ELA TECH💡
188K subscribers
1.35K photos
28 videos
410 files
1.04K links
👋 ሰላም ሰላም እንኳን ወደ ELA TECH በሰላም መጡ

ለማንኛዉም ጥያቄ , አስተያየት እንዲሁም ሀሳብ
በዚ ያገኙናል
👇
@ELA_TECHBOT

በ Youtube ጠቃሚ ቪዲዮችን ለማግኘት የ YOUTUBE ቻናላችንን ይጎብኙ
👇
https://youtube.com/@ELA_TECH
Download Telegram
Prompt Engineering? ምንድነው ?

🔻ጄኔሬቲቭ ኤ.አይ (Generative Ai) ከተዋወቀ በኋላ ሰዎች በብዛት ኤ.አይ መተግበሪያዎችን መረጃ ለማግኘት፣ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ፣ ዝርዝር ነገሮችን ለማሳጠርና ግልጽ ለማድረግና ለብዙ ጉዳዮች እየተጠቀሟቸው ይገኛል።

🔻እነዚህ አገልግሎቶች በነጻ ሁሉም ሰው በብዛት የሚጠቀማቸው ቢሆኑም ለሁሉም ሰው እኩል አገልግሎት ይሰጣሉ ማለት ግን አይደለም።

ታዲያ ለሰዎች የሚሰጠው ምላሽ ላይ ያለው ልዩነት ከምን የሚመነጭ ነው ?

🔻ኤ.አይ ሞዴሎች ለሚሰጡት ምላሽ ተገቢውን ጥያቄ፣ ወይም መረጃውን ሊረዱበት በሚችለው መንገድ ማቅረብ የተሻለ ምላሽ እንድናገኝ ይረዳናል። ይህንን ተግባር ወይም ሞያ "Prompt Engineering " ብለን እንጠራዋለን።

🔻ግልጽ ትዕዛዞችን ማስተላለፍ መቻል፣ መጠየቅ ስለምንፈልገው ጥያቄ የተገደበ እና በአጭሩ የተብራራ መረጃ መስጠት፣ በሚሰጡን ምላሾች ላይ ተደጋጋሚ ማሻሻያዎችን መጠየቅ፥ የተሻለ ምላሽ ለማግኘት ከሚጠቅሙን መካከል ይጠቀሳሉ።

🔻በተጨማሪም፥ በአንድ ጊዜ አንድ ርዕሰ ጉዳይ ነጥሎ (ትኩረት አድርጎ) መጠየቅ፤ ምሳሌዎችን ማቅረብ፤ መረጃዎች ቅደም ተከተላቸውን ጠብቀው አንዲቀመጡ ትዕዛዝ ማስቀመጥ፤ በምን አይነት መልኩ ምላሹን እንደምንፈልገው በግልጽ መግለጽ ጥራት ያለው ምላሽ እንድናገኝ ያግዙናል።

ምን ጥንቃቄ ማድረግ አለብን ?

🔻ኤ.አይ ሞዴሎች ትክክለኛ ምላሽ ላይሰጡን ስለሚችሉ መረጃዎችን እንደወረደ ከመጠቀም ተቆጥበን ምላሾቹን ማንበብ፣ ደግሞ ማጣራትና ይዘቱን መፈተሽ ያስፈልጋል።

🔻በተጨማሪም፥ ኤ.አይ ሞዴሎች አሰራራቸው ምላሽ ለመስጠት ነው። ስለዚህ የምንጠይቀው ጥያቄ ግልጽ ባይሆንም ምላሽ ይሰጣሉ።

🔻መረጃ በሌላቸው ጉዳይ ላይም የቅዠት መረጃ (AI hallucinations) ይሰጣሉ። ስለዚህ በሚሰጡን ምላሾች ላይ ማጣራት፤ መልሶ መጠየቅ እና በሌሎች መረጃዎች መደገፍ ያስፈልጋል።
8
MIT በchatGPT ተጠቃሚዎች ላይ ያጠናውን ጥናት ይፋ አድርጓል።

⛔️ጥናቱ በ3 ቡድን ተከፍሎ essay እንዲፅፉ ተደርገዋል።
_ በአምሯቸው ብቻ ተጠቅመው የሚሰሩ
_ Search engine ብቻ የጠቀሙ (Could use Google but no AI)
_ AI ብቻ የሚጠቀሙ (use GPT-4o)

⛔️የጥናቱ ተሳታፊዎች አንጎል scan ከተደረገ በኋላ
83.3% የሚሆኑት AI ተጠቃሚዎች ከደቂቃዎች በፊት በAI አማካኝነት የፃፉትን አንድም አረፍተ-ነገር ማስታወስ አልቻሉም።

⛔️የአንጎል ግንኙነታቸው ከ79 ወደ 42 ነጥብ ዝቅ ብሏል። ይህም 47% የነርቭ ግንኙነታቸው ወርዷል ተብሏል።

⛔️chatGPT መጠቀም ካቆሙ በኋላም ቀጣይነት ያለው የማስታወስ ድክመትና chatGPT ከማይጠቀሙት ያነሰ አፈፃጸም ተስተውሎባቸዋል። ይህም በAI ጥገኛ ከመሆንም ባለፈ የግንዛቤ ድክመት (cognitive weakening) ነው ተብሏል።

⛔️chatGPTን መጠቀም ስራዎችን 60% በፍጥነት ለማጠናቀቅ ቢረዳም አእምሮ ግን የመማርና የማገናዘብ ጥረቱን በ32% ቀንሶ ተገኝቷል።

⛔️በአጠቃላይ ያለAI የሰሩት ከፍተኛ የማስታወስ ችሎታን፣ የአንጎል እንቅስቃሴን ያስመዘገቡ ሲሆን chatGPTን የሚጠቀሙ ደግሞ ስራቸውን በፍጥነትና በቅልጥፍና ቢጨርሱም በተቃራኒው ዝቅተኛ የማስታወስ ችሎታና የአንጎል እንቅስቃሴ አስመዝግበዋል ተብሏል።

⛔️ስለዚህ AIን ተጠቀሙ ግን እንዲያግዛችሁ እንጂ እንዲተካችሁ አታድርጉት፤ ጥገኛ አትሁኑ፤ በማንኛውም ጊዜ በአእምሯችሁ የመስራት ችሎታችሁን አትጡ።

Credit :-
bighabesha_softwares
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
12👍7🔥3👏1
ሊቢያ በህገወጥ የክሪፕቶከረንሲ ማይኒንግ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መያዝ ጀምራለች።

🔻2 በመቶ የሚሆነው የኤሌክትሪክ ኃይል ለክሪፕቶከረንሲ ማይኒንግ ስራ የሚውልባት ሊቢያ በዘርፉ በህገወጥ መንገድ የተሰማሩ ሰዎችን ማሰር ጀምራለች።

🔻በተጠናቀቀው የህዳር ወር በብረት ፋብሪካ ውስጥ ይህንን ስራ ሲሰሩ የነበሩ 9 ሰዎች ተይዘው ትርፋቸውና ንብረታቸው ተወርሶ የ3 አመት እስር ተፈርዶባቸዋል።

🔻በሚያዝያ ወር 2024 ላይም በወር 45,000 ዶላር ትርፍ ሲያስገኙ የነበሩ 1000 የማይኒንግ መሳሪያዎችን ይዛለች። በዛው አመት 50 ቻይኖች ከ 100,000 የማይኒንግ መሳሪያዎች ጋር ተይዘው ነበር።

🔻የኤሌክትሪክ ክፍያ በኪሎዋት ሰዓት 0.004 ዶላር ብቻ የሆነባት ሊቢያ በ2021 ወቅት 0.6 በመቶ የሚሆነውን የአለም የቢትኮይን ሃሽሬት ትይዝ ነበር።

🔻ሊቢያ በ2022 የማይኒንግ ማሽኖች ወደ ሃገሯ እንዳይገቡ ብታግድም አሁንም በህገወጥ መንገድ እየገቡ ይገኛሉ።

🔻በ2018 ክሪፕቶከረንሲን መጠቀም የሽብር ተግባርንና የገንዘብ ማጭበርበር ተግባራን ያበረታታል በሚል ክሪፕቶከረንሲን መጠቀምን አግዳለች።

🔻ጠቅላይ ሚኒስትሯ አብዱል ሃሚድ ህገወጥ የክሪፕቶ ማይኒንግ በአንድ ኦፕሬሽን ከ1000-1500 ሜጋዋት ኃይል ያባክናሉ ብለዋል።

🔻በ2022 እ.ኤ.አ 54,000 የሚሆነው ዜጋዋ ክሪፕቶከረንሲ የነበራቸው የነበሩት ሊቢያ የዲጂታል መገበያያ ገንዘቡ ፍላጎት ስላላ እሱን ማስተዳደር የሚያስችል ጠንካራ ህግ ልታወጣ ይገባል ተብሏል

══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT
6👍2
Google Android ስልካችን ላይ emergency live video ማስተላልፍ የሚቻልበት feature አስተዋውቋል

🔻እንደሚታወቀው ሁሉም Android ስልኮች በአደጋ ጊዜ ለመደወልና text ለመላክ የሚያስችለን የemergency feature አለው።

🔻በአዲሱ ፊቸር ደግሞ በlive የemergency video ማስተላለፍ ይቻላል።

🔻ይህ ፊቸር ከAndroid 8 በላይ በሆኑ ስልኮች ላይ የሚሰራ ሲሆን ለጊዜው በሙከራ ደረጃ የተለቀቀው በአሜሪካ፣ በጀርመንና በሜክሲኮ ውስጥ ነው።


©bighabesha_softwares
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
5
ታላቅ የማስታወቂያ ቅናሽ አድርገናል !

- በተወዳጁ ቻናላችን ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ ?

▪️ የ ቻናል ማስታወቂያ
▪️ የ ሙዚቃ ማስታወቂያ
▪️ የ ድርጅት ማስታወቂያ
▪️ የ ቡቲክ ልብሶች ማስታወቂያ
▪️ የ ዩቲዩብና የቴሌግራም ቻናል ማስታወቂያ
▪️ ትሪትመንቶች
▪️ Consultancy
▪️ Technology accessories
▪️ ማንኛውም የትምህርት ማስታወቂያ እና
▪️ ሌሎችንም ሽያጮች ያስተዋውቁ

- ይሄን ልዩ ቅናሽ በመጠቀም ከ190,000+ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ምርቶን በማስተዋወቅ በእጥፍ ያትርፉ።

አሁኑኑ ያናግሩን
👉 @Its_eliyass
1
🔻ሃይዲ ላማር ትባላለች። በጣም ውብ ናት። ታዋቂ የሆሊውድ ተዋናይ ነበረች። ግን አንድ ተራ ተዋናይ ብቻ አልነበረችም። በጣም ስማርት ነበረች። የዋይፋይ ቴክኖሎጂን ለመፍጠር የረዳውን ሳይንስ ተመራምራ ያገኘች ሳይንቲስት ነበረች። ነገር ግን ብዙ ሰዎች ይህንን የአእምሮ ችሎታዋን ችላ ብለው የፊቷን ውበት ብቻ ያደንቁ ነበር።

🔻አብዛኛዎቹ ውብ ሴቶች በጣም እንደሚያምር ግን ውስጡ ባዶ እንደሆነ ብርጭቆ ናቸው። አዎ ብርጭቆው ከውጪ ሲታይ በጣም ያምራል። ግን ከውስጡ ምንም የለም።

🔻ታዲያ ሃይዲ እጅግ በጣም ቆንጆ የነበረች ቢሆንም ዘወትር ታዝን ነበረች። ሰዎች ውጫዊ ውበቷን ያደንቃሉ እንጂ የአእምሮ ብስለቷን ነገሬም አይሉት። እሷ የምትፈልገው በረቂቅ አእምሮዋ እንድትደነቅ እንጂ በግኡዝ መልኳ እንድትወደስ አልነበረም

══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
12👏2👍1
🔻የ 𝐂𝐇𝐈𝐍𝐀 ሀገር 𝐍𝐀𝐓𝐈𝐎𝐍𝐀𝐋 𝐔𝐍𝐈𝐕𝐄𝐑𝐒𝐈𝐓𝐘 𝐎𝐅 𝐃𝐄𝐅𝐄𝐍𝐒𝐄 𝐓𝐄𝐂𝐇𝐍𝐎𝐋𝐎𝐆𝐘 እዚ ምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ቢንቢን የምታክል ድሮኖችን በስፉት ማምረት ጀምረዋል እነዚም ድሮኖች የመከላከያ ኦፕሬሽን ስራዎችን ለመስራት አገልግሎት ላይ ይውላሉ ።
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
😱41
ይዘት ፈጣሪው ኤ.አይ (Generative AI? ) ምንድን ነው ?

🔻ባለፉት 10 ዓመታት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ድንቅ የፈጠራ ውጤት ሆኖ የሚታይ ቢሆንም በዚህ ልክ ለመስፋፋቱ ምክንያት በራሱ ይዘት መፍጠር የሚችለው ኤ.አይ (Generative AI) ይበልጡኑ እ.ኢ.አ 2022 የቻት ጂፒቲ መተዋወቅ ጋር የተያያዘ ነው።

ለመሆኑ Generative AI ምንድን ነው ?

🔻ከዚህ ቀደም ሰዎች ኢንተርኔት ላይ የሚፈልጉት ነገር ለማግኘት ኢንተርኔትን በማሰስ (Web Browsing) ነው ይህም ይህም በፊት ያሉ ውጤቶችንና መረጃዎችን የምናገኝበት መንገድ ነው።

🔻Generative AI
የምንለው ከዚህ ይለያል። ይህም ቀደም ያሉ ውጤቶችን ማምጣት ሳይሆን በሰዎች ጥያቄ ላይ መሰረት አድርጎ የተሰናሰለ አዲስ መልስ የሚሰጥ ነው።

Generative AI መሰረት ያደረገው ምን ላይ ነው ?

🔻ሰዎች ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት መሰረት የሚሆነው ቀድሞ ማሽኑን ለማሰልጠን የምንጠቀምበት ዳታ (የመረጃዎች ጥርቅም) ነው። ለዚህም በርካታ መረጃዎች ያስፈልጋሉ።

እዚህ ላይ ማወቅ ያለብን የምናገኘው መልስ በዋነኝነት በሰለጠነበት የመረጃ ክምችት ላይ የተወሰነ በመሆኑ ሊሳሳትና ትክክለኛ መልስ ሊሰጠን እንደሚችል ነው።

Generative AI ምን መስራት ይችላል ?

🔻ምስሎችን መፍጠር፣ ሙዚቃ ማቀናበር፣ ቪዲዮ መስራት፣ ጹሑፍ መጽሐፍ፣ ኮድ መጻፍ እና መሰል ተግባራትን ማከናወን ይችላል።

══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
9
ጎግል በጆሮ ማዳመጫ አማካኝነት ቋንቋዎችን የሚተረጉም መተግበሪያ ይፋ አደረገ

🔻በጆሮ ማዳመጫ አማካኝነት የተለያዩ ሀገራት ቋንቋዎችን የሚተረጉመው የጎግል መተግበሪያ ለሙከራ ይፋ ሆኗል፡፡

🔻ኩባንያው ከትርጉም እና ቋንቋ ነክ አገልግሎቶቹ ጋር ተያይዞ መተግበሪያው ላይ ማሻሻያ አድርጓል፡፡

🔻በመተግበሪያው ላይ የተካተተው ማሻሻያ የተናጋሪውን የንግግር ቅድመ ተከተል እና የድምፅ ቃና በጠበቀ መልኩ ለአድማጭ እንዲተረጉም ተደርጎ የበለፀገ ነው፡፡

🔻ይህም በየትኛውም ቦታ ሆኖ በተለያዩ ቋንቋዎች እየተደረጉ ያሉ ንግግሮች፣ ትዕይንቶች፣ ፊልሞች እና ሌሎችም ይዘቶችን ለመረዳት መተግበሪያውን ማስጀመር እና የጆሮ ማዳመጫ መጠቀም በቂ ነው ተብሏል፡፡

🔻ለሙከራ ይፋ በተደረገው መተግበሪያ የ70 ሀገራት ቋንቋን የሚተረጉም ሲሆን በዋናነት እንደ አሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ህንድ ባሉ ሀገራት ላይ እየተሞከረ መሆኑ ተነግሯል፡፡

🔻የጎግል ኩባንያ እ.ኤ.አ በ2010 የቋንቋ መተግበሪያውን ይፋ ካደረገ ጀምሮ በርካታ የማበልፀግ ስራዎችን መስራቱ የሚታወቅ ነው
፡፡
10👏2
1
ELA TECH💡
Photo
የስማርት ስልክዎ በቫይረስ ወይም በተንኮል አዘል ሶፍትዌር Malware መጠቃቱን ካወቁ፤ ስልኩን ለማጽዳት እና መረጃዎን ለመጠበቅ

📌የሚከተሉትን እርምጃዎች በፍጥነት ይውሰዱ

1. ስልኩን ማጥፋት ወይም ወደ "Safe Mode" መቀየር

- Safe_Mode: አብዛኛዎቹ አንድሮይድ ስልኮች የኃይል ማጥፊያ ቁልፉን ተጭነው ሲይዙ ወደ Safe Mode የመግቢያ አማራጭ ይሰጡዎታል። በዚህ ሁኔታ ስልኩ ሲከፈት ከስልኩ ጋር ከመጡት መተግበሪያዎች ውጪ ሌሎች አይሰሩም። ይህም ቫይረሱ እንዳይሰራጭ ያግዳል፤ ለማጥፋትም ይመቻል።

2. የማያውቁትንና አጠራጣሪ መተግበሪያዎችን ማጥፋት Uninstall
- ወደ Settings > Apps (ወይም Applications) ይግቡ።
- በቅርቡ የጫኑትን ወይም እርስዎ ያልጫኑትን ማንኛውንም መተግበሪያ ይፈልጉ።
- መተግበሪያውን ይጫኑና Uninstall የሚለውን በመምረጥ ያጥፉት።
ማሳሰቢያ: አንዳንድ ቫይረሶች የ "Administrator" ፈቃድ ስለሚወስዱ በቀላሉ ሊጠፉ አይችሉም። በዚህ ጊዜ Settings > Security > Device Administrators ውስጥ ገብተው ፈቃዱን ቀድመው ማንሳት ይኖርብዎታል።

3. የብሮውዘር Browser መረጃዎችን ማጽዳት
- ብዙ ጊዜ ቫይረሶች የሚመጡት በድረ-ገጾች በኩል ስለሆነ፣ የሚጠቀሙበትን ብሮውዘር (ለምሳሌ Chrome) ታሪክና ዳታ ያጽዱ።
- Settings > Apps > Chrome > Storage > Clear Cache / Clear Data የሚለውን ይጫኑ።

4. የፀረ-ቫይረስ Antivirus መተግበሪያ መጠቀም
- ከታመነ ቦታ (ለምሳሌ Google Play Store) ታዋቂ የፀረ-ቫይረስ መተግበሪያዎችን በመጫን ስልኩን "Scan" ያድርጉ።

5. የመጨረሻው አማራጭ፦ ወደ ፋብሪካ ሁኔታ መመለስ Factory_Reset
- ከላይ ያሉት እርምጃዎች ካልሰሩ፣ ስልኩን ሙሉ በሙሉ ማጽዳት ሊኖርብዎ ይችላል።

- ይህ እርምጃ በስልኩ ላይ ያለውን ማንኛውንም መረጃ (ፎቶ፣ ስልክ ቁጥር፣ ፋይሎች) ስለሚያጠፋ፣ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች አስቀድመው Back up ማድረጋቸውን ያረጋግጡ።
- ወደ Settings > System > Reset options > Erase all data (factory reset) በመግባት ያጽዱት።
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
12👍1
ፌስቡክ በመተግበሪያው ላይ የሚጋሩ ሊንኮችን ሊገድብ ነው።

ፌስቡክ እያደረገ ነው በተባለው ሙከራ ከ14.99 ዶላር የሚጀምረው የፌስቡክ ቬሪፋይድ ሰብስክሪፕሽን የሌላቸው ተጠቃሚዎች በሳምንት ሁለት ሊንኮችን ብቻ እንዲያጋሩ ይገድባል።

ሜታ ገደቡ የፕሮፌሽናል ሞድ የሚጠቀሙ ሰዎችንና የፌስቡክ ፔጆችን እንደሚመለከት ገልጿል።

የሜታ ቃል አቀባይ ሙከራው ከሊንኮች ጋር ተጨማሪ ልጥፎችን ማጋራት መቻል የሜታ ሰብስክሪፕሽንን እንደሚጨምር ለማየት ስለመሆኑ ገልጿል።

የሜታ ሙከራ ከሌሎች መተግበሪያዎቸ የሚደርሱትን አንባቢ ለመጨመር የሚሞክሩ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ሲኖረው ተጠቃሚዎች አሁንም በሃሳብ መስጫዎች ሊንኮችን ማጋራት ይችላሉ ብሏል።

🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
10👍1
ጋና ክሪፕቶከረንሲ መጠቀምን ህጋዊ ለማድረግ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ አፀደቀች።

ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሃገር ጋና የናይጄሪያ እና ኬንያን ፈለግ በመከተል ክሪፕቶከረንሲ መጠቀምን ህጋዊ የሚያደርግ ህግ በፓርላማዋ አጽድቃለች።

በ2025 ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሃገራት የሚደረገው የክሪፕቶከረንሲ የንግድ መጠን ከ205 ቢሊየን ዶላር የተሻገረ ሲሆን ሃገራት ከዘርፉ ለመጠቀምና ለመቆጣጠር ህጎችን እያወጡ ይገኛሉ።

ከሰሃራ በታች ካሉ ሃገራት ናይጄሪያ በንግድ መጠኑ ቀዳሚ ስትሆን ጋና፣ ኢትዮጵያ ፣ ኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ ተከታዮች መሆናቸው ተነግሯል።

የጋና 3 ሚሊየን ወጣት ክሪፕቶከረንሲ ይጠቀማል ሲባል ዘርፉ ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ይንቀሳቀስበታል ተብሎም ይገመታል።

ጋና ታዲያ ይህንን ዘርፍ የሃገሪቱ ማዕከላዊ ባንክና የሰነደ ሙአለ ንዋዮች ኮሚሽን እንዲቆጣጠረው እና ወደ መደበኛ ኢኮኖሚ ገብቶ ሃገሪቷ እንድትጠቀም የሚያስችል ህግ አፅድቃለች።

ጋና የክሪፕቶከረንሲ አገልግሎት ሰጪዎች ከሁለቱ አካላት ፈቃድ እንዲወስዱ ያስቀመጠች ሲሆን ይህም ዘርፉ የሚተችበትን የገንዘብ ማጭበርበር ለመከላከል ይረዳል ተብሏል።

ክሪፕተከረንሲ በተደጋጋሚ ከገንዘብ ማጭበርበር ጋር ተያይዞ የሚነሳ ሲሆን ናይጄሪያ ከዚህ ቀደም ባይናንስ የተሰኘውን የክሪፕቶከረንሲ መለዋወጫ የኢኮኖሚ ጥቅሜን አሳጥቶኛል በሚል የ81 ቢሊየን ዶላር ክስ መክፈቷ ይታወሳል።

የጋና ማዕከላዊ ባንክ ገዢ ጆንሰን አሲያማ ከዚህ ቀደም
በጨዋታው ወደኋላ ቀርተናል ብለው የህግ ለውጥ እንደሚኖር መናገራቸው ሲታወስ አሁን በፓርላማው የፀደቀው ህግ ያለውን ስጋት ለመቆጣጠር የሚያስችል ማዕቀፍ ይሰጣል ብለዋል።

🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT       
6
ELA TECH💡
Photo
የንግድ ባንክ አካውንታችሁን ከፋይዳ መታወቂያችሁ ጋር ለማስተሳሰር የግድ ቅርንጫፍ ሄዳችሁ መሰለፍ አይጠበቅባችሁም።

🔻የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ኅዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መመሪያ መሠረት፤ ሁሉም ደንበኞች የባንክ አገልግሎቶች ለማግኘት እና ሒሳብ ለማንቀሳቀስ የፋይዳ መታወቂያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::

🔻በዚህ መሠረት ባንካችን ደንበኞች ወደቅርንጫፍ ቀርበው የሒሳብ ቁጥራቸውን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ከሚያጣምሩበት አሠራር በተጨማሪ ባሉበት አገልግሎቱን የሚያገኙበትን አማራጭ አመቻችቷል።

🔻በመሆኑም ከታች በተቀመጠው የአሠራር ቅደም ተከተል መሠረት  የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥርዎን (16 አሀዝ-FAN Number) በማስገባት  የባንክ ሒሳብ ቁጥርዎን ከፋይዳ መታወቂያዎ ጋር ያጣምሩ::

1.  ይህን ማስፈንጠሪያ 👉
https://cbefayda.cbe.com.et/ በመጫን/ በማስገባት ገፁን ይክፈቱ፣
2.  የሂሳብ ቁጥርዎን አስገብተው ‘Get OTP’ የሚለውን ይጫኑ፣
3.  ሒሳብ ሲከፍቱ ያስመዘገቡትን የስልክ ቁጥር በሚጠቀሙበት የተንቀሳቃሽ ስልክ የተላከልዎትን የአንድ ጊዜ የሚስጥር ቁጥር (OTP) አስገብተው “Verify OTP” የሚለውን በመጫን ያረጋግጡ፣
4.  “Log with OTP” የሚለውን ይጫኑ፤
5.  የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥርዎን (16 አሀዝ-FAN Number) አስገብተው ‘Get OTP’ የሚለውን ይጫኑ፣
6.  በድጋሚ በተንቀሳቃሽ ስልክዎ የተላከልዎትን የአንድ ጊዜ የሚስጥር ቁጥር (OTP) አስገብተው “Verify” የሚለውን በመጫን ያረጋግጡ፣
7.   “Allow” የሚለውን ይጫኑ፣
8.  “Accept and Update” የሚለውን ሲጫኑ “Update complete. Pending Approval” የሚል መልእክት ይመጣልዎታል። ጨርሰዋል።

*

➡️ሲስተሙ ብዙ ጊዜ ያስቸግራል። ስለዚህ በተቻለ መጠን እየደጋገማችሁ traffic በማይበዛበት ሰአት ሞክሩት።
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
3👍3
የገናን በዓል በማስመልከት በቻናላችን ላይ ማስታወቂያ ማሰራት ለምትፈልጉ በሙሉ ታላቅ የበዓል ቅናሽ አድርገናል ።

🔻ይሄን ልዩ ቅናሽ በመጠቀም ምርትዎን እና አገልግሎትዎን በማስተዋወቅ በእጥፍ ያትርፉ።

ከ እኛ ጋ በመስራትዎ ይደሰታሉ ❗️

አሁኑኑ ያናግሩን 👇

@Its_eliyass
3
Postal Code ምንድን ነው?
Postal Code (ZIP Code)


🔻የ አንድ አካባቢ ወይም አድራሻ በትክክል ለመለየት

🔻 በፖስታ እና በመላኪያ አገልግሎቶች የሚጠቀምበት ኮድ ነው

⚙️ Postal Code እንዴት ይሰራል?

1️⃣ አገር ይለያል
👉 እያንዳንዱ አገር የራሱ የPostal Code ስርዓት አለው

2️⃣ ክልል / ከተማ ይጠቁማል
👉 Code መጀመሪያ ክፍል = ክልል
👉 መጨረሻ ክፍል = ቀጠና / መንደር

3️⃣ ፖስታ በፍጥነት ይደርሳል
👉 መልእክት ወይም እቃ
👉 በትክክል ቦታ ይደርሳል

🌍 ምሳሌ
🇺🇸 USA: 10001
🇬🇧 UK: SW1A 1AA
👉 SW = London

City
Sub-city
Phone number
በመጠቀም ይላካል

Postal Code ለምን አስፈላጊ ነው?
✔️ Online shopping (AliExpress, Amazon)
✔️ PayPal / Bank registration
✔️ Package delivery
✔️ Address verification

⚠️ ማስጠንቀቂያ

የሌለ Postal Code በዘፈቀደ አትጻፍ
✔️ ከተማህን የሚወክል code ተጠቀም
✔️ “0000” ወይም “1000” ብዙ ጊዜ ይቀበላሉ (እንደ platform)

💡 Tip
👉 Online form ሲሞላ
👉 Postal Code ካልጠየቀ
👉 “N/A” ወይም City code መጠቀም ይቻላል

══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
👍1
በ 2010 ይህ Website ስለ ገባችሁበት ብቻ ለየ ኣንዱንድ ሰዉ 5 Bitcoin በነፃ ይሰጥ ነበር።

🔻ዛሬ 5 Bitcoin $447,200 ያወጣል።
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
😭5👏21👍1🔥1