሮች ሁሉ የምንከስሰው ሰው አናጣም:: መፍትሔው ግን ራስን ማየት ነው:: "እስመ አዕይንቲሁ ለጠቢብ ዲበ ርእሱ" (የጠቢብ ዓይኖቹ በራሱ ላይ ናቸው) እንዲል

ቅዱሳን በምንም ነገር ራሳቸውን ይወቅሱ ነበር:: በገድላቸው ብዛት በሚጸልዩበት ሥፍራ ዶፍ ዝናብ እየወረደ ሳለ እርሳቸውን እንዳይነካቸው በቆሙበት ሥፍራ እንዳይዘንም ያደረገላቸው ዳግማዊው ኤልያስ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ያሉትን እናስታውስ:: በቆሙበት ሥፍራ ዝናም እንዳልዘነመ ሲያዩ "ይህችን መሬት በኃጢአቴ ዝናም አስከለከልኳት" ነበር ያሉት:: ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? ማለት ይህም አይደል?

የሙሴ ወንድም አሮን በእስራኤል ግፊት ጣኦት ሠራ፡፡ ከወርቅ አቅልጦ ጥጃ አምላክ አድርጎ ሠራላቸው፡፡ ከሠራ በኋላም መሥዋዕት ለጣኦቱ አቀረበ፡፡
ሙሴ መጥቶ ሲቆጣ ሲያይ ግን አሮን ፈራና በሕዝቡ አሳበበ የራሱን ድርሻ በተመለከተ ግን እንዲህ አለ
‘ወርቅ ሰጡኝ በእሳት ላይ ጣልሁት ይህ ጥጃ ወጣ’ {ዘጸ 32፡24}
ራሱ ከእጃቸው ተቀብሎ በመቅረጫ ቀርጾ የሠራውን ጣኦት ‘ስጥለው ጥጃ ሆነ’ አለ፡፡ ራሱ ሕዝቡን ‘ስድ ለቅቋቸው’ የነበረ በመሆኑ ‘’ጌታ ሆይ እኔ እሆንን?’’ ብሎ ራሱን ሊከስስ ይጠበቅበት ነበር፡፡

በትምህርት ቤት ሕይወታችን የማይረሱ ቀናት ግሬድ የሚለጠፉባቸው ቀናት ናቸው፡፡ ከብዙ የመታወቂያ ቁጥር መካከል ውጤቱን ያየ ተማሪ በዚያ የትምህርት ዓይነት A እንዳገኘ ሲያውቅ ለጓደኞቹ ‘’A አገኘሁ እኮ’’ ይላል፡፡ በተቃራኒው ‘F’ ያገኘ ከሆነ ‘’F ሠጠኝ’’ ይላል እንጂ ‘F አገኘሁ’ አይልም፡፡ A ከሆነ ያገኘው ተማሪው ነው ፤ F ከሆነ ግን በድክመቴ አገኘሁ ከማለት ይልቅ ጥፋቱ የመምህሩ ይሆናል፡፡ ነገሩን አልኩ እንጂ ሀገር ሰላም ብሎ የቆመ በር ጋር ስንጋጭም ‘በሩ መታኝ’ እንጂ መታሁት አንልም፡፡
እናም በሕይወታችን ለሆኑትና ለሚሆኑት ነገሮች ‘ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? ማለት ትልቅ ጸሎት ነው፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 20 2012 ዓ ም
አዲስ አበባ
ሰበር ዜና
በመስቀል አደባባይ የሚደረገው ሕገ ወጥ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጠየቀ !!!

ሚያዝያ 21 ቀን 2014 ዓ.ም (ተሚማ/አዲስ አበባ)

++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

ከአ.አ ከተማ አስተዳደር ጋር የተደረገው የጋራ ውይይት እልባት ሳያገኝ በቤተ ክርስቲያናችን ታሪካዊ ይዞታ መስቀል አደባባይ ላይ የሚደረግ ማናቸውም ሥነ ሥርዓት ተቀባይነት የለውም ያለው ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ፣ ለሰላም ሚኒስቴር ፣ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፣ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ፣ ለአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት በጻፈው ደብዳቤ
"… ነገ ሚያዚያ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. በመላው ዓለም በሁሉም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በመገኘት  #ከቅዳሴ_በኋላ_በሁሉም_አጥብያ_ከሥር_ያሉትን_መፈክሮች_እናሰማ ዘንድ ተጠይቋል። (በኮምፒዩተር ተጽፈው፤ በባነር ይዘጋጁ። በቅድስት ቤተ-ክርስትያናችን ሆነን ድምጻችን ለዓለም እናሰማ።


☞ የኦርቶዶክሳውያንን ደም በማፍሰስ የሚጸና ወንበር የለም!
☞ በአፍጥር ስም እየተካሔደ ያለው መንግሥታዊ አሻጥር ይቁም
☞በሥልጤ ኦርቶዶክሳውያን ላይ የተፈጸነው ስቃይ ስቃያችን ነው!
☞ኢትዮጵያን የኦርቶዶክሳውያን የመከራ ቋት ማድረግ ይብቃ
☞ኦርቶዶክሳዊነትን እና ኦርቶዶክሳውያ አሻራን ማጥፋት ይቁም!
☞ አባቶቻችን አታስገድሉን!
☞ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ዝምታ ይብቃ
☞ አማራን እና ተጋሩን በማጋደልቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም የሚደረገው ሴራ ገብቶናል!
☞ የኦርቶዶክሳውያን ትዕግሥት ወሰን አለው!
☞ መንግሥት ሆይየአዛኝ ቅቤ አንጓች አስመሳይነትህን አቁም!
☞ ለኦርቶዶክሳውያን ከችግኝ ያነሰ ዋጋ መስጠት ይቁም
☞ በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸም ሥርዓታዊና መዋቅራዊ ጥቃት ይቁም!
☞ ፍትሕ በወራቤ በግፍ ለተጎዱ ኦርቶዶክሳውያን!
☞ አጥቅተውን ተጠቃን ብለው የጥላቻ ንግግር በሚያሰራጩ ጽንፈኞች ላይ መንግሥት ካለ በአስቸኳይ እርምጃ ይውሰድ !

"… ትእግስት ፍራቻ ለመሰላቸው ማንነታችን ማሳየት አለብን። በየ ፑል ቤቱ፣ በየ ሺሻ ጫት ቤቱ ተጎልተህ ነገ በማጅራትህ አላህ ወአክበር እያለ ከመታረድህ በፊት ንቃ፣ ተሰባሰብ፣ ተመካከር፣ ተጠባባቅ። አከተመ።
ካላንደር ሳይዘጋው መንገድ የዘጋው ሜክሲኮ ልደታ።
+ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ +

አንድ ሰው እኔ ክርስቲያን ነኝ ሲል በአንድ ቃል ዜግነቱንና ቤተሰቡን ሥራውን ጠቅልሎ ተናገረ ማለት ነው:: የሚያምን ሰው ከሰማያዊት ኢየሩሳሌም በቀር ምድራዊ ከተማ የለውም"

🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

"እግዚአብሔር የሚጠይቅህ ጥቂት ነው የሚሠጥህ ግን ብዙ ነው

🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

"የዚህ ዓለም ኑሮ እንደ እንቅልፍ ነው:: በዚህ ሕይወት የሚሆኑት ሁሉ ሕልም ናቸው::
በሕልምህ ባለጸጋ ብትሆን ምን ጥቅም አለው? በእንቅልፍ ልብ ሆኖ በቅዠት የሚናገር ሰው ስለ ንግግሩ አይፈረድበትም:: እኛ ግን በዚህ የእንቅልፍ ዘመን የምንናገረው ሁሉ የዘላለም ሕይወትን ሊያሳጣን ይችላል"

🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

"በድህነት እና በረሃብ የሚሰቃዩ ሰዎች እንደ ሠለስቱ ደቂቅ ናቸው:: ከድህነት የበለጠ ምን እሳት አለ? ከረሃብስ የሚበልጥ ምን ነበልባል አለ?
ሦስቱ ወጣቶች እሳት ውስጥ ሆነው እንደዘመሩ በመከራ ውስጥ ሆኖ ፈጣሪን የሚያመሰግን ሰው የመከራው እሳት ውኃ ይሆንለታል:: ለድሆች ምጽዋትን የሚሠጥ ሰው ደግሞ ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት የታደገውን የእግዚአብሔር መልአክን ይመስለዋል"

🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

በትንንሽ ነገሮች ማመስገንን ከለመድህ ትንንሽ ነገሮች ብዙ ስለሆኑ ሕይወትህ ምስጋና ይሆናል"

🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

በኀዘን ጊዜ የማያጉረመርሙ ከንፈሮች ከቅዱሳን ሰማዕታት እኩል ናቸው

🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

ሕይወታችን ለሌሎች የሚያበራ ቢሆን ኖሮ ስብከት ባላስፈለገ ነበር:: በምግባራችን መመስከር የምንችል ብንሆን ኖሮ ቃላት ባላስፈለጉ ነበር:: እውነተኛ ክርስቲያኖች ብንሆን ኖሮ አረማውያን ባልበዙ ነበር

ግንቦት 12 ተዝካረ ዕረፍቱ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ወፍልሰተ አጽሙ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ወበዓላ ለቅድስት እምነ ክርስቶስ ሠምራ

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ