✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.06K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
አዲስ ዓለም ማርያም

እነሆ ብዙ ሰው ስለማያውቃት፤
ቢያውቃትም ስለማያስታውሳት፤
ቢያስታውሳትም መልሶ ስለሚረሳት
አዲስ አለም ከተማና ስለ ርዕሰ
አድባራት ደብረ ጽዮን ማርያም
ቤተክርስቲያን አመሰራረት እፅፋለሁ፡፡
.......
አዲስ አለም ከአዲስ አበባ በስተ ምዕራብ ወደ አምቦ፣ ወደ ወለጋና
አሶሳ በሚወስደው መንገድ 42ኪ.ሜ ርቃ የምትገኝ ትንሽ ከተማ ናት፡፡ አዲስ አበባ አጠገብ ተኝታ የራሷን ህልም
የምታልም፣ የራሷን ቅዠት የምትቃዥ፣ የራሷን ኑሮ የምትገፋ . . .
ለጽሁፌ በምንጭነት የተጠቀምኳቸውን ጽሁፎች ያገኘሁት የአዲስ ዓለም ርዕሰ አድባራት ደብረ ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያንን መቶኛ አመት በማስመልከት በ 1994 ዓ.ም
በወጣው መጽሄት ላይ አንጋፋው የታሪክ ምሁር ፕ/ር ታደሰ
ታምራትና አቶ ፈቃደ ሥላሴ ተፈራ (ሊቀ ጉባኤ) ከጻፏቸው
ግሩም ጽሁፎች ነው፡፡ በዕውነት እኒህ ሁለት ሊቃውንት ማለፊያ
ጽሁፎች ጽፈዋልና ታላቅ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡
‹‹እንተ ይዕቲ ሀገሩ ለንጉስ ዓቢይ ምኒልክ››
በቀድሞ ዘመናት የአሁኖቹ የመናገሻ፣ የወጨጫና የአዲስ
ዓለም አካባቢዎች እንደዝነኛው ጨንገሬ ሶኪ ና እንደ ሁኪ ጉላ
ባሉት የሜታ አሮሞ መሪዎች ስር በባላባትነታቸው የግዛት ወሰን
ውስጥ የነበሩ ሲሆን ንጉሰ ነገስት እምዬ ምኒልክ ለመጀመርያ
ግዜ አዲስ አለምን የጎበኟት በ 1874 ግንቦት ወር ወደ እንባቦ
ጦርነት ሲያቀኑ ይሉናል - ሊቀ ጉባኤ ፈቃደ ስላሴ ተፈራ፡፡
(በነገራችን ላይ የቀድሞውን የአካባቢው ባላባት ለማስታወስ
ሲባል በአሁኑ ወቅት የአዲስ ዓለም ከተማ ‹‹ኤጀሬ ጨንገሬ››
በሚባል ወረዳ ስር ትገኛለች፡፡ ፡፡)
አጤ ምኒልክ መጀመርያ እንጦጦ ላይ በኋላም አዲስ አበባ
መቀመጥ ከጀመሩ በኋላ እሳቸውን ተከትሎ በዙርያቸው
የሚኖረው ህዝብ እጅግ በጣም ስለበዛ በአካባቢው የነበረው
ጫካ በጥቂት አመታት ውስጥ እየመነመነ ሄደ፡፡ ሰራዊቱና
ህዝቡ ቤቱን የሚሰራውም ሆነ ለየቀኑ የሚያስፈልገውን ማገዶ
የሚያገኘው ከዚያው ከጫካው ስለሆነ አዲስ አበባ ከተማ ገና
አስራ ስድስት አመት ሳይሞላት በተለይ የማገዶ ችግር
እየተባባሰ ሄደ፡፡ ይሄኔ ታዲያ፤ እምዬ ምኒልክ በደን የተከበበው
የአዲስ ዓለም አካባቢ በጣም ደስ አሰኛቸውና ‹‹ዋና ከተማዬን
ለምን ወደዚህች ውብ ሀገር ኣላዛውርም?›› የሚል ሃሳብ ይዘው
ተነሱ፡፡ እንግዲህ የአዲስ ዓለም ከተማ በአጤ ምኒልክ ልዩ
ትዕዛዝ አዲስ አበባ ገና አስራ ስድስት አመት እንኳን ሳይሞላት
በ 1893 ዓ.ም ተመሰረተች ማለት ነው፡፡ ‹‹እንተ ይዕቲ ሀገሩ
ለንጉስ አቢይ ምኒልክ›› ይሏችኋል እንዲህ ነው፡፡ (ይህች ሀገር
የታላቁ ንጉስ ምኒልክ ሀገር ናት)
የስሟን አሰያየም አስመልክቶ ፕሮፌሰር ታደሰ እንደሚሉት በመጀመርያ አካባቢ የዋና ከተማውን መዛወር በይሁንታ
የተቀበሉት እቴጌ ጣይቱ አዲስ ዓለም ስትመሰረት ስሟን
እንዳወጡላት ሲገልጹ ሊቀ ጉባኤ ፈቃደ ሥላሴ በበኩላቸው
‹‹የለም ነገሩ ወዲህ ነው፤ ንጉስ ምኒልክ ወደ በቾ (ሜታ)
እንጨት ለማስጋዝ ሄደው በነበረበት ዘመን ነው አዲስ ዓለም
የሚለውን ስያሜ ለቦታዋ የሰጡት›› ይላሉ፡፡ እኔም ትንሽ ስንፍና
ያዘኝና ጠለቅ ብዬ በጉዳዩ ላይ ሳልመራመር ቀረሁ፡፡
‹‹ ይኄይስነ ንግበር ዘንተ ሕንጻ ለቤተክርስቲያን ከመ ይኩነነ
መርሐ ለመንግስተ ሰማያት ወውእቱኒ ተወክፈ ነገራ›› @embtee
‹አጤ ምኒልክ መዲናቸውን ከአዲስ አበባ ወደ አዲስ ዓለም
ለማዛወር ከወሰኑ በኋላ ባካባቢው ያለፈ ፈረንጅ ሁሉ
‹‹የወደፊቷ መዲና አዲስ ዓለም ልትሆን ነው፤ ልክ እንደ
አንኮበርና እንደ እንጦጦ አዲስ አበባም እንግዲህ ሊያልቅላት
ነው!›› እያለ መጻፍ ጀመረ፡፡ በዚህ አይነት አሁን የአዲስ አለም
ደብረ ጽዮን ማርያም ባለበት ቦታ ላይ ግሩም ቤተ መንግስት
መሰራት ተጀመረ፡፡ ቤተ መንግስቱ የተመሰረተበት መሬት
ከ‹‹ዳሞቱ››ው ባላባት ከጨንገሬ ሶኪሌ ለአጤ ምኒልክ በገጸ
በረከትነት የተሰጠ ሲሆን ንጉሱ በበኩላቸው ለባላባቱ
ከ‹‹ዳሞቱ›› በላይ ‹‹ኢርበ ዲባዩ›› ከሚባለው አካባቢ
መደዳውን የተያያዘ አስር ጋሻ መሬት ሰጥተዋል፡፡ የአጤ
ምኒልክ መኳንንትም በተመደበላቸው ስፍራ የራስ መኮንን
ሰፈር፣ የፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ሰፈር እየተባለ መስፈር
ጀመሩ፡፡ (በነገራችን ላይ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ይቆዩበት
የነበረ ቤት አሁን ድረስ አዲስ ዓለም እንደሚገኝ የምናውቅ
ስንቶቻችን ነን? ስለዚህ ጉዳይ በቅርቡ መጻፌ አይቀርም፡፡)
እናም ወደ ጨዋታችን ስንመለስ፤ የአጤ ምኒልክን ቤተ
መንግስት አሰራር አስመልክቶ ሊቀ ጉባኤ ፈቃደ ስላሴ
እንደሚተርኩት የቤተ መንግስቱን ግንባታ ያካሂዱ የነበሩት
ባናውያን (መሀመድ ዓሊዎች) ሲሆኑ መጋዝ ሳቢ የሚባሉ
ባለሙያዎች ከቡልጋ መጥተው ለጣራ ስራ፣ ለቅስትና ለመቃን
የሚሆኑ ሁነኛ የጥድ እንጨቶችን ጭረቻ ከሚባል ቦታ
እየቆረጡና እየላጉ ያዘጋጁ ነበር ብለዋል፡፡ ይህ በእንዲህ
እንዳለ ግን ያው መቼም ያልተባለው አይፈጸምምና የዋና
ከተማዋን መዛወር በተመለከተ አንዳንድ ችግሮች መፈጠር
ጀመሩ፡፡ @embtee
ፕሮፌሰር ታደሰ ችግሮቹን ሲያብራሩ፤ በጊዜው የነበሩና ለ15
አመታት ያህል አዲስ አበባ የኖሩ፤ ሀብት ንብረት ያፈሩ
ወገኖች፣ ዲፕሎማቶችና አዲስ የንግድ መስመር መፈጠሩ
ያሰጋቸው ነጋዴዎች የመዲናይቱን መዛወር አስመልክቶ ቅሬታ
ማሰማታቸው ነበር፡፡ ለነገሩ፤ ግድ ካልሆነ በቀር የቆየ ቀየውን
መቀየር ማንስ ይወዳል? ከዚያማ በቃ፤ ይህ ሀሳብ ለአዲስ
አበባ ጽኑ ፍቅር በነበራቸው እቴጌ ጣይቱ ተቀባይነት አገኘና
እርሳቸው ደግሞ በፊናቸው ንጉሰ ነገስቱን ለማሳመን ጥረት
ማድረግ ጀመሩ፡፡ አሏቸውም፤
‹‹ ይኄይስነ ንግበር ዘንተ ሕንጻ ለቤተክርስቲያን ከመ ይኩነነ
መርሐ ለመንግሰተ ሰማያት ወውእቱኒ ተወክፈ ነገራ››
(ለመንግሰተ ሰማያት መግቢያ በር እንዲኖረን ይህንን ሕንጻ
ቤተክርስቲያን እናድርገው)
‹‹አጤ ምኒልክም በሀሳቡ ተስማምተው የአዲስ ዓለም
ከተማቸው ከምድራዊ መንግስት መዲናነት ይልቅ ከዚህ እጅግ
በጣም የላቀ መንፈሳዊ ስፍራ እንዲኖራት አደረጉ፡፡›› @embtee
አንዳንዴ፤ እንዲያው አዲስ ዓለም የሀገሪቱ መዲና ሆና ቢሆን
ኖሮ ስለ አዲስ አበባ የተዜሙት ዜማዎች፣ የተገጠሙት
ግጥሞች፣ የተባሉት ነገሮች ሁሉ ምን ሊሆኑ ይችል ነበር?
እያልኩ አስባለሁ፡፡
‹‹@embtee ነው ቤቴ . . .››
ርዕሰ አድባራት ወ ገዳማት ደብረ ጽዮን አዲስ አለም ማርያም
ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ መዲናቸውን ወደ አዲስ ዓለም
ለማዛወር ያለቸውን ሀሳብ ካነሱ በኋላ ለቤተ መንግስትነት
የታሰበው ህንጻ ለቤተክርስቲየንነት በሚሆን መልኩ መገንባት
ጀመረ፡፡ የዚህም የቤተክርስቲያን ስራ እንግዳ አይነት ከዚህ
ቀደም በኢትዮጵያ ተሰርቶ የማያውቅ ነው፤ ይላሉ ሊቀ ጉባኤ
ፈቃደ ሥላሴ፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ በተጀመረ ግዜ ለቤተ
መንግስቱ ግንባታ የተዘጋጁት የግንባታ እቃዎች ሁሉ
ለቤተክርስቲያኑ ግንባታ እንዲውሉ ተደረገ፡፡ ያው መቸው
በዘመኑ ሲሚንቶ ስላልነበረ ሕንጻው የተገነባው በጭቃና
በድንጋይ ሲሆን ጭቃው የተቦካው በስንዴ ገለባ፣ በጭድ እና
በበግ ጸጉር እንደሆነ ይተረካል፡፡
የአዲስ ዓለም ማርያም ቤተክርስቲያን ሕንጻ ጎኑ 27.50 ሜ
ወርዱ 24.40 ሜትር ሆኖ በድንጋይና በጭቃ የተገነባ
እንደመሆኑ የግንቡ ውፍረት አንድ ሜትር ሲሆን በአራት ማዕዘን
ቅርጽ የተገነቡ ስድስት የግንብ አምዶች አሉት፡፡
ዳግማዊት ጽዮን አዲስ ዓለም ማርያም እና አክሱም ጽዮን
ማርያም
የአዲስ ዓለም ማርያም በአክሱም ደረጃ የተተከለችበት ዋናው
ምክኒያት፤ ይላሉ ሊቀ ጉባኤ ፈቃደ ሥላሴ፤
አጤ ምኒልክ ዓድዋ
ጦርነት ሄደው ሳለ የአክሱም ካህናት ከየአድባራቱ አለቆችና
ካህናት ጋር ሱባዔ ይዘው ሰነበቱ፡፡ ከተመለሱም በኋላ ሌሎቹ
በየቤተመቅደሳቸው ምሕላ ይዘው ድሉ የምኒልክ እንዲሆን
ይጸልዩ ነበር፡፡ ወደ ምኒልክም ይላላኩ ነበር፡፡ የአክሱም
ንቡረዕድ ወደ እሳቸው ስላልመጡና ቅሬታ ስለተሰማቸው ንጉሱ
ከድል በኋላ እጅ መንሻ ወይም አምኃ ለቤተ መቅደሱ
በባለሟላቸው አማካይነት ልከው አክሱም ሳይደርሱ ወደ አዲስ
አበባ ተመልሰዋል፡፡ ንቡረዕዱና የአጼ ዮሐንስ ደጋፊዎች ግን
የአገሬውን ተወላጅ ለማንገስ ሽር ጉድ ይሉ እንደነበር ከዚያው
አካባቢ ምስጢረኞች መስማት ተችሎ ነበር፡፡ አጼ ምኒልክ
ከድል በኋላ ወደ አዲስ አበባ ከተማ እንደገቡ የነበረው
ሀሳባቸው ለታቦተ ማርያም ቤተ መቅደስ አሰርተው ሥርዐተ
አክሱምን የሚመሰርቱበት ቦታ መፈለግ ነበር፡፡ የአዲስ አለሙ
ቤተ መንግስታቸው ወደ ቤተ ታቦት ከተለወጠና ቤተ ክርስቲያኑ
ተሰርቶ ካለቀ በኋላ ዓጼ ምኒልክ ደብሯን ዳግማዊት ጽዮን
ብለው የአክሱም ጽዮንንም ክብር ሳይነኩ ማንኛውንም
የአክሱም ስርዓት በአዲስ ዓለም ዳግማዊት ደብረ ጽዮን
መስርተው ገድመዋታል፡፡
ማልዶ የነቃ፤ ቀድሞ ያንቀላፋል
አጤ ምኒልክ ለአዲስ ዓለም ያላቸውን ጽኑ ፍቅር ለመግለጽ
ለቤተ መንግስትነት ያሰቡትን ሕንጻ ወደ ቤተ ታቦትነት
በመለወጥ የቦታውን መንፈሳዊነት ለማስጠበቅ
ከመጣራቸውም በላይ በዘመኑ የነበሩ የስልጣኔ ነጸብራቆችን
ከአዲስ አበባ ቀጥሎ በአዲስ ዓለም እንዲገኙ ይጥሩ
እንደነበር ሊቀ ጉባኤ ፈቃደ ሥላሴ ይተርካሉ፡፡
ልብ በሉ እንግዲህ፤ አጤ ምኒልክ፤
· የውሀ ቧንቧ (መዘውር) አ.አ ሲገባ
አስገብተዋል
(ዛሬ ከአዲስ ዓለም ቧንቧዎች አፍ ታሪክ እንጂ ውሀ
አይቀዳም፡፡ ታሪክ ደግሞ መጠናት እንጂ መጠጣት
አይችልም)
· የስልክና የፖስታ ስራ በ 1892 ሲጀመር
የአዲስ ዓለም ከተማ ወዲያው ስለተመሰረተች
ለአዲስ ዓለም ፖስታ ቤት አቋቁመዋል
(አጤ ምኒልክ አዲስ ዓለም ሆነው ከተጻጻፏቸው
ደብዳቤዎች አንድ ሁለቱን እነሆ፡
1- ‹‹ይድረስ ከቢትወደድ ኢልግ
. . . ለጫማ የሚሆን የብረት ቅርቃር ከዚህ ከኔ ዘንድ
ታጣ፡፡ ምናልባት አንተ ዘንድ ይገኝ እንደሆነ
እንድትሰድልኝ ይሁን፡፡ ሐምሌ 4 ቀን አዲስ ዓለም
ከተማ ተጻፈ 1893 ዓ.ም›› ምንጭ ጳውሎስ ኞኞ
2- ‹‹ይድረስ ለቢትወደድ ኢልግ
የራስ ሚካዔል አሽከር በደጋ ግንድ ስናነሳ ሳንቃ
ከሆዱ ላይ ወድቆበት በብርቱ ታሞ ሊሞት ነው፡፡
አሁንም የኢጣሊያ ሐኪም መጥቶ ሁለት ሶስት
ቀን አይቶ ቢመለስ እወዳለሁና ነገ ነግረኸው
መጥቶ እንዲያየው ይሁን፡፡ ሚያዚያ 1 ቀን
1894 ዓ.ም አዲስ ዓለም ከተማ ተጻፈ፡፡››)
· የቋንቋ ትምህርት አዲስ አበባ ሲከፈት ለአዲስ
ዓለም የጀርመንኛ ቋን ቋ ት/ቤት ከፍተዋል፡፡
· በፈረስና በበሬ የሚጎተተው የጋሪ መንገድ
ሲሰራ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ ወደ አዲስ ዓለም
እንዲጠረግ አስደርገዋል
(ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ የሚለው አባባል
ለዚህ መንገድ አይሰራም፡፡ የሄዱት የአዲስ ዓለም
ልጆች እስካሁን አልመጡም፡፡ ወዴት ናችሁ የአዲስ
ዓለም ልጆች? ‹‹ኤሰ ጅርቱ ኢጆሌ አዲስ ዓለሚ?
ኢጆሌ ኤጀሬ››
· በውሀ እንፋሎት የሚነዳ ባቡር በሙሴ ሰርኪስ
አማካይነት ከፈረንሳይ ገዝተው በማስመጣት
ከጅቡቲ እስከ አዲስ አበባ፣ ከአዲስ አበባ አዲስ
ዓለም ያለውን መንገድ የኢጣልያ ተወላጆች
በሆኑ መሀንዲሶች ካስቀየሱ በኋላ ከአዲስ አበባ
እስከ አዲስ ዓለም ያለውን መንገድ በገመድ
እያስለኩ ለእያንዳንዱ ሀገረ ገዢ ሰጡት፡፡ ከወሎ
እስከ ከፋ ያሉት ሀገረ ገዢዎችም በየግዛታቸው
የነበሩትን ገባሮች በወር ተራ እያዘዙ መሬቱን
በማስቆፈርና ድንጋዩን በማስቀጥቀጥ ከአዲስ
አበባ እስከ አዲስ ዓለም ያለውን መንገድ
አስደልድለውታል፡፡ ያንን ዘመን የሸዋ ሰው
‹‹የድንጋይ ቅጥቀጣ ጊዜ›› ብሎ ሰይሞታል፡፡
ያም የሰርኪስ ባቡር በንጉሱ ፍቃድ ሰዎችናና
ዕቃዎችን ወደ አዲስ ዓለም ያጓጉዝ ነበር፡፡
· በ 1900 አንድ ኦቶሞቢል ከፈረንሳይ ቢመጣ
ጃንሆይ አጼ ምኒልክ ኦቶሞቢሉን እያንጰረጰሩ
የተጓዙት ከአዲስ አበባ ወደ አዲስ ዓለም መሆኑ
ታውቋል፡፡
(በመኪና ሰሌዳ ቁጥር ሞላ-ጎደለ የመጫወትን ጥበብ
ለኢትዮጵያ ማቲዎች ያስተዋወቁት የአዲስ ዓለም
ልጆች ሳይሆኑ ይቀራሉ?)
አሁን አዲስ ዓለም እያንጎላዠች ነው፤ ማልዶ የነቃ ቀድሞ
ያንቀላፋልና፡፡
እኛ ግን ቅዠቶቿንም ቢሆን እያነሳሳን እንጨዋወታለን፡፡
ላሁኑ ግን ይብቃን፡፡
‹‹ሰላም!››
@embtee @embtee

Inbox @Maryamawit_bot

ሼር በማድረግ ለሌሎች እናጋራ
የካቲት_ 2_ፆመ_ነነዌ_ይጀምራል

" ምነው_ተኝተሃል ? እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ያስበን እንደ ሆነ ተነሥተህ አምላክህን ጥራ" አለው። ትንቢተ ዮናስ 1:6 ።

# የዚህ ፆም ጊዜ ሶስት ( 3 ) ቀን ብቻ ነው ። ቀኖቹም በየዓመቱ ሰኞ ማክሰኞ ረቡዕ ናቸው ። የነነዌ ፆም በመባቻ ሐሙስ( አቆጣጠር ) ከፍ እና ዝቅ ስለሚል አንድ ጊዜ በጥር አንድ ጊዜ በየካቲት ይሆናል ።

የቤተ ክርስቲያን አባቶች ይህን ፆም የወሰኑት ልትጠፋ የነበረች ነነዌን በፆም ምክንያት እግዚአብሔር ይቅር ስላላት ይህን አምላካዊ ይቅርታውን ለዘለዓለም ለማሰብና ዛሬም በዚህ ዓለም ከነነዌ የከፋ ርኩሰትንና ኃጢያትን ስላለ የነነዌ ሕዝብ ይቅር ያልክ አምላክ ዛሬን ይቅር በለን ለማለት ነው።

++ የነነዌ ሰዎችም እግዚአብሔርን አመኑ ለፆም አዋጅ ነገሩ
ከትልቁም ጀምሮ እስከ ትንሾቹም ማቅ ለበሱ ወሬውም ለነነዌ ንጉስ ደረሰ። እርሱም ከዙፋኑ ተነስቶ መጎናፀፊያውን አውልቆ ማቅንም ለበሰ። አመድ ላይም ተቀመጠ አዋጅንም አስነገረ።

++ በነነዌም ውስጥ የንጉሱንና የመኳንቱን ትእዛዝ አሳወጀ እንድህም አለ ሰዎችም እንስሶችም አንዳችም እንዳይቀምሱ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ። ሰወችና እንስሳትም በማቅ ይከደኑ። ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩሁ። ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ። እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይፀፀት እንደሄነ ከፅኑ ቁጣውስ ይመለስ እንደሆነ ምን ያውቃል በማለትም አሳሳበ።


++ እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸውም እንደተመለሱ በስራቸውም አየ። እግዚአብሔር አምላክም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተፀፀቶ አላደረገውም
ት ዮናስ ( ፫ ፤ ፭-፲ )

የነነዌ ህዝብን በምህረቱ የጎበኘ ቸር አባት ለሀገራችንም ለህዝባችንም ምህረትና ቸርነቱን ያብዛልን ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን አሜን ፫
ለመንፈሳዊነት ቅድሚያ እንስጥና የእግዚአብሔርን ብድራት እንጠብቅ፡ እግዚአብሔር ጾማችንን ጾመ ድህነት ጾመ ስርየት ሰይጣንን ድል መንሻ ፣የኃጥያት መደምሰሻ ፣ መንግስተ
ሰማያትን መውረሻ ያድርግልን
ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን
@embtee
@embtee
@embtee
እባካችሁ ሠዎች አንድ ነገር ልንገራችሁ እግዚአብሔር መሀሪ እና ቸር ነው
ስለ ምን እምነታችን ጎደለ?
ስለ ምን ፍርሀት በውስጣችን ነገሰ?
ስለ ምን ወሬ ማውራት ከመፀለይ በለጠብን?
ስለ ምን ከመንበርከክ በየፋርማሲው መሰለፍ ቀለለን?
ስለ ምን ወደ እግዚአብሔር ከመጮህ ይልቅ በየሶሻል ሚድያው ሽብር መንዛትን መረጥን ?
እግዚአብሔር ሁላችንንም በማያልቀው ምህረቱ ይቅር ይበለን
እግዚአብሔር ወደእርሱ እንድንቀርብ እና እንድንማልድ ይርዳን !
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች !
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ !
እግዚአብሔር በክንፎቹ ጥላ ኢትዮጵያን ይጋርድ
╔═★══════════📄══╗
@Zemaryan
@Zemaryan
@Zemaryan
╚══📃══════════★═╝
በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ በ24 አካባቢ ሁለቱ ወንድሞቻችን ሰማዕታነት የተቀበሉበት ቦታ ለቤተክርስቲያን ተሰጠ።
ዛሬ አመሻሽ ከቤተክህነት አካባቢ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው የፊታችን እሁድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለሚሰራው ህንፃ ቤተክርስትያን የመሰረት ደንጋይ ያስቅምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
💚💛❤️ @ZEMARYAN 💚💛❤️
“ሀገራዊ የጸሎት ጥሪ እንጂ ጾም አልተባለም”
ሊቀ ትጉኃን ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያ የሃይማኖተ ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሓፊ
መጋቢት 28/2012 ዓ/ም

የኮሮና ቫይረስ በሀገራችን መከሰቱን ተከትሎ የሃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂ አአባቶች በአንድ ላይ ሆነው ብሔራዊ የጸሎት አዋጅ ትናንተ በ27/07/2012 ዓ.ም ማወጃቸው የሚታወስ ነው ፡፡ ይሁን እንጂ የታወጀው የጸሎት አዋጅ ሆኖ እያለ በተለያዩ የማኀበራዊ ድረ ገጾች ለምዕመናን የተሳሳተን መረጃ የሰጡ መሆናቸውን ያነሱት ጠቅላይ ጸሓፊው ሊቀ ትጉኃን ታጋይ ተደለ የሃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂ አባቶች ያወጁት ለሁሉም ሃይማኖቶች ለአንድ ወር የሚቆይ ብሔራዊ የጸሎትና የንሥሓ አዋጅ እንጅ የጾም አይደለም ብለዋል፡፡

በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ጾም መሠረት ከትንሣኤ እስከ በዓለ ሃምሳ የጾም ሥርዓት እንደሌለ የሚታወቅ ሲሆን የሃይማኖት ተቋማቱ ጉባኤ በማንኛምው ቤተ እምነት ሕግና ሥርዓት ጣልቃ የማይገባ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ፈጽሞ እንደማይችል ጨምረው ገልጠዋል ፡፡

አያይዘውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሆነ የሌሎች አብያተ እምነት የጋራ ጸሎትና በኮሮና ወረርሽኝ እና መሰል ጉዳዮች የትምህርትና የጸሎት መርሐ ግብር በአራት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከዛሬ ማለትም ከ28/07/2012 ዓ/ም ከምሽቱ 3፡00-4፡00 ለተመልካች እንደሚደርስ ገልጠው ሁሉም እንዲከታተል ጠቁመዋል ፡፡

በመጨረሻም ጠቅላይ ጸሓፊው ሊቀ ትጉኃን ታጋይ ታደለ በዘመናችን የተከሰተው ክፉ ወረርሽኝ በሽታ እንዲወገድ ሁላችንም በበረታ ክንድ ልንጸል ይገባልም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመርሐ ግብር ተራ በአራቱ ጣቢያዎች
ሰኞ፡ በ ETV ከምሽቱ 3፡00-4፡00
ማክሰኞ፡በ FANA ከምሽቱ 3፡00-4፡00
ረቡዕ፡ በ ADDIS TV ከምሽቱ 3፡00-4፡00
ሐሙስ፡ በ WALTA ከምሽቱ 3፡00-4፡00
አርብ ፡ በ ETV ከምሽቱ 3፡00-4፡00
ቅዳሜ፡ በ FANA ከምሽቱ 3፡00-4፡00
እሑድ፡ በ ADDIS TV ከምሽቱ 3፡00-4፡00
©EOTC TV
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል አደረሳችሁ።
ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም
«መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው»
/መዝ. ፹፮፥፩/
ስለ እመቤታችን የትውልድ ሐረግ ከመወለዷ በፊት ነብያት በመንፈስ ቅዱስ በመቃኘት ትንቢት ይናገሩ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ በስፋት ያስተምረናል፡፡ ለምሳሌ ያህልም የዝማሬና የትንቢት ጸጋ በእግዚአብሔር የተሰጠው እንደ ልቤ የተባለ ዳዊት ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አስቀድሞ ስለ ሥርወልደቷ፣ አምላክን እንደምትወልድ፣ ስለ አማላጅነቷ በመዝሙር ተናግሯል ለምሳሌ በመዝ ፹፮፥፩ ላይ ‹‹መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን›› መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፡፡ በማለት ከቤተክህነት ከቅዱሳን እንደምትወለድ በምሳሌ ገልፆታል፡፡
ልጁም ጠቢቡ ሰሎሞን መኃ.መኃ.4.9 ‹‹እቴ መርዓት ሙሽርዬ ከሊባኖስ ነይ" እያለ የተወለደችበትን ሀገር እንደጠቀሰ መመልከት ይቻላል፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ በትንቢቱ ‹‹ትውፅእ በትር እምሥርው እሰይ ወየዐረግ ጽጌ እምኔሃ›› ትርጉሙም ከእሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከርሷ ይወጣል በማለት ተናግሯል ት.ኢሳ ፲፩፩
በሐዲስ ኪዳንም እንደምንመለከተው ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ መጀመሪያ የዘር ሐረጉን በዳዊት ጀምሮ እስከ ማታን ይቆጥራል በአይሁድ ልምድ ሴቶች በዘር ቆጠራ ስለማይቆጠሩ ዘፍራን በያዕቆብ ወገን አድርጎ ቆጠረ በዚህም ከዳዊት ወገን መሆኗን አሳውቋል፡፡
የእመቤታችን ወላጆች በምዕራብያውያኑና በምስራቅያውያኑ ዘንድ ታዋቂ በሆነው በመጽሐፈ ያዕቆብ (መጽሐፈ ልደታ ለማርያም) የእናቷ ስም ሐና የአባቷ ስም ኢያቄም እንደሚባል ጽፏል፡፡ ሐና በዕብራይስጥ "ውብ ተወዳጅ" ማለት ነው፡፡ ኢያቄም በዕብራይስጥ እግዚአብሔር የሠራው ያከናወነው ማለት ነው፡፡ እንዳንድ መናፍቃን ለእመቤታችን ካላቸው ጥላቻ የተነሳ አንድ ስለመውለዷ የጻፈ የለም ከአፄ ዘርዓያዕቆብ ውጪ ይላሉ፡፡ ግን ከላይ የተመለከትነው መጽሐፍ በጣም ጥንታዊ በዘመን የማይደራረስ መሆንን የታሪክ ድርሰቶች ይናገራሉ፡፡ አፄ ዘርዓያዕቆብ የነበረው በ1399-1468 ባሉት ዓመታት ሲሆን ሐዋርያው ታናሽ ያዕቆብ የጻፈውን መጽሐፍ በ150-215 ዓ.ም ሊቁ ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ እና ኦርገን እንደተጠቀሙበት እንመለከታለን ቀደምት አባቶቻችን ግን የሐና ቅድመ አባቶቿ ቴክታና ጴጥሪቃ ሲባሉ እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩ ደግና ቅዱሳን እንደነበሩ ይህ ቀራቸው የማይባሉ ባለጠጎች ወርቅ ብር የተትረፈረፈላቸው ነበሩ፡፡ ጴጥሪቃ ሀብቱን ሁሉ ከተመለከተ በኋላ ለሚስቱ ይህን ሁሉ ሀብት ምን እናደርገዋለን እንኳን ለእኛ ለልጅ ልጆቻችን ይተርፍ ነበር ግን እኔም አንቺም መካኖች ነን ባላት ጊዜ ቴክታ እግዚአብሔር ከኔ ልጅ ባይሰጥህ ከሌላ ይሰጥህ ይሆነናልና ሌለ አግብተህ ውለድ፡፡ አለችው እሱም ይህን እንኳን ላደርገው እንደማላስበው እግዚአብሔር ያውቃል አላት፡፡ ማታ በህልሟ ቴክታ ነጭ እንቦሳ ከማኅጸኗ ስትወጣ እንቦሳይቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ሰባተኛዋ ደረሰ ሰባተኛዋ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃ ፀሐይን ስትወልድ አይታ አድንቃ ለባሏ ነገረችው እሱም በልቡ እያደነቀ ወደ ህልም ፈቺ ጋር ሄደ፡፡ ህልም ፈቺውም ነጫጮቹ እንቦሶች ሰባት ደጋግ ልጆች ይወልዳሉ ሰባተኛዋ ግን በመላዕክት ሁሉ የከበረች ትሆናለች የፀሐይ ነገር ግን አልተገለፀልኝም በማለት ተረጎመላት፡፡ ጴጥሪቃ ሄዶ የህልሙን ፍቺ ነገራት እርሷም የእስራኤል አምላክ የሚያደርገውን እርሱ ያውቃል በማለት ፈጣሪዋን አመሰገነች፡፡ በዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች ስሟንም ሔመን አሏት ሔመን ዴርዴን ወለደች ዴርዴም ቶናን ወለደ ቶናም ሲካርን ወለደች ሲካርም ሴትናን ወለደች ሴትናም ሔርሜላን ወለደች ሔርሜላም የተከበረችና የተመረጠች ዓለሙን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ አያት የምትሆን ሐናን ወለደች፡፡ ሐና በመልካም አስተዳደግ አድጋ ለአካለ መጠን ስትደርስ ከነገደ ይሁዳ ወገን ለሚሆን የአላዛር የልጅ ልጅ ለሚሆን የቅስራ ልጅ ከሚሆን ከኢያቄም ዳሯት፡፡ ሐናና ኢያቄም በእግዚዓብሔር የሚወደዱ ደጋጎች ነበሩ ፡፡ ግን ልጅ አልነበራቸውም! ወደ ቤተ መንግስት በመሔድ እግዚዓብሔርን ደጅ ይጠኑት ነበር አንድ ቀን ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት ተመለከቱ በዚህን ጊዜ ሐና "አቤቱ ጌታዬ ግዑዛን እንስሳ ልጅ የሰጠህ ለኔ ለምን ነሳኸኝ" በማለት ሱባኤ ያዙ ኢያቄም ወደ ምድረ በዳ ሄደ ሐናም በቤቱ አትክልት ስፍራ አካባቢ ሱባኤ ያዘች በሱባኤያቸውም ፍፃሜ ራዕይ ተመለከቱ፡፡
ሐናም ለኢያቄም በህልሜ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማኅጸኔ አደረች ብላ ነገረችው ምስጢሩም ርግብ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስትሆን ነጭነቷ ንፅህናዋ፣ ቅድስናዋን የሚገልጽ ነው፡፡ ኢያቄምም የተመለከተውን ራዕይ ነገራት በህልሙ ሰባቱ ሰማያት እንደመጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወረደ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ብሎ ነገራት፡፡ ምስጢሩም ወፍ የተባለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ነጭነቱ ንጹሐ ባሕሪ መሆኑን ሲያመለክት ነው፡፡ ይህን ራዕይ ሐምሌ ፴ ቀን ተመልክተው ልጅ ብንወልድ ለእግዚአብሔር አገልጋይ ትሁን ብለው ተሳሉ እመቤታችን በእግዚአብሔር ፈቃድ በብስራተ ገብርኤል ነሐሴ ሰባት እሑድ ቀን ተፀንሳለች፡፡እመቤታችን በማኅፀንም ሆና ብዙ ተአምራትን አድርጋለች፡፡ ሁለቱን ለአብነት ያህል እናያለን፡፡
ሐና በርሴባ የምትባል አንድ ዓይና አክስት ነበረቻት ልትጠይቃት መጥታ ሳለ እግዚአብሔር በቸርነት ጎበኘሽ ብላ ማኅፀኗን በዳሰሰችበት እጇ የጠፋ ዓይኗን ብታሸው በርቶላታል፡፡ ሌሎችም እንዲሁ ሆዷን እየዳሰሱ ድነዋል፡፡
ሐና የምትወደው ሳምናስ የሚባል የአጎቷ ልጅ ሞቶ በቤተሰብ ልማድ የአልጋውን ሸንኮር ይዛ ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት ሙቱ አፈፍ ብሎ ተነስቶ ሰላም ለኪ ኦ እምሔውቱ ለዘገብረ ሰማየ ወምድረ ሰማይና ምድርን የፈጠረ የአምላክ አያቱ ሐና ሰላም ላንቺ ይሁን ብሎ መስክሮ ተመልሶ አርፏል፡፡
በእናቷ ማኅጸን ሳለችም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከአዳም ጅምሮ በዘሩ ሁሉ ሲተላለፍ የነበረው ጥንት አብሶ እመቤታችንን እንዳይነካት ከእናቷ ማኅጸን ጀምሮ ጠብቋታል፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ግንቦት 1 ቀን በሊባኖስ ተወልዳለች፡፡በሊባኖስ መወለዷም ሰሎሞን ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ መኃ.መኃ ዘሰሎሞን 4.9 ያለው ይፈፀም ዘንድ ነው፡፡ቤተ-ክርስቲያናችንም "ልደተ ለማርያም" በማለት በዓሉን በቅዳሴ፣ በማህሌት በታላቅ መንፈሳዊ ሐሴት ታከብረዋለች፡፡ ሐናና ኢያቄም እግዚአብሔር በሰጣቸው ልጅ ተደስተው በተወለደች በ8 ቀኗ ማርያም ብለው ስም አወጡላት፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምልጃዋ አትለየን፡፡ሀገራችንን ትጠብቅልን በዓለም ላይ የመጣውን መቅሰፍት ትመልስልን፡፡ዳግመኛ ተሰባስበን በዓሏን ለማክበር ያብቃን አሜን
​​ፆመ ሐዋርያት

አንዳንዶች የሰኔ ፆም የቄስ ፆም ነው በሚል ከመፆም ወደኋላ ሲሉ ይታያሉ ነገር ግን ቅድስት ቤተክርስቲያን በአዋጅ ከምትፆማቸው ሰባት አፅዋማት አንዱ እንደመሆኑ መጠን እያንዳንዱ ክርስቲያን ቢፆመው እጅግ በርካታ በረከቶችን ያገኝበታል ከነዚህም ጥቂቶችን እነሆ

1.በረከተ ሐዋርያት ይገኝበታል
ይህን ፆም መጀመርያ ፆመው እንድንፆመው ሰርዐት የሰሩልን ሐዋርያት ናቸዉ ስለዚህም ፆሙ መታሰቢያነቱ የሐዋርያት ነው የጻድቅ መታሰቢያ ደግሞ ለበረከት ነው ። ምሳ.10፥7 እኛም የሰኔን ፆም ብንፆም የሐዋርያቱን በረከት እናገኛለን ሐዋ.13፥1-3 ሐዋ.14፥23

2. በስራችንና በአገልግሎታችን በረከት እናገኛለን
ሐዋርያት ይህን ፆም የፆሙት አገልግሎታቸው እንዲከናወንላቸው እንዲባረክላቸው ነው ነብዩ ነህምያም እየሩሳሌምን የመስራት ተግባሩ እንዲባረክለት በፆመው ፆም ስራው ሁሉ ተባርኮለታል። ነህም.1፥4። እኛም የሰኔን ፆም ብንፆም በዕለት ተዕለት ተግባራችን በረከት እናገኛለን።

3. ዝናብ ምህረትን ጠለ በረከትን እናገኛለን
የሰኔ ፆም በአገራችን የክረምቱ መግቢያ ላይ የሚፆም ፆም ነው ይህም መጪው የክረምቱ ወራት የተስተካከለ የምህረት ዝናም እንዲኖረው ያደርጋል በነብዩ ኢዩኤል ዘመን ዝናብ ጠፍቶ ዛፎቹ ሳይቀር በደረቁ ጊዜ በፆም በፀሎት ወደ እግዚአብሔር በተማፀኑ ሰዓት ዝናመ በረከትን አግኝተዋል። ኢዩ.1፥13-14

4. በረከተ ምርትን እናገኛለን
የሰኔ ፆም በሃገራችን ገበሬው ዘር መዝራት በሚጀምርበት ጊዜ የሚፆም ፆም ነው ሰለዚህም በዚህ ሰዓት የሚፆመው ፆም ዘርን እንዲባረክ በረከት እንዲበዛ ያደርጋል ይህም አገር ወገን ከረሃብ ከችግር ነፃ እንዲወጣ ያደርጋል በነብዩ ኢዩኤል እንደተገለጸው በፆም የዕህል የመጠጥ በረከት ይገኛል ። ኢዩ.2፥12-14

5. የነፋስ በረከትን እናገኛለን
ፆም በመንፈስ የደከመች የዛለች ነፍስን ያበረታል የነፍስን ቁስል ይፈውሳል ስጋዊ ኃይልን ያደክማል የሥጋን ፈቃድ ለነፍስ ያስገዛል መዝ.108፥24 ፤ ገላ.5፥24 የዓለምን ሃሳብ ያስወግዳል ከእግዚአብሔር ያስታርቃል ማቴ. 17፥21 ሚስጥር ይገልጣል ዘስ.34፥27-28 ፤ ዳን. 10፥1-3 "በአምላካችን ፊት እራሳችንን እናዋርድ ዘንድ ከርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ ...... ፆምን አውጃለሁ " መጽሐፈ ዕዝራ.8፥21 ከመዋዕለ ፆሙ ረድኤት በረከት ያሳትፈን !

ፆሙን የኃጢአት መደምሰሻ የዲያብሎስ ድል መንሻ የመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ያድርግልን አሜንንንን !!!

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @Sihela_adhno 💚
💛 @Sihela_adhno 💛
❤️ @Sihela_adhno
ሰላም ለእናንተ በአይነቱ ለየት ያለ የእናንተን የቮይስ ቅጂ ዝማሬ #ቻሌንጅ የምናቀርብበት ቻናል ይቀላቀሉንን ይማሩበታል በዝማሬ አምላክን ያመሰግኑበታል 👇👇👇👇👇👇👇👇
@tewahidoortodox
@tewahidoortodox

Inbox👇
@kidanemiherat_bot
🎚🎚🎚🎚

"🎚🎚 እግዚአብሔር ታማኝ ነው"

እግዚአብሔር ታማኝ ነው። የእኛ አለመታመን የእግዚአብሔርን ታማኝነት አያጎድለውም።የእኛ በደለኛነት የእግዚአብሔርን አባትነት አይቀንሰውም።እግዚአብሔር ሁልጊዜም እግዚአብሔር ነው።ከገዘፈው ነውራችን ይልቅ ጥቃቅኗን ጽድቃችንን እየቆጠረ ለተሻለ ክብርና ለላቀ ጸጋ የሚሻን ርኅሩኅ አባት ነው።ስንረቀው ይቀርበናል፣ስንሸሽው ይከተለናል፣ስንጠፋም ይፈልገናል።ዲያብሎስ ሰብሮ ሲጥለን እግዚአብሔር ጠግኖ ያቆመናል።ዓለም ንቃ ስታዋርደን፣እግዚአብሔር ግን ወዶ ያከብረናል ።በበድልና በኃጢአታችን ምክንያት ሕይወታችን ጣዕም አልባ ልባችን እረፍት አልባ ሲሆን እግዚአብሔር ግን በፍጹም ይቅርታና ምኅረት ዳግመኛ ሌላ እድል እየሰጠ አፋችንን በሳቅ ከንፈራችንን በእልልታ ይሞላል።የውርደት ማቃችንን ቀዶ ደስታን ያስታጥቀናል።

የሰው ልጅ ባልተጠራበት ቦታ ትርፍ በተጠራበት ቦታ ግን ዋና ነው።የተጠራ ነው ለክብር ነው ፣የልጁ መልክ በእኛ እስኪሳል፤ክብርና ባለጠግነት የሕይወታችን አክሊል እስኪሆን ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት ቀርበን የመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች እስክንሆን እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቶናል።ዋናችን ክርስቶስ ክብራችንም መንግስቱ ነው።በጽድቃችን ሳይሆን በጸጋው የሚያወርሰንን ርስት በልግስና ለመስጠት እግዚአብሔር የታመነ ነው።

አልገባ ብሎን ነው እንጂ ዓለም የእኛ እኛም የዓለም አይደለንም።በዓለም እየኖርን ከዓለም የተለየን የመንግስተ ሰማያት ዜጎች ነን።ከሰማያዊ ጥሪ ተካፋይ የሆናችሁ ወገኖች ሆይ የእምነታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህን የሆነውን ክርስቶስ ኢየሱስን ተመልክተን በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግስት እንሩጥ።ሀገራችን በሰማይ ነው።ይህ ድንኳን የሆነው የምድራዊ ኑሯችን ፍጹም ከንቱና ጊዚያዊ ነው።ለጊዚያዊ የድንኳን ኑሮ እንዴት ሰው በወገኑ ደም ላይ ይቆማል ፣እንኳንስ ለጸብ ለፍቅር በማትበቃ እድሜስ እንዴት ሰው የወንድሙን መቃብር ይምሳል።የይቅርታን ድምጽ ከመስቀል ላይ የሰማ አማኝ ፣ የሰላምን ወንጌል ከፍቅር መምህር ያደመጠ ክርስቲያን እንዴት ለኩርማን መሬትና ለቁራሽ እንጀራ ፍቅርን በጸብ ይለውጣል።እንኳን ደረቅ መሬት እኛስ አፈር አይደለንም ወይ?እግዚአብሔር ያልባረከው በደም የተገኘ ርስት እርሱ አኬልዳማ የደም መሬት ነው።ቢዘሩበት እሾህ ቢያርሱበት አሜኬላ የሚያበቅል የእርግማን ምድር ነው።

እርስትም ብቻ አደለም ባለን ጥቂት ነገር እንኳ በፍቅር ተካፍለን እንኑር። በጥቂቱ ያልታመነ በብዙ አይሾምምና። ለትንሽ ነገር ስግብግቦች ራስ ወዳዶች አንሁን እግዚአብሔር ከሌለበት ጎተራ እግዚአብሔር ያለበት ጥቂት ነገር ይበልጣል። ስስት ሲኖር ፍቅር ይጠፋል፣ ፍቅር ሲጠፋ ጭካኔ እና ጥላቻ ይሰፍንብናል። በፍቅር የማካፈል ልምድ የምንጀምረው ከጥቂቷ ነገር ነውና ለኛ ይጠቅመናል ብለን የምናስባትን ትንሿ መልካም ነገር ለሌላውም እንመኛት።

በክርስቶስ ወንድሜ የሆንክ ወገኔ እባክህ ወደ ልብህ ተመለስ ደም ዘርተህ ደም አትጨድ ፤የወንድምህን ነፍስ አጥፍተህ ተናጥቀህ የምትይዘው ርስት ደዌና ደረመን በሕይወትህ ያመጣል እንጂ በረከትና ጥጋብ አይሆንልህም።በፍቅር ከሆነ ግን በኩርማን መሬት ላይ ጎተራህን ሊሞላ እግዚአብሔር የታመነ ነው።

እግዚአብሔር የልጁ የክርስቶስ ልብ እንዲኖረን በልዩ መለኮታዊ ክብር ጦርቶናልና የጠላት ዲያብሎስን ሐሳብ ጠንቅቀን አውቀን ጸብን በይቅርታ ጥላቻንም በፍቅር እንተካ።
​​የ"7" ቁጥር ምስጢራት"
= = =
➭ሰባት ቁጥር ጥልቅ ምሳሌና ትርጓሜ አለው።በዕብራውያን ዘንድ ሰባት ቁጥር ፍጹም ቁጥር ነው።

➭እግዚአብሔር ከሰኞ እስከ ዕሁድ ያሉትን ቀናት በሰባት ቁጥሮች ወስኗል።(መ.ምሳሌ 24፥16)

➭እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት ነጻ ወጥተው በሲና በረሃ ሲጓዙ ይመሩ የነበረው በሰባት ደመና ነበር።(ዘዳ 13፥21)

➭እስራኤላውያን ኢያሪኮን ለሰባት ተከታታይ ቀናቶች እንዲዞሯት፣በሰባተኛው ቀን ደግሞ ሰባት ጊዜ እንዲዞሯት ታዘው ነበር። (ኢያሱ 6፥15)

➭ጴጥሮስ ወንድሙን ይቅር እንዲለው የታዘዘው እስከ ሰባት ጊዜ ሰባ እንጂ ሰባት ጊዜ ብቻ አልነበረም።
(ማቴዎስ 18፥21, 22)

➭ሌላው የሰባት ቁጥር ምሳሌዎች በጥቂቱ እንደሚከተለው ይቀርባሉ።

ሰባቱ አባቶች
= = =
1. ሰማያዊ አባታችን እግዚአብሔር
2. የነፍስ አባት
3. ወላጅ አባት
4. የክርስትና አባት
5. የጡት አባት
6. የቆብ አባት
7. የቀለም አባት

ሰባቱ ዲያቆናት
= = =
1. ቅዱስ እስጢፋኖስ
2. ቅዱስ ፊልጶስ
3. ቅዱስ ጵሮክሮስ
4. ቅዱስ ጢሞና
5. ቅዱስ ኒቃሮና
6. ቅዱስ ጳርሜና
7. ቅዱስ ኒቆላዎስ

ሰባት የጌታ ቃላት(እኔ ነኝ)
= = =
1. የሕይወት እንጅራ እኔ ነኝ
2. የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ
3. እኔ የበጎች በር ነኝ
4. መልካም እረኛ እኔ ነኝ
5. ትነሣዔና ሕይወት እኔ ነኝ
6. እኔ መንገድና ሕይወት ነኝ
7. እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ

ሰባቱ ሰማያት
= = =
1. ጽርሐ አርያም
2. መንበረ መንግሥት
3. ሰማይ ውዱድ
4. ኢየሩሳሌም ሰማያዊት
5. ኢዮር
6. ራማ
7. ኤረር

ሰባቱ ሊቃነ መላእክት
= = =
1. ቅዱስ ሚካኤል
2. ቅዱስ ገብርኤል
3. ቅዱስ ሩፋኤል
4. ቅዱስ ራጉኤል
5. ቅዱስ ዑራኤል
6. ቅዱስ ፋኑኤል
7. ቅዱስ ሳቁኤል

ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት
= = =
1. የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን
2. የሰርምኔስ ቤተ ክርስቲያን
3. የጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን
4. የትያጥሮስ ቤተ ክርስቲያን
5. የሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን
6. የፊልድልፍልያ ቤተ ክርስቲያን
7. የሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን

ሰባቱ ተዐምራት
= = =
➭ጌታ የሰው ልጆችን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት፦
1. ፀሐይ ጨልሟል
2. ጨረቃ ደም ሆነ
3. ከዋክብት ረገፉ
4. ዐለቶች ተሠነጠቁ
5. መቃብራት ተከፈቱ
6. ሙታን ተነሡ
7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ

ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት
= = =
1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ
2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው
3. ዛሬ ከእኔ ጋራ በገነት ትሆናለህ
4. እነሆ ልጅሸ እናትህ እነሆት
5. ተጠማሁ
6. ተፈጸመ
7. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እስጥሃለሁ

ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን
= = =
1. ምሥጢረ ጥምቀት
2. ምሥጢረ ሜሮን
3. ምሥጢረ ቁርባን
4. ምሥጢረ ክህነት
5. ምሥጢረ ተክሊል
6. ምሥጢረ ንስሐ
7. ምሥጢረ ቀንዲል

ሰባቱ ዐበይት አጽዋማት
= = =
1. ዐቢይ ጾም
2. የሐዋርያት ጾም
3. የፍልሰታ ጾም
4. ጾመ ነቢያት
5. ጾመ ገሀድ
6. ጾመ ነነዌ
7. ጾመ ድኅነት

ሰባቱ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠሉ ነገሮች (ምሳ 16፥6-19)
= = =
1. ትዕቢተኛ ዓይን
2. ሃሰተኛ ምላስ
3. ንፁህን ደም የምታፈስ እጅ
4. ክፉ ሃሳብን የምታፈልቅ ልብ
5. ለክፋት የምትፈጥን እጅ
6. የሐሰት ምስክርነት
7. በወንድሞች መካከል ጠብን የምታፈራ ምላስ

ሰባቱ ፀሎት ጊዜያት
= = =
1. ነግህ የጠዋት ጸሎት
2. ሠለስት (የ3 ሰዓት ጸሎት)
3. ቀትር (የ6 ሰዓት ጸሎት)
4. ተሰአቱ (የ9 ሰዓት ጸሎት)
5. ሰርክ (የ11 ሰዓት ጸሎት)
6. ነዋም (የምኝታ ጸሎት)
7. መንፈቀ ሌሊት (የሌሊት ጸሎት)


ሰባቱ የዳዊት ሐብታት
= = =
1. ሐብተ ፈውስ
2. ሐብተ ትንቢት
3. ሐብተ በገና
4. ሐብተ መንግስት
5. ሐብተ መዊዕ
6. ሐብተ ኃይል
7. ሐብተ ክህነት

7 ቀናት፣7 ፊደላት፣7 ሰው የተፈጠረበት ባህርያት፣......