✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.06K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
Audio
ሰሞነ ሕማማት ምንድነው
የጥያቄ መልሶች በዝርዝር

በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ
ገብሩ ለቅዱስዳዊት ንጉሠ እስራኤል

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር።
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@embtee
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
🌻💐💐💐🌻🌻💓💓
🌺 🌷 እንኳን 🌼🌼🌼
🌸🌹 ለትንሣኤ 🌸🌺🌸
🌹🌺 በሰላም 🌷 🌺🌻
🌹🌷አደረሳችሁ🌷🌹🌻
🌻🌾🌾🌾🌻🌻💓💓
እንኳን አደረሳችሁ
+++ ‹‹ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል›› መዝ 92፥12 +++

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተሰጋግሞ የመነሣት እድል ካገኙ እጽዋት መካከል አንዱ የዘንባባ ተክል ነው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤት ከሠራ በኋላ በመቅደሱ የውስጥ ግንቦች ላይ ከቀረጻቸው ምስሎች ውስጥ አንዱ የዘንባባን ቅጠል ነው፡፡(1ኛ ነገ 6፡29) በእስራኤላውያን ታሪክም ድል ሲቀናቸውና ሲደሰቱ በእጃቸው የሚገኘው እጽ ይኸው ዘንባባ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች የአንድ አገር መለያ አድርገው ከሚጠቅሷቸው ምልክቶች ውስጥ ‹‹የዘንባባ ዛፍ›› አንደኛው ነው፡፡(ዘዳ 34፡3) ከዚህ ሁሉ ደግሞ በጣም የሚያስደንቀው የሐዲስ ኪዳኑ ባለ ራእይ ቅዱስ ዮሐንስ እንደ ጻፈው ሩጫቸውን በድል የጨረሱና ነጭ የለበሱ የጻድቃን ነፍሳት ‹‹የዘንባባን ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት›› መቆማቸው ነው፡፡(ራእይ 7፡19) ዘንባባ በምድር ላለ ደስታ ብቻ ሳይሆን በሰማይም ላለ የድል ነሺነትና የአሸናፊት መንፈስ መግለጫ ምልክት ሆኖ ያገለግላል፡፡

ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ጻድቃንን ለምን በዘንባባ ዛፍ ይመስላቸዋል? መዝሙረኛውስ ‹ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል› ሲል ለምን ዘመረ? ቅዱሳንን ከዘንባባ ጋር ምን አገናኛቸው?

ሁላችንም እንደምናውቀው ጣፋጭ ፍሬ ከሚሰጡ እጸዋት መካከል አንዱ ዘንባባ ነው፡፡ የዘንባባን ዛፍ ለየት የሚያደርገው ጣፋጭ ፍሬ መስጠቱ ብቻ ሳይሆን ሥሮቹ በጣም ጠንካራ እና ወደ ታች ጠልቀው የሚገቡ (የሚሰዱ) መሆናቸው ነው፡፡ ጸድቃንም እንደ ዘንባባ ፍሬ የሚጥም በጎ ምግባርን የተሸከሙ የሃይማኖት ተክል ሲሆኑ፣ የታነጹበትና የቆሙበት የእምነትና የፍቅር ሥሮችም በጣም የጸኑ እና ጥልቆች ናቸው፡፡

ሌላው የዘንባባ ዛፍ በየትኛውም ጊዜ ቢተከል ሊያፈራ የሚችልና በበረሃ የሚበቅል ልዩ ተክል ነው። ቅዱሳንም በጊዜውም ሆነ ያለ ጊዜው ጸንተው ይገኛሉ። በበረሃም እንደሚጸድቅ ዘንባባ በዚህች ክፋት በሞላባት ዓለም ውስጥ እየኖሩ በቅድስና ይገኛሉ።

የዘንባባ ዛፍ ልክ እንደ ሌሎች እጸዋት ብዙ ቅርንጫፎች የሉትም፡፡ በዚህም ምክንያት እንስሳት ፍሬው ወደሚገኝበት የዛፉ ጫፍ በቀላሉ ለመውጣትና ለመብላት ይቸገራሉ፡፡ እንዲሁ ጻድቃንም በጎ ሥራዎቻቸውንና መንፈሳዊ ደስታቸውን ከእነርሱ እንዲወስዱባቸው ለአጋንንት መግቢያ በር፣ መውጫ ቅርንጭፍ አያኖሩም፡፡ ሐሴቶቻቸውም ከፍ ያሉ ሰማያውያን በመሆናቸው ምድር ምድሩን የሚሄደው ሰይጣን በቀላሉ ሊተናኮላቸውና ደስታቸውን ሊያጠፋ አይችልም፡፡

ዘንባባ ብዙ ቅርንጫፎች የሌለው መሆኑ አንዳንዴ ድንጋይ እንዲወረወርበት እና በዱላ እንዲመታ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ እርሱ ግን ‹‹ይቅር ባይ›› ተክል ነው፡፡ በተወረወረበት ድንጋይ እና ባረፈበት ዱላ ፈንታ የሚመልሰው ጣፋጭ ፍሬውን ነው፡፡ አንተ ድንጋይ ስትወረውርበት እርሱ ደግሞ እንደ ማር የሚጣፍጠውን ፍሬ ያዘንብልሃል፡፡ ሰይጣን ለእርሱ መግቢያ ምክንያት የማይሰጡትን ጻድቃን የሚፈትነው ለክፉ ዓላማው ማስፈጸሚያ የሚያደርጋቸውን ሰዎች በመጠቀም ነው፡፡ በእነዚህም ሰዎች አማካኝነት ብዙ የስድብ፣ የጥላቻና የስም ማጥፋት ድንጋዮችን ይወረውርባቸዋል፡፡ በበቀል ዱላ ሊያቆስላቸው ይሰነዝርባቸዋል፡፡ እነርሱ ግን የሰደቧቸውን ሰዎች በመመረቅ፣ የጠላቸውን በመውደድ፣ ለበቀል ስለሚያሳድዷቸው ሰዎችም በመጸለይ ጣፋጭ ፍሬዎቻቸውን ያዘንቡላቸዋል፡፡

በሆሳዕና ዘንባባ ይዘን ዘምረን፣ እንደ ዘንባባ ዛፍ አፍርተን፣ በኋላም ከጻድቃኑ ጋር ነጭ ለብሰንና በእጆቻችን የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘን ከበጉ ፊት ለመቆም ያብቃን!

=== ልክ እንደ ጻድቃኑ የዘንባባ ሕይወት ይስጠን!!! ===

እባካችሁ leave ከምትሉ አስተያየት በ @asrategabriel ላይ አድርሱን።
✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞ pinned «Watch "🛑ምስክርነት ||Misekirenat|| Ethiopian ortodox tewahido|meron shewarega|"2013"" on YouTube https://youtu.be/iXCQ63Sfy-Y»
🎬 ©እዩና እመኑ ሰዎች "||

👤 ኪነ ተዋህዶ ቲዩብ

⚠️ ለማዳመጥ ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/FR3la1fCYk0
https://youtu.be/FR3la1fCYk0
https://youtu.be/FR3la1fCYk0
🛑ሼር🛑
በከንፈሮቹ የማያመሰግንሽ ፣ ባንደበተም የማይመርቅሽ ርጉም ነው።
ለክብርሽ የማይሰግድ ፣ ለገናንነትሽ የማይገዛ ዕደል ፈንታው ጽዋ ተርታው ገሀነመ እሳት ነው።
/ አርጋኖን 4 ፥ 12
ግንቦት አንድ ልደታ የአመት ነው
#ድንግል_ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤
በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ) (አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም)
#ልደቷን_የጨለማችን መገፈፍ የዐይናችን ማየት የብርሃናችንም መዉጣት ነዉና በፍጹም ደስታ እናስበዋለን እናከብረዋለንም፡፡"
እመቤታችን የተወለደች እለት አባቷ ኢያቄምና እናቷ ሀና ከመጠን በላይ ተደሰቱ:: የእመቤታችን ልደት ዓለም ማየት የጀመረበት ዕለት ነዉ ማለት ነዉ፡፡ በጨለማ ሲያዩት የሚያስፈራዉና ሌላ የሚመስለዉ ጉቶ ቁጥቋጦዉ ድንጋዩ ጉብታዉ ሁሉ ተራ ነገር መሆኑ የተጋለጠባት ሰዎችም የሰገዱለት ሁሉ አምላክና ጌታ መሆኑ ቀርቶ ድንጋይ ጉብታ መሆኑን ማየት የጀመሩባት ከደገኛዉ ፀሐይ ክርስቶስ ከመውጣት በፊት ከረጅሙ ዘመን ጨለማ ጭንቀት የተገላገልንባት ጨረቃ ብርሂት የቀኝ ዐይን እመቤታችን ማርያም ናት ፡፡ ስለዚህም ልደቷን የጨለማችን መገፈፍ የዐይናችን ማየት የብርሃናችንም መዉጣት ነዉና በፍጹም ደስታ እናስበዋለን እናከብረዋለንም፡፡
እመቤታችን_እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ከልደቷ ረድኤት በረከት ይክፈለን አሜን ።
# መልካምነት_መልሶ_ይከፍላል
በአንድ ወቅት አንድ ወጣት ብዙ እንጨቶችን ተሸክሞ በጫካ ውስጥ ያቋርጣል፡፡ ትንሽ እንደተጓዘ አንድ ትልቅ ሰው ተርቦ ተመለከተ፤ ልቡ በጣም አዘነ፤ ምግብ ሊሰጠው ፈለገ ነገር ግን ለእራሱም የሚበላው የለውም ነበር፡፡ እናም ምንም ሳያደርግለት መንገዱን ቀጠለ፡፡
አሁንም ከትንሽ መንገድ በኀላ አንድ አጋዘን በውሃ ጥም ሲሰቃይ ተመለከተ፤ ወጣቱ አሁንም ልቡ አዘነ፤ ውሃ ሊያጠጣው ወደደ ነገር ግን ለእራሱ የሚጠጣውም ውሃ አልነበረውምና ምንም ማድረግ ሳይችል መንገዱን ቀጠለ፡፡
አሁንም ትንሽ ከተጓዘ በኀላ የሆነ ቱሪስት ካምፕ ለመስራት ፈልጎ እንጨት ሲፈልግ ተመለከተው፤ በዚህ ወቅት ወጣቱ ለቱሪስቱ የሚያስፈልገውን ያህል እንጨት ሰጠው፡፡ ቱሪስቱም ለወጣቱ ከሰነቀው ምግብና ውሃ አካፈለው፡፡ በዚህ ወቅት ወጣቱ ወደ ተራበው ሰው ተመልሶ ቱሪስቱ ከሰጠው ምግብ አካፈለው፤ ወደ አጋዘኑ ተመልሶ ከውሃው አጠጣው፡፡
በሌላ ቀን ወጣቱ ተንሸራቶ ገደል ይገባል፤ በጣም ታመመ በዙሪያው ግን አንድም የሚረዳው ሰው አልነበረም፤ ድንገት ግን በሌላ ቀን ምግብ ያበላው ሰውዬ ሲያልፍ ወጣቱን ተመለከተና ከገባበት ገደል ጎትቶ አወጣው፤ ነገር ግን ብዙ ቦታ ተጋግጧል፡፡ በዚህ ወቅት ውሃ ያጠጣው አጋዘን ወደ ጫካው በመግባት ለመድኀኒትነት የሚጠቅመውን ዕፅ አመጣለት፡፡ ከእዛን ቀን በኀላ ወጣቱ ፣ ትልቁ ሰው እና አጋዘኑ በደስታ ይኖሩ ጀመር፡፡
እርዳታ የሚፈልግ ሰው ስንመለከት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንርዳ፤ አንድ ቀን እኛም የሰዎችን እርዳታ የምንፈልግበት ሁኔታ ይፈጠራል፤ የዛኔ መልካምነታችን መልሶ ይከፍለናል፡፡
መልካምነት ለራስ ነው
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Audio
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
#join_share
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@embtee
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
🛑_አዲስ_የንስሃ_ዝማሬ_"የማደርገውን_አላውቅም"_ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ360p.mp4
25.9 MB
new mezmur

🎤 ሊቀ መዘምር ቴድሮስ ዮሴፍ

🎼የማደርገውን አላውቅም

ሌሎች አዳዲስ መዝሙር ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇👇

🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
#join_share
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@embtee
@embtee
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
🛑_አዲስ_የበገና_ዝማሬ_"ቅዱስ"_|_ዘማሪ_አቤል_ተስፋዬ360p.mp4
20.5 MB
new mezmur

🎤 ዘማሪ አቤል ተስፋዬ

🎼ቅዱስ

ሌሎች አዳዲስ መዝሙር ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇👇

🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
#join_share
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@embtee
@embtee
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ
እመ አምላክ | @Z_TEWODROS TELEGRAM CHANNEL |
╭══•|❀:✧๑ ♡ ♡๑✧❀|: ══╮
@embtee @embtee
━━━━━━━━━━━━━━━━
Join and Share

🔔የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር ✞🔔
Audio
ተክለሃይማኖት ባህታዊ ዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ - Teklehaymanoylt bahitawi zemarit tsedale…
Mikiyas Tube ሚክያስ ቲዩብ
ተክለሐይማኖት ባህታዊ

ተክለ ሐይማኖት ባህታዊ
ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ
በአደባባዩ ተተክለሃል
ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል

ቃልኪዳን አለህ የገነነ
ምህረት የሚያሰጥ የታመነ
በስምህ ውሃ አጠጥተን
ዋጋችን በዝቷል አባታችን
#አዝ
እኛም ሆነናል ልጆችህ
ማርኮ አስቀርቶን ምግባርህ
በምልጃህ ጸሎት ትሩፋት
ቤታችን መላ በረከት
#አዝ
ምህረት ይዘንማል ከሰማይ
በአንድ እግርህ ቆመህ ስትጸልይ
ብዙ ተጋድለህ አትርፈሀል
ያገለገልከው አክብሮሃል
#አዝ
ተሰባበሩ ጣዖታቱ
አምነው ሰገዱ መኳንንቱ
የበረታው ቃል ከአፍህ ወጥቶ
የአምላክ አድርጓል ሁሉን ገዝቶ

ዘማሪት
ጸዳለ ጎበዜ