ማዕደ ሰማይ
752 subscribers
98 photos
3 videos
2 files
14 links
#በፀጋ ነው
#ፀጋው ብቻ
#የታደገን ከዓለም ጡጫ።
#በፀጋ የዳነ
#ያለፀጋ አይፅፍም
#ያዳነው እያለ
#የዳነው አይነግስም፤
#ባለፀጋው #ባይኖር
#እኔም ችዬ አልኖርም።

እንዳለው እንድኖር
ጸጋ አለ የሚያኖር።
http://t.me/ElgraceBot
ለአስተያየቶ በዚህ 👇 ይላኩልኝ።

@Surtsega
@Surafeltsegamets
Download Telegram
🙏🙏 አደራህን 🙏🙏

እፍ በልበት፤
የጸነሰች ኹላ አትወልድም
የወለዱት ሁሉ አያድግም።
የተከሉት ሁሉ አይጸድቅም፤
የወጠኑት ሁሉ አይሰምርም።
አይደለ?
ሁሌ አይሆንም ልብ እንዳለ
ሁሉ አያመሽ እንደተኳለ፡ (ጸዳ እንዳለ)
ማመሻሹንስ መች ሁሉ ታደለ?

እፍ በልበትማ
በአዋዋሌ
ሁሉ ቢቀር አንተን ልምሰል፤
ደጅህ ሆኜ
የሚበላ እስኪኖረኝ እልፌ ልብሰል።

እፍ በልበትማ
በወጠንኩት
ሰርክ እዛው እንዳልደኸይ ትላንትናን እየደገምኩት
ከእልፍ መሃል
እ'ልፍ ማለት ትቼ እንክርዳዴን እያበጠርኩት።

እፍ በልበት
እፍ በልበትማ
አደራህን እፍ በልበት በችግኜ
የተከልኩት ይጽደቅልኝ
የጀምርኩት ከፍጻሜው ይመርልኝ
ያብብ ይለምልም
የጸደቀው ተንሰራፍቶም ይሁን ዋርካ
#ሽማግሌን_የሚያስወጋ

እፍ በልበትማ
ነፍስን ይዘህ ከእስትንፋስህ
ለምን ልሙት እኔ ልጅህ?
ለምን ልሩጥ ነፍስን በእጄ እንዳኖርኩት
አዳም ሆኜ እስትንፋህን አንዳላወኩት

አደራህን
እፍ በልበት፤ እፍ በልበት
እፍ በልበት በጸነስኩት
እፍ በበልበት በወለድኩት
እፍ በልበት በወጠንኩት
እፍ በልበት በአቀናሁት
መች ይሆናል እኔ እንዳልኩት?

እፍ በልበትማ
እፍ በልበት በነገዬ
እፍ በልበት በማምሻዬ
እፍ ማለትህ ህይወት አለው
ለዛ እኮ ነው መማጠኔ።

         ━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega     @elgraceministry
@Elgracebot           @surtsega
         @surafeltsegamets
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
#Share #comment and #add_value
#መንገድ_የሚያስለቅቅ_ይመጣል

#ሰዎች በችግርህ ጊዜ #ከጠፉብህ እግዚአብሄር ወደኔ #ሊመጣ ስለሆነ ቦታ #ለቀው ነው ብለህ #ቅን አስብ።

      ━━━━━⊱✿⊰━━━━━
        ♻️  @elgraceministry  ♻️
♻️  @gtmmbetsega  ♻️
       🔱  #share and #comments   🔱
🤠🤠 #ሁሉ_ደስይበለው 🤠🤠

አንድ #መሪ ሁሉንም ሰው ማስደሰት ከፈለገ መሆን ያለበት መሪ ሳይሆን #የጣፋጭ ምግብ #ሻጭ ስሙም #ጋሽ #ሁሉ_ደስይበለው ነው ።

           ━━━━━⊱✿⊰━━━━━
        ♻️  @elgraceministry  ♻️
🔱  Revealing the truth with in grace  🔱
#የብብቷ_ነገር

''የቆጡን አወርደዉ ብላ የብብቷን ጣለች''
ይላል የሀገሬ ሰዉ

እኔን የገረመኝ ይልቅ ያሳሰበኝ🤔
በብብቷ መሀል ምን ነበረ ያለዉ

ምናልባት የማይጠቅም ነገር
ቢኖርም ቢጠፋም እርባን ያጣ ነገር።

እሱን አስባ ይሁን የቆጡን የሻተች
እድሏን ልትሞክር እጇን የሰደደች

ቆጡ ላይ ምን ነበር
የብብቷስ ነገር

አንዳንዴ ሳስበዉ
በብብቷ ያለዉ
ሸክሙ በዝቶባት
እጇን አዝሎባት

ታርፍበት ጥግ አጥታ
ትለቀዉ ዘንድ ሰበብ ሽታ

ጭንቀት ፍርሀቷን ችግሯን አምቃ
ድካም ዝለት ቁስሏን ከሰዎች ደብቃ

ድንገቴ ከቆጡ አንድ ነገር ብታይ
ለቀቀችዉ መሰል የብብቷን ስቃይ።

ታዲያ አሁን እቺ ሴት ጥፋቷ ምንድን ነዉ
ቆጡ አይሻልም ወይ አንዳችም ባይኖረዉ

ስለዉ የሀገሬን ሰዉ እሱ መልስ መች ያጣል
ከማያዉቁት መልአክ የሚያዉቁት ሰይጣን ብሎ ይተርታል
ደሞ ቤቱ ዘመን ሴጣን ተሽሎ ያዉቃል።

ተዋት የብብቷን እሷ ታዉቀዋለች
ይልቅ ከቆጡ ላይ ምን ነበረ ያየች።

በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ (@TIZITA21)

━━━━⊱✿⊰━━━━━
👉👉 @elgraceministry 👈👈
👉👉 @elgraceministry 👈👈
🙏🙏 #የመመላለሻ_ልመና 🙏🙏

“እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ #እንደሚገባ #ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤”

ኤፌሶን 4፥1

━━━━⊱✿⊰━━━━━
👉👉 @elgraceministry 👈👈
👉👉 @elgraceministry 👈👈
አንብቡትማ በጌታ

ሰውየው ተራራ መውጣት እንጀራው ነው። እና አንድ ሌሊት በተራሮች ከፍታ ላይ እያለ ከባድ ውሽንፍር ተነሳበት። ከዚህም የተነሳ ምንም ነገር ማየት አልቻለም።

እንደሱ ግምት ከተራራው አናት በታች ጥቂት ጫማ ብቻ እየቀረው ተንሸራቶ በከፍተኛ ፍጥነት ወደቀ። ምንም ዐይታየውም ነበር፤ በመሬር ስበት የመሳብ አስከፊ ስሜት ብቻ ይሰማዋል፤ መውደቁን ቀጠለ። እና በዚህ በታላቅ ፍርሃት ጊዜ ውስጥ እያሰበ የነበረው ሞት ምን ያህል ቅርቡ እንደሆነ ብቻ ነበር።

አየር ላይ ሳለ በድንገት ከወገቡ ላይ የታሰረው ገመድ በጣም ሲጎትተው ተሰማው። ገመዱ ሰውነቱን በአየር ላይ አንጠለጠለው። ይሄኔ የወገቡን ገመድ እንቅ አርጎ ይዞ...

“ፈጣሪ ሆይ እርዳኝ” ብሎ ከመጮህ ሌላ አማራጭ አልነበረውም። በድንገት አንድ ጥልቅ ድምፅ ከሰማይ መጣ “ምን ላድርግልህ?” ሲል መለሰ።
"ፈጣሪ ሆይ አድነኝ"
“በእርግጥ ማዳን የምችል ይመስልሃል?”
"በእርግጥ እኔ እንደምትችል አምናለሁ።"
"ጥሩ በወገብህ ላይ የታሰረውን ገመድ ቁረጥ።"
#ዝምታ_ሰፈነ °°° #ቅጽበቱ_አለፈ
እናም ሰውየው በሙሉ ኃይሉ ገመዱን ለመያዝ ወሰነ።

በነጋታው፤ ጓደኛቸው የጠፋባቸው የነፍስ አድን የቡድን አባላት ባልደረባቸውን ፍለጋ ተራራውን እያካለሉ ነበር፤ በቀጣዩ ቀን ተራራው ላይ ሞቶ የቀዘቀዘ አስከሬን ገመድ ላይ ተንጠልጥሎ ፣ እጆቹ ገመዱን አጥብቀው እንደያዙት ከመሬት በአንድ ጫማ ከፍታ ላይ ብቻ ሆኖ ተመለከቱ እና እነሱም ጓደኛቸው #ገመዱን_ቢለቀው ኖሮ በሰላም መሬት ላይ ያርፍ እንደነበር አዩና እጅግም አዘኑ።

እኛስ ከገመዶቻችን ጋር ምን ያህል ተጣብቀናል? ገመዶቻችንን ልንለቃቸው ዝግጁ ነን? በእግዚአብሔር ሙሉ እምነት አለን?

━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega     @elgraceministry
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወንጌል የብልጽግና ወይስ የድህነት?
ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ
━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega     @elgraceministry
@Elgracebot           @surtsega
         @surafeltsegamets
#የምሬን_ማመልክህ #ናፈቅኸኝ

ላልከኝማ አምልከኝ፥ መርጠህ ከእልፍ መሃል፤
እያዜምኩ ሳዜምልህም፥ ለአንተስ ያንስብሃል።
በምን ዕድል፥በምን ዕጣዬ፤
ከአንተ ቤተ ሰዎች፥ መቆጠሬ፤
ምስጋናዬን ያልቀዋል
ለምላሼ ሺስ ቢሆን መች ይበቃል?

በቃ አይምሽ፥ በቃ አይንጋ፤
ሺ ጊዜ ሺ ቅዱስ እያልኩህ፥
ዘላለም ጠብቶ፥ ልሁን አንተጋ።

t.me//elgraceministry
#የንቀት_ጥግ

ጻድቁ አብርሃም፥ ታላቁ የእምነት አባት፤
ድንኳን በመስራት ነው፥ አለምን የናቃት።
አይገርምም?🤔

            ━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega     @elgraceministry
@Elgracebot           @surtsega
         @surafeltsegamets
#ነፍስን #የሚያፈዘውን #ማሰብ

የተወደዳችሁ የማዕደ ሰማይ ተከታታዮች ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ወደሌላ የህይወት ምዕራፍ የምዘዋወርበትን ቀን አብረን እንሆን ዘንድ ግብዣዬን በታላቅ አክብሮት አቀርባለሁ።

#እግዚአብሔርን_አሰብሁት #ደስ_አለኝም

@elgraceministry
@elgraceministry
ሰላም እንደምን አላችሁ የሚሽን ሞቢላይዜሽን ኢትዮጵያ ቤተሰቦች!

እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን !
ይህ የምናከብረው በዓል ከክብረ-በዓልነትም በላይ የእግዚአብሄር ዘላለማዊ አጀንዳ ለህዝቦቹ የተገለጠበት፣ አማኑኤል እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ያልንበት ነው።
በወንጌል ላልተደረሱ የሕዝብ ክፍሎች እያደረግነው ያለውን ጸሎት እንቀጥላለን ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ሳምንቱን በምድራችን ላይ በአጠቃላይ እንደአህጉር ላልተደረሱ የሕዝብ ክፍሎችን ልዩ ትኩረትን በመስጠት "መወለዱን ላልሰሙት" በሚል ተከታታይ ጸሎት በእግዚአብሄር ምህረት የታሰቡ ሆነው ለጌታችን በሚቀርቡበት ስርዓተ ጸሎት እንድንሳተፍ እንጋብችዋለን!
በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ካሉት
8.00 ቢሊዮን ሰዎች 3.40 ቢሊዮን ሰዎች የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለመስማት ዕድል ወይም ተደራሽነት በሌላቸው የሕዝብ ክፍሎች ውስጥ ይኖራሉ። በጆሹዋ ፕሮጀክት መሠረት፣ በአለም ላይ 17,446 የሚጠጉ ልዩ የሕዝብ ቡድኖች ወይም ክፍሎች አሉ፣ ከእነዚህም ውስጥ 7,248 ያልተደረሱ (ከ42 በመቶ በላይ የሚሆነው የዓለም ህዝብ)! ከእነዚህ አነስተኛ ደረጃ ላይ ከሚደርሱት ቡድኖች ውስጥ አብዛኛዎቹ (85%) በ 10/40 መስኮት ተብሎ በሚጠራው ልዮ ቦታ ውስጥ ይገኛሉ እና በእነዚህ ሰዎች መካከል ከ3% ያነሰ የሚስዮናዊነት ስራ ይሰራል።

በአለማችን በወንጌል ያልተደረሱ የሕዝብ ክፍሎች
አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት ፡- 8.1 ቢሊዮን
የሀገራት ብዛት፡- 205
አጠቃላይ የሕዝብ ክፍሎች ብዛት ፡- 17,281
ያልተደረሱ የሕዝብ ክፍሎች፡- 7,248 (41.9%)
ባልተደረሱ የሕዝብ ክፍሎች ውስጥ ሚገኙ፡- 3.4 ቢሊዮን
ያልተደረሱ የሕዝብ ክፍች በፐርሰንት፡- 42.4%
አብዛኞቹ የሚገኙት ፦ በ 10/40 መስኮት (85%)
#የነፍሴ_ደዋሪ

ምራዊ ሳቃችን፥ ምታስፈነድቀን፤
ህያው ተስፋችን፥ የምትናፍቀን፤

በደሳሳ ጎጆ፥ ሙላተ ማድጋ፤
በነጠፈ ተስፋ፥ ብርቱ ባለጠጋ፤
የሻገተውን፥ ፈጽሞ አለምላሚ፤
የተቆረጠውን፥ እንደአዲስ ገጣሚ፤

ከጥንት ጥንትን መስራች፥
ከዘላለም ዘላለምን ሰሪ፤
የህይወትን ትርጉም፥ የህይወትን ፍቺ፥
ብቻውን ቀማሪ፤
የሰማይ እና የምድር ደዋሪ፤

እውነተኛው ፈገግታችን፤
ሀዘን የለሹ ደስታችን፤

ምራዊ ሳቃችን፥ ምታስፈነድቀን፤
ህያው ተስፋችን፥ የምትናፍቀን፤

መቼ ነው መምጣትህ?
መቼ ነው ምጻትህ?

መችም እንደጥንቱ በረት አትወርድም፤
ዳግም ለእኛው፥ በእኛው አትዋረድም፤
ሰማይ እያወጋህ፥
ምድርም ሸሽጋህ፥
ጠባብ ደረት፤ አጭር ቁምጣ አያመጣህም።

ምራዊ ሳቃችን፥ ምታስፈነድቀን፤
ህያው ተስፋችን፥ የምትናፍቀን፤

ልክ እንደሙሽሪት፥
ተጠናቃ ሙሽራዋን እንደምትጠብቅ፤
በንጽህና፥ እንደምትናፍቅ፤
መቼ ነው፥ `ምትመጣው?
መች አንተን፥ እንጠብቅ?

ምራዊ ሳቃችን፤ ምታስፈነድቀን
ህያው ተስፋችን፤ የምትናፍቀን

አሜን
እንደናፈቅንህ፤
አሜን
እንደራብከን፤

ሳይቀዘቅዝ
ለአንተ ያለን ንጡህ ፍቅር
ታጥበን ነፅተን እስክትመጣ እንጠብቅህ።

             ━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega    @elgraceministry
@Elgracebot           @surtsega
         @surafeltsegamets
ኢየሱስ #ጌታ(ያህዌህ) ነው።

እርሱ (ድንቁ የአብ (ኤሎሄ) ስጦታ)
ለዘላለም አባት
ለፍጥረታት ሁሉ አስገኚያቸው፤ ፈጣሪያቸው
ሰማይና ሰራዊቱ የሚሰግዱለት
ምድርና አራዊቱ ሚንቀጠቀጡለት
ንፋሳትና ባህሩ የሚታዘዙለት
ከአብርሃም በፊት የነበረ
እግዚአብሔር (ያህዌህ) እርሱ በጠባብ ደረት በአጭር ቁምጣ ከድንግል ማርያም በመወለድ ወደ ምድር ሰው ሆኖ የመጣ ግን ከዛ ዕለት ያልጀመረ ኧረ ኢየሱስ ንጉስ፣ መድሃኒት፣ ጌታ እና ክርስቶስ ነው።

ዘላለም የማይሻር ታላቅ እውነት፤ ኢየሱስ የዓለምን ሁሉ ኃጢዓት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ (የታረደው በግ) እንዲሁም የይሁዳ አንበሳ (ማህተሙን የፈታ) ጌታ መሆኑ ነው።

ለመላው የንጉስ ካህናት
መልካም የንጉስ ልደት በዓል ይሁንልን።
         @━━━━⊱✿⊰━━━━━ @
     👉👉 @elgraceministry 👈👈
     👉👉 @elgraceministry 👈👈
#እግዚአብሔር_ይመስገን!!

ስለ ዶክተር ማሙሻ ተጨንቃችሁ የነበራችሁ፣ የጸለያችሁ፣ የጠየቃችሁ፣ የደወላችሁ፣ ፍቅራችሁን የገለጻችሁ ወዳጆቻችን ተባረኩ ፥ ይኸው እግዚአብሔር ጸሎታችንን ሰምቷልና እናመሰግነው ዘንድ ይገባናል። የምትችሉ ሁሉ ለእግዚአብሔር ሰው ስላደረገው መልካም ነገር በቦታው በመገኘት #እግዚአብሔርን እናመስግን።

━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega  @elgraceministry
@Elgracebot        @surtsega
         @surafeltsegamets
#ያ_ዘመን_ሲጠባ 🔎🔎

ሞቶ መኖር እየቻለ
ኖሮ ለመሞት አዳም ተቻኮለ።

ጉድ እኮ ነው ወገን
ማስተዋል ከራቀን
ሲዖል አፋፍ ሆነን
ገነት ሚናፍቀን። 📌📌


🔐
‼️
ⓢⓤⓡⓐⓕⓔⓛ

           ━━━━⊱✿⊰━━━━━
👉👉 @elgraceministry 👈👈
👉👉 @elgraceministry 👈👈
ሳትሰስት ሳትሳሳ፥ ምህረትን እየቸርከኝ
ዳዴዬን አስጥለህ፥ በእግሮቼ ያራመድከኝ፤
ከደምነት እስከ እናት ጡት የሸሸከኝ
በጉርምስናዬ ያባበልከኝ፤
ለትዝታ ቃልህን ያስታጠከኝ፤
መቼ በለጋነት ብቻ፤
መቼ በወጣትነት ብቻ፤
ገና እስከጉልምስና
ገና እስከሽበት፤ ገና እስከእርጅና
ትሸከመኛለህ፤ ታማኝ ነህና።

ተመሰገን
ከእዛኔ እስከ አሁን፥ ሳይደበዝዝ ፍቅርህ
ሳይደምንብኝ፥ ፈገግ ያለው ፊትህ።
መኖርያ ሆነኽልኝ፥ ለአንዷ ነፍሴም ታዛ
መኖርን አስወደድከኝ፥ ዕልልታዬም በዛ።
😭😭😭
ተመስገን።

እዩት ቢባል፥
አንዳች መልካም ታይቶ በእኔ፤
ሲጠቆም ወደ እኔ
ጠቁማለሁ አንተን (#2)
የታደከኝን ከአመጽ ከኩነኔ።

ታስቆጥረኝ ገባህ፥ በዕድሜ ላይ ዕድሜ፤
የህይወቴን ማለዳ፥ ፊትህ ማህሌት ቆሜ?
ዕድል ዕንደወጣለት፥ ከንጉስ እንደተወዳጀ
ህይወትና ዓለሜ
በደምህ ተቤዥቶ
ለስምህ ተዋጀ?
ተመስገን

ስፈትል ስፈታ
ስፈተል ስፈ'ታ
አጥብቀው የያዙኝ እጆችህ ሳይላሉ፤
ሌዕቴና ቀኔ ይፈራረቃሉ።
😭😭😭

ተመሰገን፤
ምህረትህ ዘወትር ማልዶ እየጠባ፤
በሞትና በእኔ መሃል እየገባ፤
ሰነበትኩ፥ አበብኩኝ በዕድሜ በረከት
ሞገስህ አረሰረሰኝ፥ ጎበኘኝ የአንተ መገኘት፤

ሳልሰጥህ አንዳች፥ ሳትጠብቅ ከእኔ
በቀራንዮ ገድልህ፥ ሳይበቃህ መዳኔ፤
ያወራኸኝን ቃል፥ የገባህልኝን ኪዳን ልትፈፅም
ትተጋለህ አንተስ፥ ሰንፈህ አትታወቅም።
ተመስገን😭😭

ሰልፈኛው ያሴረው፥
ዕልፍ ቢሆንም ሰልፉ፤
እንደአይን ብሌን፥
ተጠንቅቀክልኝ አረታኝም ክፉ።
አንዳች እንደሌለበት በሰላም አርፌ፤
ይኸው ስንት ሌዕቶችን ነቃሁ፥
ቀኝህን ተደግፌ።
😭😭😭

ተሸክመህ አትዝልም 
አንተ ይዘህ አትጥልም
መመርኮዣ አለት ነህ የማትሰነጠቅ
መልካም እረኛ ነህ ከአውሬ ምትናጠቅ።
#ተመስገን
😭😭😭
━━━━⊱✿⊰━━━━━
@gtmmbetsega   @elgraceministry
ትገኛለህ ማለት ርካሽ ነህ ማለት ሳይሆን የተሻልክ ነህ ማለት ነው። ለሰዎች ለመገኘት ቅንነት፤ ራስ ወዳድ አለመሆን እና መልካምነት ነውና። ሰዎች በቀላሉ ካገኘነው ነገር ይልቅ ዋጋ የሚያስከፍለንን ነገር ስንወድ እንገኛለን። እንዲሁ ለሚገኙልን ነገሮች ቦታ አንሰጥም። ማወቅ ያለብን በህይወታችን የተገኙልን ሰዎች ርካሽ ስለሆኑ ሳይሆን መልካም ስለሆኑ ነው። በምንፈልገው ጊዜ ከሚገልኝልን ወዳጅ ይልቅ አዲስ ላወቅነው ሰው ትልቅ ግምት ስንሰጥ እንገኛለን።

እግዚአብሔር የሚባርክህ በሰዎች ጭምር ነው። ሰዎች ተሰተውሃል ማለት እግዚአብሔር ጎብኝቶሃል ማለት ነው። ስለዚህ ወደ ህይወታችን የሚመጡትን ሰዎች በእግዚአብሔር አንጻር መረዳት ብልህነት ነው። ሰዎች ሲርቁን ወይም በስጋ ሲያልፉ ማድነቅ እንወዳለን አጠገችን ሳሉ በህይወታችን ያላቸውን ቦታ መንገር አንወድም።

አጠገባችን ያሉትን ሰዎች ከእኛ ጋር ስለተገኙ ብቻ መሔጃ የሌላቸው፥ ምንም ማድረግ የማይችሉ አድርገን መመልከት ጤናማነት አይደለም። ሰዎች ሲወዱን ሌላ ምርጫ እንደሌላቸው ማሰብ፤ ፍቅር ሲሰጡን እንደ ሞኝ ማሰብ፤ ዋጋ ሲከፍሉልን ቦታ አለመስጠት እጅግ የሚያሳዝን ሞኝነት ነው። ሰው ለእኛ ከሆነ እንዴት ነው ለራሱ መሆን የማይችለው? ምን አልባት የሚጠበቅበት ፊቱን ዞር ማድረግ ብቻ ሊሆን ይችላል።

፨ ሰዎች ሲገኙልህን አመስግናቸው ዋጋቸውን ልንነግራቸውና የተጠቀማችሁን ጥቅም ንገሩአቸው

፨ ሰዎች ሲገኙላችሁ አመስግኗቸው ለመልካምነታቸው እውቅናን ስጡ

፨የወደዱን ሰዎች የሰጡንን ፍቅር ከማቃለል እንቆጠብ፤ ፍቅራቸውን እንደ ሞኝነት አንመልከት

፨በምድር ላይ ከሰዎች በላይ በረከት ከህብረት በላይ ከፍታ የለም። በህይወታችን ላሉ ሰዎች እውቅና እንስጥ!!


https://www.facebook.com/eyobedandargie
"I heard my mother asking the neighbors for salt." But we had salt in the house. I asked her why she was asking the neighbors for salt. And she answered me: —Because our neighbors don't have a lot of money and often they ask us for something.
From time to time, I also ask them for something small and inexpensive, so that they feel that we need them too. This way they will feel more comfortable and easier for them to keep asking us for everything they need."
Respect for human dignity is undoubtedly one of the noblest feelings.
And that's exactly what I learned from my parents... Let's build empathetic, humble, supportive children and other values to be valued..!!!…"

- Courtesy: Fatima Anfig