ELA TECH💡
188K subscribers
1.34K photos
28 videos
410 files
1.03K links
👋 ሰላም ሰላም እንኳን ወደ ELA TECH በሰላም መጡ

ለማንኛዉም ጥያቄ , አስተያየት እንዲሁም ሀሳብ
በዚ ያገኙናል
👇
@ELA_TECHBOT

በ Youtube ጠቃሚ ቪዲዮችን ለማግኘት የ YOUTUBE ቻናላችንን ይጎብኙ
👇
https://youtube.com/@ELA_TECH
Download Telegram
ሊቢያ በህገወጥ የክሪፕቶከረንሲ ማይኒንግ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መያዝ ጀምራለች።

🔻2 በመቶ የሚሆነው የኤሌክትሪክ ኃይል ለክሪፕቶከረንሲ ማይኒንግ ስራ የሚውልባት ሊቢያ በዘርፉ በህገወጥ መንገድ የተሰማሩ ሰዎችን ማሰር ጀምራለች።

🔻በተጠናቀቀው የህዳር ወር በብረት ፋብሪካ ውስጥ ይህንን ስራ ሲሰሩ የነበሩ 9 ሰዎች ተይዘው ትርፋቸውና ንብረታቸው ተወርሶ የ3 አመት እስር ተፈርዶባቸዋል።

🔻በሚያዝያ ወር 2024 ላይም በወር 45,000 ዶላር ትርፍ ሲያስገኙ የነበሩ 1000 የማይኒንግ መሳሪያዎችን ይዛለች። በዛው አመት 50 ቻይኖች ከ 100,000 የማይኒንግ መሳሪያዎች ጋር ተይዘው ነበር።

🔻የኤሌክትሪክ ክፍያ በኪሎዋት ሰዓት 0.004 ዶላር ብቻ የሆነባት ሊቢያ በ2021 ወቅት 0.6 በመቶ የሚሆነውን የአለም የቢትኮይን ሃሽሬት ትይዝ ነበር።

🔻ሊቢያ በ2022 የማይኒንግ ማሽኖች ወደ ሃገሯ እንዳይገቡ ብታግድም አሁንም በህገወጥ መንገድ እየገቡ ይገኛሉ።

🔻በ2018 ክሪፕቶከረንሲን መጠቀም የሽብር ተግባርንና የገንዘብ ማጭበርበር ተግባራን ያበረታታል በሚል ክሪፕቶከረንሲን መጠቀምን አግዳለች።

🔻ጠቅላይ ሚኒስትሯ አብዱል ሃሚድ ህገወጥ የክሪፕቶ ማይኒንግ በአንድ ኦፕሬሽን ከ1000-1500 ሜጋዋት ኃይል ያባክናሉ ብለዋል።

🔻በ2022 እ.ኤ.አ 54,000 የሚሆነው ዜጋዋ ክሪፕቶከረንሲ የነበራቸው የነበሩት ሊቢያ የዲጂታል መገበያያ ገንዘቡ ፍላጎት ስላላ እሱን ማስተዳደር የሚያስችል ጠንካራ ህግ ልታወጣ ይገባል ተብሏል

══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT
5👍2
Google Android ስልካችን ላይ emergency live video ማስተላልፍ የሚቻልበት feature አስተዋውቋል

🔻እንደሚታወቀው ሁሉም Android ስልኮች በአደጋ ጊዜ ለመደወልና text ለመላክ የሚያስችለን የemergency feature አለው።

🔻በአዲሱ ፊቸር ደግሞ በlive የemergency video ማስተላለፍ ይቻላል።

🔻ይህ ፊቸር ከAndroid 8 በላይ በሆኑ ስልኮች ላይ የሚሰራ ሲሆን ለጊዜው በሙከራ ደረጃ የተለቀቀው በአሜሪካ፣ በጀርመንና በሜክሲኮ ውስጥ ነው።


©bighabesha_softwares
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
5
ታላቅ የማስታወቂያ ቅናሽ አድርገናል !

- በተወዳጁ ቻናላችን ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ ?

▪️ የ ቻናል ማስታወቂያ
▪️ የ ሙዚቃ ማስታወቂያ
▪️ የ ድርጅት ማስታወቂያ
▪️ የ ቡቲክ ልብሶች ማስታወቂያ
▪️ የ ዩቲዩብና የቴሌግራም ቻናል ማስታወቂያ
▪️ ትሪትመንቶች
▪️ Consultancy
▪️ Technology accessories
▪️ ማንኛውም የትምህርት ማስታወቂያ እና
▪️ ሌሎችንም ሽያጮች ያስተዋውቁ

- ይሄን ልዩ ቅናሽ በመጠቀም ከ190,000+ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ምርቶን በማስተዋወቅ በእጥፍ ያትርፉ።

አሁኑኑ ያናግሩን
👉 @Its_eliyass
1
🔻ሃይዲ ላማር ትባላለች። በጣም ውብ ናት። ታዋቂ የሆሊውድ ተዋናይ ነበረች። ግን አንድ ተራ ተዋናይ ብቻ አልነበረችም። በጣም ስማርት ነበረች። የዋይፋይ ቴክኖሎጂን ለመፍጠር የረዳውን ሳይንስ ተመራምራ ያገኘች ሳይንቲስት ነበረች። ነገር ግን ብዙ ሰዎች ይህንን የአእምሮ ችሎታዋን ችላ ብለው የፊቷን ውበት ብቻ ያደንቁ ነበር።

🔻አብዛኛዎቹ ውብ ሴቶች በጣም እንደሚያምር ግን ውስጡ ባዶ እንደሆነ ብርጭቆ ናቸው። አዎ ብርጭቆው ከውጪ ሲታይ በጣም ያምራል። ግን ከውስጡ ምንም የለም።

🔻ታዲያ ሃይዲ እጅግ በጣም ቆንጆ የነበረች ቢሆንም ዘወትር ታዝን ነበረች። ሰዎች ውጫዊ ውበቷን ያደንቃሉ እንጂ የአእምሮ ብስለቷን ነገሬም አይሉት። እሷ የምትፈልገው በረቂቅ አእምሮዋ እንድትደነቅ እንጂ በግኡዝ መልኳ እንድትወደስ አልነበረም

══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
9👏2👍1
🔻የ 𝐂𝐇𝐈𝐍𝐀 ሀገር 𝐍𝐀𝐓𝐈𝐎𝐍𝐀𝐋 𝐔𝐍𝐈𝐕𝐄𝐑𝐒𝐈𝐓𝐘 𝐎𝐅 𝐃𝐄𝐅𝐄𝐍𝐒𝐄 𝐓𝐄𝐂𝐇𝐍𝐎𝐋𝐎𝐆𝐘 እዚ ምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ቢንቢን የምታክል ድሮኖችን በስፉት ማምረት ጀምረዋል እነዚም ድሮኖች የመከላከያ ኦፕሬሽን ስራዎችን ለመስራት አገልግሎት ላይ ይውላሉ ።
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
😱31
ይዘት ፈጣሪው ኤ.አይ (Generative AI? ) ምንድን ነው ?

🔻ባለፉት 10 ዓመታት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ድንቅ የፈጠራ ውጤት ሆኖ የሚታይ ቢሆንም በዚህ ልክ ለመስፋፋቱ ምክንያት በራሱ ይዘት መፍጠር የሚችለው ኤ.አይ (Generative AI) ይበልጡኑ እ.ኢ.አ 2022 የቻት ጂፒቲ መተዋወቅ ጋር የተያያዘ ነው።

ለመሆኑ Generative AI ምንድን ነው ?

🔻ከዚህ ቀደም ሰዎች ኢንተርኔት ላይ የሚፈልጉት ነገር ለማግኘት ኢንተርኔትን በማሰስ (Web Browsing) ነው ይህም ይህም በፊት ያሉ ውጤቶችንና መረጃዎችን የምናገኝበት መንገድ ነው።

🔻Generative AI
የምንለው ከዚህ ይለያል። ይህም ቀደም ያሉ ውጤቶችን ማምጣት ሳይሆን በሰዎች ጥያቄ ላይ መሰረት አድርጎ የተሰናሰለ አዲስ መልስ የሚሰጥ ነው።

Generative AI መሰረት ያደረገው ምን ላይ ነው ?

🔻ሰዎች ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት መሰረት የሚሆነው ቀድሞ ማሽኑን ለማሰልጠን የምንጠቀምበት ዳታ (የመረጃዎች ጥርቅም) ነው። ለዚህም በርካታ መረጃዎች ያስፈልጋሉ።

እዚህ ላይ ማወቅ ያለብን የምናገኘው መልስ በዋነኝነት በሰለጠነበት የመረጃ ክምችት ላይ የተወሰነ በመሆኑ ሊሳሳትና ትክክለኛ መልስ ሊሰጠን እንደሚችል ነው።

Generative AI ምን መስራት ይችላል ?

🔻ምስሎችን መፍጠር፣ ሙዚቃ ማቀናበር፣ ቪዲዮ መስራት፣ ጹሑፍ መጽሐፍ፣ ኮድ መጻፍ እና መሰል ተግባራትን ማከናወን ይችላል።

══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
9
ጎግል በጆሮ ማዳመጫ አማካኝነት ቋንቋዎችን የሚተረጉም መተግበሪያ ይፋ አደረገ

🔻በጆሮ ማዳመጫ አማካኝነት የተለያዩ ሀገራት ቋንቋዎችን የሚተረጉመው የጎግል መተግበሪያ ለሙከራ ይፋ ሆኗል፡፡

🔻ኩባንያው ከትርጉም እና ቋንቋ ነክ አገልግሎቶቹ ጋር ተያይዞ መተግበሪያው ላይ ማሻሻያ አድርጓል፡፡

🔻በመተግበሪያው ላይ የተካተተው ማሻሻያ የተናጋሪውን የንግግር ቅድመ ተከተል እና የድምፅ ቃና በጠበቀ መልኩ ለአድማጭ እንዲተረጉም ተደርጎ የበለፀገ ነው፡፡

🔻ይህም በየትኛውም ቦታ ሆኖ በተለያዩ ቋንቋዎች እየተደረጉ ያሉ ንግግሮች፣ ትዕይንቶች፣ ፊልሞች እና ሌሎችም ይዘቶችን ለመረዳት መተግበሪያውን ማስጀመር እና የጆሮ ማዳመጫ መጠቀም በቂ ነው ተብሏል፡፡

🔻ለሙከራ ይፋ በተደረገው መተግበሪያ የ70 ሀገራት ቋንቋን የሚተረጉም ሲሆን በዋናነት እንደ አሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ህንድ ባሉ ሀገራት ላይ እየተሞከረ መሆኑ ተነግሯል፡፡

🔻የጎግል ኩባንያ እ.ኤ.አ በ2010 የቋንቋ መተግበሪያውን ይፋ ካደረገ ጀምሮ በርካታ የማበልፀግ ስራዎችን መስራቱ የሚታወቅ ነው
፡፡
8👏2
1
ELA TECH💡
Photo
የስማርት ስልክዎ በቫይረስ ወይም በተንኮል አዘል ሶፍትዌር Malware መጠቃቱን ካወቁ፤ ስልኩን ለማጽዳት እና መረጃዎን ለመጠበቅ

📌የሚከተሉትን እርምጃዎች በፍጥነት ይውሰዱ

1. ስልኩን ማጥፋት ወይም ወደ "Safe Mode" መቀየር

- Safe_Mode: አብዛኛዎቹ አንድሮይድ ስልኮች የኃይል ማጥፊያ ቁልፉን ተጭነው ሲይዙ ወደ Safe Mode የመግቢያ አማራጭ ይሰጡዎታል። በዚህ ሁኔታ ስልኩ ሲከፈት ከስልኩ ጋር ከመጡት መተግበሪያዎች ውጪ ሌሎች አይሰሩም። ይህም ቫይረሱ እንዳይሰራጭ ያግዳል፤ ለማጥፋትም ይመቻል።

2. የማያውቁትንና አጠራጣሪ መተግበሪያዎችን ማጥፋት Uninstall
- ወደ Settings > Apps (ወይም Applications) ይግቡ።
- በቅርቡ የጫኑትን ወይም እርስዎ ያልጫኑትን ማንኛውንም መተግበሪያ ይፈልጉ።
- መተግበሪያውን ይጫኑና Uninstall የሚለውን በመምረጥ ያጥፉት።
ማሳሰቢያ: አንዳንድ ቫይረሶች የ "Administrator" ፈቃድ ስለሚወስዱ በቀላሉ ሊጠፉ አይችሉም። በዚህ ጊዜ Settings > Security > Device Administrators ውስጥ ገብተው ፈቃዱን ቀድመው ማንሳት ይኖርብዎታል።

3. የብሮውዘር Browser መረጃዎችን ማጽዳት
- ብዙ ጊዜ ቫይረሶች የሚመጡት በድረ-ገጾች በኩል ስለሆነ፣ የሚጠቀሙበትን ብሮውዘር (ለምሳሌ Chrome) ታሪክና ዳታ ያጽዱ።
- Settings > Apps > Chrome > Storage > Clear Cache / Clear Data የሚለውን ይጫኑ።

4. የፀረ-ቫይረስ Antivirus መተግበሪያ መጠቀም
- ከታመነ ቦታ (ለምሳሌ Google Play Store) ታዋቂ የፀረ-ቫይረስ መተግበሪያዎችን በመጫን ስልኩን "Scan" ያድርጉ።

5. የመጨረሻው አማራጭ፦ ወደ ፋብሪካ ሁኔታ መመለስ Factory_Reset
- ከላይ ያሉት እርምጃዎች ካልሰሩ፣ ስልኩን ሙሉ በሙሉ ማጽዳት ሊኖርብዎ ይችላል።

- ይህ እርምጃ በስልኩ ላይ ያለውን ማንኛውንም መረጃ (ፎቶ፣ ስልክ ቁጥር፣ ፋይሎች) ስለሚያጠፋ፣ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች አስቀድመው Back up ማድረጋቸውን ያረጋግጡ።
- ወደ Settings > System > Reset options > Erase all data (factory reset) በመግባት ያጽዱት።
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
8
ፌስቡክ በመተግበሪያው ላይ የሚጋሩ ሊንኮችን ሊገድብ ነው።

ፌስቡክ እያደረገ ነው በተባለው ሙከራ ከ14.99 ዶላር የሚጀምረው የፌስቡክ ቬሪፋይድ ሰብስክሪፕሽን የሌላቸው ተጠቃሚዎች በሳምንት ሁለት ሊንኮችን ብቻ እንዲያጋሩ ይገድባል።

ሜታ ገደቡ የፕሮፌሽናል ሞድ የሚጠቀሙ ሰዎችንና የፌስቡክ ፔጆችን እንደሚመለከት ገልጿል።

የሜታ ቃል አቀባይ ሙከራው ከሊንኮች ጋር ተጨማሪ ልጥፎችን ማጋራት መቻል የሜታ ሰብስክሪፕሽንን እንደሚጨምር ለማየት ስለመሆኑ ገልጿል።

የሜታ ሙከራ ከሌሎች መተግበሪያዎቸ የሚደርሱትን አንባቢ ለመጨመር የሚሞክሩ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ሲኖረው ተጠቃሚዎች አሁንም በሃሳብ መስጫዎች ሊንኮችን ማጋራት ይችላሉ ብሏል።

🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
2