ሰኪነቱል ሩህ🖤
486 subscribers
41 photos
3 videos
1 link
መልካም የሆነ ማንፀባረቅን ከዉስጥ የሚዘልቅ ንፅፅርን እንዲሁም እርጋታን የሚሰጥ ፅሁፍን በአንድ ላይ ተሰናድቶ የሚቀርብበት channal🙌
Download Telegram
"አትርገሙት… እርሱኮ አላህና መልዕከተኛውን ያፈቅራል።" ረሱል
በየጊዜው መጠጥ እየጠጣ የሚገረፍ ሰሓባቸውን አስመልክቶ የተናገሩት ቃል ነበር… ታውቃለህ? ጊዜ ያዳልጣል ፣ ትናንትና ዛሬ አንድ ላትሆን ትችላለህ… ስሜትህ አሸንፎህ ኃጢያት ውስጥ ትዘፈቅ ይሆናል… ምናልባት ለመቁጠር የሚያዳግት ኃጢያት ውስጥ…  ግን የአላህና የመልዕክተኛው ፍቅር ከውስጥህ አይለይ… መውደድህን ቀጥል… አንድ እለት ፍቅር በተግባር ይገለጣል… ውዴታህ ስሜትህን ያሸንፋል…
❤‍🔥11
አንዳንድ ሰዎች ግን አጀብ ያሰኛሉ...

አላህ ወፍቆት የ ፈጅር (ሱብሂ) ሰላት በጀመዐ ከሰገደ..
ዛሬ ፈጅር ላይ የነበረውን ብርድ አይተኸዋል..🥶 እያለ ላገኘው ሰው ማውራት ይወዳል.🗣

ያ አህባብ..
ድብቅ ወንጀል እንጂ
ድብቅ ኸይር ስራ የሌለን ደካማ የ አላህ ባሮች ነን,
ኸይር ስራችንን አላህ ካወቀልን በቂ ነው።🙌🏼
🥰12🫡1
በየቀኑ በሰላምና ጤና ስለምንቀበላቸው ቀናት ሁሉ ምስጋና ለአላህ ይሁን፤ አልሐምዱሊላህ!!

صباح النور
❤‍🔥15🥰3👏1
" ኢብሊስ መቶ... አላህን ስንቴ እየለመንከው
ምንም እንዳልተቀበለህ አታይም? ካለህ..

እኔ በዱዐዬ ጌታዬን እየተገዛሁ ነው በለው! "

#ኡብኑል_ጀውዚይ [ ረሂመሁላህ ]
🥰17🤝3
.
አዛኝ ጌታ እንዳለኝ አስታወስኩ ግን....
አላህዬ ለካ የሚታመፅ ጌታ አልነበረም💔
💔10😢5
አላህ ሥስት መሀላን ምሎ የሰው ልጆችን ባማረ አቋም እንደፈጠረ ነግሮን ሳለ..!                
"لَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ فِي أَحْسَنِ تَقْوِيمٍ“
❝ሰውን በጣም በአማረ
አቋም ላይ ፈጠርነው፡፡❞

.
አንዳንድ ሴቶች ምንድነው ያምርብናል ብላቹ የማይሆን ነገር ተጠቅማቹ ላባዋ የረገፈ ዶሮ የምትመስሉት.😑

አላህ መሀሪ እንደሆነ ሁሉ
አሳማሚ ቅጣትም እንዳለው የዘነጋነው መሰለኝ።
አላህን እንፍራ🙌🏼
💯10
Someone said:

መውደቅ አይቀሬ ነውና የጉዟችሁ መነሻ ላይ ተደጋግፋችሁ መነሳት የምትችሉትን ሰው አስከትሉ።።

صباح الورد
👌8👏2🤝1
በእምባ እና ተሀጁድ መሀከል
ክፍል 3
የሩሂ ፈተና በእናቷ ግልምጫ እና ቁጣ አላበቃም
የ 12ኛ ክፍል ተማሪ ናት ማጥናት ማንበብ ልምዷ ነዉ ጎበዝ ናት ጉብዝናዎ የደረጃ ብቻ አልነበረም ስትናገር ምክንያታዊ ናት በዛዉ ልክ በቀላሉ በሰዎች ላይ እምነት ትጥላለች ………
በሰዎች የተከበበች ናት ብዛት ያላቸዉ ጎደኞች አሏት ስትወድ በልቅ ነዉ ስታቀርብ ወሰን የላትም ………

ዛሬ እንደተለመደዉ በጊዜ የትምህርት ቤቷ ግቢ ተገኝታ ለመግባት እየተራመደች ነዉ ብቻዎን አይደለችም ሃዩ ነባ ሲትራና መቅዲ ከጎን ጎናዎ ተደራርበዎል
ሃዩ: "ስሙ ዛሬ ከሰአት አስፈቅደን መዉጣት አለብን ለነገዉ ፕሮግራም ለመዘጋጀት "

ሩሂ :የቱ ፕሮግራም የህፃናቶቹን ምርቃት ነዉ ....

ሲትራ : "እና ሌላ አለ?
ምን አይነት ጥያቄ ነዉ "ስትል አፈጠጠች
መልስ ሳይሰጣጡ ወደየክፍላቸዉ ገቡ በጠዎቱ የዝናብ ካፍያ ስለነበር የሰልፍ ፕሮግራም አልነበረም
የምሳ ሰአቱ ተገባዶ የ6ተኛ ክፍለጊዜ መጀመርያ ላይ ሩሂ የጠዎቱ ንግግራቸዉ ትዝ አላት አስተማሪዉ ከመግባቱ ስትጣደፍ ወታ ከአጠገቧ ወዳለዉ የሲትራ ክፍል ዘዉ ብላ ገባች አስተማሪ አለመኖሩ ጠቀማት እንጂ በ displine ያስቀጣት ነበር
በአይኗ አማተረች ሲትራን ግን ልታያት አልቻለችም መንከራተቷ የገባዉ የክፍሉ ተጠሪ አማር ሩሂ ሲትራ ከሆነች አስፈቅዳ ሄዳለች ብሎ ድምፁን አንጠራርቶ ገላገላት
በሀሳቧ ብዙ ሀሳቦችን እያጉተመተመች ወደ ክፍሏ ተመለሰች
ማለቁ አይቀር ወደ ቤት መሄጃ ማብሰርያ ደወል ሲደወል ሁሉም ሲጣደፉ ሩሂ ግን እንደተለመደዉ ጎደኞቻን መጠበቅ ጀመረች የንፋስ ሽዉታ እንኳን የለም ግቢዉ ጭር ሊል በጣት የሚቆጠሩ ተማሪዎች ቀሩ ከክፍሉ ወታ ብዙ ብትንጎራደድም ሩሂ ነይ እንሂድ የሚሏት የጎደኞቻ ድምፅ የዉሃ ሽታ ሆነ ቀረ ……
ረስተዉኝ ነዉ ግን እንዴት እያለች ጭንቅላቷን በጥያቄ አጣደፈችዉ
መቀየር የማችለዉ ነገር ሆነና ብቻዎን ለመሄድ እቃዎቻን ሸካክፋ ተነሳች ከበሩ ሳትወጣ ሩሂ የሚል ድምፅ ከበስተሗላ ተሰማ
በመቅፅበት ዞራ የጠራትን ሰዉ ማንነት ለማወቅ አቆበቆበች……………
🥰10🍓2❤‍🔥1🔥1💯1
...አንድ ቀን አላህ በምትጠብቀው መልካም ነገር ያበስርሃል... እርሱ ዕጣ ፈንታን በቅጽበት ቀያያሪ የሆነ ጌታ ነው .... ምቾትንም መከራ ካደከመው ልብ ውስጥ ሊከስት ዘንድ ቻይ ነውና....በአላህ ላይ መልካምን እንጅ አትጠርጥር...
                                  
             
      [..وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ..]     
     «.. አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡...»

صباح النور ☕️
💔5🔥1
Someone said

🌱ለጉዳይህ ስትል ሶላትህን በጥድፊያ አትስገድ ምክንያቱም የቆምከው የቸኮልክበትን ጉዳይህን ጨምሮ
ዱኒያን ሁሉ የያዘው ጌታህ ፊት ነውና»
🔥12🥰5
በእምባና ተሀጁድ መሀከል
ክፍል 4

የግቢያቸዉ አለ ከሚሉት ጎበዝና ትጉ አስተማርያቸዉ ሪድዎን ነዉ ሩሂን ከመንገዷ ገታ ያደረጋት ......

ሪድዎን: " ምነዉ ሩሂ የደነገጥሽ ትመስያለሽ"
ሩሂ : አረ ምንም ሚስተር የምጠብቀዉ ሰዉ መስለኸኝ ነዉ
ሪድዎን: እንዴት እስካሁን አረፈድሽ ሰርቪስ ተጠቃሚም አይደለሽም አላት
ሰርቪስ ብዙ ጊዜ ቆይቶ ስለሚመጣ ያንን ለምክንያት እያቀረበ .....
መልስ አልሰጠችዉም እሱ ግን ቀጠለ
አጋጣሚዎችን ስጠብቅ ነበር ወደ አንቺ ቀርቦ ለማዉራት
እንደምታዉቂዉ ነዉ እዚ ግቢ ሙስሊም ተማሪ እንጂ ሙስሊም አስተማሪ እብዛም የለም ሙስሊም አስተማሪ በመሆኔ ከተማሪ ባልተናነሰ መልኩ በደሎችን ላስተናግድ እችላለዉ ብሎ ከማለቱ እንዴት የሚል አስተያየት ቀና ብላ አየችዉ
ምን መሰለሽ ሩሂ ብዙ ጊዜ የሰላት ሰኣቴ ይሸራረፋል አንዴ ስብሰባ አንዴ ቲቶር አንዴ ደግሞ ክላስ በሚል አላስፈላጊ ሀተታ ብቻ ሁሉም ነገር እንደገፅታዉ ቀላል አይደለም ብዙ የተሸሸጉ ከዉስን ሰዎች ዉጪ የማያዉቁት ጉድለቶች አሉብን
ይህን ስልሽ በሀይማኖት ተቻችሎ መኖር የለም እያልኩሽ ሳይሆን አንዳንድ ጊዜ እና ቦታ ሚዛናዊ አይደለም እያልኩሽ ነዉ አላት ለዚ መፍትሄ ደግሞ የእናንተ ቁልፍ ሙስሊም ተማሪዎች መበርታንና መጠንከር ነዉ ብዙ ቢቀጥልና ብዙ ብታዳምጠዉ ምኞቱ ቢሆንም መለያያ ታክሲያቸዉ ጋር መድረሱን የረዳቶቹ ጩኸት አቋረጠዉ
በይ ሌላ ጊዜ እንጨዎወታለን እያላት ወደ ቀረበዉ ተረኛ ታክሲ እግሮቹን አከታተለ
ሩሂ ግራ ገባት ለምን ነገረኝ እንዴትስ እንዲ ግልፅ ሆኖ አወራኝ እያለች ስታስብ ቆይታ የመሄጃዎ ታክሲ በመድረሱ ሀሳቧን ለጊዜዉ ሰብስባ ወደ ቤቷ ለመሄድ ተጠባበቀች
አረፋፍዳ በመድረሷ እንደለመደችዉ የለመደቻትን ወክ ለመዉጣት አልታደለችም እዚ እዛ ስትል የመግሪብ ሰአት አብቅቶ ወደ ኢሻ መግቢያ ጥሪ ተሰማ
አለመሄዷ በማርፈዷ ምክንያት ቢሆንም የሩሂ እናት ወይዘሮ ከድጃን አንጀት ግን ሳይበላዉ አይቀርም
አይ ልጄን ባልኳት ነገር አስቀይምያት ነዉ እንጂ ስንት አመት ሙሉ ሰአቱን ጠብቃ የምትወጣዉ ወክ እንዴት ያስጠላታል እያለች የእናትነት አስተያየትን እየተመለከተች ሩሂን አየቻት
በአፏ አዉጥታ ይቅርታ ባጠይቅም በተግባሮቻ በትንሹም ቢሆን ለሩሂ አሳየቻት
ሩሂ ከእናቷ ጋር መታረቋ ቢያስደስታትም አሁንም ግን ከፍቷቷል ጎደኞቻ ጥለዎት መሄዳቸዉ ሳያንስ ይቅርታም ብለዉ አልጠየቋትም ጭንቅላቷ ላይ የተፈጠሩትን ጥያቄዎች ሳትመልስ ለማደር ተገደደች
ሁሌም ሲከፋት አልያም ስትደሰት ወደ አላህ መጣራት የለመደችዎ ነብስ ዛሬም በሰአቷ የለይልን ሰላት ለመስገድ ተንጠራራች.......


ሃዩ : ወይ ቅሌት!!አሁን ምን ይባላል እንደዛ ተጣድፈን ወተን ፕሮግራሙን ማዘዎወር.
ሲትራ : እኔ ግን የደበረኝ ሩሂን ዝም ማለታችን
ነባ : ባክሽ ተያት ብትኖር ምን ትጠቀም ነበር እንኳን አልመጣች
ሃዩ : ጋይስ ለሩሂ ግን እንዲህ ብለን መናገር የለብንም እሷን ትተን መሄዳችን ከዛ ደግሞ አለመሳካቱን ስታዉቅ ታሽሟጥጥብናለች ስለዚህ ነባ ወይ ሲትራ ታመዉ ተጣድፈን ወጣን እንላለን አይሻልም
ነባ : ዞሮ ዞሮኮ መስማቷ አይቀርማ
ሲትራ ቢሆንም እኛ እንደአዲስ እንዳልሰማን እንሆናለን ብላ ሀሳባቸዉ በከፈቱት የሶስትዮች የስልክ ጥሪ አገባደደች ........

ሩሂ በእምባ ታጥባለች
አላህዬ ብላ የጠራቻቸዉ ዱኣዎች መና የቀሩ መሰላት
ትናንት እማ እንደዛ ብላኝ ያሁሉ ነገር ነግሬኽ ልቤን ትጠግንልኛለህ ብዬ ስጠብቅ ዛሬ ደግሞ በብቸኝነት መንገድ ላይ አንሳፈፍከኝ አላህዬ የቱ ጋር ይሁን የሳትኩት የቱ ጋር ይሁን የጎደልኩት አላህዬ ተዉ ስማኝ እያለች በደከመችዎ ልብ ተማፀነች
አላወቀችም እንጂ በእናቷ ቁጣ የተገፈፈች ነፍሷን ነፍስ ለመዝራት ስትል የሰገደቻት ሰላት ከ እያንዳንዱ ጥሩ ብላ ካሰበቻቸዉ ዉጤታቸዉ ግን እሷን ጎጂ ከሆነ ነገር ጠብቋታል

አላህዬ ከማይጠቅመኝ ነገር ጋር አታወዳጀኝ ከሚቆጨኝ ጉዳይ ጋር አታገናኘኝ ያለቻት

ያቺ ቃሏ ከጎደኞቻ ተነጥላ ለመቅረቷ ምክንያት ሆነ

አላህዬ የወደፊቴን አላዉቅምና አሁን ላይ ከስር መሰረቱ እንድፀና አግዘኝ

ብላ የተማፀነችዉ ዱኣ አሁን ላይ ባይሆንም ወደፊት ለምትገነባት ሩሂ በአስተማሪዉ ሪድዎን በኩል መልእክትን አሰናድቶላታል
ያለ ምክንያት አልተገናኙም
በጎደኞቻ ምክንያት አረፋፍዳ ያልወጣችዉ ወክ ከእናቷ ጋር የነበራትን የቅሬታ ጭላንጭልን አስተካክሎላታል
የተሀጁድ ዉጤቷን በጥቃቅን ብላ በተወቻቸዉ ነገሮች ገርቶላታል.....

ይቀጥላል.....
🥰10❤‍🔥1
ፈገግታ ሱና ነው ፈገግ በሉ🙂


የግጥሜ ርዕስ አይዞህ ..!☺️😁

መኖርህ መጥፋትህ የሚያስጭንቃቸው
ማጣት መከፋትህ የሚያሳስባቸው
የሚጨነቅልህ ስላንተ የሚያስብ በዙሪያ ከጠፋ 
ማንም የለኝ ብለህ ከቶ እንዳትከፋ.
❝መኖርክን ፈላጊ ጠዋት ማታ አሳቢ እንዲኖር በተስፋ
በርከት ያለ ገንዘብ ተበድረህ ጥፋ❞🥲..!!

😂😂
😁14
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
ጨዋታ ላይ የማይጎረብጡ ምቹ ሰው ነበሩ!


አንድ እለት ከሰሃባዎቻቸው ጋር ተቀምጠው ተምር እየበሉ
ጨዋታ ይዘዋል…… ከፊታቸው የተቀመጠ አንድ ሰሃባ ሊቃልዳቸው ፈልጎ ተምሩን ይበላና የተምሩን ፍሬ እሳቸው በልተው ካስቀመጡት የተምር ፍሬ ጋር ሳያዩት ያስቀምጠዋል… አሁንም ይበላና ፍሬውን ከሳቸው ፊት ይጨምረዋል
.....
መጨረሻ ላይ "ያ ረሱለላህ፣ ዛሬ ያለ ወትሮዎ ብዙ ተመገቡኮ" አላቸው……
እሳቸውም ዝቅ ብለው ከፊታቸው ያሉትን የተምር ፍሬ ሲመለከቱት በዛባቸው(ተከምሯል)😳😁..
ሰሀብዩው ወደተቀመጠበት ቦታ ሲመለከቱ ምንም የተምር ፍሬ የለም…😉
ሁሉም ያለው ከሳቸው ፊት ነው……
ረሱልም(ሰ.ዐ.ወ) ነገሩ ፈገግ አሰኛቸውና እንዲህ አሉት…
❝የኔ ይህን ሁሉ ተምር መብላት ብቻ ሳይሆን ያንተ ከነ ፍሬው መዋጥህም ይገርማል❞🧠😁

የግድ ጁምዐ መሆን የለበትም
ዝም ብላቹ 🫳🏼      
                       صل الله عليه وسلم
                   (ﷺ🌹(ﷺ🌹(ﷺ)
🥰13
Someone said:

የተረጋጋሁት ነገሩ ቀሎ ሳይሆን ጉዳዩን ለ አላህ ሰጥቼው ነው 🥀

صباح الورد
🤗13
⚠️Deep message 🛑

ሴት ልጅ ወንድን ልጅ ለማማለል ሁለን ነገር አድርጋለች…
መራቆት ፣ አጭር ልብስ መልበስ ፣ ሜካፕ ፣ እምብርት መክፈት ፣ አርቲፊሻል ሰውነት ፣ ወደ ባእድ ወንዶች መቅረብ ወዘተ ግን ከዚያስ? ?

የወንዶች አይን ተጨማሪ ከመፈለግ አልተወገዱም ፣ ግራ ቀኝ ከመዟዟር አልባዘኑም ፣ cheating ከመጨመር  አልተቋረጠም ...

ከተቅዋ ውጪ ለወንድን ልጅ አይን የምትበቃ  ሴት በፍፁም አትገኝም ፣ ስለዚህ ንግስቲት ሆይ አሏህ የሚፈራ ወንድ ላይ አተኩሪ!

©
🥰14🤝1
🎴አንዴ ብቻ ይድላኝ ፣
አንዴ ብቻ ልረፍ፣
አንዴ ብቻ ልኑር ፣
አንዴ ብቻ ልትረፍ ፣
ፋታ ብቻ ላግኝ እንደምፈልገዉ፣
እንዴት እንደማለቅስ እኔ ነኝ የማቀዉ ።

..
💔10😢6
ምንም እንኳን ከሰዎች ፊት ጠንካራ ብትመስልም........ነገር ግን አሏህ ያዉቃል በሌሊት የምታለቅሰዉን የሚሰማህን ህመም ጭምር

..........እርሱ አይረሳህም
አንድ ቀን የዛሬ እንባህ ደስታ ይሆናል

ታገስ....
አሏህ ከአንተ ጋር ነዉ!

صباح الخير
🥰12
የአላህን ቤት [መስጅድን] በመጠበቅ የምታዘወትር አይን ምነኛ ታደለች።🥰
🥰17🔥1
ከተረዳሁት 7

" ...ታላላቅ ኃይላት ጸጥ ያሉ ናቸው ::

የመሬት ስበት ጮኾ ያውቃል !? ፀሐይ አጓርታ ታውቃለች !? ዛፍ በቁመት ሲያድግ ድምጽ አለው !? ኤሌትሪክ በኮረንቲ ውስጥ ሲያልፍ ይሰማል !? የቢሊዮኖች የሳምባ ትራፊ ካርበን ዳይኦክሳይድ ወደ እስትንፋስ ግብአታችን ሲቀየር የማሽኖች ኳኳታ ያሰማል !?

💰ዝምታ ግዝፈቱ አይታወቅም ። ዝምታ ትንሽ አይደለም ::  ቀና ብሎ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ የተዘረጋውን ጠፈር ላስተዋለ ሰው ዐይኑ የተመለከተውን ጠለል ጆሮው ግን አይሰማውም ዝምታ ትልቅ ብቻ አይደለም በጥቃቅን ረቂቅ መስተጋብሮችም ውስጥ የዝምታ ሚስጥር ተቀብሯል ።

💰ሚሊዮን እና ሚሊየኖች የሰውነታችን ህዋሳት እልፍ ቦታ ይካፈላሉ ይራባሉ ይላላካሉ ይዋጋሉ ይገድላሉ ይሞቱማል ። አያማርሩም አያቃስቱም አይነጫነጬም በዝምታ ይመላለሳሉ ::

በዝምታ ማስተንተን  የህይወትን ጣፋጭ መቅኔ እንደመምጠጥ ነው :: "
🥰7