✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.06K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
Audio
ተክለሃይማኖት ባህታዊ ዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ - Teklehaymanoylt bahitawi zemarit tsedale…
Mikiyas Tube ሚክያስ ቲዩብ
ተክለሐይማኖት ባህታዊ

ተክለ ሐይማኖት ባህታዊ
ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ
በአደባባዩ ተተክለሃል
ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል

ቃልኪዳን አለህ የገነነ
ምህረት የሚያሰጥ የታመነ
በስምህ ውሃ አጠጥተን
ዋጋችን በዝቷል አባታችን
#አዝ
እኛም ሆነናል ልጆችህ
ማርኮ አስቀርቶን ምግባርህ
በምልጃህ ጸሎት ትሩፋት
ቤታችን መላ በረከት
#አዝ
ምህረት ይዘንማል ከሰማይ
በአንድ እግርህ ቆመህ ስትጸልይ
ብዙ ተጋድለህ አትርፈሀል
ያገለገልከው አክብሮሃል
#አዝ
ተሰባበሩ ጣዖታቱ
አምነው ሰገዱ መኳንንቱ
የበረታው ቃል ከአፍህ ወጥቶ
የአምላክ አድርጓል ሁሉን ገዝቶ

ዘማሪት
ጸዳለ ጎበዜ
ሰላም ለኪ እያለ
♡ የ መዝሙር ግጥሞች ♡
​​ሰላም ለኪ እያለ

ሰላም ለኪ እያለ(፪)
ሐርና ወርቁን ስታስማማ
የገብርኤል ድምፅ ተሰማ
ተሰማ የመልአኩ ድምፅ ተሰማ
ተሰማ የገብርኤል ድምጽ ተሰማ

ውሃ ስትቀጂ ክንፉን እያማታ
ሊያበስርሽ የመጣው በታላቅ ደስታ
ከሞገስሽ ብዛት (፪) ሲታጠቅ ሲፈታ
አቅርቦልሽ ነበር የክብር ሰላምታ
አዝ = = = = = =
የምሥራቹን ቃል ምስጢር ተሸክሞ
ገብርኤል ተላከ ሊያረጋጋት ደግሞ
እርጋታ ተሞልታ(፪)ነገሩን መርምራ
የመልአኩን ብሥራት ሰማችው በተራ
አዝ = = = = = =
ይደሰታል እንጂ መንፈሴ በአምላኬ
በምስጋና ሳድር ዘወትር ተንበርክኬ
ሃሳቤ ለቅፅበት(፪)ሌላ መች ያስባል
ለእኔ ልጅን መውለድ እንዴት ይቻለኛል
አዝ = = = = = =
ከአንቺ የሚወለደው ልዑል ነው ክቡር
የተመስገነ በሰማይ በምድር
ምስጢሩ ኃያል ነው (፪) ይረቃል ይሰፋል
ከአንቺ በቀር ይኼን ማን ይሸከመዋል
አዝ = = = = = =
እጹብ ነው ድንቅ ነው አንቺን የፈጠረ
አንቺን በመውደዱ ሰውን አከበረ
ዓለም ይባረካል (፪) በማሕፀንሽ ፍሬ
ክብርሽን አልዘልቅም ዘርዝሬ ዘርዝሬ

መዝሙር
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

"መንፈስቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል "
ሉቃ ፩፥፴፭
❤️❤️❤️ፍቅርን በቁጥሮች❤️❤️❤️
በአንድ ወቅት በቁጥሮች ዓለም እንዲሆነ 9 ቁጥር 8 ቁጥርን በንቀት ዓይታ ኮረኮመቻት 8ቁጥር እንዳትመታት ትበልጣታለች ዝቅ ስትል (7) ጎንበስ ብሎ አገኘችው እዛው ባቀረቀረበት ኮርኮም አረገገችውና እልኋን ተወጣች ሰባትም ሊደርስባት ብድሩን ሊመልስ አልቻለም በብስጭት እዛውአጎንብሶ እያለ 6ትን ጀርባዋን ወደእርሱ አዙራእግሯን ሆዷውስጥ አጥፋ ያያታል እሷንም ኮርኩሞ ንዴቱን ያበርዳል 6ትደግሞ 5ትን 5ደግሞ 4ትደግሞ 3ትን 3ደግሞ 2ትን 2ደግሞ በአቅሟ አንድን መታቻት 1 ግን ዜሮን ባየቻት ጊዜ ብመታት ማንአላት እኔም አንድ ነኝብቻዬን በቃ ለሌሎቹ ፍቅር እናስተምራቸው ብላ የዜሮን ባዶነት ሳታይ ከጎኗ ብትቆምላት ሁሉንም በልጠው
1 እና 0 አስር (10) ተባሉ ከዛ በኋላ ሁሉም ቁጥሮች በህብረት አየሆኑ ትንሹም ትልቁም በመከባበር አሁን የምንጠቀምባቸው ቁጥሮች ሆኑ
❤️❤️❤️❤️❤️🌺🌺🌺🌺🌺🌹🌹🌹🌹
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" ቅዱስ አባታችንን "

<b>ይህንን ግፍ አለም ሁሉ ይመልከተው ሼር / SHARE አድርጉት ‼️</b>

• ፖሊሶች ቢሮአቸው ድርስ ሆነው
• ሰድበዋቸዋል !
• አመናጭቀዋቸዋል !
• አንገላቷቸዋል !

• ማዘዝ አይለችሉም
• መናገር አይችሉም
• መግለጫ ማውጣት አይችሉም !

• በቁም ታስረዋል ! የሲኖዶሱን ቢሮ ፖሊሶች ወደ ቃሊት እስርቤትነት ቀይረውታል !

ቪዲዮውን Download አድርገው ስሙት ! ትንሽ ሳንቲም ናት !

💵 Data Package ካላቹ 1.30
💵 Mobile Data ከሆነ 2.20 ብር
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
‼️ ኦርቶዶክስ አደጋ ላይ ነች ‼️

<b>ይህንን ግፍ አለም ሁሉ ይመልከተው ሼር / SHARE አድርጉት ‼️
</b>
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
╔═★══════════📄══╗
@Zemaryan
@Zemaryan
@Zemaryan
╚══📃══════════★═╝
👉ሰው ከመጠመቁ በፊት ሐይማኖቱ ምንድን ነው ?ሰው ሲፈጠር ሐይማኖቱ ምንድን ነው?👈
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ተወዳጆች ሆይ ሁላችንም ከመጠመቃችን በፊት ሐይማኖታችን ኦርቶዶክስ ነው።ይህን ያልኩት እንዲሁ በደፈናው አይደለም ምክንያት አለኝ።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
ኦርቶዶክስ ማለት ቃሉ የግሪክ ሲሆን አማርኛው ትርጉሙ እውነተኛ ፣ ቀጥተኛ መንገድ የሆነች ሃይማኖት ማለት ነው።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ሥማችን ኦርቶዶክስ ነበር የቀደመችዋ ቀጥተኛዋ መንገድ
ይቺ ቀጥተኛ መንገድ ከማን መጣች ኦርቶዶክስ የማን ሐይማኖት ናት ካልችሁኝ ደግሞ ከአዳም ጀምሮ የመጣው ሐይማኖት ኦርቶዶክስ ነው
እላለው እንዴት አትሉኝም?
ቆያ ላብራራላችሁ። ይኸውልህ የአዳም ሐይማኖት ተጠምቆ መፈጠር ነው።
ማስረጃው ዘፍ 1÷1 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ።ምድርም ባዶ ነበረች አትታይም ነበር የተዘጋጀችም አልነበረችም።ጨለማም በውሃ ላይ ነበር የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃ ላይ ይንሳፈፍ ነበር ይላል ከውሃ ውስጥ የብሱ ይገለጥ ብሎ ምድርን ፈጠረ ( አፈርን )ማለት ነው ከአፈር አዳምን ፈጠረ ከአዳም ሔዋንን ፈጠረ ከሔዋንና ከአዳም እኛ ተፈጠርን ሔዋን ከአዳም አዳም ከአፈር አፈር ከውሀ ያ ውሀ የእግዚአብሔር መንፈስ አለበት።የአዳም አባት አፈር አያቱ ውሃ ያ ውሃ የእግዚአብሔር መንፈስ አለበት ስለዚያ አዳም በጥንት አያቱ ተጠምቆ የተፈጠረው የእግዚአብሔር መንፈስ ካለበት ውሃ ተዘፍቆ ተፈጠረ ።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉አይደለም አዳምና ሔዋን የሰው ዘር ቀርቶ ሰማይና ምድር ጭምር በውሃ ተጠምቀው ነው የተፈጠሩት
የእግዚአብሔር መንፈስ ካለበት ውሃ። ምነው?ገረማችሁ? ልንገራችሁ
2ኛ ጴጥ 3÷5 ምን ይላል መሰላችሁ ነገር ግን እነዚያ ሰዎች ሰማያት ከጥንት ጀምሮ በእግዚአብሔር ቃል ተፈጥረው እንደሚኖሩ መሬትም በውሃ መካከልና በውሃ እንደተሰራች ሆን ብለው ይክዳሉ በዚያን ጊዜ የነበረው አለም በውሃ ሰጥሞ ጠፉ።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉በኖህ ዘመን የነበሩ ሰዎች ለምን ጠፉ? ቢባል ሰማይና ምድር ከውሃ እንደተፈጠሩ ሆን ብለው ይክዳሉ።ስለዚህ ጠፉ በውሃው ጥምቀት ያመኑ ኖህና ቤተሰቦቹ ዳኑ በውሃው ጥምቀት ያላመኑ የኖህ ዘመን ሕዝቦች ጠፉ በውሃው ጥምቀት ያመኑት እስራኤል ዘስጋ ዳኑ በውሃው ጥምቀት ያላመኑት ፈርኦንና ሰራዊቱ ጠፉ 1ኛ ቆሮ 10÷1 መስረጃ ወንድሞቻችን ሆይ አባቶቻችን ደመና እንደጋረዳቸው ሁሉም በባህር መካከል አልፈው እንደሔዱ ልታውቁ እወዳለሁ ሁሉንም ሙሴ በደመናና በባህር አጠመቃቸው።
👉ስለዚህ አይደለም አዳምና ሔዋን ሰማይና ምድርም የእግዚአብሔር መንፈስ ካለበት ውሃ ተጠምቀው ነው የተፈጠሩት።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉የአዳም ሐይማኖት የእግዚአብሔር መንፈስ ካለበት ውሃ ተጠምቆ መፈጠር ነው ።ያ ውሃ በሰይጣን ተበላሽቶ ተቋረጠ።ከዛም ክርስቶስ መጣ ለ ኒቆዲሞስ እንዲህ አለው ዮሐ 3÷5 እውነት እውነት እልሀለሁ ዳግመኛ ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም አለው።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ያ የድሮ ውሃ ተበላሽቶ ክርስቶስ መጣና ያንን ውሃ ቀደሰው ስለዚህ ድጋሚ አዳም ከተወለደበት ውሃ ተወለዱ ከዛ ውሃ ያልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግስትን አያይምምምምም።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
ስለዚህ አሁን ኦርቶዶክሶች ስንጠመቅ በፊት አዳም ከተወለደበት ውሃ ተወልደናልና የእግዚአብሔርን የልጅነት ፀጋ ተቀብለን ወደ መንግስተ ሰማያት እንገባለንንንንንንን።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ክርስቲያን ነው ካልን ለምን ይጠመቃል? 👈
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉የተጠመቀ የእግዚአብሔርን መንግስት ይወርሳል ያልተጠመቀ ደግሞ አይወርስም ይህንንንም ጌታ ነው ያለው እኛ የተዋህዶ ልጆች የተጠመቅን ነን መንግስቱ የኛ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ለተጠመቅን ብቻ ነው አራት ነጥብ።ለተጠመቁ ብቻቻቻቻቻቻ
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ህፃናት በ40 እና 80 ቀናቸው የሚጠመቁት እንዴት አምነው ነው ?
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ተወደጆች ሆይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን ዋቢ አድርጋ ሕፃናትን በሙሉ ማለትም ወንዶችን በተወለዱ በ፵ ቀናቸው ሴቶችን ደግሞ በተወለዱ በ፹ ቀናቸው ታጠምቃለች፡፡ ይህም ለአንዳንዶች እንደሚመስላቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ያልተገኘ አዲስ ሥርዓት አይደለም፡፡
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉አዳም በተፈጠረ በ፵ኛው ቀን ሔዋንም በተፈጠረች በ፹ኛው ቀን በይባቤ መላእክት ታጅበው ገነት መግባታቸውን መሠረት ያደረገ ሥርዓት ነው እንጂ (ኩፋ. ፬፥፱-፲፬፡፡) በተጨማሪም እግዚአብሔር አምላካችን ሴት ልጅ ከውርስ ስለምትነጻበት፣ ወደ መቅደስ ስለምትገባበትና የተወለደውን/ችውን/ በእግዚአብሔር ፊት ማቆም ስለሚችሉበት ጊዜ ሲናገር ለወንድ ልጅ ፵ ቀን ለሴት ልጅም ፹ ቀን መቆየት እንደሚያስፈልግ ሥርዓት ሠርቷል።(ዘሌ. ፲፪፥፩-ፍጻሜው፡፡)
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ቀደም ብሎም የእግዚአብሔር ወገን የመሆን የቃል ኪዳን ምልክት የሆነው ግዝረት ሕፃናት በተወለዱ በስምንተኛው ቀን ይፈጸም ነበር፡፡ (ዘፍ. ፲፯ ፥፩‐ፍጻሜው፡፡ ቈላ. ፪፥፲፩‐፲፬፡፡)
👉በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትም የሕፃናትን ጥምቀት በተመለከተ በርካታ ማስረጃዎች አሉ፡፡ ሐዋርያት አባቶቻችን አማኞችን ባጠመቁ ጊዜ እንደ ክርስቶስ ፴ ዓመት እስኪሞላቸው የሚጠብቁ አልነበረም፡፡ ሁሉንም (ሕፃናትንም ጭምር) በተገኙበት ዕድሜ በማጥመቅ ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና ያሰጧቸው ነበር እንጂ፡፡ እዚህ ላይ ሕፃናት ባመኑ ወላጆቻቸው እምነት አብረው ይጠመቁ እንደነበር ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ (ሐዋ. ፲፥፵፯-ፍጻሜ፤ ፲፩፥፲፬፤ ፲፮፥፲፭፡፴-፴፬፤ ፩ቆሮ. ፩፥፲፮፡፡) ከዚህም በተጨማሪ ጌታችን ኢየሱስም ሕፃናትን ተውአቸው፤ ወደ እኔም ይመጡ ዘንደ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና፡፡(ማቴ. ፲፱፥፲፬-፲፮፡፡) በማለት አዝዞናል።
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉እሱ ከፈቀደላቸው በኋላ እግዚአብሔር የተቀበላቸውን ዕድሜያችሁ ገና ነውና ዘወር በሉ! በማለት እኛ ልንከለክላቸው አንችላለንን? እግዚአብሔር የተቀበላቸውን እኛ መከልከል እንደማንችል መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ሕፃናት ሳያውቁ ከእናት አባታቸው በሥጋ እንደተወለዱ ሁሉ እንደዚሁም ሳያውቁ (ሳያምኑ) በወላጆቻቸው እምነት መንፈሳዊ ልደትን በጥምቀት ያገኛሉ ማለት ነው! አለማወቅና ሕፃንነት እግዚአብሔር የሚሰጠውን ድኅነተ ሥጋ፣ ድኅነተ ነፍስ ሊገድበው አይችልም፡፡ ሌላው ቀርቶ እግዚአብሔር ሕፃናትን ከእናታቸው ማኅፀንም ሳይቀር እንደሚመርጣቸውና እንደሚቀድሳቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ (ኤር. ፩፥፭፡፡ ሉቃ. ፲፥፵፬፡፡)
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
👉ማንኛውም የሰው ዘር ክርስቲያንም ተብሎ ይጠራ ሙስሊምም ይሁን፣መናፍቃን ይሁን ........ካልተጠመቀ አይድንም አራት ነጥብ
🌺ነጭ ነጠላ ለምን እንለብሳለን🌹
ይህን ጥያቄ ስንቶቻችን እናውቀዋለን???
ለሚለው አንዳንዶች ባለማወቅም ይሁን በቅናት ክርስትና ነጠላ ለብሶ ቤተክርስቲያን መሄድ አይደለም ሲሉ ይደመጣሉ። የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ግን መጽሐፍ ቅዱስን ምክንያት አርጋ ምሥጢሩን ከተግባር ጋር ትገልጻለች።
እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን ስንሄድ ነጭ ነጠላ መልበሳችን የተገባ ነው። ነጭ ነጠላ ወይም ጋቢ አደግድገን ወይም በትእምርተ መስቀል ለብሰን ቤተመቅደስ ስንቆም የምናስባቸው ምስጢራት አሉት
የክርስቶስን መከራ ለማሰብ፣ ነጠላው ወደ ግራ ቀኝ በትእምርተ መስቀል አምሳል ይጣፋል። በዚህ ጊዜ ጌታችን በዕለተ አርብ የተቀበላቸው ጸዋትወ መከራ እንዲሁም በቀራንዮ በምልዕልተ መስቀል መሰቀሉን ያስታውሰናል። ይኸውም የተመሳቀለ ነጠላ የሚመለከትም ሁሉ የጌታችንን መከራ መስቀል መቀበሉን ያስባል።
አንድም ከግራ ወደ ቀኝ አመሳቅንለ መልበሳችን
ወደ ቀኝ የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ
ወደ ግራ የሲኦልም ምሳሌ ነው ።
የምናጣፋው ነጠላ ነጭ የሆነባቸው የተለያዩ ምክንያቶች አለው
1ኛው የሚጠብቀንን ሰማያዊ ክብር በማሰብ ነጭ እንለብሳለን".....
ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ እስከመቼ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር ላይእንኳን በሚኖሩት ላይ እስከመቼ ድረስ አትበቀልም አሉ ለእያንዳንዳቸው ነጭ ልብስ ተሰጣቸው....." /ነጠላራዕ.6፤9~10 ከዚህም በኋላ አየሁ እንሆም አንድ ሊቆጥራቸው የማይችል ከህዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባም ዝንጣፊም በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊትቆሙ" /ራዕ.7፤9
እኛም ቅዱሳንን አብነት በማድረግና ከበጉ ቀኝ ነጭ ለብሰን የመቆም ተስፍ በመሰነቅ ነጭ ነጠላን እንለብሳለን
2ኛው ቅዱሳን መላእክት ከእኛ ጋር መሆናቸውን ማሰብ".....ይህም ማለት ጌታችን በፈቃዱ ነፍሱን ከስጋው በለየ ጊዜ በሶስተኛው ቀን መቅደላዊት ማርያም
ማርያም ግን እያለቀሰች ከመቃብር በስተ ውጪ ቆማ ነበር።ስታለቅስም ወደ መቃብር ዝቅ ብላ ተመለከተች ሁለት መላእክትም ነጭ ልብስ ለብሰው የጌታ የኢየሱስ ሥጋ በነበረበት ቦታ አንዱ በራስጌ ሌላው በግርጌ ተቀምጠው አየች።" እኛም ክርድቲያኖች ልክ እንደ መላእክት የትንሳኤአችን ምስእከል በሆነች ቤተክርስቲያን ነጭ ነጠላብ ለብሰን ወደ በቤተክርስቲያን እንሄዳለን ማለት ነው
3ኛው ከጌታችን ጋር እንዳለን እናስባለን".....
ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራረ ለብቻቸው አወጣቸው። በፊታቸውም መልኩ ተለወጠ ፊቱም እንደ ፀሐይ አበራ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ።" /ማቴ 17፤1~9 -/
ክርስትና በሰማያዊ ተስፋ የተሞላች ብርሀናማ ህይወት ነውና ይህንን ተስፍችንን በማሰብ ነጭ ነጠላን እንለብሳለን ሰለዚህም መስቀለኛ አጣፍተን መከራ መስቀሉን በማሰብ የምንለብሰው በዘፈቀደ የሚለበስ አለመሆኑን በመገንዘብ ስርአቱን ልንተገብር ልናውቅና በስርአተ ቤተክርስቲያን ስርአትን መከተል ይኖርብናል
ነጭ ነጠላ መልበስ መንፈሳዊ ትርጉም አለውና ወንዶችም ሴቶቹም በኪዳኑ፣ በቅዳሴውና በንግሱ ላይ ያለ ነጠላ ከምንሄድ ነጠላ ብንለብስ እህቶቼም ሥርዓቱን የጠበቀ ነጠላ ለብሰን ከላይ የተጠቀሱትን እያሰብን በቤቱ ብንገኝ መልካም ነው። አባቶች የሠሩትን የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፍልስ። ይላል መጽሐፉ ቅዱስ ሁላችንም ሥርዓተ ቤተክርስትያንን እንድንጠብቅ ልቦና ይስጠን። እግዚአብሔር ሁላችንንም እንደ ፍላጎታችን ሳይሆን እንደ እርሱ ፈቃድ እንድንመራ ዓይነ ልቦናችንን ያብራልን! ይህ እራስን መግዛት ለቃሉ ብዙዎቻችን ጋር ያለ ችግር ነው ይህ የሆነው የእግዚአብሔር ፍቅር በውስጣችን ሳይኖር አለመታዘዝ የዓለምን ፍቅር አብልጠን ምን ችግር አለው? እያልን በእግር ብቻ በቤቱ መሄድ ስለለመድን ነው። ትልቁ ችግር ያመጣው ምን ችግር አለው? ነው።
አንዳንዶቻችን ግን ነጠላ ስለከበስኩይ ሳይሆን እንላለን
ይሄ ግን ይሄ ምክንያት አይሆንም።
እያወቅን በድፍረት ሳናውቅ በስህተት ከምንሰራቸው ነገሮች አይነ ልቦናችንን ያብራልን አሜን!!
🌺🌹ወስብሐት ለእግዚአብሔር🌹🌺
አሜን
+++ በመስቀሉ ፈልገህ አግኘው! +++
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተራራ ወርዶ ፤ ወደ እርሱ መጥቶ ያነጻው ዘንድ የጠየቀውን አንድን ለምጻም ዳስሶ ከፈወሰ በኋላ ፤ ወደ ቅፍርናሆም ሄዶ ሽባ ሆኖ የሚሰቃየውን የመቶ አለቃውን ልጅ በቃል ብቻ ተናግሮ አዳነለት። ቀጥሎም በንዳድ በሽታ ታምማ የተኛችውን የጴጥሮስን አማት ዳስሶ ፈወሳት። ምሕረቱ የበዛ ነውና ብዙ ሕሙማን ከየችግራቸው ነፃ አወጣቸው አዳናቸውም። ከዚያም ባሕሩን ይሻገር ዘንድ ወደ ታንኳ ገባ ፤ "ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት።" (ማቴ. 8: 23) ፤ የባሕር ላይ ጉዞአቸውን እንደጀመሩ ማዕበሉ ታንኳይቱን እስኪደፍናት ድረስ በባሕር ታላቅ መናወጥ ሆነ ፤ ጌታችን ግን ተኝቶ ነበር። ደቀ መዛሙርቱም ከመጨነቃቸው የተነሣ ፦ "ጌታ ሆይ፥ አድነን፥ ጠፋን" እያሉ አስነሡት።
ጌታችንም ከእንቅልፉ እንደተነሣ ፤ "ምን ተፈጠረ? ምንስ አገኛችሁ?" አላለም ፤ ይልቁንም "እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ ስለ ምን ትፈራላችሁ? አላቸው። ከዚህ በኋላም "ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፥ ታላቅ ጸጥታም ሆነ" (ማቴ. 8: 26)። ይገርማል! ተፈጥሮ ከወዴት አቅም አግኝታ ፤ እንዴት ማንነቱን ብትዘነጋ ፤ ይሆን አምላኳ ያለበትን ታንኳ እንዲህ ያሰጨነቀችው? ፈጣሬ ፍጥረታት ፣ አኀዜ ዓለማት ታንኳይቱ ስትጨነቅ ፤ እስኪያስነሡት ድረስ እርሱ ተኝቶ ነበር! ሳያውቅ ቀርቶ ነው እንዳንል "ሰው በስውር ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን?" (ኤር. 23: 24) የሚለው የነቢዩ ቃል አያሰናብተንም።
እውነት ነው ሁሉን የሚያውቅ(Omniscent) ነው ፤ ከእርሱ የሚሰወር አንዳች የለም። ስለዚህም ቀስቅሰውት ከእንቅልፉ እንደተነሣ ማብራሪያ ሰጪ ሳያስፈልገው ባሕሩን ገሠጸው። ወዳጄ ሆይ! እንኳን የገጠመህን ፣ በልብህ ያለውን አልፎም ፣ ስለነገህ ያውቃል! ነገር ግን የአንተን ድርሻ እንድትወጣ ፣ የእምነትህንም ጽናት ያይ ዘንድ ይፈልጋል ፤ ነገሩ ቢከብድህ የማይቻልህ ቢሆን በጸሎትህ ቀስቅሰው ፤ እርሱ ጥያቄዎችህን ሁሉ ይመልሳል። 'ክርስቶስ ከእኔ ጋር ባይኖር እንጂ ፈተና ባልበዛብኝ ነበር' አትበል ፤ እርሱን ስትከተል ከእርሱ ጋር ስትኖር የእርሱ የሆነው መስቀሉም ከአንተ ጋር ነውና ፤ ልብህን አታዘናጋ! "ፈልጎ ያገኘህ በመስቀሉ ነውና ፤ አንተም ፈልገህ የምታገኘው በመስቀሉ ነው!" ቀደምት አበው ስለዚህች ታንኳ እና ስለ ቅዱስ መስቀሉ ብዙ ድንቅ ትምህርት አስተምረዋል። ደቀ መዛሙርቱ ጌታችን ወደ ታንኳ ሲገባ ተከትለውት ነበር ፤ እውነት ነው እርሱ ክርስቶስ "በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ።" (ሉቃ. 9: 23) ብሎ ነበርና ተከተሉት። ጌታ ያለባት ታንኳ ከማዕበሉ የተነሣ ተናወጸች ፤ መድኃኔ ዓለምም በመስቀል ላይ ከአይሁድ መከራ የተነሣ ታመመ። በታንኳይቷ ውስጥ ክርስቶስ ተኝቶ ነበር ፤ እውነት ነው የሰውን ልጅ ለማዳን በመስቀል ላይ እንቅልፍ የተባለ ሞትን ቀመሰ። ደቀ መዛሙርቱም ተኝቶ ሲያዩት "ጌታ ሆይ፥ አድነን፥ ጠፋን" እያሉ ቀሰቀሱት ፤ ወደ ታንኳ ከመግባታቸው አስቀድሞ የለምጻሙን መንጻት ፣ የሽባውን መተርተርና ብዙዎችን በመፈወስ የገለጠውን ኃይሉን የዘነጉ ይመስላል "ልንጠፋ ነው" አሉት። እውነትም ደቀ መዛሙርቱ በመስቀል ላይ ሞቶ ሲመለከቱት "የሰው ልጅ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጣል፥ ይገድሉትማል፥ ተገድሎም በሦስተኛው ቀን ይነሣል" (ማር. 9: 30-31) በማለት አስቀድሞ የነገራቸውን ዘንግተውት ኖሮ ይጨነቁና ያዝኑ ነበር።
በታንኳይቱ ውስጥ ጌታችን ከእንቅልፉ ተነሥቶ ማዕበሉን ጸጥ እንዳደረገው ፤እንዲሁ መድኃኔ ዓለም ሞትን ድል አድርጎ ፣ በሞት ግዞት የሚያስጨንቀውን የአጋንንት ኃይል አጥፍቶ በሦስተኛው ቀን ተነሣ።
+++
"ወዳጄ ሆይ! 'ክርስቶስ ከእኔ ጋር ባይኖር እንጂ ፈተና ባልበዛብኝ ነበር' አትበል ፤ እርሱን ስትከተል ከእርሱ ጋር ስትኖር የእርሱ የሆነው መስቀሉም ከአንተ ጋር ነውና ፤ ልብህን አታዘናጋ! "ፈልጎ ያገኘህ በመስቀሉ ነውና ፤ አንተም ፈልገህ የምታገኘው በመስቀሉ ነው!"
+++
"ባሕር የተባለ የዚህ ዓለም መራራ እና ጨለማ የመከራ ሕይወት ነው ፤ እውነተኛ አማኝ ታንኳ የተባለውን ቅዱስ መስቀሉን ይዞ የዚህን ዓለም ፈተናዎች በማለፍ ከመንግሥተ ሰማያት ወደብ ማረፊያ ይደርሳል" (ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ)
+++
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ዲያቆን ደረጀ ድንቁ
ጓደኞትን ይጋብዙ ትምህርት ጀምረናል
@embtee
@embtee
@embtee
ለሁሉም የድንግል ወዳጆች ሼር ሼር ሼር

ስለ ምን እንማር?
1 ትምህርተ ሃይማኖት ❤️
2 ነገረ ማርያም 🧡
3 ለመናፍቃን መልስ 💚
4 የአቡነ ሺኖዳ ምክሮች 💜
5 ምክረ አበው 💙
የርሶ ድጋፍ ዋጋ አለውና ፍላጎቶን ይግለጹ

እናመሠግናለን 🙏🙏🙏