✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.06K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሰን።

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለምንድን ነው ለመስቀል ክብር የምትሰጠው?

መስቀል
"መስቀል ኃይላችን ነው
ኃይላችን መስቀል ነው
የሚያፀናን መስቀል ነው
መስቀል ቤዛችን ነው
መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው
አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋለን ያመነው እኛም በመስቀሉ
እንድናለን ድነናልም።" /የዘወትር ጸሎት/

በብሉይ ኪዳን መስቀል የእርግማን ምልክት ና የወንጀለኞች መቀጫ ነበር::(ዘዳ 21:23)
ክርስቶስ በደሙ ስለቀደሰው ግን ቅዱስ መስቀል ተብሏል። በመስቀል ድህነትን አግኝተናል።(1ኛ. ጴጥ 2: 24-25)
ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለሙን ከኃጢአትና ከሞት ለማዳን በቀራኒዮ የተሰቀለበት ቤዛችን ነው።
መስቀል የነጻነታችን ግርማ: የድህነታችን መገኛ: ጠላትን ድል የምንነሣበት መሳሪያችን ነው።
ሰውን በመስቀል ላይ መቅጣት የተጀመረው በጥንቱ ፋርስ በዛሬዋ ኢራን /ከክርስቶስ ልደት በፊት/339-33/ ዓመት ነው።

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለምንድን ነው ለመስቀል ክብርን የምትሰጠው?

1. ክርስቶስ መስዋዕት ሆኖ ራሱን የሠዋበት እውነተኛ መንበር በመሆኑ፤
2. የክርስቶስ ደም የፈሰሰበት: እኛ የዳንበት የነጻነት አርማችን ስለሆነ፤
3. የአምላካችን መለኮታዊ ፍቅር የተገለጠበት መሳሪያ በመሆኑ፤

የመስቀል ዓይነቶች
___

1. የመጾር መስቀል:-
±±±±±±±±±±±±±
በቅዳሴ እና በማዕጠንት ጊዜ ሠራዒው ዲያቆን የሚይዘው ነው።

2. የእጅ መስቀል:-
±±±±±±±±±±±±±±±
ካህናት ምእመናንን የሚባርኩበት በእጅ የምትያዝ የመስቀል ዓይነት ናት።
3. የአንገት መስቀል:-
±±±±±±±±±±±±±±±±
ምእመናን ለአምላካቸው ያላቸውን ፍቅር ለመግለጽ ከማዕተባቸው ጋር በአንገታቸው የሚያደርጉት ነው።

4. እርፈ መስቀል:-
±±±±±±±±±±±±±±
በማንኪያ ቅርጽ ተሠርቶ በእጅታው ላይ የመስቀል ምልክት ያለበት ነው። ሠራዒው ዲያቆን በቅዳሴ ጊዜ የአምላካችንን ክቡር ደሙን ለምእመናን የሚያቀብልበት ነው። እንዲሁም ጌታችን በእለተ አርብ የተወጋበት ጦር ምሳሌ ነው።
መስቀል ከተለያዩ ማዕድናት ይሰራል

መስቀል ከተለያዩ ማዕድናት ሊሰራ ይችላል: መስቀሉ የሚሰራባቸው ማዕድናት የራሳቸውን ባህርያት እንዳላቸው ሁሉ ምሳሌውን ለመግለጽ ብቁ ናቸው ብለው አባቶች ያስቀመጡትን እንደሚከተለው እንመለከታለን፦

1. የእንጨት መስቀል:-
----------------------------
ጌታችን የተሰቀለው በዕጽ በእንጨት ላይ መሆኑን ለማመልከት ነው።
+ ለምን ኢየሱስ ክርስቶስ በእንጨት ተሰቀለ? አዳም ዕጽ/ እንጨትን በልቶ ሞትን በማምጣቱ ክርስቶስም በእንጨት ተሰቀሎ ህይወትን ሊሰጠን በእንጨት መስቀል ተሰቀለ።
2. የብረት መስቀል:-
-------------------------'-'
ጌታችን በአምስቱ ቅንዋተ ለመቸንከሩ ምሳሌ ነው።

3. የብር መስቀል:-
---------------------------
ይሁዳ በሠላሳ ብር አሳልፎ ስለመስጠቱ። በተጨማሪም ከብር ቢሰራ ተስፋን: ዕድልን ያመለክታል። ይኸውም እርሱ ለሰው ልጆች ሁሉ ቤዛ ሊሆን በደሙ ዋጋ ከፍሏልና ከእርሱ ተስፋ እንድናደርግ ያመለክተናል።
4. የወርቅ መስቀል፦
---------------------------
ከወርቅ ቢሰራ ወርቅ ንጹህ እንደሆነ ንጹሀ ባህርይ እድፈት የሌለው
ጽኑ አንተ ነህ ብሎ ለመመስከር ነው።

5. የመዳብ መስቀል:-
------------------------------
መዳብ ቀለሙ ቀይ ይመስላል: ጌታችን ለእኛ ብሎ ያፈሰሰው ደም ምሳሌ ነው።

ብዙዎች የመስቀል ጣላት ሆነው መስቀልን ጣኦት ነው ይላሉ ጣኦት ማለት ግን የሠይጣን ስም የሚጠራበት ፣የሚመለክበት ነው።
መስቀል ደግሞ የመድኃኒዓለም ስም የሚጠራበት ህማሙን የሚድኑበት አርማችን፣ ኃይላችን ነው እንጂ መስቀል አምላክ አይደለም። በመስቀል የተሠቀለው ግን አምላክ ነው።
ምሳሌ: ሰው አልጋ ላይ ሲተኛ አልጋ ላይ ተኛ ይባላል እንጂ እንጨቱ ላይ ተኛ አይባልም: ሰው የቤቱን በር ሲዘጋ እጨቴን ልዝጋ አይልም በሩን ልዝጋ ይላል እንጂ: አልጋ አልጋ ይባላል የተሰራው ከእንጨት ሊሆን ይችላል ነገር ግን እንጨት ተብሎ አይጠራም: በርም በር ይባላል እንጂ እንጨት ተብሎ አይጠራም። እንዲሁም ጌታ የተሰቀለበትን መስቀል መስቀል ይባላል ፤እንጂ እንጨት አይባልም።

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ብሏል:
"ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ።
መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው።
(ፊልጵ 3÷18-19)

" ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ
ይራቅ።" ( ገላ 6:14)
@Zemaryan
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።
የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ የአስተዋዮችንም ማስተዋል እጥላለሁ ተብሎ ተጽፎአልና።
(1ኛ ቆሮ 1÷18-19)

ጌታ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን፡፡
@Zemaryan
መስከረም 16ቀን 2013ዓ.ም

መልካም በዓል
@Zemaryan @Zemaryan
፨ ሲኦል ይሻለኛል ፨
እነ አባ ኤፍሬም ውዳሴ ማርያምን ፅፈው እውነት ካልፀደቁ እነ አባ ህርያቆስ ቅዳሴ ማርያምን ፅፈው እውነት ካልፀደቁ እነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አርጋኖንን ሰዓታትን ደርሰው እውነት ካልፀደቁ እነ ቅዱስ ያሬድ አንቀፀ ብርሀንን ድጓን ደርሰው እውነት ካልፀደቁ እነ ቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ መፅሀፍትን እንደዛ አመስጥረው እውነት ካልፀደቁ እነሱ ከሌሉበት ገነት ይልቅ እነሱ ያሉበት ሲኦል ይሻለኛል ። የሚያረጅ እምነት ስለሌለን የሚታደሰ ሀይማኖት የለንም ። እኛ በሀጥያት ስናረጅ ቤተክርስቲያን እኛን በንስሀ እና በስጋ ወደሙ ታድሰናለች እንጂ እሷ አትታደስም ። አባቶቻችን የቀደሱትን ቅዳሴ እንቀድሳለን ፡ እነሱ የደገሙትን ውዳሴማርያምና ዳዊት እንደግማለን ። እነሱ የቆሙትን ሰዓታትና ማህሌት እንቆማለን ። እነሱ የተቀበሉትን ስጋና ደም እንቀበላለን ። ከዛስ ? እነሱ የገቡበት እንገባለን ። እምነታችን ይህ ነው ።
@Sihela_adhno
@Sihela_adhno
#ከማኅበረ_ሥላሴ_አንድነት_ገዳም_የተላከ_መልዕክት

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ቢያንስ ለ 15 የተዋህዶ ልጆች Share በማድረግ ክርስትያናዊ ግዴታችንን እንወጣ ።


#በኢትዮጵያና_በመላው_ዓለም_ለምትገኙ_ኦርቶዶክስ
_ክርስቲያኖች_በሙሉ_ከጥቅምት_24_እስከ_30_ከ
ህፃናት_እስከ_ሽማግሌ_ማንም_ሳይቀር_በማህበረ_መ
ነኮሳቱ_አማካኝነት_ፆም_ታውጇል::
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱአምላክ አሜን
በክርስቶስ ክርስቲያን ለተሰኛችሁና በደሙ የዋጃችሁ በኢትዮጵያ
የምትገኙ ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ በቤታችሁም ያላችሁ
በህመም ምክንያት በሆስፒታል ያላችሁ በማረሚያ ቤት ያላችሁ
በጦር ሜዳም ያለችሁ እንዲሁም በተለያየ ስፍራ የምትገኙ
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የከበረ ሰላምታችንን
በያላችሁበት ይድረሳችሁ፡፡
እኛ ማኅበረ ስላሴ እንድነት ገዳም የምንገኝ ማኅበረ መነኩሳት
በሀገራችን ሰላም መታጣት ምክንያት ከሀዘናችን ጋር አምላክ
አበው ክብር ምስጋና ይግባዉ ደኅና ነን፡፡
እግዚአብሔር ገና ሃያ ሁለቱን ስነ-ፍጥረት ፈጥሮ ሳያበቃ
ሳጥናኤል በዓለተ ረቡዕ በሶስተኛዉ ሰማይ በጌታ ላይ በማመጽ
በጀመረዉ ጸብ ምክንያት ከመላዕክቱ ጋር ተዋግቶ ተሸንፎ ወደ
ምድር ተጥሎ እነሆ ያለ እረፍት ለሰባ ሺ አምስት መቶ አመታት
በመላዉ ዓለም ደም ሲያፈስ ቆይቷል፡፡ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ፡፡
ጌታ የተሰጠዉ የቀጠሮ ቀን እስኪፈጸም ድረስ ታግሶታል፡፡
አሁን ግን ከወትሮዉ ለየት ያለዉ ነገር የእግዚአብሔር ቤተ -
መቅደስ በሆነችዉና የቅዱሳን የአስራት ሀገር በተሰኘችው
በኢትዮጵያ ሀገራችን የሳጥናኤል ጭፍሮች ክተት ሰራዊት ምታ
ነጋሪት ብለዉ ዘምተዉ በታሪክም ያልሰማነዉ በዘመናችንማ
አይተን የማናቀዉ የአርስ በአርስ እልቂት እንኳን ከክርስቲያን
ከሰብአዊ ፍጡር የማይጠበቅ ድርጊት ተፈጽሟል እየተፈጸመም
ነዉ፡፡
ሰይጣን ብቻዉን ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ ከሰዉ ጋር ሆኖ
በሰዉ ልብ አድሮ ግን ምንም የሚቀረዉ የሀጢያት ሥራ የለም፡፡
በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፭፡፲፭ ላይ ብትወዱኝስ ትዕዛዜን ጠብቁ
ያለዉ የጌታ ቃል ተጥሷል፡፡
ቀድሞ አንድ ሰዉ ለሥራም ሆነ ለንግድ ወይም ለተለያየ
ጉዳይ ወደ ማያዉቀዉ ወደ ሚያዉቀዉም በኢትዮጵያ ክፍላተ
ሀገር ወይም ክልል ሲዘዋወር ለሀገሩ እንግዳ ለሰዉ ባዳ ነኝ
ብሎ አይጨነቅም፡፡ የእግዚአብሔር እንግዳ ተብሎ ከመሸበት
ገብቶ እግሩን ታጥቦ ቤት ያፈራውን በልቶ ጠጥቶ ከመልካም
ምንጣፍ ተኝቶ አድሮ ሲነጋ ተነስቶ መርቆ ቀሪዉን ምንገድ
ይጓዛል፡፡
ዛሬ ግን ያ ቀረና የእግዚአብሔር እንግዳ እራቱ ጥይትና ገጀራ
መጠጡ ደም ሆኗል፡፡ በማቴዎስ ወንጌል ምዕ ፳፭፥፵፪ ላይ
የተጠቀሰዉ እንግዳ ሆኜ ብመጣ አልተቀበላችሁኝም ብራብ
አላበላችሁኝም የሚለዉ የጌታ ቃል ትዉልዱን እየተዋቀሰዉ ነዉ፡፡
በእርግጥም በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነዉ ብሎ ዮሐንስ
ወንጌላዊ እንደተናገረዉ እንግዶች የሰላም ተጓዦች መሆን
ይጠበቅባቸዋል፡፡ነገር ግን የሰላም ሰዎችም አብረዉ
ተጨፍልቀዉ የጥፋት ሰለባ ሆነዋል፡፡ ሁሉን ቻይ የሆነ
እግዚአብሔር አሁንም ታግሶናል፡፡እኛ አሁን ከሞት የተረፍነዉ
ከጥላ ያረፍነዉ በጽድቃችን አይደለም በቸርነቱ ለንስሐ ጊዜ
ተሰጥቶን ነዉ እንጅ፡፡
ነቢያት ስለ ጥፋት ሲተነብዩ በሰዉ ልጅ ሐጥያት ከእግዚአብሔር
የሚታዘዘዉን መቅሰፍት ማስገንዘባቸዉን እንጅ ጥፋት ዝም ብሎ
ደርሶ የሚታዘዝ አይደለም፡፡
አሁን በኃጢያታችን ምክንያት እየተጎነጨነዉ ያለዉ መከራ ከዚህ
በፊት ብዙ የተነገረ ቢሆንም በትንቢተ ዮናስ ታሪካቸዉ
እንደተጠቀሰዉ እንደ ሰብዓዊ ነነዌ ወደ እግዚአብሔር በጾም
በጸሎት ሆኖ በመለመን በማልቀስ መከራዉን ማስቀረት
እንዲቻል ቅዱሳን በመጽሐፍት አስተምረዉናል፡፡
በኖህ ዘመን ምድር በዉሃ ሙላት የጠፋችዉ በኃጢያት ምክንያት
ነዉ፡፡ በሎጥ ዘመን በሰዶም ሀገር የተቃጠለችዉና ከምድረ ገጽ
የጠፋችዉ በኃጢያት ምክንያት ነዉ፡፡
ዛሬስ እየተሰራ ያለዉ ኃጢያት በዚያ ዘመን ከነበረዉ ያንሳልን ?
ያን ጊዜስ በንስሀ ላልተመለሱ ሰዎች ፈርዶ ያጠፋቸዉ አምላክ
ዛሬስ ፈርዶ ማጥፋቱ ይሳነዋል ወይ ? አይሳነዉም
እንዲያዉም እንደ ዘመናችን ኃጢያት ብዛትና ክብደት
ላልፈረደብን እግዚብሔር እያመሰገንን ይህን መልዕክት
በያላችሁበት ሲነበብላችሁ ከሰማችሁት በኋላ ወደ ልባችሁ
ተመለሱ ከእንግዲህ ወዲህ በዘር ፣ በጎሳ ፣ በቋንቋ ፣ በሀገር ፣
በብሔር መለያየት ይብቃ ፣ መገዳደል ይብቃ ፣ መዘራረፍ ይብቃ
፣መሰደድም ይብቃ አጠቃላይ የጥፋት ዘመቻ ይብቃ፡፡ ወደ
ቀድሞ ኢትዮጵያዊ አንድነታቸን እንመለስ በኅብረት ተቻችለን
እንኑር፡፡
የኃጢያታችንን ካባ አዉልቀን በነብስም በሥጋም የሚያድነንን
የንስሐ ካባ እንልበስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፭፥፲፪ ላይ እኔ
እንደወደድኳችሁ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ ብሎ ጌታችን ባዘዘብ
መሰረት ጥላቻን አስወግደን የዘር ፣የጎሳ፣ የቋንቋ ፣ የክልል
ልዩነት ሳይኖረን እርረ በእርሳችን እንዋደድ፡፡
በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፬፥፳፯ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ ያለዉ ጌታ
ቃሉ አይለወጥም እና ይህ ከሆነ ብቻ እዉነተኛዉን ሰላም
ማግኘት ይቻላል፡፡
የተከበራችሁ ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ ነብዩ ኢሳያስ በትንቢቱ ምዕ
፩፥፲፱ ላይ ‹‹ እሺ ብትሉና ብትሰሙኝ የምድርን በረከት
ትበላላችሁ እምቢ ብትሉና ባትሰሙኝ ግን ሰይፍ ትበላችኃለች
የእግዚአብሔር አፍ ይህንን ተናግሯልና›› የሚለዉን የትንቢት ቃል
ዛሬም በእኛ ኢትዮጵዊያን ላይ እንዳይደርስብን ለእግዚአብሔር
ቃል እንታዘዝ እና ክፋትን ሁሉ ትተን ንስሀ ገብተን የምድርና
በረከት እንብላ፡፡ አለበዚያ ግን ምሕረት በእጁ የሆነ አምላክ
መዓተም በእጁ ነዉና ምርጫዉ ግን የእናንተ ነዉ፡፡ በሀገራችን
ሰላም ይሰፍን ዘንድ ማንኛዉም ክርስቲያን የተጣላ ታርቆ ፣
የበደለ ክሶ ፣ ይቅር ተባብሎ ፤ ከጥቅምት ፳፬ እስከ ጥቅምት ፴
ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም ድረስ ልጅ አዋቂ ሳይለይ እስከ ዘጠኝ ሰዓት
እየጾማችሁ በሀዘን በለቅሶ ምህላ በመያዝ ከእግዚአብሔር
ምህረትና ይቅርታ በጋራ እንድንለምን እኛ የማኅበረ ሥላሴ
አንድነት ገዳም ማኅበረ መነኮሳት ሁሉን በፈጠሩ በቅድስት
ሥላሴ ስም አምላክን በወለደች በእናታችን በቅድስት ድንግል
ማርያም ስም በታላቅ አክብሮት መልዕክታችንን ለመላዉ ሕዝበ
ክርስቲያን አስተላልፈናል፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን ሰላም ይስጥልኝ
የሞቱትን ሁሉ ነብስ ይማርልን
የጠፋዉን የተቃጠለዉን የወደመዉን ንብረት ሆሉ ይተካላችሁ
አሜን ይሁን ይደረግልን
መምህር አባ ወልደ ሰንበት ነጋሽ
የማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም አበመኔት
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Share share share share share share

1 ሰው ለ 15 ምዕመን
╔═★══════════📄══╗
@Zemaryan
@Zemaryan
@Zemaryan
╚══📃══════════★═╝
ሰላም የቻናላችን ተከታታዩች
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስብከተ ወንጌል የተለያዩ መፃፀፎች መንፈሳዊ ዜናዎች
እንደሚያቀርብ ይታወቃል ያሎትን ሀሳብ አስተያየት ቢቀነስ ቢጨመር የምትሉትን ይፃፉል አስተያየታቹ ያበረታታናልና

እናም በዚ ቻናል ለማገልገል ፍላጎት ያሎት 👉 https://t.me/maryamn111bot
​​#ሕዳር_ሚካኤል !

#እንኳን_ለመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ሚካኤል #በዓለ_ሲመት_በሠላም_አደረሰን !

በዓለ ሲመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል (ሕዳር 12)
(አንብባችሁ ስትጨርሱ ለሌሎችም ታሪኩን እንዲያዉቁ #SHARE_SHARE_SHARE
ብታደርጉ ብዙ አተረፋችሁ፡፡)

ቤተ ክርስቲያን ልጆቹዋ የመላእክትን ተራዳኢነት አውቀው እንዲጠቀሙና የመንግሥቱ ወራሾች ለመሆን እንዲበቁ ስትል ለቅዱሳን መላእክት የመታሰቢያ ቀን በመስጠት በእነርሱ የምናገኛቸውን እርዳታዎች እንዲታወሱ ታደርጋለች፡፡

በዚህም መሠረት በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡

እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል። ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በተሰኘው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡

የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው ፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት “… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘ ሰው በፊቱ ቆመ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት
አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” (ኢያ.5፡13) ይለናል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ሹመቱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይም በመሆኑ ስለ እነርሱ ዲያብሎስ ይዋጋው፣ በጸሎትም ይራዳቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ኃጢአት ሠርተው ሲያገኛቸው ለእግዚአብሔር አድልቶ ኃጢአተኞችን ስለሚቀጣ እግዚአብሔር ሕዝቡን “በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት” (ዘጸ.23፡21) ብሎ አስጠንቅቋቸው ነበር፡፡

ይህም ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙን ያስረዳናል፡፡ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱት ጥቅሶች ሕዝበ እስራኤልን ይራዳቸው የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ አያረጋግጥም የሚል ካለ “መልአክ” የተባለው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ነቢዩ ዳንኤል በተላከ ጊዜ ገልጦልን እናገኛለን፡- ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ቅዱስ ሚካኤል ስለመሾሙ ሲመሰክር “በእውነት በመጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ ማንም
የለም”(ዳን.10፡21) ብሎአል፡፡

ስለዚህም ለኢያሱ የተገለጠውና እስራኤላውያንንም የመራው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን እንረዳለን፡፡

@christian930 💚
@christian930 💛
@christian930

የቅዱስ ሚካኤል አለቅነት በሐዲስ ኪዳንም አንደሚቀጥል ይህ ነቢይ በትንቢቱ “በዚያ ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ ሚካኤል ይነሣል..” (ዳን.12፡1) በማለት ተናግሮለታል ፡፡

ስለዚህም ቅዱስ ሚካኤል እኛን ከሰይጣን አሽክላና ወጥመድ ይጠብቀንና በጸሎቱ በእግዚአብሔር ፊት ይቆምልን ዘንድ በእኛም ላይ ሹም ነው። ምክንያቱም እኛ የእግዚአብሔር ሕዝቦችና የርስቱ ወራሾች ነንና፡፡

እግዚአብሔር ነቢዩ ሙሴን የሕዝቡ መሪ አድርጎ መሾሙ እጅግ ትሑትና ስለመንጎቹ ነፍሱን እንኳ አሳልፎ እስከመስጠት ደርሶ ስለሚወዳቸው ነበር፡፡ (ዘኁል.12፡3፤ዘጸአ.32፡32)በሕዝቡም ላይ እርሱን መሾሙ እንዲሠለጥንባቸው ወይም እንዲገዛቸው ሳይሆን በትምህርቱና በጸሎቱ እነርሱን እንዲያግዛቸው ነው፡፡ እንዲህም ስለሆነ ቅዱስ እስጢፋኖስ ስለሙሴ ሲመሰክር “እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው”አለ፡፡ (የሐዋ.7፡35)

እንዲሁ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እጅግ ትሑትና ለሠራዊቱ ተቆርቋሪ የሆነ መልአክ በመሆኑ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ተሾመ፡፡ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙ ልክ እንደ ሙሴ በእነርሱ ላይ ሊሠለጥንባቸው ወይም ሊገዛቸው ሳይሆን መላእክትን ሊመራ ፣ እኛን ደግሞ ከሰይጣን ጥቃት ሊጠብቀንና በጸሎቱ ሊራዳን ነው (ይሁዳ.12) ፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን መላእክት እኛን እንደሚጠብቁና እንደሚራዱ እንዲሁም ስለእኛ በፊቱ አንደሚቆሙ ሲያስተምረን “ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ስንኳ እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ሁል ጊዜ በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁ” (ማቴ.18፡10) ብሎናል፡፡

እኛን ይጠብቁ ዘንድ የተሰጡን ቅዱሳን መላእክት ስለእኛ እንዲህ የሚቆረቆሩና ስለመዳናችን የሚተጉ ከሆነ በቅድስናው ልቆ የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመው ቅዱስ ሚካኤል እንዴት ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ይበልጥ አይቆም? (ሉቃ.13፡6-9) እንዴትስ በተሰጠው ሥልጣንና ኃይል አይረዳን? (መዝ.33፡7) እርሱ “ስለሕዝብህ ልጆች የሚቆመው” መባሉም እኛን በጸሎቱና በተራዳኢነቱ የጽድቅ ሕይወታችንን በሚገባ እንድናከናውን እንደሚራዳን የሚያሳይ ኃይለ ቃል ነው፡፡

የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ጸሎቱና በረከቱ በእኛ ላይ ለዘለዓለሙ ይደርብን አሜን፡፡
@zemaryan
ወደ ዝምታዬ ተመለስኩ
~የልቤ ደስታ የእረፍቴ ከተማ ሆይ~~
ድንግል ሆይ በማን እና በምን እንድመስልሽ አሰብኩ። በዚህ አለም በሚገኙ ሁሉ አንቺን ይገልጹሽ ዘንድ አወጣሁ አወረድኩ ግን አላገኘሁም። መንፈሴንም አየር አየራት ብልክ ከፍጡራን አንቺን የሚመስልሽ ስላጣሁ ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን ሁሉ በላይ መሆንሽን በማወቅ ልቤ ወደማደሪያው ተመለሰ።
የልቤ ደስታ ሆይ፥- የአዳም ተስፋው ነሽ ብልሽ ለአዳም እና ለእኛ ለልጆቹ ተስፋ ስለሆንሽ ነው፤ ቀስተ ደመናይቱ ሆይ፥- ከጥፋት ውሃ በኋላ እግዚአብሔር ምድርን ዳግመኛ በንፍር ውሃ እንዳያጠፋ ለኖህ የገባለት የኪዳኑ ምልክት ቀስተደመና ነሽ፤ እግዚአብሔር በኃጢያታችን ተቆጥቶ እንዳያጠፋን የባህሪያችን መመኪያ የሆንሽ ቀስተ ደመናችን ነሽ
፥- በኖህ መርከብ ብንመስልሽ ኖህ በመርከቡ የሰበሰባቸውን ፍጥረታት ከጥፋት ውሃ እንደተጠበቁ ሁሉ በአማላጅነትሽ ለምንተማመን ሁሉ በመከራ ከሚመጣ ሞተ ስጋ እና በሃጥያት ከሚመጣ ሞተ ነፍስ ስለምታድኝን ነው።
እናቴ ሆይ፥- ያለውንድ ዘር የወለድሽው ልጅ ሃይል ምርኩዛችን ነው። እጸ ጳጦስ ዘሲና ሆይ፥- ሙሴ በሲና ያየሽ በእሳት የተከበብሽ ቁጥቋጦ አንቺ ነሽ፥-መለኮትን በማህጸንሽ የተሸከምሽ፣ ከነፍስሽ ነፍስ ከስጋሽ ስጋ በነሳ ጊዜ ባህርየ መለኮት ያላቃጠለሽ እና ያለወጠሽ። ያዕቆብ ሎዛ በተባለች ስፍራ በራዕይ መላዕክት ሲወጡና ሲወርዱባት ያየው መሰላሉ ሆይ፥- በአማላጅነትሽ መሰላልነት የሰው ሁሉ ልመና ወደ ባህርይ አምላክ ይደርሳልና።
የእረፍቴ ከተማ ጽዮን ሆይ፥- በታቦተ ጽዮን አስርቱ ትዕዛዛት አድሯል አንቺ ከታቦተ ጽዮን ትበልጫለሽ የህጉ ባለቤት ጌታ በማህጸንሽ አድሯልና። እስራኤላውያን በታቦተ ጽዮን ፍልስጤማውያንን ድል እንዳደረጉ እኛ የሰው ልጆችም ኣንቺ በወለድሽው ልጅ ከዲያቢሎስ እጅ ድነናልና።
@embtee
@embtee
እንዲህ እና እንዲህ እያልኩ ብመስልሽ እንኳ ሁሉ ስላንቺ ያንስብኛል፣ ከምሳሌዎቹ ሁሉ በላይ ነሽ።
ድንግል ሆይ አንቺን እኮ ማመስገን የሚቻለው ልጅሽ ሲፈቅድ ብቻ ነው፣ መልአኩ ከሰማይ አንቺን ለማመስገን ሲመጣ የላከው እግዚአብሔር እንዲያመሰግንሽ ስለፈቀደለት ነው፣ አንቺን እናመሰግንሽ ዘንድ የሚበቃ ማንነትስ ያለን እኛ ማን ነን? እንዲያው በፈቃዱ ሆነ እንጂ። ጽዮን ሆይ እንዲያው ዝም ብዬ እወድሻለሁ አልኩሽ። እኔ ባላመስግንሽ ቢጎልብኝ እንጂ ለአንቺ ዘውትር የምስጋና ወንዘ በፊትሽ ይፍሳል።
ምንም ብል ምንም ብጽፍ ምንም ሆነብኝና ወደ ዝምታዬ ተመለስኩ!!!!!
ድንግል ማርያም ህልማችሁን እውን ታድርግላችሁ
@embtee
@embtee
•እንኳን ደስ አላችሁ የዳዊት ዜማ በዩቲዩብ መቷል!«ተከፈተ»

መንፈስን አዳሽ የሆኑ ዝማሬዎችን አውደ ስብከቶችን ግጥሞች በምስል እና በቪዲዬ በታገዘ ወቅታዊ የሆኑ ዝግጅቶችን ይዘን እንቀርባለን እንዳያመልጦ ከስር የተቀመጠው ሊንኩን ከፍተው ሰብስክራይብ 🔻 ያድርጉት የደወል 🔔 ምልክቱንም ይጫኑ በየእለቱ ወደናንተ የምንለቀው ይደርሶታል እናመሰግናለን !

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://m.youtube.com/channel/UCuzDApz9RTu02VXXFRnwQtg
👆👆👆👆ይክፈቱት👆👆👆👆
(
እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!

ታህሳስ 19 ቀን በዚህ ቀን ሰለስቱ ደቂቅ "የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶኑ ሊያድነን ይችላል" ያሉበት ዕለትና ቅዱስ ገብርኤል ከእሣት ያዳቸው ዕለት መታሰቢያ በዓል ነው።

ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን አባቶቻችን እንዳስተማሩን ነገሩ እንዲህ ነው። ዘመኑ ጣኦት የሚመለክበት ንጉስ ናቡከደነፆር የእግዚአብሔር ሰዎች የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች የነበሩት ወጣቶች ሥም አይጣላልናንያ (ሲድራቅ) ፤ አዛርያ (ሚሣቅ) ፤ ሚሣኤል (አብድናጎ) ነበሩ። ት/ዳንኤል 3፡1-30 ታሪኩ እንደሚግረን ንጉስ የጣኦት ምስል አሰራ በገሊላ አውራጃ ያለውን ሕዝብ ጠርቶ ለጣኦቴ ያልሰገደ ወደ እሣት ውስጥ ብሎ አወጀ።

በዚህ መካከል ሰልስቱ ደቂቅ ነበሩ። የንጉስ ትህዛዝ ነውና ሕዝቡ ሁሉ ለጣኦቱ ሲንበረከክ እነርሱ ግን ቆመው ያዩ ነበር። የእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምንም ነገር አያስፈራውምና ናቡከደነፆር እርሱ ላስቆመው ጣኦት አለመስገዳቸውን ሲሰማ ተናደደ ፤ ተበሳጨም እሳቱን 7 እጥፍ እንዲነድ አስደረገ ሦስቱንም አስሮ እሣቱን እያሳየ "ከመቃጠል ወይስ ለእኔ ጣኦት መስገድ የቱ ይሻል?" ባላቸው ጊዜ የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶን ሊያድነን ይችላል ባያድነንም እንኳን አንተ ለመታመልከው ጣኦት አንሰግድም አሉት።

በዚህ ጊዜ ጉልበት ያላቸው ሠዎች ተፈልገው ሦስቱን ወጣቶች አስረው ወደ እሣት ቶን ውስጥ ጣሏቸው አስረው የጣሉቸው ወታደሮች የእሣቱ ወላፈን አቃጠላቸው ሠልስቱ ደቂቅን ግን መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ እሳቱን አበረደላቸው አጠፋላቸው።

በዚህም ጊዜ ንጉስ ናቡከደነፆር እንዲህ በማለት መሰከረ "እኛ አስረን የጣልናቸው ሦስት ነበሩ አሁን ግን አራተኛው ሰው በእሳቱ ሲመላለስ ይታየኛል እንዲያውም የአማልክትን ልጆች ይመስላል " አለ። የእግዚአብሔር የማዳኑ ስራ ሲገለጥ ቅዱስ ገብርኤል ሲታይ አዋጁ ሁሉ ተሻረ ጉልበት ሁሉ ለጣኦት ተብሎ የነበረው "ጉልበት ሁሉ ለሰልስቱ ደቂቅ አምላክ ይስገድ ይንበርከክ" ተባለ ይህን ሁሉ ታህሳስ 19 ቀን ሆነ በዚህም ምክንያት በታላቅ ደስታ እናከብረዋለን!

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የመላዕክት የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃው ረድኤት በረከቱ አይለየን አሜን!
የማንቂያው ደወል ልዩ ጉባኤ የተዋህዶ ልጆችን የማንቃት ጉዞውን በመቀጠል፣ ከጥር 21-24 /2012/ዓ/ም በወላይታ ሶዶ ከተማ ታላቅ ጉባኤ ያደርጋል ።ይህ ጉባኤ፣ የጠላትን ምሽግ የሚያፈራርስ፣ የጠፉትን ልጆች ወደቤታቸው የሚመልስ፣ እግዚአብሔር አምላክ ትልቅ ሥራ የሚሰራበት ጉባኤ ሊሆን እንደሚችልም ይታመናል።እግዘአብሔር አምላክ በጉዞአችን ሁሉ ሳይለየን፣በኛ በደካሞቹ ላይ አድሮ ትልቅ ሥራን እንዲሰራ በጸሎታችሁ አግዙን።ሼር በማድረግም ፣ ላልሰሙት እያሰማን ፣የመልካም ሥራ ተካፋዮች እንሁን።

╔═★══════════📄══╗
@Zemaryan
@Zemaryan
@Zemaryan
╚══📃══════════★═╝
እንኳን በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ለጸናች ለዓለም ሁሉ እመቤት ለአምላክ እናት ለንጽህት ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የእረፍት በዓል አደረሳችሁ!!!
💟በዓለ አስተርእዮ "ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ” ጥር 21 በዓለ አስተርእዮ (የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት) እንኳን ለዚህች ታላቅ በዓሏ አደረሰን፡፡

🌿🌿 ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በስድሳ አራት አመቷ ከሞት ወደ ሕይወት ከመከራ ወደ ደስታ የተሸጋገረችበት ዕለት ነው፡፡
@Sihela_adhno
🌿🌿💟ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ያሬድም “ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ” ትርጉሙ ሞት ለማናኛቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል በማለት አደነቀ በመሆኑም በዓሉ የወላዲተ አምላክ በዓለ ዕረፍት ከመሆኑ የተነሳ ታላቅ በረከት የሚያስገኝ ስለሆነ በየዓመቱ ይከበራል፡፡
@Sihela_adhno
🌿🌿💟 ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ መካነ ፍሥሓ ምጡቀ ፤ በአእባነ ባሕርይ ዘተነድቀ ፤ ማርያም ደብተራ እንተ ኢትትከደኒ ሠቀ፤` እመቤታችን በ5485 ዓ.ዓ ከአባቷ ከኢያቄም ከእናቷ ከሐና “እም ሊባኖስ ትወጽዕ መርዓት ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች” ተብሎ በተነገረው መሠረት ነሐሴ 7 ቀን ተጸነሰች፡፡

🌿🌿💟 ግንቦት አንድ ቀን ሊባኖስ በምትባል ቦታ በብጽዓት እንደተወለደች የቤተክርስቲያን ታሪክ በሰፊው ያስረዳል፡፡ በጾም በጸሎት በአስተብቁዖት የተገኘች ናት፡፡ ንጽሕት በመሆኗም ማኅደረ ወልድ ሆናለች፡፡

🌿🌿💟 እመቤታችን ከእናትና ከአባቷ ዘንድ ሦስት ዓመት፣ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት፣ 💟ውስተ ቤተ መቅደስ ነበረት በድንግልና። መድኃኔዓለምን በማኀጸንዋ ጸንሳ ዘጠኝ ወር። ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ 33 ዓመት ከሦስት ወር፣ ከዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ዘንድ 14 ዓመት ከዘጠኝ ወር 🌿🌿💟ጠቅላላ ድምር 64 ዓመት ሲሆናት ጥር 21 ቀን በ49 ዓመተ ምሕረት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡
@Sihela_adhno
🌿🌿💟የእረፍቷስ ነገር እንደምን ነው ቢሉስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር 21 እሁድ ቀን ጌታ እልፍ አዕላፋት መላዕክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት፡፡ ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁミ አለችው፡፡ በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል አላት፡፡ እኚህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው፡፡
@Sihela_adhno
🌿🌿💟 ቅድስት ሥጋዋን ከቅስስት ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ ባባ ይዘወት ወደ ጌሰማኒ ሲስደት አይተው ልጇን ተነሳ አረገ እያሉ ሲውኩን ይኖራሉ አሁን ደግሞ እሷን ተነሳች አረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለም ብሎ ኑ እናቃጥላት ተባባሉ፡፡ ከመካከላቸው አንዱ ታውፋንያ ዘሎ ያልጋውን ሸንኮር ያዘ፡፡ የታዘዘው መላእክት መጥቶ በሰይፍ ሁለት እጁን ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት ድኖለታል፡፡ ከዚህ ቦሃላ ዮሐንስን ጨምሮ ከመካከላቸው ነጥቆ በእጸ ሕይወት ሥር አኑሯታል፡፡
@Sihela_adhno
🌿🌿💟 አንድም በዓሉ-፡ እግዚአብሔር ወልድ በሰውነት ተወልዶና ማንነቱ በይፋ ታውቆ በተገለጠበት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር የ“አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል፡፡ አስቀድመው አሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ሁሉ ተበትነው ነበርና በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ሁሉም ደመናን ጠቅሰው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ መርቶ አመጣቸው እንጂ ለምን እንደመጡ አያውቁም ነበር፡፡ እመቤታችንም ለምን እንደመጡ ጠየቀቻቸው፡፡
@Sihela_adhno
🌿🌿💟 ቅዱስ ጴጥሮስም፡- “ጸጋን የተመላሽ ቅድስት ሆይ! የመምጣታችን ምሥጢርማ እኛ አንቺን እንጠይቅ እንጂ አንቺም እኛን ትጠይቃለሽን? ሁላችንም ለምን እንደመጣን አናውቅም፡፡ ለምሳሌ እኔ አስቀድሜ በአንጾክያ ነበርኩኝ አሁን ግን እነሆ እዚህ ነኝ፡፡ ለምን እንደመጣሁኝ ግን አላውቅም” አላት፡፡ እርሷም ሁሉም በአጠገቧ በተሰበሰቡ ጊዜ የሚሆነውን ነገር አስቀድማ ከልጇ ከወዳጇ አውቃ ተዘጋጅታ ነበርና ለምን እንደመጡ (ዕረፍተ ሥጋዋን ለማየት እንደሆነ) ነገረቻቸው፡፡ ሌሊቱንም በሙሉ በጸሎትና በማኅሌት ደግሞም በዝማሬ ሲያመሰግኑ አደሩ፡፡

🌿🌿💟 ከዚህ በኋላ የተወደደችው እናት በረከቷን አሳድራባቸው በሰላም አንቀላፋች፡፡ ነፍሷም በዐብይ ዕልልታና በታላቅ ምስጋና በመላእክት እጅ ወደ አምላኳ ሄደች፡፡ ኋላ ሐዋርያቱ ዮሐንስን ሲያገኙት፡- “እመቤታችን እንደምን ሆነች?” አሉት፡፡ እርሱም “በገነት በዕጸ ሕይወት ሥር ዐርፋለች” አላቸው፡፡ የቀሩት ሐዋርያት “ዮሐንስ ያን ድንቅ የእግዚአብሔርን ሥራ አይቶ እኛስ ሳናይ እንዴት እንቀራለን?! አቤቱ ለእኛም ቸርነትህን አድርግልን” ብለው በነሐሴ መባቻ በአንድነት ሆነው ወደ ፈጣሪያቸው የሚቀርብ የአንድ ሳምንት ጾምና ጸሎት ጀመሩ፡፡
@Sihela_adhno
🌿🌿💟በሁለተኛው ሱባዔ ማብቂያ ዕለት ነሐሴ 14 ቀን እሑድ የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ መልአኩ ከገነት አምጥቶ ለሐዋርያቱ ሰጣቸው፡፡ እነርሱም ልመናቸው ስለ ተፈጸመላቸው ፈጣሪያቸውን በጸሎት አመስግነው በዚያችው ዕለተ እሑድ ቅዱስ ሥጋዋን ወስደው ቀብረውታል፡፡ እርሷም በሦስተኛው ቀን ነሐሴ 16 ቀን ማክሰኞ ተነሥታለች፡፡ ትንሣኤዋ “ከመ ትንሣኤ ወልዳ- እንደ ልጇ ትንሣኤ” ያሰኘው ይህ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይታ የመነሣቷ እውነታ ነው፡፡@Sihela_adhno

የአዛኚቱ ድንግል አማለጅነትና በረከት አይለየን፡፡ ሁላችንም ባለንበት ይህ ታላቅ በዓሏን እያሰብን ጸልየን የበረከቷ ተካፋዮች እንሆን ዘንድ ልዑል እግዚአብሔር ይርዳን አሜን አሜን አሜን በዓሉን በዓለ ሠላም ወሐሴት ያድርግልን

መልካም በዓል !!
@Sihela_adhno
?👇👇👇👇👇👇
@Sihela_adhno
@Sihela_adhno
አዲስ አለም ማርያም👇👇👇