✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.06K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
✥ ሰምተን ያልተገበርነው ትምህርት

አባ በምዋ (Abba Bemwa) ዓለምን ትቶ ወደ በረሃ በሄደ ጊዜ፣ ለዚህ አዲስ ሕይወቱ የሚጠቅመውን ምክር ይሰጡት ዘንድ ወደ አንድ ቅዱስ አረጋዊ ቀርቦ "ምን ላድርግ" ሲል ጠየቃቸው። እኒህም አረጋዊ ንግግራቸውን የጀመሩት "በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ" በሚለው በቅዱስ ዳዊት የመዝሙር ቃል ነበር። (መዝ 39፥1) አባ በምዋም ይህንን የመጽሐፍ ቃል በሰማ ጊዜ "ይበቃል አባቴ፣ ይህን ተምሬ እስክፈጽም ድረስ ሌላ ምንም አዲስ ትምህርት አይንገሩኝ" በማለት ወደ በዓቱ ሄደ።

ከዚያም ቀን ጀምሮ ለብዙ ጊዜያት ወደ አረጋዊው አልተመለሰም ነበር። ከዕለታት በአንዱ ቀን አረጋዊው ጻድቅ አባ በምዋን አግኝተው ለምን ለሌላ ተጨማሪ ትምህርት መልሶ ወደ እርሳቸው እንዳልመጣ ጠየቁት። እርሱም "እመኑኝ አባቴ፣ ገና የመጀመሪያውን ትምህርት በሚገባ አልተማርኹትም" ሲል መለሰላቸው። ከረጅም ዓመታትም በኋላ ወዳጁ የሆነ አንድ መነኩሴ የሰማውን የነቢዩ የዳዊትን ቃል እስከ አሁን አጥንቶ ጨርሶ እንደሆነ አባ በምዋን ጠየቀው። ቅዱሱም "በዚህ የነቢዩ ቃል ላይ ለማሰላሰል እና በሚገባ ወደ ተግባር ለመቀየር አርባ አምስት ዓመታት ወስዶብኛል" ሲል በትሕትና መለሰለት። የአባ በምዋን ታሪክ የጻፈልን ቅዱስ ጰላድዮስ እንደሚናገረው አባ በምዋ በሕይወቱ ሁሉ ፍጽምት የሆነች የዝምታን ሕይወት የመራ ሲሆን፣ በሞቱም ጊዜ "ምነው ይህን ባልተናገርኩ" የሚል አንድም የሕሊና ወቀሳ ሳያገኘው በሰላም አርፏል።

ቅዱስ እንጦንስም በአንድ ወቅት ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ሲል መክሯቸው ነበር ፦ "ዝም በሉ፤ ዝምተኛን ሰው እግዚአብሔር በፊቱ ካሉት ሠራዊተ መላእክት እንደ አንዱ ይቆጠረዋልና"

ስለዚህ ከመላእክት ጋር እንቆጠር ዘንድ አብረን ዝም እንበል!
ዛሬ ሰሙነ ሕማማት

ዕለታት ስያሜዎች ጌታችን የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግስቱ ከቢታንያ ሲወጣ ተራበ፤ በመንገድም ሲያልፍ ቅጠል ያላት በለስን ከሩቁ ተመለከተ፡፡ ወደ በለሲቱም በቀረበ ጊዜ ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ያንጊዜም ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ለዘለዓለም ከአንቺ ፍሬ የሚበላ አይኑር›› ሲል በለሲቱን ረገማት፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ይህንን ሰሙት፡፡ በዚህም ምክንያት ይህች ዕለት በለሲቱ የተረገመችባት ቀን ናትና መርገመ በለስ ተብላ ትጠራለች፡፡ (ማር.፲፩፥፲፩-፲፬)
በዚህ አገላለጽ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ስትሆን ፍሬ የተባለ ደግሞ ሃይማኖትና ምግባር ነው፡፡ መድኃኒታችን ክርስቶስ ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈልጎ አላገኘባቸውም፡፡ እስራኤል፦ ሕዝበ እግዚአብሔር፣ የአብርሃም ዘር መባልን እንጂ የአብርሃምን ሥራ በመሥራት በምግባር በሃይማኖት ጸንተው መኖር አይፈልጉምና ደግ ሰው አልተገኘባቸውም፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በለስ የተባለች ኦሪት ናት፡፡ ኦሪት በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛትም አማናዊ ድኅነትን የምታሰጥ ሆና አላገኛትም፡፡ ይሁን እንጂ በእርሷ ድኅነት ባይገኝባትም ‹‹ኦሪትና ነቢያትን ከመፈጸም በቀር ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ›› በማለት ሕገ ኦሪትን ፈጽሟታል፡፡ ከዚህም ባሻገር በለስ የተባለች ኃጢአት ናት፡፡ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አግኝቷታል፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሠሩት ለጊዜው ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም በአ
✞እንዴት እንዲያጠፉት✞
♡የመዝሙር ግጥሞች♡
✞ እንዴት እንዲያጠፉት ✞

እንዴት እንዲያጠፉት ካህናት መከሩ
ያመነቱ ነበር ሕዝብን እየፈሩ
ሰይጣን በይሁዳ ገብቶ ነበርና
አሳልፎ እንዲሰጥ ልቦናውም ጸና

ከመቅደስ አዛዦች ከካህናት ጋራ
ስለጌታ መሞት ባንድ ላይ አወራ
ካህናት በደስታ ይሁዳን አቀፉት
አምላኩን እንዲያሲዝ ሰላሳ ብር ሰጡት
አዝ
ሕዝብ በሌለበት በአሳቻ ስፍራ
ጌታን እንዲያሲዘው አደረገ ሴራ
ኧረ እንዴት ጨከነ ይሁዳ አንጀትህ
ጌታን ያስገደልከው እንደዚያ ሲወድህ
አዝ
በረከቱን ከጅህ ሥልጣኑን በራስህ
ሊሰጥህ አስቦ ኢየሱስ ሊያከብርህ
ሰማየዊ ሀብትን ሰማያዊ ፀጋ
አድሎህ ነበረ አልፋና ኦሜጋ
አዝ
የቃየል መሰዋዕት የኤሳው ብኩርና
ጌታውን የሚሸጥ ከፍጡር ሆነና
በሰላሳ ዲናር በሚጠፋው ብዕል
እንዲህ ያለ ጌታ ኧረ እንዴት ይከዳል

ግእዝን ለመማር


╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@embtee
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
Audio
ሰሞነ ሕማማት ምንድነው
የጥያቄ መልሶች በዝርዝር

በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ
ገብሩ ለቅዱስዳዊት ንጉሠ እስራኤል

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር።
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@embtee
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
🌻💐💐💐🌻🌻💓💓
🌺 🌷 እንኳን 🌼🌼🌼
🌸🌹 ለትንሣኤ 🌸🌺🌸
🌹🌺 በሰላም 🌷 🌺🌻
🌹🌷አደረሳችሁ🌷🌹🌻
🌻🌾🌾🌾🌻🌻💓💓
እንኳን አደረሳችሁ
+++ ‹‹ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል›› መዝ 92፥12 +++

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተሰጋግሞ የመነሣት እድል ካገኙ እጽዋት መካከል አንዱ የዘንባባ ተክል ነው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤት ከሠራ በኋላ በመቅደሱ የውስጥ ግንቦች ላይ ከቀረጻቸው ምስሎች ውስጥ አንዱ የዘንባባን ቅጠል ነው፡፡(1ኛ ነገ 6፡29) በእስራኤላውያን ታሪክም ድል ሲቀናቸውና ሲደሰቱ በእጃቸው የሚገኘው እጽ ይኸው ዘንባባ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች የአንድ አገር መለያ አድርገው ከሚጠቅሷቸው ምልክቶች ውስጥ ‹‹የዘንባባ ዛፍ›› አንደኛው ነው፡፡(ዘዳ 34፡3) ከዚህ ሁሉ ደግሞ በጣም የሚያስደንቀው የሐዲስ ኪዳኑ ባለ ራእይ ቅዱስ ዮሐንስ እንደ ጻፈው ሩጫቸውን በድል የጨረሱና ነጭ የለበሱ የጻድቃን ነፍሳት ‹‹የዘንባባን ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት›› መቆማቸው ነው፡፡(ራእይ 7፡19) ዘንባባ በምድር ላለ ደስታ ብቻ ሳይሆን በሰማይም ላለ የድል ነሺነትና የአሸናፊት መንፈስ መግለጫ ምልክት ሆኖ ያገለግላል፡፡

ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ጻድቃንን ለምን በዘንባባ ዛፍ ይመስላቸዋል? መዝሙረኛውስ ‹ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል› ሲል ለምን ዘመረ? ቅዱሳንን ከዘንባባ ጋር ምን አገናኛቸው?

ሁላችንም እንደምናውቀው ጣፋጭ ፍሬ ከሚሰጡ እጸዋት መካከል አንዱ ዘንባባ ነው፡፡ የዘንባባን ዛፍ ለየት የሚያደርገው ጣፋጭ ፍሬ መስጠቱ ብቻ ሳይሆን ሥሮቹ በጣም ጠንካራ እና ወደ ታች ጠልቀው የሚገቡ (የሚሰዱ) መሆናቸው ነው፡፡ ጸድቃንም እንደ ዘንባባ ፍሬ የሚጥም በጎ ምግባርን የተሸከሙ የሃይማኖት ተክል ሲሆኑ፣ የታነጹበትና የቆሙበት የእምነትና የፍቅር ሥሮችም በጣም የጸኑ እና ጥልቆች ናቸው፡፡

ሌላው የዘንባባ ዛፍ በየትኛውም ጊዜ ቢተከል ሊያፈራ የሚችልና በበረሃ የሚበቅል ልዩ ተክል ነው። ቅዱሳንም በጊዜውም ሆነ ያለ ጊዜው ጸንተው ይገኛሉ። በበረሃም እንደሚጸድቅ ዘንባባ በዚህች ክፋት በሞላባት ዓለም ውስጥ እየኖሩ በቅድስና ይገኛሉ።

የዘንባባ ዛፍ ልክ እንደ ሌሎች እጸዋት ብዙ ቅርንጫፎች የሉትም፡፡ በዚህም ምክንያት እንስሳት ፍሬው ወደሚገኝበት የዛፉ ጫፍ በቀላሉ ለመውጣትና ለመብላት ይቸገራሉ፡፡ እንዲሁ ጻድቃንም በጎ ሥራዎቻቸውንና መንፈሳዊ ደስታቸውን ከእነርሱ እንዲወስዱባቸው ለአጋንንት መግቢያ በር፣ መውጫ ቅርንጭፍ አያኖሩም፡፡ ሐሴቶቻቸውም ከፍ ያሉ ሰማያውያን በመሆናቸው ምድር ምድሩን የሚሄደው ሰይጣን በቀላሉ ሊተናኮላቸውና ደስታቸውን ሊያጠፋ አይችልም፡፡

ዘንባባ ብዙ ቅርንጫፎች የሌለው መሆኑ አንዳንዴ ድንጋይ እንዲወረወርበት እና በዱላ እንዲመታ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ እርሱ ግን ‹‹ይቅር ባይ›› ተክል ነው፡፡ በተወረወረበት ድንጋይ እና ባረፈበት ዱላ ፈንታ የሚመልሰው ጣፋጭ ፍሬውን ነው፡፡ አንተ ድንጋይ ስትወረውርበት እርሱ ደግሞ እንደ ማር የሚጣፍጠውን ፍሬ ያዘንብልሃል፡፡ ሰይጣን ለእርሱ መግቢያ ምክንያት የማይሰጡትን ጻድቃን የሚፈትነው ለክፉ ዓላማው ማስፈጸሚያ የሚያደርጋቸውን ሰዎች በመጠቀም ነው፡፡ በእነዚህም ሰዎች አማካኝነት ብዙ የስድብ፣ የጥላቻና የስም ማጥፋት ድንጋዮችን ይወረውርባቸዋል፡፡ በበቀል ዱላ ሊያቆስላቸው ይሰነዝርባቸዋል፡፡ እነርሱ ግን የሰደቧቸውን ሰዎች በመመረቅ፣ የጠላቸውን በመውደድ፣ ለበቀል ስለሚያሳድዷቸው ሰዎችም በመጸለይ ጣፋጭ ፍሬዎቻቸውን ያዘንቡላቸዋል፡፡

በሆሳዕና ዘንባባ ይዘን ዘምረን፣ እንደ ዘንባባ ዛፍ አፍርተን፣ በኋላም ከጻድቃኑ ጋር ነጭ ለብሰንና በእጆቻችን የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘን ከበጉ ፊት ለመቆም ያብቃን!

=== ልክ እንደ ጻድቃኑ የዘንባባ ሕይወት ይስጠን!!! ===

እባካችሁ leave ከምትሉ አስተያየት በ @asrategabriel ላይ አድርሱን።
✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞ pinned «Watch "🛑ምስክርነት ||Misekirenat|| Ethiopian ortodox tewahido|meron shewarega|"2013"" on YouTube https://youtu.be/iXCQ63Sfy-Y»
🎬 ©እዩና እመኑ ሰዎች "||

👤 ኪነ ተዋህዶ ቲዩብ

⚠️ ለማዳመጥ ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/FR3la1fCYk0
https://youtu.be/FR3la1fCYk0
https://youtu.be/FR3la1fCYk0
🛑ሼር🛑
በከንፈሮቹ የማያመሰግንሽ ፣ ባንደበተም የማይመርቅሽ ርጉም ነው።
ለክብርሽ የማይሰግድ ፣ ለገናንነትሽ የማይገዛ ዕደል ፈንታው ጽዋ ተርታው ገሀነመ እሳት ነው።
/ አርጋኖን 4 ፥ 12
ግንቦት አንድ ልደታ የአመት ነው
#ድንግል_ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤
በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ) (አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም)
#ልደቷን_የጨለማችን መገፈፍ የዐይናችን ማየት የብርሃናችንም መዉጣት ነዉና በፍጹም ደስታ እናስበዋለን እናከብረዋለንም፡፡"
እመቤታችን የተወለደች እለት አባቷ ኢያቄምና እናቷ ሀና ከመጠን በላይ ተደሰቱ:: የእመቤታችን ልደት ዓለም ማየት የጀመረበት ዕለት ነዉ ማለት ነዉ፡፡ በጨለማ ሲያዩት የሚያስፈራዉና ሌላ የሚመስለዉ ጉቶ ቁጥቋጦዉ ድንጋዩ ጉብታዉ ሁሉ ተራ ነገር መሆኑ የተጋለጠባት ሰዎችም የሰገዱለት ሁሉ አምላክና ጌታ መሆኑ ቀርቶ ድንጋይ ጉብታ መሆኑን ማየት የጀመሩባት ከደገኛዉ ፀሐይ ክርስቶስ ከመውጣት በፊት ከረጅሙ ዘመን ጨለማ ጭንቀት የተገላገልንባት ጨረቃ ብርሂት የቀኝ ዐይን እመቤታችን ማርያም ናት ፡፡ ስለዚህም ልደቷን የጨለማችን መገፈፍ የዐይናችን ማየት የብርሃናችንም መዉጣት ነዉና በፍጹም ደስታ እናስበዋለን እናከብረዋለንም፡፡
እመቤታችን_እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ከልደቷ ረድኤት በረከት ይክፈለን አሜን ።
# መልካምነት_መልሶ_ይከፍላል
በአንድ ወቅት አንድ ወጣት ብዙ እንጨቶችን ተሸክሞ በጫካ ውስጥ ያቋርጣል፡፡ ትንሽ እንደተጓዘ አንድ ትልቅ ሰው ተርቦ ተመለከተ፤ ልቡ በጣም አዘነ፤ ምግብ ሊሰጠው ፈለገ ነገር ግን ለእራሱም የሚበላው የለውም ነበር፡፡ እናም ምንም ሳያደርግለት መንገዱን ቀጠለ፡፡
አሁንም ከትንሽ መንገድ በኀላ አንድ አጋዘን በውሃ ጥም ሲሰቃይ ተመለከተ፤ ወጣቱ አሁንም ልቡ አዘነ፤ ውሃ ሊያጠጣው ወደደ ነገር ግን ለእራሱ የሚጠጣውም ውሃ አልነበረውምና ምንም ማድረግ ሳይችል መንገዱን ቀጠለ፡፡
አሁንም ትንሽ ከተጓዘ በኀላ የሆነ ቱሪስት ካምፕ ለመስራት ፈልጎ እንጨት ሲፈልግ ተመለከተው፤ በዚህ ወቅት ወጣቱ ለቱሪስቱ የሚያስፈልገውን ያህል እንጨት ሰጠው፡፡ ቱሪስቱም ለወጣቱ ከሰነቀው ምግብና ውሃ አካፈለው፡፡ በዚህ ወቅት ወጣቱ ወደ ተራበው ሰው ተመልሶ ቱሪስቱ ከሰጠው ምግብ አካፈለው፤ ወደ አጋዘኑ ተመልሶ ከውሃው አጠጣው፡፡
በሌላ ቀን ወጣቱ ተንሸራቶ ገደል ይገባል፤ በጣም ታመመ በዙሪያው ግን አንድም የሚረዳው ሰው አልነበረም፤ ድንገት ግን በሌላ ቀን ምግብ ያበላው ሰውዬ ሲያልፍ ወጣቱን ተመለከተና ከገባበት ገደል ጎትቶ አወጣው፤ ነገር ግን ብዙ ቦታ ተጋግጧል፡፡ በዚህ ወቅት ውሃ ያጠጣው አጋዘን ወደ ጫካው በመግባት ለመድኀኒትነት የሚጠቅመውን ዕፅ አመጣለት፡፡ ከእዛን ቀን በኀላ ወጣቱ ፣ ትልቁ ሰው እና አጋዘኑ በደስታ ይኖሩ ጀመር፡፡
እርዳታ የሚፈልግ ሰው ስንመለከት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንርዳ፤ አንድ ቀን እኛም የሰዎችን እርዳታ የምንፈልግበት ሁኔታ ይፈጠራል፤ የዛኔ መልካምነታችን መልሶ ይከፍለናል፡፡
መልካምነት ለራስ ነው
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Audio
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
#join_share
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@embtee
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
🛑_አዲስ_የንስሃ_ዝማሬ_"የማደርገውን_አላውቅም"_ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ360p.mp4
25.9 MB
new mezmur

🎤 ሊቀ መዘምር ቴድሮስ ዮሴፍ

🎼የማደርገውን አላውቅም

ሌሎች አዳዲስ መዝሙር ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇👇

🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
#join_share
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@embtee
@embtee
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
🛑_አዲስ_የበገና_ዝማሬ_"ቅዱስ"_|_ዘማሪ_አቤል_ተስፋዬ360p.mp4
20.5 MB
new mezmur

🎤 ዘማሪ አቤል ተስፋዬ

🎼ቅዱስ

ሌሎች አዳዲስ መዝሙር ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇👇

🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
#join_share
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@embtee
@embtee
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ
እመ አምላክ | @Z_TEWODROS TELEGRAM CHANNEL |
╭══•|❀:✧๑ ♡ ♡๑✧❀|: ══╮
@embtee @embtee
━━━━━━━━━━━━━━━━
Join and Share

🔔የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር ✞🔔