ELA TECH💡
188K subscribers
1.34K photos
28 videos
410 files
1.03K links
👋 ሰላም ሰላም እንኳን ወደ ELA TECH በሰላም መጡ

ለማንኛዉም ጥያቄ , አስተያየት እንዲሁም ሀሳብ
በዚ ያገኙናል
👇
@ELA_TECHBOT

በ Youtube ጠቃሚ ቪዲዮችን ለማግኘት የ YOUTUBE ቻናላችንን ይጎብኙ
👇
https://youtube.com/@ELA_TECH
Download Telegram
Evolution_of_Windows

🔻
Windows 1  1985
🔻Windows 3.1 1992
🔻Windows 95 1995
🔻Windows xp 2001
🔻Windows vista 2007
🔻Windows 7 2009
🔻Windows 8 2012
🔻Windows 10 2015
🔻Windows 11 2021


══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
7
ቻይና የግብረሰዶማዊ ይዘት ያላቸውን አፕሊኬሽኖች Appleን በማስገደድ ከApple store ላይ ማስወረዷ ተገለፀ።

🔻አፕል የቻይና መንግስትን ትዕዛዝ በማክበር በቻይና ውስጥ ሁለት በጣም ታዋቂ የሆኑ የግብረ-ሰዶማውያን dating መተግበሪያዎችን ከApp Store ላይ አስወግዷል።

🔻መተግበሪያዎቹ የቻይና የሳይበር ስፔስ አስተዳደር በሰጠው ቀጥተኛ ትዕዛዝ ከIOSና ሌሎች ብዛት ያላቸው የAndroid stores ላይ እንዲወርዱ ተደርገዋል።

🔻የአፕል ቃል አቀባይ "የምንሠራባቸውን ሀገሮች ህግ እናከብራለን። ለዚህም የቻይና የሳይበር ስፔስ አስተዳደር በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት ሁለት መተግበሪያዎችን ከቻይና store ላይ አስወግደናል።" በማለት በኢሜል መግለጫ ሰጥተዋል።

🔻ቻይና በሀገሯ ውስጥ የነበሩ በርካታ የግብረሰዶማውያን መብት ተሟጋች ድርጅቶችን ዘግታለች። እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ የግብረሰዶማዊ ይዘት ያላቸውን ይዘቶች ከፍተኛ ቁጥጥር ታደርጋለች አካውንቶችንም ትዘጋለች።

🔻Apple ግብረ ሰዶማዊነትን በማቀንቀን ከፊት የሚሰለፍና የግብረ ሰዶማውያንን መብት በምንም አይነት ሁኔታ እንደማይደራደርበት የሚናገር ድርጅት ቢሆንም ትልቅ የገበያ መዳረሻው የሆነችውን ቻይናን ግን መጋፈጥ አልፈለገም።


©️@bighabesha_softwares
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
👍2017👏12🔥2
በ"ChatGpt" የተፃፈው የፓኪስታን ጋዜጣ ፅሁፍ

🔻የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ከመጣ በኋላ ሁሉም በየዘርፉ ለመጠቀም እየሞከረ ሲሆን በ1941 በፓኪስታን መታተም የጀመረው "Dawn" የተሰኘው ጋዜጣ ሰሞነኛ ተግባር ግን መነጋገሪያ ሆኗል።

🔻በጋዜጣው ላይ ፀሃፊ የሆነው አንዱ ጋዜጠኛ ስለ መኪና ሽያጭ መጨመር የሚያብራራ ፅሁፍ የፃፈ ሲሆን በፅሁፉ መካከል ከቻትቦቱ የተሰጠዎ ምላሽ ተካቶበታል( በምስሉ የሚታየው)።

🔻የሰው ሰራሽ አስተውህሎቱን ብዙዎቹ "ChatGpt" እንደሆነ ሲጠቅሱ በፅሁፉ ውስጥም በተካተተው ምላሽ ፊት ገጹን ሊሰራለት እንደሚችል ሲጠይቀው ተካቷል።

🔻ጋዜጣው ፅሁፉ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የተሰራ መሆንን ያመነ ሲሆን ኦንላይን ባለው ይዘት ላይ ማሻሻያ በማድረግ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት እንደተሰራ የሚያሳይ ማስታወሻ አካቶበታል።

🔻ጋዜጣው ተግባሩ ፖሊሲውን የጣሰ እንደሆነ ገልፆ ምርመራ መጀመሩንም ገልጿል።

ዘገባው ከፋይናንሻል ኤክስፕረስ የተወሰደ ነው። 🔎

══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
13
በ2020 የተለያዩ ሰዎችን የቲዊተር አካውንት ጠልፎ የነበረው ግለሰብ 5.4 ሚሊየን ዶላር የሚያዋጣ ቢትኮይኑ ሊወረስ ነው።

🔻ጆሴፍ ጀምስ የተባለው የ26 ዓመት ወጣት በወቅቱ እንደ ጆ ባይደን፣ ኢሎን መስክ፣ ባራክ ኦባማ፣ ቢል ጌትስና ዋረን ቡፌት ያሉ ዝነኞችን የቲዊተር አካውንት ከጠለፈ በኋላ ሰዎችን ሲያጭበረብር ነበር።

🔻በጠለፋቸው አካውንቶችም ተከታዮች በርከት ያለ ቢትኮይን እንዲልኩና በምላሹ እጥፍ አድርጎ እንደሚመልስ ቃል በመግባት በርካቶችን አጭበርብሮ ነበር።

🔻በ2021 በስፔን ከተያዘ በኋላ ስፔን ግለሰቡን ለአሜሪካ አሳልፋ የሰጠች ሲሆን በ2023 በአሜሪካ የአምስት አመት እስር ተፈርዶበት ነበር።

🔻የብሪታኒያ መርማሪዎችም ከማጭበርበሩ ጋር የተገኙ 42 ቢትኮይንና ሌሎች የዲጂታል ሃብቶችን ለመያዝ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል።

🔻ቢትኮይኑና ግለሰቡ በማጭበርበሩ ያገኛቸው ሌሎች ዲጂታል ሃብቶች በፍርድ ቤት በሚመረጥ አካል በኩል እንዲሸጥ እና ግለሰቡ ሲፈታ ምንም አይነት ጥቅም ከማጭበርበሩ እንዳያገኝ ወስኗል።
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
3
በዓለም ዙሪያ የዋትስአፕ ተጠቃሚዎችን ያነጣጠረ መጠነ ሰፊ የሳይበር ጥቃት ዘመቻ መከፈቱ ተገለጸ።


🔻ይህ የሳይበር ጥቃት አላማም የዋትስአፕ አካውንቶችን በመጥለፍ ተጠቃሚው በዋትስአፕ WhatsApp ፕላትፎርም ላይ ያለውን እምነት ማሳጣት እንደሆነ   CTM360 የተባለዉ የሳይበር ደህንነት ምርት አቅራቢ ኩባንያ ጠቁሟል። 

🔻ይህ ዋትሳፕን ኢላማ አድርጎ የተከፈተዉ  ዘመቻ “HackOnChatˮ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

🔻ከዚህ አጥፊ ተልዕኮ ጀርባ ያሉ አጭበርባሪዎች ጥቃታቸዉን ለመሰንዘር የተለያዩ የማጭበርበሪያ አማራጮችን የሚጠቀሙ ሲሆን ከእነዚህ መካከልም ተመሳስሎ የተሰራ ድረ-ገጽ በመፍጠርና የዋትሳፕ ገጽታን በመላበስ  የሚፈጸም ማጭበርበር ነዉ።

🔻የመረጃ መንታፊዎቹ ተጠቃሚዉ ወደ አካዉንቱ ከፍቶ ሲገባ እንዳይጠራጠር ጉዳዩ አስቸኳይ እንደሆነ በማስመሰል ትኩረት የመበተን ታክቲክን እንደሚጠቀሙ ተገልጿል።

🔻“HackOnChatˮ የጥቃት ዘመቻ የተለያዩ የማህበራዊ ምህንድስና ቴክኒኮችን የሚጠቀም ሲሆን አለምአቀፍ የዋትሳፕ ተጠቃሚዎችን ለማጥቃት በተለያዩ ቋንቋዎች ሀሰተኛ ገፆችን በመክፈት ተጽእኖዉን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ማሳደጉ ታዉቋል።

🔻“የCTM360” የስጋት ትንተና ቡድን በአሁኑ ሰዓት የዚህን የጥቃት ዘመቻ ዝግመተ ለውጥ የመከታተል፣ ቴክኒካል ስልቶቻቸውን የመተንተን እና ስርጭታቸውን ለመግታት የተለያዩ  እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝ ገልጿል።
 
🔻ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በሃገራችን የዋትሳፕና የቴሌግራም አካዉንቶች ጠለፋ እየተበራከተ ይገኛል። በመሆኑም ዋትሳፕን ጭምሮ ሌሎች አካዉንቶታችንን ከፍተን ስንገባ የምንገባበት ድረ-ገጽ ትክክለኛ ገጽ መሆኑን በማረጋገጥ ሊድርስብን የሚችልን ጥቃት ልንከላከል ይገባል።
══════❁✿❁═══════                          
9👍1👏1
Telegram tip

🔻የስልካችሁ contact list ውስጥ ያሉ ሰዎች ቴሌግራም አካውንት ሲከፍቱ እንትና joined telegram እያለ ሜሴጅ እየገባ ካሰለቻችሁ እንዴት እንደምታስተካክሉት አነሆ፦

🔻በመጀመሪያ ወደ telegram settings ከሄድን በኋላ notification and sounds የሚለውን በመንካትና ትንሽ ወደታች ዝቅ አድርገን የምናገኘውን contact join telegram የሚለውን off ወይም disable ማድረግ። ተገላገላችሁ።
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
👍43🥰1
ታላቅ የማስታወቂያ ቅናሽ አድርገናል !

- በተወዳጁ ቻናላችን ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ ?

▪️ የ ቻናል ማስታወቂያ
▪️ የ ሙዚቃ ማስታወቂያ
▪️ የ ድርጅት ማስታወቂያ
▪️ የ ቡቲክ ልብሶች ማስታወቂያ
▪️ የ ዩቲዩብና የቴሌግራም ቻናል ማስታወቂያ
▪️ ትሪትመንቶች
▪️ Consultancy
▪️ Technology accessories
▪️ ማንኛውም የትምህርት ማስታወቂያ እና
▪️ ሌሎችንም ሽያጮች ያስተዋውቁ

- ይሄን ልዩ ቅናሽ በመጠቀም ከ190,000+ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ምርቶን በማስተዋወቅ በእጥፍ ያትርፉ።

አሁኑኑ ያናግሩን
👉 @Its_eliyass
5
ለተራራማዎቹ የቻይና ግዛቶች የትራንስፖርት ችግር መፍትሔ እየሆኑ ያሉት የጭነት ድሮኖች

🔻በደቡብ ምዕራብ ቻይና የምትገኘው የጉዊዡ ግዛት ባላት የተፈጥሮ አቀማመጥ ምክንያት ለዘመናዊ ትራንስፖርት አመቺ የምትባል አይደለችም።

🔻በግዛቷ አደጋ ሲከሰት እና በፍጥነት መድኃኒቶችን እና አስፈላጊ ግብዓቶችን  ለማከፋፈል በሚያስፈልግበት ወቅት የሚወስደውን ጊዜ ለመቀነስ መፍትሔ በማፈላለግ ላይ የነበሩ የግዛቷ ባለሥልጣናት የጭነት ድሮኖችን መጠቀም  ተመራጩ መፍትሔ መሆኑን ለይተው ወደ ሥራ ገብተዋል።

🔻በኤሌክትሪክ የሚሠሩት የጭነት ድሮኖቹ ከመደበኛው የድሮን ዓይነቶች የሚለዩት በሚይዙት የጭነት ብዛት በዝቅተኛ ከፍታ መብረር መቻላቸው ነው ተብሏል።

🔻በዚህም ለተራራማዋ መንደር አስፈላጊ ናቸው የተባሉ መድኃኒቶችን እና የግብርና ምርቶችን የያዘ እስከ 2 ቶን የመሸከም አቅም ያለው ድሮን 118 ኪ.ሜ በተሳካ ሁኔታ በረራ ማድረግ ችሏል።
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
3👍3🔥1
🔻ብዙ ጊዜ ላፕቶፓችሁ የሆነ ስራ እየሰራችሁ ድንገት የሚዘጋ ወይም restart የሚያደርግ ከሆነ most probably ፋኑን ቆሻሻ ደፍኖት ነው የሚሆነው።

🔻ስለዚህ ፎርማት ከማድረጋችሁ ወይም technician ላይ ወስዳችሁ ከማሳየታችሁ በፊት ራሳችሁ ከቨሩን አንስታችሁ ፋኑን አፅዱት።


©bighabeshaTech
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
6
ELA TECH💡
Photo
ለቻይናውያን የተሰራው Douyin አፕ ፡ ከቲክቶክ በምን ይለያል ?
....
🔻ቻይና ፡ ቲክቶክን ከቻይና ምድር አስወግዳ ፡ ለሀገሯ ህዝብ የፈጠረችው ይህ Douyin የሚባል አፕ ፡ ከቲክቶክ ጋር የሚመሳሰለው በሎጎ ብቻ ነው ። ከዛ በተረፈ  በዓላማ ፡ በይዘትና በቁጥጥር ከቲክቶክ ፍጹም የተለየ ነው ።
.......
🔻የቲክቶክ ፈጣሪ የሆነችው ቻይና  ቲክቶክን በሀገሯ ከልክላ Douyin የተሰኘውን ተመሳሳይ አፕ ለምን መፍጠር አስፈለጋት ከተባለ ቲክ ቶክ በአለም አቀፍ ደረጃ  እየፈጠረ ያለውን የሥነምግባርና  ተያያዥ ችግሮች ስለምታውቅ ነው ።
......
🔻ይህ ለቻይናውያን የተሰራ አፕ  በተለይም ለወጣቱ ትውልድ ልክ እንደ ቲክቶክ ዝም ብሎ መዝናኛ ላይ ብቻ ያተኮረ ይዘት ከማቅረብ ይልቅ  እንደ ብሔራዊ የሞራል እና የእውቀት ማበልጸጊያ መሣሪያ ሆኖ ያገለግላል።
....
🔻ይህን አላማው አድርጎ ስለተሰራም ብልግና ነክ ኮንተንቶች ሌላው ቀርቶ ከልክ ያለፈ የቅንጦት ሕይወት ማሳየት እና ጊዜን የሚያባከኑ ቪዲዮዎች በአጠቃላይ የባህላዊ እሴቶችን የሚቃረን ማንኛውም ይዘት በአልጎሪዝሙ  ይሰረዛል ወይም ከእይታ ውጭ ይደረጋል።

🔻በተቃራኒው የ Douyin አልጎሪዝም ሆን ተብሎ የበለፀገው  አዎንታዊና ገንቢ ኮንተንቶች ላይ ነው ።
......
🔻በዚህም መሰረት አልጎሪዝሙ ቫይራል የሚያደርጋቸው ቪዲዮዎች የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ትምህርቶች ፡ ፋይናንስ የፈጠራ ችሎታ፡ የበጎ አድራጎት ሥራ፣ ጠንካራ የቤተሰብ ትስስር እና ብሔራዊ ኩራትን የሚያጎሉ ቪዲዮዎች ናቸው።
.........
🔻ሌላው የእድሜ ቁጥጥር ነው ። በዚህ አፕ የሚጠቀሙ ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች በቀን ከ40 ደቂቃዎች በላይ አፑን መጠቀም እንዳይችሉ ተደርጎ ነው የተሰራው ።

🔻እንዲሁም ተማሪዎች ከምሽቱ 4  ሰዓት እስከ ጥዋት 12 ሰአት ድረስ ባለው ጊዜ አፑን  እንዳይጠቀሙ ሙሉ ለሙሉ ይዘጋል ይህም ወጣቶች ለትምህርታቸውና  ለእረፍታቸው ተገቢውን ጊዜ እንዲሰጡ  ለማድረግ ተብሎ ነው ።
......
🔻አስገራሚው ነገር ፡ በተቃራኒው ቲክቶክ ላይ ቫይራል የሚሆኑ ነገሮች በቻይናው አፕ ላይ የሚከለከሉ ነገሮች ናቸው ።

🔻አስገራሚው ነገር ፡  በዘፈቀደ የሚመራውን ቲክቶክን ለአለም ያበረከተችውም  . .. በጥብቅ የዲሲፕሊን ህግ የሚመራውንና   ከሀገሯ የሞራልና የልማት ግቦች ጋር በሚስማማ መልኩ የሚሰራውን Douyinንም የፈጠረችው ቻይና መሆኗ ነው ።
......
🔻ዘግይቶም ቢሆን ይህ እየገባቸው ያሉ እንደህንድ እና ኢራንን የመሳሰሉ  ሀገራት ቲክቶክን ከሀገራቸው ካገዱ ቆይተዋል ።

©ዋሲሁን ተስፋዬ
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
👍96
Best-Selling Phones Ever (2025)

1️⃣ Nokia 1100 — 250M
2️⃣ Nokia 1110 — 248M
3️⃣ iPhone 6/6 Plus — 222M
4️⃣ Nokia 105 — 200M
5️⃣ iPhone 6S/6S Plus — 174M
6️⃣ iPhone 5S — 165M
7️⃣ Nokia 3210 — 161M
8️⃣ iPhone 7/7 Plus — 160M
9️⃣ iPhone 11 Series — 159M
🔟 iPhone XR/XS Series — 151M
©Ethio tech
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
🔻"ሰዎች ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) የሚነግራቸውን ሁሉ በጭፍን ማመን የለባቸውም

🔻የኤአይ ሞዴሎች ለስህተት የተጋለጡ ናቸው። ሰዎች ከሌሎች መሳሪያዎች ጋር ሊጠቀሟቸው ይገባል።

🔻ሰዎች እነዚህን መሳሪያዎች ጥሩ በሆኑት ጉዳይ ላይ ብቻ መጠቀምን መማር እንዲሁም የሚናገሩትን ሁሉ በጭፍን አለማመን አለባቸው" - ሳንዳር ፒቻይ (የጉግል እናት ኩባንያ አልፋቤት ኃላፊ)


ምንጭ: ቢቢሲ
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
1
ELA TECH💡
Photo
ህንድ የስማርት ስልክ አምራቾች በራሷ የበለፀገውን የሳይበር ደህንነት መተግበሪያ ቀድመው በስልኮቹ እንዲጭኑ አዛለች።

🔻የህንድ የቴሌኮም ሚኒስትር የስማርት ስልክ አምራቾች በመንግስት የበለፀገውን የሳይበር ደህንነት መተግበሪያ ቀድመው አዳዲስ በሚያመርቷቸው ስልኮች እንዲጭኑ በሚስጥር መጠየቁ የተነገረ ሲሆን መተግበሪያውን ከስልክ ላይ ማጥፋት አለመቻሉ ደግሞ የግለሰባዊ ደህንነት ጥያቄን አጭሯል።

🔻ህንድ እየበዛ ያለውን የማጭበርበር እና የሳይበር ወንጀሎች ለመከላከል እንደዚሁም ሰዎች በተሰረቁ ስልኮች ወንጀሎችን እንዳይፈፅሙ ለመከላከል ይህንን እርምጃ መውሰዷ ተሰምቷል።

🔻እንደ አፕልና ሳምሰንግ ያሉ የስልክ አምራቾችም ይህንን መተግበሪያ በአዳዲስ ስልኮች መጫን እንዲጀምሩ የ90 ቀናት የጊዜ ገደብ ሲሰጣቸው እየተመረቱ ባሉ ስልኮች ላይ ደግሞ በሶፍትዌር ማሻሻያ መልክ እንዲጫኑ ለህዝብ ይፋ ባልሆነው ጥያቄ አዛለች።

🔻ሳንቻር ሳታሂ የተባለው ይህ መተግበሪያ የሩሲያ ማክስ የተሰኘ መልዕከት መለዋወጫ በስልኮች ላይ ቀድሞ እንዲጫን ባለፈው ነሐሴ ወር ካስገደደች በኋላ የመጣ ነው።

🔻ህንድ ይህ መተግበሪያ ባለፈው ጥር ወር ከተለቀቀ በኋላ ከ700,000 በላይ የጠፉ ስልኮች እንዲገኙ ምክንያት ሆኗል ስትል 30 ሚሊየን የሚሆን የማጭበርበር ግንኙነቶችንም አቋርጧል ብላለች።

🔻በ2025 በህንድ ከሚገኙት 735 ሚሊየን ስማርት ስልኮች ውስጥ 4.5% ተጠቃሚዎች ያሉት አፕል ህጉ የመንግስት መተግበሪያዎችን ቀድሞ በስልኮች ላይ መጫንን የሚከለክል ሲሆን ሌሎች የስልክ አምራቾች በጉዳዩ ላይ ምላሽ አልሰጡም።

ዘገባው የሮይተርስ ነው።
══════❁✿❁═══════
                                                                           
5
የኤ.አይ (AI) ክህሎትና እውቀት መቼ ያስፈልገናል ? . . . አሁን ያስፈልገናል!

🔻ኤ.አይን መሰረት ያደረጉ ሀሰተኛ መረጃዎች ሥርጭት በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ በመሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡

🔻ከዚህ ቀደም በጹሐፍ ወይም ፎቶ በማቀናበር ይለቀቁ የነበሩ ሀሰተኛ መረጃዎች አሁን ላይ በቀላሉ ጹሑፍም ሆነ ተለጣፊ ምስል( Picture ) ወይም ተንቀሳቃሽ ምስል( Video ) የታገዘ ለማድረግ ቀላል ሁኔታዎች ስለተመቻቹ ሥርጭቱንና መጠኑን ጨምሮታል፡፡

🔻በኤ.አይ የሚፈጠሩ ይዘቶች ለዕይታ ታሳቢ እና አጓጊ ሆነው ስለሚፈጠሩም በቀላሉ ሰዎች ጋር የመድረስ እና የማሳመን አቅማቸው ከፍተኛ ነው፡፡

🔻እንዳንዶቹን ይዘቶች መለየት እስከሚከብድ ድረስ ለፍጹም ምስስል የቀረቡ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ የኤ.አይ (AI) ክህሎትና እውቀት አሁን ያስፈልገናል ስንል ይህንን ለመለየት አቅም መፍጠር ግድ ስለሚል ጭምር ነው።

🔻በአንጻሩ፥ ኤ.አይን ለሥራችን እንዲሁም ለመልካም ነገር ለመጠቀም ትክክለኛውን አጠቃቀም መረዳት ያስፈልጋል። ለዚህም አስፈላጊውን ክህሎትና እውቀት ማዳበር ያስፈልጋል።
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
4
Prompt Engineering? ምንድነው ?

🔻ጄኔሬቲቭ ኤ.አይ (Generative Ai) ከተዋወቀ በኋላ ሰዎች በብዛት ኤ.አይ መተግበሪያዎችን መረጃ ለማግኘት፣ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ፣ ዝርዝር ነገሮችን ለማሳጠርና ግልጽ ለማድረግና ለብዙ ጉዳዮች እየተጠቀሟቸው ይገኛል።

🔻እነዚህ አገልግሎቶች በነጻ ሁሉም ሰው በብዛት የሚጠቀማቸው ቢሆኑም ለሁሉም ሰው እኩል አገልግሎት ይሰጣሉ ማለት ግን አይደለም።

ታዲያ ለሰዎች የሚሰጠው ምላሽ ላይ ያለው ልዩነት ከምን የሚመነጭ ነው ?

🔻ኤ.አይ ሞዴሎች ለሚሰጡት ምላሽ ተገቢውን ጥያቄ፣ ወይም መረጃውን ሊረዱበት በሚችለው መንገድ ማቅረብ የተሻለ ምላሽ እንድናገኝ ይረዳናል። ይህንን ተግባር ወይም ሞያ "Prompt Engineering " ብለን እንጠራዋለን።

🔻ግልጽ ትዕዛዞችን ማስተላለፍ መቻል፣ መጠየቅ ስለምንፈልገው ጥያቄ የተገደበ እና በአጭሩ የተብራራ መረጃ መስጠት፣ በሚሰጡን ምላሾች ላይ ተደጋጋሚ ማሻሻያዎችን መጠየቅ፥ የተሻለ ምላሽ ለማግኘት ከሚጠቅሙን መካከል ይጠቀሳሉ።

🔻በተጨማሪም፥ በአንድ ጊዜ አንድ ርዕሰ ጉዳይ ነጥሎ (ትኩረት አድርጎ) መጠየቅ፤ ምሳሌዎችን ማቅረብ፤ መረጃዎች ቅደም ተከተላቸውን ጠብቀው አንዲቀመጡ ትዕዛዝ ማስቀመጥ፤ በምን አይነት መልኩ ምላሹን እንደምንፈልገው በግልጽ መግለጽ ጥራት ያለው ምላሽ እንድናገኝ ያግዙናል።

ምን ጥንቃቄ ማድረግ አለብን ?

🔻ኤ.አይ ሞዴሎች ትክክለኛ ምላሽ ላይሰጡን ስለሚችሉ መረጃዎችን እንደወረደ ከመጠቀም ተቆጥበን ምላሾቹን ማንበብ፣ ደግሞ ማጣራትና ይዘቱን መፈተሽ ያስፈልጋል።

🔻በተጨማሪም፥ ኤ.አይ ሞዴሎች አሰራራቸው ምላሽ ለመስጠት ነው። ስለዚህ የምንጠይቀው ጥያቄ ግልጽ ባይሆንም ምላሽ ይሰጣሉ።

🔻መረጃ በሌላቸው ጉዳይ ላይም የቅዠት መረጃ (AI hallucinations) ይሰጣሉ። ስለዚህ በሚሰጡን ምላሾች ላይ ማጣራት፤ መልሶ መጠየቅ እና በሌሎች መረጃዎች መደገፍ ያስፈልጋል።
8
MIT በchatGPT ተጠቃሚዎች ላይ ያጠናውን ጥናት ይፋ አድርጓል።

⛔️ጥናቱ በ3 ቡድን ተከፍሎ essay እንዲፅፉ ተደርገዋል።
_ በአምሯቸው ብቻ ተጠቅመው የሚሰሩ
_ Search engine ብቻ የጠቀሙ (Could use Google but no AI)
_ AI ብቻ የሚጠቀሙ (use GPT-4o)

⛔️የጥናቱ ተሳታፊዎች አንጎል scan ከተደረገ በኋላ
83.3% የሚሆኑት AI ተጠቃሚዎች ከደቂቃዎች በፊት በAI አማካኝነት የፃፉትን አንድም አረፍተ-ነገር ማስታወስ አልቻሉም።

⛔️የአንጎል ግንኙነታቸው ከ79 ወደ 42 ነጥብ ዝቅ ብሏል። ይህም 47% የነርቭ ግንኙነታቸው ወርዷል ተብሏል።

⛔️chatGPT መጠቀም ካቆሙ በኋላም ቀጣይነት ያለው የማስታወስ ድክመትና chatGPT ከማይጠቀሙት ያነሰ አፈፃጸም ተስተውሎባቸዋል። ይህም በAI ጥገኛ ከመሆንም ባለፈ የግንዛቤ ድክመት (cognitive weakening) ነው ተብሏል።

⛔️chatGPTን መጠቀም ስራዎችን 60% በፍጥነት ለማጠናቀቅ ቢረዳም አእምሮ ግን የመማርና የማገናዘብ ጥረቱን በ32% ቀንሶ ተገኝቷል።

⛔️በአጠቃላይ ያለAI የሰሩት ከፍተኛ የማስታወስ ችሎታን፣ የአንጎል እንቅስቃሴን ያስመዘገቡ ሲሆን chatGPTን የሚጠቀሙ ደግሞ ስራቸውን በፍጥነትና በቅልጥፍና ቢጨርሱም በተቃራኒው ዝቅተኛ የማስታወስ ችሎታና የአንጎል እንቅስቃሴ አስመዝግበዋል ተብሏል።

⛔️ስለዚህ AIን ተጠቀሙ ግን እንዲያግዛችሁ እንጂ እንዲተካችሁ አታድርጉት፤ ጥገኛ አትሁኑ፤ በማንኛውም ጊዜ በአእምሯችሁ የመስራት ችሎታችሁን አትጡ።

Credit :-
bighabesha_softwares
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
10👍7🔥3👏1