✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.06K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
🌺ነጭ ነጠላ ለምን እንለብሳለን🌹
ይህን ጥያቄ ስንቶቻችን እናውቀዋለን???
ለሚለው አንዳንዶች ባለማወቅም ይሁን በቅናት ክርስትና ነጠላ ለብሶ ቤተክርስቲያን መሄድ አይደለም ሲሉ ይደመጣሉ። የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ግን መጽሐፍ ቅዱስን ምክንያት አርጋ ምሥጢሩን ከተግባር ጋር ትገልጻለች።
እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን ስንሄድ ነጭ ነጠላ መልበሳችን የተገባ ነው። ነጭ ነጠላ ወይም ጋቢ አደግድገን ወይም በትእምርተ መስቀል ለብሰን ቤተመቅደስ ስንቆም የምናስባቸው ምስጢራት አሉት
የክርስቶስን መከራ ለማሰብ፣ ነጠላው ወደ ግራ ቀኝ በትእምርተ መስቀል አምሳል ይጣፋል። በዚህ ጊዜ ጌታችን በዕለተ አርብ የተቀበላቸው ጸዋትወ መከራ እንዲሁም በቀራንዮ በምልዕልተ መስቀል መሰቀሉን ያስታውሰናል። ይኸውም የተመሳቀለ ነጠላ የሚመለከትም ሁሉ የጌታችንን መከራ መስቀል መቀበሉን ያስባል።
አንድም ከግራ ወደ ቀኝ አመሳቅንለ መልበሳችን
ወደ ቀኝ የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ
ወደ ግራ የሲኦልም ምሳሌ ነው ።
የምናጣፋው ነጠላ ነጭ የሆነባቸው የተለያዩ ምክንያቶች አለው
1ኛው የሚጠብቀንን ሰማያዊ ክብር በማሰብ ነጭ እንለብሳለን".....
ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ እስከመቼ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር ላይእንኳን በሚኖሩት ላይ እስከመቼ ድረስ አትበቀልም አሉ ለእያንዳንዳቸው ነጭ ልብስ ተሰጣቸው....." /ነጠላራዕ.6፤9~10 ከዚህም በኋላ አየሁ እንሆም አንድ ሊቆጥራቸው የማይችል ከህዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባም ዝንጣፊም በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊትቆሙ" /ራዕ.7፤9
እኛም ቅዱሳንን አብነት በማድረግና ከበጉ ቀኝ ነጭ ለብሰን የመቆም ተስፍ በመሰነቅ ነጭ ነጠላን እንለብሳለን
2ኛው ቅዱሳን መላእክት ከእኛ ጋር መሆናቸውን ማሰብ".....ይህም ማለት ጌታችን በፈቃዱ ነፍሱን ከስጋው በለየ ጊዜ በሶስተኛው ቀን መቅደላዊት ማርያም
ማርያም ግን እያለቀሰች ከመቃብር በስተ ውጪ ቆማ ነበር።ስታለቅስም ወደ መቃብር ዝቅ ብላ ተመለከተች ሁለት መላእክትም ነጭ ልብስ ለብሰው የጌታ የኢየሱስ ሥጋ በነበረበት ቦታ አንዱ በራስጌ ሌላው በግርጌ ተቀምጠው አየች።" እኛም ክርድቲያኖች ልክ እንደ መላእክት የትንሳኤአችን ምስእከል በሆነች ቤተክርስቲያን ነጭ ነጠላብ ለብሰን ወደ በቤተክርስቲያን እንሄዳለን ማለት ነው
3ኛው ከጌታችን ጋር እንዳለን እናስባለን".....
ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራረ ለብቻቸው አወጣቸው። በፊታቸውም መልኩ ተለወጠ ፊቱም እንደ ፀሐይ አበራ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ።" /ማቴ 17፤1~9 -/
ክርስትና በሰማያዊ ተስፋ የተሞላች ብርሀናማ ህይወት ነውና ይህንን ተስፍችንን በማሰብ ነጭ ነጠላን እንለብሳለን ሰለዚህም መስቀለኛ አጣፍተን መከራ መስቀሉን በማሰብ የምንለብሰው በዘፈቀደ የሚለበስ አለመሆኑን በመገንዘብ ስርአቱን ልንተገብር ልናውቅና በስርአተ ቤተክርስቲያን ስርአትን መከተል ይኖርብናል
ነጭ ነጠላ መልበስ መንፈሳዊ ትርጉም አለውና ወንዶችም ሴቶቹም በኪዳኑ፣ በቅዳሴውና በንግሱ ላይ ያለ ነጠላ ከምንሄድ ነጠላ ብንለብስ እህቶቼም ሥርዓቱን የጠበቀ ነጠላ ለብሰን ከላይ የተጠቀሱትን እያሰብን በቤቱ ብንገኝ መልካም ነው። አባቶች የሠሩትን የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፍልስ። ይላል መጽሐፉ ቅዱስ ሁላችንም ሥርዓተ ቤተክርስትያንን እንድንጠብቅ ልቦና ይስጠን። እግዚአብሔር ሁላችንንም እንደ ፍላጎታችን ሳይሆን እንደ እርሱ ፈቃድ እንድንመራ ዓይነ ልቦናችንን ያብራልን! ይህ እራስን መግዛት ለቃሉ ብዙዎቻችን ጋር ያለ ችግር ነው ይህ የሆነው የእግዚአብሔር ፍቅር በውስጣችን ሳይኖር አለመታዘዝ የዓለምን ፍቅር አብልጠን ምን ችግር አለው? እያልን በእግር ብቻ በቤቱ መሄድ ስለለመድን ነው። ትልቁ ችግር ያመጣው ምን ችግር አለው? ነው።
አንዳንዶቻችን ግን ነጠላ ስለከበስኩይ ሳይሆን እንላለን
ይሄ ግን ይሄ ምክንያት አይሆንም።
እያወቅን በድፍረት ሳናውቅ በስህተት ከምንሰራቸው ነገሮች አይነ ልቦናችንን ያብራልን አሜን!!
🌺🌹ወስብሐት ለእግዚአብሔር🌹🌺
አሜን
+++ በመስቀሉ ፈልገህ አግኘው! +++
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተራራ ወርዶ ፤ ወደ እርሱ መጥቶ ያነጻው ዘንድ የጠየቀውን አንድን ለምጻም ዳስሶ ከፈወሰ በኋላ ፤ ወደ ቅፍርናሆም ሄዶ ሽባ ሆኖ የሚሰቃየውን የመቶ አለቃውን ልጅ በቃል ብቻ ተናግሮ አዳነለት። ቀጥሎም በንዳድ በሽታ ታምማ የተኛችውን የጴጥሮስን አማት ዳስሶ ፈወሳት። ምሕረቱ የበዛ ነውና ብዙ ሕሙማን ከየችግራቸው ነፃ አወጣቸው አዳናቸውም። ከዚያም ባሕሩን ይሻገር ዘንድ ወደ ታንኳ ገባ ፤ "ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት።" (ማቴ. 8: 23) ፤ የባሕር ላይ ጉዞአቸውን እንደጀመሩ ማዕበሉ ታንኳይቱን እስኪደፍናት ድረስ በባሕር ታላቅ መናወጥ ሆነ ፤ ጌታችን ግን ተኝቶ ነበር። ደቀ መዛሙርቱም ከመጨነቃቸው የተነሣ ፦ "ጌታ ሆይ፥ አድነን፥ ጠፋን" እያሉ አስነሡት።
ጌታችንም ከእንቅልፉ እንደተነሣ ፤ "ምን ተፈጠረ? ምንስ አገኛችሁ?" አላለም ፤ ይልቁንም "እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ ስለ ምን ትፈራላችሁ? አላቸው። ከዚህ በኋላም "ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፥ ታላቅ ጸጥታም ሆነ" (ማቴ. 8: 26)። ይገርማል! ተፈጥሮ ከወዴት አቅም አግኝታ ፤ እንዴት ማንነቱን ብትዘነጋ ፤ ይሆን አምላኳ ያለበትን ታንኳ እንዲህ ያሰጨነቀችው? ፈጣሬ ፍጥረታት ፣ አኀዜ ዓለማት ታንኳይቱ ስትጨነቅ ፤ እስኪያስነሡት ድረስ እርሱ ተኝቶ ነበር! ሳያውቅ ቀርቶ ነው እንዳንል "ሰው በስውር ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን?" (ኤር. 23: 24) የሚለው የነቢዩ ቃል አያሰናብተንም።
እውነት ነው ሁሉን የሚያውቅ(Omniscent) ነው ፤ ከእርሱ የሚሰወር አንዳች የለም። ስለዚህም ቀስቅሰውት ከእንቅልፉ እንደተነሣ ማብራሪያ ሰጪ ሳያስፈልገው ባሕሩን ገሠጸው። ወዳጄ ሆይ! እንኳን የገጠመህን ፣ በልብህ ያለውን አልፎም ፣ ስለነገህ ያውቃል! ነገር ግን የአንተን ድርሻ እንድትወጣ ፣ የእምነትህንም ጽናት ያይ ዘንድ ይፈልጋል ፤ ነገሩ ቢከብድህ የማይቻልህ ቢሆን በጸሎትህ ቀስቅሰው ፤ እርሱ ጥያቄዎችህን ሁሉ ይመልሳል። 'ክርስቶስ ከእኔ ጋር ባይኖር እንጂ ፈተና ባልበዛብኝ ነበር' አትበል ፤ እርሱን ስትከተል ከእርሱ ጋር ስትኖር የእርሱ የሆነው መስቀሉም ከአንተ ጋር ነውና ፤ ልብህን አታዘናጋ! "ፈልጎ ያገኘህ በመስቀሉ ነውና ፤ አንተም ፈልገህ የምታገኘው በመስቀሉ ነው!" ቀደምት አበው ስለዚህች ታንኳ እና ስለ ቅዱስ መስቀሉ ብዙ ድንቅ ትምህርት አስተምረዋል። ደቀ መዛሙርቱ ጌታችን ወደ ታንኳ ሲገባ ተከትለውት ነበር ፤ እውነት ነው እርሱ ክርስቶስ "በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ።" (ሉቃ. 9: 23) ብሎ ነበርና ተከተሉት። ጌታ ያለባት ታንኳ ከማዕበሉ የተነሣ ተናወጸች ፤ መድኃኔ ዓለምም በመስቀል ላይ ከአይሁድ መከራ የተነሣ ታመመ። በታንኳይቷ ውስጥ ክርስቶስ ተኝቶ ነበር ፤ እውነት ነው የሰውን ልጅ ለማዳን በመስቀል ላይ እንቅልፍ የተባለ ሞትን ቀመሰ። ደቀ መዛሙርቱም ተኝቶ ሲያዩት "ጌታ ሆይ፥ አድነን፥ ጠፋን" እያሉ ቀሰቀሱት ፤ ወደ ታንኳ ከመግባታቸው አስቀድሞ የለምጻሙን መንጻት ፣ የሽባውን መተርተርና ብዙዎችን በመፈወስ የገለጠውን ኃይሉን የዘነጉ ይመስላል "ልንጠፋ ነው" አሉት። እውነትም ደቀ መዛሙርቱ በመስቀል ላይ ሞቶ ሲመለከቱት "የሰው ልጅ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጣል፥ ይገድሉትማል፥ ተገድሎም በሦስተኛው ቀን ይነሣል" (ማር. 9: 30-31) በማለት አስቀድሞ የነገራቸውን ዘንግተውት ኖሮ ይጨነቁና ያዝኑ ነበር።
በታንኳይቱ ውስጥ ጌታችን ከእንቅልፉ ተነሥቶ ማዕበሉን ጸጥ እንዳደረገው ፤እንዲሁ መድኃኔ ዓለም ሞትን ድል አድርጎ ፣ በሞት ግዞት የሚያስጨንቀውን የአጋንንት ኃይል አጥፍቶ በሦስተኛው ቀን ተነሣ።
+++
"ወዳጄ ሆይ! 'ክርስቶስ ከእኔ ጋር ባይኖር እንጂ ፈተና ባልበዛብኝ ነበር' አትበል ፤ እርሱን ስትከተል ከእርሱ ጋር ስትኖር የእርሱ የሆነው መስቀሉም ከአንተ ጋር ነውና ፤ ልብህን አታዘናጋ! "ፈልጎ ያገኘህ በመስቀሉ ነውና ፤ አንተም ፈልገህ የምታገኘው በመስቀሉ ነው!"
+++
"ባሕር የተባለ የዚህ ዓለም መራራ እና ጨለማ የመከራ ሕይወት ነው ፤ እውነተኛ አማኝ ታንኳ የተባለውን ቅዱስ መስቀሉን ይዞ የዚህን ዓለም ፈተናዎች በማለፍ ከመንግሥተ ሰማያት ወደብ ማረፊያ ይደርሳል" (ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ)
+++
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ዲያቆን ደረጀ ድንቁ
ጓደኞትን ይጋብዙ ትምህርት ጀምረናል
@embtee
@embtee
@embtee
ለሁሉም የድንግል ወዳጆች ሼር ሼር ሼር

ስለ ምን እንማር?
1 ትምህርተ ሃይማኖት ❤️
2 ነገረ ማርያም 🧡
3 ለመናፍቃን መልስ 💚
4 የአቡነ ሺኖዳ ምክሮች 💜
5 ምክረ አበው 💙
የርሶ ድጋፍ ዋጋ አለውና ፍላጎቶን ይግለጹ

እናመሠግናለን 🙏🙏🙏
በመጀመሪያ 20 ፍላጎት ያገኘውን እንጀምራለን
ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ
@embtee
@embtee
ነገ ወይም ማታ እንጀምራለን ትምህርት።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#አስደሳች_ዜና_ለግእዝ_ትምህርት_ፈላጊዎች
በሐገር ውስጥም ከሐገር ውጪም ላላችሁ የግእዝ ሥልጠና ፈላጊዎች ባላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ሥራችሁን እየሠራችሁ ትምህርታችሁን እየተማራችሁ በኦንላይን በቴሌግራም የልሳነ ግእዝን መሠልጠን ከፈለጉ በ @ASRATEGABRIEL ላይ አሁኑኑ ያነጋግሩን አጠቃላይ ክፍያ 200ብር ብቻ
✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞ pinned «#አስደሳች_ዜና_ለግእዝ_ትምህርት_ፈላጊዎች በሐገር ውስጥም ከሐገር ውጪም ላላችሁ የግእዝ ሥልጠና ፈላጊዎች ባላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ሥራችሁን እየሠራችሁ ትምህርታችሁን እየተማራችሁ በኦንላይን በቴሌግራም የልሳነ ግእዝን መሠልጠን ከፈለጉ በ @ASRATEGABRIEL ላይ አሁኑኑ ያነጋግሩን አጠቃላይ ክፍያ 200ብር ብቻ»
ውበት ነሽ ለቤቴ.aac
5 MB
✞ ውበት ነሽ ✞

▦ዘማሪት እታፈራሁ ወርቁ▦
╔═★══════════📄══╗
@Zemaryan
@Zemaryan
@Zemaryan
╚══📃══════════★═╝
እንኳን አደረሳችሁ

"ሀያል ነህ አንተ ሀያል ደጉ መላእክ ገብርኤል
ይውደቅ ይሸነፍ ጠላት አንተ ተራዳን በእውነት..."


#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ገብርኤል 19
✝️✝️✝️

🛑 ሼር
4 More join us👇

╔═★══════════📄══╗
@Zemaryan
@Zemaryan
@Zemaryan
╚══📃══════════★═╝
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
​​የመስቀል አደባባይ ባለቤት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሆኗ ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም ....ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

(ጥር 01 ቀን 2014 ዓ .ም
አዲስ አበባ፥ ኢትዮጵያ)

ዛሬ ጥር 1 ቀን 2014 ዓ.ም 9:00 ሐዋርያ ዘለዓለም የተባለ የወንጌላውያን አማኞች ኅብረት አባል የሆነ ፓስተር መስቀል አደባባይ ላይ ለጠራው የአምልኮ ፕሮግራም ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በጽህፈት ቤታቸው ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።

ብፁዕነታቸው የፓስተሩ የመስቀል አደባባይ ፕሮግራም እንዲሰረዝ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን ገልፀው ማሰረዝ ግን አልተቻለም ብለዋል።

እንዲህ ዓይነት ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች ሲኖሩ በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት በኩል ተፈቅዶ መሆን ሲገባው ነገር ግን በአንድ ግለሰብ ጥሪ ከሃይማኖት ተቋማት ዕውቅና ውጭ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ ጥሪ መተላለፉ አሳዝኖኛል ብለዋል።

ሐዋርያ ዘለዓለም የተባለን ሰው የወንጌላውያን ኅብረትም እንደማያቀው አጣርተው ለዚህ ፕሮግራም መንግሥት ዕውቅና መስጠት የለበትም በሚል ከፍተኛ ጥረት እንዳረጉ አውሰተዋል።

ሆኖም ግን መርሐ ግብሩ ቀድሞ የተያዘና ዓላማውም በጦርነቱ ለተጎዱ ድጋፍ ማሰባሰቢያ የሚል ሽፋን ይዞ በመንቀሳቀሱ ጥረታቸውን ክቡድ እንዳደረገው ተናግረዋል።

ክብርት ከንቲባዋ ጋር በአጭር ቀን ውስጥ ለመነጋገር ቀጠሮ እንዳላቸው የገለፁት ብፁዕነታቸው በስመ ሃይማኖት እኩልነት ቤተ ክርስቲያን በየጊዜው ድርሻዋን ማጣት የለባትም ብለዋል።

የመስቀል አደባባይ ባለቤት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለመሆኗ ዓለም የመሰከረው በዩኔስኮ የተመዘገበው ከማይዳሰስ ቅርሷ በተጨማሪ ከጥንት ጀምሮ የደመራ በዓልን ማክበሯ እና ለስሙ ያላት አበርክቶዋ ምስክር ነው ብለዋል።

ቀደም ሲል ለባለብዙ አገልግሎት የታደሰው መስቀል አደባባይ ሲታደስ ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ጋር የገባነው ውል አድሰው ለቤተክርስቲያን ሊያስረክቡ የነበረ መሆኑን አውሰተው ደብዳቤው በእጃችን ያለ በመሆኑ ይሄው ውል እንዲከበር ለመንግሥት ጥሪ አቅርበዋል።

በመስቀል አደባባይ እንደ የሕዝብ ስፖርት፣ ኮንሰርት እና ሌሎች ኩነቶች ፈቃጁ ሌላ መሆኑን ገልፀው ሃይማኖታዊ ከንዋኔ ሲሆን ግን የሚመለከታት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ብቻ ናት ብለዋል።

ቤተክርስቲያን ለልማት እና ለአብሮነት ያላት አስተዋጽኦ በጽኑዕ አቋም ከቃላት በላይ በተግባር የተገለፀ ነው ያሉት ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በ2011 ዓ.ም የአዲስ ከተማ አስተዳደር ቤተሰብ ለሌላቸው ተማሪዎች ለምገባ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ በጠየቀን ጊዜ ያለ ሃይማኖት ልዩነት ለሁሉም ተማሪዎች ምግብ የሚሆን 10.000.000 (አስር ሚሊዮን ብር) የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መለገሱን የቤተክርስቲያኒቱን ለሁሉ አዛኝ መሆኗንም አስታውሰዋል።
ገንዘቡን ለመመለስ ዝግጁ ነን!
“በህዝብ ገንዘብ ነው የተሰራው፣ ስለዚህ የሁሉም አደባባይ ነው የምትሉ ከሆነ ገንዘቡን ለመመለስ ዝግጁዎች ነን። መስቀል ማክበሪያ ቦታ እርስታችን ነው፣ የተዋህዶ ልጅ ደሞ ለእርስቱ ናቡቴን ነው!

ቀሲስ መምህር ዶክተር ዘበነ ለማ
ከበኩረ ሰባክያን ምህረተአብ አሰፋ የተላከ መልዕክት

ተደዋወል፣ተነጋገር፣ተመካከር፣ይበቃል በል።ሌላው በኛ ቤት እንደልቡ ሲሆን፣ምን ያመጣሉ፣አንድ ሰሞን ተንጫጭተው፣በዛው ይቀራሉ፣እያለ ሲናገር፣አንተ ግን በገዛ ቤትህ መሰብሰብና መፍትሄ ማፈላለግ ካቃተህ፣በእውነት የአቡነ ጴጥሮስ አጽም እሾህ ሆኖ እንዳይወጋህ፣ረቡዕ ጥር 4 በቦሌ መድኃኔዓለም እንገናኝ።

Share አድርጉ!!!! ስልክህ ተዓምር መስራት ይችላል!
ፈዘናል ፈዘናል ፈዘናል!!
ሲጠበቅ የነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ተራዘመ።
(ኢኦተቤ ቴቪ ጥር ፮ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም
ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር ፮ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ሊያደርግ ያሰበው ስብሰባ በቅዱስነታቸው አለመገኘት ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፏል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በገጠማቸው የጤና ችግር ምክንያት ሆስፒታል ስለገቡና ቅዱስነታቸው በመንበራቸው ላይ በሌሉበት ሁኔታ ጉባኤውን ማካሔድ ስለማይቻል የቅዱስ ፓትርያርኩ ጤና እስከሚመለስ ድረስ ጉባኤው ላልተወሰነ ጊዜ የተላለፈ መሆኑን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ገልጿል። እግዚአብሔር ለቅዱስነታቸው ምሕረቱን ሰጥቶ ወደ መንበራቸው ይመለስልን።
ፎቶ:- ከፋይል