ሰኪነቱል ሩህ🖤
486 subscribers
41 photos
3 videos
1 link
መልካም የሆነ ማንፀባረቅን ከዉስጥ የሚዘልቅ ንፅፅርን እንዲሁም እርጋታን የሚሰጥ ፅሁፍን በአንድ ላይ ተሰናድቶ የሚቀርብበት channal🙌
Download Telegram
...አንድ ቀን አላህ በምትጠብቀው መልካም ነገር ያበስርሃል... እርሱ ዕጣ ፈንታን በቅጽበት ቀያያሪ የሆነ ጌታ ነው .... ምቾትንም መከራ ካደከመው ልብ ውስጥ ሊከስት ዘንድ ቻይ ነውና....በአላህ ላይ መልካምን እንጅ አትጠርጥር...
                                  
             
      [..وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ..]     
     «.. አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡...»

صباح النور ☕️
💔5🔥1
Someone said

🌱ለጉዳይህ ስትል ሶላትህን በጥድፊያ አትስገድ ምክንያቱም የቆምከው የቸኮልክበትን ጉዳይህን ጨምሮ
ዱኒያን ሁሉ የያዘው ጌታህ ፊት ነውና»
🔥12🥰5
በእምባና ተሀጁድ መሀከል
ክፍል 4

የግቢያቸዉ አለ ከሚሉት ጎበዝና ትጉ አስተማርያቸዉ ሪድዎን ነዉ ሩሂን ከመንገዷ ገታ ያደረጋት ......

ሪድዎን: " ምነዉ ሩሂ የደነገጥሽ ትመስያለሽ"
ሩሂ : አረ ምንም ሚስተር የምጠብቀዉ ሰዉ መስለኸኝ ነዉ
ሪድዎን: እንዴት እስካሁን አረፈድሽ ሰርቪስ ተጠቃሚም አይደለሽም አላት
ሰርቪስ ብዙ ጊዜ ቆይቶ ስለሚመጣ ያንን ለምክንያት እያቀረበ .....
መልስ አልሰጠችዉም እሱ ግን ቀጠለ
አጋጣሚዎችን ስጠብቅ ነበር ወደ አንቺ ቀርቦ ለማዉራት
እንደምታዉቂዉ ነዉ እዚ ግቢ ሙስሊም ተማሪ እንጂ ሙስሊም አስተማሪ እብዛም የለም ሙስሊም አስተማሪ በመሆኔ ከተማሪ ባልተናነሰ መልኩ በደሎችን ላስተናግድ እችላለዉ ብሎ ከማለቱ እንዴት የሚል አስተያየት ቀና ብላ አየችዉ
ምን መሰለሽ ሩሂ ብዙ ጊዜ የሰላት ሰኣቴ ይሸራረፋል አንዴ ስብሰባ አንዴ ቲቶር አንዴ ደግሞ ክላስ በሚል አላስፈላጊ ሀተታ ብቻ ሁሉም ነገር እንደገፅታዉ ቀላል አይደለም ብዙ የተሸሸጉ ከዉስን ሰዎች ዉጪ የማያዉቁት ጉድለቶች አሉብን
ይህን ስልሽ በሀይማኖት ተቻችሎ መኖር የለም እያልኩሽ ሳይሆን አንዳንድ ጊዜ እና ቦታ ሚዛናዊ አይደለም እያልኩሽ ነዉ አላት ለዚ መፍትሄ ደግሞ የእናንተ ቁልፍ ሙስሊም ተማሪዎች መበርታንና መጠንከር ነዉ ብዙ ቢቀጥልና ብዙ ብታዳምጠዉ ምኞቱ ቢሆንም መለያያ ታክሲያቸዉ ጋር መድረሱን የረዳቶቹ ጩኸት አቋረጠዉ
በይ ሌላ ጊዜ እንጨዎወታለን እያላት ወደ ቀረበዉ ተረኛ ታክሲ እግሮቹን አከታተለ
ሩሂ ግራ ገባት ለምን ነገረኝ እንዴትስ እንዲ ግልፅ ሆኖ አወራኝ እያለች ስታስብ ቆይታ የመሄጃዎ ታክሲ በመድረሱ ሀሳቧን ለጊዜዉ ሰብስባ ወደ ቤቷ ለመሄድ ተጠባበቀች
አረፋፍዳ በመድረሷ እንደለመደችዉ የለመደቻትን ወክ ለመዉጣት አልታደለችም እዚ እዛ ስትል የመግሪብ ሰአት አብቅቶ ወደ ኢሻ መግቢያ ጥሪ ተሰማ
አለመሄዷ በማርፈዷ ምክንያት ቢሆንም የሩሂ እናት ወይዘሮ ከድጃን አንጀት ግን ሳይበላዉ አይቀርም
አይ ልጄን ባልኳት ነገር አስቀይምያት ነዉ እንጂ ስንት አመት ሙሉ ሰአቱን ጠብቃ የምትወጣዉ ወክ እንዴት ያስጠላታል እያለች የእናትነት አስተያየትን እየተመለከተች ሩሂን አየቻት
በአፏ አዉጥታ ይቅርታ ባጠይቅም በተግባሮቻ በትንሹም ቢሆን ለሩሂ አሳየቻት
ሩሂ ከእናቷ ጋር መታረቋ ቢያስደስታትም አሁንም ግን ከፍቷቷል ጎደኞቻ ጥለዎት መሄዳቸዉ ሳያንስ ይቅርታም ብለዉ አልጠየቋትም ጭንቅላቷ ላይ የተፈጠሩትን ጥያቄዎች ሳትመልስ ለማደር ተገደደች
ሁሌም ሲከፋት አልያም ስትደሰት ወደ አላህ መጣራት የለመደችዎ ነብስ ዛሬም በሰአቷ የለይልን ሰላት ለመስገድ ተንጠራራች.......


ሃዩ : ወይ ቅሌት!!አሁን ምን ይባላል እንደዛ ተጣድፈን ወተን ፕሮግራሙን ማዘዎወር.
ሲትራ : እኔ ግን የደበረኝ ሩሂን ዝም ማለታችን
ነባ : ባክሽ ተያት ብትኖር ምን ትጠቀም ነበር እንኳን አልመጣች
ሃዩ : ጋይስ ለሩሂ ግን እንዲህ ብለን መናገር የለብንም እሷን ትተን መሄዳችን ከዛ ደግሞ አለመሳካቱን ስታዉቅ ታሽሟጥጥብናለች ስለዚህ ነባ ወይ ሲትራ ታመዉ ተጣድፈን ወጣን እንላለን አይሻልም
ነባ : ዞሮ ዞሮኮ መስማቷ አይቀርማ
ሲትራ ቢሆንም እኛ እንደአዲስ እንዳልሰማን እንሆናለን ብላ ሀሳባቸዉ በከፈቱት የሶስትዮች የስልክ ጥሪ አገባደደች ........

ሩሂ በእምባ ታጥባለች
አላህዬ ብላ የጠራቻቸዉ ዱኣዎች መና የቀሩ መሰላት
ትናንት እማ እንደዛ ብላኝ ያሁሉ ነገር ነግሬኽ ልቤን ትጠግንልኛለህ ብዬ ስጠብቅ ዛሬ ደግሞ በብቸኝነት መንገድ ላይ አንሳፈፍከኝ አላህዬ የቱ ጋር ይሁን የሳትኩት የቱ ጋር ይሁን የጎደልኩት አላህዬ ተዉ ስማኝ እያለች በደከመችዎ ልብ ተማፀነች
አላወቀችም እንጂ በእናቷ ቁጣ የተገፈፈች ነፍሷን ነፍስ ለመዝራት ስትል የሰገደቻት ሰላት ከ እያንዳንዱ ጥሩ ብላ ካሰበቻቸዉ ዉጤታቸዉ ግን እሷን ጎጂ ከሆነ ነገር ጠብቋታል

አላህዬ ከማይጠቅመኝ ነገር ጋር አታወዳጀኝ ከሚቆጨኝ ጉዳይ ጋር አታገናኘኝ ያለቻት

ያቺ ቃሏ ከጎደኞቻ ተነጥላ ለመቅረቷ ምክንያት ሆነ

አላህዬ የወደፊቴን አላዉቅምና አሁን ላይ ከስር መሰረቱ እንድፀና አግዘኝ

ብላ የተማፀነችዉ ዱኣ አሁን ላይ ባይሆንም ወደፊት ለምትገነባት ሩሂ በአስተማሪዉ ሪድዎን በኩል መልእክትን አሰናድቶላታል
ያለ ምክንያት አልተገናኙም
በጎደኞቻ ምክንያት አረፋፍዳ ያልወጣችዉ ወክ ከእናቷ ጋር የነበራትን የቅሬታ ጭላንጭልን አስተካክሎላታል
የተሀጁድ ዉጤቷን በጥቃቅን ብላ በተወቻቸዉ ነገሮች ገርቶላታል.....

ይቀጥላል.....
🥰10❤‍🔥1
ፈገግታ ሱና ነው ፈገግ በሉ🙂


የግጥሜ ርዕስ አይዞህ ..!☺️😁

መኖርህ መጥፋትህ የሚያስጭንቃቸው
ማጣት መከፋትህ የሚያሳስባቸው
የሚጨነቅልህ ስላንተ የሚያስብ በዙሪያ ከጠፋ 
ማንም የለኝ ብለህ ከቶ እንዳትከፋ.
❝መኖርክን ፈላጊ ጠዋት ማታ አሳቢ እንዲኖር በተስፋ
በርከት ያለ ገንዘብ ተበድረህ ጥፋ❞🥲..!!

😂😂
😁14
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
ጨዋታ ላይ የማይጎረብጡ ምቹ ሰው ነበሩ!


አንድ እለት ከሰሃባዎቻቸው ጋር ተቀምጠው ተምር እየበሉ
ጨዋታ ይዘዋል…… ከፊታቸው የተቀመጠ አንድ ሰሃባ ሊቃልዳቸው ፈልጎ ተምሩን ይበላና የተምሩን ፍሬ እሳቸው በልተው ካስቀመጡት የተምር ፍሬ ጋር ሳያዩት ያስቀምጠዋል… አሁንም ይበላና ፍሬውን ከሳቸው ፊት ይጨምረዋል
.....
መጨረሻ ላይ "ያ ረሱለላህ፣ ዛሬ ያለ ወትሮዎ ብዙ ተመገቡኮ" አላቸው……
እሳቸውም ዝቅ ብለው ከፊታቸው ያሉትን የተምር ፍሬ ሲመለከቱት በዛባቸው(ተከምሯል)😳😁..
ሰሀብዩው ወደተቀመጠበት ቦታ ሲመለከቱ ምንም የተምር ፍሬ የለም…😉
ሁሉም ያለው ከሳቸው ፊት ነው……
ረሱልም(ሰ.ዐ.ወ) ነገሩ ፈገግ አሰኛቸውና እንዲህ አሉት…
❝የኔ ይህን ሁሉ ተምር መብላት ብቻ ሳይሆን ያንተ ከነ ፍሬው መዋጥህም ይገርማል❞🧠😁

የግድ ጁምዐ መሆን የለበትም
ዝም ብላቹ 🫳🏼      
                       صل الله عليه وسلم
                   (ﷺ🌹(ﷺ🌹(ﷺ)
🥰13
Someone said:

የተረጋጋሁት ነገሩ ቀሎ ሳይሆን ጉዳዩን ለ አላህ ሰጥቼው ነው 🥀

صباح الورد
🤗13
⚠️Deep message 🛑

ሴት ልጅ ወንድን ልጅ ለማማለል ሁለን ነገር አድርጋለች…
መራቆት ፣ አጭር ልብስ መልበስ ፣ ሜካፕ ፣ እምብርት መክፈት ፣ አርቲፊሻል ሰውነት ፣ ወደ ባእድ ወንዶች መቅረብ ወዘተ ግን ከዚያስ? ?

የወንዶች አይን ተጨማሪ ከመፈለግ አልተወገዱም ፣ ግራ ቀኝ ከመዟዟር አልባዘኑም ፣ cheating ከመጨመር  አልተቋረጠም ...

ከተቅዋ ውጪ ለወንድን ልጅ አይን የምትበቃ  ሴት በፍፁም አትገኝም ፣ ስለዚህ ንግስቲት ሆይ አሏህ የሚፈራ ወንድ ላይ አተኩሪ!

©
🥰14🤝1
🎴አንዴ ብቻ ይድላኝ ፣
አንዴ ብቻ ልረፍ፣
አንዴ ብቻ ልኑር ፣
አንዴ ብቻ ልትረፍ ፣
ፋታ ብቻ ላግኝ እንደምፈልገዉ፣
እንዴት እንደማለቅስ እኔ ነኝ የማቀዉ ።

..
💔10😢6
ምንም እንኳን ከሰዎች ፊት ጠንካራ ብትመስልም........ነገር ግን አሏህ ያዉቃል በሌሊት የምታለቅሰዉን የሚሰማህን ህመም ጭምር

..........እርሱ አይረሳህም
አንድ ቀን የዛሬ እንባህ ደስታ ይሆናል

ታገስ....
አሏህ ከአንተ ጋር ነዉ!

صباح الخير
🥰12
የአላህን ቤት [መስጅድን] በመጠበቅ የምታዘወትር አይን ምነኛ ታደለች።🥰
🥰17🔥1
ከተረዳሁት 7

" ...ታላላቅ ኃይላት ጸጥ ያሉ ናቸው ::

የመሬት ስበት ጮኾ ያውቃል !? ፀሐይ አጓርታ ታውቃለች !? ዛፍ በቁመት ሲያድግ ድምጽ አለው !? ኤሌትሪክ በኮረንቲ ውስጥ ሲያልፍ ይሰማል !? የቢሊዮኖች የሳምባ ትራፊ ካርበን ዳይኦክሳይድ ወደ እስትንፋስ ግብአታችን ሲቀየር የማሽኖች ኳኳታ ያሰማል !?

💰ዝምታ ግዝፈቱ አይታወቅም ። ዝምታ ትንሽ አይደለም ::  ቀና ብሎ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ የተዘረጋውን ጠፈር ላስተዋለ ሰው ዐይኑ የተመለከተውን ጠለል ጆሮው ግን አይሰማውም ዝምታ ትልቅ ብቻ አይደለም በጥቃቅን ረቂቅ መስተጋብሮችም ውስጥ የዝምታ ሚስጥር ተቀብሯል ።

💰ሚሊዮን እና ሚሊየኖች የሰውነታችን ህዋሳት እልፍ ቦታ ይካፈላሉ ይራባሉ ይላላካሉ ይዋጋሉ ይገድላሉ ይሞቱማል ። አያማርሩም አያቃስቱም አይነጫነጬም በዝምታ ይመላለሳሉ ::

በዝምታ ማስተንተን  የህይወትን ጣፋጭ መቅኔ እንደመምጠጥ ነው :: "
🥰7
« አዋጅ የአላህን እርዳታ ባልጠየቅንበት ጉዳይ ላይ ለሚገጥመን መጥፎ ነገር የማማረር መብት የለንም!

አዋጅ! የምንፈልገውን እንጂ የሚበጀንን ስጠን ባላልንበት ጉዳይ ላይ አላህን የማማረር መብት የለንም!

አዋጅ! የአላህን እዝነት አውቆ ያዝንልኛል ብሎ ሆነ ብሎ ማጥፋት የአላህን እዝነት ማነወር ነው!

አዋጅ! በስሜታችን ስክር ብለን ተንገዳግደን ከወደቅን በኋላ አላህ አላዘነልኝም ማለት በደል ነው። »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
🥰8👏2🔥1
ትንሽ ፈገግታ😊

የሆነ ሰው ወደ ኢማም አቡ ሀኒፍ መጣ አሉ......
ሰውየውም ልብሴን አውልቄ ወደ ወንዝ ገብቼ ስታጠብ ወደ ቂብላ ነው የምዞረው ወይስ ወደ ሌላ ሲል ጠየቀ.........?
ኢማሙም በላጩ ልብስህ ወዳለበት ብትዞር ነው የሚሻለው እንዳትሰረቅ....!
😁19
🫀
أَلَيْسَ اللَّهُ بِكَافٍ عَبْدَهُ ۖ

አላህ ባሪያውን በቂ አይደለምን?
🥰9🔥1
ረሱል📿 🥰🤌

📢ለዱኒያም ለዓኼራም ሓጃዎች ሰለዋት ማብዛት ጠቃሚ ነውና ነቢዩ ላይ ሰለዋት ማውረድ እናብዛ።

اللهم صل وسلَّم وبارك على نبينا محمد وعلى آلہ وصحبہ أجمعين.
🥰10
Someone said

አንድን ነገር ስጣቱት ግን
አንዳይቆጫችሁ ከናንተ ምንም
እንዳይቀር አድርጋችሁ
ያንን አድርጌው በነበር ብላችሁ
እንዳትቆጩ አድርጋችሁ እጡት
🙌
💯15🔥2
.
"ቁም ነገር የላችሁም"
እስክትባሉ ድረስ ከማንም ጋር
deeply አትቀራረቡ!❤️‍🩹
😁7🔥4💯1
.🍂
ትንሽ መናገር ጥበብ፣ ትንሽ መመገብ ጤና፣ ትንሽ መተኛት ጸሎት ሲሆን በብቸኘነት ውስጥም ሰላም አለ፡፡

ዑመር (ረዲየሏሁ ዓንሁ)
🔥5🥰3💯1
በእምባ እና ተሀጁድ መሀከል
ክፍል 5

ከባለቤቱ በላይ አዎቂ አይደለምና ነገራቶች በኛ ላይ ሀያል ሆነዉ ከማስተዎል አዘናጉን
ሩሂም ምንም እንኳን አስተዎይ ብትሆንም የተደራረበባትን የወርቅ እንቆቅልሽ ለመፍታት አዳግቷቷል

መንጋቱን ለማብሰር ወፎች ሲንጫጩ እና ፀሀይ በብርሃኗ አለምን ስታደምቅ
የሩሂ እናት ወይዘሮ ኸድጃ ሩሂን ለመቀስቀስ ከክፍሏ በር ላይ ተገኙ
ሩሂ አለሜ ተነሽ ክላስ ረፍዷል
እሺ እናቴ መጣዉ በቃ
ጎሽ ልጄ ቶሎበይ አባትሽ ይሸኝሻል ብለዎት እየተጣደፉ ወደ ኪችን ገቡ
ሩሂ የቤቱ የመጀመርያ ልጅ ብትሆንም እናትና አባቷ ልክ እንደመጨረሻ ልጃቸዉ በስስት ነዉ የሚያዩዎት ከሷ በታች 3 ሴቶችና 1 የመጨረሻ ታናሽ ወንድም ረያን አላቸዉ

የጠዎት ዝግጅቷን በጊዜ እንዳጠናቀቀች በአባቷ መኪና ለመሄድ ተሰናዳች
ብዙ ቁምነገሮችን እያወሩ ወደ ትምህርት ቤት ደጃፍ ደረሱ በወጉ ተሰነባብተዉ ተሸኛኙ
የግቢዉን በር ጋር አማር የነ ሲትራ የክፍል አለቃ ጋር ተገጣጠመች
አማር ረጅም ነዉ ደርባባ ሰዉነት መጠን ካለች ፂም ጋር ተሰቶታል ልክ እንደ ሩሂ ቀይ ነዉ ጨዎ አዎቂ እናም ዝምተኛ ቢሆንም ብዙ ጊዜ ሩሂ ጋር ሲሆን ባህሪዉን ለመቀየር ሲሞክር ፍንትዉ ብሎ ያንፀባርቅበታል
ዛሬም ሲያያት ወደ ሗላ አሸግሽጎ ጠበቃት
አማር ሩሂ አላት በዝግታ እያያት
አቤት እንደማለት ኮስተር ብላ ቀና ብላ አየችዉ
አማር:አሰላሙ አለይኩም
ሩሂ:ወአለይኩም አሰላም
አማር:ምነዉ ብቻሽን እነ ሲትራስ
ሩሂ:አይ ምንም ቀደም ብዬ መምጣት ፈልጌ ነዉ
አማር:ቲቶር አላችሁ እንዴ አላት ሀሳብ ለመፍጠር እየሞከረ
ሩሂ በአንገቷ አይ ብላ ነቅነቅ አድርጋ ጥላዉ ተራመደች ……………

ሀሚዶ ፈጠን በል ዛሬ እኮ እዛኛዉ ትምህርትቤት እንሄዳለን እያለ የሀሚድ ጎደኛ ቅዱስ ይነተርከዎል
ሀሚድም ጫማ ብቻ ነዉ ሚቀረኝ መኪናዉን አስነሳዉ በቃ አለ እየተጣደፈ
በሰአታቸዉ ለመድረስ መኪናዉን እያበረረ መንዳት ጀምረ
ሀሚድ በፍጥነት መንዳቱን ባይወደዉም አማራጭ ስላልነበረዉ በዝምታ ተባበረዉ

እነ ሃያት ክላስ ለመሄድ እየተቻኮሉ ነዉ
ሃዪ:ሲትራ ባንቺ ምክንያት ነዉ ሁሌም አያልፍልሽም
ሲትራ: እንቅልፍ እኮ እያስቸገረኝ ለምን አደዉሉልኝም
ነባ:ሩሂ ነበረች ሲጀምር የምሰበስበን
ሃዩ:በሉ በቃ ቶሎ ቶሎ እንሂድ እያለች ከነ ሲትራ ፈጠን ብላ አስፓልቱት ለመሻገር ተፈተለከች ነገር ግን ልክ እንደሷ ጉዳይ ኖሮባቸዉ እየፈጠኑ በመንዳት ላይ የነበሩት ሀሚድ እና ቅዱስ መኪና ጋር ተገጣጠሙ መኪናዉ
ሲጥጥጥ ሲል ነባ እና ሲትራ ሃዩ እያሉ ቀወጡት……………


ይቀጥላል
💔7