✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.06K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
ሰላም የደጓ እናቴ ማርያም ቻናል አባላት
አዲስ ዜና አለ 🌍🌍🌍
አዲስ የማስተማርያ bot ከፍተናል ገብታቹ ተማሩ
ሊንኩ 👉👉👉 @maryamawit_bot
እንኩዋን አደረሳችሁ

"' በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ "'

+*" ሰማዕታተ ኢትዮጵያ "*+

አመ ዐሡሩ ወአሚሩ ለሚያዝያ በዛቲ ዕለት አዕረፉ ሰማዕታተ ኢትዮጵያ:: በረከቶሙ የሃሉ ምስሌነ ለዐለመ ዐለም አሜን፡፡

ከመዝ ኮነ በውስተ ሀገረ ሊብያ በዕሥራ ምዕት ወሰብዐቱ ዐመተ ምሕረት፡፡ በአሜሃ ዘመን ተንሥኡ ተንባላት እለ ስሞሙ አይሲስ በውስተ ሀገረ ኢራቅ ወሶርያ ወሊብያ ወየመን፡፡ አሐዙ ይቅትሉ ሰብአ ዘረከቡ ወፈድፋደሰ እለ ኮኑ ክርስቲያነ በእምነቶሙ፡፡

ብዙሓን ክርስቲያን ተመትሩ አርእስቲሆሙ በአይሲስ ወተወክፉ አክሊለ ስምዕ እምእላ ሀገራት፡፡ በዝ ዘመን ውእቱ ዘረከቦሙ አይሲስ ለሰብአ ኢትዮጵያ በውስተ ሀገረ ሊብያ እንዘ የሐውሩ ኀበ ሀገረ ኢጣልያ በእንተ መፍቅደ ልቦሙ፡፡ እሉ ከሀድያን ውሉደ ሰይጣን ወአራዊተ ገዳም አሐዝዎሙ ወአዘዝዎሙ ወአፍርሕዎሙ ከመ ይክሀዱ ስሞ ለኢየሱስ ክርስቶስ፡፡

ወእምዝ ዘበጥዎሙ በዘዚአሁ ዝብጠታተ በእንተ ዘኮኑ ክርስቲያነ ርእዮሙ ማዕተበ ክሣዶሙ፡፡ ውእቶሙሰ አበዩ ይእዜኒ ክሂደ ሃይማኖቶሙ እመኒ አመከርዎሙ በረሐብ ወጽምዕ ወበካልኣን ኵነኔያት፡፡ ሶበ አበዩ ክሂደ ወሰድዎሙ ኀበ ምድረ በድው ኀበ አልቦ እክል ወማይ ከመ ይእመኑ እምጽንዐ ረሐብ ወጽምዕ፡፡

ወእምዝ ጠየቅዎሙ ከመ ይብትኩ ማዕተበ ክሣዶሙ ወይክሀዱ ስሞ ለእግዚአብሔር አምላኮሙ፡፡ እሉሰ ሰማዕታት ይእዜኒ አበዩ ክሂደ ስሞ ለፈጣሪሆሙ፡፡ አዲ ይቤልዎ ለአይሲስ "ኦ አይሲስ ለእመ ክህልከ ቀቲሎታ ለሥጋነ ኢትክል ቀቲሎታ ለነፍስነ፡፡ ኢንፈርሕሂ ወኢንደነግጽ እምብልሐ ሰይፍከ እስመ አቅዲሙ ነገረነ አምላክነ እንዘ ይብል ኢትፍርሕዎሙ ለእለ ይቀትሉ ሥጋክሙ ወለነፍስክሙሰ ኢይክሉ ቀቲሎታ፡፡"

አዲ ይቤለነ በውስተ ወንጌሉ ቅዱስ እስመ ኵሉ ዘከቀተለክሙ ይመስሎ ከመ ዘመሥዋዕተ ያበውእ፡፡ ይእዜኒ አንተ ላእኩ ለዲያብሎስ ፈጽም በላዕሌነ መልእክተከ ሰይጣናዌ ወአብእ መሥዋዕተከ ርኩሰ ለእምላክከ ሰይጣናዊ፡፡ ንህነኒ ናበውእ ክሣደነ ንጹሐ ለእምላክነ ዘፈጠረነ እስመ ነአምር ዘከመ ያነሥአነ በትንሣኤሁ ቅድስት አመ ዳግም ምጽአቱ፡፡

አሲስኒ አላዊ መተሮሙ አርእስቲሆሙ በሰይፍ ወኮኑ ሰማዕተ በከመ ዛቲ ዕለት፡፡ ወእምዝ ተሀውከት ኵላ ኢትዮጵያ ወኵላ ዐለም እስመ ትርእየ ትእይንተ ጥብሐቶሙ ለሰማዕታት በመስኮተ ትእይንት፡፡ ኵሎሙ ሰብአ ኢትዮጵያ አስቆቀዉ ወበከዩ ብካየ መሪረ እንዘ ይገብሩ ሰላማዌ ትእይንተ በበአዕዋዲሁ ወበበፍኖቱ፡፡

ወይብሉ በበቃሎሙ "አይሲስ አይሲስ እንተ ትቀትሎሙ ለሰማዕታት: ወታውሕዝ ደመ ንጹሓን በበፍናዊሁ ከመ ደመ አክልብት: ይደልወከ ትቁም ውስተ ዐውደ ፍትሕ ሰማያዊ፡፡"

በዝንቱ ዘመን ቈስለ ልቡ ለህዝብ በሐዘነ ሥጋ እስከነ ይብል "ፍትሐ ጽድቅ ዘዐርገት ውስተ ሰማይ ከመ ትንበር ምስለ ዘፈጠራ እግዚአብሔር እስመ ኢረከበት ውስተ ዛቲ ምድር ኀበ ትነብር ወኀበሂ ታጸልል፡፡ ናሁ ይጸርሕ ደሞሙ ለሰማዕታት ቅድመ ገጹ ለኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ይረድ ፍትሐ ርትዕ ዲበ ምድር ወይሠረው አሲስ እምውስተ ገጻ ለምድር፡፡"

በረከቶሙ: ወጽንዐ ገድሎሙ ለእሉ ሰማዕታት ይሕድር ላዕሌነ ለዐለመ ዐለም አሜን፡፡

ሰላም ለክሙ በቃለ ማሕሌት ወእንዚራ፡፡
ምስለ ሰማዕታት ዘግብጽ መከራቲክሙ ዘሐብራ፡፡
ቅዱሳን ሰማዕታት ዘኦርቶዶሳዊት ሐራ፡፡
እፎ ክህልክሙ ተዐግሦ ጽኑዕ መከራ፡፡
እስከ ክሳውዲክሙ በአሲስ ተመትራ፡፡
(ኢያዕመርኩ ከመ መኑ ጸሐፎ)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ይትባረክ አምላከ አባዊነ ያብፅአነ እስከ ዘአቲ ሰአት
እስከዚህ ሰዓት ያደረሰን የአባቶቻችን አምላክ ይባረክ
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖
ስንክሳር ዘወርኃ ሚያዚያ 12
✞✞✞ እንኩዋን ለጻድቅ ሰው "አባ ሳሙኤል
ዘቆየጻ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
✞✞✞

+*" አባ ሳሙኤል ዘቆየጻ "*+

=>በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መካከለኛው ዘመን
(በተለይ ከ13ኛው እስከ 15ኛው መቶ ክ/ዘመን ድረስ
ያለው) የብርሃን ዘመን ይባላል:: ምክንያቱም ዘመኑ
*ክርስትና ያበበበት::
*መጻሕፍት የተደረሱበት::
*ስብከተ ወንጌል የተስፋፋበት::
*ገዳማዊ ሕይወት የሠመረበት ወቅት በመሆኑ ነው::

+ለዚህ ትልቁ አስተዋጽኦ ደግሞ:-
¤አቡነ ተክለ ሃይማኖት::
¤አቡነ ኤዎስጣቴዎስ::
¤አባ ሰላማ ካልዕ::
¤አቡነ ያዕቆብ::
¤ቅዱሱ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ::
¤አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ::
¤አቡነ መድኃኒነ እግዚእን የመሰሉ አበው መነሳታቸው
ነው::

+በተጨማሪም:-
¤12ቱ ንቡራነ ዕድ::
¤7ቱ ከዋክብት::
¤47ቱ ከዋክብት::
¤5ቱ ከዋክብት የሚባሉ አበው አስተዋጽኦም ልዩ ነበር::

ከእነዚህ መካከልም የ7ቱ እና የ47ቱ ከዋክብት
አስተማሪ: የአበው 3ቱ ሳሙኤሎች (ዘዋልድባ: ዘጣሬጣና
ዘቆየጻ): የሌሎችም እልፍ አእላፍ ቅዱሳን አባት የሆኑት
አባ መድኃኒነ እግዚእ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ::

+ጻድቁ ቅዱሳኑን ሰብስበው: አስተምረው: አመንኩሰው:
መርቀው ሰደው: ሃገራችንን እንዲያበሩ በማድረጋቸው
እንደ አባ ኢየሱስ ሞዐ እርሳቸውም "ወላዴ አእላፍ
ቅዱሳን" ይባላሉ:: ታላቁ ጻድቅና ሰባኬ ወንጌል አባ ዓቢየ እግዚእም (ጐንደር ውስጥ እባብና ጅብ እንዳይጐዳ
የገዘቱ አባት ናቸው) የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ነበሩ
ይባላል::

=>ከ7ቱ ከዋክብት አንዱ የሆኑት የቆየጻው አባ ሳሙኤል
የመድኃኒነ እግዚእ ደቀ መዝሙር ናቸው:: ፋሾ ውስጥ
(ትግራይ አካባቢ) ተወልደው : እንደሚገባ አድገው :
መጻሕፍትን ተምረው ደብረ በንኮል ገብተዋል::
+በዚያም ከ6ቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር የምናኔን ምሥጢርና
ተጋድሎን አጥንተው በመነኮሱበት ቀን ብርሃን
ወርዶላቸዋል:: በጻድቁ መምህራቸው ለአገልግሎት
ሲላኩም ለእርሳቸው ቆየጻ (ትግራይ) ደርሷቸዋል::
+በዚያም በጾም በጸሎት እየተጉ : ስብከተ ወንጌልን
እያስፋፉ : ደቀ መዛሙርትን እያፈሩ ለዘመናት ኑረዋል::
አባ ሳሙኤል በተለየ መንገድ ቅዱሳት መጻሕፍትን ይጽፉ
ነበርም ይባላል::

+በጊዜው 72ቱ ከዋክብት (70ው ሊቃናት) ከሚባሉ
አበው ጋር በመተባበር 4ቱ ወንጌል በብራና : በልዩ ጌጥ :
በ120 ሐረግ : በ4 ዓምድ ተጽፏል:: ያንንም ወስደው
በመቃብራት አካባቢ ቢያስቀምጡት 211 ሰዎች ከሞት
ተነስተዋል::

+"ማን አስነሳችሁ?" ሲባሉም "አምላከ ጻድቃን ወሰማዕት
: ወአምላከ ሳሙኤል ጻድቅ" ሲሉ መስክረዋል:: ይህን
ወንጌል ሲጽፉም ቅዱሳን መላእክት ረድተዋቸዋል::
+ጻድቁ አባ ሳሙኤል ዘቆየጻ ከብዙ ድካምና ተጋድሎ
በሁዋላ እዚያው በገዳማቸው ዐርፈዋል::
መቃብራቸውንም 5 አናምርት (5 ነብሮች) ቆፍረውላቸው
ተቀብረዋል::
(ስዕሉ የአባ ሳሙኤል ዘቆየጻ ነው)

=>አምላከ ቅዱሳን ከጻድቁ በረከት ይክፈለን::

=>+"+ በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው:: የኃጥአንን አፍ
ግን ግፍ ይከድነዋል:: የጻድቅ መታሠቢያ ለበረከት ነው::
+"+ (ምሳ. 10:7)

=>+"+ እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና::
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል. . .
ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::
በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::
የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም:: +"+ (መዝ. 36:28-31)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
#ክብረ_እመቤታችን_ድንግል_በክልዔ_ንጽሕተ_ንጹሐን_ቅድስተ_ቅዱሳን_ድንግል_ማርያም
እግዚአብሔር ዘላለማዊ ኃይሉንና አምላክነቱን ለዓለም ከገለጸበት ታላቅ ሥራ መካከል በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም የገለጸው ድንቅ ሥራው በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛል፡፡ ይህንን ኹኔታ ድንግል ማርያም ‹‹ብርቱ የኾነ እርሱ ታላቅ ሥራን በእኔ አድርጓል፤ ስለዚህም ፍጥረት ኹሉ ያመሰግኑኛል›› /ሉቃ.፩፥፵፱/ በማለት ገለጸችው፡፡
ቅድስት ኤልሳቤጥም ‹‹የጌታዬ እናት›› አለቻት /ሉቃ.፩፥፵፫/፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ‹‹ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ›› አላት /ሉቃ.፩፥፳፰/፡፡ ቅዱስ ዳዊት ደግሞ ‹‹ልጄ›› ይላታል /መዝ.፵፬፥፱/፡፡ ሰሎሞንም ‹‹እኅቴ›› ይላታል /መኃ.፭፥፩/፡፡ ለወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስም እናት ኾና ተሰጥታዋለች /ዮሐ.፲፱፥፳፮/፡፡ ይህን ድንቅ ምሥጢር ውስንና ደካማ የኾነ አእምሮ ሊገነዘበው ከሚችለው በላይ ነው፡፡
ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች በጻፈው መልእክቱ እንደገለጸው ‹‹የቅድስት ማርያም ዘለዓለማዊ ድንግልና፤ አማኑኤልን መውለዷና የማይሞተው ጌታ መሞቱ›› እነዚህ ሦስቱ ከዚህ ዓለም ጥበበኞችና ገዢዎች የተሰወሩ ምሥጢራት ናቸው፡፡ ቅዱስ አግናጥዮስ ‹‹እነዚህ ድንቅ ምሥጢራት በራሳቸው ከንግግርና ከቋንቋዎች ኹሉ በላይ ኾነው የሚነገሩ በእግዚአብሔር የዝምታ መጐናጸፊያ የተጠቀለሉ ድብቅና ጣፋጭ ምሥጢሮች ናቸው›› ይላል፡፡
የእመቤታችን ምስጋናዋ የበዛለት ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊም ‹‹አቤቱ መሰንቆ ልቡናዬን አነቃቃ፤ የልቤንም እንዚራ፡፡ ድምፁን ከፍ አድርጎ የዳዊት ልጅ የኾነችውን፣ የጌታውን እናት ድንግል ማርያምን ያመሰግናት ዘንድ፤ ለዓለም ሕይወት የሚሰጠውን የወለደች እናቱ የኾነች እርሷን ከፍ ከፍ ያደርጋት ዘንድ›› ብሏል፡፡ በሌላም አንቀጽ ደግሞ ‹‹ከሕሊናት ኹሉ በላይ ለኾነ ለዚህ ነገር አንክሮ ይገባል፡፡ ምድራዊት ሴት ፈጣሪዋን ወለደችው፤ እርሱም እናቱን ፈጠረ›› አለ፡፡ ስለእነዚህ ነገሮች ኹሉ ምን ማለትን እንችላለን? እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስለ ድንግል ማርያም ያልተናገረበት ጊዜ፤ ያላናገረው ቅዱስ እንደሌለ እንመለከታለን፡፡
‹‹በእግዚአብሔር፣ በመላእክትና በሰው ፊት የከበረ ሰው መታሰቢያው ለዘለዓለም ነው፡፡ በቤቱ በቅጥሩ የማይጠፋ የዘለዓለም ስምን ይቀበላልና›› /ኢሳ.፶፭፥፫/፡፡ ይህንን ታላቅ በረከት እንደሚሰጣቸው የተናገረው የማይዋሸው ቅዱስ እግዚአብሔር ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ወልድ እናት ከድንግል ማርያም የበለጠ በሰውና በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ማንን ልንጠራ እንችላለን? እንደ እርሷስ ሊታሰብ፣ ሊከበርም የሚችል በቅድስና ሕይወት ያለፈ ማን ይኖራል?
ቅዱስ እግዚአብሔር ፍጥረቱንና ዓለሙን ለማዳን የወሰነው ጊዜ በደረሰ ጊዜ ከድንግል ማርያም በድንግልና ተወለደ፡፡ አስቀድሞ በመልአኩ አፍ እንዳናገረ ክብሩ በእርሷ ላይ ታየ /ኢሳ.፷፥፪/፡፡ ማኅፀኗን ከተማ አድርጎ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በእርስዋ አደረ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በእመቤታችን ላይ የማደሩ ምሥጢር ያነጻቸው፤ ይቀድሳቸው፤ በሥጋም በነፍስም መርቶ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ያገባቸው ዘንድ በነቢያት፣ በሐዋርያት ላይ እንዳደረው ዓይነት አይደለም፡፡ ከሦስቱ አካል አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ (ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ) ከሥጋዋ ሥጋን፣ ከነፍስዋ ነፍስን ነስቶ ፍጹም ሰው፣ ፍጹም አምላክ ኾነ እንጂ፡፡ ቅዱስ ሉቃስ ይህን ዘለዓለማዊ እውነት ‹‹መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑል ኃይልም ይጸልልሻል፡፡ ስለዚህ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል›› በማለት ገልጾታል /ሉቃ.፩፥፵፭/፡፡
ኢትዮጵያዊው ሊቅ ደራሲና ገጣሚ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም ‹‹የእስራኤል ንጉሥ በእስራኤል ልጅ አደረ፤ የዳዊት አምላክ ከዳዊት ልጅ ሥጋን ለበሰ፡፡ የዕብራውያን ጌታ በዕብራውያን ልጅ ማኅፀን ተወሰነ፡፡ ለአብርሃም የዕብራይስጥ ልሳን ያስተማረው ከቀድሞም ያልሰማውን ልሳን እንዲናገር አፉን ጆሮውን የከፈተለት ከዕብራዊት ድንግል ተወለደ፤ በድንግልና ወተት ጥቂት ጥቂት እያለ አደገ፡፡ የሕፃናትን ሥርዓት እንዳያጎድል አፉን የሚፈታባት ዘመን እስኪፈጸም ጥቂት ጥቂት እያለ በዕብራይስጥ ልሳን ሲናገር ኖረ፡፡ ለሙሴ በዕብራይስጥ ልሳን በጣቶቹ የተጻፉትን ዐሠርቱ ቃላትን የሰጠ የዕብራይስጥ ፊደል ለመማር ከመምህር እግር በታች ተቀመጠ፡፡ የባቢሎን አውራጃ በምትኾን ሰናዖርም የፍጥረትን ሁሉ ቋንቋ የበተነ እርሱ የአሕዛብን ቋንቋ እንደማያውቅ ኹሉ እናቱ አፍ በፈታችበት ልሳን በዕብራይስጥ ልሳን ሲናገር ኖረ፡፡ ጆሮ ይህንን ነገር ከመስማት የተነሣ የሚለመልምበት ይህ ነገር ዕፁብ ድንቅ ነው፡፡ ለዚህ አንክሮ ይገባል›› አለ፡፡ ይህ በሰው ጥበብ በብራናና በቀለም የተጻፈ እውነት ሳይኾን ለድኅነት በተጠሩ ሰዎች ሁሉ ልቡና በአምላክ ጥበብ የተጻፈ እውነት ነው፡፡
የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከት ይደርብን፤ የልጇ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክረስቶስ ጸጋ ይብዛልን፡፡
✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር
✞✞ ወለወላዲቱ ድንግል
✞✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን 🙏🙏🙏
+ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑሻል +

የመላእክት አንድነት ኹሉ ያመሰግኑሻል በንፅህና ሥርዓት እነርሱን ትመስያለሽና።

የነቢያት አንድነት ያመሰግኑሻል ተስፋ ትንቢታቸው እውን ሆኖ በአንቺ ተፈፅሟልና።

የሐዋርያት አንድነት ሁሉ ያመሰግኑሻል የተወደደው ልጅሽ ወንድሞች አድርጓቸዋልና።

ድለ መልካሞች ሰማዕታት ያመሰግኑሻል የልጅሽ
መከራ አንድነት በሥጋቸው ተሸክመዋልና

ደናግልና መነኮሳት ያመሰግኑሻል ሕይወታቸውን ለንፅሕናሽ ምሳሌ ብፅዕት አድርገዋልና።

ሊቀ ጳጳሳትና ኢጲስ ቆጶሳት ያመሰግኑሻል ለማዕረገ
ክህነታቸው ልጅሽ አለቃ ሆኗልና።

አንባቢዎችና መዘምራን ያመሰግኑሻል ልጅሽን ለማመስገን እንደ ወርቅ ጸናጽሎች በቤተ መቅደስ ይጮኻሉና።

የክርስቲያን አንድነት ኹላቸው ያመሰግኑሻል ከልጅሽ
ጎን በፈሰሰው ውሃ የጥምቀት መጎናጸፊያን ለብሰዋልና።

(አርጋኖን - ሊቁ አባ ጊዮርጊስ)
++ እመቤታችን በቅዱስ ኤፍሬም ++

" ጌታ ሆይ አንተን ምን ብሎ መጥራት እንዳለበት የሚያውቅ ሰው ማን ነው? ጌታ ሆይ እናትህን ድንግል ብለን እንጥራትን? እንዲያ ብለን እንዳንጠራት የአንተ እናት መሆኑዋ ምስክር ይሆንብናል፤ ጌታ ሆይ እናት እንበላትን? እንዲህ እንዳንል ወንድ የማታውቅ ድንግል ናት፤ የእናትህ ነገር ለመረዳት የረቀቀ ከሆነ አንተን ሊረዳ የሚችል ሰው ማን ነው? ሁሉን በቀላሉ የምታከናውን የሁሉ አስገኝ የሆንክ ክብር ምስጋና ለአንተ ይሁን፡፡

እርሷ ብቻ ያንተ እናት ናት፤ ከሁሉ ጋር ደግሞ እኅትህም ናት፤ ስለዚህም እርሷ ለአንተ እናትም፣ እኅትም፣ ሙሽራም ሆናለች። እንደ ሌሎች ቅዱሳኖችህ፤ የእናትህን ደም ግባት ገንዘብህ
ያደረግህ አንተ እርሱዋን በበረከት ሁሉ አስጌጥኻት፡፡

አንተ ወደ እርሷ ከመምጣትህ በፊት ቅድስት ድንግል ማርያም በልማዳዊ መንገድ ይጠብቃት ዘንድ ለዮሴፍ ተሰጠች፤ አንተ ወደ እርሱዋ ከመጣህ በኋላ ግን ከተፈጥሯዊ ሥርዓት ውጪ አንተን በድንግልና ፀነሰችህ፤ አንተ ብቻ ቅዱስ የሆንክ ጌታ ሆይ እርሷ አንተን ቅዱስ በሆነ ልደት በድንግልና ወለደችህ፤ ጌታ ሆይ ቅድስት እናትህ ድንግል ሳለች አንተን ፀንሳ በመውለድ እናትህነትን ገንዘቧ አደረገች።

ድንግል ሆና ሳለች ከጡቶቿ ወተት ፈሰሰ፤ ድንግል ከሆነች መሬት ንጹሕ ምንጭ እንዲፈልቅ፤ እንዲሁ ድንግል ከሆነችው እናትህ ጡቶች ወተት ፈለቀ፡፡ እርሱዋ አንተን ብትሸከምህ አንተ ጽንዕ ሰጥተሃት ነው፤ በተራብክ ጊዜ አንተን ከጡቶቿ ትመግብህ ዘንድ፣ ነቢዩ ዳንኤል በታላቅ ተራራ የመሰለህ አንተን አንደ ሕፃናት ታቀፈችህ። በፈቃድህ የተጠማህ አንተን በእጆቹዋ በፍቅር ትዳብስህ ዘንድ፤ የምህረት እሳት የሆንኽ አንተ ክንዶቿን መለኮታዊው እሳት እንዳያቃጥላቸው ጠበቅኻቸው፡፡

ጌታ ሆይ እናትህ ግሩም የሆኑ ተአምራት የተፈጸሙበት መካን ናት፤
ከዚህ ቻናል leave ከማለት
የሚስተካከል ነገር አለ ብላችሁ ብትጠይቁ የተሻለ ይመስለኛል
ለዚህም ነው በዚህ ቻናል
ጥሩ ጎንም ሆነ መጥፎ
@asrategabriel
ወይም
@yita21
ላይ አድርሱን እንላለን
እናመሰግናለን። 🙏🙏🙏🙏
#ነገረ_ማርያም


💓💓💓💓💓💓💓💓💓💓💓💓💓💓💓
#ርዕሱን ወደተመለከተው ወደ ዋናው ትምህርት ከመግባታች አስቀድሞ የርዕሱን ትርጉም ማወቅ ይቀድማልና ነገረ ማርያም የሚለውን ትርጉም እናያለን። ነገረ ማርያም ማለት የእመቤታችንን ነገር (ስለ እመቤታችን) የሚያወሳ ነገር ወይም ትምህርት ማለት ነው። ይህም አስቀድማ በአምላክ ሕሊና መታሰቧን፣ ትንቢት የተነገረላት፣ ምሳሌ የተመሰለላት መሆኗን ልደቷን፣ እድገቷን፣ አምላክን ፀንሳ መውለዷን ዕረፍቷን ትንሣኤዋን ወዘተ የሚተርክ የሚያስተምር ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማርያም በሚል ስም የሚጠሩ ብ ሴቶች አሉ። እነዚህም በብሉይና በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ላ ተጠቅሰው ይገኛሉ። እነርሱም፡-
1ኛ. #የሙሴ_እህት_ማርያም፡- ይህች ማርያም ሙሴ በወንዝ ዳ በተጣለ ጊዜ በእርሱ ላይ የሚሆነውን ነገር ስትከታተል ነበር ዘፀ.2፥4-8
– እስራኤል ባሕረ ኤርትራን ሲሻገሩ ከበሮ በመያዝ በመዝሙ እግዚአብሔርን አመስግናለች። ዘፀ. 15፥20-22
2ኛ. የዕዝራ የልጅ ልጅ (የዬቴር ልጅ) ማርያም 1ኛ. ዜና. 4፥17
3ኛ. #የማርታና_የአልዓዛር_እኅት_ማርያም ዮሐ. 11፥1
– ክርስቶስ ወደ ቤታቸው እየሄደ ይጎበኛቸው ያስተምራቸው ነበር።
– ቃሉን ለመስማት ትተጋ ስለነበር ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አመስግኗታል። ሉቃ. 10፥39-42
-ጌታን ሽቱ ቀባችው እግሩንም በጠጉርዋ አበሰችው። ዮሐ. 11፥2፣ ዮሐ.12፥1-8
4ኛ. #መግደላዊት_ማርያም
– ክርስቶስ ሰባት አጋንንትን አወጣላት። ሉቃ. 8፥2
– ከትንሣኤው በኋላ በአትክልት ቦታ ለእርሷ ለብቻዋ ታያት ተገለጠላት። ዮሐ. 20፥1-8
5ኛ. #የታናሹ_የያዕቆብና_የዮሳ_እናት_ማርያም ማር. 15፥40
6ኛ. #የቀለዮጳ_ሚስት_ማርያም- ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ከመስቀሉ አጠገብ ቆማ ነበር። ዮሐ. 19፥25
7ኛ. #የማርቆስ_እናት_ማርያም ሐዋ. 12፥12
8ኛ. #የኢየሱስ_ክርስቶስ_እናት_ቅድስት_ድንግል_ማርያም
ከላይ የተዘረዘሩት ማርያም በሚል ስም የተጠሩ ሴቶች እንዳሉ ለማመልከት እንጂ ስለ ሁሉም ለመተረክ ተፈልጎ አይደለም ከዚህ በኋላ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ስለወለደ ስለቅድስት ድንግል ማርያም እንፅፋለን።
ሀ) #የእመቤታችን_መወለድ (ልደታ ለማርያም)
የወደቀው ሰው ከውድቀቱ ይነሳ፣ ከርኩሰቱ ይቀደስ ዘን አምላክ ከእርሷ እንዲወለድ የወላዲተ አምላክ የአማናዊው ፀሐይ የክርስቶስ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ግድ ነበር። ስለዚህም ነው “እግዝእትነ ማርያም ነበረ እምቅድመ ዓለም በሕሊና አምላክ” (እመቤታችን ማርያም ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር) የተባለው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ እንደምናገኘው ብዙ ሰዎች ልጅ በማጣት አዝነው እግዚአብሔርን ፀንተው በመለመን ልጅ ያው ታላላቅ ልጆችን እንዳገኙ እናነባለን። እንዲያውም አንዳንዶ ካረጁና የመውለጃ ጊዜአቸው ከተላለፋቸው በኋላ ነው ልጅ የሚያገኙት። የሳራና የአብርሃም፣ የኤልሳቤጥና የካህኑ ዘካርያስ የሐና እና የሕልቃና ወዘተ. ታሪክ ለዚህ ማስረጃ ይሆነናል። ዘፍ. 21፥1-8፣ ሉቃ. 1፥8-23፣ ሉቃ. 1፥57-67፣ 1ኛ ሳሙ. 1፥1-21። የእመቤታችን እናት ሐና እና አባቷ ኢያቄም ከላ እንዳየናቸው ሁሉ መካን ሆነው ይኖሩ ነበር። በኋላ ግን ለሳራ አብርሃም ይስሐቅን፣ ለኤልሳቤጥና ዘካርያስ መጥምቀ መለኮ ዮሐንስን፣ ለሐና እና ለሕልቃና ሳሙኤልን የሰጣቸው እግዚአብሔር ለሐና እና ለኢያቄምም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ሰጣቸው።
እመቤታችን ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች። ገና በማሕፀን ሳለች አንድ ዓይነ ስውር ዘመዷ ኤልሳቤጥ ፀነሰች ቢሏት ዳስ ካላረጋገጥኩ አላምንም ብላ የሐናን ሆድ ነክታ መፅነሷ ስታረጋግጥ በአድናቆት እጇን ዓይኗ ላይ ብታደርገው በሐ ማሕፀን ያለችው የአምላክ እናት ናትና የዓይነ ስውሯ ዓይ በራላት። የሞተ ሰው ይዘው ሲሄዱ የሐና ጥላ በሙቱ ላይ ሲያር የሞተው ሰው ተነስቷል። ከዚህ በኋላ ግንቦት 1 ቀን በሊባኖስ ተራራ ተወለደች። የእመቤታችን የዘር ሐረግ በአባቷ ከነገ ይሁዳ በእናቷ ደግሞ ከነገደ አሮን ነው።
ለ) #እመቤታችን_ወደ_ቤተ_መቅደስ_መግባት (በአ ለማርያም)
በአታ ለማርያም ማለት የማርያም ወደ ቤተ መቅደስ መግባ ማለት ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእናት ከአባቷ ጋር አብራ የኖረችው ለሦስት ዓመታት ብቻ ነው የብፅዓት ልጅ ናትና ሦስት ዓመት ሲሆናት እናትና አቧ በስእለታቸው መሠረት ለእግዚአብሔር ቤት ለመስጠት ወ ቤተመቅደስ ወሰዷት። በጊዜው የነበረው ሊቀ ካህን ዘካርያስ ነበርና ወደ ዘካርያስ አቀረቧት። እርሱም ምን እንደሚያደርግ ግ ገብቶት ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ፋኑኤል ፅዋ ሰማያዊ ኅብስት ሰማያዊ ይዞ ወረደ። ዘካርያስ፣ ካህና ኢያቄምና ሐና ወደ መልአኩ ቢቀርቡ እርሱ ግን ራቃቸ የመጣው ለእነርሱ አይደለምና። እመቤታችንን ብቻዋን ሲተዋት ግን መልአኩ ወርዶ በክንፎቹ ጋርዶ መግቧት አርጓል። ዘካርያስ የሆነውን ሁሉ አይቶ ፈቃደ እግዚአበሔር መሆኑን ተረድቶ ከቤተ መቅደስ አስገብቷታል።
እመቤታችን በቤተመቅደስ የኖረችው ለአሥራ ሁለት ዓመ ሲሆን ከዚህ በኋላ አይሁድ ቤተመቅደሳችንን ታረክሳለች ትውጣ ብለው ቢያምፁ ዘካርያስ አይሁድ እንዲህ አሉ ም ላድርግ አላት። እመቤታችንም እኔ ምን አውቃለሁ አለችው። ወ እግዚአብሔር ቢያመለክት ከነገደ ይሁዳ ሚስቶቻቸ የሞቱባቸውን ወንዶች በትር ሰብስበህ ከቤተመቅደስ አስገብተህ ጸልይበት እኔም ምልክት እሰጥሀለሁ አለው ዘካርያስም እንደተባለው በትር ላይ “ዮሴፍ ሆይ ማርያምን ጠብቃት” የሚል ምልክት ሰጠው ዕጣ ቢጣል ለዮሴፍ ወ ርግብም በዮሴፍ ራስ ላይ አረፈች። በእነዚህ ሁሉ ምልክቶች ተረድቶ ካህኑ ዘካርያስ እመቤታችንን ለዮሴፍ ሰጣት። ይህ ሁ የሆነው በጥበበ እግዚአብሔር ነው። በብሉይ ኪዳን ህግ አንዲ ሴት ያለ ባል የፀነሰች እንደሆነ በድንጋይ ተወግራ በእሳት ተቃጥላ ትገደል ነበርና እመቤታችን ይህ ሞት እንዳያገኛት በእጮኛ ስም ለዮሴፍ ተሰጠች። እመቤታችን በሄሮድ ምክንያት የሚደርስባት ስደትና መከራ አለና ረዳቷና ጠባቂ እንዲሆን ለዮሴፍ በእጮኝነት ስም ተሰጠች። ኃይል አርያማዊት አለመሆኗ ከአዳም ዘር የተገኘች ሰው መሆኗ ይገለጥ ይታወቅ ዘንድ ለዮሴፍ በእጮኝነት ስም ተሰጠች።
ሐ) #አምላክን_መውለዷ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለማሕደረ ሥሉስ ቅዱስ አስቀድማ ተመርጣለችና እግዚአብሔር አብ ለአፅንኦ (ለማፅናት እግዚአብሔር ወልድ ለተሰብኦ (ሰው ለመሆን) እግዚአብሔ መንፈስ ቅዱስ ለአንፅሖ (ሊያነፃት) አድረውባታል። በተለ እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆነ ረቂቁ መለኮት ግዙፉን ሥጋ ተዋሐደ አምላክ ሰ ሰውም አምላካ ሆነ። እመቤታችን ደግሞ ይህ ታላቅ ምስጢ የተከናወነባት ሙዳየ ምሥጢር ሆነች። ይህ ምሥጢር በእመቤታችን ማሕፀን ሲከወን በፍፁም ድንግልና ነው። ይህ ማለት እመቤታችን ከመፅሷ በፊት፣ በፀነሰችም ጊዜ፣ ከፀነሰችም በኋላ እንዲሁም ከመውለዷ በፊት በወለደችም ጊዜ ከወለደችም በኋላ “ወትረ ድንግል” ሁሌም ፍፁም ድንግል ናት። ሕዝ.44፥1-4፣ ኢሳ.7፥14።
✥ ሰምተን ያልተገበርነው ትምህርት

አባ በምዋ (Abba Bemwa) ዓለምን ትቶ ወደ በረሃ በሄደ ጊዜ፣ ለዚህ አዲስ ሕይወቱ የሚጠቅመውን ምክር ይሰጡት ዘንድ ወደ አንድ ቅዱስ አረጋዊ ቀርቦ "ምን ላድርግ" ሲል ጠየቃቸው። እኒህም አረጋዊ ንግግራቸውን የጀመሩት "በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ" በሚለው በቅዱስ ዳዊት የመዝሙር ቃል ነበር። (መዝ 39፥1) አባ በምዋም ይህንን የመጽሐፍ ቃል በሰማ ጊዜ "ይበቃል አባቴ፣ ይህን ተምሬ እስክፈጽም ድረስ ሌላ ምንም አዲስ ትምህርት አይንገሩኝ" በማለት ወደ በዓቱ ሄደ።

ከዚያም ቀን ጀምሮ ለብዙ ጊዜያት ወደ አረጋዊው አልተመለሰም ነበር። ከዕለታት በአንዱ ቀን አረጋዊው ጻድቅ አባ በምዋን አግኝተው ለምን ለሌላ ተጨማሪ ትምህርት መልሶ ወደ እርሳቸው እንዳልመጣ ጠየቁት። እርሱም "እመኑኝ አባቴ፣ ገና የመጀመሪያውን ትምህርት በሚገባ አልተማርኹትም" ሲል መለሰላቸው። ከረጅም ዓመታትም በኋላ ወዳጁ የሆነ አንድ መነኩሴ የሰማውን የነቢዩ የዳዊትን ቃል እስከ አሁን አጥንቶ ጨርሶ እንደሆነ አባ በምዋን ጠየቀው። ቅዱሱም "በዚህ የነቢዩ ቃል ላይ ለማሰላሰል እና በሚገባ ወደ ተግባር ለመቀየር አርባ አምስት ዓመታት ወስዶብኛል" ሲል በትሕትና መለሰለት። የአባ በምዋን ታሪክ የጻፈልን ቅዱስ ጰላድዮስ እንደሚናገረው አባ በምዋ በሕይወቱ ሁሉ ፍጽምት የሆነች የዝምታን ሕይወት የመራ ሲሆን፣ በሞቱም ጊዜ "ምነው ይህን ባልተናገርኩ" የሚል አንድም የሕሊና ወቀሳ ሳያገኘው በሰላም አርፏል።

ቅዱስ እንጦንስም በአንድ ወቅት ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ሲል መክሯቸው ነበር ፦ "ዝም በሉ፤ ዝምተኛን ሰው እግዚአብሔር በፊቱ ካሉት ሠራዊተ መላእክት እንደ አንዱ ይቆጠረዋልና"

ስለዚህ ከመላእክት ጋር እንቆጠር ዘንድ አብረን ዝም እንበል!
ዛሬ ሰሙነ ሕማማት

ዕለታት ስያሜዎች ጌታችን የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግስቱ ከቢታንያ ሲወጣ ተራበ፤ በመንገድም ሲያልፍ ቅጠል ያላት በለስን ከሩቁ ተመለከተ፡፡ ወደ በለሲቱም በቀረበ ጊዜ ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ያንጊዜም ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ለዘለዓለም ከአንቺ ፍሬ የሚበላ አይኑር›› ሲል በለሲቱን ረገማት፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ይህንን ሰሙት፡፡ በዚህም ምክንያት ይህች ዕለት በለሲቱ የተረገመችባት ቀን ናትና መርገመ በለስ ተብላ ትጠራለች፡፡ (ማር.፲፩፥፲፩-፲፬)
በዚህ አገላለጽ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ስትሆን ፍሬ የተባለ ደግሞ ሃይማኖትና ምግባር ነው፡፡ መድኃኒታችን ክርስቶስ ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈልጎ አላገኘባቸውም፡፡ እስራኤል፦ ሕዝበ እግዚአብሔር፣ የአብርሃም ዘር መባልን እንጂ የአብርሃምን ሥራ በመሥራት በምግባር በሃይማኖት ጸንተው መኖር አይፈልጉምና ደግ ሰው አልተገኘባቸውም፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በለስ የተባለች ኦሪት ናት፡፡ ኦሪት በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛትም አማናዊ ድኅነትን የምታሰጥ ሆና አላገኛትም፡፡ ይሁን እንጂ በእርሷ ድኅነት ባይገኝባትም ‹‹ኦሪትና ነቢያትን ከመፈጸም በቀር ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ›› በማለት ሕገ ኦሪትን ፈጽሟታል፡፡ ከዚህም ባሻገር በለስ የተባለች ኃጢአት ናት፡፡ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አግኝቷታል፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሠሩት ለጊዜው ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም በአ
✞እንዴት እንዲያጠፉት✞
♡የመዝሙር ግጥሞች♡
✞ እንዴት እንዲያጠፉት ✞

እንዴት እንዲያጠፉት ካህናት መከሩ
ያመነቱ ነበር ሕዝብን እየፈሩ
ሰይጣን በይሁዳ ገብቶ ነበርና
አሳልፎ እንዲሰጥ ልቦናውም ጸና

ከመቅደስ አዛዦች ከካህናት ጋራ
ስለጌታ መሞት ባንድ ላይ አወራ
ካህናት በደስታ ይሁዳን አቀፉት
አምላኩን እንዲያሲዝ ሰላሳ ብር ሰጡት
አዝ
ሕዝብ በሌለበት በአሳቻ ስፍራ
ጌታን እንዲያሲዘው አደረገ ሴራ
ኧረ እንዴት ጨከነ ይሁዳ አንጀትህ
ጌታን ያስገደልከው እንደዚያ ሲወድህ
አዝ
በረከቱን ከጅህ ሥልጣኑን በራስህ
ሊሰጥህ አስቦ ኢየሱስ ሊያከብርህ
ሰማየዊ ሀብትን ሰማያዊ ፀጋ
አድሎህ ነበረ አልፋና ኦሜጋ
አዝ
የቃየል መሰዋዕት የኤሳው ብኩርና
ጌታውን የሚሸጥ ከፍጡር ሆነና
በሰላሳ ዲናር በሚጠፋው ብዕል
እንዲህ ያለ ጌታ ኧረ እንዴት ይከዳል

ግእዝን ለመማር


╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@embtee
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
Audio
ሰሞነ ሕማማት ምንድነው
የጥያቄ መልሶች በዝርዝር

በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ
ገብሩ ለቅዱስዳዊት ንጉሠ እስራኤል

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር።
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@embtee
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
🌻💐💐💐🌻🌻💓💓
🌺 🌷 እንኳን 🌼🌼🌼
🌸🌹 ለትንሣኤ 🌸🌺🌸
🌹🌺 በሰላም 🌷 🌺🌻
🌹🌷አደረሳችሁ🌷🌹🌻
🌻🌾🌾🌾🌻🌻💓💓
እንኳን አደረሳችሁ
+++ ‹‹ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል›› መዝ 92፥12 +++

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተሰጋግሞ የመነሣት እድል ካገኙ እጽዋት መካከል አንዱ የዘንባባ ተክል ነው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤት ከሠራ በኋላ በመቅደሱ የውስጥ ግንቦች ላይ ከቀረጻቸው ምስሎች ውስጥ አንዱ የዘንባባን ቅጠል ነው፡፡(1ኛ ነገ 6፡29) በእስራኤላውያን ታሪክም ድል ሲቀናቸውና ሲደሰቱ በእጃቸው የሚገኘው እጽ ይኸው ዘንባባ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች የአንድ አገር መለያ አድርገው ከሚጠቅሷቸው ምልክቶች ውስጥ ‹‹የዘንባባ ዛፍ›› አንደኛው ነው፡፡(ዘዳ 34፡3) ከዚህ ሁሉ ደግሞ በጣም የሚያስደንቀው የሐዲስ ኪዳኑ ባለ ራእይ ቅዱስ ዮሐንስ እንደ ጻፈው ሩጫቸውን በድል የጨረሱና ነጭ የለበሱ የጻድቃን ነፍሳት ‹‹የዘንባባን ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት›› መቆማቸው ነው፡፡(ራእይ 7፡19) ዘንባባ በምድር ላለ ደስታ ብቻ ሳይሆን በሰማይም ላለ የድል ነሺነትና የአሸናፊት መንፈስ መግለጫ ምልክት ሆኖ ያገለግላል፡፡

ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ጻድቃንን ለምን በዘንባባ ዛፍ ይመስላቸዋል? መዝሙረኛውስ ‹ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል› ሲል ለምን ዘመረ? ቅዱሳንን ከዘንባባ ጋር ምን አገናኛቸው?

ሁላችንም እንደምናውቀው ጣፋጭ ፍሬ ከሚሰጡ እጸዋት መካከል አንዱ ዘንባባ ነው፡፡ የዘንባባን ዛፍ ለየት የሚያደርገው ጣፋጭ ፍሬ መስጠቱ ብቻ ሳይሆን ሥሮቹ በጣም ጠንካራ እና ወደ ታች ጠልቀው የሚገቡ (የሚሰዱ) መሆናቸው ነው፡፡ ጸድቃንም እንደ ዘንባባ ፍሬ የሚጥም በጎ ምግባርን የተሸከሙ የሃይማኖት ተክል ሲሆኑ፣ የታነጹበትና የቆሙበት የእምነትና የፍቅር ሥሮችም በጣም የጸኑ እና ጥልቆች ናቸው፡፡

ሌላው የዘንባባ ዛፍ በየትኛውም ጊዜ ቢተከል ሊያፈራ የሚችልና በበረሃ የሚበቅል ልዩ ተክል ነው። ቅዱሳንም በጊዜውም ሆነ ያለ ጊዜው ጸንተው ይገኛሉ። በበረሃም እንደሚጸድቅ ዘንባባ በዚህች ክፋት በሞላባት ዓለም ውስጥ እየኖሩ በቅድስና ይገኛሉ።

የዘንባባ ዛፍ ልክ እንደ ሌሎች እጸዋት ብዙ ቅርንጫፎች የሉትም፡፡ በዚህም ምክንያት እንስሳት ፍሬው ወደሚገኝበት የዛፉ ጫፍ በቀላሉ ለመውጣትና ለመብላት ይቸገራሉ፡፡ እንዲሁ ጻድቃንም በጎ ሥራዎቻቸውንና መንፈሳዊ ደስታቸውን ከእነርሱ እንዲወስዱባቸው ለአጋንንት መግቢያ በር፣ መውጫ ቅርንጭፍ አያኖሩም፡፡ ሐሴቶቻቸውም ከፍ ያሉ ሰማያውያን በመሆናቸው ምድር ምድሩን የሚሄደው ሰይጣን በቀላሉ ሊተናኮላቸውና ደስታቸውን ሊያጠፋ አይችልም፡፡

ዘንባባ ብዙ ቅርንጫፎች የሌለው መሆኑ አንዳንዴ ድንጋይ እንዲወረወርበት እና በዱላ እንዲመታ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ እርሱ ግን ‹‹ይቅር ባይ›› ተክል ነው፡፡ በተወረወረበት ድንጋይ እና ባረፈበት ዱላ ፈንታ የሚመልሰው ጣፋጭ ፍሬውን ነው፡፡ አንተ ድንጋይ ስትወረውርበት እርሱ ደግሞ እንደ ማር የሚጣፍጠውን ፍሬ ያዘንብልሃል፡፡ ሰይጣን ለእርሱ መግቢያ ምክንያት የማይሰጡትን ጻድቃን የሚፈትነው ለክፉ ዓላማው ማስፈጸሚያ የሚያደርጋቸውን ሰዎች በመጠቀም ነው፡፡ በእነዚህም ሰዎች አማካኝነት ብዙ የስድብ፣ የጥላቻና የስም ማጥፋት ድንጋዮችን ይወረውርባቸዋል፡፡ በበቀል ዱላ ሊያቆስላቸው ይሰነዝርባቸዋል፡፡ እነርሱ ግን የሰደቧቸውን ሰዎች በመመረቅ፣ የጠላቸውን በመውደድ፣ ለበቀል ስለሚያሳድዷቸው ሰዎችም በመጸለይ ጣፋጭ ፍሬዎቻቸውን ያዘንቡላቸዋል፡፡

በሆሳዕና ዘንባባ ይዘን ዘምረን፣ እንደ ዘንባባ ዛፍ አፍርተን፣ በኋላም ከጻድቃኑ ጋር ነጭ ለብሰንና በእጆቻችን የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘን ከበጉ ፊት ለመቆም ያብቃን!

=== ልክ እንደ ጻድቃኑ የዘንባባ ሕይወት ይስጠን!!! ===

እባካችሁ leave ከምትሉ አስተያየት በ @asrategabriel ላይ አድርሱን።
✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞ pinned «Watch "🛑ምስክርነት ||Misekirenat|| Ethiopian ortodox tewahido|meron shewarega|"2013"" on YouTube https://youtu.be/iXCQ63Sfy-Y»