መዝሙር ደምፀ እገሪሁ ከሰኔ ፳፮ እስከ ሐምሌ ፪
(በ፪/ኒ) ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ሶበ ይዘንም ዝናም ይትፌሥሑ ነዳያን (ደ) ሶበ ይዘንም ዝናም ይጸግቡ ርኁባን (ደ) ወሠርዐ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ደምፀ እገሪሁ ለዝናም።
ትርጕም፦
የዝናም እግሩ ተሰማ ዝናም በሚዘንም ጊዜ ነዳያን ደስ ይሰኛሉ ዝናም በሚዘንም ጊዜ የተራቡ ይጠግባሉ ለሰው ዕረፍት ሰንበትን ሠራ የዝናም እግሩ ተሰማ።
የዕለቱ ምንባባት፦
፩ቆሮ ፲፭፥፴፫ - ፶፩፤
ያዕ ፭፥፲፮ - ፍ፤
ግብ ፳፯፥፲፩ - ፳፩፤
የዕለቱ ወንጌል፦ ሉቃ ፰፥፩ - ፳፪
ቅዳሴ፦ ዘኤጲፋንዮስ፤
የዕለቱ ምስባክ፦
ዘይገለብቦ ለሰማይ በደመና፤
ወያስተዴሉ ክረምተ ለምድር፤
ዘያበቊል ሣዕረ ውስተ አድባር። መዝ ፻፵፮፥፰
ትርጕም፦
ሰማዩን በደመና የሚሸፍን፤
ለምድር ክረምትን የሚያዘጋጅ፤
በተራሮች ላይ ሣርን የሚያበቅል እግዚአብሔር ነው።

መዝሙር ይሰጠዎ ከሐምሌ ፫ እስከ ሐምሌ ፱
(በ፩/ዩ) ይሰጠዎ ወይሰምዖ ጸሎቶ ለኵሉ ለዘሰአሎ እግዚኣ ለሰንበት አምላከ ምሕረት ያርኁ ክረምተ በበዓመት ይሰምዑ ቃሎ ደመናት።
ትርጉም፦
ይመልስለታል የለመነውን ሁሉ ጸሎቱን ይሰማዋል የይቅርታ አምላክ የሰንበት ጌታ በየዓመቱ ክረምትን ይከፍታል (በጋና ክረምትን ያፈራርቃል) ደመናት ቃሉን ይሰማሉ።
የዕለቱ ምንባባት፦
ዕብ ፮፥፯ - ፍ፤
፩ጴጥ ፫፥፰ - ፲፭፤
ግብ ፲፬፥፰ - ፲፱፤
የዕለቱ ወንጌል፦ ማቴ ፲፫፥፩ - ፴፩
ቅዳሴ፦ ዘእግዚእነ፤
የዕለቱ ምስባክ፦
አርውዮ ለትለሚሃ፤
ወአሥምሮ ለማእረራ፤
ወበነጠብጣብከ ትበቊል ተፈሢሓ። መዝ ፷፬፥፲፤
ትርጕም፦
ትልሟን አርካው፤
መከሯንም አብጀው፤
በነጠብጣብህም ደስ ብሏት ትበቅላለች።
ምሥጢር፦
የኢየሩሳሌም ትልሟን አርካው፤
መከሯን የበጀ/የሚጠቅም አድርገው፤
እንዲህ የሆነ እንደሆነ ጠብ ጠብ ብሎ በሚዘንመው ዝናም ደስ ብሏት ተካክላ ትበቅላለች። ብርቱ ዝናም የዘነመ እንደሆነ ከነመሬቱ ድሶት (ጠራርጎት) ይሄዳል፤ ለሰስ ብሎ የወረደ እንደሆነ ደስ ብሏት ተካክላ ትበቅላለችና።
አንድም ልቡናዋን ደስ አሰኘው፤
ሚጠተ ሥጋውን የበጀ አድርግላት፤
በዘሩባቤል ደስ ብሏት ተካክላ ትወጣለች።
አንድም ነፍሷን ደስ አሰኘው፤
ሚጠተ ነፍሷን የበጀ አድርገው፤
ከቀኝ ጎንህ በፈሰሰ ጽሩይ ማይ ተጠምቃ ደስ እያላት ከሲኦል ወደገነት ትወጣለች።

ለእመ ኮነ በዓለ ሐዋርያት በሰንበት መዝሙር አሠርገዎሙ
(በ፬/ኪ) አሠርገዎሙ ለሐዋርያት በሰማያት (አ) ወንጌለ መንግሥት አወፈዮሙ (አ) ሰንበተ ክርስቲያን ለዕረፍት ሠርዐ ሎሙ (አ) ከመ ወርቅ በእሳት ፈተኖሙ (አ) ወከመ ጽንሐሐ መሥዋዕት ተወክፎሙ አሠርገዎሙ ለሐዋርያት በሰማያት።
ትርጕም፦
ሐዋርያትን በሰማያት አስጌጣቸው/ሸልማቸው፤ የመንግሥትን ወንጌል ሰጣቸው፤ ሰንበተ ክርስቲያንን ለዕረፍት አዘጋጀላቸው፤ እንደ ወርቅ በእሳት ፈተናቸው፤ እንደ ተወደደ መሥዋዕት ተቀበላቸው፤ በሰማያት አስጌጣቸው/ሸለማቸው።
የዕለቱ ምንባባት፦
፪ጢሞ ፬፥፩ - ፍ፤
፩ጴጥ ፩፥፲፪ - ፲፱፤
ግብ ፳፫፥፲ - ፍ፤
ወንጌል፦ ሉቃ ፮፥፩ - ፳፤
ቅዳሴ፦ ዘአበዊነ ሐዋርያት፤
የዕለቱ ምስባክ፦
አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ፤
ውስተ ኵሉ ምድር ወጽአ ነገሮሙ፤
ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ። መዝ ፲፰፥፫፤
ትርጕም፦
ነገራቸው ቃላቸው ያልተሰማበት ነገር የለም፤
ቃላቸው ወደምድር ሁሉ ወጣ፤
ነገራቸው እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ።
ምሥጢር፦
የመዓልተ እሑድ የመዓልተ ሰኑይ የሌሊተ እሑድ የሌሊተ ሰኑይ ነገራቸው ያልደረሰበት ያልተነገረበት የለም፤ ሥነ ፍጥረት ያልደረሰበት የለምና አንድም መሸ ጠባ/ነጋ የማይል የለምና።
በአራቱ ማዕዘን ሁሉ ተነገረ፤
ጽንፍ እስከ ጽንፍ ደረሰ።
አንድም የነቢያት ትንቢታቸው የሐዋርያት ስብከታቸው ያልደረሰበት ያልተነገረበት የለም። አንድም “በቃሎሙ” ይላል ነቢያት በቃላቸው ያልተናገሩት ትንቢት ሐዋርያት ያላስተማሩት ትምህርት ያልሰበኩት ስብከት የለም።
የነቢያት ትንቢታቸው የሐዋርያት ስብከታቸው በአራቱ ማዕዘን ደረሰ፤
የነቢያት ትንቢታቸው የሐዋርያት ስብከታቸው ከሰው ጆሮ ደረሰ፤ ጽንፍ አለው ጆሮን? የአካል ዳርቻ ነውና። አንድም ከምድር ጽንፍ እስከ ምድር ጽንፍ ተነገረ።