ELOHIM LIFE CHANNEL(ELC)
407 subscribers
2.43K photos
82 videos
127 files
405 links
ይሄ የክርስቲያን ቻናል የተከፈተበት አላማ ክርስቲያኖችን ላቅ ወዳለና ተጽዕኖ ወደሚፈጥር ሕይወት ለማምጣት ነው።በዚህ ቻናል ውስጥ የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ።

ከእነዚህም ውስጥ
፦የአዕማድ ሰዎች ንግግሮች
፦ከታማኝ ምንጭ የተገኙ ዜናዎች
፦የድሮም የአሁንም አዳዲስ ዝማሬዎች
፦ህይወት ለዋጭ፣የሚያንጽ ስብከቶችና ትምህርቶች ስነጽሁፎች፣ታሪክና ምሳሌዎች።
https://youtu.be/-bmaoih
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።”
— ፊልጵስዩስ 4፥13
የእምነት ጉዞ እግዚአብሔር በሚሰጠን የጸጋ መግቦት የምንሄደው እንጂ በግል ጥረት የምንሄድበት አይደለም።እግዚአብሔር አትፍራ ካለህ ሣትፈራ የምትጓዝበትን ጸጋ ይሰጥሃል፣አትደንግጥ ካለህ በሚያስደነግጥ ነነር ውስጥ ሳትደነግጥ የምትሄድበት ጸጋ ሰጥቶሃል ማለት ነው፣እግዚአብሔር ሰው አይደለምና እርሱ ያስጀመረህን ጉዞ በራስህ ጨርሰው አይልም።ዳዊት እንዲህ ይላል ከንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም።በልዑል መጠጊያ ውስጥ የምትኖር ከሆነ ስለምንም ነገር መፍራት አይጠበቅብህም፤ምክንያቱም አንተ የእርሱ ነህ።
#share
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
ሮሜ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦
¹¹ ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ፤ አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፤ ሁሉ ተሳስተዋል፥


²³ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤

“የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።”
— ሮሜ 6፥23
#share
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
የሕይወት ቁራሽ

ጆናታን ኤድዋርድስ በአሜሪካ ግዛት ታላቁን መንፈሳዊ መነቃቃት የጀመረው በፍርድ የተያዘ ጊዜ ነው። "ሰዎች ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር እንዲኖሩ ተወስኗል" ሲል በአስራ ዘጠኝ ዓመቱ በማስታወሻው ላይ ጻፈ። ከዚያም “ሌሎች ይህን(ለእግዚአብሔር ክብር ቢኖሩም ባይኖሩ) ቢያደርጉም ባያደርጉም እኔ አደርገዋለሁ ብዬ ወስኛለሁ” ሲል ጨመረ። ጆናታን ኤድዋርድስ በታላቅ ፍርድ ተፈረደበት።

ዊልያም ቡዝ በንጉሥ ኤድዋርድ ሰባተኛ አውቶግራፍ አልበም ላይ እነዚህን ቃላት ጻፈ፣ "የአንዳንድ ሰዎች ምኞት ጥበብ ነው፣ የአንዳንድ ሰዎች ምኞት ዝና ነው፣ የአንዳንድ ሰዎች ምኞት ወርቅ ነው። የእኔ ምኞት የሰዎች ነፍስ ነው።"

ፓዴሬቭስኪ ብዙ ጊዜ ሙዚቃን በትክክል ለመጫወት ከሚሰራው ስራ በፊት አርባ ወይም ሃምሳ ጊዜ ይጫወት ነበር። በንግስት ቪክቶሪያ ፊት ከተጫወተ በኋላ "ሚስተር ፓዴሬቭስኪ እርስዎ ሊቅ ነዎት" የሚለውን የውዳሴ ቃል ተቀበለ። ፓዴሬቭስኪ "ይህ ሊሆን ይችላል ነገር ግን አዋቂ ከመሆኔ በፊት እኔ የሙዚቃው ባሪያ ነበርኩ።"አላቸው።ይሄንንም ያለው ውስጡ የአሁኑን ሳይሆን ለዚህ ያበቃውን የህይወት መንገድ ስለሚያይ ነው።

እነዚህ ሶስት ሰዎች በሕይወታቸው ካለፉበት ነገር የተነሣ እነዚህን ጠንካራ መርህ ተምረዋል።እኛስ መከራው አጥፍቶናል ወይስ በጥንካሬ አልፈነው ለመናገር፣ለመተረክ በቅተናል።
#share
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
እንኳን ከአረጀው አዲስ ወደሆነው አመት ተሸጋገራችሁ🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
🌻🌻 መልካም 🌻🌻️
🌻🌻 አዲስ 🌻🌻
🌻🌻 ዓመት 🌻🌻️
🌻️🌹🌾🌻💐🌷🌻🕊🌻🌻🌻🌻🌻️🕊
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌺 መልካም 🌺🌻
🌻🌻 በዓል! 🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻💐💐💐🌻🌻
🌻🌺 እንኳን 🌺🌻
🌻🌹አደረሳችሁ🌹🌻
🌻🌻🌾🌾🌾🌻🌻🌻🌻💐💐💐🌻🌻🌺🌻🌺🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌺 “መከራህንም ትረሳለህ፤🌺🌻
🌺🌻 እንዳለፈ ውኃ ታስበዋለህ።”🌺🌻
🌺🌻— ኢዮብ 11፥16 🌺🌻
🌻🌹 🌹🌻
🌻🌻🌾🌾🌾🌻🌻
እንደንጋት ብርሃን በጸጋው እየጨመርን ምንሄድበት አመት 2016🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
#ሼር
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
በአዲስ አመት አዲስ ዜና
"ኢየሱስ" የመዝሙር አልበም
ዘማሪ ይድነቃቸው ተካ
#ሼር
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
አንበሶች ሊያጡ፣ሊራቡ ይችላሉ፤እግዚአብሔርን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጎልባቸውም።
መዝ 34፡10
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
ዘጸአት 20
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።
⁴ በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
አራት ምስሎች ነገር ግን ይሄ ሁሉ የአንዷ ሴት ምስሎች ናቸው።ሰይጣን ውሸታም ነው፣ያማረብን ያህል እንዲሠማን ያደርጋል፣አንዳንድ ዘመናዊነቶች ሰይጣናዊ ናቸው።ሁሉን ነገር እያስተዋልን እየመረመርን እናድርግ።
#ሼር
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
#የመስቀል_በዓል_እውን_መጽሐፍ
#ቅዱሳዊ_ነውን?
==================================
✍️የመስቀል በዓል በአብዛኛው በክርስትናው አለም ያልተለመደ ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በጥንት የቤተክርስቲያን ታሪክ የማይታወቅና እውቅና የለውም ነው።

✍️ መስቀል ሲነሳ መነሳት ያለበት እንጨቱ ሳይሆን የተሰቀለው ጌታና የመጣበት አላማ ሊሆን ይገባል። የተሰቀለውን ጌታና የመጣበትን አላማ ስተን የተሰቀለበት እንጨት ላይ ትኩረት ብናደርግ ሐይማኖታዊ ስርአትን ከመፈጸም ውጭ ደህንነትን ልንካፈል አንችልም።
ከዚህ የተነሳ ሁላችንም ወደ መጽሐፍ ቅዱሱ ሀሳብ በትህትና ልብ ልንመለስ ያስፈልገናል።

1 ቆሮንቶስ 2፡15፤
መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል

ዮሐንስ 8 (John)
32፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።

📌የመስቀል ፍቺ:-
----------------
Greek: σταυρός
Transliteration: staurós
Pronunciation: stow-ros'
በጥንቱ ገጽ የግሪክኛ ቋንቋ ይህ “መስቀል ተብሎ የተተረጐመው ቃል [ስታዉሮስ ] ማንኛውም ነገር የሚሰቀልበትን ወይም [ለአጥር የሚሆንን] እንጨት ወይም ቀጥ ያለ ምሰሶ ወይም ግንድ ያመለክታል።

(Cross) “ክሮስ” የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል የተወሰደው "ክሩክስ" ከሚለው የላቲን ቃል ሲሆን
በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች “መስቀል” (“የመከራ እንጨት” ) ተብሎ የተተረጐመው ነው።

📌የመስቀል አይነቶች ፦
-----------------
👉1) ክሩክስ ኢሚሳ (ተ) = (Crux immissa) የላቲኖች መስቀል
👉2) ክሩክስ ኳዳርታ (+) = (Crux quadrata) የግሪኮች መስቀል
👉3) ክሩክስ ኮሚሳ (Crux commissa) (T) =ወይንም በተለምዶ የቅዱስ አንቶኒ መስቀል
(St. Anthony’s cross) ተብሎ ይጠራል፡፡
👉4) ክሩክስ ዲኩሳታ (Crux decussate) (X)= ወይንም በተለምዶ የቅዱስ እንድርያስ መስቀል (St.Andrew’s cross) ተብሎ ይጠራል።

📌መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል??
-------‒-----------------
1 ቆሮንቶስ 1፡18
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።.....
23፤ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ኃይል የሚለው የመስቀሉን ቃል እንጂ የመስቀሉን እንጨት(ቅርጽ) እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባናል።

አንድ ሰው ሆዱን ቢታመም እና ሽሮፕ ቢታዘዝለት የሚያድነውን ሽሮፑን ደፍቶ ጠርሙሱን ያድናል ቢልና ይዞት ቢዞር ከበሽታው ሊፈወስ አይችልም። እንዲሁ የተሰቀለው ጌታ እንጂ የተሰቀለበት እንጨት ሊያድነን አይችልም።

📌በተሰቀለው በ ኢየሱስክርሰቶስ የተቆጠሩልን በረከቶች፦
====================================
መጽሐፍ ቅዱስ በ1ኛ ቆርንቶስ 1፣23 ላይ " እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን" ይለናል።

ከዚህም የተነሳ በሰቀለው በኢየሱስ ክርስቶስ፦
👉የእግዚአብሔር ልጆች ሆነናል ዮሐ 1:12
👉-በተሰቀለው ደህንነት አግኝተናል። ዮሐ3:14-18
👉-በተሰቀለው ከሞት ወደ ሕይወት ተሻግረናል። ዮሐ 5:24
👉-በተሰቀለው ዘላለማዊ ስርየት አግኝተናል።ዕብ 9:22

👉-በተሰቀለው ለዘላለም ተቀድሰናል።ዕብ 10:10
👉-በተሰቀለው የዘላለም ፍጹማን ሆነናል። ዕብ 10:14
👉-በተሰቀለው የእድሜ ዘመን የሀጢያት ስርየት አግኝተናል ። ዕብ 10:17-18,ሮሜ4:5-6
👉- በተሰቀለው ከሕግ ርግማን ነጻ ወጥተናል ገላ3:13
👉-በተሰቀለው ከኩነኔ አምልጠናል። (ሮሜ 8:1)
👉-በተሰቀለው ከኃ ጢያትና ከሞት ሕግ ነጻ ወጥተናል። (ሮሜ 8፡2)።

📌መስቀል ሲነሳ መነሳት ያለበት እንጨቱ ሳይሆን የተሰቀለው ጌታና የመጣበት አላማ ነው። የተሰቀለበት እንጨት ላይ ትኩረት አድርገን የተሰቀለውን ጌታ አላማ ብንስት ሐይማኖታዊ ስርአትን ከመፈጸም ውጭ ደህንነትን ልንካፈል አንችልም።
የተሰቀለውን ጌታ እንጂ የተሰቀለበትን አንሰብክም
የተሰቀለበት እንጨት ከተሰቀለው ጌታ አላማ ውጭ ምንም ነው።

✍️1 ቆሮንቶስ 1 (1 Corinthians)
18፤ የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።

✍️1 ቆሮንቶስ 1 (1 Corinthians)
23፤ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥

ዮሐንስ 8 (John)
32፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።

ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ለሁላችንም ይብዛ።

የወንጌል እውነት ቤተክርስቲያን ጅማ
Gospel Truth church Jimma.
ከሚጠቀለለው ነገር በላይ የሚጠቀለልበት ሚያሳስበው አምላክ አለን
=========================================================
እዚህ ምድር ላይ ማንም ምንም ልትሆን ትችላለህ።ደግ ሰው፣ሀብታም ሰው፣ደሀ ሰው፣ባለጠጋ፣ታዋቂ፣ወታደር፣ማናጀር የትኛውም ነገር ልትሆን ትችላለህ።እግዚአብሔር ይሄም ያም የትኛውም ነገር ትኩረቱን አይስበውም።እግዚአብሔር ጉዳዩ ከእኛ የሆነ ነገር ጋር አይደለም።እግዚአብሔር እኛ ከሆንነው በላይ ልጁ በእኛ ውስጥ እኛም በእርሱ ውስጥ መኖራችን ግን ለእርሱ ዋና ነገር ነው።

ብዙ ጊዜ ለስጦታ፣ለሽልማት፣ለልደት፣ለሰርግ ይዘን የምንሄደውን ዕቃ በስጦታ መጠቅለያ ጠቅልለን ይዘን እንሄዳለን፤ምክንያቱም ይዘን የምንሄደውን ዕቃ ስጦታ ወይም ሽልማት ተቀባዩ ከፍቶ እንዲያየው ስለምንፈልግ።እግዚአብሔርም እንዲህ ነው ምንም ልትሆን ምንም ልታደርግ ትችላለህ ነገር ግን ያንን መልካም ስራህን፣የሆንከውን ነገር አለማትን በፈጠረበት በልጁ ደግሞ አለምን የሚጠቀልለው በክርስቶስ በአንድያ ልጁ ስለሆነ ፍጥረት ሁሉ በልጁ እንዲጠቀለል ይፈልጋል።

እግዚአብሔር ያንን መጠቅለያ ፈቶ ማየት ይፈልጋል።ልጅነት፣ጽድቅ፣ቅድስና፣መልካም ስራ ሁሉ በልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ ነው።ካልተጠቀለልክ እግዚአብሔር ጋር መልካም ስራህ፣ጽድቅህ፣ቅድስናህ መንገድ ላይ ይቀራል እግዚአብሔር ጋር አይደርስም።እግዚአብሔር ከምንጠቀለለው በላይ የምንጠቀለልበት አንድያ ልጁ በእኛ ህይወት ውስጥ እርሱም በእኛ መሆኑ ያሳስበዋል።
========================================================
በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡10
========================================================
ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። የዮሐንስ ወንጌል 3፡17
========================================================
ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን። ዕብራውያን 1፡2
========================================================
#share
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
የእግዚአብሔር ቃል ጠላትን የምትቃወምበት ትልቁ መሣሪያ ነው።
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
"GOSPEL"=
G-For GOD so loved the world, that he gave his
O-Only
S-Begotten SON that whosoever believes in him should not
P-Perish
E-But have EVERLASTING
L-Life

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
For God so loved the world, that he gave his only begotten Son, that whosoever believeth in him should not perish, but have everlasting life.
ዮሐ 3፡16
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
ክርስትናና እስልምና

አንድ ጊዜ ጳጳስ ፍሮድሻም ሚባሉ ሰው እንዲህ ሲሉ ተናገሩ:- “በብዙ የዓለም ክፍሎች ለክርስትና ትልቅ አስተዋጽኦ ካበረከቱት ሰር ዊልያም ማክግሪጎር ጋር በአንድ ወቅት በምዕራብ አፍሪካ ስላለው የእስልምና እምነት ፈጣን እድገት ተወያየን። ክርስትና፡ ‘ይህ ብቻ ነው፡ እያንዳንዱ ሙስሊም ራሱን እንደ ሚሲዮናዊ አድርጎ ይቆጥራል፡ አብዛኛው ክርስቲያኖች ግን የሌላ ሰው ስራ ነው ብለው ያስባሉ።"ብለው አሉ።

እውነት ነው በዚህ ዘመን ክርስቲያኑም አለማዊ አለማዊውም ክርስትያን መስሎ የሚታይበት ድብልቅልቆሹ የበዛበት ዘመን ነው።እስልምና ውስጥ ከአለባበስ ጀምሮ እስላም መሆናቸውን የሚገለጹ ብዙ ነገሮች ያደርጋሉ።ያም ብቻ አይደለም ዊልያም ማክግሪጎር እንዳሉት እስላሞች እራሳቸውን እንደሚሲዮናዊ ወይም እስልምናን ለማስፋፋት እንደተላኩ ያምናሉ።ስለዚህ በመዋለድም ሆነ ከሰው ጋር ባላቸው ግንኙነት ሁሉ ኃይማኖታቸውን ሚሰብኩበት መንገድ ብዙ ነው።ክርስቲያኖች ግን ወንጌል መስበክን ወንጌልን ለሚሰብኩ አገልጋዮች ብቻ የተሰጠ አድርገን ስለምናይ የምስራቹን ለማውራት ያቅተናል።ሁላችንም በያለንበት ሚስዮናዊ የተላኩ ነን።ወንጌል የሁላችንም ስራ ነው።አንድ ለአንድም ሰበክን በጀማም ሰበክን ዋናው የጠፋውን የሰው ልጅ ወደቤቱ ማስገባትና ደቀ መዝሙር ማድረግ ነው።ለዚህ ምን ያህል እንተጋለን?መልሱን ለየራሳችን እንመልሰው።
#የጌታ ጸጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ።
#ሼር
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
"አንተ ጣት ነህ"

አንድ ጊዜ አንድ ወጣት ላልተለወጠና ንስሀ ገብቶ ስለማይመለስ ጎረቤቱ እንዲህ እያለ ይጸልያል "ጌታ ሆይ እባክህ በጣትህ ንካው !" እያለ ይጸልያል።ጌታ እስከሚናገረው ድረስ ይሄንን ጸሎት ይደጋግማል። በመጨረሻም ጌታ ተናገረው "አንተ የእግዚአብሔር ጣት ነህ።ባልንጀራህን ጠርተኸው ስለ መዳን አንዲት ቃል ነግረኸው ታውቃለህ? አሁን ሂድና ጎረቤትህን ጥራውና ንገረው እናም ጸሎትህ ምላሽ ያገኛል።"አለው።ይሄም የእግዚአብሔር አገልጋይ ራሱን ኰነነ ከተንበረከከበት ተነሣ።

"እንግዲህ እድል ባገኘን መጠን ለሰው ሁሉ መልካም እናድርግ።"

አያችሁ ወገኖቼ አንዳንድ ጊዜ ምንጸልየውን አናውቅም።እግዚአብሔር የሆነ ሰው የጸሎት መልስ አድርጎ አስቀምጦን እኛ ግን ሌላ አካል መልስ እንደሆንን እንዲነግረን እንጠብቃለን።አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ድሆችን እንዲባርክ እንጠብቃለን ነገር ግን እግዚአብሔር ድሆችን ሚባርከው በእኛ ነው።የማይታየው እግዚአብሔር በምንታየው በእኛ ውስጥ በረከትን፣ወንጌልን፣የሚበዛን ነገር አስቀምጧል።ከዛሬ ጀምሮ ጌታን አንድ ነገር እንጠይቅ እኔ ለማን አስፈልጋለው?እግዚአብሔር ከሚመልስልን መልስ ጋር ደግሞ እንቁም እንነሳና አድርጉ ያለንን እናድርግ።እኛ የእግዚአብሔር ጣት ነን፣እርሱ በእኛ ሚሰራው ስራ አለ።እንወቅ፣እንነሳ፣እንስራ !
#share
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
የአዕማድ ሰዎች ንግግር

"በሉቃስ ወንጌል ላይ ሳታቋርጡ ስበኩ ሳይሆን ሳታቋርጡ ጸልዩ ነው የሚለው።ለመስበክ ብዙ አስቸጋሪ አይደለም፣በምትጸልዩበት ጊዜ ግን በገለልተኛ ስፍራ ላይ ከጨለማ ኃይላት ጋር የውጊያን ጸሎት እየተፋለማችሁ ነው።ያን ጊዜ ድል የማድረግ ምስጢር በሚገባ ምን እንደሆነ ትረዳላችሁ።"
-ኢቫን ሮበርትስ
#share
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
#short teachings#1

አብርሃም ልጅ ፈለገና እግዚአብሔር ሕዝብ ሰጠው።ዛሬ የእግዚአብሔር በረከት ለአንተ አን ከጠበቅከውና ከፈለግከው በላይ ነውና ከሚሰጥህ ነገር በላይ እርሱን እያየህ እርሱን ጠብቅ።
እግዚአብሔርን ስትታገስና ስትጠብቅ ከምታስበውና ከምትጠብቀው በላይ ይሰጥሃል።እግዚአብሔር ሊመልስልህ ያለውን ነገር ያዘገየው እርሱን እንድታይና እንድትጠብቅ ነው።እርሱን ስትፈልግ የምትፈልገው ነገር ይከተልሃል።እግዚአብሔርን መጠበቅ ዋጋ ቢያስከፍልም ለጠበቅከው መጠበቅና መታገስ ግን ብድራት/ዋጋ/ አለው።

አንተን መጠበቅ ብዙ ትርፍ አለው
ለታገሰ ሰው ጸጋ ላስቻለው
አንተን ጠብቆ ያፈረ የለም
በዚህ ምድር ይሁን
በወዲያኛው አለም
#share
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
🔴🔴🔴SECURITY ALERT⚠️⚠️⚠️⚠️
ቴሌግራማቹን ከአጭበርባሪዎች ይጠብቁ!!!

🔺ቴሌግራም ላይ ከማንኛውም ሰው በ cutt.ly ወይም bit.ly የሚጀምር ማንኛውም ሊንክ ተልኮላችሁ ስታገኙ እንዳትከፍቱት ምክንያቱም ሰሞኑን የመጣ ቫይረስ አለ ሙሉ ለሙሉ የተፃፃፋችሁትን እና Join ያደረጋችሁትን ቻናሎች ሁሉ ያጠፋውና እንደ አዲስ ነው አካውንት ክፈቱ የሚላቹ ይሔ ትልቅ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነገር ነው ።

🔺እንደዚህ ዓይነት ሊንኮች በምታውቋቸው ሰዎች ስም ጭምር ሊላክላችሁ ይችላል ነገር ግን በጭራሽ እንዳትከፍቱ።

🔺በተጨማሪም ከሀከሮች አካውንታችሁን ለማዳን በምታስታውሱት Password Two-Step Verification On አድርጉ!
#TIKVAH
@ELOHIMLIFECHANNEL
"150 አመት እኖራለው"

ማይክል ጃክሰን በንድ ወቅት ይህን ተናግሮ ነበር።

75አመታትን የአለም ህዝብን በተሰጥኦው የማዝናናት እና ቀሪው ግማሹን 75 አመታት ደግሞ ፈጣሪውን በማገልገል ለመኖር አስቦ ነበር።

ይህንንም ለማሳካት ሲል የሚመገባቸውን ምግቦች ጤናማ ማድረግ  እና በመኝታ ክፍሉ ውስጥ ንፁህ አየር እንዲኖር በማሰብ Oxygen Bag በተባለ ድንኳን መሰል አልጋ ውስጥ ይተኛ ነበር።ለዚህም እጅግ በጣም በርካታ ዶላሮችን አፍስሶ ነበር።

ነገር ግን ምን ይደረጋል በፈጣሪ እቅድ ነው እምንኖረው እና እ.ኤ.አ. በ2009 ከሚወደው ስራው እና 150 አመታትን እኖርባታለው ብሎ ያሰባትን አለም 50አመታትን ኖሮ ላይመለስ ተሰናበታት።
---------------------------------------//-----------------------------------
ለየትኛው እድሜ ነው ምናቅደው? ስለነገ እናቅዳለን እንጂ ነገ ምን እንደምንሆን አናውቅም።ስለዚህ ባለን ነገርና በተሰጠን ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር እንኑር።አንደፈለግን ኖረን በመጨረሻ ጌታን ማሰብ ሳይሆን በጉብዝና ወራት፣ወቅት ሁሉን ነገር ማድረግ በምንችልበት ጊዜ እግዚአብሔር የሰጠንን ስራ ለነገ ብለን ሳይሆን ቀን ሳለ ማድረግ ሚገባንን እናድርግ።

ነፍሴ ወደአምላኳ
ስጋም ወደአፈሩ ሣይመለስ
ቶሎ ቶሎ ብዬ ስራዬን ልጨርስ
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv