✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.06K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
​​የ"7" ቁጥር ምስጢራት"
= = =
➭ሰባት ቁጥር ጥልቅ ምሳሌና ትርጓሜ አለው።በዕብራውያን ዘንድ ሰባት ቁጥር ፍጹም ቁጥር ነው።

➭እግዚአብሔር ከሰኞ እስከ ዕሁድ ያሉትን ቀናት በሰባት ቁጥሮች ወስኗል።(መ.ምሳሌ 24፥16)

➭እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት ነጻ ወጥተው በሲና በረሃ ሲጓዙ ይመሩ የነበረው በሰባት ደመና ነበር።(ዘዳ 13፥21)

➭እስራኤላውያን ኢያሪኮን ለሰባት ተከታታይ ቀናቶች እንዲዞሯት፣በሰባተኛው ቀን ደግሞ ሰባት ጊዜ እንዲዞሯት ታዘው ነበር። (ኢያሱ 6፥15)

➭ጴጥሮስ ወንድሙን ይቅር እንዲለው የታዘዘው እስከ ሰባት ጊዜ ሰባ እንጂ ሰባት ጊዜ ብቻ አልነበረም።
(ማቴዎስ 18፥21, 22)

➭ሌላው የሰባት ቁጥር ምሳሌዎች በጥቂቱ እንደሚከተለው ይቀርባሉ።

ሰባቱ አባቶች
= = =
1. ሰማያዊ አባታችን እግዚአብሔር
2. የነፍስ አባት
3. ወላጅ አባት
4. የክርስትና አባት
5. የጡት አባት
6. የቆብ አባት
7. የቀለም አባት

ሰባቱ ዲያቆናት
= = =
1. ቅዱስ እስጢፋኖስ
2. ቅዱስ ፊልጶስ
3. ቅዱስ ጵሮክሮስ
4. ቅዱስ ጢሞና
5. ቅዱስ ኒቃሮና
6. ቅዱስ ጳርሜና
7. ቅዱስ ኒቆላዎስ

ሰባት የጌታ ቃላት(እኔ ነኝ)
= = =
1. የሕይወት እንጅራ እኔ ነኝ
2. የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ
3. እኔ የበጎች በር ነኝ
4. መልካም እረኛ እኔ ነኝ
5. ትነሣዔና ሕይወት እኔ ነኝ
6. እኔ መንገድና ሕይወት ነኝ
7. እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ

ሰባቱ ሰማያት
= = =
1. ጽርሐ አርያም
2. መንበረ መንግሥት
3. ሰማይ ውዱድ
4. ኢየሩሳሌም ሰማያዊት
5. ኢዮር
6. ራማ
7. ኤረር

ሰባቱ ሊቃነ መላእክት
= = =
1. ቅዱስ ሚካኤል
2. ቅዱስ ገብርኤል
3. ቅዱስ ሩፋኤል
4. ቅዱስ ራጉኤል
5. ቅዱስ ዑራኤል
6. ቅዱስ ፋኑኤል
7. ቅዱስ ሳቁኤል

ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት
= = =
1. የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን
2. የሰርምኔስ ቤተ ክርስቲያን
3. የጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን
4. የትያጥሮስ ቤተ ክርስቲያን
5. የሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን
6. የፊልድልፍልያ ቤተ ክርስቲያን
7. የሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን

ሰባቱ ተዐምራት
= = =
➭ጌታ የሰው ልጆችን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት፦
1. ፀሐይ ጨልሟል
2. ጨረቃ ደም ሆነ
3. ከዋክብት ረገፉ
4. ዐለቶች ተሠነጠቁ
5. መቃብራት ተከፈቱ
6. ሙታን ተነሡ
7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ

ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት
= = =
1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ
2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው
3. ዛሬ ከእኔ ጋራ በገነት ትሆናለህ
4. እነሆ ልጅሸ እናትህ እነሆት
5. ተጠማሁ
6. ተፈጸመ
7. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እስጥሃለሁ

ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን
= = =
1. ምሥጢረ ጥምቀት
2. ምሥጢረ ሜሮን
3. ምሥጢረ ቁርባን
4. ምሥጢረ ክህነት
5. ምሥጢረ ተክሊል
6. ምሥጢረ ንስሐ
7. ምሥጢረ ቀንዲል

ሰባቱ ዐበይት አጽዋማት
= = =
1. ዐቢይ ጾም
2. የሐዋርያት ጾም
3. የፍልሰታ ጾም
4. ጾመ ነቢያት
5. ጾመ ገሀድ
6. ጾመ ነነዌ
7. ጾመ ድኅነት

ሰባቱ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠሉ ነገሮች (ምሳ 16፥6-19)
= = =
1. ትዕቢተኛ ዓይን
2. ሃሰተኛ ምላስ
3. ንፁህን ደም የምታፈስ እጅ
4. ክፉ ሃሳብን የምታፈልቅ ልብ
5. ለክፋት የምትፈጥን እጅ
6. የሐሰት ምስክርነት
7. በወንድሞች መካከል ጠብን የምታፈራ ምላስ

ሰባቱ ፀሎት ጊዜያት
= = =
1. ነግህ የጠዋት ጸሎት
2. ሠለስት (የ3 ሰዓት ጸሎት)
3. ቀትር (የ6 ሰዓት ጸሎት)
4. ተሰአቱ (የ9 ሰዓት ጸሎት)
5. ሰርክ (የ11 ሰዓት ጸሎት)
6. ነዋም (የምኝታ ጸሎት)
7. መንፈቀ ሌሊት (የሌሊት ጸሎት)


ሰባቱ የዳዊት ሐብታት
= = =
1. ሐብተ ፈውስ
2. ሐብተ ትንቢት
3. ሐብተ በገና
4. ሐብተ መንግስት
5. ሐብተ መዊዕ
6. ሐብተ ኃይል
7. ሐብተ ክህነት

7 ቀናት፣7 ፊደላት፣7 ሰው የተፈጠረበት ባህርያት፣......
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🎬 ©አለምን የያዙት መዳፎቹ" ዘማሪ አብርሐም ያደታ | zemary abrham yadeta

👤 ኪነ ተዋህዶ ቲዩብ

⚠️ ዝማሬውን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/F26Nnc6DHyk
https://youtu.be/F26Nnc6DHyk
ውድ የተዋህዶ ልጆች እስቲ ዛሬ አንድ ነገር ላስቸግራቹ በፎቶው እንዳያቹች እናት ቤተክርስትያናችን በዩቱብ ተከታይ ያላትና መስቀል ከሚያስበጥሰው ebs ያለውን ልዩነት እዩት ያሳዝናል እውነት ebs ሰብስክራይብ አድርገን EOTC TV ካላደረግን በጣም ያሳዝናል

EOTC 21.8
EBS 1.05 ሚሊዮንንንን

አሁን ሁላችንም EOTC TV & ማህበረ.ቅዱሳን SEBSCRIBE እናድርግ

ለሌሎች ያጋሩ
@embtee
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🎬 ©ኑ ተመልከቱልኝ" ዘማሪት ሊዛ በየነ| zemarit Liza beyene

👤 ኪነ ተዋህዶ ቲዩብ

⚠️ ዝማሬውን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/KNnawxfZjc4
https://youtu.be/KNnawxfZjc4
🎬 ©ንስሀ" ሐና ዳኘው |Niseha| Hana dagnew

⭕️ሊደመጥ ሚገባ⭕️

👤 ኪነ ተዋህዶ ቲዩብ

⚠️ ለማዳመጥ ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!

https://youtu.be/QzrSmQi4Qp0
https://youtu.be/QzrSmQi4Qp0
🎬 ©ንስሀ" ሐና ዳኘው |Niseha| Hana dagnew

⭕️ሊደመጥ ሚገባ⭕️

👤 ኪነ ተዋህዶ ቲዩብ

⚠️ ለማዳመጥ ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!

https://youtu.be/QzrSmQi4Qp0
https://youtu.be/QzrSmQi4Qp0
ዐቢይ_ጾም

ጾም ማለት ሰውን ከምግብ መከልከል ነው፡፡ (ፍትሃ ነገስት አንቀፅ.15) “ጾምሰ ተከልኦተ ብዕሊ ዕምመብልዕ በጊዜ እውቅ” ጾም ማለት በታወቀው ዕለት በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ የሚከለከለው መከልከል ነው፡፡ መብል መጠጥ የኀጢአት መሠረት ነው በመብል ምክንያት ሞት በሰው ልጆች ላይ መጣ “ይችን ዕፀ በለስ ብትበሉ ሞትን ትሞታላችሁ” ዘፍጥረት 2፥17 ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መከልከል ለሰውነት የሚያምረውን የሚያስጐመዥውን ነገር መተው ማለት ነው። መብል መጠጥ ከልክ ሲያልፍ ከተዘወተረም ከእግዚአብሔር ይለያል፤ “ያዕቆብ በላ ጠገበ ወፈረ ገዘፈ ደነደነ ፈጣሪው እግዚአብሔርን ተወ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር ተለየ” ዘዳግም 32፥15-17 “የእግዚአብሔር መንግሥት መብልና መጠጥን አትሰብክም” ሮሜ 14፥16፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 8፥8-13 “ዛሬ የሚራቡ የሚጠሙ ብፁአን ናቸው ይጠግባሉና ማቴዎስ 5፥6 ጾም የሥጋ መቅጫ ነው፤ “ነፍሴን /ሰውነቴን/ በጾም ቀጣኋት መዝሙር 68፥10 ጾም በነቢያት የተመሠረተ በክርስቶስ የጸና በሐዋርያትም የተሰበከና የተረጋገጠ ለክርስቲያኖች ዲያብሎስን ድል የምንነሣበት መንፈሳዊ የጦር ዕቃ ነው፡፡ ስለዚህ ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እንደምታስተምረን ይህን ጾም ከምግብ ለመከልከል ጋር ጸሎትን፥ ስግደትን፥ ምጽዋትንና የንስሐ ዕንባን ጨምረን እንጹመው፡፡ ጌታችንና ነቢያት፣ ሐዋርያት የተውልን መንፈሳዊ መሣሪያ ነውና

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ጾም የጾመው ለአብነት፣ ለማስተማር፣ ለአርዓያ ነው፡፡ በዚህ ታላቅ ጾም ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ፣ ከሰው የሥጋ ጠባይ የሚመጣ ስስትና ፍቅረ ንዋይ ድል የተነሱበት ነው፡፡ እኛም ይህን እያሰብን በተለያየ መንገድ የሚመጣብንን ፈተና ለማራቅ ከዚህ ታላቅ ጾም በረከት እንድናገኝ እንጾማለን፡፡ ጸልዮ ጸልዩ፣ ጾሞ ጹሙ ብሎናል፡፡ ማቴዎስ 6፥16 ስለዚህም ትእዛዙን ለማክበር እንጾማለን

የዚህ ታላቅ ጾም ስያሜዎች፦

ዐቢይ_ጾም
ባሕርይ አምላክ በሆነዉ በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተመሠረተ በመሆኑ ዐቢይ ወይም ታላቅ ጾም ይባላል

ጾመ_ሁዳዴ
በጥንት ጊዜ ገባሮች ለባለ ርስት የሚያርሱት መሬት ሁዳዴ ተብሎ ይጠራ ነበር፡፡ እኛም ባለቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስን እያሰብን የምንጾመው በመሆኑ ጾመ ሁዳዴ ተብሏል

የካሳ_ጾም
አዳምና ሔዋን ከገነት የተባረሩት ለውርደት ሞት ለሲዖል ባርነት የበቁት በመብል ምክንያት ነው፡፡በመብል ምክንያት የሞተውን የሰው ልጅ ጌታችን በፈቃዱ በፈጸመው ጾም ካሰው፤ መንፈሳዊ ረሃብን በረሃቡ ካሰለት፡፡ ስለዚህም የካሳ ጾም ተባለ

የድል_ጾም
አርዕስተ ኃጣውእ /ማቴዎስ 4/ ድል የተነሱበት በመሆኑ የድል ጾም ተብሏል

የመሸጋገሪያ_ጾም
ጌታችን ከሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል ሊያሸጋግረን የጾመው ጾም በመሆኑ የመሸጋገሪያ ጾም ተብሏል

ጾመ_አስተምህሮ
ጌታችን የጾመው ለትምህርት ነው፡፡ እርሱ መጾም ያለበት ሆኖ አይደለም፡፡ ስለዚህም ይህ ጾም ጾመ አስተምህሮ ይባላል፡፡ አርባ መአልትና አርባ ሌሊት ጾመ። ማቴዎስ 4፥2

የቀድሶተ_ገዳም_ጾም
ጌታችን ከከተማ ርቆ ከሰው ተለይቶ በመጾም ከከተማ ርቆ ከሰው ተለይቶ በብሕትውና መኖርን ቀድሶ የሰጠበት፣ የመጥምቁ ዮሐንስና የነቢዩ ኤልያስን ገዳማዊነት የባረከበት በመሆኑ የቀድሶተ ገዳም ጾም ተብሏል

የመዘጋጃ_ጾም
ሕዝበ እሥራኤል የፋሲካውን በግ ከመመገባቸው በፊት ዝግጅት ያደርጉ ነበር፡፡ እኛም ትንሣኤን ከማክበራችን፣ ሥጋና ደሙን ከመቀበላችን በፊት በጾምና በጸሎት ዝግጅት የምናደርግበት በመሆኑ የመዘጋጃ ጾም ተብሏል
++ ዛሬ ነገ ነው? ++

‘‘አባዬ ዛሬ ነገ ነው?’’ አለ አቡሽ አባቱን ከተኛበት እየቀሰቀሰ
አባት እየተበሳጨ ‘ምንድን ነው የምትለኝ?’ አለ፡፡
ልጅ ‘ዛሬ ነገ ነው ወይ?’
አባት እንቅልፉ ስላልቀቀው ‘ሂድና እናትህን ጠይቃት በቃ ልተኛበት’ አለና እየተበሳጨ ፊቱን ሸፈነ፡፡
ልጅ ወደ እናት ሔዶ ያንኑ ጥያቄ ደገመላት
‘’እማዬ ዛሬ ነገ ነው?’’ እናት ፈገግ አለች
‘ምን ማለት ነው ደግሞ ዛሬ ነገ ነው? ማለት?’’ አለች የልጅዋን የተጋለጠ ደረት እየሸፈነች
‘ትናንት አስተማሪያችን ‘ነገ ትምህርት የለም’ ብላን ነበር ፤ ዛሬ ነገ ነው?’’
እናት ‘እ እ አዎ ልክ ነህ ዛሬ ነገ ነው’ አለች እየሳቀች፡፡
ይህ ለሕጻኑ ጥያቄ የተሰጠ መልስ ለእኛም ሳያስፈልገን አይቀርም፡፡ ብዙዎቻችን የምንኖረው ለነገ ነው፡፡ ለነገ እንማራለን ፣ ለነገ እንሠራለን ፣ ለነገ እንገነባለን፡፡ የተፈጠርነው ለዘላለማዊነት ነውና እንደምንኖር አስበን ማቀዳችን ባልከፋ፡፡ ነገር ግን ላላየነው ነገ ስናስብ ያየናትን ዛሬ እንዘነጋታለን፡፡ ለነገ ደመና የዛሬን ፀሐይ እንገፋታለን፡፡ እንዳቀድን እንዳለምን ለመኖር ስንዘጋጅ እንሞታለን፡፡ መጽሐፍ ‘’ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና’ ‘ነገ ለራሱ ያስባልና ለነገ አትጨነቁ! ይላል፡፡ /ያዕ 4፡15 ፤ ማቴ 6፡34/
ሰይጣን ከሚጠቀምበት ሰውን ማጥቂያ መሣሪያም አንዱ ‘ነገ’ በሚል ቃል ማዘናጋት ነው፡፡ ነገ እማራለሁ ፣ ነገ እሔዳለሁ ፣ ነገ የታመመ እጠይቃለሁ ፣ ነገ ንስሓ እገባለሁ ፣ ነገ ወደ እግዚአብሔር እመለሳለሁ ፣ ነገ ይሄንን መልካም ነገር እሠራለሁ ነገ ነገ ነገ
ፈርኦን የሚባለው ጨካኝ ንጉሥ በመቅሠፍት ጓጉንቸር ተወርሮ ነበር፡፡ በመጨረሻም እስራኤልን እለቃለሁ ሲል ሙሴ ፦ ጓጉንቸሮቹ ከቤትህ እንዲጠፉ መቼ ልጸልይልህ? አለው፡፡ ፈርኦንም ፦ ነገ አለ፡፡
እንግዲህ ዛሬን ከጓጉንቸሮች ጋር ማደር ፈልጓል ማለት ነው፡፡ ወዳጄ በሕይወትህ ውስጥ ጓጉንቸሮች ምንድን ናቸው? ምን ዓይነት ክፉ አመል አለብህ ፣ ምን ዕረፍት ያሳጣህ ፣ ሰላም የነሳህ ነገር አለ? አልላቀቅ ያለህ ሱስ ፣ አልስተካከል ያለህ ድክመት ፣ አልድን ያለህ ቁስል ምንድን ነው? እርሱን መቼ ትላቀቀዋለህ? መቼ መዳን ትሻለህ? ነገ ካልከኝ ፈርኦን መሆንህ ነው? ‘አቤቱ አሁን አድን’ ካልክ ደግሞ እንደ ዳዊት ትሰማለህ
ነገ ይህንን ሱስ እተዋለሁ ፣ ነገ ይህን ልማድ እላቀቃለሁ ፣ ነገ ይህን መልካም ነገር አደርጋለሁ የሚል ቀጠሮ ሠርቶ አያውቅም፡፡ ነገ እንላለን እንጂ የሚገርመው በማግሥቱም መልሳችን ነገ ነው፡፡ ‘ዱቤ ዛሬ የለም ነገ ነው’ እንደሚለው የብልጥ ባለሱቅ ማስታወቂያ ነገ ስንሔድ ነገ እየተባለ የምንፈልገውን ሳንሠራ የማንፈልገውን እየሠራን እንኖራለን፡፡ ወዳጄ ነገ የአንተ አይደለችም ‘የተወደደው ሰዓት አሁን ነው’ መኖርህን ሳታውቅ ቀጠሮ አትሥጥ፡፡ ኃይልህ በአሁን ላይ ብቻ ነው፡፡ ማንም ሊሠራባት የማይችላት ሌሊት ሳትመጣ አሁንን ተጠቀምባት፡፡
አሁኑኑ ተነሥ ያሰብከውን መልካም ነገር ለመሥራት ፣ ክፉውን ነገር ለመተው ነገ አደርገዋለሁ አትበል
ትናንት ኅሊናህ ሲጠይቅህ ‘ነገ አደርገዋለሁ’ ብለህ ነበር ፤ ዛሬም ‘ነገ’ አትበል ምክንያቱም ሕጻኑ እንዳለው ‘ዛሬ ነገ ነው’

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ሌሎች እንዲያነቡትም ሼር ያድርጉ

╔═★══════════📄══╗
@Zemaryan
@Zemaryan
@Zemaryan
╚══📃══════════★═╝
እንኳን ለጻድቁ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓለ ጽንሰት በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት(share it)


ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ
ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዓይን ናቸው። ጻድቁን መንካት የቤተ ክርስቲያንን ዓይኗን መጠንቆል ነው።
ተክለ ሃይማኖት እንደ ሊቃውንት ሊቅ፣ እንደ ሐዋርያት ሰባኬ ወንጌል፣ እንደ ሰማዕታት ብዙ ግፍ የተቀበሉ፣ እንደ ጻድቃን ትሩፋት የበዛላቸው፣ እንደ ደናግል ንጽሕናን ያዘወተሩ፣ እንደ ባሕታውያን ግኁስ፣ እንደ መላእክትም ባለ ክንፍ አባት ናቸው። ለዚህ ነው ተክለ ሃይማኖትን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዓይኔ የምትላቸው።

ልደት

መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ ጸጋ ዘአብ ካህኑና እግዚእ ኃረያ ናቸው። እርሱ በክህነቱ እርሷ በደግነቷ፣ በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል።
በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው ቅዱስ ሚካኤል ጸጋ ዘአብን ከሞት እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል። በኋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል።
ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተጸነሱት መጋቢት ፳፬ ቀን በ፲፪፻፮ ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ደግሞ ታኅሣሥ ፳፬ ቀን በ፲፪፻፯ ዓ/ም ነው። በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል። ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል።

ዕድገት

የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን" ይሰኛል። ይህንን ስም ይዘው አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል። በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት፣ ሐዲሳትን) ተምረዋል። በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል። ዲቁናም ከወቅቱ ጳጳስ አባ ጌርሎስ ተቀብለዋል።

መጠራት

አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑት በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ።
የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ። "ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን። ከዚህ በኋላ አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ። ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ።" ብሎ በግርማ ዐረገ። ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ በኋላ ሰዓትን አላጠፉም። ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ።

አገልግሎት

ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከጳጳሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ። በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ (ጽላልሽ) አካባቢ ብቻ በአሥር ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ። ያን ጊዜ ኢትዮጵያ ሁለት መልክ ነበራት።
፩ኛ.ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል።
፪ኛው. ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር።
ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ። ሕዝቡንና መሳፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው ማርያኖችን (ጠንቋዮችን) አጥፍተዋል።

ገዳማዊ ሕይወት

ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮጵያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል። እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በሦስት ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል።
እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለአሥራ ሁለት ዓመታት፣ በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለሰባት ዓመታት፣ በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለሰባት ዓመታት በአጠቃላይ ለሃያ ስድስት ዓመታት አገልግለዋል።
በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በኋላም ወደ ምድረ ሽዋ (ዞረሬ) ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለሃያ ሁለት ዓመታት ቆመው ጸልየዋል። በተሰበረ እግራቸውም ስድስት ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለሰባት ዓመታት ጸልየዋል።

ስድስት ክንፍ

ኢትዮጵያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል። ጻድቁ ምድረ እስራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ፣ እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር።
የወቅቱ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል። ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በኋላ ነው። ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር።
ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም። በገሃድ፦
በቤተ መቅደስ ብስራቱን፣
በቤተ ልሔም ልደቱን፣
በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን፣
በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን፣
በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር።
የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ።
በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ አባታችንን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው። @zemaryan
በዚያም፦
የብርሃን ዓይን ተቀብለው፣
ስድስት ክንፍ አብቅለው፣
የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው፣
ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው፣
ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው፣
ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው "ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል።

ተአምራት

የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው።
ሙት አንስተዋል፣
ድውያንን ፈውሰዋል፣
አጋንንትን አሳደዋል፣
እሳትን ጨብጠዋል፣
በክንፍ በረዋል፣
ደመናን ዙፋን አድርገዋል።
ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል። በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕፃናት አብረው ኑረዋል። በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና። @zemaryan

ዕረፍት

ጻድቅ፣ ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው፣ መከራን በብዙ ተቀብለው፣ እልፍ አእላፍ ፍሬን አፍርተው በተወለዱ በዘጠና ዘጠኝ ዓመት ከስምንት ወር ከአንድ ቀናቸው ነሐሴ ፳፬ ቀን በ፲፫፻፮ ዓ/ም ዐርፈዋል። ጌታ፣ ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል። አሥር ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል።
አምላከ ቅዱሳን ከጻድቁ አባታችን በረከትን ይክፈለን።
መጋቢት ፳፬ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ

የቅዱሳን በዓላት

፩.ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት (ጽንሰታቸው)
፪.ቅዱሳን እግዚእ ኃረያና ጸጋ ዘአብ
፫.ቅዱስ አባ መቃርስ ሊቀ ጳጳሳት
ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ አጋቢጦስ ጻድቅ
፪.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
፫.ቅዱስ ሙሴ ፀሊም
፬.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
፭.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
፮.ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ
"በረከት በጻድቅ ሰው ራስ ላይ ነው። የኀጥአንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል። የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው። የኀጥአን ስም ግን ይጠፋል።"
(ምሳሌ ፲፥፮-፯)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

╔═★══════════📄══╗
@Zemaryan
@Zemaryan
╚══📃══════════★═╝
ሰላም የደጓ እናቴ ማርያም ቻናል አባላት
አዲስ ዜና አለ 🌍🌍🌍
አዲስ የማስተማርያ bot ከፍተናል ገብታቹ ተማሩ
ሊንኩ 👉👉👉 @maryamawit_bot