የእመቤታችን ተምሳሌት እና ስም ከነ ጥቅሱ ========~~~==============
1|የማክሰኞ እርሻ ~[ዘፍ 1፡10-13]
2|የኖህ እርግብ ~[ዘፍ 7፡2-3 ኩፍ 6፡28]
3|የኖህ እርግብ ~[ዘፍ 8፡6]
4|የኖህ ቀስተ ደመና ~[ዘፍ 9፡8-15 ]
5|የሌም ድንካን ~[ዘፍ 9፡27]
6|የአብርሃም ድንካን ~[ዘፍ 18 ፡1-15]
7|የአብርሃም እፀሳቤቅ ~[ዘፍ 22፡9]
8|የአብርሃም እርሻ ~[ዘፍ 23-17:-20]
9|የያቆብ መሰላል ~[ዘፍ 28 ፡ 10 -12] 10|የሙሴ ሐመልማል ~[ዘፀ 3፡1-5] 11|የሲና ተራራ ~[ዘፀ 31፡18]
12|የሙሴ ታቦት ~[ዘፀ 32፡1-2]
13|የአሮን በትር ~[ዘሁ 17፡1-8]
14|የእያሱ ሐወልት ~[ኢያ 24፡25]
15|የጌዲዎን ፀመር ~[መሣ 6፡36-40]
16|ሳሙኤል የሽቶ ቀንድ ~[1ኛ ሳሙ 16፡13]
17|የዳዊት መሰንቆ ~[1ኛ ሳሙ 16፡14-23]
18|የአሚናደብ ሰረገላ ~[2ኛ ሳሙ 6፡3-4]
19|የኤልያስ ደመና ~[1ኛ ነገ 15 ፡ 14 -46]
20|የኤልሳዕ ማሠሮ ~[2ኛ ነገ 2፡ 19 -22]
21|የኤልያስ መሶቦወርቅ ~[1ኛ ነገ 19፡1-8]
22|የሰለሞን አክሊል ~[መ13 ፡11]
23|የእየሩሳሌማዊት ፅዩን ~[ኢሳ 2፡3 - መዝ 131 ፡13]
24 |የእሴይ በትር ~[ኢሳ 11፡1]
25|አቤል ደነት ~[ዘፍ 4፡2]
26|የኢሳያስ ደመና ~[ኢሳ 19፡1]
27|ኤደምያስ ~[ኢሳ 63 ፡1]
29|የፋራን ተራራ ~[ዕን 3፡3]
30|የዳዊት መስክ ~[መዝ 72 ፡2]
31|ሴት ~[ዘፍ 3፡15 -ዩሐ 2፡2,ዩሐ 19 ፡25]
32|ድንግል ~[ኢሳ 7፡14]
33|የኢየሱስ እናት ~[ዩሐ 2፡2,ዩሐ 19፡25]
34|ማርያም ~[ማቴ 1፡ 18]
35|የጌታዬ እናት /እመቤቴ /~ሉቃ 1፡431]
36|የጌታዬ ዙፋን ~[ኢሳ 6፡1]
37|የወርቅ መሶበወርቅ ~[ዕብ 9፡4]
38|የእግዚአብሔር ከተማ ~[መዝ 86፡1 -ኢሳ 60፡14]
39|ሙሽራ [መዝ 18 ፡5] 40ክርስትያኖች እናት ~[ዩሐ 19፡25] {ምልጃና በረከቷ አይለየን አሜን።}
@embrhan_lijoch

ልባም ሴት (Lebam Set) በመ_ር ዶ_ር ዘበነ ለማ (Memeher Dr. Zebene Lemma)
<unknown>
AUD-20181009-WA0044
<unknown>
🌿🌿🌿🌿🌿🌿
++ ‹‹እግዚአብሔር ያስታውሳል›› ++
በሉቃስ ወንጌል መጀመሪያ ላይ ታሪኩ ተመዝግቦ የሚገኘው የመጀመሪያው ቤተሰብ የካህኑ ዘካርያስ ቤተሰብ ነው፡፡ በወንጌል መጀመሪያ ላይ የምናገኘው ይህ ካህን (በኦሪት መጀመሪያ ላይ እንደሚገኘው ካህን እንደ አሮን ሁሉ) የሚስቱ ስምዋ ኤልሳቤጥ ነው፡፡ (ዘጸ. 6፡23) ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ‹በሰው ፊት ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ› የሚሔዱ ሲሆን ልብንና ኩላሊትን በሚመረምረው ‹በእግዚአብሔር ፊት ደግሞ ጻድቃን ነበሩ› ይላል ወንጌሉ፡፡
ካህኑ ዘካርያስ እና ሚስቱ ኤልሳቤጥ እንደማንኛውም ባልና ሚስት ልጅ ለመውለድ የተመኙት በወጣትነታቸው ጊዜ ነበር፡፡ በተለይም ክህነት በዘር ሐረግ ብቻ በሚተላለፍበት በዚያ ዘመን ከአሮን የልጅ ልጅ ከአብያ ቤተሰብ የሆነው ዘካርያስ ወንድ ልጅ ወልዶ ልጁ እሱ በሚያገለግልበት መቅደስ ተተክቶ እንዲያገለግል ይመኝ ነበር፡፡ ይሁንና ሚስቱ ኤልሳቤጥ መካን ነበረች፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስረዳን መካንነት በወንድም በሴትም ሊከሰት ይችላል፡፡ ‹‹የተባረክህ ትሆናለህ ፤ በሰዎችህም ሆነ በእንስሳትህ ዘንድ ሴት ብትሆን ወይም ወንድ መካን አይሆንብህም›› የሚለው ቃል መካንነት በወንድም ሊከሰት እንደሚችል ያስረዳናል፡፡ (ዘዳ. 7፡14) በመጽሐፍ ቅዱስ ሰባት መካን ሴቶች ተጠቅሰዋል፡፡ እነዚህም ሣራ ፣ ርብቃ ፣ ራሔል ፣ አንትኮዬ (የሶምሶን እናት) ፣ ሃና (የሳሙኤል እናት) ፣ ሜልኮል እና ኤልሳቤጥ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ሰባት መካን ሴቶች ውስጥ ያልወለደችው የዳዊት ሚስት የሳኦል ልጅ ሜልኮል ብቻ ስትሆን ያልወለደችበት ምክንያት መካንነትዋ የመጣው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት የሚዘምረው ባልዋን ዳዊትን ስለናቀችውና አሽሙር ስለተናገረች ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ልጅ ባለመውለድ የተጠቀሰችው ሌላ ሴት ሱነማዊቷ ሴት ስትሆን ያለመውለድዋ ምክንያት በባልዋ ሽምግልና ምክንያት እንጂ በእርስዋ አለመሆኑ አብሮ ተጽፎአል፡፡ (2ነገሥ. 4፡14)
ኤልሳቤጥ ልጅ ካለመውለድዋ ይልቅ ትልቅ ስቃይ የሆነባት የሰዎች ነቀፌታ ነበር፡፡ በዚህ መሰቃየቷን የምንረዳው ከጸነሰች በኋላ እንኳን ጸነስኩ ብላ ለመናገር ተሳቅቃ አምስት ወራት ያህል ጽንሱን መሰወርዋ ነው፡፡ በእርግጥም ብዙዎች ከመካንነት በላይ ስቃይ የሚሆንባቸው የሰዎች ክፉ ንግግር ነው፡፡‹መቼ ነው የምትወልዱት?› ‹ትዳር ያለ ልጅ እንዴት ይሆናል?› ‹እስካሁን አልወለድሽም?› እየተባሉ በጥያቄ የሚቆስሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ አልፎ ተርፎም በአሽሙር የሚሰደቡ ፣ በነገር ጅራፍ የሚገረፉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የምትሆነን ጣውንትዋ ፍናና ታስቆጣትና ታበሳጫት የነበረችው ሃና ናት፡፡ ሃና ባለመውለድዋ በሚደርስባት ነቀፋ ምክንያት እህል እንኳን አስጠልቷት አትቀምስም ነበር፡፡ ደግነቱ ባልዋ ሕልቃና አለመውለድዋን አይቶ አልናቃትም ይልቁንም ‹‹ለምን ታዝኚአለሽ? ለምንስ እህል አትቀምሺም? ከአሥር ልጆች እኔ አልሻልሽም?›› ብሎ የሚያጽናና መልካም ባል ነበረ፡፡ (1ሳሙ. 1፡4-8)
ኤልሳቤጥም የገጠማት ይህ ዓይነቱ ፈተና ነው፡፡ መካን መሆንዋ ብቻ ሳይሆን የሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ሚስት ሆና አለመውለድዋ የበለጠ ፈተና ነበር፡፡ ሰው መቼም በሰው ለመፍረድ ብዙ አይቸገርም፡፡ ‹ባልዋ በቤተ መቅደስ እያገለገለ እግዚአብሔር ልጅ የነሣቸው ክፉዎች ቢሆኑ ነው እንጂ›› ብሎ ማሰቡም አይቀርም፡፡ ዘካርያስ ካህኑ ግን በሚስቱ በኤልሳቤጥ ላይ አንዳች ክፉ ቃል አልተናገረም ፤ ተናግሮ ቢሆን ኖሮም ‹ሁለቱም ጻድቃን ነበሩ› ባልተባለለት ነበር፡፡ የሚገርመው ዘካርያስ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ፊት እንኳን ‹እኔ ሽማግሌ ነኝ ፤ ሚስቴም አርጅታለች› አለ እንጂ ስለ ‹ሚስቴ መካን ናት› ብሎ አንዲትም ቃል አልተናገረም፡፡
እነዚህ ጻድቃን ባልና ሚስት ልጅ ተመኝተው ባያገኙም ‹ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ› ይላል፡፡ ልብ አድርጉ ልጅ ሳይኖራቸው ፣ በኑሮአቸው ደስተኛ ሳይሆኑ በፈጣሪ ሕግና ትእዛዝ መሔድ መቻላቸው በጣም ከባድ ነው፡፡ በሰው ፊት ፈጣሪን ላለማማረር የሆዳቸውን በሆዳቸው ይዘው በውስጣቸው ሊሳደቡ አልሞከሩም፡፡ ‹‹ምነው ፤ ምን አደረግንህ?›› እንኳን ብለው ፈጣሪያቸውን አልወቀሱም፡፡ በስቃይ ውስጥ ሆነው እንኳን ልብን በሚመረምረው አምላክ ፊት ‹ጻድቃን ነበሩ›፡፡ ቤት በልጆች ሳቅ ተሞልቶ ፣ ጤንነት ተሟልቶ ፣ ሀብት ንብረት ሳይጎድል እግዚአብሔርን ማምለክ ብዙ ላያስቸግር ይችላል ፤ በማጣት ፣ በመከራ ፣ በመሰደብ ውስጥ እየኖሩ ጻድቅ ሆኖ መገኘት ግን እጅግ አስደናቂ ነው፡፡
ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ ለመውለድ ፈጣሪን ሲማጸኑ ቢኖሩም የወጣትነታቸው ዘመን ግን አለፈ፡፡ ኤልሳቤጥ የሆድዋን ፍሬ ሳትመለከት ፣ ዘካርያስ የአብራኩን ክፋይ ሳያይ ፣ እንደ ካህናት ልማድ ልጁን ለቤተ መቅደስ አገልግሎት ሳይተካ ሁለቱም አረጁ፡፡ ‹‹እባክህ ፈጣሪ ሆይ ልጅ ሥጠን›› ብለው እየለመኑ ዓመታት አለፉ፡፡ ከብዙ ዓመታት በኋላ ግን ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ‹ዘካርያስ ሆይ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ልጅን ትወልድልሃለች› አለው፡፡ ዘካርያስ ግራ ገባው ፤ ከጸለየው ዓመታት ያለፈው ጸሎቱን ፣ ከተመኘው ዘመናት ያለፈው ምኞቱን አሁን ‹ተሰምቶልሃል› ሲባል ለደስታ አቅም አጠረው፡፡
ነቢዩ ዳንኤል ፈጣሪውን ሲለምን ወዲያው መልስ አልመጣለትም ነበር ፤ ከሃያ አንድ ቀን በኋላ ግን ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ‹ሰይጣን ከመንገድ አዘግይቶኝ ነው እንጂ ወደ አንተ የተላክሁት በዕለቱ ነበር› አለው፡፡ ዳንኤልም ሃያ አንድ ቀን ቢዘገይም እንኳን ገና ጸሎቱን አላቋረጠም ነበርና ከሦስት ሳምንት በኋላ የጸሎቱን መልስ ማግኘቱ ብዙም ግራ አላጋባውም፡፡ (ዳን.10፡12) ቅዱስ ገብርኤል ወደ ዘካርያስ መጥቶ ‹ጸሎትህ ተሰማ› ያለው ግን እንደ ዳንኤል ከሃያ አንድ ቀን በኋላ አይደለም፡፡ ከሃያ አንድ ዓመታት በኋላም እንኳን አይደለም፡፡ ዘካርያስ ሽማግሌ እስኪሆን ፣ ኤልሳቤጥም እስክታረጅ ድረስ ቆይቶ የወጣትነት ዘመኑን ጸሎት ነው ‹ተሰምቶልሃል› ያለው፡፡ ስለዚህ ዘካርያስ ‹ስእለቴ ሰመረ› ለማለት እንኳን ግራ ተጋባ፡፡
እግዚአብሔር አሠራሩ እንዲህ ነው ‹‹እርሱም አይዋሽም ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገሠው እርሱ አይዘገይም።›› ተብሎ እንደተጻፈ እግዚአብሔር መልስ የሚሠጥበት ጊዜ በሰው ሕሊና የሚመረመር አይደለም፡፡ (ዕን. 2፡3) የለመንነውን ነገር ሳያደርግልን ልናረጅ ፣ ልንሸመግል እንችላለን፡፡ ከዚያም አልፎ የተመኘነውን ነገር ሳይሠጠን ልንሞትም እንችላለን፡፡ ፈቃዱ ከሆነ ግን የጸሎታችንን መልስ ከመቃብር ቀስቅሶ ሊሠጠን ይቻለዋል፡፡ ይህን የማያምን ሰው ሙሴን መጠየቅ ይችላል፡፡
ሙሴ እግዚአብሔርን ‹ክብርህን አሳየኝ› ብሎ ለመነ ፤ እግዚአብሔርም ‹‹በዓለት ላይ አቆምሃለሁ ... ጀርባዬን ታያለህ ፊቴን አታይም›› ብሎ መለሰለት፡፡ ሙሴ ይህን እግዚአብሔርን ሳያይ ወደ መቃብር ወረደ፡፡ ሊሞት ሲል እንኳን ‹ያልከኝን ሳታሳየኝ› ብሎ ሳይጠይቅ የዋሁ ሙሴ ወደ መቃብር ገባ፡፡ በመቃብር ውስጥ ሆኖ በሺህ የሚቆጠሩ ዓመታት አሳለፈ፡፡ ከዘመናት በኋላ ግን ሙሴ በታቦር ተራራ ዓለት ላይ እንዲቆም ተጠራ፡፡ ‹ክብርህን አሳየኝ› ብሎ ለለመነው ልመና መልስ ተሠጠው፡፡ በታቦር ተራራ ‹አንድ ልጅም በአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር ያለውን ክብሩን አየ› የብሉይ ኪዳን ሰው ሆኖ ሳለ የሐዲስ

ኪዳን ዕድል ደረሰው፡፡ እኛ ሰው ሆኖ ያየነውን እግዚአብሔርን አየው፡፡ (ዘጸ.33፡18-23፤ማቴ.17፡3፤ዮሐ.1፡14) እግዚአብሔር ከመቃብር ቀስቅሶ ለጸሎት ምላሽ የሚሠጥ ከሆነ ለዘካርያስ በእስተርጅናው መልስ ቢሠጠው ምን ያስደንቃል?
እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ እናንሣ፡፡ እግዚአብሔር ለካህኑ ዘካርያስና ለሚስቱ ኤልሳቤጥ ልጅ መሥጠቱ ካልቀረ ለምን ወዲያው አልሠጣቸውም? ‹ልጅ በልጅነት ነው› እንደሚሉት ብሂል በልጅ አምሮት በተሰቃዩበት እና በደስታ ሊያሳድጉ በሚችሉበት ጊዜ ልጅ መስጠት እየቻለ አምሮታቸው ከጠፋና ተስፋ ከቆረጡ በኋላ መሥጠቱ ለምንድን ነው? ሽማግሌው ዘካርያስ ልጁን ሮጦ በማያጫውትበት ፣ እንደልቡ በማያዝልበት ፣ ወደ ቤተ መቅደስም ወስዶ በሙሉ ጉልበቱ ሥርዓቱን ለልጁ በማያስተምርበት በእርጅና ዘመኑ ፈጣሪ አምጥቶ ልጅ መሥጠቱ ለምን ይሆን? አንዳንድ ሰው እንደሚለው ‹ፈጣሪ ካላጣው ጊዜ› ምነው ቀደም አድርጎ ቢሰጣቸው? አይችልም ነበር?
ይችላል! ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም፡፡ ወጣት እያሉ ልጅ ሊሠጣቸው ይችላል፡፡ ያዘገየው ግን በሌላ ምክንያት ነው፡፡ እነዚህ ባልና ሚስት በወጣትነታቸው ቢወልዱ ኖሮ ልጅ አግኝተው ይደሰቱ ነበር፡፡ ዘካርያስም በእግሩ የሚተካ ካህን ያገኝ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ግን ለእነዚህ በሕጉና በትእዛዙ ለሔዱ በፊቱ ጻድቃን ሆነው ለተገኙ ባልና ሚስት እንደማንኛውም ሰው ‹ልጅ› ብቻ ሊሠጣቸው አልፈለገም፡፡ ‹‹ከሴቶች ከተወለዱት ሁሉ ከእርሱ የሚበልጥ ማንም አልተነሣም›› ተብሎ በጌታ የተነገረለትን ፤ ነቢይ ፣ ሐዋርያ ፣ ባሕታዊ ፣ ሰባኪ ፣ ካህን ፣ ሰማዕት ሊሠጣቸው ፈለገ፡፡ በኦሪት መቅደስ የሚያጥን ሳይሆን በባሕር መካከል አምላኩን የሚያጠምቅ ቅዱስ ልጅ ሊሰጣቸው ፈለገ፡፡ ከእናቱ ማኅጸን ስብከት የሚጀምር ከሞተም በኋላ ስብከቱ ከዳር ዳር የሚሰማ መምህር ፣ የሙሽራው ክርስቶስ ሚዜ ፣ ከፀሐይ በፊት ያበራ ጨረቃ ፣ ከቃል መምጣት በፊት የተሰማ ድምፅ ፣ በመወለዱ የብዙዎች ደስታ ምክንያት የሆነ ዮሐንስን ሊሠጣቸው ፈለገ፡፡ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን ለመውለድ ጌታ ሊወለድ ስድስት ወር እስኪቀረው ድረስ መጠበቅ ነበረባቸው፡፡ ‹ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ የሠራ› እግዚአብሔር በኀዘን ድባብ የኖረውን የእነዚህን ጻድቃን ቤት ዳግም በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ልጅ ለመውለድ ከሆነስ እንኳንስ ማርጀት መሞትም አያስቆጭም፡፡
አንድ ነገር እንጨምር፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ለዘካርያስ ‹ጸሎትህ ተሰምቶልሃል› ሲለው ዘካርያስ የደነገጠው ከጊዜው ርዝመት የተነሣ ተስፋ ቆርጦ ጸሎቱን ዘንግቶት ስለነበር ነው፡፡ ዘካርያስ የጸለየውን ጸሎት ቢረሳውም እግዚአብሔር ግን አልረሳውም፡፡ ዘካርያስ ማለት የስሙ ትርጉም ‹እግዚአብሔር ያስታውሳል› ማለት ነው፡፡
የጻድቃን ወላጆቹ እና የመጥምቁ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁንልን፡፡ ቅዱስ ያሬድ ‹ዮሐንስ እዴከ መጥወኒ› ‹ዮሐንስ እጅህን ሥጠኝ› እንዳለ መድኃኔዓለምን ባጠመቁ ቅዱሳት እጆቹ ሁላችንን ይባርከን ዘንድ ጸሎታችን ነው።
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
┏━━° •❈• ° ━━┓
@Embtee
@Embtee
@Embtee
┗━━° •❈• ° ━━┛

AUD-20181011-WA0102
<unknown>
AUD-20181016-WA0112
<unknown>
ቅዱሳን_ስዕል_ለምን_እንጠቀማለን___—_በዲ_ን_ሄኖክ_ኃይሌ
<unknown>
AUD-20181024-WA0126
<unknown>